የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር) @ephrem_views Channel on Telegram

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

@ephrem_views


በዚህ የቴሌግራም ገጽ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቁ ስርዓተ አምልኮና ትምሕርቶች እንዲሁም ዝማሬዎች ይቀርቡበታል። ክርስቲያናዊ የሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮችም ይነሱበታል።

" ያየሁትን እናገራለሁ የሰማሁትን እመሰክራለሁ! "

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር) (Amharic)

ኤፍሬም እይታዎች (መ/ር) በዚህ የቴሌግራም ገጽ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማ፣ቀኖና እና ትውፊትን የጠበቁ ስርዓተ አምልኮና ትምሕርቶች እንዲሁም ዝማሬዎች ይቀርቡበታል። ክርስቲያናዊ የሆኑ ማህበራዊ ጉዳዮችም ይነሱበታል።nየእርግዝናና ምንጭ ማህበራዊ ትምህርት ተመልከቱን የሚፈልጉ ስለተለያዩ መልኩት ጋር የመዝገበ እና የመፍትሄ እና መኪና ፍትህ እርምጃዎችን ይሰጥባቸዋል። የቴሌግራም ገጽ ከሆድን ጀምሮ መንገድ አልትላላው አምላኮም እንዲሆን ይግባ። አዲስ መንገድ መዝገበኛዎችና መፍትሄ ፍትህ ለመስራት በተለያዩ መልኩ ሊሆን ይችላል።nመንገድ እና ርቀትም ለምን ያልተነበሩ ብቻ እንዲቆይ በመልክት ይኖራል። የእውነት ህዝብና የመሰረት መንገዶችን በመንገደኛ መለያ ፣የስማዕቱንና የሳተላውያን ተግባራት ያለአንድነትዎ ለመዝገብ ያስፈልገዋል።nክርስቲያ መንገድ ከእነሲ ዓዲዋ ህዝብ ስንዴ እና በድንጋይ፤ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዶግማና ብቻ የገባንበትን የመጠጥ መልእክት ይቀረቡበታል።nበተለያዩ ውድ መሄዴ ላይ በማኅበሩ ጥናት መንገዱን ለማስፈልገት ሟልሁን ይስጥልን። ከጠንከሮ ኦስጅን መሆን ከሚፈቀደው ጉዞ ከኦነጋ ማደረ ጉዞን ራእይ ይሽጥልን።nከእንግሊዝ በወረቀት የተደገ ጉዞ መናገር ሰጥቶናል። የህክምና ኦነጋ የሚገኙ ጉዞዎችም መለያየቱን ለመገንዘብ እና ሁከትን ለመደገዝ ይስጡ። ምንም በለይቶ እልልቶ ወጣቶአልም።nስለምንከምታይተክጠንለው ፣ነገሩ እኮ አለባው። ስለምንከምታይተክጠንለው ፣እርግዝና ልክ በል።

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

20 Nov, 18:32


እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል የመታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ። የእስራኤል ታዳጊያቸው፤የችግረኞች ረዳታቸው፤የሞት ደብዳቤን ቀያሪ፤ለጠሩት ፈጥኖ ደራሽ ሃያሉ ሚካኤል ለሀገራችን ሰላም አድነቷን ይመልስልን።

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

18 Nov, 17:18


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ በስልታዊ እቅድ፣ በተቋማዊ መነቃቃት፤ በአስተዳደራዊ ክትትልና እገዛ ዘመኑን በዋጀና ወጣቱን ማዕከል ባደረገ ወንጌል ላይ ካልሰራች ነገ ያስፈራኛል።

✍️የኤፍሬም እይታዎች

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

17 Nov, 16:20


መንግሥተ ሰማያትና ገሃነመ እሳት !
...............................
ብዙ ጊዜ ከሞት በሗላ ስለ ሚኖረን ሕይወት ማሰብ አንፈልግም። አንዳንድ ጊዜ በውስጣችን ጥያቄው ቢመላለስም ደጋግመን ለማሰብ ፈቃደኞች አይደለም።
የሰው ልጅ ሞቱን ማሰቡ ስለ ዘለዓለማዊ ቤቱ እንዳይዘናጋ ያደርገዋል። ምክንያቱም የሰው ሕይወት በመወለድ ተጀምሮ በሞት የሚጠናቀቅ እንዳልሆነ ስንዱዋ እመቤት ቤተክርስቲያን በሚገባ አስተምራናለችና።

