Bisratfm101.1 @bisrat101fm Channel on Telegram

Bisratfm101.1

@bisrat101fm


Bisrat FM 101.1 is a radio station established by Oyaya Multimedia. Journalist Messele Mengistu, is the owner of Oyaya Multimedia and who remained in the hearts of the Ethiopian radio listeners for the past 5 years, has just realized his long time dream a

Bisratfm101.1 (English)

Are you looking for a radio station that brings you the latest news, entertainment, and music all in one place? Look no further than Bisrat FM 101.1! Established by Oyaya Multimedia, this radio station is the brainchild of renowned journalist Messele Mengistu. With a passion for delivering quality content to Ethiopian radio listeners, Mengistu has captured the hearts of many over the past 5 years. Now, he has made his long-time dream a reality with the creation of Bisrat FM 101.1

Bisrat FM 101.1 offers a diverse range of programs to cater to all interests. From current affairs and political discussions to music shows and entertainment news, there is something for everyone. With a team of talented presenters and journalists, the station promises to keep you informed and entertained throughout the day

With a focus on promoting Ethiopian culture and talent, Bisrat FM 101.1 also showcases local artists and musicians, giving them a platform to share their work with a wider audience. If you're a fan of homegrown talent or simply want to stay up to date with the latest in Ethiopian music, this is the station for you

Stay tuned to Bisrat FM 101.1 for your daily dose of news, entertainment, and music. Join the ever-growing community of listeners who have made this station their go-to for quality content. Whether you're at home, in the car, or on the go, you can enjoy the best of Ethiopian radio right at your fingertips. Don't miss out on what Bisrat FM 101.1 has to offer – tune in today and experience the difference for yourself!

Bisratfm101.1

24 Nov, 13:17


በመላው #ዓለም የቀጥታ ስርጭት።

ሊንኩን በመጫን በቀጥታ ማድመጥ ትችላላችሁ።👇👇👇


https://www.youtube.com/watch?v=ONe-8olNeTg


የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 11:29


ህዳር 15፤2017 - ኔዘርላንዳዊው አማካኝ ፍሬንኪ ዲዮንግ ትላንት ምሽት ባርሴሎና ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ሴልታቪጎን በገጠመበት ጨዋታ ላይ ባሳየው ደካማ አንቅስቃሴ ምክንያት ብዙ ትችቶች በ እራሱ ማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ እያጋጠመው ይገኛል። የባርሴሎና ደጋፊዎች ቡድናቸውን ለቆ አንዲወጣ መልክቶችን እየላኩትም ይገኛሉ።

በ መሳይ ተስፋዬ ✍️


#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 11:28


ህዳር 15፤2017 - ዘ ሰን ፋትቦል ይዞት አንደወጣው መረጃ መሰረት ስኮትላንዳዊዉ የቀደሞ የመዶሻዎቹ ዌስትሀም ዮናይትዶች አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ የ መርሲሳይዱ ቡድን ኤቨርተን ኢላማ መሆኑ ተሰምቷል። ሲያን ዲያች ከስራቸው የሚሰናበቱ ከሆነ ሞይስ መዳረሻው ጉዲሰን ፓርክ ሊሆን አንደሚችል ተገልጿል።

በ መሳይ ተስፋዬ ✍️


#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 11:27


ህዳር 15፤2017 - ፖርቱጋላዊው የግራ መስመር ተመላላሽ ኑኖ ሜንዴስ በ ፓሪስ ሴንት ጀርሜን ቤት ያለውን ውል ለማራዘም ተቃርቧል ሲል እውቁ ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ሮማኖ ተናግሯል። በ ሩበን አሞሪም ስር የተያዙት ማንቸስተር ዮናይትዶች እንደሚታወሰው ስማቸው ከ ተጫዋቹ ጋር ሲያያዝ ከርሞ ነበር።

በ መሳይ ተስፋዬ ✍️


#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 10:42


ህዳር 15፤2017 - በትላንትናው እለት በአለልቱ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ-#11_ሰዎች ህይወት አለፈ

