Sankofa_Readers_Association @sankofabooks Channel on Telegram

Sankofa_Readers_Association

@sankofabooks


Read, Change, Share
እናንብብ፤ እንለወጥ፤ እናካፍል

This is the channel of sankofa readers association working with the motive "reading leads to change then to nearest perfection in doing art."comment is welcomed
Contact: @Poco_L0c0 @markrylos
https://t.me/sankofab

Sankofa_Readers_Association (English)

Are you a book lover looking for a community that shares your passion for reading and making a difference? Look no further than Sankofa Readers Association! This Telegram channel, with the username @sankofabooks, is dedicated to promoting the power of reading, encouraging change, and sharing knowledge among its members. Sankofa Readers Association believes in the transformative power of literature. Their motto, 'read, change, share', reflects their belief that through reading, individuals can bring about positive changes in themselves and their communities. The channel is a platform for book lovers to come together, discuss literary works, and inspire each other to make a difference through the written word. Whether you're a seasoned reader or just starting to explore the world of books, Sankofa Readers Association welcomes everyone with open arms. The channel is a space for individuals to engage in meaningful conversations about literature, art, and the impact they can have on society. Members are encouraged to share their thoughts, recommendations, and insights with fellow readers, fostering a sense of community and camaraderie. At Sankofa Readers Association, they believe that reading is not just a hobby but a powerful tool for personal growth and social change. By engaging with diverse literary works, members can broaden their perspectives, challenge their beliefs, and ultimately become more empathetic and understanding individuals. If you're looking to connect with like-minded individuals who share your love for reading and desire to make a difference, Sankofa Readers Association is the perfect place for you. Join their Telegram channel today and be part of a community that is dedicated to using the written word as a catalyst for positive change. For more information and to join the discussion, you can contact @Poco_L0c0 or @markrylos. Come be a part of Sankofa Readers Association and embark on a journey of reading, change, and shared knowledge!

Sankofa_Readers_Association

21 Nov, 18:56


ሙዚቃ ሙዚቃ
ባልኖርነው ሲቃ አሳቃ አሸማቃ
ባላየነው ፌሽታ ሲያሻት አሳስቃ
ከልባችን ገብታ መንጥቃ እፍ አርጋ
በራ ታከንፋለች ወዳጇን ከሷጋ

ኑ ስለሙዚቃ በጥበብ ቋንቋ በጥበብ ቦታ ጥበብ ሽመታ ውለን ስለሙዚቃ እንለፍፍ ኑ ስለሙዚቃ በሙዚቃ እንክነፍ
በሰውኛ ስሜት በሙዚቃ ቋንቋ አብረን እንንሳፈፍ
ቦታ አይጠየቅም። ሰዓት ግን አርብ 1 ስዓት ላይ በጥበብ መድረካችን በሳንኮፋ እንገናኝ።

#አርብን በሳንኮፋ

Sankofa_Readers_Association

11 Nov, 13:12


"Each generation must, out of relative obscurity, discover its mission, fulfill it, or betray it." -Franz Fanon

ጭረት ተመልሳለች

ሁሉም ነገር በመጫር ይጀምራል!



@sankofabooks

Sankofa_Readers_Association

07 Nov, 14:21


ተዋበችና ካሳ

“ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል" የሚለው ተረት እንደ ተዋበችና ካሳ ላሉት የሚነገርላቸው ነው፡፡

ተዋበች የካሳ አይነት ሰው ነበረች፡፡ ከመዋረድ መሞትን የምትመርጥ! ደርቡሾች ማርከዋት ክብርናዋን ሊደፍሩ ሲሉ፣ የደርቡሽ ጩቤ ጫፉ ላይ ገዳይ መርዝ እንዳለው በማወቋ፣ የአንዱን ጩቤ ሳያስበው በፍጥነት መዘዘችና የገዛ አናቷን ወጋችው፡፡ ካሳ በጊዜ ደርሶ ባያስጥላት ደምዋን አስመጥጦ መርዙን ባያስወጣላት ኖሮ ሞታ ነበር፡፡ ውርደትን ከመቅመስ ይልቅ ሞትን መቅመስ መምረጧን ሲያይ ካሳ ምንኛ አደነቃት ይሆን? ልዩ ውበትን ከልዩ ሰብአዊ ኩራት አጣምሮ የሰጣት ሴት! ያኔ ሳይሆን አይቀርም የሷ ፍቅር ያደረበት፡፡ እንደዚያ ሳታስበው ደርሶላት ከውርደቱም ከሞቱም ያስጣላትን ጀግና እሷም በዚያች ሰአት ልትወደው ሳትጀምር አልቀረችም፡፡