ከሞት በሗላ ሕይወት አለ። ወይ የመከራ ወይም የደስታ።
ገነትና ሲኦል ሗላም መንግተ ሰማያት እና ገሃነመ እሳት አሉ።
መንግሥተ ሰማያት አስቀድማ በመንፈሳዊ ሕይወት በሚመላለሱትና በሚመሩት መካከል ትገኛለች። ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ፈሪሳውያን ቀርበው " የእግዚአብሔር መንግሥት መቼ ትመጣለች? " ብለው በጠየቁ ጊዜ "የእግዚአብሔር መንግሥት በመጠባበቅ አትመጣም ከዚህ አለች ከዚያ የለችም አትባልም የእግዚአብሔር መንግሥት እነሆ በመካከላችሁ ናት" እንዳላቸው። ሉቃ 10÷20-21።

ታጥቦ ጸድቶ፣ነጩን ልብስ ለብሶ መብራቱን ይዞ ለሚጠብቅ ሰው መንግሥተ ሰማያት ከእርሱ ጋር ናትና።
መንፈሳዊ ሰው በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ፤ በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን የሚያውቀውን ሕይወት የሚገኝበት ትምሕርት በሕይወት እየገለጠ፣ በዘመናት መጨረሻ ላይ ሰዎች ሁሉ እንዲያዩት በኃይል እና በክብር በግርማ መለኮቱ ጌታ ሲገለጥ ለማየት " አሜን ጌታ ሆይ ቶሎና እያለ ሙሽራውን በናፍቆት የሚጠብቅ ነው።

የክርስቶስ የመጨረሻ መምጣት በሰው ሁሉ ላይ ለመፍረድ ይሆናል። ያንጊዜ ጌታ የሚመጣው ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው መጠን ለመክፈል ነው።

አሁን ሰዎች ያለ ክርስቶስ ፍቅር በሕይወታቸው (በአካለ ሥጋ) መኖር ይችላሉ። በነፍስ ሞተው በሥጋ ቆመው። ክርስቶስ፣ መንፈስ ቅዱስ፣ቤተ ክርስቲያን፣ መንፈሳዊ ሕይወት የሌለ እስኪመስል ድረስ ይህንን ሁሉ ዘንግተው ሊኖሩ ይችላሉ። እርሱን ባለማወቅ ሊመላለሱ ይችላሉ። ነገር ግን ቃሉ ይፈርድ ዘንድ ወንጌል ለሰው ልጅ ሁሉ ይሰበካል። "ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ " እያለች ቤተክርስቲያን ታውጃለች።

ነገር ግን በዘመናት መጨረሻ ላይ ይህ ሁሉ በክርስቶስ ፍርድ ያበቃል።በመጨረሻም ክፉዎችም፣ መልካሞችም ፣ጻድቃንም ፣ኃጥአንም ፣የወጉትም የሰቀሉትም፤የተፉበትም የገረፉትም ፤ሰዎች ሁሉ የእርሱን ፊት በግርማው ያያሉ።

ስለ እኛ ሲል ስለ መዳናችን ከሰማይ የወረደውን ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የእኛን ሥጋ የለበሰውን ... በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን መከራ የተቀበለውን፣ እርሱን የገደሉት ክብሩን እየተመለከቱ “ሞቶ የነበረውንና ሕያው የሆነው” (ራዕይ 1፡17) እርሱ ክርስቶስ ለፍርድ በግልጥ ይመጣል።

በዚህም ጊዜ ጌታን ለሚወዱ፣የእርሱን መምጣት በናፍቆት የሚጠብቁ ፤በምግባር በሃይማኖት ያጌጡ፣መብራታቸውን ከዘይታቸው ጋር የያዙ ፤የእርሱ መምጣት ማለቂያ የሌለው ዘለዓለማዊ ፍጹም ደስታና እረፍት፣ የዘላለም ሕይወት ይሆንላቸዋል። በመንግሥተ ሰማያትም ከእርሱ ጋር በሕይወት ይኖራሉ።

