Amhara Communications @amharacommunications Channel on Telegram

Amhara Communications

@amharacommunications

This is the official Telegram channel of Amhara Regional State Government Communications Office.

Amhara Communications (English)

Are you interested in staying up-to-date with the latest news and updates from the Amhara Regional State Government? Look no further than the official Telegram channel of Amhara Communications! As the official communications office of the Amhara Regional State Government, this channel provides a direct line of communication between the government and its citizens. From important announcements to press releases, you can find all the information you need right here. Who is it? The Amhara Communications channel is the official Telegram channel of the Amhara Regional State Government Communications Office. It serves as a platform for the government to communicate with the public and share important news and updates. What is it? This channel provides a direct line of communication between the Amhara Regional State Government and its citizens. It is a valuable resource for those wanting to stay informed about the latest developments in the region, including announcements, press releases, and other important information. Stay informed and connected with the Amhara Communications channel on Telegram today! Join us to be part of the conversation and receive timely updates straight from the source.

Amhara Communications

12 Jan, 15:39

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እየተከናወኑ ያሉ ወቅታዊ  የልማት ስራዎች በከፊል።

Temesgen Tiruneh - ተመስገን ጥሩነህ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

12 Jan, 13:38

"በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለሁ" የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር)

Abiy Ahmed Ali

Amhara Communications

12 Jan, 13:35

"የአማራ ክልል መንግስት የህዝቡን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የ25 አመት እቅድ አቅዶ ወደ ተግባር ገብቷል"

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር )

የክልሉ መንግስት የህዝባችንን የኢኮኖሚና የመሠረተ ልማት ችግር ለመፍታት የ25 ፍኖተ ካርታ በመንደፍ ለዚሁ እቅድ ማስፈፀሚያ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ዝግጅት አድርጎ እየሰራ ነው።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ/ር ) በዛሬው እለት በደቡብ ወሎ ዞን የሃይቅ ከተማና ተሁለደሬ ወረዳ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክትን መርቀዋል።

በደቡብ ወሎ ዞን ተዘዋውረን የመረቅናቸውና ያየናቸው የልማት ስራዎች የእቅዳችንን ትክክለኛነት ማሳያዎች ናቸውም ብለዋል።

Amhara Communications

11 Jan, 16:47

"የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮዽያ መጡ እላለሁ" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

11 Jan, 16:39

በ60 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር በጀት የተገነባው የወይን አምባ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ፕሮጀክት ተመረቀ !

በተያዘው በጀት ዓመት 500 ሺህ የማኅበረሰብ ክፍሎችን የንጹሕ መጠጥ ውኃ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የአማራ ክልል ውኃ እና ኢነርጅ ቢሮ አስታውቋል።
👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/100064600724843/posts/pfbid02ojm1GFyjbAPzefWggUmw5bYGjwweTqcTVLTND3JscS4jtVb9D2diGB6B7PyuPsEGl/?app=fbl

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

11 Jan, 16:32

"የሴቶች የልማት ህብረት ጥምረቶች የሴቶችን ተሣትፎና ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማሳደግ የሚያግዙ ስትራቴጂያዊ አማራጮች እና የአደረጃጀቶች አስኳል ናቸው" ክቡር አቶ ይርጋ ሲሳይ

የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሞዴል የሴቶች የልማት ህብረቶችን ለመፍጠር ያለመ የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ አካሂዷል።
👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/100064600724843/posts/pfbid03vYtFbx6nqrrHW4C6dseyowZbqxTzpywEz5fdTrjvadyn5C1RmEzRUGhEgpAj8Uql/?app=fbl

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

11 Jan, 11:36

በአማራ ክልል ከአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ !!! 
👇👇👇👇👇
https://www.facebook.com/100064600724843/posts/pfbid05wQTrTWx9bKj2FYMp524MhRzBzoAj4oXq9D39N31whThANY8rhbSj1EdzB6r2y6Nl/?app=fbl

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

08 Jan, 15:06

"በታማኝነትና ሃቀኝነት ህዝብን ማገልገል የሀገር ወዳድ የሚሊሻ አባላት መገለጫ ነው " አቶ አህመድ አሊ አባፋሮ

በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር በባቲ ከተማ አስተዳደር ከሁሉም ቀበሌ የተውጣጡ አዳዲስ ሚሊሻዎች ለተከታታይ 20 ቀናት ስልጠና ሲወስዱ የቆዩ የሚሊሻ አባላትን የሚመለከታቸው አካላት ተገኙበት ምረቃ ተካሂዷል።

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ አባአፍ፦ የሚሊሻ አባላቱ በስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ተጠቅመው በታማኝነትና በሀቀኝነት ህብረተሰቡን ለማገልገል ሀላፊነታችሁን እደሚወጡ ተስፋ አደርጋለሁ።

ታጥቀው በጫካ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችም በሰላማዊ መንገድ እንዲገቡ ጥሪየን አስተላልፋለሁ ሲሉ ተናግረዋል።

የ102ኛ ኮር አዛዥ ጄ/ እሸቱ መንግስቴ በበኩላቸው፦ የተጀመረው ስልጠና መልካም እንደሆነና በዚሁ መቀጠል እንዳለበት መልእክት አስተላልፈዋል።

ከተመራቂ የሚሊሻ አባላት መካከል አህመድ ኑር እና ወ/ሮ ዘሀራ አብዱ እንደተናገሩት፦ በነበረው ሰልጠና ተገቢውን ክህሎት እንዳገኙ ገልጸው በሰለጠኑት አግባብ ማህበረሰቡን ለማገልገል ቁርጠኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።

በመርሐ ግብሩ መጨረሻ ለነባር የሚሊሻ አካላት እና በስልጠናው አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እውቅና ተሰጥቷል።

በፕሮግራሙ የኦሮሞ ብ/አስተዳደር ዋና አስተዳደሪ አቶ አህመድ አሊ አባአፍሮን ጨምሮ የከተማና የቀበሌ አመራሮች እንዲሁም ሰልጣኝ የሚሊሻ አባላት ተገኝተዋል።

Amhara Communications

08 Jan, 09:07

በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ 015 ቱሉ ባቦኛ ቀበሌ 115 ሄ/ር የሚሸፍን መሬት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማ ዘር ተሸፍኗል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

07 Jan, 17:15

የክልሉ መንግሥት ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የሚያደርገውን የሰብዓዊ ድጋፍ ለማገዝ ዝግጁ መኾኑን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ፡፡
***

