ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1 @halal_tbeb_1 Channel on Telegram

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

@halal_tbeb_1


ቻናሉን እንደምትወዱት 100% እርግጠኛ ነኝ ብቻ ተቀላቀሉን.....

✨ ጥበብ የሙስሊሞች ናት✨

Comment @husni50

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1 (Amharic)

እንደምትወዱት ቻናሉን 100% እርግጠኛ ነኝ ብቻ ተቀላቀሉን! ይህ ጥበብ ለሙስሊሞች የታለላችሁበት እና በእንግሊዘኛ በሆቴላችሁ ሆን ነው። እባኮት በትክክል @husni50 ወደኛ ምንጮች መምራት እንችላለን። ያልተለያዩ ጥበብን የሚመለከታችሁ ይህን ቦታ ግንባር ከተማ መፈክር የሚረዳባቸውን የሚባሉ እና ለግንባታ ለብዙ ስሞች እየተገናኘ ነው። የቻናሉን ስለሆነ፣ ለአሰፋ በሚፈነው ቀበሌ ጥበብ ስማኝ በመሆን አዝናኝን ጥበብ አልላልንም።

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

22 Oct, 11:17


አሰላሙ አለይኩም ያጀምዐ ሰሞኑን በአንዳንድ የመንግስት ትምህርት ቤቶች በኒቃብ ጉዳይ መነጋገሪያ ሆኗል ይህም ሙስሊም ሴት እህቶቻችን ኒቃብ ማዉለቅ አልያም ትምህርቱን ማቋረጥ እየተገደዱ ያሉበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል ስለዚህ እኛም ከጎናቸዉ እንደሆንን ለማሳየት በዱዐ እንዲሁም ከላይ☝️ የምትመለከቱትን ምስል ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ሼር በማድረግ ሶሻል ሚዲያ ላይ ተፅእኖ እንፍጠር ከእህቶቻችን ጎን ቁመን ኢስላማዊ ግዴታችንን እንወጣ
       

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

22 Oct, 04:44


አሰላሙአሊኩም ከቻልክ ትንሽ ጥያቄ እና እንደምትችል አውቃለሁ።  እኛ ለጋዛ ዘመቻ ልንሰራ ስለፈለግን ይህንን አረፍተ ነገር እንድትልክልኝ እፈልጋለው (ክብር ለአላህ ይገባው እና አላህ ሆይ ጋዛን እና ህዝቦቿን ጠብቅ አላህ ሆይ በጋዛ እና በህዝቦቿ ላይ ሰላም እና ሰላም ይሁን)  እኔ ከነሱ አንዱ ብሆንም እስከ 20 ጓደኞች።  ይህ አደራ እና የአላህ ጣልቃ ገብነት ጥያቄ ነው።
            
የሚቀጥሉት 72 ሰዓቶች ለፍልስጤም በተለይም ለጋዛ በጣም ወሳኝ ናቸው።
እስራኤል ጋዛን እና ሃማስን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት 100,000 ወታደሮችን ከተጨማሪ 200,000 ተጨማሪ ወታደሮች ጋር አሰባስባለች።
መላው ኡማ ከዱዓ በታች እንዲያነብ ይጠየቃል።  በሚቀጥሉት 72 ሰአታት ውስጥ እያንዳንዱን ዱዓ 10 ሚሊዮን ጊዜ በጋራ ለማንበብ ኢላማ እናደርጋለን።

حَسْبُنَا اللَّهُ وَ نِعْمَ الْوَ كِيلُ

اَللّٰهُمَّ إنَّا نَجْعَلُكَ فِي نُحُوْرِهِمْ وَنَعُوذُ بِكَ مِنْ شُرُورِهِمْ

እባኮትን ይህን መልእክት ለሁሉም አድርሱ እና 10 ሚሊዮን ኢላማ ላይ ለመድረስ የበኩላችሁን ተወጡ።  ጠላት እቅድ አለው አላህ ግን ከሁሉ የተሻለ እቅድ አውጪ ነው።

ጀዛከላህ!