በጉ ክርስቶስን የዘነጉ፣ ከምግባር ከሃይማኖት የተራቆቱ፤
ጌታን ለሚጠሉ፣የዘይት ማድጋቸው ባዶ የሆነ፤ መብራታቸውን ያልያዙ፤ ከጽድቅ ከቅድስና የተራቆቱ፤ ለዘለዓለም ማለቂያ በሌለው ስቃይ ፤ያለ እረፍት እግዚአብሔርን አጥተው፤ ከክርስቶስ መንግሥት ተለይተው የዘላለም ሞት ያገኛቸዋል። በገሃነመ እሳትም ከግብር አባታቸው ከዲያብሎስ ጋር ወደ ሥቃይ ይጣላሉ።

በእግዚአብሔር እውነተኛ ፍርድም ከእዚህ ዓለም አምሮትና ምኞት የራቁ፤ለጽድቅ ሥራ የመነኑ ፣በእምነት ያጌጡ በመጨረሻ መለኮታዊ የፍርድ ፍጻሜ የዘለዓለም ሕይወት ያገኛሉ። ዓለምና አምሮቷ ያታለላቸው፣ደሃ የበደሉ ፍርድ ያጓደሉ፣ከሕገ እግዚአብሔር ፈቀቅ ያሉ፣በእምነትና ምግባር ያላጌጡ ሁሉ ለራሳቸው፣ለዘለዓለም ቤታቸው ጥሪት አልቋጠሩምና ለዘለዓለም ማለቂያ በሌለው ስቃይ ቅጣታቸውን እና ሞታቸው ይሆናል። የእነርሱም ፍርድ “ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት” ወዳለበት ይሆናል። (ማቴ 25 )

በዚህን ጊዜ የሰው ልጅ መላእክቱን ይልካል ከመንግሥቱም ስንዴውና እንክርዳዱን እንዲለዩ ስንዴውን ወደ ጎተራ (መንግሥተ ሰማያት) እንክርዳዱንም ወደ እቶን አሳት (ገሃነመ እሳት) ይጥሉአቸዋል። በዚያ ሰዎች ያለቅሳሉ ጥርሳቸውንም ያፋጫሉ። ያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ያበራሉ (ማቴ 13፡41–43)።

በእግዚአብሔር መንግሥት መምጣት ኃጢአተኞችን የሚበላው “እሳት” በቅዱሳን ላይ በድምቀት የሚያበራው “እሳት” ነው። የእግዚአብሔር ፍቅር "እሳት" ነው። (ዕብ 12:29) " ይህ "እሳት" እግዚአብሔርን ለሚወዱ እና ፈቃዱንም ለሚፈጽሙ/ለፈጸሙ በእርሱ ውስጥ ያሉትን ፍጥረታት ሁሉ ለሚወዱ የሚያበራ ብርሃን እና የማይነገር ደስታ የሚሰጥ እሳት ነው። እግዚአብሔርን ለማይወዱ እና ጨርሶ ፈቃዱንም ላልፈጸሙ፣ ይህ “የሚበላ እሳት" ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ሰውን በቁሳዊ እሳት ወይም አካላዊ ሥቃይ እንደማይቀጣው የቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርት እንደሆነ እንረዳለን። እሳቱ ከዚህም ያበሰ
" እግዚአብሔርን ማጣት" ያስከተለው እረፍት የማይሰጥ የሚያቃጥል ማብቂያ ማለቂያ የሌለው የእሳት ስቃይ ነው።

በመንግሥተ ሰማያት ደግሞ በቅዱሳን ላይ የሚያበራ፣ በአማናዊት ምስራቅ በድንግል ማርያም በኩል የወጣ የጽድቅ ጸሐይ ክርስቶስ እያበራ፣ማለቂያ ፣ማብቂያ በሌለው በዘለዓለማዊ ደስታ ውስጥ ሆነን ያለ ማቋረጥ በቤተክርስቲያን ሐብረት ውስጥ ከድንግል ማርያም ጋር ከቅዱሳኑ ጋር በጌታ ቀን በጌታ ፊት ለዘለዓለም በምስጋና እንኖራለን።

ተወዳጆች ሆይ እናንተስ በየት መኖር ትፈልጋላችሁ ?

👉በመንግሥተ ሰማያት ወይስ በገሃነመ እሳት ?

