እዚህ ቤት @gazetaw Channel on Telegram

እዚህ ቤት

@gazetaw


አገር አገር ስልሽ—ደስ ይበልሽ በጣም
ኢትዮጵያዊ ሆነን—የሚያግባባ አናጣም!

ዕወቂው ዐለሜ...!

ኢትዮጵያዊ መሆን—የውርስ እንቁጣጣ
በአጥንት ክስካሽ—በደም ቅብ የመጣ!

|ታመነ መንግሥቴ ውቤ—አባ ወራው|

ግቡ፦ስለ አገር፣ፍቅር፣ሰላም፣ባሕል እና ጥበብ እናወጋለን!

ጀበናዋ ተጥዳለች! ፍንጃሎቹ ሳይሞሉ፣የገባችሁ ሳትቋደሱ ረከቦት አይነሳም!

ክሕሎት፣ጥበብ፣ መሻታችሁ በቤቱ ይስተናገዳሉ።

ትውልድ

እዚህ ቤት (Amharic)

እዚህ ቤት የገናው ቤተሰብ ማዕከል ነው። የኢትዮጵያዊ ልዩ አምስት ጽሑፍዎችን እና ምልዓለም አገራችንን የያዘ ይሁን። በእርስዎ ቤተሰብ እና መምህር አገሮች ላይ ታሪካዊ እና ህይወት በአጭሩ መሳጭና ልባሰን በመሆን ከእነዚህ ጽሑፍ ጋር ለማግኘት እባኮትን ይጠብቁ። ቤት ማህበረሰብን፣ ፍቅርን፣ ሰላምን፣ ባሕልን እና ጥበብን ለማቅረብ የምንፈልጉት ቤተሰብ ነው። ቤተሰቦች ሁሉ በአተምህረው መንግሥት ውቤ ተመልከቱ። ምልዓለም፣ አገራችን እና አገር መሆኑን ይጠቁ።

እዚህ ቤት

04 Jan, 19:34


#ባጭሩ

እንደማንም ሰው ነኝ ስጋ እንደለበሰ፣
ሹመት ማዕረግ አልቦ የተግበሰበሰ።

#BamU

እዚህ ቤት

01 Jan, 06:34


#ባጭሩ

ጭልጥ... እልም: እንደጭጋጋማ ቀን ጉዞ፣
አንድ እርምጃ ተረግጦ ለቀጣዩ ተስፋን ይዞ!

#BamU

እዚህ ቤት

31 Dec, 18:35


#ባጭሩ

ሁሌም "አሃ" የማስባል ያክል የሚደንቀኝ መልእክት ካላቸው ሀሳቦች መካከል አንዷ ጂም ሮን (Jim Rohn) የሚባል አሜሪካዊ ሰው (ባለብዙ ሞያ) የሆነ ትምህርታዊ ንግግሩ ላይ ሲላት የሰማሁት ዓ.ነገር: "it's easy to pay the price when the promise is clear." የምትል ናት። በአብዝሃኛው የሕይወታችን ሁነቶች ውስጥ የምትሰራ አጠቃላይ ህግ እንደሆነች አምናለሁ።

#BamU

እዚህ ቤት

28 Dec, 20:17


#ባጭሩ

ስጋማ ቢያንሰው ነው
ምን ቢቃጠል ቢነድ፣
ጥንተ አመሉ'ኮ ነው
ከአልጋ ሲሉት ካመድ።

#BamU

እዚህ ቤት

24 Dec, 05:52


#ባጭሩ

"ለመኖር ብላ እንጂ ለመብላት አትኑር" የሚል መፈክር የሚመስል ሀሳብ (አቋም?) የሚያራምዱ ሰዎች አጋጥመውኝ፣ "እና ለምንድነው የምትኖሩት?" ብዬ ጠይቄአቸው አላውቅም ነበር። አሁን ይሄን አጋጣሚ ተጠቅሜ ልጠይቃችሁ፣ ለመኖር ትበላላችሁ፤ ለምንድነው የምትኖሩት?

#BamU

እዚህ ቤት

22 Dec, 18:22


#ባጭሩ

የሆነ አጥብቆ የሚወደው ነገር (ምንም ይሁን ምን) ያለው ሰው ከብዙው የሰው ዘር ተብዬ እሩቅ እንደሚጓዝ ነው የማምነው። "እንዲያው ለብ ያልክ ስለሆንክ አውጥቼ ልተፋህ ነው" የሚለውን ዓረፍተ-ነገር በተለየ ከምወዳቸው ሀሳቦች መሃል ያካተትኩም ለዚያ ነው።

#BamU

እዚህ ቤት

19 Dec, 09:35


#ባጭሩ

የዚህ ዓለም እውነተኛ ገዢ ፍርሃት ይባላል (ማነው? የት ነው ያለው? ለሚለው በየጓዳዎቻችን ብንንጎዳጎድ አናጣውም)።

#BamU

እዚህ ቤት

17 Dec, 17:14


#ባጭሩ

መሰለኝ ተሳሳትኩ፣
አዘንኩ ወይ ተደሰትኩ?
የለም፥ ይልቅ ተማርኩ።

#BamU

እዚህ ቤት

16 Dec, 09:18


#ባጭሩ

ልቤን በሀሳብ መድፌ ጠቃሁ፣
ሲፈስ እንዳያዩት ደም አነባሁ።

#BamU

እዚህ ቤት

12 Dec, 00:03


አይዟችን

https://t.me/Gazetaw

እዚህ ቤት

11 Dec, 09:25


#ባጭሩ

እጅህን ስጠኝ አለችኝ ሕይወት፣
ተማረክ ነው ተባረክ ስላለየሁት
እስኪ ትንሽ እንቆይ ነው ያልኳት።

#BamU

እዚህ ቤት

18 Nov, 05:15


መርካቶ ዝግ ሆኗል ተባለ!

ሕዳር 09 ቀን 2017 ዓ.ም

በመርካቶ የሚገኘው ጃቡለኒ ሕንፃ ትናንት እሁድ የእሳት ቃጠሎ ከደረሰበት በኋላ ዛሬ ጠዋት በገበያ ማዕከሉ እና ዙሪያው አገልግሎት የለም ሲሉ የዘ-ጆርናሊስት ምንጭ ከቦታው ገልጸዋል።

ምንጩ በጠዋት ለጣቢያችን በላኩት መረጃ "መርካቶ አድማ ላይ ነች፤ሁሉም ዝግ ሆኗል፤"ብለዋል።

የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካ ትልቁ ገበያ በተቀራራቢ ሳምንታት ውስጥ ለሁለት ጊዜ አውዳሚ የእሳት አደጋ አጋጥሞታል።

ባሳለፍነው ሳምንት ደግሞ እንዲሁ የአድማ እና ጥርጣሬ ዜናዎች ሲወጡ ነበር።

በመርካቶ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ያሉ የእሳት አደጋዎች ቢከሰቱም ዘ-ጆርናሊስት ይህን ዘገባ እስከሚያጠናቅርበት ጊዜ ድረስ ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት  የአደጋው መንሥኤ ተጣርቶ አልተገለጸም።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

17 Nov, 14:27


የዞን አሥተዳዳሪው መኪና ተመታ!