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

21 Oct, 18:14


ሶላት የተዛባ የሕይወት
ሚዛናችንን ማስተካከያ ናት።
የሞቀው ብርድ ልብስህን ግፈፍና
የፈጅርን ሶላት ስገድ"

صلاة_الفجر
سلام على من اتبع الهدى🫀🫳

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

21 Oct, 16:41


👑ሁለተኛው ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ👑

🍁🍁
🍁ክፍል 3🍁
🍁🍁


ዑመር ስለጉዳዩ ከጠየቁ በኋላ በቅድሚያ የእህታቸውን ባል ሰፈሩበት
አይጣል !በጥፊ፣በርግጫ ፣በጡጫ...
እህታቸው ፋጢማ ጣልቃ ለመግባት ስትሞክር ክፉኛ ስለመቷት ፊቷ ደማ።
ሲቃና ሳግ በተናነቀው ድምፅ "የፈለአውን አድርግ፣እኛ በኢስላም ላይ እንዳለን ለመሞት ቆርጠናል።"ስትል ጮኸችባቸው
ደሟ እንዲያ ሲወርድ ሲያዩት በሀፍረት ስሜት ትንሽ ቀዝቀዝ አሉ።
ከዚያም ቁርአኑን እንድታሳያቸው ሲጠይቋት"ታጥበህ ራስህን ካላፀዳህ ልትነካው አትችልም "ስትል መለሰች።
(የማን እህት ሆነችና😒!!!)



ዑመር ተጣጥበው መጡና ቁርአኑን ያነብቡት ጀመር ።የሱረቱል ጧሀ የመጀመሪያው አካባቢ ነበር ።



"እኔ አላህ ነኝ ያለ እኔ አምላክ የለምና ተገዛኝ፤ሶላትንም(በርሷ)እኔን ለማስታወስ ስገድ።"(20፥14)



የሚለው አንቀጽ ላይ ሲደርሱእጅግ ልባቸውን ስለነካው "በእርግጥም ይህ የአላህ ቃል ነው ።ወደ ሙሀመድ ውሰዱኝ" አሉ በአድናቆት ።


የዚህ ጊዜ ነበር ባልናሚስቱን ቁርአን ሲያስጠናቸው የነበረው ኸባብ የተባለው ሶሀባ ከተደበቀበት የወጣው 🤭


ከዚያም "ዑመር እንኳን ደስ ያለህ !🥳
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባለፈው ምሽት ያደረጉት ዱዐ ላንተ ሳይደርስ አልቀረም

'አላህ ሆይ !በዑመር ኢብኑል ኸጧብ ወይም በዑመር ኢብኑ ሂሻም፣እንዲሁ አንተን ደስ ባለህኢስላምን አጠናክረው ።'

በማለት ዱዐ አድርገው ነበር ።ሲል ያበሰራቸው።

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

20 Oct, 11:09


“በቤተሰቡ መሀል በሠላም ያደረ ሰውነቱ በሙሉ ጤነኛ ሆኖ ያነጋ፤ የዕለት ጉርሱን ያገኘ ዱንያን በሙሉ ሰብሰቧታል።”
نبينا الكريم عليه أفضل الصلاة وأزكى التسليم ﷺ

سلام على من اتبع الهدى 🫀🫳

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

20 Oct, 08:31


👑ሁለተኛው ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየሏሁ ዐንሁ👑

🍁🍁
🍁ክፍል 2🍁
🍁🍁


ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) ለመግደል ዑመር ተመረጠ።
ዑመር ሰይፋቸውን መዝዘው ወደ ነብዩ ሰዐወ ሲነጉዱ መንገድ ላይ ያገኟቸው ሰዕድ ኢብን አቢ ወቃስ ወዴት እየሄዱ እንደሆነ ይጠይቋቸዋል ።ሰዕድ የዑመርን ምላሽ ከሰሙ በኋላ "መጀመሪያ የራስህን ቤት ብትጠብቅ ጥሩ ነው ።እህትህ ከነባሏ ኢስላምን ተቀብላለች ።"ሲሉ አረዷቸው(መርዶ ከተባለ )።




