Ethiopost @ethiopianpostal Channel on Telegram

Ethiopost

@ethiopianpostal

130 years of legacy and service. Many more ahead providing modern solutions to modern problems.

Ethiopost (English)

Welcome to Ethiopost, the Telegram channel dedicated to the Ethiopian Postal Service. With a legacy of 130 years of service, Ethiopost has been a cornerstone of the country's communication infrastructure, connecting people from all corners of Ethiopia. The channel, with the username @ethiopianpostal, aims to provide modern solutions to modern problems, ensuring that the postal service continues to evolve with the changing times. Who is Ethiopost? Ethiopost is the national postal service of Ethiopia, established over a century ago to facilitate communication and commerce within the country and beyond. With a rich history and a commitment to excellence, Ethiopost has become a trusted name in the postal industry, serving millions of customers every year. What is Ethiopost? Ethiopost is not just a postal service; it is a symbol of national pride and unity. Through its network of post offices and distribution centers, Ethiopost ensures that letters and packages reach their destinations safely and efficiently. In addition to traditional mail services, Ethiopost also offers modern solutions such as e-commerce fulfillment, logistics, and digital communication services. Join us on Telegram at @ethiopianpostal to stay updated on the latest news, promotions, and events from Ethiopost. Whether you are a business looking for reliable shipping solutions or an individual sending a letter to a loved one, Ethiopost is here to meet your needs. With 130 years of legacy and service behind us, we look forward to many more years of serving the people of Ethiopia with dedication and innovation. Let Ethiopost be your trusted partner in communication and logistics.

Ethiopost

09 Jan, 11:43

የኢትዮጵያ ፖስታን የኢ-ኮሜርስ መደብር ወይም ፖስት ሾፕን መጠቀም የምርትዎን ተደራሽነት ለማስፋት ሁነኛ መፍትሄ ነው። የኢትዮጵያ ፖስታ ምርትዎን በድረ ገጻችን ላይ በማኖር ለደንበኞች በቀላሉ ስለ ምርቱ የሚገልጽ በፎቶ የታገዘ ዝርዝር መረጃ ስለሚሰጥ ለንግድዎ ቅልጥፍና እንዲሁም ቀላል ግብይት እንዲኖር ያስችላል።

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

07 Jan, 02:59

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ፖስታ ለክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም የገና በዓል እንዲሆንልዎ ይመኛል።

መልካም በዓል! መልካም ገና!
የኢትዮጵያ ፖስታ

#Ethiopost #ገና #christmass

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok |

Ethiopost

03 Jan, 05:12

ቢሮ ለመቀየር አስበዋል!

የኢትዮጵያ ፖስታ ለሁሉም የሎጂስቲክስ ፍላጎትዎ የታመነ አጋርዎ ነው። የሎጅስቲክስ አገልግሎቶቻችንን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት [email protected] ይጽፉልን።

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

01 Jan, 05:59

ስጋት አይግባዎ፣ የጥቅል መልዕክትዎን በአደራ ተቀበለን እናደርሳለን!

የጥቅል መልዕክትዎን ለመላክ ወይም ለመቀበል ከፈለጉ የሁልጊዜ ታማኝ ባለአደራ የሆነውን የኢትዮጵያ ፖስታን ይጠቀሙ።
ከ700 በላይ የሃገር ውስጥ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከ190 በላይ አለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት የኢትዮጵያ ፖስታ መልዕክትዎን በጥንቃቄ ተቀብሎ በአስተማማኝ ሁኔታ ያደርስልዎታል።

ለበለጠ መረጃ ወደ 8536 በነፃ ይደውሉ፣ ልናስተናግድዎ ዝግጁ ነን!
በቴሌግራም @etpccsbot ይፃፉልን።

ፖስታ ለሁሉም!
የኢትዮጵያ ፖስታ

#Ethiopost #Parcel

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

01 Jan, 04:17

🎇🎉 Ethiopost Wishes You a Happy New Year! 🎉🎇🎇

As we step into a brand-new year, Ethiopost extends warm wishes to all our customers worldwide. May 2025 bring you joy, prosperity, and endless opportunities to connect with your loved ones! 🌟

From delivering heartfelt messages to ensuring your packages reach every corner of the globe, Ethiopost is here to make every connection meaningful. 📦💌

Let’s make this year a journey of growth, success, and cherished memories together! Cheers to 2025! 🥂💖