ሕዳር 08 ቀን 2017 ዓ.ም

በትግራይ ክልል የማዕከላዊ ዞን አስተዳዳሪ ከአክሱም ወደ መቀለ እየተጓዙ ያሉበት መኪና በጥይት መመታቱን ዘ-ጆርናሊስት ከታማኝ ምንጩ ሰምቷል።

በጥቃቱ  አስተዳዳሪውም ሆነ ሌሎች ግለሰቦች ላይ የደረሰው ጉዳት አልተረጋገጠም።

ከጥቂት ወራት በፊት የዚሁ ዞን ዋና ከተማ የሆነችው የአክሱም ከንቲባ ማንነታቸው ባልታወቀ አካላት የግድያ ሙከራ እንደተፈጸመባቸው መዘገባችን ይታወሳል።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

31 Oct, 05:43


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፓርላማ ይገኛሉ!

ጥቅምት 21 ቀን 2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከደቂቃዎች በኋላ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የዓመቱን የመጀመሪያ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሏል።

የዘ-ጆርናሊስት ምንጮች ከቦታው እንደገለጹት የተለመደው እና ከ15 ቀናት ቀደም ብሎ በሕዝብ ተወካዮቹ በጽሑፍ የገባው ጥያቄ መልስ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል።

የዚህኛው ዓመት የምክር ቤቱ ጉባኤ ከሳምንታት በፊት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ከርዕሰ ብሔርነት በማሰናበት እና ታዬ አጽቀሥላሴን  በመተካት መከፈቱ ይታወሳል።

ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀደም ተብሎ ሥልጣን የተሰጣቸው እና የተሸጋሸጉ ሚኒስትሮች ሹመት በምክር ቤቱ ጸድቋል።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

29 Oct, 09:42


ደሳለኝ ጫኔ አዲሱ ተሿሚ ጌድዮን ጢሞትዮስ ላይ ወቀሳ አቀረቡ!

ጥቅምት 19 ቀን 2017 ዓ.ም

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ደሳለኝ ጫኔ ጌድዮን ጢሞትዮስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸው ላይ ጥያቄ አንስተዋል።

በደሳለኝ ጫኔ "የፍትሕ ዘርፉን ከፍተኛ ችግር ውስጥ ከትተዋል፤" የሚል ትችት የቀረበባቸው አዲሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የምክር ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት ያላቸው ሆነው በእስር ሲቆዩ የፍትሕ ሚኒስትር ምንም አልሠራም ተብለውም  ተወቅሰዋል።

የቀድሞው የአብን ሊቀ-መንበር አክለው ጌድዮን ጢሞቲዎስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ብቁ አለመሆናቸውን ገልጸዋል።

ደሳለኝ ጫኔ ባለሥልጣን የሚሾምበት እና ከኃላፊነት የሚነሳበት አሠራር ከግልጽነት እና ከተጠያቂነት መርሕ አንጻር ጥያቄ እየሚያስነሳም ገልጸዋል።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

28 Oct, 18:35


ሰደድ እሳቱ የባቡር ጉዞ ከለከለ!

ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም

በድሬደዋ እና ሱማሌ ክልል ሽንሌ ዞን መካከል ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 18 ቀን 2017 ዓ.ም በተከሰተው የሰደድ እሳት ምክንያት የባቡር እንቅስቃሴ ቆሟል።

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና  ሥራ አሥፈጻሚ ታከለ ኡማ በፌስቡክ ገጻቸው "እሳቱን ለመቆጣጠር እና አገልግሎቱን ለማስጀመር የድሬደዋ የእሳት አደጋ እና የሽንሌ ዞን ሀላፊዎች ከጣቢያው ሰራተኞች ጋር በመሆን ባደረጉት ርብርብ  እሳቱን ማጥፋት ተችሏል፤"ብለዋል።

ከቀናት በፊት የእሳት አደጋዎች የአዲስ አበባውን መርካቶ ጨምሮ በባሕዳርም የገበያ ማዕከላት ብሎም የባሕል ምሽት ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

27 Oct, 16:00


በሶማሊያ ያለው ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ሊለይለት ነው!

እሑድ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት በሶማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) ካበቃ በኋላ  በሶማሊያ ወታደራዊ ድጋፍ የሚያደርጉ አገራት የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ለመምከር በሚቀጥለው ሳምንት በኮትዲቯር ስብሰባ እንደሚካሄድ ኢንሳይድ አፍሪካ ጽፏል።

ውይይቱ የሚደረገው የአፍሪካ ኅብረት የሰላም እና የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት፣ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት እና በሶማሊያ የሰላም ማስከበር ሥራዎችን ከሚያግዙ ምዕራባውያን አገራት ጋር በጋራ  በመቀናጀት ነው።

በአገሪቱ ለዓመታት የቆየው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት እጣ ፋንታም በዚሁ ሥብሰባ ላይ ሊወሰን ይችላል።

የሶማሊያ ባለሥልጣናት በቅርቡ በሚያደርጓቸው ንግግሮች በምድራቸው ያለውን እና ከሁሉም ሰላም አስከባሪዎች በቁጥርም፣በግዳጅ አፈጻጸምም የላቀ ነው የሚባለውን የኢትዮጵያ ጦር ማንኳሰስ ጀምረዋል።

ይቀላቀሉን፦ @zejournalist

እዚህ ቤት

27 Oct, 12:34


ኢትዮጵያ ተጨማሪ የጭነት መርከቦችን ልትገዛ ነው!

እሑድ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የኢትዮጵያን የገቢ እና የወጪ ንግድ ፍላጎት ለማስተናገድ የሚያስችሉ ተጨማሪ የጭነት መርከቦችን ለመግዛት ማቀዱን አስታውቋል።

ግዢው አቅምን ለማሳደግ፣በኮንቴይነር እጥረት ምክንያት የሚፈጠሩ መስተጓጎሎችን ለመቅረፍ እና የወደብ መዘግየቶችን ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች አካል መሆኑም ተጠቁሟል።

በአሁኑ ጊዜ 45% የሚሆነውን የአገሪቱን ገቢ የሚያስተዳድረው ተቋሙ ባለፈው በጀት ዓመት 57 ቢሊዮን ብር ገቢ በማግኘት በውጭ ምንዛሪ ገቢ ከፍተኛ ዕድገት አስመዝግቧል።

ይቀላቀሉን፦ @zejournalist

እዚህ ቤት

26 Oct, 06:24


ያሙተኝ

ጋሸ ማረፋቸውን ቴዎድሮስ ጠና ነገረኝ።

ታምራት መድኅን ለእኛ አገር ቤት ላለን ኢትዮጵያዊያን  የተደበቀ ታላቅ ሥም ነው።አትላንቲክ ማዶ ግን ዝነኛ ናቸው።

"ጉማ"የተባለው የመጀመሪያው የአገራችን ባለቀለም ፊልም ሲሠራ ሳንቲሙን የቻሉት እሳቸው መሆናቸውን ነግረውኛል።

"ጉማ አዋርድ" ሥለ'ሚሉት ሸላሚዎች አንስቸባቸው "ተዋቸው" ዓይነት ናቅ አርገው ነበር ያለፉት።

ጋሸ ከዚህ በላይ ናቸው።ለአምሳ ዓመት በተጠጋው የአሜሪካ ኑሯቸው በዚያ ላሉ ኢትዮጵያዊያን እና ጥቁሮች መኩሪያ ነበሩ።

ይህንን ጉዳይ እነ Washington Post ጽፈውበታል።

ያገኘኋቸው ሕይወታቸውን ልሰንድ ነበር።ሥጀምርም ዳሽን ተራራ ሆቴል ተራራ የሚያህል ምሳ ጋብዘውኛል።

ሥለ መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ልደቱ አያሌው፣ዐቢይ አሕመድ፣ጃንሆይ እና ሥለ እሳቸው ብሎም ሥለ እኔ ትውልድ እያነሳን ተከራክረናል።

የእኛን ትውልድ ቀልብ ማጣት እና ድባቴያምነት በአንድ ልዩ ምሳሌ ነበር ያስረዱኝ።

"እዚህ ሆቴል ውስጥ"አሉኝ።

"እዚህ ሆቴል ውስጥ ወጣት አስተናጋጆች ያዘዝኳቸውን 'እሺ' ብለውኝ ይሄዱ'ና ተመልሰው'ረሳነው'ብለውኝ ይመጣሉ!"