ዑመርም ይበልጥ ጦፈውና ግመው ወደ እህታቸው ቤት ገሰገሱ ።የቤቱን በር በጡጫ ሲነርቱት ባልና ሚስቱ ኸባብ ከተባለ ሶሀባ ጋር በመሆን ቁርአን እያጠኑ ነበር ።እህታቸው ፋጢማ የሰውየውን ማንነት ገና በድምፁ ስለሐየችው የምትይዘው የምትጨብጠው ጠፋት፤በእጇ የነበረውንም ቁርአን ለመደበቅ ሞከረች ።

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

20 Oct, 02:20


.
እናት ልጆቿን ለሱብሂ ሰላት ስትቀሰቅስ ዘወትር እንዲህ ትላቸዋለች...

"ከተኛችሁበት ንቁ ለሱብሂ ሰላት ቁሙ ከእኛ መካከል አንድም ሰው ጀነት ውስጥ እንዲጎድል አንፈልግምና

🥀🥀🌹🌹🥀እናት💐💐

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

19 Oct, 14:48


🤍አህባቢ ስሙኝማ😊

አሁን ላይ ጭንቀት ውስጥ ከሆናችሁ የማይፈታ የሚመስል ችግር ውስጥ
ከገባችሁ..🥀.
አብሽሩ እሽ 💛
በኣላህ ፍቃድ ነገሮች ሁሉ የተሻለ ይሆናሉ። ይሄ 👇👇
የአላህ ቃል ኪዳን ነው😍😍

@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

18 Oct, 05:18


اللهم صل وسلم على نبينا محمد🌻
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🍁
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🍀
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🌼
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم علىنبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🌸
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🌺
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🌹
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد💐
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد
اللهم صل وسلم على نبينا محمد🌷

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

17 Oct, 15:55


️ أحبتي في الله
... የኔ ዱዓ ለናንተ
አይኖቻቹህ እንዳያዝኑ፣ ፈገግታቹህ እንዳይጠፋ፣ እና አላህ ህይወታችሁን በደስታና በአፊያ  እንዲያኖራችሁ ነው....ከሞትም በኀላ ሰፊዋን ጀነት እንዲወፍቃቹ 😊

سلام على من اتبع الهدى 🫀🫳

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

17 Oct, 10:48


👑ሁለተኛው ኸሊፋ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረዲየላሁ ዐንሁ👑

🍁🍁
🍁 ክፍል 1🍁
🍁🍁



"ከእኔ በኋላ ነብይ የሚመጣ ቢሆን ኖሮ ዑመር በሆነ ነበር "
(ነብዩ ሰ.ዐ.ወ)




_ ዑመር ከልደት እስከ ኢስላም _

"ዓዲይ"ከተሰኘው የነገደ ቁረይሽ ቅርንጫፍ የሚወለዱት ዑመር ኢብኑል ኸጧብ በስምንተኛው አያታቸው ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የዘር ግንድ ጋር ይገናኛሉ ።
ዑመር አቡ ሀፍስ በመባል ሲታወቁ አል ፋሩቅ የሚል የማዕረግ ስምም ነበራቸው ።
የተወለዱት ከታላቁ ሂጅራ 40 አመታት ቀደም ብሎ በ583 (እ.አ.አ)ሲሆን የህፃንነት ዘመናቸው ታሪክ ብዙም አይታወቅም ።



በወጣትነት ዘመናቸው የወጣላቸው ተደባዳቢና ጉልበተኛ ነበሩ ።ከፍተኛ የሆነ የንግግር ችሎታም ነበራቸው ።ኢስላም ከመምጣቱ በፊት ማንበብና መፃፍ ይችሉ ከነበሩት ጥቂት መካዊያን መካከል ዑመር አንዱ ነበሩ ።እንደ አብዛኛው የመካ ነዋሪ የዑመርም ዋና መተዳደሪያ ንግድ ነበር ።