አደጋው የደረሰው ከፍተኛ ሀገር አቋራጭ ተሽከርካሪ አሸዋ ከጫነ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መሆኑን የአለልቱ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ቅዳሜ ህዳር 14 ቀን ከጠዋቱ 1ሰአት ከ30 ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ወሎ ደሴ ከተማ 63 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3- 56204 ኢቲ ታርጋ የተመዘገበ አገር አቋራጭ ታታ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከአለልቱ ወደ ሰንዳፍ አሸዋ ጭኖ ሲጓዝ ከነበረ ኮድ 3-75234 ኢቲ ከሆነ ከባድ ተሽከርካሪ ከሆነ ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ 11 ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ማለፍን የአለልቱ ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢንስፔክተር ጋዲሳ አደሬ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በዚህ  አደጋ በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ12 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት የረሰባቸው ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎችን ለህክምና ወደአዲስ አበባ  የተለያዩ ሆስፒታሎች እና ሰንዳፍ በኬ ሆስፒታል ህክምና እያገኙ ይገኛል። ይህ መረጃ እስከተጠናከረበት ጊዜ በሆስፒታል ካሉ ሰዎች ህይወቱ ያለፈ ሰው አለመኖሩን ብስራት ማረጋገጥ ችሏል።

አደጋው የደረሰው ከአዲስ አበባ 67 ኪሎሜትር ላይ በምትገኘው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል የተባለ ስፍራ ላይ ነው፡፡ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሳይሳካ በመቅረቱ ሕይወቱን ማትረፍ አልተቻለም፡፡

የአደጋው መንስኤ ሀገር አቋራጩ አውቶብስ ደርቦ ለማለፍ ባደረገው ጥረት መንገዱን ይዞ ከሚጓዘው ሲኖትራክ ጋር በመጋጨቱ መሆኑን ኢኒስፔክተር ጋዲሳ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/48Do

Bisratfm101.1

24 Nov, 10:19


ህዳር 15፤2017 - ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠነው ውክልና የለም ሲል የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን ከሚሉ ህገወጦች እራሳችሁን ጠብቁ ሲል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል።

በዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጫት ህብረተሰቡን ላላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ በመሆኑ መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

በውጭ ሀገራት ስራ ስምሪቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል የሰጠው ውክልና የሌለ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዜጎችን በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

የሁለትየሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች የሚከተለውን ዌብሳይት (lmis.gov.et) በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ማሳወቁን ብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/48Do

Bisratfm101.1

24 Nov, 10:01


ህዳር 15፤2017 - በአሜሪካ የልብ ስራን የሚያቆም መድኃኒት በመስጠት ህሙማንን ሲመርዝ የነበረው ዶክተር በ190 ዓመታት እስራት ተቀጣ

በታካሚዎች የጉሉኮስ መስጫ ከረጢት ውስጥ የልብ ማቆሚያ መርዝ በመርፌ በመመረዝ የተከሰሰው የቴክሳስ የሰመመን ባለሙያ ዶክተር በ190 ዓመታት እስራት ተቀጥቷል።

ሬይናልዶ ሪቪዬራ ኦርቲዝ የተባለው የ60 ዓመቱ የህክምና ባለሙያ "የህክምና አሸባሪ" የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቶታል። ከቀረቡበት የክስ መዝገቦች መካከል በአራት ክሶች የህክምና ምርቶችን በመመረዝ ከባድ የአካል ጉዳት በማድረስ ፣ በአንድ ክስ በህክምና ምርት ላይ ጉዳት እንዲያደርስ በማድረግ እና በአምስት መዝገብ ደግሞ ሆን ብሎ ተገቢ ያልሆነ ንጥረ ነገር በመጨመር በህክምና ሂደቱ የጥራት ጉድለት እንዲፈጠር በማድረግ ጥፋተኛ ሆኖ ተገኝቷል። ባለፈው ዓመት በሚያዝያ ወር ከስምንት ቀናት የምርመራ ሂደት በኋላ ተደርሶበታል። የቅጣት ውሳኔ የተላለፈው በዩናይትድ ስቴትስ ዋና ዳኛ ዴቪድ ጎድቤይ ሲሆን የኦርቲዝን ድርጊት ከግድያ ሙከራ ጋር እኩል በመሆኑ የተነሳ ነው።

የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ሊጋ ሲሞንተን በውሳኔ ሀሳቡ ተስማምቷል። ነውረኛ ድርጊትን የፈፀመው ይህው ዶክተር የጦር መሳሪያ የታጠቀ አካል በህዝብ ላይ ያለ ልዩነት ጥይት እንዲመተኩሰው ሁሉ ይህ ተግባርም ተመሳሳይ ነው ተብሏል። ዶ/ር ኦርቲዝ በዘፈቀደ የግሉኮስ ከረጢቶች ላይ ሕመምተኞች እንዲፈውሱ ለመርዳት በተዘጋጀው መድኃኒት ውስጥ መርዝ ይቀላቅል እንደነበር አቃቤ ህግ ሲሞንተን ተናግረዋል።ቢያንስ በዘጠኝ የተለያዩ አጋጣሚዎች ንቃተ ህሊና የሌላቸውን ታካሚዎች በቀዶ ህክምና አልጋ ላይ ተኝተው እንዳጠቃቸው የክሱ ዝርዝር ያሳያል። የጉዳት ሰለባዎቹ እና ቤተሰቦቻቸው በብዙ ቢጎዱም አጥፊው ለህግ በማቅረባችን በአጋሮቼ ኩራት ይሰማኛል ሲሉ አቃቤ ህግ ሊጋ ሲሞንተን ገልፀዋል።

ከቴክሳስ ሰሜናዊ አውራጃ የዩናይትድ ስቴትስ አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው የወንጀል ድርጊቱ በሚፈፀምበት ወቅት ዶክተሮች የታካሚዎቻቸው የደም ግፊት በድንገት ሲጨመሩ ግራ ይጋቡ እንደነበር ተናግረዋል ። የሕክምና መዝገቦችን ከገመገሙ በኋላ ከእያንዳንዱ ክስተት ጋር አንድ የሚያመሳስለው ነገር አግኝተዋል። ድንገተኛ አደጋዎች የተከሰቱት በግሉኮስ መስጫ ከረጢቶች መመረዝ እንደሆነም ደርሰውበታል። የቀረቡት መረጃዎች እንደሚያሳዩት እ.ኤ.አ. በ 2022 በተለመደው የሕክምና ሂደቶች የልብ ድንገተኛ አደጋዎች ህሙሟን አጋጥሟቸዋል ይላል።

ምክንያቱ ካልታወቀ ድንገተኛ የልብ ህመም በኋላ፣ አንድ የማደንዘዣ ባለሙያ ለራሷ እንደተመረዘ ያላወቀችውን የጉሉኮስ ከረጢት በተጠቀመችበ ዕለት ህይወቷ አልፏል። ባለቤቷ ዶ / ር ጆን ካስፓር የሚስቱን ህልፈት ሲያስታውስ "ሕይወት አልባ ዓይኖች" አሁንም እንደሚያሳዝኑት መጥፎ ትዝታ ጥለውበት እንዳለፈ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል። እሷ በህይወቴ በጣም ጠንካራዋ ሴት ነበረች በማለት አክለዋል።ሌላ ተጎጂ እንዳለው የልብ ህመም ከደረሰብኝ በኋላ ከእንቅልፌ ስኑ እንደታኘክ ዓይነት ስሜት ይሰማኝ ነበር ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ደህና አይደለሁም ሲል ተደምጧል።ኦርቲዝ ፍርዱ ሲሰጥ እና የተጎጂዎችን ቃል ላለመስማት መብቱን ተጠቅሞ በችሎት ቦታው አልነበረም።