በርግጥም ታዝበውናል።

የሆነው ሆኖ ታሪካቸውን እዚህ ላለው ወገኔ እንዳደርስላቸው ይፈልጉ ነበር።ጀምረንማል።ቴሌቪዥን ላይ ሊተላለፍ የቃል መጠይቅ አድርጌላቸው-አለሁ።በዝግጅቱ ሒደት፦

"ሰላም የኔ ወንድም ፡ ይህ Title ከኔ ካሰብኩት ጋራ ጥሩ ሊሆን ይችላል -- Saving The Lives of the Ethiopian  Immigrants In America  from a Savage Ruthless Military Dictator Was My Mission."ብለውኛል።

ያ በሆነ በወሩ አረፉ፣አሉ።

ቤተሰቦቻቸው ከረዱኝ አደራ ሳልበላ ሕይወታቸውን ለመሰነድ ዝግጁ ነኝ።

ታዲያ ሳልሞት ነው።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

26 Oct, 04:06


"እነሱም ይላሉ ቃታ’ም አናስከፍት
እኛም እንላለን ቃጣታ’ም አናስከፍት
እንዲህ ብለን ብለን የተገናኘን ለ’ት
አሞራ ተሰብሰብ እንድትበላ ዱለት!"


Bisrąt Árgąw IV በፌስቡክ በአንድ ልጥፌ ሥር ያጋራኝ ፉከራ ነው።

ምሥሉ ለእሱ ታሪካዊ ነው።ጊዜው ሲደርስ እናወጋበታለን።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

26 Oct, 03:01


አጽንኦት ለመሥጠት ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ የትግራይን ያህል የተደራጀ ብሔርተኝነት የለም።አማራም፣ኦሮሚያም፣ሶማሌም ከትግራይ አንጻር ደካማ ብሔርተኞች ናቸው።

በቅርቡ ያነበብኳቸው ሰነዶች ትግራይን ለዚህ ምልዑ ብሔርተኝነት ያበቃት ጠባቡ የምድር መልኳ፣በመሬቷ ውስጥ ብዙ ተቀናቃኝ የሌለው ትግርኛ የተባለ ቋንቋዋ እና እኔ የምገምተው ደግሞ ለመቶ ዓመታት የዘለቀው ራሥ ገዝ አሥተዳደሯ ነው።

ይህ መንፈስ በሁለት የሰባት እና ሥምንት ዓመት አዳጊ ሕፃናት ውስጥ ሰርጾ ያገኘሁበትን አጋጣሚ ላምጣው።

ትናንት ነው።ምሳ እየበላሁ ሁለት ነገረ ሥራቸው የዐደይ ትግራይ ልጆች የሚያስመስላቸው ሶፍት እና ማስቲካ አዟሪዎች ገቡ።የምግብ ቤቱ ባለቤት ፊት ለፊቴ የራሧን ሳህን ይዛ እየበላች ነበር።

"አየህ እኒህ ልቅም ያሉ የትግራይ ልጆች..." ብላኝ ከምትበላው ላይ ታጎርሳቸው ጀመረች።

በዚያው ወሬ ቀጠሉ።

"አገራችሁ ማን ይባላል?" አለቻቸው።

"ትግራይ" ሲሉ መለሱ!

ደንበኛዬ "ኢትዮጵያዊ ነኝ"ባይ ናትና "አገራችሁ ኢትዮጵያ ናት፤ እሺ!" እያለች ልትሰብካቸው ሞከረች።

ጉንጭ አልፋ ስብከት ነበር።

ወደ ነገሩ ሥረ መሠረት እናዝግም...

የ20ኛው የዘመን ክፍል ረፋድ ላይ ኢትዮጵያ ከነበሯት የአስኳላ ምሩቃን ዋናው ገብረ-ሕይወት ባይከዳኝ በአንድ መጽሐፉ ላይ"ጃንሆይ የትግራይን ሕዝብ እንደ ራሥዎ ሕዝብ ያዩታልን?"ሲል ዳግማዊ ምኒልክን ጠይቋቸዋል።

ቀለሜው ገብሬ የሆነ ችግር ታዝቧል ማለት ነው።

ያች በመሪዎች "እንደ ራሥ ሕዝብ"አለመታየት ደግሞ በመጀመሪያው የወያኔ አመጽ፣በ1960ዎቹ ለፈሉት ታጣቂ ኃይሎች ሕዝባዊ ምሽግ በመሥጠት ወዘተ ስትገለጽ ቆይታ በ1983 ዓ.ም ትንሿ ትግራይ የወለደቻቸው ልጆች የአራት ኪሎ ጌታ ሲሆኑ ተጠናቀቀ።

ከ30 ዓመታት በኋላ ዳግም ትግራይ ከኢትዮጵያ አገረ መንግሥት እና ከአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተዋጋች።

ይሄ ይሄ ተደማምሮ የሰባት እና ሥምንት ዓመት ሕፃናት፣ለዚያውም በአዲስ ጎዳናዎች ላይ ለሥላሳ ወረቀት እና ማስቲካ የሚሸጡት፣ከአንዲት አማራ እጅ ምግብ እየጎረሱ፦

"አገራችሁ የት ነው?" ተብለው ሲጠየቁ

"ትግራ" አሉ።

እንዲሁ ከዓመት በፊት የተዋወቅኋት ጓል መቐለ በአንድ የቴሌግራም ምሥሏ ላይ"እኔ ትግራዋይቲ ነኝ፤"ብላ ጽፋ ተመልክቸ-አለሁ።

በተዋወቅን ሰሞንም አብዛኛው የሚያገኛት የአዲስ አበባ ሰው በተጋሩነቷ ያገላት እንደነበረ ነግራኛለች።

የዚህ ድምር ውጤት ምን እንደሆነ፣መፍትሔውም ከምን ሊመነጭ እንደሚችል፣ይጎዳናል ወይስ ጥቅም ይኖረዋል የሚለውን ጉዳይ ፖለቲካን የተማራችሁ ጻፉበት።

ቸር ያሰማን(በነጋሽ ሞሐመድ ቃላት🤔)!

@Gazetaw

እዚህ ቤት

26 Oct, 03:01


"የትግራይ ልጅ ነኝ!"

[በታመነ መንግሥቴ ውቤ]

...

እዚህ ቤት

25 Oct, 17:16


ኦሮሞ ወደ ርሥቱ እየተመለሰ ነው🤔?

