ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት @finottebiirhan Channel on Telegram

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

@finottebiirhan


የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለማንኛውም ጥያቄ
@Finotebrhan

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት (Amharic)

የአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት ለማንኛውም ጥያቄ በልዩ በዓላት፣ የህይወት ቤተክርስቲያን እና ሰንበት ትምህርት ላለው ቤተክርስቲያን በፊኖትህ ይሁን። ምክንያቱም ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት፣ ህይወት ቤተክርስቲያን፣ ትምህርት እና አገልግሎቶች ከመሆን በቀላሉ ማድረግ የሚሻል ነው። እናትህን ለሕይወት መንገደቅደም እና መናገሩን ለግንባታ ሃይሌ እንዲሰጡ ሊሰጥ ነው። ስለዚህም ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት @Finotebrhan ለአስተማሪ ተጠቃሚነትን እና መሹን በትክክል ታማኝ ፎቶዎች እንድናገኝ መረጃዎችን እንዲሁም ለአሁን ሊቀርብ እና ሊከብሩ ያሉ ፎቶዎችን በይዞና ይመልከቱ።

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

03 Dec, 06:20


"የንስሐ ልጆች ቀን" መንፈሳዊ ጉባኤ
በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን
ኅዳር 29 ቀን 2017ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

01 Dec, 09:02


" የ ፳፻፲፯ ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የአጋማሽ (Mid) ፈተና ተሰጠ። "

በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥርዓተ ትምህርት የዓመቱ እቅድ መሠረት የ ፳፻፲፯ ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት የአጋማሽ (Mid) ፈተና ኅዳር ፳፩ እና ፳፪ ለመስጠት ታቅዶ እንደነበር ይታወሳል፤
በአቃቂ መንበረ ሕይወት መድኃኔዓለም ቤ/ክ ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤትም በእቅዱ መሠረት የመደበኛ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት የትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት አጋማሽ ፈተና ዛሬ ኅዳር ፳፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ከ ፩ኛ እስከ ፲፪ኛ ክፍል በእሑድ መርሐግብር ለሚማሩ መደበኛ ተማሪዎች ተሰጥቷል።
በቀጣይም የትምህርቱ መርሐግብር በመደበኛው መንገድ የሚቀጥል መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

ማስታወሻ!
በቅዳሜ መርሐግብር የሚማሩ ተማሪዎች አጋማሽ ፈተና በቀጣይ የሚከናወን መሆኑን እንገልጻለን።

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት የተከታታይ ትምህርት ንዑስ ክፍል።

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

30 Nov, 18:31


በዓመቱ የትምህርት እቅድ መሠረት ነገ እሑድ የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት አጋማሽ (Mid) ፈተና መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም በመደበኛው #የእሑድ መርሐግብር የምትማሩ ከ 1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች ከዚህ በላይ በተቀመጠው መርሐግብር መሠረት #ፈተናውን_የምትፈተኑ መሆኑን አውቃችሁ በሰዓቱ እንድትገኙ በማለት መልእክታችንን እናስተላልፋለን።

ማሳሰቢያ:- ለፈተናው ስትመጡ አስፈላጊውን የፈተና ሥነምግባር ማሟላታችሁን እንዳትረሱ።

መልእክቱን ለሌሎች ያጋሩ!

የተከታታይ ትምሀርት ንዑስ ክፍል

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

30 Nov, 15:07


የኅዳር ወር የሰሌዳ መጽሔት

የኅትመት ዝግጅት እና ስርጭት ንዑስ ክፍል

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

29 Nov, 19:10


ኅዳር 21  በቅዳሴ ቅድመ ወንጌል የሚባል  ምስባክ

የአብነት እና አርድእት ንዑስ ክፍል

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

27 Nov, 03:31


መንፈሳዊ ጉዞ

ዓመታዊው የታኅሳስ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊውን ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በሰንበት ትምህርት ቤታችን ጉዞ ክፍል ወደ ታላቁ ቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ጉዞ ተዘጋጅቷል ።

ከወዲሁ እንድትመዘገቡ እንጋብዛለን !!