#HappyNewYear #Welcome2024 #Ethiopost #GlobalConnections #SendingJoy

Ethiopost

30 Dec, 06:01

የኢትዮጵያ ፖስታ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

የኢትዮጵያ ፖስታ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር በከተማ መስተዳድሩ ስር በሚገኙ 36 ወረዳዎች የኢትዮጵያ ፖስታ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ተደራሽነታቸውን ለማስፋትና ለደንበኞቹ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ያስችለው ዘንድ ይህን የጋራ ስምምነት ተፈራርሟል።  በዚህ አብሮ የመስራት ስምምነት ውስጥ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ከመጨመር በዘለለ በየወረዳዎቹ ለተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ ዕድልም የሚፈጥር ነው።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር  ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ጋልጋሎ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ፖስታ ከሚሰጣቸው ዘርፋ ብዙ የአንድ መስኮት አገልግሎቶች ውስጥ የፋይዳ ብሔራዊ መታውቂያ ካርድ ስርጭትን ጨምሮ ሌሎች በቀላሉ ወደ ማሕበረሰቡ የሚደርሱ አገልግሎቶችን በተቀላጠፈና በዘመነ መልኩ ለማቅረብ የሚያስችል አብሮ የመስራት ስምምነት እንደሆነ አስረድተዋል።

#Ethiopost #MOU

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok |

Ethiopost

23 Dec, 12:29

ስለ አገልግሎቶቻችን ለማወቅ ፣ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት እንዲሁም ምቹ የመልዕክት መላኪያ መፍትሄዎችን ለማየት ethio.post ላይ ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ።

#Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

19 Dec, 12:44

ካርድዎን በአቅራቢያ ካለ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ ይውሰዱ!

በስልክዎ id.et ላይ ገብተው የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ህትመት ሲያዙ በመላው ኢትዮጵያ ከሚገኙ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች የሚቀርብዎትን ቅርንጫፍ መርጠው ማዘዝ ይችላሉ።

👉🏽በስልክዎ ከፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ የFAN ወይም FIN የ16 አኃዝ ቁጥር ከደረስዎ፣ ለካርድ ህትመት መመዝገብ ይችላሉ።

#Ethiopost #NID

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

18 Dec, 06:32

ለአስተማማኝ የመልዕክት ፍላጎትዎ የኢትዮጵያ ፖስታን ይጠቀሙ!

የደንበኞቹን ፍላጎት ለማሟላት ሁሌም የሚተጋው የኢትዮጵያ ፖስታ የመልዕክትዎን የጉዞ ደህንነት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ ለመከታተል ወደ https://globaltracktrace.ptc.post/gtt.web/ ይግቡ።
የመልዕክትዎን አሁናዊ የሚያረጋግጥ ቴክኖሎጂ ባቀረበው የኢትዮጵያ ፖስታ መልዕክትዎን ይላኩ፥ ይቀበሉ።

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost #Letter

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

12 Dec, 14:04

የኢትዮጵያን የቡና አፈላል ስነ-ስርዓት በቴምብሮች!

በዛሬው የፊላቴሊ ሐሙስ የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስርዓት የሚያሳዩ ቴምብሮችን እናያለን።
ከባህላዊው የኢትዮጵያ ቡና አፈላል ስነ ስርዓት ውስጥ የሚወዱት የቡና አፈላል ክፍል ምንድን ነው? የቡና ቁርሱን፣ እጣኑ ነው ወይስ ሌላ?
በጣም የሚወዱት የቡና ሥነ ሥርዓት የትኛውን ክፍል ነው? በሃሳብ መስጫው ላይ ሀሳብዎን ለእኛ ያካፍሉ።

እነዚህን እና ሌሎች ቴምብሮችን ለማየት https://www.pinterest.com/ethiopost ይጎብኙ።

#PhilatelyThursday #Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

12 Dec, 08:03

የኢትዮጵያ ፖስታ ከቶፓን ግራቪቲ ኢትዮጵያ ጋር አብሮ የመስራት ስምምነት ተፈራረመ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም National ID Ethiopia አካል የሆነውን የፋይዳ #ፋይዳ መታወቂያ ካርድ የአቅርቦት አቅምንና ስርዓትን ለማሳደግ የአጋርነት ስምምነቱን የኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና የቶፓን ግራቪቲ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ት ቃልኪዳን አረጋ ዛሬ የፈረሙ ሲሆን ይህ የሥራ ስምምነት ጥራቱን የጠበቀና አስተማማኝ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ ለነዋሪዎች በተቀላጠፈና በዘመነ መልኩ ለማቅረብ የሚያስችል ነው።
በተጨማሪም እያደገ የመጣውን የማህበረሰባችን የፋይዳ መታወቂያ ካርድ ፍላጎት ለማሟላትና ሁሉን አቀፍ እና አካታች የሆነውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዓላማ ለማሳካት የበኩላችንን አስተዋፅዖ ለማድረግ ያለንን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።
#Ethiopost #toppangravityethiopia #faydacard #nationalidprogram