ኢስላም ተልዕኮውን በጀመረ በ ስድስተኛው አመት ላይ ቁረይሾች ጉባኤ ጠርተው ነብዩ ሙሀመድን (ሰ.ዐ.ወ) የሚገድል ሰው ሲያፈላልጉ ፣ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ፈቃደኝነታቸውን ገለፁ ።
ተሰብሳቢዎቹም በሙሉ ግድያውን ለመፈጸም ብቃት ያለው ትክክለኛው ሰው እሱ ነው ሲሉ በአንድ ድምፅ ተስማሙ።

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

16 Oct, 11:05


.
ባል ወደ ቤት ሲገባ ሚስቱ የአልጋውን ጫፍ ተደግፋ ተንሰቅስቃ እያነባች አገኛት። ደነገጠ ስታለቅስ ሲያያት ሆዱ ተላወሰ። ያፈቅራት ነበርና ሐዘኗ አሳዘነው። አቅፎ ደግፎ ግንባሯን እየሳመ ለምን እንደምታለቅስ ጠየቀ።
"ከቤታችን ፊት ለፊት የሚገኘው ዛፍ ላይ ያሉት ወፎች ዘወትር ልብሴን ስቀይር ፀጉሬን ያዩብኛል። ይህም አላህን ማመፅ እንዳይሆንብኝ ብዬ እፈራለሁ ለዚህ ነው የማለቅሰው" ብላ መለሰችለት።

   ባል በንጽሕናዋና አላህን በመፍራቷ ተደንቆ በዓይኖቿ መካከል ሳማትና መጥረቢያውን አውጥቶ ከቤታቸው ደጃፍ ላይ የበቀለውን ዛፍ ቆረጠ።

ከሳምንቱ መጨረሻ በአንደኛው ቀን ስራ አድክሞት ያለ ወትሮው ወደቤቱ አቀና። ሌላ ጊዜ ከሚገባበት ሰዓት ቀደም ብሎ ወደ ቤት ተመለሰ። በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ሲዘልቅ ሚስቱ በሌላ ወንድ እቅፍ ውስጥ ተኝታ አገኛት። አልጋው ላይ እሱ የገዛውን አንሶላ ከሌላ ወንድ ጋር ለብሳ ተመለከታት።

የሚያስፈልገውን እቃ ሻንጣው ውስጥ ሸክፎ ምንም ሳይናገር የትውልድ ቀየውን ለቆ ወጣ።

   ራቅ ወዳለ ሥፍራ ተጓዘ። መንገድ በማቋረጥ ላይ ሳለ ከአንድ ቤተ መንግስት አቅራቢያ ሰዎች ተሰብስበው ተመለከተ። ለምን እንደተሰበሰቡ ሲጠይቃቸው የንጉሱ ግምጃ ቤት ተዘርፎ ሌባው አለመገኘቱን ነገሩት።

በዚህ መሐል በእግሮቹ ጣት ጫፍ በቀስታ የሚራመድ ሰው ተመለከተ። ስለማንነቱም ጠየቀ "የከተማው ሸይኽ ነው ጉንዳን ረግጦ አላህ ዘንድ እንዳይጠየቅ በዝግታ ይጓዛል ከአላህ ፍራቻ ብዛት የጉንዳኖችን ህይወት ላለመቅጠፍ በመስጋት በቀስታ ይራመዳል" ብለው መለሱለት።

ወደ ንጉሡ ውሰዱኝ አለ። ወሰዱት። ለንጉሱም የአንተን ግምጃ ቤት የዘረፈው በጣቶቹ የሚራመደው ሸይኽ ነው። እሱ ሆኖ ካልተገኘ ፍርዴ ሞት ይሁን አለ። ንጉሱ ተገረመ በተቅዋው የሚታወቀው ሸይኽ እንዴት ሊዘርፈኝ ይችላል ሲል ራሱን ጠየቀ።

