𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄 @asiya_tubee Channel on Telegram

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

@asiya_tubee


𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄 (English)

Welcome to the 𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄 Telegram channel, also known as @asiya_tubee! This channel is dedicated to all things related to Asian culture, entertainment, and lifestyle. Whether you are a fan of K-pop, anime, Bollywood, or traditional Asian cuisine, this channel has something for everyone. Discover the latest trends, news, and updates from various Asian countries right at your fingertips. Who is it for? If you are a lover of Asian culture and want to stay informed about the latest happenings in the Asian entertainment industry, then this channel is perfect for you. From music to movies to food, you will find a wide range of content that will cater to your interests. What is it about? The 𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄 channel is a one-stop destination for all things Asian. Stay updated on the latest music releases, movie trailers, celebrity gossip, and cultural events happening across Asia. Engage with like-minded individuals who share your passion for Asian culture and exchange recommendations for the best Asian restaurants, travel destinations, and more. Join the 𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄 channel today and immerse yourself in the vibrant and diverse world of Asian culture!

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

23 Nov, 15:02


የሬሳ ሳጥን መሸጥ
~
የሌሎች ሃይማኖቶች የእምነት መገለጫ ምልክቶችን መጠቀም፣ የመስቀል ጥልፍ ያለበት ባህላዊ ልብስ መልበስ፣ መሸጥ፣ መስቀል ያለባቸው የሬሳ ሳጥን መሸጥ አይፈቀድም። እናታችን ዓኢሻ – ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ – እንዲህ ትላለች: –
لم يكن رسول الله صلى الله وسلم يترك في بيته شيئا فيه تصاليب إلا نقضه
"የአላህ መልእክተኛ – ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለም – ቤታቸው ውስጥ መስቀሎች ኖረውበት ሳያበላሹት የሚተውት ነገር አልነበረም።" [ቡኻሪ]

እዚህ ላይ አንዳንድ በባህል ሽፋን ወደ እምነታቸው የሚጣሩ ብልጦች ይህንና መሰል ትምህርቶችን እንደ ማክረር ሊቆጥሩ ይችላሉ። አክራሪዎቹ ግን እነሱ ናቸው። በሌሎች እምነት ውስጥ ገብቶ ብይን ለመስጠት ማንጋጠጥ ፅንፈኝነት ብቻ ሳይሆን ብል -ግናም ጭምር ነው። እኛ "ኮፍያ ወይም ጂልባብ ልበሱ" አላልንም። "እንደኛ ካልለበሳችሁ አካራሪዎች ናችሁ" የምንል አጉል ደፋሮችም አይደለንም። ያወራነው ስለራሳችን እምነት ብይን ብቻ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል :-
t.me/IbnuMunewor

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

23 Nov, 14:42


አንዳንዶች ደግሞ አሉ...
ደስታቸዉ ብቻ የሚያስደስተን፥ ሀዘናቸዉ እኛንም ሚያስከፋን፥ ንግግራቸዉ ሚናፍቀን፥ ባሰብናቸዉ ቁጥር ቀልዳቸዉ ፈገግ ሚያስብለን.....

አላህ ባሉበት ይጠብቅልን።🌹🌺

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

16 Nov, 08:31


የሸይኽ ሙሐመድ ዑስማን ማራኪ ቲላዋ ነው፣ አድምጡት

https://t.me/Qurantilawas

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

13 Nov, 19:22


Urgent Notice
ሚሊኒየሯ እየተፈለገች ነው ዘምዘም መሀመድ አሊ   እባክሽ  የማታ ሲሳይሽን  ዱባይ  ፈርመሽ ውሰጅ እስከ ታህሳስ 20 ,2017 ድረስ ሸር አርጉት
ይችን በፎቶ የምታዮዋትን ልጅ እምታውቁ እባካችሁ ተባበሩ በተለይ ወሎየወች ፓሥፖርቷን ያወጣችው ደሤ ነው ተብሏል
ጉዳዩ ምንድን ነው ላላችሁ ህይወቷን የሚቀይር ገንዘብ ዱባይ ላይ እየጠበቃት ነው ነገሩ እንድህ ነው ዱባይ ቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ ትሠራ ነበር 2004 አካባቢ ይመሥለኛል ከዛ ሠወቹ አለመግባባት ተፈጥሮ ጉዳት ያደርሡባታል የኢትዮጵያ ቆንጽላ ጽ/ቤት ጉዳዩ  ይደርሣል ጽ/ ቤቱም ጠበቃ ቀጥሮ ይከራከራል በዝህ መሀል ልጅቱ አገር ቤት ገብታለች ከዛ አሰሪወቿ ከከፍተኛ የገንዘብ ቅጣት ጋ ሸንፈትን ተኮናነቡ ልጅቱ አድራሻዋ ጠፋ እሥከ ጥር ድረሥ እየተጠበቀች ነው በነገራችን ላይ ወላጆቿ ቤተሠቧቿ ካሉም የ DNA ምርመራ ተደርጎ ይሠጣቸዋል ተብሏል ሥሟ ዘምዘም መሀመድ አሊ ትባላለች እና እባካችሁ ይሄኔ ምን ላይ እንደሆነች አናውቅም::