Ethiopost

09 Dec, 07:40

የኢትዮጵያ ፖስታ የፈጣን መልእክት አገልግሎት

መልዕክቶችዎን ወደ አለምአቀፍ መዳረሻዎች ለመላክ እጅግ አስተማማኝ፣ ፈጣን እና በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ ነው።

የፈጣን መልዕክት ለመላክ ወይም ለመቀበል ፈልገው መረጃ ካሻዎት ወደ
☎️8536 ጥሪ ማዕከላችን በነጻ ይደውሉ ፥ ልናስተናግድዎ ሁሌም ዝግጁ ነን።

ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት በቴሌግራም @etpccsbot ያገኙናል።

#Ethiopost #EMS #Fast

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

05 Dec, 06:26

የ2024 የእስያ ፊላቴሊክ ኤግዚቢሽን በቻይና።

በሻንጋይ የተካሄደው የ2024 የኤዥያ አለም አቀፍ የቴምብር ኤግዚቢሽን የእስያን ባህል በፊላቴሊ ጥበብ የሚያሳይ ደማቅ በዓል ነበር። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች አስደናቂውን የቴምብር ማሳያ አድንቀዋል፣ እያንዳንዱም የቴምብር ስራዎች ታሪክን፣ ጥበብን እና ወግን ይናገራሉ።

ይህ በአይነቱ ልዩ በሆነውን የቴምብር ኤግዚቢሽን የዓለም የፊላቴሊ ልማት ማህበር (WADP) በፊላቴሊ ፈጠራ ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ እና አውደ ጥናት አዘጋጅቷል። የኢትዮጵያ ፖስታ በዚሁ ዝግጅት ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የፊላቴሊ ማዘመኛ መንገዶችን ለመቀየስ የሚረዳውን ልምድና እውቀት አግኝቷል።

ይህንንም ተከትሎ ቴክኖሎጂንና አዳዲስ አቀራረቦችን በመከተል የኢትዮጵያን ባህላዊ ቅርሶችንና ትውፊቶችን እንዲሁም ሀገራዊ ታላላቅ ኩነቶችን በፊላቴሊ ዘርፍ ለዓለም የማስተዋወቁን ተግባር የኢትዮጵያ ፖስታ አጠናክሮ ይቀጥላል።

#The2024AsianPhilatelicExhibition #PhilatelyInnovation #EthiopianCulture #StampExhibition2024 #CryptoStamps

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

03 Dec, 08:53

አስደሳች ዜና ከኢትዮጵያ ፖስታ!

ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ተመዝግበው ለህትመት በ id.et/cardprint ላይ ሲያዙ ለመደበኛ በ15 ቀን ይደርስ የነበረው ወደ ከ5 - 7 ቀን እንዲሁም ለአስቸኳይ በ5 ቀን ይደርስ የነበረው ወደ ከ2-3 ቀን ማጠሩን ስንገልጽ በደስታ ነው።

አሁኑኑ ይዘዙ ፥ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ካርድዎን በእጅዎ ይያዙ!

#Ethiopost #NID

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

27 Nov, 09:50

የኢትዮጵያ ፖስታ ለ110 የመንግስት እና 50 የግል ሆስፒታሎች ናሙናዎች ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ እንዲጓጓዙ በማድረግ የኢትዮጵያን የጤና ሴክተር ለማሳደግ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ከፍተኛ ጥንቃቄን በማድረግ የሚጓጓዙት እነዚህ ናሙናዎች በሰዓታቸው ለመድረሳቸው የኢትዮጵያ ፖስታ ዋስትና ነው

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

25 Nov, 06:22

መልካም የስራ ሳምንት!

በአዎንታዊነት የተሞላ ውጤታማ እና አስደሳች የስራ ሳምንት እንዲሆንልዎ የኢትዮጵያ ፖስታ ይመኛል!