ወታደሮቹ ሸይኹን አምጥተው ከንጉሱ ፊት አቀረቡት። ምርመራው ተጀመረ ሸይኹ መስረቁን አምኖ ተቀበለ። መዝረፉም ተረጋገጠ።

ንጉሱም ወደ ሰውየው ዞሮ ሌባው እሱ መሆኑን እንዴት አወቅክ ሲል ጠየቀው
ሰውየውም፡-
    "አላህን እንፈራለን ብለው ራሳቸውን የሚያጋንኑ ሰዎችን ከተመለከትክ ወንጀላቸውን ለመደበቅ የሚያደርጉት ጥረት መሆኑን እወቁ" ሲል መለሰለትና በሩን ከፍቶ ከቤተ መንግስቱ ግቢ ወጣ።

@H_Islamic_tube
@H_Islamic_tube

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

16 Oct, 07:44


«#ለጉዳይህ ስትል ሶላትህን በጥድፊያ አትስገድ ምክንያቱም የቆምከው የቸኮልክበትን ጉዳይህን ጨምሮ ዱኒያን ሁሉ የያዘው ጌታህ ፊት ነውና»

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

15 Oct, 15:17


በጣም አስቸጋሪው የሂሳብ አሰራር አላህ የሰጣችሁን በረከቶች መቁጠር ነው...
وإن تعدوا نعمة الله لا تحصوها "
ALHAMDULILAH😊

سلام على من اتبع الهدى 🫀🤌

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

14 Oct, 16:25


አሰላሙ ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

ውድ ቤተሰቦች እንደምን ከረማችሁ



የታላቁን ሶሀባ (የአቡበክር ረ.ዐ)ታሪክ ባነበባችሁት መልኩ አጠናቀነዋል።
አልሃምዱሊላህ !!!
አላህ ባነበብነው የምንጠቀም ያድርገን !🤲 🤲 🤲

በዚህ አናበቃም ኢንሻአላህ የሌሎቹን ሶሀቦች ታሪክ እንቀጥላለን
ነገር ግን በአፃፃፌ ላይ ማንኛውም አይነት ሀሳብ ና አስተያየት ካላችሁ ሰንዝሩ

ግን ስትሰነዝሩ አይኔን አደራ 🙈

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

14 Oct, 09:48


🌺======<<>>=====🌺

💡 ድሀ ሷሊህ ሰለፍያ ሚስት ከ1ሺ ሀብታም ሚስቶች
  ትበልጣለች!

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

13 Oct, 09:56


🕊 የአስ ሲዲቅ ጉዞ 🕊


እሜቴ አዒሻ (ረ.ዐ) ወደ ቤት ገብታ ማልቀስ ስትጀምር አስ ሲዲቅ ከለከሏት።ከዚያም አጠገባቸው ተቀምጣ ግጥሞችን ትገጥም ጀመር ።አቡበክርም አዒሻን እሱን ተዪና እንዲህ የሚለውን የቁርአን አንቀጽ አንብቢ አሏት ።


"የሞትም መከራ እውነቱን ነገር ታመጣለች።(ሰው ሆይ !)፦"ይህ ያ ከርሱ ትሸሸው የነበርከው ነው "(ይባላል )።በቀንዱም ውስጥ ይንነፋል።
ያ ቀን የዛቻው (መፈፀሚያ) ቀን ነው ።"
ቃፍ(19_20)




አስ ሲዲቅ በመሞቻቸው ዕለት የተናገሯት የመጨረሻዋ ንግግር እንዲህ የምትል ነበረች ።"ሙስሊም አርገህ ግደለኝ ከመልካሞቹም ጋር አስጠጋኝ።"
አቡበክር የሞቱት ሰኞ ለሊት ነበር ።
በጀናዛቸው ላይ ያሰገዱትም ዑመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)ነበሩ ።


መላው የመዲና ከተማ በአቡበክር ሞት ምክንያት ስታነባ ዋለች ።ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ካረፉበት መካነ መቃብር አጠገብ ተቀበሩ
ዓሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ) ወደ መቃብሩ ተጠጉና እንዲህ አሉ ፦