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ልዑካንን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

ከልዑካኑ ጋር በክልሉ ሁሉን አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፎች ተደራሽ ስለሚኾኑበት እና ከክልሉ መንግሥት ጋር በትብብር ስለሚሠሩበት ሁኔታ መነጋገራቸውን ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ተናግረዋል፡፡

ቀይ መስቀል ማኅበር በክልሉ በርካታ የሰብዓዊ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ በቀጣይ በሚኖራቸው ሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ላይም የክልሉ መንግሥት ለማገዝ ዝግጁ መኾኑን አረጋግጠውላቸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ከዚህ በፊት በሰሜኑ ጦርነት ሁሉን አቀፍ ሰብዓዊ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑካን መሪ ብሩስ ቢቨር አውስተዋል፡፡

አሁንም በአማራ ክልል የተለያዩ ሰብዓዊ ድጋፎችን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ መኾናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በክልሉ ያለውን የሰብዓዊ አገልግሎት ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ እና መጠን ተደራሽ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ያነሱት ደግሞ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ የሻምበል ዋለ ናቸው፡፡

በቀጣይም በክልሉ ከሚመለከታቸው የክልል ቢሮ ኀላፊዎች ጋር ተጨማሪ ውይይቶችን በማድረግ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንደሚገቡም ጠቁመዋል፡፡

Amhara Communications

07 Jan, 08:48

በቤተ መንግሥት ለዐቅመ ደካሞች የገና በዓል መዕድ ማጋራት እና ጉብኝት መርሐ ግብር::

#PMOEthiopia

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

04 Jan, 17:55

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አደረገ

የሀገር መከላከያ ሠራዊት የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በላሊበላ ከተማ በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉን ያደረጉት በሀገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ምሥራቅ እዝ 803ኛ ኮር 61ኛ ከፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አዛዥ ሻምበል ጫላ ደቢሳ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከሰላም ማስከበር ጎን ለጎን በዝቅተኛ ኑሮ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።

አቅመ ደካሞችን፣ አሳዳጊ የሌላቸውን ልጆች እና ሌሎች ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን እንደሚደግፉም አመላክተዋል።

ሠራዊቱ የሚያደርገው ድጋፍ በራሱ ፈቃድ እና ተነሳሽነት መሆኑን ተናግረዋል።

ሰላምን ከማስከበር ጎን ለጎን የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የገለጹት።

የተደረገው ድጋፋ ዘላቂ ችግሮቻቸውን ባይፈታ እንኳን በዓሉን በደስታ እንዲውሉ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት።

የላሊበላ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ወንድምነው ወዳጅ፦ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እያደረገ ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋውያን እና ለሕጻናት ድጋፍ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት በተፈጠረው የቱሪዝም መቀዛቀዝ ምክንያት የከተማ ነዋሪዎች ለችግር መገላጣቸውንም አስታውሰዋል።

ሌሎች ተቋማት እና ግለሰቦች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

Amhara Communications

04 Jan, 17:26

በጎንደር ከተማ የሰዓት ገደብ እንቃስቃሴ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

በጎንደር ከተማ የነበረው የፀጥታ ችግር መሻሻል ማሳየቱን ተከትሎ የከተማው የፀጥታ ም/ቤት በተሽከርካሪና በሰው እንቅስቃሴ ላይ ጥሎት የነበረውን የሰዓት ገደብ ማሻሻሉን ተገልጿል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ረ/ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ እንደገለጹት የከተማው የፀጥታ ም/ቤት በተሽከርካሪና በሰው እንቅስቃሴ ላይ ጥሎት የነበረውን የሰዓት ገደብ ወደ አራት ሰዓት ከፍ እንዲል ውሳኔ አሳልፏል።

የተፈቀደላቸው ባጃጆች እስከ ምሽት አራት ሰዓት መስራት እንደሚችሉ የገለጹት ረዳት ኮሚሽነሩ ሌሎች ባጆጆች ደግሞ በቀደመው የሰዓት ገደብ እስከ 12 ስዓት ብቻ መንቀሳቀስ እንደሚችሉ ገልጸዋል።

ከተማዋ የገናና የጥምቀት በዓልን በድምቀት እንድታከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው የከተማው ነዋሪም ሆነ እንግዶች በነፃነት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ታስቦ የሰዓት ማሻሻያ መደረጉን አስረድተዋል፡፡

በከተማዋ በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች መስታወት ላይ ጥቁር ስቲከር የለጠፉ ሁሉ እንዲያነሱ ውሳኔ መተላለፉም ተናግረዋል፡፡

ይህን በማያደርጉ አካላት ላይ የፀጥታ ሃይሉ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ነው አጽንኦት የሰጡት፡፡

የሰዓት ማሻሻያ ገደቡ ከነገ ታህሳስ 27/2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ሁሉም የተጣለውን የሰዓት ገደብ እንቅስቃሴ አክብሮ እንዲንቀሳቀስ ኮሚሽነሩ አሳስበዋል።

Amhara Communications

04 Jan, 14:11

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የጎንደር ከተማ ኮሪደር ልማት እና የፋሲል አብያተ መንግሥት ቅርሶች እድሳት በምስል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

04 Jan, 14:09

"የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ ነው" አቶ ቴዎድሮስ ገደፋው

በአማራ ክልል የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር መጪውን የገና በዓል ምክንያት በማድረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እንዳይደረግ የክትትልና ቁጥጥር ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የገንዳውሃ ከተማ አሥተዳደር የእንሰሳትና እንሰሳት ተዋፅኦ ግብይት የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተፈራ በላይ፦ አሁን ባለው የበዓል ግብይት በቁም አንሰሳት ድልብ ዘርፉ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ እንደማይኖር ተናግረዋል።

መጪውን የገና በዓል ህብረተሰቡ በሰላምና በተረጋጋ ሁኔታ እንዲያከብር የንግዱ ማህበረሰብ ፍትሃአዊ እና ጤናማ የሆነ የግብይት ሥራዓት ለተገልጋዩ ማቅረብ እንደሚገባው አሳስበዋል።

የዞኑ ንግድና ገቢያ ልማት መምሪያ ተወካይ ኃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ገደፋው በበኩላቸው፦ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ምክንያታዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪን ለመከታተል እና የበዓል ግብይትን ስርዓት ለማስያዝ ግብረኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ ገብቷል።