የኢትዮጵያ ፖስታ

#Ethiopost #Happy_Week

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

21 Nov, 11:23

የኦፓል ቴምብሮች

በዛሬው የፊላቴሊ ሃሙስ የኢትዮጵያን አስደናቂ የኦፓል ውበት በቴምብሮች እናያለን!
ቴምብሮቹ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ውድ የከበሩ ድንጋዮችን የሚያወሱ ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል ፡- ቡናማ የከበረ ኦፓል፣ ሚልክ ኦፓል፣ ፋየር ኦፓል እና ቢጫ ውድ ኦፓል ይገኙበታል። እነዚህ ቴምብሮች የሀገራችንን የማዕድን ሀብት ለአለም በማስተዋወቅ ብርቱ ሚናን ተጫውተዋል።

እነዚህን እና ሌሎች ቴምብሮችን ለማየት https://www.pinterest.com/ethiopost ይጎብኙ።

#PhilatelyThursday #Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

19 Nov, 07:21

አነስተኛ ጥቅሎችን ወደ ተለያዩ መዳረሻዎች መላክ አስበዋል ?

በአነስተኛ ጥቅል መልእክት አገልግሎታችን እስከ 2 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ አነስተኛ ጥቅሎችን ከ700 በላይ የሃገር ውስጥ እንዲሁም ከ190 በላይ አለም አቀፍ መዳረሻዎች ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ በቀላሉ ይላኩ ፥ ይቀበሉ! አገልግሎታችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና የመድህን ሽፋንን ስለሚያካትት አስተማማኝነቱ አያሳስብም!

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost #smallpacket #affordable

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

15 Nov, 11:02

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ፖስታን ጎበኙ።

በክቡር አቶ እውነቱ አለነ የተመራ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ፖስታ ሁለንተናዊ ተሃድሶ እንዲሁም አጠቃላይ የስራ ክንውን ላይ ውይይት እና የመስክ ጉብኝት አካሂደዋል። በጉብኝታቸውም ወቅት በድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ ስለ ድርጅቱ አሁናዊ የስራ ክንውንና በቀጣይ ሊተገበሩ የታቀዱ የሪፎርም ሥራዎች ላይ ሰፊ ገለፃ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ፖስታ ዋናው መስሪያ ቤት የተሰሩ የሕንጻ እድሳት ስራዎችን ፣ የህጻናት ማቆያ ፣ ከጥሪ ማእከል ፣ ከመልእክት መቀበል እስከ እደላ ያሉ የኦፕሬሽን ስራዎችን ከሙያዊ ማብራሪያ ጋር ጎብኝተዋል። ከዋናው መስሪያ ቤት በተጨማሪም በአራት ኪሎ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤት በመገኘት የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደትን እና ሌሎች በቅርንጫፍ ፖስታ ቤቱ የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

የአገልግሎቶቻችንን ምህዳር እና ጥራት በማሳደግ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚነት እየሰራን ባለንበት በዚህ ወቅት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን እያደረጋችሁልን ስላለው ድጋፍ እናመሰግናለን!

#Ethiopost  #HPRE #ECA #performancereview #visitation

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

15 Nov, 07:12

የንግድ ተደራሽነትዎን ያሳድጉ!

የንግድ ሥራዎትን የአገር ውስጥ እንዲሁም የአለም አቀፍ ተደራሽነቱን ለማስፋት አስበዋል?
የኢትዮጵያ ፖስታ በጥቅል መልዕክት አገልግሎቱ ከ190 በላይ አለም አቀፍ መዳረሻዎች እንዲሁም ከ700 በላይ የሃገር ውስጥ ቅርንጫፎች መልዕክትዎን በፍጥነት እና በላቀ ጥንቃቄ እናደርስልዎታለን !

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

08 Nov, 13:52

ለማንዴላ የርቀት ትምህርት ተማሪዎች አስደሳች ዜና!

የኢትዮጵያ ፖስታ ከማንዴላ የርቀት ትምህርት አካዳሚ ጋር በመተባበር ለእርስዎ ምቾት እየተጋ ይገኛል። በማንዴላ የርቀት ትምህርት ቤት ተመዝግበው የመማሪያ ሞጁል ለመቀበል እርቀው መሄድ ሳይጠበቅብዎ ፤ በተመረጡ የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች ይውሰዱ።

👉አገልግሎቶቹን የሚያገኙባቸው የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፎች
1. ቃሊቲ
2. አቃቂ
3. ቤቴል
4. አስኮ
5. መገናኛ
6. ኮተቤ
7. ጀሞ
8. ላምበረት
9. አለምገና
10. ሰበታ

ርቀት ሳይገድብዎ በምቾት ይማሩ!