#መልሳችሁ :- በመንግሥተ ሰማያት ከሆነ ጌታ መቼ እንደሚመጣ አታውቁምና ነጩን ልብስ ለብሳችሁ መብራታችን ይዛችሁ ፤በጋኖቻችሁ ዘይትን ሞልታችሁ ተቸጋጅታችሁ ጠብቁ።ተዘጋጅተን እንጠብቅ።
👉 @ephrem_views
@ephrem_views 👈

✍️ ኤፍሬም ሀብተ ማርያም
የህዳር ሥላሴ ተጻፈ
7/3/2016 አምና

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

16 Nov, 18:32


#መካነ_ወንጌል_ደብረ_መዊዕ❗️
በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጥንታዊው በደብረ መዊዕ አዲሱ ሚካኤል ካቴድራል(መርካቶ) ለ6 ተከታታይ ቀናት በተዘጋጀው ዐቢይ ጉባኤ የመጀመሪያው ቀን አጅግ ግሩም የአገልግሎት ጊዜን አሳለፍን። ጉባኤውን ያስፋልን።

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

11 Nov, 05:19


https://youtu.be/XsL1T6xLbfU?si=npeNycIAAeqYRD2D

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

07 Nov, 17:55


" #የስም_ክርስቲያን_ነበርኩ "
...................................
👉 ጊዜ ሰጥተው ያንብቡት -👉Share በማድረግ ያጋሩት!

" ይገርምሃል ያኔ ወጣት ሳለሁ ለእግዚአብሔር በሕይወቴ ውስጥ ቦታ ሰጥቼ ለክርስትናዬም ዋጋ ሰጥቼ አልኖረውም ነበር ። ኦርቶዶክስ ነበርኩ ግን በስም ብቻ። አዘውትሬ ወደ ቤተ ክርስቲያን አልሄድም ፣ አልጾምም፤ የንስሓ አባትም አልነበረኝም።
ቢሆንም ግን በውስጤ ከፍ ያለ ሃይል እንዳለ ሁል ጊዜ ይሰማኝ ነበር፣ ግን ይህ የሩቅ ምስጢር ሆኖ የቀረ ነው። አንዳንድ ጊዜ አምላክ እንዳለ እና እሱን ለማወቅ የሚያስችል መንገድ ይኖር ይሆን ብዬ አስብ ነበር።
ያደግኩት ጥብቅ ማህበራዊና ሃይማኖታዊ መስተጋብር ባለባት በናዝሬት ከተማ 09 ነው። ቤተ ክርስቲያንም አልፎ አልፎ ቢሆንም እሄዳለሁ። ግን በልማድ ሲሄዱ ለመሄድ።

ኦርቶዶክስ ብሆንም ስለ ሃይማኖቴ ምንም የማውቀው ነገር ስለሌለ ወደ ሌሎች እምነትም አማትር ነበር እውነቱን ፍለጋ። ከሆነ ጊዜ በሗላ መንፈሳዊ እውቀትን በጥልቀት ለመረዳትና ለማወቅ ፈለግሁ። የትኛው ሃይማኖት ነው ትክክል የሚለውን ማጥናት ጀመርኩ። ማንበብ ፣ ማሰላሰልን ተያያዝኩ። በዚህ ጊዜ ሁሉ ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበረኝ ግንኙነት አነስተኛ ነበር።

ለጥያቄዬ መልሱ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ በአፍንጫዬ ስር እንደነበረ አልተገነዘብኩም ነበር። ኦርቶዶክስን የወረስኩት ከቤተሰብ ነው። የኔ ቤተሰቦች ጠንካራ መሠረተ እምነት ነበራቸው።
ይህም በተግባር የተገለጠ በሕይወት የሚኖር እንጂ በቃል የሚነገር አልነበረም። ለእነርሱ ቤተክርስቲያን እና የህይወት እንቅስቃሴዎች ሁሉም የተዋሃዱ ነበሩ እንጂ በጥቅስና በማስረጃ የተደገፉ አልነበሩም። የሚኖር ክርስትና ነው ያላቸው። ለካም ክርስትና ከእውቀት በላይ የሚኖር ነው።

የኔ ሕይወት ግን በጥያቄ የተሞላ ነበር። የቱ ነው እውነት ?
አንዳንዴም ለዘለዓለም በሕይወት እንደምኖር ይሰማኝ ነበር። በሥጋ የማልሞት።