[በታመነ መንግሥቴ ውቤ]

"አዲስ አበባ የማን ናት?"የሚለው አሰልች ጥያቄ ከአምስት ዓመታት በኋላ እየተመለሰ ነው።

በቅርቡ የምንሰማቸው ተባራሪ ወሬዎች አበባይቱ ከኢትዮጵያዊያንም እጅ ወጥታ እንደ'ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ባሉ ዲታዎች ልትዘወር ነው ይላሉ።

ኦቦ ቀጀላ መርዳሳ ደግሞ "አዲስ አበባ ተጠራነቷ ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት እንዲሆን እንጠይቃለን፤"ሲሉ ኦነግን ወክለው ከሰሞኑ ለአዲስ ማለዳ በሰጡት የቃል መጠይቃቸው ላይ ተናግረዋል።የኦነጉ ሰው አክለው የፌዴራል ዋና ከተማ ባሕዳር ሊደረግ እንደሚችል አብራርተዋል።

ካነሱትስ አይቀር ቀኃሥ ያችን የጣና ዳር ገነት እንዲያ የተጠበቡባት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሊያደርጓት እንደነበረ የሚነገረውን ጉዳይ እናስታውሰው።

ከሰሞኑ ደግሞ አዲስ አበባን ከሶስት ጊዜ በላይ የተፈታተናት የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ተከትሎ የቤታችን ሌላኛው አባወራ ጃንሆይ ባሕርዳርን ለዋና ከተማነት ያጯት ሸገር እንዲህ እንደምትንቀጠቀጥ ተነግሯቸው ነው ብሎኛል።

የቀጀላ ምክር እና የመሬት መንቀጥቀጡ ሥጋት ተገናኙ ማለት ነው።እናም የዐባይ ጓሮዋ ቆንጆ፣የጎንደር ጓሮ ተክሏ፣የጎጃም ነገድ መነሻዋ፣ማንገስም፣መሰልጠንም ብርቋ ያልሆነው ባሕርዳር ብትዘጋጅ ጥሩ ነው።

አንዳንድ ሰርግ አለ።"ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ"የሚባልለት።እንዲያ መሆን የለባትም።

ምናልባትም ኦቦ ቀጀላ በአንድ ሌላ የቃል መጠይቃቸው"መገንጠል የምትለውን ሥሟንም አንቀበልም፤"ቢሉም አዲስ አበባን ይዘው አገር ሊሆኑ አምሯቸው ይሆናል።የኢፌዲሪ ሕገመንግሥትም ይህንን ይፈቅዳል።

ታዲያ ኢትዮጵያዊያንን በጋራ የምታስተሳስረዋን አዲስ አበባ የተባለች ከተማ ለኦሮሚያ ክልል ትሰጥ ማለትን ምን አመጣው?ብለን ጠይቀን ጨዋታችንን ወደ ሌላ ዐውድ እንግፋው።

እርግጥ ነው ከተማዋ ኦሮሞን በድላዋለች።በተስፋፋች ቁጥር በዙሪያዋ ያሉ ደሃ ገበሬዎችን ጨፍልቃለች።

ከዚህ በተቃራኒ ኦሮሞ ነው ራሧን አዲስ አበባን የወረራት የሚሉ ምንጮች አሉ።እኒህ ወገኖች ከ16ኛው የዘመን ክፍል በፊት የነበረችውን አዲስ አበባ ያስታውሳሉ።

ያኔ ሥሟ "በረራ"ይባል ነበር ብለው የጻፉ አጋጥመውኛል።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የመሪነት ዘመናት ጅማሮ ላይ "በረራ"የተባለ ጋዜጣ መታተም ጀምሮ ነበር።አዲስ አበባ የአማሮች የጥንት ባድማ እንደነበረች ያትታል።

እኒህ እና እንዲህ ያሉ ወገኖች ኦሮሞ በታላቁ የመሥፋፋት ጊዜው ላይ ወደዚያኔዋ የነገሥታት መንደር በረራ ወይም ወደዛሬዋ አዲስ አበባ ከ500 ዓመታት በፊት ገባ እንጂ አዲስ አበባ ከርስቱ አልነቀለችውም ባይ ናቸው።

ቀጀላ መርዳሳ ግን ይህን አሳብ አይቀበሉትም።ከበቃሉ አላምረው ጋር በነበራቸው አንድ የቃል መጠይቅ ላይ ተናገሩት ተብሎ መጠቆሚያ(Thumbnail) ላይ የተጻፈው ቃላቸው "ኦሮሞ በታሪኩ ተስፋፍቶ አያውቅም፤ነፍጠኛ ግን ወረራ ፈጽሟል፤"የሚል ነው።

ይህኛው የቀጀላ ንግግር በታሪካዊ ሰነዶች ሥለመደገፉ ርግጠኛ መሆን አይቻልም።

በ1520ዎቹ መጀመሪያ የዚያኔው የኢትዮጵያ ንጉሥ ዐፄ ልብነድንግል የዛሬዋ አዲስ አበባ ገደማ ሆነው አገር ይመሩ እንደነበረ የሚገልጹ ሰነዶች ግን እልፍ ናቸው።

በዛሬዋ ቢሾፍቱ አካባቢ የነበረችው ሽምብራ ቆሬ ደግሞ ንጉሡ ከኢማም አሕመድ ኢብን አልጋሃዚ ጋር የተዋጉባት ቦታ መሆኗ ለዚህ ጥሩ አሥረጅ እየሆነ ይቀርባል።

ቀጀላ በዚህ አይስማሙም።ኤካ፣ጉለሌ እና ገላን የተባሉ የኦሮሞ አባቶች በዛሬዋ አዲስ አበባ ላይ ርሥት ይዘው የኖሩ ናቸው ሲሉ በአዲሱ የቃል መጠይቃቸው ላይ አውግተውናል።እንዲያውም ኤካ የሚለው የአፋን ኦሮሞ ቃል የካ እየተባለ መጠራቱ "ወንጀል"የሚል ትርጉም እስከመሥጠት ደርሷል ባይ ናቸው።ቦታው ከባለቤቱ ውጭ ሲተዳደር የተፈጠረ ሥህተት ነው የሚል ድምጸት አላቸው።

ይህን እና እንዲህ ያለውን የኦሮሞ ሰዎች ዕይታ ይዘን አዲሲቱ አዲስ አበባ በኦሮሞ ገበሬ ላይ የፈጸመችውን ግፍ ስንመዝን በርግጥም የ2009ኙ እና የዚያ ዘመኑ የቄሮ እንቅስቃሴ ተገቢ ነው ያሰኘናል።

ያኔ ደረታቸውን ለ"አጋዚ" እና "ጉጅሌ"ጥይት የሰጡ የኦሮሞይቱ ልጆች "ፊንፊኔን ከዙሪያዋ ከተሞች ጋር የሚያስተሳስረውን የተቀናጀ የከተሞች እድገት ፕላን እንቃወማለን።የኦሮሚያ ገበሬ መሬት እየተነጠቀ ለባለ ሃብቱ መሰጠቱ ባስቸኳይ ይቁምልን፤"ሲሉ ያንን መዘዘኛ "ማስተር ፕላን"የተባለ ሰነድ ተቃውመው ወጡ።

የዚህ ቡድን የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾች መሪ ጃዋር ሲራጅ ሞሐመድ ነበር።

የዛሬው ሥደተኛ ፖለቲከኛ ጃዋር ሞሐመድ ለጋሽ ደረጀ ኃይሌ በሰጠው የቃል መጠይቅ ውስጥ ደጋግሞ "የገበሬ ልጅ ነኝ፤"ብሎታል።

የገበሬ ልጅ ተሁኖ ገበሬ ከገርጅ እስከ ጣፎ እየተፈናቀለ በልቶ የማይጠግብ ባለሃብት ሲንቀባረርበት ማየት በርግጥም ያማል።ጉዳዩ በብሔር ሳይሆን በመደብ ዐይን መታየት አለበት።