በዚህም ግብረኃይሉ ከከተማ አስተዳደሩና ወረዳዎች ጋር በመሆን ገበያው እንዲረጋጋ እና ህብረተሰቡ በዓሉን በሰላም እንዲያሳልፍ የክትትልና ቁጥጥር ስራውን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

ህግን በመተላለፍ ያለአግባብ ሀብትና ንብረት በማጋበስ በአቋራጭ ለመበልጸግ በሚሰሩ እና ምርትን በሚደብቁ አካላት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳ ሲሉም ነው አቶ ቴዎድሮስ ያስጠነቀቁት።

Amhara Communications

03 Jan, 15:17

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ወለህ ቀበሌ እየለማ ያለ ሽንኩርት ከፊል ገጽታ በፎቶ።

🫐ዋግ ኽምራ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

03 Jan, 14:20

በሴፍትኔት ፕሮግራም ታቅፈው በከተማ ግብርና የተሠማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገበያውን በማረጋጋት የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን የኮምቦልቻ ከተማ ምግብ ዋስትና ሴፍትኔት ጽ/ቤት አስታወቀ::
👇👇👇👇👇
https://web.facebook.com/AmharaCommunications/posts/pfbid02ocL1StcxEAVkWJGAnErXL1s45jrD4nz6tyWnY3BsfjBxnp8hnGVE5pppZXY1fegUl

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

03 Jan, 13:36

‹‹በሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ ሁሉም ተቋማት በባለቤትነት ሊሰሩ ይገባል›› ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ

የአማራ ክልል ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ለክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ሰራተኞች በስርዓተ ጾታ አካቶ ትግበራ ዙሪያ የግንዛቤ ማሰጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።

ስልጠናውን በየፋ ያስጀመሩት የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ፡- በሴቶች፣ ህፃናት፣ አረጋዊያን እና አካል ጉዳተኞች የሚደርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ ከፍተኛ ነው፡፡ ተፅእኖውን ለመቀነስ ሁሉም ተቋማት በባለቤትነት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮም የእነዚህን የማህበረሰብ ክፍሎች ችግር ለመቅረፍ ተግባራቱን አካቶ ከመስራት ባለፈ የግንዛቤ ፈጠራ ስራ በመስራት ትግበራው የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ይሰራልም ብለዋል ወይዘሮ ትብለጥ፡፡

የግንዛቤ የስልጠና ሰነዱን ያቀረቡት በሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የአካቶ ትግበራ ባለሙያ አቶ በቃሉ ዳኛው፡- የሴቶች፣ የህፃናት፣ የአረጋውዊያን፣ የአካል ጉዳተኞች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍትሀዊነት፣እኩልነት እና ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የአካቶ ትግበራው የህግ ማቀፍ ተዘጋጅቶለት ወደ ስራ ገብቷል ያሉት ባለሙያው፡- እስካሁን የተሰራው ስራ አበረታች ቢሆንም የሚጠበቀው ውጤት እንዳልመጣ ጠቁመዋል፡፡

ሁሉም ተቋማት በሚሰሩት ስራ ስለሚመዘኑ የአካቶ ትግበራውን ከመደበኛ ተግባራቸው ጎን ለጎን ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም በተሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ተሰጥቶ ቀጣይ በየተቋማቱ መሰራት በሚገባው የአካቶ ትግበራ ላይ የጋራ መግባባት ተደርሷል፡፡

Amhara Communications

03 Jan, 12:47

‹‹በተያዘው በጀት ዓመት በበጋ መስኖ ስንዴ 782 ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል፡፡›› የአልብኮ ወረዳ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን የአልብኮ ወረዳ አስተዳደር ግብርና ጽ/ቤት በፈላና ቀበሌ የበጋ መስኖ ስንዴ ዘርን አስጀምሯል፡፡

በወረዳዉ በተያዘው በጀት ዓመት በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ከ1 ሺህ 139 ሄክታር በላይ መሬት ለማልማት የታቀደ ሲሆን ከዚህም 782 ሄክታር መሬቱ በዘር መሸፈኑን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

መረጃው የአልብኮ ኮሙንኬሽን ነው

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

03 Dec, 10:17

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የቦርከና ወንዝ ዳርን ለማልማት ከወሎ ዩኒቨርሲቲ ጋር የስምምነት ፊርማ አካሄደ።
*****
ከተማ አስተዳደሩ እና ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቱን እውን ለማድረግ የሚያስችል የአሰራር ማዕቀፍ የተካተተበት የስምምነት ፊርማ አካሂደዋል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ ፣ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አወል ሰይድን ጨምሮ የከንቲባ ኮሚቴ አባላትና የዩኒቨርስቲው ተወካዮች በተገኙበት የስምምነት ፊርማ ተካሂዷል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወንዶሰን ልሳነወርቅ በስምምት ፊርማው ላይ እንደገለጹት የቦርከና ወንዝ ከተማዋን ለሁለት ከፍሎ የሚያልፍ በመሆኑ ወንዙ ለከተማው የሚያስገኘውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በጥናት በመለየት በተለይ በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ከወንዙን ገጸ በረከት ከተማው ተጠቃሚ እንዲሆን መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተወካይ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አወል ሰይድ በበኩላቸው የቦርከና የወንዝ ዳር ልማት ፕሮጀክት ለከተማው ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ መስተጋብሮች ፋይዳው የጎላ በመሆኑ ዩኒቨርስቲው ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አብራርተዋል።

ዩኒቨርስቲው ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

Kombolcha city communication
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO

Amhara Communications

03 Dec, 10:06

በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የበጋ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በጅሌ ጥሙጋ ወረዳ የ2017 ዓ.ም የበጋ ስንዴና ሌሎች የግብርና ስራዎች ንቅናቄ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የበጋ ስንዴ እና ሌሎች የግብርና ሰራዎች ምርታማነትን ለማሳደግ ከተለያዮ ባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረኩን እያካሄደ ነው።

በንቅናቄ መድረኩ የቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የቀበሌ አመራሮች፣የውሃ ኮሚቴዎች፣ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች፣የግብርና ጽ/ቤት ባለሙያዎች እና የወረዳ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።በንቅናቄ መድረኩ በወረዳው የታቀደውን የበጋ ስንዴና ሌሎች የግብርና ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ በባለድርሻ አካላት የተሻለ መግባባት ይፈጠራል ተብሎ ይታሰባል።