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Nov, 17:03


የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላት ያላቸውን ሙያ ለሰንበት ትምህርት ቤቱ አገልግሎት ለመጠቀም ያለመ መደበኛ የሰንበት ትምህርት ቤቱ አባላትን ማዕከል ያደረገ " የበጎ ፈቃድ ሙያዊ አገልግሎት ለሰንበት ትምህርት ቤት(ለቤተክርስቲያን)" በሚል የአቅም ማጎልበቻ ትምህርታዊ ሥልጠና በሰንበት ት/ቤቱ ጽ/ቤት አማካኝነት በረድኤተ እግዚአብሔር ዛሬ ተከናወነ።

የፍኖተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት ጽ/ቤት

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

24 Nov, 04:25


ጾመ ነቢያት        


[ የጾመ ነብያት ምስጢር ምንድነው ? ]   

ጾመ ነቢያት [ የገና ጾም ] ከልደት አስቀድሞ የሚጾም ጾም ነው ከህዳር ፲፭ [ 15 ] ጀምሮ ለ ፵፫ [43] ቀናት የሚጾም ሲሆን ፋሲካው [ ፍቺው ] በልደት በዓል ነው ይህም ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ቅዱሳንና ምዕመናን ጾመውታል፡፡

ጾመ ነብያት ስያሜውን ያገኘው ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት ነው በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምስጢር ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ  የረቀቀው ገዝፎ ጎልቶ እየተመለከቱ ትንቢት ተናገሩ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ጾሙ ጸለዩ፡፡

ነቢያት ከእመቤታችን ስለ መወለዱ ፥ ወደ ግብፅ ስለ መሰደዱ ፥ በባሕረ ዮርዳኖስ ስለ መጠመቁ ፥ ብርሃን በሆነው ትምህርተ ወንጌል ጨለማውን ዓለም ስለ ማብራቱ ፥ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ ፥ ስለ ትንሣኤው ፥ ስለ ዕርገቱና ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፡፡

ለአዳም የተሠጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን ተማፀኑትም እንጂ በየዘመናቸው ፦ "አንሥእ ኃይልከ ፈኑ እዴከ" እያሉ ጮኹ በጾምና በጸሎት ተወስነውም እግዚአብሔር ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት ፣ በሳምንታት ፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ በ፬፵፮ ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋን ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡

ነቢያት ተስፋው በዘመናቸው ተፈጽሞ በዓይነ ሥጋ ለማየት ባይችሉም እግዚአብሔር ፦ "አያደርገውን አይናገር የተናገረውን አያስቀር" ብለው አምነው ከወዲሁ ተደሰቱ ለዘመነ ሥጋዌ ቅርብ የነበሩ እነ ነቢዩ ኢሳይያስ ጾሙ እንዴት መፈጸም እንዳለበት ተናግረዋልም [ኢሳ.፶፰፥፩] በመሆኑም በጌታ ልደት ትንቢተ ነቢያት ስለተፈጸመበት ይህ ጾም "የነቢያት ጾም" ይባላል የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት ስለሆነም "ጾመ ስብከት" ይባላል፡፡

ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡ እነርሱም፦

† ፩. [    ጾመ አዳም   ]

አዳም ዕፀ በለስን በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ በፈጸመው በደል አዝኖ  ተክዞ  አለቀሰ [እንባ ቢያልቅበት እዥ እስከሚያፈስ  እዥ ቢያልቅበት ደም በዓይኑ እስከሚፈስና ዓይኑ ይቡስ ወይም ደረቅ እስከሚሆን ድረስ አለቀሰ] ጾመ ጸለየ ከልብ የሆነ ጸጸቱን፣ ዕንባውን፣ በራሱ መፍረዱንም እግዚአብሔር አይቶ ተስፋ ድኅነት ሰጠው፡፡ "ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ  በደጅህ ድኼ  በዕፀ መስቀል ተሰቅዬ ሞቼ አድንሃለሁ" የሚል ነው፡፡ [ገላ. ፬፥፬፣ መጽ.ቀሌምንጦስ] ስለዚህ ጾሙ የተሰጠው ተስፋ  የተቆጠረው ሱባኤ ስለተፈጸመበት "ጾመ አዳም" ይባላል፡፡

