ADDIS INSIDER - ETH @addisinsider_eth Channel on Telegram

ADDIS INSIDER - ETH

@addisinsider_eth


ይህ ቻናል ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና የተረጋገጡ እና አዝናኝ የሆኑ መረጃዎች የሚቀርቡበት ነው!

ADDIS INSIDER - ETH (Amharic)

አዲስ እንስሳት - ኢትዮጵያ ፡ የዚህ ቡድን ቦታዎች አሉታዊና ትክክለኛ የመከታተያ ምንልና አምልኮና የቃልም ነገር። ይህ ቢስ በኢትዮጵያ በተመኖችና ወደ ህዝብ ሰላችኋል። ይህ ቢስ እናውቃለን፣ ለሁለተኛ ኀጥያት የመከታተያ ምንልና የአገልግሎትን ያለ የሚሆን መረጃዎችን ያግኙ።

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 16:01


የቆጣሪዎች ቅያሪ ሊደረግ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከጥር ወር ጀምሮ አውቶሜትድ የሆኑ የቅድመ ክፍያ (Pre-Paid) ቆጣሪዎች ቅያሪ እንደሚያደርግ ገልጿል።

አዲሶቹ ቆጣሪዎች ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ሲውሉ የነበሩ በካርድ የሚሰሩ የቅድመ ክፍያ ቆጣሪዎችን የሚያስቀር ነው ተብሏል።

የመጀመሪያ ዙር ትግበራ 10ሺ በሁለተኛ ዙር ትግበራ 15 ሺ በአጠቃላይ 25 ሺ ቆጣሪዎች ላይ ቅያሪ ይከናወናል ተብሏል።

ደንበኞች በስልካቸው በቴሌብር ወይም በሞባይል ባንኪንግ የኤሌክትሪክ ግዢ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው እንደሆነ ተነግሯል።

ቆጣሪዎቹን የመቀየር ፕሮጀክት የሚካሄደው ዝቅተኛ የሃይል ተጠቃሚ በሆኑና ለቤት ውስጥ አገልግሎት የሚውሉ የሲንግል ፌዝ (Single Phase) ቆጣሪዎች ላይ እና በአነስተኛ ኢንዱስትሪዎች አገልግሎት ላይ በሚውሉ የስሪ ፌዝ (Three Phase) ቆጣሪዎች ላይ መሆኑ ተገልጿል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 15:57


ሩሲያ ለመጀመሪያ ጊዜ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል በዩክሬን ላይ ተኮሰች።

ሩሲያ ዛሬ ጠዋት ላይ ከደቡባዊ ከተማዋ አስትራክሃን አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል (አይሲቢኤም) የተባለውን ረጅም ርቀት ሚሳዔል መተኮሷን የዩክሬን አየር ኃይል አስታወቀ።

አየር ኃይሉ እንዳለው በተለያዩ ዓይነት ሚሳዔሎች በተፈፀመው ጥቃት ዲኒፕሮ ክልል ዒላማ ተደርጋለች።

የክልሉ ኃላፊ በተፈፀመው በዚህ ጥቃት የደረሰው ጉዳት በውል ባይታወቅም ቢያንስ 15 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ከተጎዱት መካከል የ16 እና የ17 ዓመት ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰው ዘጠኝ ሰዎች በሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው እንደሆነ፤ ነገር ግን ስላሉበት ሁኔታ አለመታወቁን የክልሉ ኃላፊ ሴሪይ ሊይሳክ ገልጸዋል።

የዩክሬን ድንገተኛ አገልግሎት በእሳት የተያያዙ የመኖሪያ ሕንጻዎች እና የወደመ የአካል ጉዳተኞች የማገገሚያ ማዕከልን የሚያሳዩ ምሥሎችን አጋርቷል።

የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪም አገራቸው 'በአዲስ የሩሲያ ሮኬት' መጠቃቷን እና ጥቃቱ የተፈፀመበት መሣሪያ አይሲቢኤም የተባለው የባልስቲክ ሚሳዔል ዓይነት ባህርይ እንዳለው ገልጸዋል።

ሆኖም ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ወደ ዩክሬን የተተኮሰው ሚሳዔል ባሊስቲክ ሚሳዔል እንጂ አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል አይደለም ማለታቸውን የቢቢሲ የአሜሪካ አጋር የሆነው ሲቢኤስ ኒውስ ዘግቧል።