ለዚህ እንዲጠቅመን በቅርብ ዓመታት ውስጥ የመቀሌ ጊዚያዊ አስተዳደር ከንቲባ ሆኖ የነበረውን ወጣት አታኽልቲ ኃይለሥላሴን እናስታውሰው።

አታኽልቲ ለቴዎድሮስ ተክለአረጋይ በ"ፍልስምና ፮"ላይ እንደነገረው በእንደርታ ገጠር መሐል የቆመችው የሰሜኗ ኮከብ የአካባቢውን ገበሬዎች ሕይወት ሲኦል አድርጋባቸዋለች።

ይህ እውነት ለባሕዳር፣ለሞጣ፣ለጎንደር እና ለአዳማ ሁሉ ይሠራል።

ኦቦ ቀጀላ መገርሳ በሰሞነኛው ንግግራቸው እንደሚሉት ከሆነ የገበሬዎችን የጤፍ መሬት እየቀማች ታባርር የነበረችው አዲስ አበባ በአዲሱ መንግሥት ጊዜ አድባለች።በአዲስ አበባ ከተማ እና በኦሮሚያ ክልል መካከል ችካል ተቀብቅቧል።

አዲስ አበባ ኦሮሞዎቹ እንደሚሉት ከ100 በላይ ዓመታት በኋላ በቅርብ ጊዜ የኢሬቻ'ን በዓል ማክበር ጀምራለች።ከቂርቆስ ክፍለከተማ ፊት ለፊት ያለውን ወንዝ ተንተርሶ የኢሬቻ ማክበሪያ ቦታው በይፋ "ሆረ ኢሬቻ"ተብሎ ተጽፎበት ተከልሏል።

የእነ ጉለሌ፣ኤካ እና ገላን ልጆች ርሥታችን የሚሉትን ምድር ዳግም መውረስ ቻሉ ማለት ነው።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

25 Oct, 16:43


የነፍሴ ሙዚቃ ነው።

"የማን ነሽ ይላታል
የማን ልትለው?
የአገው ምድር ልጅ ናት የፈረሰኛው!"


@Gazetaw

እዚህ ቤት

25 Oct, 08:37


"አንቺ ለምንድን ነው በሩን የዘጋሽ፣
ባላገሩ ከፍቶት ሲያድር እያየሺ።

ባላገሮች ከፍቶናል
!"

ከ Geta Belete Debebe የፌስቡክ ገጽ ላይ አገኘሁት!

ምሥሉ፦ ጎጃም፣ሞጣ አውራጃ፣ቢቡኝ ወረዳ፣ድጎቃንጣ ቀበሌ፣ሉባጊዮርጊስ በተባለችው የመንግሥቴ ውቤ ቀዬ፣እኛ መሬት(የማሞ ርሥት ላይ)፣የዛሬ ሶስት ዓመት በዚህ ሰሞን(ራሥ በራሥ—Selfi በምትሉት) ዘዴ የተነሳ ነው።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

24 Oct, 13:56


"እምቢ ነው መልካም
እምቢ ነው መልካም
አንበሳ ጠጉሩን
ዝንብ አያስነካም!"


ከአባ የፉከራ ግጥሞች አንዷ ናት።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

24 Oct, 11:02


የጎልያድ ንቀት የጎልያድ ውድቀት
በዓሉ ግርማ፣ኦሮማይ!

ለመሆኑ ጎልያድ ግፈኛ ነበርን🤔?

@Gazetaw

እዚህ ቤት

23 Oct, 17:03


ጥያቄ🤔?

BRICS ላይ የኢትዮጵያ እና በቅርቡ አብረዋት እንደ አዲስ የተቀላቀሉት አገራት ሥማቸው በማሳጠሪያው(ምኅጻሩ) ማለትም BRICS በሚለው ውስጥ የማይካተት ለምንድን ነው?

@Gazetaw

እዚህ ቤት

23 Oct, 16:44


መምህሬ አብርሐም ፀሐዬ

"ቆንጆዎቹ እና ሠርቅ ዳ.

ይህን ደራሲ አንድ ጊዜ ፍልስፍና ነክ ሐሳቦችን ሲያቀርብ ተገናኘን።

አየሁት። በደንብ አየሁት... ቆንጆዎቹንና የቃየን መስዋዕት መጻሕፍቱን በምልሰት ገልጥኳቸው። ለመጠየቅ አማረኝ። የቱን አስታውሼ? ጠፉብኝ። ቆንጆዎቹን ስጨርስ ነሽጦኝ ነበር፤ የቃየን መስዋዕት ሲያልቅ ደግሞ አዞረኝ።

ሠርቅ ዳ. መልኩ ፈረንጅ  ነው... ። ሳየው ደስ አለኝ! በስራህ የሚወዱህ ካሉ ዕድለኛ ነህ። አዎ እርሱ ዕድለኛ ነው። ተወዳጅ ብዕርተኛ!

አንድ ወንደሰን የሚባል የአራት ኪሎ ምሩቅ ወዳጅ ነበረኝ። ኬሚስትሪ ሲማር ስነ ልቡናን የሚያስተምራቸው ይኸው ደራሲ ነበር። ስለሱ ሲነግረኝ በወሬው መሐል እየሳቀ እንደነበር አስታውሳለሁ። ጨዋታ የሚችሉ፣ የሚያስቁ ግን ታድለው!

ካልተሳሳትኩ በዕውቀቱ ስዩምን አስተምሮታል። ራሱ ሰርቅ ዳ. ያወራ መሠለኝ። እንደውም ምናልባትም ዘነበ ወላ እባካችሁ ይህን ሰው አገናኙኝ ብሎ ሠርቅ ዳ. አንዴ ከተገናኙ በኋላ እንደጠፋበት የሚናገር የአፋልጉኝ መጣጥፉን አይፐሲዜ መጽሐፍ ላይ አኑሯል። 'ኩርኮራ' በሚል ርዕስ ስር።

የበዕውቀቱ ወዝ ግምሽ አካሉ ከሰርቅ ዳ. የተቀዳ ይሆን?!

ታሜ ከሠርቅ ዳ. ቆንጆዎቹ መጽሐፉ ላይ ስለርብቃ የተጫረ አንድ አንተ እንደጻፍከው ዓይነት የተጫረ ነገርን አስታውሳለሁ።

የውጭ ጉዳዩ ሰው ናትናኤል ላይ ሰላይ ሆና ተመድባ የተላከችበት ርብቃ ስለላዋን ትታ ከልቧ ወደደችው።

በአንድ ዲያሎጋቸው ላይ ርብቃን እንዲህ ይላል፦

"ርብቃ እነዚህ ጭኖች ይዘጉ" ይላታል።
እሷም መልሳ
"እሱ የከፈተውን እሱ ይዘጋዋል" ስትል ትመልሳለች።
ቆንጆ ብዕር ያኖረ ምርጥ ጸሐፊ ነው።

ከግርግሩ ግን አብዝቶ ይሸሻል። ይሽሽ!