ሟች የመሆኔ እውነታ ስለ ሕይወት ዓላማ ጥያቄዎችን ማንሳት የጀመርኩት ሚስት ካገባሁ ጀምሮ በጥቂቱ ሲሆን 50 ዓመት ገደማ ስደርስ ግን እየበረታ መጣ። ከሚስቴና ከልጆቼ ጋር በየጊዜው ወደ ቤተ ክርስቲያን ስሄድ በኦርቶዶክስ ሥርዓት እና ትምህርት እየተማረኩ መጣሁ።

ወደ 40 እና 50 ዕድሜ የሚጠጉ፣ ብዙ ሰዎች የሕይወትን ዓላማ ማሰላሰል ይጀምራሉ። ይህ ሕይወት ለዘላለም እንደማይቆይ መገንዘብ ይጀምራሉ. ዕድለኛ የሆኑት ይህ ሕይወት ለሚመጣው የዘላለም ሕይወት መዘጋጃ ብቻ እንደሆነ ይማራሉ። እኔም እግዚአብሔር አብ አንድያ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለ ሰው ልጆች ፍቅር መስዋዕት አድርጎ መስጠቱን በተግባር የተማርኩት በዚህ ጊዜ ነበር።

ይህም ነገረ እግዚአብሔርን ማወቅ፣መረዳትና እና ከእርሱ ጋር አንድ መሆን ይቻላል የሚለው ሀሳብ በኦርቶዶክስ እምነት ያለ ማዕከላዊ እውነት እንደሆነ ተማርኩ። እግዚአብሔርን ማወቅ የሚቻለው በሕጉ በኩል፣ ከምስጢራት ሱታፌ በማድረግ፤የሚያውቁትን እውነት በሕይወት በመኖር ወደ መለኮታዊ ባሕርይ ተካፋይነት ማደግ እንደሚቻል በደንብ ተገነዘብኩ።

አንድ ሰው በትክክል ክርስትናን ሲኖረው ወደዚህ እውነት እና ሕይወት እንደሚደርስ ገባኝ።

አንድ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ለመዋሃድ ትክክለኛውን መንገድ ኦርቶዶክስ እንደሆነ ገባኝ።በዚህም ፈውስ የሚያስፈልገው የታመመ ነፍስ እንዳለችኝ ተረዳሁ። አሁን በጣም ደስ ብሎኛል ምክንያቱም ህመሜን አግቼዋለሁ። መድኃኒቱንም አውቄዋለሁ። ምክንያቱም በክርስቶስ የተመሰረተችው ቅድስት ቤተክርስቲያን የጠፋሁትን እኔን መፈለግ ዓላማዋ ይህ እንደሆነ ተገንዝቢያለሁና።

ቤተክርስቲያን ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የምታደርስ የእግዚአብሔር መንገድ እንደሆነች ባወቅኩበት ቅጽበት ከእርሱ ጋር አንድ ለመሆን መንፈሳዊ መመሪያን በካህናት በኩል ፈለግሁ ።እናም ክርስቶስ በቤተክርስቲያን በኩል የሰጠንን የህይወት መንገድ መከተል ጀመርኩ።ለቤተሰቤም ንስሐ አባት ያዝኩ። እኔም ቤተሰቤም የንስሐ ሕይወትን ጀመርን። ከምስጢራትም ተሳተፍን። ጋብቻችን በቅዱስ ቁርባን ዳግም በልጆቻችን ታጅበን አደስን።

በእውነት በሂደት የቤተክርስቲያንን ታሪኳን ሳጠና፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ በሐዋርያት በኩል የተላለፈውን ይህን ሁለንተናዊ፣ ምሥጢራዊ እና የማይለወጥ እውነተኛ መንገድ ሰንሰለት ጠብቃ በትውፊት ቅብብሎሽ እዚህ እንደደረሰች ተረድቻለሁ። የሚገርመው ከልማድ ጉዞ ወደ እውነተኛ የእምነት መመላለስ ወደ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መግባት ስጀምር ሁሉም አምልኮአዊ ሥርዓቶች ሰማያዊ ሥርዓት በምድር እየተከናወነ እንደሆነ ትገነዘባለህ።
የዕጣን ሽታ፣ የዝማሬው ውበት፣ በተመስጦ የሚደረገው ጸሎት፣ የቅዳሴው ሥርዓት ፤ማኅሌቱ ሰዓታቱ በቃ ሁሉም ነፍስህን ከሥጋህ የሚለዩ ድንቅ ሥርዓት ናቸው። ከዚህ ሕብረት ነበር ነፍሴ ተለይታ የኖረችው። አሁን እኔም ቤተሰቤም ከምስጢራት እሁድ እሁድ እንሳተፋለን። በሰዓታቱ በማኅሌቱ አንለይም።