ሩሲያ በባልስቲክ ሚሳዔል ጥቃት ፈፅማለች ስለመባሏ የተጠየቁት የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ አስተያየታቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

ሩሲያ ጥቃቱን መፈፀሟ ከተረጋገጠ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወረራ ከፈፀመችበት ጊዜ ጀምሮ በአይሲቢኤም ጥቃት ስትፈፅም ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ይሆናል።

ቢቢሲ

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 15:47


ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ

ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ዕዝ አውጥቷል፡፡

ከኔታንያሁ ባሻገር የቀድሞው የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮዓቭ ጋላንት እና የሐማስ ጦር አዛዥ የእስር ትዕዛዝ ወቶባቸዋል።

የዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICC) ዳኞች በእስራኤል የቀረበውን መከራከሪያ ውድቅ አድርገውታል።

ምንም እንኳን መሀመድ ዴኢፍ በእስራኤል ጦር ተገድለዋል ቢባልም የእስር ትዕዛዙ ወቶባቸዋል።

በጋዛው ጦርነት የጦር ወንጀል ፈጽመዋል፤ ሰብዓዊ ያልሆኑ ድርጊቶችን ፈጸምዋል በሚል ነው ሶስቱም የእስር ትዕዛዙ የወጣባቸው።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 12:53


በደራ ወረዳ በአንድ ወጣት ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ ቁጣን ቀስቅሷል።

ከሳምንቱ መጀመሪያ ቀናት ወዲህ በማህበራዊ ሚዲያ በመሰራጨት ላይ የነበረው የደራ ወረዳ ነዋሪ የሆነ የ17 አመት ወጣት አንገቱ ሲቆረጥ የሚያሳየው ቪዲዮ በርካቶችን ያሳዘነ፣ ቁጣን የቀሰቀሰ ተግባር ሆኗል።

አሰቃቂ ግድያውን የሚያሳይ ቪዲዮ ከመሰራጨቱ በፊት፤ በአከባቢው በታጣቂዎች በሚፈጸም ተደጋጋሚ ጥቃት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለው በጫካ ውስጥ የተደበቁ ሰዎች ፎቶግራፎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ዘዴዎች በስፋት ተጋርተዋል።

ከቅርብ አመታት ወዲህ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኘው የደራ ወረዳ የጦርነት አውድማ ሆናለች፣ በወረዳዋ በመካሄድ ላይ ያሉት ግጭቶች ከፍተኛ ውድመት አስከትለዋል።

በተለይም ከ2015 በኋላ በመንግስት ሃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተደረጉ ከፍተኛ ውጊያዎች ወረዳዋን ወደ አሳዛኝ የግጭት ማዕከልነት ቀይሯታል፤ በዚህም የበርካታ የአከባቢው ነዋሪዎች ህይወት ተቀጥፏል፣ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ቀውስ ዳርጓል።

ከሀምሌ ወር 2016 ዓ.ም እስከ ጥቅምት ወር 2017 ዓ.ም ባሉት አራት ወራት ውስጥ በመንግስት ሀይሎች እና በታጣቂዎች መካከል በተደረጉ ግጭቶች ከ43 በላይ ንፁሀን ዜጎች ህይወት ማለፉን አዲስ ስታንዳርድ ከደራ ወረዳ ነዋሪዎች መረጃ ማግኘቱን ዘግቧል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 12:31


የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ አሳለፈ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በስድስት የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ የተወያየ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከል የመካከለኛ ዘመን (2017-2021) የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ አንዱ ነው፡፡

ምክር ቤቱ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ሙሉ ይዘት ከላይ በፎቶ (ፒዲኤፍ) ተያይዟል፡፡

#PMOEthiopia

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 12:20


የ15 ዓመቱ ጣልያናዊ በይፋ ከቅዱሳን መካከል አንዱ ተብሎ ሊከበር ነው።

የኮምፒውተር ሙያውን በመጠቀም የካቶሊክ ዕምነትን በማስፋፋት ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል የተባለ የ15 ዓመቱ ጣልያናዊ ካርሎ አኩቲስ በይፋ ቅዱስ ተብሎ እንደሚከበር ተዘግቧል።

በለንደን የተወለደው ካርሎ አኩቲስ፤ ገና በ15 ዓመቱ ነበር በፈረንጆቹ 2006 ላይ በሳምባ ምች ህይወቱ ያለፈው፡፡

የትኛውንም ዕምነት ከማይከተሉ ቤተሰቦቹ የተወለደው አኩቲስ ገና በልጅነቱ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያ እንደነበር ተገልጿል፡፡