ዘገባው የጅሌ ጥሙጋ ኮሙኒኬሽን ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

03 Dec, 09:54

የመንግስት ግዥ በእቅድ ላይ የተመሰረተ እና መሰረታዊ የግዥ መርሆችን የጠበቀ መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበት ተገለፀ።
***
የመንግስት ግዥ በእቅድ ላይ የተመሰረተ እና መሰረታዊ የግዥ መርሆችን የጠበቀ መሆኑ መረጋገጥ እንዳለበት ተገለፀ።

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት ገንዘብ ቢሮ ለቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች፣ አባላት እና ባለሙያዎች በመንግስት ግዥ አፈፃፀም መሰረታዊ ፅንሰ ኃሳቦች እና መርሆች ዙሪያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

አቶ ቻላቸው ካህሊ በገንዘብ ቢሮ የመንግስት ግዥ ንብረት አስተዳደር ኦዲት ክትትል ዳይሬክተር ስልጠናውን ሲሰጡ እንደገለፁት፤ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች እና አባላት በመንግስት የግዥ አፈፃፀም ፣ተግባርና ኃላፊነት ዙሪያ የተሟላ እውቅና እንዲኖራቸውና ስለ አፈፃፀማቸው በሚያደርጉት የክትትልና ቁጥጥር ተግባር ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማገዝ ስልጠናው ያለው ጠቀሜታ የጎላ እንደሆነ ገልፀዋል።

የመንግስትን ግዥ በሕግ የመምራት አስፈላጊነትን የገለፁት አቶ ቻላቸው፤ በአንድ ወጭ ስርዓት ለመምራት እና ለግዥ የሚውለው ወጭ ከመንግስት ጠቅላላ ወጭ ያለው ድርሻ ከፍተኛ በመሆኑ የህዝብ ሐብት ለብክነት እንዳይጋለጥ እና በሕግ እንዲመራ ለማድረግ አጋዥ በመሆኑ ፣የሰው ኃይል ፣አቅራቢና ገበያውን በስርዓት ለመምራት አስፈላጊ እንደሆነ ገልፀዋል።

ባለ በጀት የመንግስት ተቋማት የግዥ እቅድ አዘጋጅቶ ማፀደቅና በጀት መኖሩን ከማረጋገጥ በተጨማሪ የመንግስት ግዥ በእቅድ ላይ የተመሰረተ እና መሰረታዊ የግዥ መርሆችን የጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን ዳይሬክተሩ በስልጠናው ወቅት ገልፀዋል።

ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም ማስገኘት፣ ከአድልዎ ነፃ የሆነ አሰራር መፍጠር ፣ ግልፅነት እና ተጠያቂነት የመንግስት ግዥ መርሆች እንደሆኑ ተገልጿል።

የግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት በግዥ ዘዴ፣ ዓይነት፣ የበጀት ምድብ፣ ዋጋ፣ ጊዜን በዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ የግዥ እቅድ እንደሆነ ከመገለፁ በተጨማሪ፤ የግዥ ፈፃሚ አካላት የሚፈፀመውን የግዥ እቅድ መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበትና በአዋጁ እና በመመሪያው የተደነገገ፣ እንዲሁም በጀት ፀድቆ በደረሰው ለሰላሳ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ተከልሶ ማፀደቅ እንደሚጠበቅበት ተገልጿል።

ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ግዥዎች ለመለየት፣ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማን ለማከናወን ፣ የቁጥ ቁጥ ግዥን በመከላከል ጊዜና ወጭን ለመቆጠብ፣ የጨረታ ውድድር አድማስን ለማስፋት እና የተመደበውን በጀት በወቅቱና በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን ለመረዳት የግዥ እቅድን ማዘጋጀት አስፈላጊ እንደሆነ ተገልጿል።

ዘገባው፦ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

26 Nov, 10:42

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በአበርገሌ ወረዳ 03 ሰቃ ቀበሌ ጥራሬ ወንዝን ተጠቅመው እየለማ ያለ ሽንኩርት!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

26 Nov, 10:40

"ግዙፍ የጤና ተቋማት ግንባታ ለክልሉ ህዝብ የሚያበረክቱት አስተዋጾኦ ከፍተኛ ነው" አብዱልከሪም መንግስቱ

1 ቢሊየን ብር በሚጠጋ በጀት እየተገነባ የሚገኘው የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ሆስፒታል የክልል እና የዞን እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች በተገኙበት ጉብኝት ተካሂዷል።

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ክቡር አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በጉብኝቱ ወቅት እንደተናገሩት ግንባታው ለከተማው ህዝብ ከሚሰጠው አገልግሎት ባሻገር በዞኑ አካባቢ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

ቢሮ ሃላፊው አያይዘውም ግንባታው በተያዘለት ቀን እንዲጠናቀቅ ቢሮው አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ያሉ ሲሆን ተቋራጩ ድርጅትም ግንባታውን በፍጥነትና በጥራት በማጠናቀቅ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

አዲሱ ጠቅላላ ሆስፒታል በ60 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈና ባለ ሶስት ወለል ህንፃ ያለው ሲሆን የፊዚካል ስራው 63 በመቶ መጠናቀቁ የተገለጸ ሲሆን ሶስት መቶ አልጋዎች እና ሌሎች ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች እንዲሁም ሁለት ሊፍቶች የተገጠሙለት መሆኑም ተመላክቷል።

በአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ በክቡር አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ የተመራ የልዑካን ቡድን በደብረ ብርሃን ከተማ ጤና መምሪያ ስር የተከናወኑ ዋና ዋና የጤና ተግባራት ጉብኝት እና የአገልግሎት አሰጣጥ እና ሂደት ተዟዙረው ተመልክተዋል።