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost #MandelaAcademy #distance_education

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

08 Nov, 06:00

የኢትዮጵያ ፖስታ ኢትዮ-ጆብስ በሚያዘጋጀው አመታዊ የስራ ትርኢት ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ከጥቅምት 27 - 28 ተሳትፏል።

የኢትዮጵያ ፖስታ ለወጣት ባለተሰጥዎች የስራ እድልን ለማመቻቸት እና ተሰጧቸውን የሚያወጡባቸውን የስራ ምህዳር ከማስፋት አኳያ ሰፊ እንቅስቃሴን እያደረገ ይገኛል። በዚህ የስራ ትርኢት ላይ መገኘታችን በፖስታ ኢንደስትሪ ውስጥ ስኬታማ ስራዎችን ለመጀመር ከሚጓጉ ግለሰቦች ጋር የመገናኘት እድልንም ፈጥሮልናል።

#Ethiopost #Ethiojobs #Careerdevelopment

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

06 Nov, 12:55

ለሎጀስቲክስ ፍላጎትዎ የኢትዮጵያ ፖስታን ምርጫዎ ያድርጉ።

ለመንግስት ተቋማት፣ ለግል ድርጅቶች እንዲሁም ለግለሰቦች አስተማማኝ የማጓጓዝ አገልግሎት እንሰጣለን። አገልግሎቶቻችንን ለማግኘት ዛሬውኑ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

#Ethiopost #logestics

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

04 Nov, 11:28

የፋይዳ መታወቂያ ካርድዎን በእጅዎ ይዘዋል?

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ አካሂደው ካርዱን ማሳተም ሲፈልጉ
ወደ id.et/cardprint በመግባት ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የካርድ ህትመት ይመዝገቡ።
በመላው ሃገሪቱ ካሉን ቅርንጫፎች አቅራቢያዎ በሚገኘው የፖስታ ቤት ቅርንጫፍ ካርድዎን ይውሰዱ!

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ያግኙን።

የኢትዮጵያ ፖስታ

#Ethiopost #NID

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

31 Oct, 12:06

የፊላቴሊ ሐሙስ!

በዚህ ሳምንት፣ ከኢትዮጵያ ጥንታዊ ቅርሶች አንዱ የሆነውን የሳቢያን ኢንስክሪፕሽን ቴምብሮችን እናያለን። እነዚህ በጥንታዊው የኢትዮጵያ ፊደል በግእዝ የተጻፉት በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን ያስቆጠሩ እና የሀገሪቱን ታሪክ ለመረዳት ቁልፍ ናቸው። ቴምብሮቹ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባሕላዊ መሠረት እና የሳቢያን ሥልጣኔ ታሪካዊ ጠቀሜታ የሚያንፀባርቁትን የእነዚህን ጥንታዊ ጽሑፎች ውበት ያሳያሉ።

እነዚህን እና ሌሎች ቴምብሮችን ለማየት https://www.pinterest.com/ethiopost ይጎብኙ።

#PhilatelyThursday | #EthiopianHistory | #SabeanInscriptions

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

30 Oct, 06:43

የኢትዮጵያ ፖስታ እና ኦሮሚያ ጤና ቢሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ላይ ያተኮረ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ።

የኢትዮጵያ ፖስታ  ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመገናኘት በክልሉ የሚገኙ የጤና ናሙና ሎጂስቲክስ፣ የፋይናንሺያል እና የመልዕክት አገልግሎቶችን በቅንጅት መስጠት ላይ ያተኮረ የትብብር ስራዎችን ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂዷል። የኢትዮጵያ ፖስታ ላለፉት አስር አመታት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ የመንግስት የጤና ተቋማት የጤና ናሙናዎችን ተቀብሎ ወደ መመርመሪያ ጣቢያዎች በማድረስና ውጤቱንም መልሶ ለጤና ተቋማት በማስረከብ የሎጅስቲክስ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ይህ አሰራር በናሙና ዝውውር ላይ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ለህብረተሰቡ የጤና ሽፋንን ከመጨመር አንፃር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጓል።