ይህ ታዳጊ የኮምፒውተር ሙያውን በመጠቀም የካቶሊክ ዕምነትን በማስፋፋት ብዙ አስተዋጽኦ አድርጓል የተባለ ሲሆን፤ የፈጣሪን ህያውነት አረጋግጫለሁ በሚል ስብከቱም በበርካቶች ይታወቃል ተብሏል፡፡

ታዳጊው ህይወቱ ካለፈ በኋላ የተቀበረበት አፈር የተጠቀሙ ታማሚዎችን ፈውሷል መባሉ፤ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱሳን መካከል አንዱ እንዲሆን መወሰኗን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አቡነ ፍራንሲ በቫቲካን ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ቅዱስ አኩቲስ በመጪው ሚያዝያ 26 ላይ በይፋ ቅዱስነቱ ይታወጃል ሲሉ ለምዕመናን ተናግረዋል፡፡

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 12:01


በኦሮሚያ ክልል ለወታደራዊ ስልጠና የሚደረግ አስገዳጅ ምልመላ መባባሱን ነዋሪዎች ገለጹ።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ለወታደራዊ ስልጠና በግዳጅ የሚወሰዱ ወጣቶች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ በሰሜን ሸዋ ዞን ያያ ጉለሌ ወረዳ የፍታል ከተማ ነዋሪ ተማሪዎችን እና አርሶ አደሮችን ጨምሮ ከ250 በላይ ሰዎች በግዳጅ ወደ ወታደራዊ ስልጠና መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

በአዳማ ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንዲት እናት ህዳር 2 ቀን 2017 ዓ.ም የ17 አመት ልጃቸው ጌታቸው ተድላ ሂሪጎ በመንገድ ላይ ቆሎ እየሸጠ በነበረበት ወቅት በፖሊስ መታሰሩን ለማስለቀቅ 30 ሺህ ብር መክፈል ባለመቻላቸው ልጃቸው ለውትድርና ስልጠና መወሰዱን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ በጅማ ዞን ሰጠማ ወረዳ የግጦሽ ቦታ ለባለሀብቶች መሰጠቱን የተቃወሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ቤተሰቦቻቸው እስከ 70 ሺህ ብር እንዲከፍሉ የተጠየቀባቸው ሲሆን መክፈል የማይችሉ ከሆነ ግን “ወታደራዊ ግዳጅ እንደሚጠብቃቸው” ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 11:00


የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ጥበበ ግዮን ሆስፒታል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ አገልግሎቱ ተስተጓጎለ።

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስር የሚገኘው ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሠራተኞች በሚደርስባቸው ተደጋጋሚ ዝርፊያ እና የደኅንነት ስጋት በከፊል ሥራ ማቆማቸውን ተናገሩ።

ባለፈው ሳምንት “ጭምብል የለበሱ” እና ማንነታቸው አይታወቅም የተባሉ ታጣቂዎች በሆስፒታሉ ቅጥር ጊቢ ስምንት ሰዎችን መዝረፋቸው የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ሥራ እንዲያቆሙ አድርጓል ተብሏል።

በአማራ ክልል ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት በሆስፒታሉ “አልፎ አልፎ” የአገልግሎት መስተጓጉሎች እንዳሉ የጠቆሙ አንድ የሆስፒታሉ ሠራተኛ፤ ከሰሞኑ በተፈጸመ ጥቃት ባለሙያዎች የደኅንነት ስጋት ውስጥ መውደቃቸውን ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የሆስፒታሉ ሠራተኞች እና የሕክምና ተማሪዎች ጊቢው ያልታጠረ እና ጥበቃውም ያልተጠናከረ በመሆኑ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ ሠራተኞች እና ባለሙያዎች ባለፈው ሳምንት የተፈጸመውን ዝርፊያ ተከትሎ “እስከ መቼ” በሚል ጥያቄው መጠናከሩን ተናግረዋል።

የሆስፒታሉ ጥበቃዎች ክልሉ ውስጥ ባለው ክልከላ ምክንያት መሳሪያ ያልታጠቁ በመሆናቸው “ማንም ሰው ገብቶ እንደፈለገው ያደርጋል” ያሉት አንድ የሆስፒታሉ ባለሙያ፤ ይህም ስጋት አሳድሯል ብለዋል።

