Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 @daily_news_ethiopian Channel on Telegram

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

@daily_news_ethiopian


Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
🇪🇹ኢትዮጵያ
አዳዲስ መረጃዎች እንዲደርስዎ ቤተሰብ ይሁኑ
Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵
@Daily_News_Ethiopian
አስተያየትና መልክት ካሎት @Natty19
ምርትና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
@Natty19

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵 (Amharic)

የኢትዮጵያ ዜና ቅናሽን 🇪🇹🔵 በአማርኛnnየአንድ ቀን ዜናዎችን በአዳዲስ ክፍል እንዲደርስዎ ቤተሰብ በጥቅም ይዟቸው። የአንድ ቀን ዜና በደረሰ መረጃ እና መልክት ካሎቶች በነፃነት ለማከብና ለመመልከት በ@Natty19 ስም ተከታዮቸውን ይከታተሉ። በተመሳሳይ ዜና ብቻ ተደርሷል።nnአንዳንዶ ስለ ዜናዎች ለአንተ ለማቅረብ ፣ ለተመሳሳይ መረጃ ብቻ እንደሚሠራ እና ለማሰብ እንደሚችሉ ለተጠቃሚው ህዝብ እንደሚሰፋ፣ ዜናዎችን ከታተሜ አስፈላጊ ይጠቀሙ።nnበቀኑ የአንድ ቀን ዜና መነሻ አልፓም፣ የጊዜው ዜናን እያካባቢ እንደሚስት ለአንተ ውስጥ ያለው ዜና ይመልከቱ። ከዚህ በታች የተመረጠ ዜናውን በጥሩ እና ልብህ በልም።

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

21 Nov, 11:27


ህዳር ሲታጠን አዲስ አበባ

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

17 Nov, 17:13


አክሱም ላይ ህዝብን ማሸበር ይቁም

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

16 Nov, 15:27


#ባህርዳር
ባህርዳር ኤርፖርት ዛሬ 6:15 አንድ ሄሊኮፕተር በመንደርደር ላይ እያለ አደጋ እንዳጋጠመው ተሰምቷል።

📌በዚህ ምክንያት ወደ ባህርዳር የሚደረጉ የዛረ በረራዎች ተስተጓጉለዋል!

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

02 Nov, 13:36


በቤተመንግስት ተገኘ ስለተባለው 400 ኪ/ግ ወርቅ

ጠ/ሚር አብይ አህመድ ፓርላማ ላይ "ባደረግነው የቤተመንግስት ዕድሳት ተቆልፎበት የተቀመጠ 400 ኪሎ ግራም ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ አስገብተናል" ማለታቸው ይታወሳል።

"ይህ ወርቅ ምን ይሆን ብዬ?" አንዳንድ ማጣራቶችን ለማድረግ ሞክሬ ነበር። ያገኘሁት መረጃ አስደንጋጭም፣ አሳሳቢም ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

ይህ ወደ ብሄራዊ ባንክ ተላከ የተባለ ወርቅ በኢትዮጵያ የንጉሳዊ ስርዐት ወቅት ለበርካታ መቶ አመታት ነገስታት ሲገለገሉባቸው የነበሩ በወርቅ እና በሌሎች የከበሩ ማዕድናት የተሰሩ ቁሳቁሶች፣ ከሌሎች ሀገራት በስጦታ የተሰጡ ቅርሶች እንዲሁም በርካታ በነገስታቱ ታዘው የተሰሩ እና የተገዙ ናቸው።

"ታድያ እነዚህ ወደ ሙዚየም እንጂ ለሽያጭ ወይም ለወርቅ ክምችት ወደ ባንክ እንዴት ሊላክ ይችላል?" ብዬ ጥያቄ ያቀረብኩላቸው ጉዳዩን የሚያውቁ ግለሰቦች ምላሻቸው "ማን ሰምቶን?" ነው።

ቅርስ ጥበቃ፣ ብሄራዊ ባንክ፣ የጠ/ሚር ፅ/ቤት እንዲሁም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ዙርያ መክሮ እነዚህን የኢትዮጵያ ታሪክ የሆኑ ንብረቶች ወደነበሩበት ቦታ ወይም ወደ ሙዚየም እንዲመለሱ ማድረግ አለባቸው።

እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ ነው!

@EliasMeseret

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

28 Oct, 12:54


ስፖርት:-ማንቸስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን አባረረ::

ክለቡ ዛሬ ባወጣው መግለጫ "ኤሪክ በኤፕሪል 2022 የተሾመ ሲሆን ክለቡን በ2023 የካራባኦ ካፕ እና በ2024 የኤፍኤ ዋንጫን በማንሳት ክለቡን ሁለት የሀገር ውስጥ ዋንጫዎችን አሸናፊ ማድረጉን"ጠቅሷል:

"ኤሪክ ከእኛ ጋር ባደረገው ቆይታ ላደረገው ነገር ሁሉ አመስጋኞች ነን እና ለወደፊቱ መልካም እንዲሆንለት እንመኛለን።" ያለው ማንቸስተር ዩናይትድ "ሩድ ቫን ኒስቴልሮይ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ቡድኑን ይመራዋል፣ አሁን ባለው የአሰልጣኝ ቡድን ይደገፋል፣ ቋሚ ዋና አሰልጣኝ ደግሞ ይመለመላል።" ብሏል::

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

27 Oct, 16:50


15 '