† ፪. [   ጾመ ነቢያት   ]

ነቢያትም የምሥጢረ ሥጋዌ ነገር ተገለጦ ስለታያቸው ክርስቶስ ለሰው ልጅ የሚከፍለውን የፍቅር ዋጋ በትንቢት ተመልክተው ጾመውታልና ጾመ ነቢያት ይባላል፡፡ ይህ ጾም ከአባታችን አዳም እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ የተነሱ አበውና እናቶች ድኅነትንና ረድኤትን ሲሹ የጾሙት ጾም ነው:: በተለይ አባታችን አዳም  ቅዱስ ሙሴ ቅዱስ ኤልያስ  ቅዱስ ዳንኤልና ቅዱስ ዳዊት በጾማቸው የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው:: [ዘዳ.፱፥፲፱ ፣ ነገ.፲፱፥፰ ፣ ዳን.፱፥፫ መዝ.፷፰፥፲ ፻፰፥፳፬] ቅዱሳን ነቢያት በጭንቅ በመከራ ሆነው የጾሙት ጾም ወደ መንበረ ጸባኦት ደርሶ ወልድን ከዙፋኑ ስቦታል ለሞትም አብቅቶታል::

† ፫.  [   ጾመ ሐዋርያት  ]

ሐዋርያት "ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጾመን እናከብራለን  ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብረዋለን?" ብለው ከልደተ ክርስቶስ በፊት ያሉትን ፵፫ ዕለታት ጾመዋልና፡፡

† ፬.  [   ጾመ ማርያም   ]

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር አምላክ ቅድስናዋን አይቶ በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ አምላክን ያለ ሰስሎተ ድንግልና በግብረ መንፈስ ቅዱስ ጸንሳ እንደምትወልደው ቢነግራትም የትሕትና እናት ናትና "ምን ሠርቼ የሰማይና ምድርን ፈጣሪ እችለዋለሁ?" ብላ ጌታን ከመውለዷ አስቀድማ ጾማለችና "ጾመ ማርያም" ይባላል፡፡

† ፭.  [   ጾመ ፊልጶስ   ]

ሐዋርያው ቅዱስ ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ እያስተማረ ሳለ በሰማዕትነት ሲሞት  አስክሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስክሬን እንዲገለጽላቸው ከኅዳር ፲፮ ጀምረው ጾመው በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስክሬን ተመልሶላቸዋል ነገር ግን አስከሬኑ ቢመለስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል፡፡

† ፮.  [   ጾመ ስብከት  ]

የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት  የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመ ስብከትም ይባላል፡፡

† ፯.  [   ጾመ ልደት   ]

የጾሙ መጨረሻ [ መፍቻ ] በዓለ ልደት ስለሆነ "ጾመ ልደት" ይባላል፡፡

በጾማችን በጸሎታችን - ስለ ቤተክርስቲያን ፥ ስለ ሀገር እና ስለ ሕዝብ በማሰብ በእንባ እራሳችንን ዝቅ በማድረግ እንጾም ዘንድ ይገባል፡፡


ወስብሐት ለእግዚአብሔር  ወለወላዲቱ ድንግል  ወለመስቀሉ ክቡር አሜን!
                   🔹〰️🔹〰️🔹〰️
   መገናኛ ብዙሃን ንዑስ ክፍል
@finotebrhan

ፍኖተ ብርሃን ሰንበት ትምህርት ቤት

23 Nov, 13:46


ኅዳር 15  በቅዳሴ ቅድመ ወንጌል የሚባል  ምስባክ

የአብነት እና አርድእት ንዑስ ክፍል