በስምኦን ደረጄ

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #usa

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 09:54


ህዳር 15፤2017 - የባርሴሎናዉ አሰልጣኝ ሀንስ ዲተር ፍሊክ የባርሴሎና ተጫዋቾችን ተችቷል ትናት ምሽት ከሴልታቪጎ ጋር 2-2 ከተለያዮ በኋላ በመልበሻ ክፍል ተጫዋቾችን ሰብስቦ በድብቅ ባደረጉት ስብሰባ አሰልጣኙ ዛሬ ባሳያችሁት እንቅስቃሴ ልታፍሩ ይገባል እንደዚህ አይነት ክስተቶችን ከዚህ በኋላ አልታገስም በጨዋታዉ ትኩረት አልነበራችሁም አንዳንዶቻችሁ ምን ስሰሩ ነበር ብየ ብጠይቃችሁ እርግጠኛ ነኝ አትመልሱልኝም በቀጣይ በሻምፒዮንስ ሊጉ ከብረስት ጋር ለሚኖረን ጨዋታ መዘጋጀት አለብን በማለት ተጫዋቾችን በብስጭት ዉስጥ ሆኖ ተናግሯቸዋል በማለት ካታሎኒያ ሬዲዮና ሙንዱ ዲፖርቲቮ መዘገባቸዉ ተሰምቷል።

በ"ሙለቀን ሙጨ"

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 09:52


ህዳር 15፤2017 - የአታላንታ ስኬት ሚስጥር የሴሪኤዉ ድምቀት አሰልጣኝ የሆኑት ጂያን ፒየሮ ጋስፔሪኒ ትናንት ፓርማን 3-1 በማሸነፍ ሊጉን መምራት ጀምረዋል። ታዲያ ትናንት በቀይ ካርድ መሰናበታቸዉ ይታወቃል የ66 አመቱ ጣሊያናዊ አሰልጣኝ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ሀሳባቸዉኔ አጋርተዋል ዳኛዉ ጨዋታዉን ለመምራት ሲቸገሩ አየሁ ከዛ ጠራሁትና እኔን አትመልከተኝ ጨዋታዉን ብቻ በጥሩ መንገድ ምራ ብየ ስላናገርኩት በቀይ ካርድ ሊያሰናብተኝ ችሏል አሁንም በማሸነፋችን እንቀጥላለን በቡድኔ በጣም ደስተኛ ነኝ በማለት ጋስፔሪኒ አስተያየታቸዉን ሰተዋል።

በ"ሙሉቀን ሙጨ"

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 09:51


ህዳር 15፤2017 - በተርኪ ሱፐር ሊግ ፌነርባቼ ካይዘሪስፖርን 6-2 ካሸነፉ በኋላ ጋዜጠኞች ለጆዜ ሞሪኒሆ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ወደ ፌነርባቼ ለማምጣት እያሰቡ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ ሲባሉ ጆዜ ሞሪኒሆ ተከታዮን ብለዋል በሳኡዲ አረቢያና ፖርቱጋል መካከል ባለዉ መንገድ መሀል ላይ ስለሆነ ክርስቲያኖ ምግብ ለመብላት ኢስታንቡል ሊመጣ ይችላል ወይም የግል ጀቴን ይዞ በመምጣት የኔ ሆቴል የምንበላበት የቀድሞ ጓደኛዉን ጆዜ ሞሪኒሆን ለማየት ይችል ይሆናል ዜናዉ አስቂኝና መሠረተ ቢስ ወሬ ነዉ ታማኝ የሚባሉ ሚዲያዎች መዘገባቸዉ ደግሞ በጣም አስገርሞኛል በማለት ጆዜ ተናግረዋል።

በ"ሙሉቀን ሙጨ"

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #sports

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/4

Bisratfm101.1

24 Nov, 09:48


ህዳር 15፤2017 - የገዛ ወንድሙን በመግደል በአውሬ በማስበላት ቤተሰቦቹን ያሳመነው ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በምዕራብ አርሲ ዞን ሲራር ወረዳ ውስጥ በእርሻ መሬት ምክንያት በተፈጠረ አለመግባባት ወንድሙን በመግደል በአውሬ በማስበላት የተሰወረው ግለሰብ የፍርድ ውሳኔ ተላልፎበታል።