አርሰናል 1-1 ሊቨርፑል

ሳካ ቫንዳይክ

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

27 Oct, 16:48


የሳካ ጎል

አርሰናል 1-0 ሊቨርፑል

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

27 Oct, 16:47


Arsenal 1 Liverpool 0

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

08 Oct, 15:31


ቤንዚን በሊትር 91 ብር ገባ

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል
ዝርዝሩ ከላይ ተቀምጧል

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

08 Oct, 15:10


#Afar

በአፋር ክልል ዱለሳ ወረዳ በተከሰተ " የመሬት መንቀጥቀጥ " ምክንያት ከተፈጠረ የመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ መፍለቅ መጀመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች እና የወረዳው አስተዳደር ተናግረዋል።

ከትናንት ሌሊት ጀምሮ መፍለቅ የጀመረው ፍል ውሃ መጠኑ እየጨመረ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አፋር ክልል ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ እያስተናገደ ነው።

በክልሉ ጋቢ ራሱ ዞን በሚገኘው ዱለሳ ወረዳ ሳንጋቶ ቀበሌ ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው ትናንት ሰኞ መስከረም 27/2016 ዓ.ም. ምሽት " የመሬት መንቀጥቀጥ " ከተከሰተ በኋላ እንደሆነ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ እና ሁለት የቀበሌው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

- ትናንት ምሽት ሦስት ሰዓት ገደማ መከሰት የጀመረው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ ሶስት ጊዜ ያህል ተደጋግሟል።

- የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የሚናገሩት ካቆመ በኋላ ሌሊት 10 ሰዓት ገደማ ላይ ድምፅ ሰማን። ጠዋት ላይ  ድምፅ ወደተሰማበት ቦታ ስናመራ ከመሬት ስንጥቅ ውስጥ ፍል ውሃ እየፈለቀ ተመልክተናል።

- ውሃው የወጣው የአካባቢው ማህበረሰብ በሚኖርበት ሰፈር ውስጥ ነው። ድምፅ ነበረው። ማታ ፈርተን ነው ያደርነው። በጠዋት ሄደን ሁሉንም ነገር ለማየት ችለናል።

- ውሃው በሚወጣበት የመሬት ስንጥቅ ስር ድምፅ ይሰማል። ወደላይ የሚፈናጠረው ፍል ውሃ መጠን እና የሚፈልቅበት ስንጥቅ መጠን እየጨመረ ነው።

ፍል ውሃው በወጣበት ሳንጋቶ ቀበሌ ውስጥ ፍል ውሃ ባለመኖሩ አዲሱ ክስተት ነዋሪዎች ድንጋጤ እና ስጋት ላይ ጥሏል።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሊ ደስታ ምን አሉ ?

° ከትናንት በስቲያ ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አንጻር የትናንቱ ትንሽ ያነሰ ነው።

° ከዚህ በኃላ ነው ፍል ውሃ መፍለቅ የጀመረው።

° ሰዎች በቅርበት እዚያ አካባቢ ይኖራሉ። የእኛ አካባቢ ማህበረሰብ አርብቶ አደር ከመሆኑ አኳያ ከብቶቻቸውን ፍየሎቻቸውን የሚጠብቁበት ቦታ ነው።

° የወረዳው አስተዳደር ክስተቱን ለማጣራት ባለሙያዎችን ወደ ቀበሌው ልኳል።

° የሚፈጠረው ነገር ስለማይታወቅ ነዋሪዎች’ ከዚያ አካባቢ ለቅቀው ወደ ሌላ ቦታ እንዲሄዱ የማድረግ ስራ እየሰራን ነው። እንደዚህ አይነት ነገር ታይቶም ስለማይታወቅ ከፍተኛ ስጋት ነው ያለው።

የአፋር ክልል ጋቢ ራሱ ዞን በተደጋጋሚ እያጋጠመ ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ነዋሪዎች ከሰፈሩበት አካባቢ እንዲነሱ እየተደረገ ነው።

አንዱ አካባቢው ይኸው የዱለሳ ወረዳ ነው።

አጎራባቹ አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ ከሁለት ሳምንት በፊት በአካባቢው በሚገኘው ከሰም ግድብ እና ፈንታሌ ተራራ አካባቢ የሚኖሩ ከ700 በላይ ሰዎችን ገላጣ ሜዳ ወደሆኑ አካባቢዎች አዘዋውሯል።

መረጃው የቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ሲሆን ፎቶና ቪድዮ የአብዶ ሀሰን፣ ሱልጣን ከሚል ነው።

Daily News Ethiopian 🇪🇹🔵

08 Oct, 13:08


ሰበር!!

ሰሞኑን በአፋር ክልል በዞን ሶስት በተለየዩ አካባቢዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መፈጠሩ የሚታወቅ ሲሆን ከእነዚህ ቦታዎቹ ሰጋንቶ ቀበሌ አንዱ የእዚህ ተጋላጭ ነበር በመሆኑም በዛሬው እለት ቀን 28/1/2017 በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከመሬት ወስጥ የወጣው ፍል ወሃ በምስሉ ይሄን ይመስላል።በዚህ አከባቢ እሳተጎሞራ ሊፈጠር ስለሚችል የዘርፉ ባለሞያዎች እዚህ አከባቢ ትኩረት ቢያደርጉ እንላለን።