(ኢዮብ አልፏል፤ ሕይወት ይቀጥላል። ይኸው ወደሌላ መጣጥፍ ተሸጋገርን)"

እዚህ ቤት

23 Oct, 11:45


ይህን ጽሑፍ ካጋራኋቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች አንዱ በ24 ሰዓታት ውስጥ ራሡን በራሡ የሚያጠፋውን የቴሌግራም አሠራራቸው አርመዋል።

እንዲህ ያዝልቀን

@Gazetaw

እዚህ ቤት

23 Oct, 05:22


የጎጃም "ፒያሳ"አለ🤔?

ኢትዮጵያ ውስጥ በመሐል ከተማ "ፒያሳ"የሚለው ቃል የሌለባቸው የቆዩ ከተሞች የጎጃሞቹ እንደሆኑ ሁለት ጎጃሜ ሰዎች አውግተውኛል።

በእኔም ጥናት ከደብረማርቆስ እስከ ሞጣ፣ከባሕር ዳር እስከ ደንበጫ "ፒያሳ"የሚባል መጠሪያ ያለው የከተሞች ክፍል አላጋጠመኝም።

በተለዬ ይህ ለምን ሆነ?

ባሕር ዳር አንድ ሰፈር በቅርቡ"ፒያሳ"በሚል ሥም የሚጠራ የአገልግሎት መሥጫ ቦታ ያለው ሰው ተመልክቻለሁ።

በጊዜ "ተው"ይባል!

ቢቢሲ በዚህ ጽሑፉ በሮማ ከተማ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መንገድ ተሰይሞላቸዋል ይለናል።አንብቡለት።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

22 Oct, 13:18


ትግራይ "መዓረይ"

የእነ ሥሑል ሚካኤል፣የእነ ሰባጋዲስ፣የእነ ደጃጅ ውቤ ኃይለማርያም፣የእነ ካሳ ምርጫ፣የእነ አሉላ አባነጋ፣የእነ ኃይለማርያም ረዳ፣የእነ ኃዬሎም አርአያ አገር ትግራይ ኩራቷ ይደላኛል።

ዳንኤል ክብረት እና እሳቸውን የመሳሰሉ ጸሐፊያን ትግሪኛ ቋንቋ እና በቁጥር ያነሰ ግን በተቀራረበ የመልክ ምድር ላይ የሚኖር ሕዝብ የፈጠረላት ብሔርተኝነት በኢትዮጵያ ውስጥ ተወዳዳሪ የሌለው ነው ይሉላታል።

አሁን ግን በውስጧ የተፈጠረው ጎጠኝነት፣ጥቅም ያስተሳሰረው የወታደሮች በአዛዦቻቸው ሥር መቧደን፣ከከባድ ጦርነት በኋላ የሚያጋጥም ማኅበረሰባዊ መዛል እየፈተናት ነው።

የምወዳት አገሬ—ኢትዮጵያ አስኳል ለሆነችው ትግራይ ዛሬም የተጠና የማገገሚያ መፍትሔ ያስፈልጋታል።

"መዐረይ"የሚሉ ቆነጃጅት ያሏት ሌላ የኢትዮጵያ ክፍለ-አገር ታውቃላችሁ😀?

@Gazetaw

እዚህ ቤት

22 Oct, 08:29


"አፍንጫ መጎረድ
በዘር አለብን
ከንፈራችን ማር ናት
ትቀመስልን!"


ከዚህ በፊት የማላውቃት ግሩም ሥንኝ ናት🤔

@Gazetaw

እዚህ ቤት

22 Oct, 06:05


"በዚህ ሥፍራ ድሆች ከነመብታቸው አሉ፣ በዚህ ሥፍራ ሻጮች ሳይነሱ፣ ዞር በሉ ያልተባሉ ጉሊተኞችን ማየት ይቻላል። የአገልግሎት ክፍያ አምጡ ሳይባሉ ገብተው የሚወጡ... ከልጅ እስከ አዋቂ በሰማያዊ ተስፋ የሚመላለሱትን አየሁ። እየተሰጣጡ!

#ይሁን!"

ሙሉው በዐውድማ https://t.me/litjournalism/103088 ውስጥ በመምህራችን አብርሐም ፀሐዬ ተጽፎ-አለላችሁ

እዚህ ቤት

22 Oct, 05:31


በመርካቶ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከአምስት በላይ የባንክ ቅርንጫፎች ወድመዋል!

ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም

ትናንት ምሽት በመርካቶ ሸማ ተራ አካባቢ በተነሳው እሳት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከአምስት በላይ የባንክ ቅርንጫፎች ወድመዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸማ ተራ ቅርንጫፍ ተቃጥሏል ያሉን አንድ የዐይን እማኝ፣ ሌላ ከአምስት በላይ ሕንፃው ላይ የነበሩ ባንኮች ወድመዋል ብለዋል።

አጋጣሚውን ተጠቅመው ዝርፊያ ሲፈፅሙ የነበሩ አካላት መኖራቸውም ተጠቁሟል።

እሳቱ በአንዳንድ ቦታዎች እስከ ጠዋት ድረስ አልጠፋም ተብሏል።

በቦታው ሲያለቅሱ እና ሲጮኹ ከነበሩ ባለንብረቶች መካከል የታሰሩ መኖራቸውንም ሰምተናል።

ይቀላቀሉን 👉 @zejournalist

እዚህ ቤት

22 Oct, 03:58


"...በእኛ ሞያ (በጋዜጠኝነት) ደባሪ ቀናት ከአስደሳቾቹ የሚለዩት በዕለቱ በሚከሰተው የዜና እና የመረጃ ክብደት ብቻ ነው።"

የፈራ ይመለስ፣ከተመስገን ደሳለኝ፣2008 ዓ.ም፣ገጽ-53

@Gazetaw

እዚህ ቤት

21 Oct, 19:13


#መርካቶ

[በታመነ መንግሥቴ ውቤ]


በኢትዮጵያውያን የዘመን ቀመር ሺህ ዘጠኝ መቶ 65 ዓመተ ምህረት ተሸላሚው ጸጋየ ገብረ መድኅን በኢትዮጵያው የገበያዎች ውቅያኖስ መርካቶ ተገኝቶ ታዘበ።

በዝነኛ ነበልባል ብዕሩ እንዲህ ሲል ከተበ፦

"አይ መርካቶ__
በቁሳቁስ ግሣንጉሱ
ለቱጃር የጥጋብ ቅርሱ
ለኔ ብጤም የቀን ጉርሱ
አባ መስጠት እጦት ቢሱ"

"መርካቶ ማለት የሰፊው ሕዝብ እና የአገር ተወላጁ ገበያ ነው።"የሚለው ጸጋየ ገብረ መድኅን ይህንን የአፍሪካ ገበያዎች አውራ"አባ መስጠት እጦት ቢሱ"ማለቱ ሃቅ መሆኑን ለመረዳት " ምናለሽ ተራ"እንታደም።

በመርካቶ ቀየ ድብድብ፣አባሮሽ "ያዘው ልቀቀው"እንጅ ፋታ አግኝቶ መደመም አይታሰብም።

ቢሆንም "ምናለሽ ተራ"ውስጥ የሌለ የለምና ፋታ በሌለበት አፍታም መደመም ግድ ነው።የደላቸው መሃል መርካቶ መፅሔት ገልጠው ቃላት ይለቅማሉ፣የሰለቻቸው ሁሉንም ትተው ጫት ይቅማሉ።



አፈ ታሪክ ስለ ምናለሽ ተራ እንዲህ ይላል፦
"በደርግ ዘመን ስኳርና ዘይት በመንግስት እጅ ነበሩ።ከደርጉ እኒህን ሸቀጦች ያገኙ በጉያቸው ድብቅ አድርገው መርካቶ የድሮው ቡና ተራ ለሽያጭ ተገኙ።ተቀባይ ነጋዴዎቹም በሹክሹክታ"ምናለሽ?"እያሉ መጠየቅና መግዛት ጀመሩ።በቃ ይሄው"የምናለሽ ተራ ምስጢሩ!"