ስማቸው ሳይጠቀስ ለቢቢሲ የተናገሩ አንድ የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ ባለፈው ሳምንት የሆስፒታሉን ሜዲካል ዳይሬክተር ጨምሮ ባለሙያዎች መሳሪያ በታጠቁ ሰዎች ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው ጠቁመው፤ ተደጋጋሚ ዝርፊያ እና ዛቻ ስለደረሰባቸው ስጋታችን ካልተቀረፈ ሥራ እናቆማለን ማለታቸውን ገልጸዋል።

ቢቢሲ

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 09:22


ፎርድ ኩባንያ ሰራተኞችን ሊቀንስ መሆኑ ገለፀ።

ግዙፉ የመኪና አምራች ኩባንያ የሆነው ፎርድ በእንግሊዝ እና በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞችን ሊቀንስ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ኩባንያው ሰራተኞቹን ለመቀነስ የወሰነው ባጋጠመው ዝቅተኛ የገበያ ትስስር ምክንያት የኤሌክትሪክ መኪኖች በበቂ ሁኔታ አለመሸጣቸውን ተከትሎ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም ፎርድ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በእንግሊዝ ብቻ ከ800 በላይ ሰራተኞችን እንደሚቀንስ ያስታወቀ ሲሆን፤ በሌሎች የአውሮፓ ሀገራት ባሉት ቅርንጫፎቹ ደግሞ ከ4 ሺህ በላይ ሰራተኞችን እንደሚቀንስ አስታውቋል፡፡

የአስተዳደር ዘርፍ ሰራተኞች፣ የምርት ልማት፣ ደጋፊ የስራ ዘርፎች እና የኩባንያው የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ሰራተኞች ሊቀነሱ ከሚችሉ ሰራተኞች ውስጥ መሆናቸው ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ፎርድ ኩባንያ ባለፉት 100 ዓመታት ውስጥ በመኪና አምራችነት የሚታወቅ ኩባንያ ነው።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 09:11


Advert 👇👇👇

#የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኜ ወዳንተ መጥቻለሁ

“በጎዳናህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስላንተ ያዝዛቸዋል በእጃቸውም ይደግፉሃል፡፡” ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት፡፡ ይልቁንም የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ በርካቶችን ሲጠብቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተመልክተናል፡፡ በየዓመቱ በህዳር በ12 ቀን በዓለ ሲመቱ የሚከበረው ቅዱስ ሚካኤል የዋህ፣ ርህሩህ፣ አዛኝ፣ ለወዳጆቹ ቅርብ፣ የሰው ሁሉ ልጆችን ጠላት በእሳት ሰይፍ መትቶ የጣለው በክንፎቹ ረድኤት የሚጠብቀንም ነው፡፡ “በሰማይ ብርቱ ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላአክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም አልቻላቸውም። ከዚያም በኃላ በስማይ ቦታ አልተገኘለትም” ተብሎ በራዕይ 12÷7 እንደተጻፈ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከወደቀ በኋላ የመላዕክት ሁሉ አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡

አምላካቻን እግዚአብሔር ወደር የማይገኝለት ኃያል፣ የሚመስለው የሌለ ብርቱ፣ ዘመን የማይቆጠርለት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ መላዕክቱን መንፈስ የሚላኩትን የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው ተብሎ እንደተጻፈ የኃይሉ መገለጫ ከሆኑት አንዱ ናቸው ቅዱሳን መላዕክት፡፡ ይልቁንም የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ አምላክ ማለት የሆነው ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በርካታ ድንቅ ስራ ሰርቷል፡፡ በበዓለ ሲመቱም በየዓመቱ ከሕዳር 12 እስከ የአእላፍ መላእ በዓል እስከሚከበርበት ሕዳር 13 ለሰው ልጆች ሁሉ ከአምላካችን ምሕረት ይለምናል፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነፍሳትንም ከሲዖል ያወጣል፡፡

ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት መርቶ ያወጣበትም ቀን ነው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩባት ምድረ ግብጽ በሙሴ መሪነት ሲጓዙ፣ ግርማ ሌሊቱን በብርሃን አምድ፣ የቀኑን ሐሩር ደግሞ በደመና ጋርዶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ያገባቸው እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም ኢያሪኮን ለመያዝ ሲሰናዳ የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገለጸለት፡፡ እርሱም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለት፡፡ ወደ እርሱ ቀርቦም “አንተ ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቻአለው አለው፡፡ ኢያሱ 5÷13፡፡ የኢያሪኮ ግምብን አፍርሶም ድልን አጎናጽፎታል፡፡