የምዕራብ አርሲ ዞን ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ዋና ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደገለጹት ተከሳሽ መሃመድ ቁፋ የተባለው ግለሰብ ከወንድሙ ጋር በነበረ የእርሻ መሬት አለመግባባት ድርጊቱን መፈጸሙ ገልጸዋል ።

ተከሳሹ ረመዳን የተባለው ወንድሙ ላይ በነበረው ቂም ምክንያት ገድሎ ራሱ አስከሬኑን በአውሬ ካስበላ በኋላ ወላጆቹ ወደ ክስ እንዳይሄዱ በአውሬ እንደተበላ ሲያስመስል እንደቆየ ተጠቁሟል። በተጨማሪም ድርጊቱን ከፈጸመ በኋላ ከአካባቢው ለመሰወር ቢሞክርም በተደረገ ክትትል በቁጥጥር ሥር ውሏል።

ፖሊስ ቀሪውን አስከሬኑን ለምርመራ በመላክ ጉዳዩን አጣርቷል። ተከሳሹ ድርጊቱን መፈጸሙን እና ቤተሰቦቹን ለማሳመን ሲሞክር እንደነበር ቃሉን ሰጥቷል። ፖሊስ መዝገቡን ከሆስፒታል በተገኘ ማስረጃ እና በሌሎች መረጃዎች በማጠናከር ለዓቃቢህግ ይልካል። ከፖሊስ የደረሰውን መዝገብ በመመልከት ዓቃቢ ህግ ክስ ይመሰርታል ።

የምዕራብ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም በተከሳሽ መሃመድ ቁፋ በወንጀሉ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ22 ዓመት እስራት ላይ እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር ከድር ጅቦ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በኤደን ሽመልስ

#BisratNews #BisratFm #BisratRadio #Ethiopia

የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/48Do

Bisratfm101.1

24 Nov, 05:13


ህዳር 15፤2017 -   ውድ የብስራት ሬዲዮ አድማጮች የ facebook ገጻችን like, share እና Comment በማድረግ ሃሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን።

በ-#እንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ  የ-#ኢፒስዊች እና #ማንችስተር_ዩናይትድ-ን ጨዋታ   #ሞዛይክ_ስፖርት    ይዘውላችሁ ይቀርባሉ።

ማነኛውንም ሃሳብ አስተያየት አድርሱን። መልሰን ወደ እናንተ አናደርሳለን።

  ምሽት ከ1:00-3:00  ሰዓት  ይጠብቁን!

በመላው ዓለም በዩቲዩን ገጻችን ይጥብቁን። 👇👇👇
https://www.youtube.com/@Bisrat_Fm_101.1


የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/48Dozt9

Bisratfm101.1

24 Nov, 05:10


ህዳር 15፤2017 -   ውድ የብስራት ሬዲዮ አድማጮች የ facebook ገጻችን like, share እና Comment በማድረግ ሃሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን።

በ-#እንግሊዝ_ፕሪምየር_ሊግ  የ-#ሳውዝአምፕተን እና #ሊቨርፑልን-ን ጨዋታ   #ቲፎዞ    ይዘውላችሁ ይቀርባሉ።

ማነኛውንም ሃሳብ አስተያየት አድርሱን። መልሰን ወደ እናንተ አናደርሳለን።

  ቀን ከ10:00-1:00  ሰዓት  ይጠብቁን!

በመላው ዓለም በዩቲዩን ገጻችን ይጥብቁን። 👇👇👇
https://www.youtube.com/@Bisrat_Fm_101.1


የብስራትን የተለያዩ ማህበራዊ ገጾች በመቀላቀል፤ ወቅታዊ መረጃዎችን እና ፕሮግራሞችን ይከታተሉ…

Facebook: https://bit.ly/3Hng6Qt
Website: https://www.bisrattv.com/
Telegram: https://t.me/Bisrat101fm
YouTube: https://bit.ly/3zAAOrB
Twitter: https://twitter.com/Bisrat101fm
TikTok: https://bit.ly/48Dozt9