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

10 Nov, 05:00


* የራስን ብሄር በተለየ ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ የሌሎችን ብሄር የሚያንቋሽሹ፣ ሰዎች በብሄራቸው ተለይተው ጥቃት ሲደርስባቸው ለአጥፊዎቹ የሚከላከሉ ፖስቶችን ወይም ኮሜንቶችን ሼር፣ ላይክ የምታደርጉ፣
* ዘር ላይ ያነጣጠሩ ዘረኛ ቀልዶችን በሳቅ የምታጅቡ፣
* በየትኛውም መልኩ ለዘር ተኮር ጥላቻ ድጋፍ የምታደርጉ አካላት የወንጀሉ ተካፋይ ናችሁ።
* የራሳችሁ ዘር ላይ ቢፈፀም የማትወዱትን ሌላው ላይ ሲሆን የምታደርጉት ከሆነ የዘረኝነት በሽታ ላይ ወድቃችኋል። "ተዋት! እሷ ጥንብ ነች!"
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

09 Nov, 13:45


#ሐሜትን_እንጠየፍ!

قال الحسن البصري: (من نمّ إليك، نمّ عليك)
"አንድ ሰው መጥቶ ስለሌሎች ሲነግርህ ስላንተም ለሌሎች እንደሚያወራ እርግጠኛ ሁን።"

ሐሰን አልበስሪይ(ረሂመሁላህ)

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

08 Nov, 04:56


إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
(ﷺ)🌸🌸🌸🌸🌸🌸

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

04 Nov, 20:51


➷"በተግባር  የታጀበ  እውቀት ፍሬ
            እንዳለው ዛፍ ነው!


ተግባርን ያላካተተ እውቀት ደግሞ ፍሬ
እንደሌለው ዛፍ ነው "  [ ሸይኽ ሷሊህ
አል
ፈውዛን (ሀፊዘሁሏህ) ]

{ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻋﻠﻤﻨﺎ ﻣﺎ ﻳﻨﻔﻌﻨﺎ ﻭﺍﻧﻔﻌﻨﺎ ﺑﻤﺎ
ﻋﻠﻤﺘﻨﺎ إﻧﻚ أﻧﺖ ﺍﻟﻌﻠﻴﻢ ﺍﻟﺤﻜﻴﻢ}
https://t.me/jenah9

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

02 Nov, 07:38


በእውቀት ፍለጋ ላይ 18 አመት አሳልፊያለሁ፣ ነገር ግን ልፋቴ የተፈለገውን ውጤት እንዳላስገኘ ይሰማኛል። ጦለበል ዒልምን ትቼ በዒባዳ ላይ ላሳልፍ ወይ?

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

31 Oct, 05:08


ሴኩላሪዝም ሙስሊሙን ለማፈን የሚጠቀሙበት፣ ለራሳቸው ግን የማይተገብሩት ትርክት!

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

30 Oct, 10:44


🫀🫀🫀

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

28 Oct, 09:31


ጥርት ያለ ተዉባ ማለት የሰራኸዉን ወንጀል
የወደድከዉን ያክል ስትጠላዉ እና ገና ስታስታዉሰዉ አስተغፊሩላህ የምትልበት ነዉ።
    
       ሀሰነል በስሪ رحمه الله

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

27 Oct, 11:32


{ إِلَّا مَن تَابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ عَمَلًا صَالِحًا فَأُولَـٰئِكَ يُبَدِّلُ اللَّهُ سَيِّئَاتِهِمْ حَسَنَاتٍ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا }

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

26 Oct, 15:59


ብዙ ሰው ትኩረት ነፍጎታል። በተቃራኒው በማይረባ ነገር ተጠምዷል። መረጃው ያለው ሰው ትንሽ ስለሆነ ይመስለኛል።

አመናችሁም አላመናችሁም ሰሞኑን በበርካታ ትምህርት ቤቶች ኒቃብ ተከልክሏል። የሚደርስላቸው ተቋምም ሆነ ድምፅ የሚሆናቸው ግለሰብ አጥተው በርካታ ኒቃቢስቶች ትምህርት ካቆሙ ሳምንት አልፏቸዋል።

ለማን ቢነገር ይሻላል? መጅሊስ ይህን ጉዳይ ከሚመለከተው አካል ጋር ተነጋግሮ በቋሚነት ለምን አይፈታም? ምን እየተካሄደ ነው? ዛሬስ በምን እናመካኝ?