ተዋበች እንደ ካሳ ቆራጥ ነበረች፡፡ ካገባች በኋላ አያቷ እቴጌ መነን ክብሩን ስለነኩባት እንዲሸፍት ሳታደፋፍረው ሳትገፋፋው አልቀረችም፡፡ አብራውም ሸፈተች፡፡ እስከእለተ ሞቷ ድረስም፧ እንደ ህሊናው ወይም እንደ ጥላው አይነት ምንም ቢሰራና የትም ቢሄድ ተለይታው የማታውቅ የፍቅር ቁራኛው ሆነች፡፡

ተዋበች ለካሳ የህልሙም የእድሉም ተካፋይ የሆነች ውብ ሚስት ነበረች፡፡ ምግቡን እሷ ራሷ ነበረች የምታበስልለት፡፡ ከውጭ እንደመጣ በተልባ ፈትፍታ ታጎርሰዋለች፡፡ በሰላም ጊዜ ሆነ በዘመቻ ተለይታው አታውቅም፡፡ እና ወደ ወሎ ዘምተው ሳለ ተዋበች በንዳድ (ወባ) በሽታ ሞተች፡፡ ምን ያህል እንዳዘነ፤ ምን ያህል እንዳጎደለችው ከመሞከር ይልቅ ዝም ማለት ይመረጣል፡፡ አስክሬኗን ወደ መቃብር ለመወሰድ
ሲከተል ካወረዳቸው የለቅሶ ቅኔዎች በጣም የሚታወቀው ተዋበች ለካሳ ምን እንደነበረች ይጠቁመናል፡፡

"እጅግ ስራ አዋቂ ትናንትና ሞተች
መድሀኒቱን ምሳ ታበላኝ ነበረች፡፡
እስቲ ጠይቁልኝ ርቃ ሳትሄድ
እቴጌ ተዋበች ሚስት ናት ገረድ?”

ሚስቱም፤ እናቱም፤ ገረዱም፤ ጓደኛውም፤ ፍቅረኛውም የነበረችው ተዋበች ከሞተችበት በኋላ ነው ካሳ የተለወጠው፡፡ ምን አለ ካሳ፣ ተዋበች ምንኛ ታላቅ ሰው እንደነበረች ለኛ ሊያመለክተን የሚችል?

“እግዚአብሄር ሲወድህ ሁለት ነገር ይሰጥሀል፡፡ ከሰዎች መርጦ መሪ አለቃ ያደርግሀል፡፡ ለዚህ ስራ አብራህ የምትሰለፍ ታማኝ ሚስትም ይሰጥሀል፡፡ እኔንም ይወደኝ ነበረ፤ አሁን ግን ተጣልቶኛል፡፡" | አፄ ቴዎድሮስ

ምንጭ : እነሆ ጀግና| ስብሐት ገ/እግዚአብሔር

#ተዋበች
#እናንብብ፣እንለወጥ፣ እናካፍል
#ሳንኮፋ

Sankofa_Readers_Association

05 Nov, 11:21


links / via

Sankofa_Readers_Association

05 Nov, 11:21


ፅጌሬዳ?

አቤት

ግርማ በየነን ታውቂዋለሽ?

አዋ

ዕፀገነት የምትባል ፌመስ ሚስት ነበረችው።

እሺ

ፌመስ ስልሽ... ከሞተች በኋላ ነው። ሰውየው ስለ እሷ አውርቶ አይጠግብም። መድረክ ላይ ትንሽ ክፍተት ካገኘ "ዕፀገነት..." ብሎ ወሬ ይጀምራል።