Amhara Communications

26 Nov, 10:38

በዘንድሮው የአማራ ክልል መስኖ ልማት ምን እየተከናወነ ነው?
የአማራ ክልል አርሶ አደሮች ከመኸር ሰብል መሰብሰብ ጎን ለጎን ትኩረታቸውን በበጋ መስኖ ልማት ላይ አድርገዋል።
ለመስኖ ልማት የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ፦
🌱 በያዝነው ዓመት 1 ሚሊዮን 197 ሺህ 028 አርሶ አደሮች በመስኖ ልማት ይሳተፋሉ።
🌱 60 በመቶ የሚጠጉ አርሶ አደሮች መስኖ ማልማት ጀምረዋል።
🌱 487 የአርሶ አደሮች የመስኖ ልማት ውይይቶች ተካሂደዋ።
🌱 በውይይቶቹ 248359 አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡
🌱 6 ሺህ 237 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመስኖ ቦይ ጠረጋ ተካሂዷል።
- በዘመናዊ የተጠረገ የመስኖ ቦይ 1397 ኪሎ ሜትር
- በባሕላዊ የተጠረገ የመስኖ ቦይ 4840 ኪሎ ሜትር
🌱 በመስኖ ሰብል አመራረት የጊዜ ሰሌዳ ለ94 ሺህ 885 አርሶ አደሮች እንዲዘጋጅላቸው ተደርጓል።
🌱 የዘንድሮውን መስኖ በሜካናይዜሽን ለማገዝ እየተሠራ ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

23 Nov, 18:54

#የጥራት_መንደር_ብሔራዊ_የጥራት_መሠረተ_ልማት‼️

ስለ 'የጥራት መንደር' በጥቂቱ፦
👇👇👇

✍️ ከ8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ መዋእለ ንዋይን በመመደብ የተገነባ መንደር ነው፣

✍️ ከ7 ነጥብ 2 ሄክታር በላይ ቦታ ላይ ያረፈ ነው፣

✍️ በውስጡ እጅግ ዘመናዊ ፋሲሊቲዎች ተሟልተዋል፣

✍️ እጅግ የዘመኑ ቤተሙከራዎችን ይዟል፣

✍️ በቂ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችን ይዟል፣

✍️ ከ1 ነጥብ 3 ሄክታር በላይ ቦታ የአረንጓዴ ስፍራ አለው፣
🌾🌾🌾🌾🌾🌾🌾

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

23 Nov, 18:32

የሩዝ ሰብል ወደ ሀገራችን የገባበት ታሪካዊ አመጣጥና አሁናዊ እንቅስቃሴ

የሩዝ ሰብል ወደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የገባው መቼና የት ክልል እደሆነ ያውቃሉ? አዎ ሩዝ ወደ ኢትዮጵያ ምደር የገባው 1976 ዓ.ም ሲሆን በክልልም ደረጃ አማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ጅግና ቀበሌ ሲሆን አሁን "ጀግና" ተበሎ የሚጠራው የሩዝ ዝርያ ከዚሁ የአካባቢ የተሰጠ የስም ስያሜ ነዉ።

ሩዝ ለመጀመረያ ጊዜ ከስሜን ኮርያ ወደ ኢትዮጵያ የገባና ለመግባቱ ምክንያት የሆነው የደረግ መንግስት የህብረት ስራ ማህበራትና ሰፈራ መር በመሆኑ ከኮርያኖች ተሞክሮ በመውሰድ በተለይ በደቡብ ጎንደር ዞን የጅግና አምራቾች ህብረት ሰራ ማህበራት ሰለነበረ ሰሜን ኮርያ የሩዝ ምርትና የሰራ ባህልን ሳምንቱን ሙሉ መሰራት ያለማመዱና በተግባር ያሳዩ ነበር።

የስራ ባህላቸውን በተለይ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች እንዲለማመዱና የፎገራ ወረዳ አርሶ አደሮች "ውሀ በላኝ ሲል የነበረው አሁን ዉሀ አበላኝ" ወደ ሚል አባባል ያስቀየረ የሩዝ ሰብል፣ ለምግብነት፣ ለዳቦ፣ ለእንጀራ፣ ለጠላ እና ለቅንጨ ከብዙ በጥቂቱ ለነዚህ አገልግሎት ይውላል።

በገብያም ቢሆን ከጤፍ ትዩዩ የሆነ ዋጋ አለው።

ሩዝን በአካባቢው ለመጀመሪያ ጊዜ ያመረቱና ተጠቃሚ የሆኑ አረሶ አደሮች ያሉ ሲሆን ከነዚህም ውሰጥ በደራ ወረዳ የጅግና ቀበሌ አርሶ አደር የሆኑት አርሶ አደር አብራሃም ተፈረደባቸው፤ የሩዝ ሰብል በተለይ ለውሃ ገብ መሬት ጋር ተስማሚ በባለሙያ ከተደገፈ በምርታማነትም ከሌሎች የሰብል አይነት የተሻለ ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልል ደረጃም ልዩ ትኩረት የተሰጠውና ለሁሉም ዞን በሚባል ደረጃ ዕቅድ ተሰጥቷቸው በማልማት ላይ መሆናቸውን ከግብርና ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

Amhara Communications

23 Nov, 18:15

በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሰሃላ ሰየምት ወረዳ በአቅኝ ቀበሌ በመሽሃ ወንዝ ዳርቻ በመስኖ እየለማ የሚገኝ የማንጎ ተክል ከፊል ገጽታ በፎቶ።

📸ዋግ ኽምራ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

23 Nov, 18:08

በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓንጓ ወረዳ እየለማ ያለ የኑግ እና የደጉሳ ልማት ከፊል አሁናዊ ገጽታ በፎቶ

📸ጓንጓ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

18 Nov, 17:53

“የወልቃይት ሕዝብ ማንነቱን አስጠብቆ እዚህ ደርሷል፡፡” መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

18 Nov, 17:38

ፕሮዴቨሎፕ መንት ኔትወርክ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት አካሄደ

ፕሮዴቨሎፕ መንት ኔትወርክ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ከአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት ጋር በመተባበር በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና አካባቢው በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከማህበረሰቡ ጋር በከሚሴ ከተማ ውይይት አካሂዷል፡፡

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊን እና የከሚሴ ከተማ ከንቲባ ሸሪፍ ቃሲምን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎችን አቀባበል አድርገዋል።

የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ እንደገለፁት፤ ድርጅቱ ከዚህ በፊት በአካባቢው ሰላም ዙሪያ በርካታ ስራዎች መስራቱን ገልፀው በዚህም ከአጎራባች ዞኖችና ወረዳዎች ጋር የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ወደ ዘላቂ ሰላም በማሸጋገር የበኩሉን ድርሻ ለማበርከት እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ኢንጌጅመንት ዳይሬክተር ወ/ሮ ብሌን አስራት በበኩላቸው፤ ድርጅቱ በአካባው ሰላምና ፀጥታ ላይ እንደሚሰራም ገልጸው በአካባቢው የሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የሰላም እጦት ችግሮች መንስኤዎችና መፍትሄዎች ላይ በዞኑ ከሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ በአካባቢው የሚከሰቱ የሰላም ችግሮች ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ እንዲፈቱ ግብረሰናይ ድርጅቱ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው ለሰላም መስፈን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡

Amhara Communications

18 Nov, 17:34

በምእራብ ጎጃም ዞን ጃቢ ጠህናን ወረዳ ርግብ ቀበሌ በቀሪ ርጥበት እየለማ የሚገኝ የሽምብራ ሰብል አሁናዊ ገጽታ::

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

18 Nov, 16:33

በአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ባለ ብዙ ጸጋ በሆነችው ጓንጓ ወረዳ ቻጃምቋ ቀበሌ በኩታ ገጠም (ክላስተር) የበጋ መስኖ ስንዴ ለማልማት እየተደረገ ያለ አሁናዊ የማሳ ዝግጅትና የዘር ስራ በከፊል።

📸ጓንጓ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

06 Nov, 06:32

ከረሃብ ነፃ ዓለም ጉባዔ ተሳታፊዎች በቤተመንግሥት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከረሃብ ነፃ ዓለም ጉባዔ ተሳታፊዎች ጋር በቤተመንግስት በፎቶ::

ኢ.ፕ.ድ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

06 Nov, 06:23

በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ጃማ ወረዳ የእለማ የሚገኝ የስንዴ ሰብል አሁናዊ ገጽታ በከፊል

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

06 Nov, 06:11

"የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ"
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

ኢ ፕ ድ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

06 Nov, 06:03

የጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገቡ

የየጊኒ ጠቅላይ ሚኒስትር አማዱ ኡሪ ባህ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ሲገቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

06 Nov, 05:55

ሩሲያ ከአጋርና ወዳጅ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለፁ
*****************
በሩስያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ገነት ተሾመ (ዶ/ር) የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን አቅርበዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፕሬዝዳንት ፑቲን ባስተላለፉት መልእክት ሩሲያ የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ከመሰረቱ አገራት ጋር ጠንካራ ወዳጅነት ያላት መሆኑን ገልጸዋል።

የሩስያ-አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሰብስባን ለማስተናገድ ዝግጅት ማጠናቀቋን ተናገረዋል።

በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰብዓዊ ጉዳዮች ከአጋርና ወዳጅ አገራት ጋር በጋራ ለመሥራት ዝግጅት መሆኗን መግለፃቸውን የኢ.ፕ.ድ ዘግቧል፡፡

በቅርቡም በካዛን ከተማ 16ኛውን የBRICS መሪዎች ጉባኤ ተካሂዷል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

01 Nov, 15:43

በወለቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሲሰጥ የቆየው የመካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተጠቀቀ

በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን "የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ቃል ለሶስተኛ ዙር አመራሮች ለተከታታይ አስር ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

በመድረኩም የአማራ ክልል ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ አማረ ሰጤ፣ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት ኃላፊ አቶ ገ/እግዚአብሔር ደሴ፣ ከፍተኛ የዞኑ የስራ ኃላፊዎችና ሰልጣኞች ተገኝተዋል።

ስልጠናው በቀጣይ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሮችን ለመስራት ትልቅ አቅምን የሚሰጥ ነው ያሉት የአማራ ክልል ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤ አቶ አማረ ሰጤ ሰልጣኞች በተሻለ መነሳሳትና ቁርጠኝነት የወሰዱትን ስልጠና በመጠቀም መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ጠንካራ ስራን ለመፈፀም የሚረዳና ታች ያሉትን ሰራተኞች በተሻለ ሁኔታ በማብቃት ሁሉም የስራ ኃላፊዎች ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

ስልጠናው ከአሁን በፊት ለከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ መቆየቱን ያነሱት የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ ቤት ኃላፊ አቶ ገ/እግዚአብሔር ደሴ ብቁና ሀገረን ወደተሻለ እድገት የሚያሻግር አመራርን ለመፍጠር ስልጠናው ትልቅ አቅም እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

ሰልጣኞች ያገኙትን ስልጠና ወደ ተግባር በመቀየር የተሻለ ስራን በመስራት ለመጭው ትውልድ አሻራን ማሳረፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ስልጠናው በቀጣይ ለሌሎች የመንግስት ሰራተኞች በተዋረድ እንደሚሰጥ ጠቁመው አማራዊ ማንነታችን በህግ እስኪረጋገጥ ከምንጊዜውም በላይ በመተባበር መስራት አለብን ሲሉ ተናግረዋል።

ከስልጠናው የተሻለ ልምድ እንዳገኙ የገለጹት ደግሞ በስልጣናው የተሳተፉ ሰልጣኞች ናቸው።
Wolkayt Tegedie Setit Humera Zone Communication

Amhara Communications

01 Nov, 15:34

በአማራ ክልል ደቡብ ጎንደር ዞን በፎገራ ወረዳ የለማ አሁናዊ የሩዝ ሰብል ከፊል ገጽታ በፎቶ፤

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

01 Nov, 13:55

‹‹ስልጠናው ህዝብን ለማገልገል ተደማሪ እውቀትና ክህሎት ፈጥሮልናል፤ በቀጣይም የሚከናወኑ ተግባራትን በቁርጠንነት ለመፈፀም ያስችለናል፡፡›› በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳ ውሃ ማዕከል ሰልጣኞች

"የህልም ጉልበት ለእምርታዊ ዕድገት" በሚል በሚል መሪ ሀሳብ ለተከታታይ ቀናት በዞኑ ለሚገኙ ከፍተኛና መካከለኛ የሥራ ኃላፊዎች በገንዳ ውሃ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

በሥልጠና ማጠቃለያ የአብክመ ህዝብ ቅሬታ ሰሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አገኘው ካሳ፤ ሰልጣኝ የስራ ኃላፊዎቹ ሰላምን በዘላቂነት በማጠናከር የተሰጣቸውን ስልጠና በመጠቀም በሚያገለግሉበት ተቋም ህዝብን በታማኝነትና በቁርጥኘነት ማገልገል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ህልም ዕውን እንዲሆን በየደረጀው የሚገኙ አመራሮች በፅናት፣ ቁርጠኝነት እና በትብብር መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል።

የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ በበኩላቸው፤ ለተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በጥሩ ሁኔታ መጠናቀቁን ገልጸው፤ ከስልጠናው የተገኘውን እውቀትና ግንዛቤ በመወስድ በየደረጃው የሚገኙ የስራ ኃላፊዎች በቀጣይ ስራዎችን በትጋት ማከናወን እንደሚጠበቅ አስገንዝበዋል።

ስልጠናው የአመራሩን አቅም በማሳደግ ውስጣዊ አንድነትን ለማጠናከርና የሀገርን ብልጽግና ለማረጋገጥ ያለመ ነው ያሉት ደግሞ የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ እያሱ ይላቅ ሲሆኑ ሰላምን በዘላቂነት ለማፅናት ምንግዜም ተግተን መስራት አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

ስልጠናው ህዝብን ለማገልገል ተደማሪ እውቀትና ክህሎት ፈጥሮልናል፤ በቀጣይም የሚከናወኑ ተግባራትን በቁርጠንነት ለመፈፀም ያስችለናል ሲሉ የማዕከሉ ሰልጣኞች መናገራቸውን ከምዕራብ ጎንደር ዞን ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Amhara Communications

01 Nov, 13:29

“ኢቲዮ ቴሌኮም ከማገናኘት አልፎ የሚያገበያይ ተቋም ሆኗል”
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

01 Nov, 13:23

"የተቋም ግንባታ ላይ እርብርብ በማድረግ በግብርና ዘርፉ የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ይገባል" ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የአንደኛው ዙር የባለሙያዎች የቴክኒክ ቡድን የመስክ መልስ ግምገማ ጥቅምት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ግምገማ አካሂዷል።

ከግብርና ቢሮ እና ከተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ በመውረድ የመስክ ላይ ክትትልና ድጋፍ አድርገዋል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ በግምገማ መድረኩ ተገኝተው ማጠቃለያና የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል።

በክትትልና ድጋፍ ወቅት የታዩ መልካም ስራዎች፣ ድክመቶች፣ ልምድ የሚወሰድባቸው ተግባራትና የቀጣይ የትኩረት ማዕከል በሚል ተለይተው የየዞኖችን አፈፃፀም በሚያሰይ መልኩ ዝርዝር ግብረ መልስ መዘጋጀት እንዳለበት ተናግረዋል።

ወቅታዊ የግብርና ስራዎች ላይ ከፍተኛ እርብርብ ማድረግ አለብን ያሉት ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ቀድመው የሚደርሱ ሰብሎችን መሰብሰብ፣ ሰብልን ከተባይና ከበሽታ መከላከል በተለይ የግሪሳ ወፍና ቢጫ ዋግን ለመከላከል በቅንጅት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። መደበኛ ኮምፖስት ዝግጅት በወቅቱ ማጠናቀቅ ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።

የመስኖ ልማት በተለይም የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የአምናውን በሚያካክስ ሁኔታ መፈፀም እንዳለበት ተናግረዋል። የተፈጥሮ ሀብት ልማትና ጥበቃ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ በክልሉ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርን በዓይነትና በጥራት ማስፋፋት ያስፈልጋል ብለዋል። በህብረት ስራ ማህበራት የተጀማመሩ የሪፎርም ስራዎች በተሟላ ሁኔታ መተግበር እንዳለበት እንዲሁም የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ተግባራት ትኩረት ተሰጥቷቸዋል እንዲፈፀሙ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ከዞን እስከ ቀበሌ ድረስ የተቋም ግንባታ የቀጣይ ቁልፍ ተግባር ሆኖ እንዲፈፀም አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ግብርናን ሊያሻግር የሚችል ብቁ የሰው ሀይል ማዘጋጀት፣ ስራን ማዘመን ወይም ዲጅታላይዝ ማድረግ፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን እየቀመሩ ማስፋት እና የስራ አፈፃፀምን መሰረት በማድረግ ሰራተኛን ማበረታታትና እውቅና መስጠት ለሞዴል ተቋም ግንባታ መሰረታዊ ነገሮች መሆናቸውን ዶ/ር ድረስ ሳህሉ አስረድተዋል።
Amhara Agriculture Bureau

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

27 Oct, 01:11

በአማራ ከልል ደቡብ ጎንደር ዞን ፎገራ ወረዳ የሩዝ ሰብል አሁናዊ ከፊል ገጽታ በፎቶ፤

ፎገራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

27 Oct, 01:07

"የአሰራር ስርዓትን ማሻሻል፣ በቴክኖሎጂ ማዘመን እና ትብብር ለኮንስትራክሽን ዘርፉ ዕድገት ወሳኝ ነው" አህመዲን መሐመድን (ዶ.ር) በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ

በአማራ ክልል ከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ የባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

በመድረኩ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተሞች እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሐመድን (ዶ.ር) የኮንስትራክሽን ዘርፍ ያለበት ደረጃ፣ የገጠሙት እንቅፋቶች፣ የተወሰዱ መፍትሄዎች እና ከባለ ድርሻ አካላት የሚጠበቁ ጉዳዮችን በሚመለከት በዝርዝር አይተናል ያሉ ሲሆን የውይይቱ ተሳታፊዎችም ዘርፉ እንዲጠናከር ያግዛሉ ያሏቸውን ጉዳዮች አንስተዋል ብለዋል።

ሃላፊዉ አክለዉም የአሠራር ሥርዓትን ከማሻሻል ጀምሮ ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን እና የክትትልና ድጋፍ ስርዓትን በማጠናከር ፕሮጀክቶች ተጠናቅቀው ለሕዝብ ተጠቃሚነት ዝግጁ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ መግባባት ላይ ደርሰናል። ሥራ ተቋራጮችን፣ አማካሪዎችን እና በዘርፉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ማበረታታት እና አቅም ማሳደግ ይገባል። ከለውጡ ወዲህ የፕሮጀክት መፈጸም ባህል ተሻሽሏል፤ ተቋርጠው የነበሩ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ። ይህንን መልካም ባህል ለማስፋትም የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ትብብር ወሳኝ ነው ብለዋል።

የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከችግር ማነቆ እንዲወጣ ለማስቻልና ለኢኮኖሚው የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እንዲያድግ የክልላችንን ሰላም ማስጠበቅ ወሳኝ ነው ያሉት ሃላፊዉ በቀጣይም በክልላችን በሚከናወኑ የግንባታ ፕሮጀክቶች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች በማድረግ፣ ፕሮጀክቶችን በመከታተል፣ መረጃ በማሰባሰብ እና ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ ለዘርፉ ስኬት በትብብር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል።
Ahmedin M. Ahmed

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

27 Oct, 01:01

በደቡብ ወሎ ዞን አልብኮ ወረዳ በ013 ቀበሌ የጤፍ ሰብል አሁናዊ ገጽታ በከፊል፤

South Wollo Zone Gov. Communication Dept.