እህቶቻችንን ስልታዊ በሆነ መልኩ ከትምህርት ገበታ ማገድ እስከ መቼ?

ትኩረት ለኒቃቢስት ተማሪዎች!

ኒቃቧንም ትለብሳለች፣ ትምህርቷንም ትማራለች።


(ይህን መልዕክት በማሰራጨት ቢያንስ ሰዎች ዘንድ እየሆነ ስላለው ነገር መረጃው እንዲኖር እናድርግ። በዱዓችንም እናግዛቸው።

||
t.me/MuradTadesse

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

25 Oct, 19:17


በጊዜ ተንፍስ
~
አንዳንድ ወንድሞች በሆነ የዒልም ዘርፍ ከእኩዮቻቸው ሲበልጡ ወይም የበለጡ ሲመስላቸው ትእቢት ሲፈትናቸው ይታያሉ። አንዱን መናቅ፣ ያኛውን ማጣጣል፣ ሌሎችን በመገምገም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ይጠመዳሉ።
የሸሪዐ እውቀት አላህን መፍሪያ መሳሪያ መሆኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም። ማወቅህ ትእቢት ካወረሰህ፣ በማወቅህ ለሌሎች ንቀትን ካዳበርክ ወላሂ ማወቅህ ጎድቶሃል። ጅህልና ላንተ የተሻለ ነበር። ሰው ቴኳንዶ ሰልጥኖ ቀድሞ ያልነበረውን አደብ ሲላበስ በምናይበት ጊዜ የሆነን ዒልም ሲማር እብሪትና ንቀትን የሚያዳብር ማየት አሳፋሪ ነው።
ወንድሜ ሆይ! መከበር ከፈለግክ ሰዎችን አክብር። ሌሎችን መናቅ ምናልባት ጥቂት ጊዜ ቢያስከብር ነው። ወይ ሰዎች እስከሚነቁ፣ ወይ ደግሞ ማንነትህ እስከሚገለጥ ድረስ ቢዘልቅ ነው። ከዚያስ? ከዚያማ መናቅህ መንናቅን ነው የሚያስከትልብህ። መተንፈስህ ላይቀር አፀፋ ሳያስተነፍስህ በፊት አላህን ፈርተህ ተንፍስ። በጊዜ ተንፍስ። አዎ መተንፈስ ይሻልሃል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

𝐀𝐒𝐈𝐘𝐀 𝐓𝐔𝐁𝐄

25 Oct, 14:53


🔰 ሑረሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) 🔰

አላሁ ሱበሀነሁ ወተዓላ ቁርአኑን ግልፅ በሆነ አረብኛ ቋንቋ አውርዶታል።
وَإِنَّهُ لَتَنْزِيلُ رَبِّ الْعَالَمِينَ (192) نَزَلَ بِهِ الرُّوحُ الْأَمِينُ (193) عَلَى قَلْبِكَ لِتَكُونَ مِنَ الْمُنْذِرِينَ (194)بِلِسَانٍ عَرَبِيٍّ مُّبِينٍ(195)

{እርሱም በእርግጥ #ከአለማት_ጌታ_የተወረደ ነው። ታማኙ መንፈስ(ጅብሪል) አወረደው። ከአስፈራሪዎቹ (ነቢያት) ትሆን ዘንድ በልብህ ላይ (አወረድነው)፡፡ ግልጽ በኾነ ዐረብኛ ቋንቋ አወረደው፡
📚[አሹዐራእ፡26:192-195] 
➩ ቁርአን ንግግሩም ሀሳቡም(መልእክቱም) ከአላህ ዘንድ የሆነ የአላህ ቃል ነው።
➩ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ የቁርአን አንቀፆች የተብራሩ ሆነው አወረዳቸው።
كتابٌ فُصِّلَتْ آيَاتُهُ قُرْآنًا عَرَبِيًّا لِّقَوْمٍ يَعْلَمُونَ
አንቀጾቹ የተብራሩ የኾነ መጽሐፍ ነው፡፡ ዐረብኛ ቁርኣን ሲኾን ለሚያውቁ ሕዝቦች (የተብራራ) ነው፡፡
📚 ፉሲለት 41÷3