ከመሸ መጣሁ። ዕድሜዬ ከገፋ ደጅ ጠናሁህ ብዬ ሳለቅስ ባለቤቴ " አርፍዶ ለመጣም ፣ቀድሞ ለመጣም ዋጋ ከፋዩ ቸርነውና ዋጋውን አያሳንሰውም " ትለኛለች። ከዚህ ሰማያዊ ምስጢርና አምልኮ አንድነት ሳልሳተፍ ምነው አረፍዱኩ ብዬ ሁሌም እቆጫለሁ። የስም ክርስቲያን ብቻ ሆኜ የኖርኩበት ዕድሜ፣ ማስቀደስ እየቻልኩ በዘፈንኩበት ዕድሜዬ፣ መስገድ እየቻልኩ የጨፈርኩበት ዘመኔ በዕለተ ሰንበት ሰዎች ወደ ቅዳሴ ሲሄዱ ወደ መጠጥ ፣ወደ መሸታ ቤት መሄዴ ሁሌም ይቆጨኛል። የንስሓ አባቴ ይህን ስል ሲሰሙ " የማይጠቅም ጸጸት ነው ፣ቀጣዩ ሩጫህን በትዕግሥት ሩጥ። ክርስትና ሩጫውን ከመጀመሪያውም ጀምር ከመኻል ማጠናቀቁ ላይ ነው ምስጢሩ ስለዚህ በቀጣዩ ጉዞህ በርታ ልጄ" እያሉ ያበረታቱኛል።

ዛሬ ቤቴም እኔም በእውነተኛው ሰላም በክርስቶስ ተባርከናል። ከጠፋሁበት የፈለገኝ፤እርሱን ካለማወቅ የጨለማ ሕይወት አውጥቶ ወደ ሚደንቅ ብርሃን ያመጣኝ ፣ስረሳው ያልረሳኝ፣ብተወው ያልተወኝ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።" አለኝ። እኔም ስለ እርሱ አምላኬን አመሰገንኩ። ብዙ ተጨዋወትን ፤ብዙም ነገር አወጋን። ቀጠሮ ይዘን ተለያየን።

ለካ ክርስቲያን ሆኖም የስም ክርስቲያን መሆን አለ??

ተወዳጆች ሆይ እኛስ የቱ ጋር እንሆን ?

👉 እሩቅ ወይስ የቅርብ ሩቅ ?

ኤፍሬም ሀብተማርያም (መ/ር)
👉 @ephrem_views

✍️ናዝሬት-አዳማ ኢትዮጵያ

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

06 Nov, 06:13


በሞቱ ሞትን ሽሮ በስልጣኑ ሙስና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሳው፤ የማንነታችን ምክንያት የህይወታችን ምስጢር ፤ጀርባው ስለእኛ የደማ፤ በደሙ ያነጻን፤ ዘለዓለማዊ የልጅነት ክብርን ያደለን ቸሩ መድሃኔ ዓለም ክብርና ምስጋና ለእርሱ ይሁን🙏ዘመን የማይቆጠርለት፤ ለግዛቱ ወሰን የሌለው፤ በፍቅሩ አለምን የሚገዛ በያላችሁበት ሰላማችሁን ያብዛላችሁ!እንኳን አደረሳችሁ🙏

@ephrem_views
@ephrem_views
....
....

የኤፍሬም እይታዎች (መ/ር)

04 Nov, 16:37


ለመጀመሪያ ጊዜ በአዳማ ከተማ የተዘጋጀው "ምዕራግ " ትምህርተ ወንጌልና ኦርቶዶክሳዊ የኪነ ጥበብ መርሐግብር እጅግ በአስደናቂ መልኩ ተጠናቀቀ 🙏🙏

3,272

subscribers

900

photos

12

videos