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

22 Oct, 13:53

የአዊ ብሄ/አስ ብልፅግና ፓርቲ የስልጠና መርሃ -ግብር በእንጅባራ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

የስልጠና መርሃግብሩ " የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት " በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተሰጠ የሚገኘው።

በብልጽግና ፓርቲ የአዊ ብሄ/አስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለሙ ሰውነት፥ የስልጠናው ዓላማ የአመለካከት እና የተግባር አንድነትን በማጎልበት፣ የመሪዎችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ መሆኑን ገልጸዋል።

ብልጽግና ፓርቲ በችግር ውስጥም ሆኖ ስኬቶችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ እንደሆነ አቶ አለሙ ተናግረዋል ።በ2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና የሚያጠናክር ለመዋቅሩ በተደራጀ ሁኔታ ስልጠና እየተሠጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በተሰጡት ስልጠናዎችም ለውጦች መመዝገባቸውን አንስተዋል።ህልመኞች ሀገር ያሻግራሉ፣ ህልመኞች ስንሆን ያለንን ፀጋ እንረዳለን፣ሀገር ስለመገንባትና ህዝብ ስለመለወጥ እናስባለን ነው ያሉት ሀላፊው።አሁናዊው ትንቅንቅ የፖለቲካ አውድ ሳይበግረን ህልማችንን ለማሳካት የተስፋ ስንቅ የሚጨበጥበት መድረክም እንደሆነ አመላክተዋል።

ስልጠናው ሰላም እና መረጋጋት የምንፈጥርበት፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር የገጠመንን ስብራት የምንጠግንበት ትልቅ መድረክም እንደሆነ ተናግረዋል።

የአዊ ብሄ/አስ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለው እንደገለፁት ስለነገ መዳረሻችን የምናስብ ከሆነ የጋራ የተግባባ ህልም ያስፈልገናል ብለዋል።ለዚህ ደግሞ ከአምና ዘንድሮ መሻሻል ያለው የትርክት እምርታ(ሪፎርም) እንደሚያስፈልግ አስገንዘበዋል ።በስልጠናው የውስጣችንን ልዩነት በማጥበብ እና ህብረ ብሔራዊ አንድነትን የምናጠናክርበት ነው ብለዋል።

የስልጠናው ግብ ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር፣ የተጀመረውን ሪፎርም መሬት ማስነካት፣ የፓርቲውን እሳቤ እና ፍላጎት መረዳት እና መገንዘብ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡አያይዘውም ጠንካራ ተቋማት መገንባትእና መሪዎች በሥነ ምግባር ተምሳሌት ልንሆንም ይገባናልም ብለዋል፡:

የአማራ ክልል ምክር ቤት መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አየን ብርሃንአቶ አየን ብርሃን ባስተላለፍት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ በችግር ውስጥም ሆኖ የስኬቶች ባለቤት እንደሆነ ገልፀዋል። ሀገርን ለማሻገር የሚያስችሉ የተለያዩ ሴኬታማ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ ይገኛል።

ስልጠናው አመራሩ ወቅቱ የሚጠይቀውን የአመለካከት ጥራት ግንዛቤ የሚፈጥር እና አሁን ለገጠሙን የሰላም እጦት ችግሮቻችን መፍትሄ የሚቀመጥበት እንደሆነም ተናግረዋል። የገጠምንን የፖለቲካ እና የሰላም ስብራት የሚጠግን እና አቅም የሚፈጥር በመሆኑ ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ አሳስበዋል።

የአሁኑ ስልጠና አምና ላይ" ከእዳ ወደ ምንዳ "በሚል መሪ ሀሳብ የተካሄደው ቀጣይ የስልጠና ክፍል ነው።

Awi communication

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

22 Oct, 13:49

ደቡብ ወሎ ዞን ተንታ ወረዳ የጤፍ ክላስተር ከፊል ገጽታ በፎቶ::

ደቡብ ወሎ ኮሙኒኬሽን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et

Amhara Communications

22 Oct, 13:47

"የሕልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛ ዙር የብልጽግና ፓርቲ የአመራር ስልጠና ጀመረ

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች "የሕልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት"በሚል መሪ ሃሳብ ከጥቅምት 12/2017 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም የሚቆይ 3ኛ ዙር የአመራር ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በስልጠናው የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች፣ ከሁሉም ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ተሳትፈዋል።

የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ምክትል አስተዳደሪና የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ሹመት ጥላሁን የህልም ጉልበት ለእምርታዊ እድገት በሚል ሃሳብ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ወደ ውቢቷ ሰቆጣ ከተማ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።

አቶ ሹመት አያይዘውም በዚህ ስልጠና ሁለት አቢ አላማዎችን ያሉትና በጥቅብ ዲሲፕሊን የሚመራ ሲሆን አንደኛው አላማ ፓርቲያችን ብልጽግና በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና በውጨ ግንኙነት ሃገር ሊያሻገር የሚችል ጥልቅ ሃሳብ የያዘ ስልጠና ነው ሲለ ገልጸዋል።

ከእዳ ወደ ምንዳ ቀጣይ ምዕራፍ የሆነው ስለህልም ጉልበትና ልንደርስበት ስለምንፈልገው እድገት ከጽንስ ሃሳብ ጀምሮ ይህ አመራር ሊረዳቸው የሚገቡ ጉዳዮችና ባለፉት ስድስት አመታት ፓርቲው ሃገር እየመራባቸው የመጣባቸውና በፈተና ውስጥ ሆኖ ያሳካቸው የልማት፣ የፖለቲካና የውጭ ግንኙነት የዲፕሎማሲ ድሎችን በስፋት የምናይበት ስልጠና ነው ሲሉ አቶ ሹመት ገልጸዋል።

ሁለተኛ አላማው ርዕሰ በርሳችን የምንማርበትና ልምድ የምቀስምበት የስልጠና መድረክ ነው ሲሉ አሳስበዋል።

Amhara Prosperity Party /APP/

Amhara Communications

22 Oct, 13:46

Amhara Communications pinned Deleted message