➣ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች የቁርአን አንቀፆች ግልፅ ከሆኑ "ሑሩፉል ሙቀጠዓዎችን" እየጠቀሱ ተርጉሙልን ምንድን ነው መልእክቱ??እያሉ ይጠይቃሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ሑሩፎቹን በመጥቀስ መልእክት የሌላቸው በማስመሰል በሀርፎቹ ሲያፌዙ እና ሲያላግጡ ይታያሉ።
በአላህ አንቀፆየሚያላግጡና የሚያፌዙትን መራቅ አለብን

وَقَدْ نَزَّلَ عَلَيْكُمْ فِي الْكِتَابِ أَنْ إِذَا سَمِعْتُمْ آيَاتِ اللَّهِ يُكْفَرُ بِهَا وَيُسْتَهْزَأُ بِهَا فَلَا تَقْعُدُوا مَعَهُمْ حَتَّىٰ يَخُوضُوا فِي حَدِيثٍ غَيْرِهِ ۚ إِنَّكُمْ إِذًا مِّثْلُهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ جَامِعُ الْمُنَافِقِينَ وَالْكَافِرِينَ فِي جَهَنَّمَ جَمِيعًا
(ሱረቱ አል-ኒሳእ - 140)
በእናንተም ላይ በመጽሐፉ ውስጥ የአላህን አንቀጾች በርሷ ሲካድባትና በርሷም #ሲላገጥባት #በሰማችሁ #ጊዜ በሌላ ወሬ ውስጥ እስከሚገቡ ድረስ #ከእነሱ #ጋር #አትቀመጡ፡፡ ማለትን በእርግጥ አወረደ፡፡ እናንተ ያንጊዜ ብጤያቸው ናችሁና፡፡ አላህ መናፍቃንን እና ከሓዲዎችን በሙሉ በገሀነም ውስጥ ሰብሳቢ ነውና፡፡

ለጠያቂዎቹ የምንመልሰው መልስ👇
➣➣ በመጀመሪያ ሁሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) የሚባሉት የቁርአን 29 ምዕራፎች የተጀመሩባቸው የአረብኛ ፊደላት ሲሆኑ። ለምሳሌ الم(አሊፍ ላም ሚም)፣ حم (ሐ ሚም)፣ ص(ሷድ) ፣كهيعص(ካፍ ሀ ያ ዐይን ሷድ) ወዘተ ናቸው።
➣ ኡለሞች በእነዚህ ፊደላት ላይ ያላቸው አቋም የተለያየ ሲሆን
አንዳንድ ኡለሞች ትርጉማቸው አላህ ብቻ ነው ሚያውቃቸው(አላሁ አዕለም ቢሙራዲህ) ያሉ ሲሆኑ
➩ ሌሎቹ ደግሞ ትርጉም አላቸው ብለዋል።  ትርጉም አላቸው ያሉ ኡለሞች ደግሞ
አንዳንዶቹ የአላህ ስሞችን ለማመላከት የገቡ ፊደላት ናቸው ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ የቁርአን ስሞች ናቸው ሌሎቹ ደግሞ የምዕራፎቹ ስያሜ ነው እያሉ የተለያዩ ትርጓሜ ቢሰጡትም ትክክለኛው የኡለሞች አቋም ፊደላቱ ልክ እንደ ሌሎቹ የአረብኛ ፊደላት ትርጓሜ የላቸውም።
ለምሳሌ አንድ ሰው መጥቶ أ (አሊፍ) ب (ባ) ወዘተ ቢል ትርጉም የለውም። ብቻቸው ትርጉም የላቸውም
ልክንደዚሁ ሁሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) ብቻቸው ትርጉም የላቸውም። ትርጉም የላቸውም ስንል ግን ምንም መልእክት ምንም ጥበብ የላቸውም ማለት አይደለም።
ምክንያቱም አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ቁርአን ውስጥ ምንም መልእክትና ምንም ሂክማ ጥበብ የሌለው ነገር አላወረደም።
የሁሩፉል ሙቀጠዓህ(የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት) የሚያስተላልፉት መልእክትና ሂክማቸው(ጥበባቸው) ምንድን ነው ከተባለ👇👇👇
" ጥበቡ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ እነዚህ የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላቶችን ከየምዕራፎቹ መጀመሪያ ማድረጉ የቁርአንን ሙዕጂዛ(ተአምራዊነትን) ያመላክታል። ምክንያቱም ቁርአን የተገነባው አረቦች በንግግሮቻቸው በሚጠቀሟቸው ከነዚህ ا ل م ح ي ከመሳሰሉት ሀርፎች የተዋቀረ ነው። ይህ ከመሆኑ ጋር እሱን የመሰለ ግን ማምጣት እንደማይችሉ ለማመላከት ነው" ብለዋል።
ለዚህ ማሳያ ደግሞ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ እነዚህ የተቆራረጡ የቁርአን ፊደላት የተጀመሩባቸውን ምዕራፎች ሁሉ ብንመለከት ከፊደላቶቹ በኃላ ስለ ቁርአን መጥቀሱና ቁርአን ከአላህ ዘንድ መሆኑንና መናገሩ ራሱ ፊደላቶቹ የቁርአን ሙዕጂዛን ቁርአን ከነዚህ ፊደላት የተዋቀረ ከመሆኑ ጋር ፍጡራን እሱን የመሰለ ማምጣት እንደማይችሉ ለማመላከት የገባ ነው።
ለምሳሌ:-
الۤمۤ  ذَٰلِكَ الْكِتَابُ لَا رَيْبَ ۛ فِيهِ ۛ هُدًى لِّلْمُتَّقِينَ