በኦሮሚያ ጤና ቢሮ ስር ከሚገኙ የዞንና ከተማ ጤና ቢሮ ኃላፊዎች ጋር  የተደረገው ይህ ውይይት የጤና ናሙና ሎጂስቲክስን በቴክኖሎጂ ማዘመንና አጋርነትን ከፍ በማድረግ ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ መሆን ላይ ያተኮረ ነበር። ይህንንም ለመተግበር የኢትዮጵያ ፖስታ በኦሮሚያ ጤና ቢሮ ሥር በሚገኙ 1440 የጤና ተቋማት ውስጥ የአገልግሎት መስጫ ቦታዎችን ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደርሷል። በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ  የኢትዮጵያ ፖስታ የናሙና አሰባሰብ ሂደቱን ለማቀላጠፍ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ተጨማሪ አገልግሎቶችን ለመስጠት ከኦሮሚያ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በነዚህ የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት መስጫ ጽ/ቤቶችን በማቋቋም አገልግሎት መስጠት ይጀምራል።

Follow us
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram Pinterest | TikTok

Ethiopost

29 Oct, 07:59

የጥቅል መልእክት ትዕዛዞችዎን በአስተማማኝ አገልግሎታችን በቀላሉ ይላኩ።

በተመጣጣኝ ዋጋ ፣ ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ከ190 በላይ አለም አቅፍ መዳረሻዎት ባሉት የኢትዮጵያ ፖስታ በቀላሉ ይላኩ!
የኢትዮጵያ ፖስታ የመልእክት አገልግሎት ህይወትዎን ቀላል ለማድረግ ያለሙ ናቸው።

ጥቅልዎን ለመላክም ሆነ ለመቀበል በአቅራቢያዎ የሚገኘውን የፖስታ ቅርንጫፍ ይጎብኙ!

በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ያግኙን።

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

25 Oct, 06:59

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢግልድ የሸቀጦች ጅምላ ንግድ አስመጪ ድርጅት መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ::

በኢትዮጵያ ፖስታ ቺፍ ኮሜርሻል ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኢግልድ የኢንዱስትሪ ዉጤቶች ግዥ እና ሽያጭ ዘርፍ ም/ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አበባዬ ገዛኸኝ የተፈረመው ይህ አጋርነት የኢግልድ የኢንዱስትሪ ዉጤቶችን በኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች በኩል ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግና በኦንላይን የኢግልድን የኢንዱስትሪ ዉጤቶች ለሚገበያዩ ደንበኞች በሚመርጡት ቦታ ዕቃዎችን ለማድረስ የሚያስችል ነው::
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ፖስታ ተደራሽነቱን ከማስፋት አንፃር የኢግልድን ቅርንጫፍ ቢሮዎች ለሚሰጣቸዉ የተለያዩ አገልግሎቶች በፍራንቻይዝነት መጠቀምን ያካትታል ::

#Ethiopost #Eiide #logestics #franchise

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

24 Oct, 12:24

የኢትዮጵያ ብር ኖቶች በቴምብር!

በዚህ ሳምንት በ1981 ዓ.ም የወጣውን የ5ብር፣ የ10ብር እና የ100ብር ኖቶችን የያዘውን "የኢትዮጵያ ብር ኖቶች" በቴምብር እናያለን። እነዚህ በልዩ ሁኔታ የተነደፉ ቴምብሮች የኢትዮጵያን የብር ኖት ታሪክ እና የንድፍ ጥበብ በመያዝ የብርን ታሪካዊ ለውጥ ያሳያሉ።

እነዚህን እና ሌሎች ቴምብሮችን ለማየት https://www.pinterest.com/ethiopost ይጎብኙ።

#PhilatelyThursday #Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

24 Oct, 08:46

ድርጅትዎን በቀላሉ ለማስተዋውቅ የኢትዮጵያ ፖስታ ሁነኛ አማራጭ ሆኖ ቀርቦሎታል።

ከ190 በላይ ዓለም ዓቀፍ መዳረሻዎች ባሉት የኢትዮጵያ ፖስታ ወደ ተለያዩ ሃገራት በሚጓዙ ጥቅሎች ውስጥ ስለድርጅትዎ የሚገልጹ ማስታወቂያዎችን በመላክ ባህር ማዶ ያሉ ደንበኞችን ያፍሩ። ምርት እና አገልግሎቶን ያስተዋውቁ፣ የሽያጭ መጠንዎን በብዙ እጥፍ ይጨምሩ።

ለበለጠ መረጃ [email protected] ይጻፉልን ወይም በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ።

ለበለጠ መረጃ [email protected] ይጻፉልን ወይም በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ።

#Ethiopost #Letter #realstates #promotion #startups

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

23 Oct, 10:56

ባለፈው ሳምንት የጠየውን ጥያቄ እናስታውሳችሁ።

'' የኢትዮጵያ ፖስታ የመጀመሪያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ማን ነበሩ? ''
መልሱ፦ ቀኝ አዝማች በየነ ይመር

ቃል በገባነው መሰረት ወርሃዊ የኢንተርኔት ጥቅል አሸናፊዎችን ለይተናል ከተመለሱ መልሶች መካከል 4 ሰዎች ብቻ በትክክል መልሰዋል።
እነርሱም:-
@Abdi Farah
@Citizenof Cosmos
@deremersha
@MG
—————————————————————————————
የሳምንቱ ጥያቄ፣ ይመልሱ ይሸለሙ!