እሺ

እኔም ያወኳት እንደዛ ነው። የሞተችው የዛሬ ሰላሳ ምናምን አመት ገደማ ነው። እና ስትሞትበት ፥ ዘፈን እርግፍ አድረጐ አቆመ። ሁሉንም ነገር አቆመ ለነገሩ። ከሰው ተቆራርጦ ፥ ውጭ ሀገር ጋዝ ስቴሽን ይሰራ ነበር። ለሰላሳ ምናምን አመት ይኸውልሽ... ብቻውን። እና አንድ ቀን ነው ድንገት ፥ "ግርማ እኮ እዚህ ቦታ ታየ" ተብሎ እነ ፍራንሲስ(ኢትዮፒክስ) አፈላልገው አገኙት። ድሮ የተሰሩ ድንቅ ድንቅ ዘፈኖቹን እንዲቀዳላቸው አግባቡት። አልበሙም በጥራት ወጣ። እሱም ዳግም መዝፈን ጀመረ ምናምን

እሺ ግን... ምንድነው ይሄ ሁሉ ኢንፎርሜሽን አሁን?

እኮ አይገርምሽም? ሰውየው እስካሁን እንደቆረበ ነው። ጅጅት ብሎ ተቀምጦ እየዘፈነ "ዕፀገነት" ይላል። ጭራሽ ባለፈው ያየሁት ቪዲዮ ላይማ "ፍቅረኞቻችሁ በህይወት ያሉላችሁ አመስግኑ። የሞቱባችሁም ግን እንዳሉ አድርጋችሁ ፥ አጠገባችሁ እንዳሉ አምናችሁ መኖር ትችላላችሁ። እንችላለን።" የሚል ንግግር ሰጠ።

እና እሺ?

ይኸውልሽ ፅጌሬዳ... እኔ እንደዚህ አልችልም።

የራስህ ጉዳይ ነው። እኔ የምሞት መስሎሃል!

Sankofa_Readers_Association

27 Oct, 19:48


**"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ።"*,

ቴክስት ገባልኝ

ማሂ ናት
"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ " የሚለው ብቻ በጉልህ ታየኝ ።

በቀደም "አብረኸኝ ሁን በጣም ...በጣም ከፍቶኛል" ብላኝ ያለሁበትን ጠቆምኳት ያለሁበት መጣች ። እየጠጣን፣ ትንሽ ፈገግ ቁዝምም እያለች፣ ነፍ ነገር እየቀደድን እየተጫወትን አመሸን ።

ወደ ቤቷ መሄድ እንደማትፈልግ ገባኝ ፣ ራይድ ደወልኩ፣ መነሻ እና መድረሻ ተናገርኩ ቤቴ ወሰደን ።

ቆሎ ከኮመዲኖ፣ ከፍሪጅ ቢራ አቀርብኩላት ። ቆሎ እየቆረጠምን፣ ቢራ እየጠጣን ቢጃማ አውጥቼ ሰጠኋት እና ሱቅ እቃ ገዝቼ መጣው ብዬ ወጣሁ።

ትንሽ የማልገዛውን እቃ እየጠየኩ ቆይቼ ተመለስኩ

ቢጃማዬን ለብሳ ቆየችኝ ።

ቢጃማዬን ገላዋን አስገብታበት አሳምራዋለች ። መሞናደሏን ቢጃማዬ አሳበቀባት ። አይኗ፣ ሁኔታዋ፣ አወራሯ ሁሉ ነገሯ መሞናደሏን ከልሎታል ።

ሰው ስሜትን ሳያነብ ስሜታዊ ከሆነ ምኑ ጋር ነው ስውነቱ ?

ትንሽ እንደተጨዋወትን የአልጋዬን አንሶላ ገልጠን ገባን ። አቀፍኳት ሳቅፋት ሰውነቷን ኩምትር እንዳደረገች  ነበር ።

መሳቀቋ ገብቶኛል፤ ግን እንዳልገባኝ ሆኜ ግንባሯን ሳምኩት።
አሳሳሜ  'አትሳቀቂ  ይሄው ትከሻዬ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር ግንባሯን በታላቅነት በአለሁልሽ ነው የሳምኳት።

መልዕክቴ  በትክክል ይድረስ አይደረሳት አላወኩም ።

ሲያጉረመርም የነበረው  ዶፍ ዝናብ ዘነበ
አቀፍኳት ፣ በረዳት ወይ አመነችኝ  መሰል በደንብ ጥግት ብላብኝ ታቀፈች ።

"ለምንድን ነው የምወደው ነገር ሳፈጥበት ገሸሽ የሚለው ?፣ የምጠላው ሳይቀር እኮ መውደድ ስጀምር ጥላ ያጠላበታል ።  እያጡ ማዘን እኮ  ደከመኝ።
እንደ እናቶች ተረግሜ  ፣ተደግሞብኝ  ወይ ደግሞ አይነጥላ ይሆን? ለማለት ጫፍ ላይ እየደረስኩ ነው። "