መርካቶ የገበያዎች ውቅያኖስ ቢሆን ምናለሽ ተራ ደግሞ የገበያዎች ባህር ነው።በስሩ እነ ቡና ተራ፣ሸክላ ተራ፣ሸማ ተራ ሃይቅ መስለው አሉ።

በቡና ተራ እናቶች ሁሌም አቀርቅረው አረንጓዴውን ወርቅ ያሰማምራሉ።ቡና በመርካቶ የሚሸጥም የሚጠጣም ሃብት ነው።

እዚህ ቀና ብሎ ሰማይ ለማየት የሚሆን ፋታ የለም።ብረት መደብደብ፣ጎጆ የሚያህል እቃ መሸከም፣መጣር መጋር ነው።እናም ቡና እንደ ጉድ ይጠጣል።

ሸክላ ተራ ብቅ ላለም የቡናን ማዕረግ የምታስከብረው ጀበና እንደ እንቁላል በጭድ ስትጀቦን ይታዘባል።

በቃ መርካቶ ውስጥ ምን አለሽ ተራ የሌለ ምን ይገኛል?

በምናለሽ መንደር የሌለ የለምና ቤት ይጠባል።ከዕድሜው መርዘም የተነሳ አፈር የመሰለው ጣሪያ ከሆዱ የተረፈውን ግሳንግስ በላዩ ላይ ይሸከማል።

አይ መርካቶእንዲል ተሸላሚው
ምናለሽ ተራ ላይ ሕይወት በስምምነት ትተማለች።የውሻ ቡችላ የኤሌክትሪክ እቃዎች ተጠግነው ዳግም ነፍስ ከሚዘሩበት ሸራ ላይ "አገር ሰላም"ብላ እንቅልፏን ትለጥጣለች፣የመርካቶ አህያ የጫኗትን ትወስዳለች ታመጣለች!

ሕይወት በዚህ ቀየ እየመረረች ትጣፍጣለች!

የምናለሽ ተራ እናቶች ተራ ነጋዴዎች አይደሉም።የሰሩትን፣የለፉ የጣሩበትን እንጅ የገዙትን አይሸጡም።

እንሰትን ከጉራጌ ምድር አምጥተው ቆጮ እና ቡላ የሚባሉ ባህላዊ ምግቦችን በአደባባይ ይሰራሉ።

እንሰቱን እንደ እንጨት ታስሮ ለሚመለከተው ረብ የለሽ ይመስላል። በስልቻ ተከቶ ጊዚያትን ይፈጅና እንደ በረዶ ይነጣል።የዱቄት ለዛ እስኪኖረው በቢላዋ ተደጋግሞ ይቆራረጣል።ከዚያ ለመጋገር ብቁ መሆኑ ይረጋገጣል።

በምናለሽ ቀየ ይህ ስራ በነበረበት የሚረግጥ አድካሚ ሂደት ነው።ታቦተ ፅዮንን ሊፈልግ የመጣው ግርሃም ሃንኮክ እንደሚለው "ኢትዮጵያ በዘመናት ኑረት የማትለወጥ "መሆኑ ያሳዝናል።የኒህ መንፈሰ ጠንካራ ልበ ተራራ እናቶች ድካምም ለውጥ አልባነታችንን ይመሰክርብናል።
እዚህ አክርማ ተነክሮ በቀለም አጊጦ ያስዋበው ቀለምሻሽ የዐይን አዋጅ ይሆናል።ቆዳ እንደ ወረቀት ሲተጣጠፍና ሲቀረጣጠፍ አጃኢብ ያሰኛል።

የመርካቶ ባተሌ ሰርክ ይዳክራል፤ብረት ቀጥቅጦ አገር ይሰራል፤ወናፍ አናፍቶ እሳት ይፈጥራል፤በእሳት አግሎ ፌሮ ይገራል።

ግን ምን ይሆናል?

በ21ኛው ክፍለ ዘመን ባለበት የሚረግጥ፣የአባቱን ወናፍ ያልቀየረ መሆኑ ያሳዝናል።
ፌሮ ብረትን ሲቆለምም መጠነኛ ዘመናዊ መሳሪያ የተጠቀመ ይመስላል።ቶርኖ ስራ የሚለው ነገር ግን አድካሚነቱ ያው ብረት ቅጥቀጣውን ያክላል።

በውቅያኖሱ መርካቶ ገበያ ፣በባህሩ ምናለሽ ተራ አዳፋ የለበሱት፣ከሕይወት ጋር ነግቶ እስከሚመሽ የሚታገሉት እናቶች ይተጋሉ፣ይፈጋሉ፤ለውጥ እምብዛም የለም።

በሌላ በኩል መርካቶ ለእንግዳ ሰው ጫጫታው ጭንቅላት ቢበጠብጥም፣አባሮሹ መንፈስ ቢያናውጥም፣ለለመደው አቤት ድባቡ ሲጥም?

ድማፃዊ አብዱ ኪያር፦

"መቸም የገባሁ ቀን፤ካገር ከመንደሬ
ደስታ ነው 'ሚሰማኝ ገና ሳየው
መርካቶ ሰፈሬ"
ሲል ያዜመው የመርካቶን ከባቢ አድገውበት ለሚያጣጥሙት ነው።


መርካቶ፦

"ተዋዶ ያለበት እስላም ክርስቲያኑ
ተዘነጋሽ እንዴ? ኢትዮጵያ መሆኑ!
ሸገር አዲስ አ'ባ አንች ያለሽበት
ራጉኤል አይደል ወይ? የአንዋር ጎረቤት!"

ሲል ቴዎድሮስ ካሳሁን ገርማሞ _ቴዲ አፍሮ ያዜመላት ነጭ፣ጥቁር፣አረብ፣አበሻ፣ሕንድ፣አርመን ወይ ባላገር ገዝቶ የሚሸጥባት፤ሰው በሰው ላይ፣ቤት በቤት ላይ፣ሸቀጥ በሸቀጥ ላይ ተደራርቦ የሚኖርባት "ምናለሽ?"ሲሏት"ሁሉም"የምትል የሁሉ አደባባይ ናት።

መርካቶ ሰፊ ነው።ውቅያኖስ! ጣሪያቸው አፈር በለበሱ ቤቶች ውስጥ ድንቅ የእጅ ጥበብ፣ምትሃት የሚመስል ትጋት አለ።

ልብ ያለው ሁሉ እኒያን ለፍቶ አዳሪ ኢትዮጵያዊያን በዘመናዊ መሳሪያ ደግፎ ከጥበባቸው ቢቋደስ አገር የሚሰራ አቅም አላቸው።ሥራቸው አድካሚ፣ገቢያቸው መናኛ፣ለአገር ምጣኔ ሃብት ያላቸው ድርሻ የማይተካ ነውና ይደገፉ፣ይታገዙ እንላለን።

ዛሬ የደረሰባቸው አደጋም የዚሁ ችግራቸው ቅጥያ ነው!