👉🏽 የኢትዮጵያ ፖስታ በሀገር ውስጥ ስንት ቅርንጫፎች አሉት?

በአስተያየት መስጫው ላይ መልስዎን ይስጡ! ወርሃዊ የኢንተርኔት ጥቅልን ለማሸነፍ ከመጀመሪያዎቹ 5 ትክክለኛ መልስ ሰጪዎች አንዱ ይሁኑ!

ይህ እድል እንዳያመልጥዎ! የማሸነፍ እድሎዎን ለመጨመር ለጓደኞችዎ እና ለቤተሰብዎ ያጋሩ!

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

22 Oct, 07:09

ብሄራዊ ፈተና ሰርተፍኬትዎን እንደገና ማውጣት ይፈልጋሉ?

የጠፋ ወይም የተቀደደ የ6ኛ፣ 8ኛ፣ 10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የምስክር ወረቀቶችን በድህረገጽ https://services.eaes.et/usr በማዘዝ በአቅራቢያዎ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ይጻፉልን።

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

21 Oct, 07:10

በኢትዮጵያ ፖስታ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!

በኢትዮጵያ ፖስታ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳግማዊ ኃይልዬ እና በኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኤልያብ ጌታቸው የተፈረመው ይህ የአጋርነት ሰነድ የቤት ለቤት መልእክቶችን እና ሌሎች የመልዕክት ልውውጥ አገልግሎቶችን ለደንበኞች ለማድረስ የሚያስችል ነው። የኢትዮጵያ ፖስታ ባሉት 700 የሃገር ውስጥ ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች የበሽ ገበያ እንዲሁም በትልቅ የሎጅስቲክስ አቅም የሚጓጓዙ የኢስት አፍሪካ ትሬዲንግ ሃውስ ምርቶችን በሃገር ውስጥ እንዲሁም በተለያዩ የውጪ ሃገራት ለሚገኙ ደንበኞች ማድረስን ያካትታል።

#Ethiopost #MOU #Eastafticantradinghouse

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

18 Oct, 13:34

የኢትዮጵያ ፖስታ የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ የነበሩት ክብርት ወ/ሮ ሐና አርአያስላሴ የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው የኢትዮጵያ ፖስታ የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች የተሰማንን ደስታ ለመግለጽ እንወዳለን።

ይህ አዲስ ምዕራፍ የስኬት እንዲሆን ከልብ እንመኛለን።

Ethiopost

18 Oct, 08:59

በየኢትዮጵያ ፖስታ እና በኦሮምያ ባንክ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ!

በየኢትዮጵያ ፖስታ ኮሜርሺያል ቺፍ ኦፊሰር ወ/ሮ ትዕግስት በቀለ እና በኦሮምያ ባንክ የሪቴል እና ኤስ ኤም ኢ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ጆቴ ቀናቴ የተፈረመው ይህ አጋርነት ከ700 በላይ ቅርንጫፎች ባሉት የኢትዮጵያ ፖስታ የባንክ አገልግሎቶችን በወኪልነት እንዲሰራ የሚያስችል ነው። ትብብራችን ደንበኞች የባንክ እና ሌሎች ከባንክ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን አገልግሎቶች በቀላሉ እንዲያከናውኑ ብሎም ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ይረዳል።

#Ethiopost #MOU

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

17 Oct, 12:07

የኢትዮጵያ ከተሞች በቴምብሮች!