በለሆሳስ ስታወራ በጨለማው ውስጥ ኩልል ያለ እንባ ያፈሰሰች መስሎኛል ። ይሄን የቅሬታ ድምፅ ከእንባ ውጪ መተንፈስ የሚቻል አልመሰለኝም ።

"አይዞሽ ሁሉም በግዜው ይስተካከላል። ሳንካ የሆነብሽ ሁሉ ወደ ጥሩ ይለወጣል ። ትላንት የከበደን ስንት ነገር ቀሎልን የለ?"

የበለጠ አቀፍኳት ፤ ደረቴ ላይ ተኛች ።

የሆነች ነፍስ አምናኝ የተጠለለችብኝ መሰለኝ ። ሙሉ ሰው የሆንኩ መሰለኝ ።  ስጋዬን ችላ ማለት የምችል አይነት  ስሜት ተሰማኝ ደረቴ ላይ እንደተኛች በደስታ ፈገግ አልኩ ።

እንዳቀፍኳት እንደታቀፈችኝ  ለሊት ላይ ነቃሁ፣ አየኋት እንቅልፍ ውስጥ ጭልጥ ብላለች። አምናኝ ባዶ ክፍል ራሷን ገላዬ ላይ ጥላ  ተኝታለች ። ደስስ  እንዳለኝ ተኛሁ።

ጠዋት ቁርስ በላን እና ሄደች።  አስራ እንድ ሰአት ከሃያ ቴክስት ላከችልኝ :

"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ።
መሄጃ አጥቼ መሄጃ ስለሆንከኝ አመሰግናለሁ።"

ቴክስቱን እንዳየሁት አለቀስኩ ። ለመዋሰብ ታግያት  ቢሆን ኖሮ እንዴት ነበር የሚሰማት? ብዬ አሰብኩ።

አባቴ   እግሩ በተቆረጠበት ሰዓት ፣
ስራ በተባረረበት ሰዓት፣
ንብረቱን በተቀማበት ሰዓት፣

የዘመዶቹን የጓደኞቹን የብዙ ሰው ስም እየጠራ   "ብቻዬን ተውኝ: ብቻዬን ተውኝ"  ብቻውን መተውን እየተናዘዘ  በዛው አእምሮ እንደታወከ ስላስታወሰቺኝ ይሆን

ብቻ መተው ማለት ትርጉሙ ገብቶኝ ይሆን ?
ከብዙ ግዜ በኃላ ቃሉን ስለሰማሁት ይሆን?
የአባቴ ሁኔታ አይኔ ላይ ስለመጣብኝ ይሆን?

ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ የሚለው 'message' አስለቀሰኝ ።

ጌታዬን ወደ ሰማይ አንጋጥጬ አመሰገንኩት ።

"መሸሸጊያ ያጣች ድክም ያላትን ነፍስ : በኔ ምክንያት  የበለጠ እንዳታዝን ስላደረከኝ አመሰግናለሁ ጌታዬ።"
         Adhanom Mitiku

Sankofa_Readers_Association

12 Oct, 10:54


የዘንድሮውን በሥነ ጽሑፍ ዘርፍ የኖቤል ሽልማት የ53 ዓመቷ "ሃን ካንግ"(Han kang) ወስዳዋለች ። በሽልማቱም  ሀገሯ ደቡብ ኮርያን ለመጀመሪያ ጊዜ በሥነጽሑፍ ዘርፍ ስሟን ማጻፍ ችላለች።
"The vegeterian, the white book, human acts and Greek lessons" የተባሉ መጽሀፍት ያሏት ሲሆን የሽልማት ኮሚቴው ያሸነፈችበትን ምክንያት እንዲህ ሲል አስፍሮላታል "for her intense poetic prose that confronts historical traumans and exposes the fragility ofhuman life"

ሀገራችንም አንድ ሳያስፈልጋት አይቀርምና እያነበብን፣ እያሰብንና እየጻፍን ትላለች ሳንኮፋ።


              "54NK0F4"