አሊፍ ላም ሯ ይህ መጽሐፍ (ከአላህ ለመኾኑ) ጥርጥር የለበትም፤ ለፈራህያን መሪ ነው፡፡
📗ቁርአን ሱራ በቀራህ 2:1-2❵

يس* وَالْقُرْآنِ الْحَكِيمِ
ያ ሲን ጥበብ በተመላበት ቁርኣን እምላለሁ፡፡
(📗ሱረቱ ያሲን 1- 2)

حم ﴿١﴾ تَنزِيلٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ الرَّحِيمِ ﴿٢〗
ሐ.መ.(ሓ ሚም)። (ይህ ቁርኣን) እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ ከሆነው (አላህ) የተወረደ ነው።
📗❴ሱራ ፉሲለት 1-2

{ق وَالقُرآنِ المَجيدِ}
ቀ (ቃፍ) በተከበረው ቁርኣን እምላለሁ (በሙሐመድ አላመኑም)፡፡
📗ሱራ ቃፍ 1

☝️ በሁሩፉል ሙቀጠዓህ የሚጀምሩ እነዚህና ሌሎች ምዕራፎች ላይ ከሁሩፎቹ በኃላ ስለ ቁርርአን መጥቀሱና ቁርአን ከአላህ ዘንድ መሆኑንና መናገሩ ራሱ ፊደላቶቹ የቁርአን ሙዕጂዛን እና ቁርአን ከነዚህ ፊደላት የተዋቀረ ከመሆኑ ጋር ፍጡራን በተለይ በንግግራቸው አንደበተ ርቱዕ የነበሩ አረቦች እሱን የመሰለ ማምጣት እንደማይችሉ እና አለመቻላቸው ለማመላከት የገባ ነው።
☝️ ይህንን አቋም የመረጡት ሼይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ከተማሪዎቻቸው ኢብኑል ቀይምና አዝዘሀቢይ እንዲሁም የብዙ ኡለሞች አቋም ነው።
📖 ተፍሲር ኢብኑ ከሲር ተፍሲር ኢብኑ ዑሰይሚን፣ተፍሲሩል ሙየሰር ለሱረቱል በቀራ 2:1 የሰጡት ተፍሲር ይመልከቱ
አላህ እንዲህ ይላል
"قُلْ لَئِنِ اجْتَمَعَتِ الْإِنْسُ وَالْجِنُّ عَلَى أَنْ يَأْتُوا بِمِثْلِ هَذَا الْقُرْآنِ لَا يَأْتُونَ بِمِثْلِهِ وَلَوْ كَانَ بَعْضُهُمْ لِبَعْضٍ ظَهِيرًا " سورة الإسراء 88
“ሰዎችም ጋኔኖችም የዚህን ቁርአን ቢጤ በማምጣት ላይ ቢሰበሰቡ ከፊላቸው ለከፊሉ ረዳት ቢሆንም እንኳ ብጤውን አያመጡም በላቸው፡፡” ❴📗ሱረቱል ኢስራዕ 88❵


حسين خضر
https://t.me/iwnetlehullu1

1,077

subscribers

214

photos

94

videos