በዚህ ሳምንት የፊላቴሊ ሐሙስ በየኢትዮጵያ ፖስታ በተዘጋጁ የኢትዮጵያን ውብ ከተሞች የሚያሳዩ እና በአስደናቂ ዲዛይን የተሰሩ ቴምብሮችን እናያለን። እነዚህ ቴምብሮች የእያንዳንዱን ከተሞች ልዩ ገጽታ እና ታሪክን ያመላክታሉ። እነዚህን እና ሌሎች ቴምብሮችን ለማየት https://www.pinterest.com/ethiopost ይጎብኙ።

#Ethiopost #PhilatelyThursday #TownsOfEthiopia

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest (Philately) | TikTok |

Ethiopost

16 Oct, 11:27

የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ካርድ ለማዘዝ 5 ቀላል ደረጃዎች

የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ካርድ ህትመት መመዝገብ ቀላል ነው! እነዚህን 5 ቀላል ቅደምተከተሎች ይከተሉ:

1️⃣ የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባን ማከናወን እንዲሁም የአጭር መልእክት መቀበልዎን ያረጋግጡ

2️⃣ ወደ id.et/cardprint በመግባት ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ የካርድ ህትመት ምዝገባን ያካሂዱ

3️⃣ በፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባ ወቅት የሞሉትን ስም፣ አድራሻ ፣ ስልክ. . . ወ.ዘ.ተ ትክክለኛነት ያረጋግጡ

4️⃣ ክፍያዎን ካሉበት ሆነው በተቀመጡት የክፍያ አማራጮች ይክፈሉ

5️⃣ የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያዎን በአቅራቢያዎ በሚገኘው እና በመረጡት የኢትዮጵያ ፖስታ ቅርንጫፍ ይቀበሉ

ለበለጠ መረጃ ለበለጠ መረጃ በአቅራቢያዎ የሚገኘውን ፖስታ ቅርንጫፍ ይጎብኙ!
ወደ 8536 በነፃ ይደውሉ፣ ልናስተናግድዎ ዝግጁ ነን! በቴሌግራም @etpccsbot ይፃፉልን።

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

14 Oct, 06:59

በፖስታ ሳጥን ርቀት ሳይገድብዎ ድርጅትዎን ማስተዋወቅ እንደሚችሉ ያውቃሉ?

ከ700 በላይ የሀገር ውስጥ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከ500,000 በላይ የፖስታ ሳጥን ደንበኞች ባሉት የኢትዮጵያ ፖስታ ምርት እና አገልግሎትዎን ያስተዋውቁ ትርፋማ ይሁኑ!

ብዙዎችን ለመድረስ ሁነኛ አማራጭ !

ለበለጠ መረጃ በ [email protected] ይጻፉልን
በነጻ የስልክ መስመር 8536 ይደውሉልን ወይም በቴሌግራም @etpccsbot ያግኙን።

#Ethiopost

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

12 Oct, 11:40

የዓለም ባንክ እና የፋይዳ ብሔራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች በየኢትዮጵያ ፖስታ ጉብኝት አካሄዱ።

የአለም ባንክ እና የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የፋይዳ ብሄራዊ መታወቂያ ካርዶችን በማተም እና በማሰራጨት ላይ ያለውን የሥራ ሂደት እንዲሁም የደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥን በየኢትዮጵያ ፖስታ በመገኘት ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ዜጎች ከየኢትዮጵያ ፖስታ ጋር እንዴት እንደሚገናኙ ከመጀመሪያው የካርድ ህትመት ጥያቄ እስከ መጨረሻ ካርድ አሰባሰብ ድረስ የደንበኞችን ጉዞ ምን እንደሚመስል ቃኝተዋል።

በተጨማሪም ለዜጎች የፋይዳ አገልግሎት ተደራሽነትን ከማስፋፋት አንፃር የኢትዮጵያ ፖስታ አጋርነትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ውይይት ተደርጓል።

#Ethiopost #natinalid #worldbank

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

10 Oct, 06:55

የፊላቴሊ ሐሙስ!

የኢትዮጵያን የበለፀገ ባህል እና ቅርስ በማስመልከት የኢትዮጵያ ፖስታ ጥንታዊቷን የአክሱምን ከተማ ለማስታወስ ቴምብር እንዳወጣ ያውቃሉ?
ይህች ታሪካዊ ከተማ የኢትዮጵያን የበለፀገ ባህል እና ቅርስ ማሳያ ነች። ስለ አክሱም እና ሌሎች የቴምብር ስብስቦችን ለመመልከት በ Pinterest አካውንታችን ይጎብኙ።
https://pinterest.com/ethiopost

#PhilatelyThursday #Ethiopost #Axum #EthiopianHeritage

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok

Ethiopost

09 Oct, 14:00

የአለም የፖስታ ቀን አከባበር በየኢትዮጵያ ፖስታ

Follow us on our social media platforms
Facebook | Telegram | LinkedIn | Twitter | Instagram | Pinterest | TikTok