እዚህ ቤት

21 Oct, 17:17


የ"አዲመራ" ነገር

ያሬድ ነጉ ትናንትና ሚለን ኃይሉ ሥልክ እንደዘጋችበት ነገረን።ኤርትራም በኢትዮጵያ ላይ ሥልክ ዘግታለች።"አዲመራ"አከተመለት።

አዲስ አበባ ከተማ ሰሚት አካባቢ 20 ሜትር የሚባል ሰፈር አለ።እዚያ አንድ ኤርትራዊ ጠጉር አስተካካይ ደንበኛ ነበሩኝ።ኢትዮጵያን ዞረው እንደሚያውቋት ነግረውኛል።የጠጉር ቤታቸው ሥም "አዲመራ" ነበር።

ጋሸ ከሰሞኑ ተሰውረውብኛል።የአዲስ አበባ እና አሥመራ ግንኙነትም ቀዝቅዟል።የያሬድ ነጉ አዲመራ ዘፈንም ሰሚ የለውም።በሚለን ኃይሉ እና በያሬድ ነጉ መካከል የቀዘቀዘው ፍቅር ከኢሳይያስ አፈወርቂ እና ዐቢይ አሕመድ ፍቅር መቀዝቀዝ ጋር እንደሚገናኝ መጠርጠርም ይበጃል።

ያኔ ያሬድ ነጉ፦
"መቼ ይደክመኛል ለመመላለሱ?
ትኬቱን ልቁረጠው ሳይሞላ አውቶብሱ"


ብሎ ዘፍኖ ነበር።

ከአዲስ አበባ ተነስቶ አሥመራ የደረሰ አውቶብስ ዐየሁ ያለ አልገጠመኝም።የሰማዩ ባቡር የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሄው የአሥመራ በረራውን ተከልክሏል።

የእኛ ነገር ያሳዝናል።ነገራችን ሁሉ"የሞኝ ለቅሶ መልሶ መላልሶ"ሆኖብናል።

አሁን "ዳሕላክ ላይ ልሥራ ቤቴን" የሚለው የቴዲ አፍሮ ዘፈን "አዲመራ"ን ተክቶታል።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

21 Oct, 10:15


እጅግአየሁ ሺባባው ከደረጀ ኃይሌ ጋር

"...የ28 ዓመት ኮረዳ ናት።ገና ለጋ...ገና ቀንበጥ...ገና እሸት'...አዎ እንዲያ ናት ጂጂ ማለት።ተወልዳ ያደገችው ጎጃም ነው።ለያውም የጎጃም ባላገር ሆና...የጎጃም ሳዱሌ ተሰኝታ።"

ደረጀ ኃይሌ(የእኔው ባለውለታ፣ደጉ፣የዋሁ ቅኑ) ከእኔዋ የጥበብ ፈርጥ እጅጋየሁ ሺባባው ጋር ያደረገው የቃል መጠይቅ በ1994 ዓ.ም ኢትጶጵ መጽሔት ላይ ሲታተም በመግቢያው ያለላት ነው።

ሌላ አምሳ ዓመት ለልዕልታችን እመኛለሁ

@Gazetaw

እዚህ ቤት

20 Oct, 18:55


በነገራችን ላይ👇

1.ጌዲዮን ጢሞትዮስ (ዶ/ር)_ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር (የሃና ባለቤት)

2. ሀና አርዓያ ሥላሴ_ፍትሕ ሚኒስትር (የጌዲዮን ባለቤት)

3. ዮዳሄ አርዓያ ሥላሴ_የብሔራዊ መታወቂያ ዲጂታል ፕሮጀክት ዋና ዳይሬክተር (የሃና ወንድም)



"የአንድ አፈር አፈሮች" እንዲል ገጣሚ ኤፍሬም ስዩም፥ የአንድ ቤት … ናቸው

እዚህ ቤት

20 Oct, 18:06


የሰንበት የመጽሐፍ ግብዣ

"ቢቡኝ ከሚባለው አገር የቢቡኝ ዘሮች አገራቸውን ሥለወደዱ ከወንድሞቻቸው ተለይተው ዜጋ ሆነው በገባርነት ይኖራሉ።...ቢቡኝ የመለሎ ልጅ ነው።ከተማውም ድጓ ጽዮን ነው።የአጎቱ የሰለሎ ልጅ አረፋ በቢቡኝ ወረዳ የወንዝ/ቀበሌ ሥም ሆኖ ይገኛል።"

ጥንታዊው የጎጃም ታሪክ፣አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ፣ገጽ 249 እና 264

መጽሐፉ፦

ሀ.ደብረ ማርቆስ ደርሷል።

ሁ.ባሕርዳር (አዳነ መጽሐፍ መደብር ዘንባባ ሕንፃ ሥር) ይገኛል።

ሂ.አዲስ አበባ ላላችሁ፦

1.ጸሐፊውን በ 0913308226  አግኙት።

2.አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ ባለቤት በሆነበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳቡ 1000211733296 ላይ የመጽሐፉን ዋጋ(ስድስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) አስገቡለት።

ወዲያውኑ መጽሐፉ እንዲደርሳችሁ ይደረጋል ብሏል።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

20 Oct, 14:34


"በላያ በላያ በላያ በላያ
ትምጣ የአገሬ ልጅ
የወንዜ ቡቃያ...!"

እዚህ ቤት

18 Oct, 17:53


ላኩለት ለዚህ ሰው🤔

"ምነው በቅዳሜ ምነው በእሁድ ቢያርሱ
ከባለ ጠጋ ቤት ከሚመላለሱ ?

ደርሶ ማንጎራጎር ልማዱ ነው ድሃ
እየቀዘቀዘው የሚጠጣው ውሃ

አርሶ መራብና ተኩሶ መሳት
የሚያንገበግበው እንደ እግር እሳት!
"

@Gazetaw

እዚህ ቤት

18 Oct, 08:51


"የጎጃም ታሪክ ማለት የኢትዮጵያ፣የዓለም ታሪክ መነሻ...ነው።"ጥንታዊው የጎጃም ታሪክ፣አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ፣ገጽ-32

መጽሐፉ፦

ሀ.ደብረ ማርቆስ ደርሷል።

ሁ.ባሕርዳር (አዳነ መጽሐፍ መደብር ዘንባባ ሕንፃ ሥር) ይገኛል።

ሂ.አዲስ አበባ ላላችሁ፦

1.ጸሐፊውን በ0713361288  አግኙት።

2.አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ ባለቤት በሆነበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳቡ 1000211733296 ላይ የመጽሐፉን ዋጋ(ስድስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) አስገቡለት።

ወዲያውኑ መጽሐፉ እንዲደርሳችሁ ይደረጋል ብሏል።

@Gazetaw

እዚህ ቤት

18 Oct, 06:58


ጥንታዊው የጎጃም ታሪክ

አዲስ መጽሐፍ ነው።ጸሐፊው አበረአረፈዐይኔ አዳሙ ይባላል።የጎጃምን ታሪክ ከአዳም እስከ በላይ ዘለቀ ዘመን ጽፎታል።

የመጀመሪያውን ክፍል መጽሐፍ ለመግዛት፦

1.ጸሐፊውን በ0713361288 ያግኙት።

2.አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ ባለቤት በሆነበት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳቡ 1000211733296 ላይ የመጽሐፉን ዋጋ(ስድስት መቶ የኢትዮጵያ ብር) ያስገቡለት።

ማስታወቂያው እንደ አስፈላጊነቱ ይደጋገማል።

@Gazetaw