"አቡበክር ሆይ አላህ ይዘንልህ።ወላሂ ከሙስሊሞች አንደኛ አንተ ነበርክ ።በኢማን ጥልቀትና ጥንካሬ አንተን የሚያክል የለም ።



ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ) በመንከባከብ ፣እስልምናንም በመጠበቅ ወደር አልነበረህም።ለሙስሊሞች ሩህሩህ ነበርክ ።ከረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ጋር በአፈጣጠርም ፣በስነምግባርም፣በግርማ ሞገስም ተመሳሳይ ነበርክ ።ለእስልምና እና ለረሱል (ሰ.ዐ.ወ)የከፈልከውን ውለታ አላህ በመልካም ይመልስልህ።ሰዎች ረሱልን (ሰ.ዐ.ወ)እምቢ ሲሏቸው አንተ አስተናገድካቸው፤ተቀበልካቸው።ሲያገሏቸው አንተ አቀረብካቸው።ምን ጊዜም ከጎናቸው ነበርክ ።አላህ በመፅሀፉ እውነተኛ ብሎ ጠርቶሀል።"ያም በእውነት የመጣው በርሱ ያመነውም"

ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)ያመጡትን እውነት እውነት ብለህ የተቀበልከው አንተ ነህ ።
ወላሂ ለእስልምና 🛡️ ጋሻ እና መከታ፤ለከሀዲያን ደሞ ቅጣት ነበርክ ።
ጎርፍም ሆነ አውሎ ነፋስ የማያናጋው ተራራ ⛰️ ነበርክ።


ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ስላንተ እንደተናገሩት ሰውነትህ ለስላሳ ቢሆንም በአላህ ትዕዛዝ ላይ ግን ጠንካራ ነበርክ ።ለራስህ የምትተናነስ ብትሆንም አላህ ዘንድ ግን ከፍ ያልክ ነህ ።በምድር ላይ ሀያል ፣ሙስሊሞች ዘንድ ደሞ ታላቅ ነበርክ ።
ለእኛ የዋልከውን ውለታ አላህ በመልካም ይመልስልህ።በአንተ ላይ ቂምም ሆነ ብሶት ያለበት ሰው የለም ።


ደካማ የድርሻውን እስካላገኘ ድረስ አንተ ዘንድ ሀያል ነበር ።ሃያሉ የሌሎችን ድርሻ እስኪሰጥ ድረስ አንተ ዘንድ ደካማ ነበር ።
ምንዳህን አላህ አይከልክለን።ከአንተም በኋላ አያጥምመን።"


ረ ዲ የ ሏ ሁ ዐ ን ሁ!!!



ምስጋና ይገባው ለአላህ ይህን ታሪክ አስጀምሮ ላስጨረሰን🤲


ተጠናቀቀ

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

12 Oct, 18:30


❤️የወዳጆች መመሳሰል ❤️


አቡበክር "ዛሬ ቀኑ ማነው?" ሲሉ ጠየቁ።
"ሰኞ ነው" አሏቸው ።"ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)በምን ቀን ነበር ያለፉት?" ሲሉ አከሉ።ሰኞ ቀን።አቡበክርም እንዲህ አሉ"አላህ ሆይ ሞቴን በዚችው ለሊት አድርግልኝ "
ከዚያም እንዲህ ጠየቁ "ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተከፈኑት በምን አይነት ከፈን ነበር ?"
የተከፈኑበትን ነገሯቸው ።
"እኔንም በዚያው አይነት ከፍኑኝ።አስከሬኔንም ባለቤቴ አስማእ ቢንት ዑመይስ ትጠበኝ"

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

12 Oct, 16:47


ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1 pinned «    መልካም ስራህ በጭንቅ ጊዜ መዳኛህ ሰበብ ነው! :¨·.·¨:  `·. سلام على من اتبع الهدى 🫀»

ᕼᗩᒪᗩᒪ ጥበብ 1

12 Oct, 13:31


    መልካም ስራህ
በጭንቅ ጊዜ መዳኛህ ሰበብ ነው!
:¨·.·¨:
 `·.
سلام على من اتبع الهدى 🫀

3,567

subscribers

236

photos

49

videos