ለሚጠሩት ሰዎች ሁሉ ቅርብ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም በዙሪያችን ከቦ ይጠብቀናል፣ ያድነንማል፡፡ ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም “በዚያም ዘመን ለሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታለቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” እንዲል ሁሌም ጥበቃው ከኛ ጋር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን ልጆቹን ለመርዳት ቸል አይልም፡፡ ይልቁንም በዱር በገደል ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ዳዋ ለብሰው የሚኖሩትን ገዳማዊያን ዘወትር ይጠብቃቸዋል ጸሎታቸውንም ያሳርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኖ ወደ እነርሱ ይመጣል፡፡ ለእነዚህ ገዳማዊያንና ለገዳማቸው እገዛ በማድረግ የመልአኩ ጥበቃና የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 08:43


በትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በይፋ ተጀመረ

የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከሰባት ክልሎች ከ371 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማዕከላት ለማስገባት የመለየት ሥራ መጠናቀቁን ገልጿል፡፡

በዛሬው ዕለትም በመጀመሪያው ምዕራፍ በትግራይ 75 ሺህ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በይፋ መጀመሩን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በሁለት ዓመታት ውስጥ በሚከናወነው የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ከ760 ሚሊየን ዶላር በላይ በጀት መያዙ ተጠቁሟል፡፡

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 08:13


የኢትዮጵያ ወታደሮች ጁባላንድ ግዛት ላይ ስድስት የሱማሊያ ወታደሮችን አሰሩ።

የኢትዮጵያ ወታደሮች ጁባላንድ ግዛት ዶሎ አየር ማረፊያ ላይ ስድስት የሱማሊያ ወታደሮችን እንዳሠሩ የአገሪቱ  ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ከሞቃዲሾ የተነሱት ወታደሮች በታሠሩበት ወቅት ሲቪል ለብሰው እንደነበር ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

ወታደሮቹ ታሠሩ የተባለው፤ የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት ጁባላንድ በቅርቡ ልታካሂደው ያሰበችውን ቀጥተኛ ያልሆነ ምርጫ ኃይል በመጠቀም ለማስተጓጎል እንዳቀደ እየተነገረ ባለበት ወቅት ነው ተብሏል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 08:04


ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ቀጥለዋል - ተመድ

ከጥር ወር 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት አስር ወራት 20ሺ የሚሆኑ ኤርትራውያን ሀገራቸውን ጥለው ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ ጥገኝነት በመጠየቅ የሚኖሩ ኤርትራውያን የተጠናከረ ጥበቃ እንዲደረግላቸውም ጠይቋል።

"ኤርትራውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች በአፋር እና ትግራይ ክልሎች በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡት አለም አቀፍ ከለላ እና መሰረታዊ እርዳታ ለማግኘት ነው" ሲል ኮሚሽኑ ትላንት ህዳር 11 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

በአስር ወራቱ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ከተሰደዱ 20ሺ ኤርትራውያን በተጨማሪ በኢትዮጵያ ከ70 ሺ የሚበልጡ በኮሚሽኑ የተመዘገቡ ስደተኞች መኖራቸውንም የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን በመግለጫው አመላክቷል።

በስደት ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ኤርትራውያኑ ስደተኞችን እንደደረሱ ድጋፍ መስጠት ያስፈልጋል ያለው ኮሚሽኑ ስደተኞቹን መመዝገብ እና ሰነድ እንዲዘጋጅላቸው ማድረግ ለሚሰጣቸው ከለላ የመጀመሪያው እና ወሳኙ እርምጃ ነው ሲል አሳስቧል።

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH

ADDIS INSIDER - ETH

21 Nov, 07:54


በጅቡቲ ችግር ላይ የነበሩ 104 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በጅቡቲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 104 ኢትዮጵያውያን ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

ኤምባሲው ጅቡቲ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት (አይኦኤም) ጋር በመተባበር ነው ዜጎችን በሁለት ዙር ከነጋድ ባቡር ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ያደረገው።

ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ላይ በተጀመረው ክትትል ስራ በየቀኑ በርካታ ዜጎችን የህግ ከለላ እንዲያገኙ በማድረግ ከእንግልት እና ከሞት መታደግ መቻሉም ተገልጿል።

ይህ ተግባርም በሚቀጥሉት ጊዜያት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

@Addisinsider_ETH
@Addisinsider_ETH