የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command @commando_and_airborne_command Channel on Telegram

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

@commando_and_airborne_command

Addis abeba Ethiopia

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command (Amharic)

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ አማርኛ ትምህርት ምስጋና በኢትዮጵያ - በደረሰ አደጋ እና በደላችን የመንገድ ቅድሚያ ምንጭ፣ ለማህበረሰብ እና ለድርጅት ዝርዝር በመላክ እንዲሰረዝ በአፕሱ የተያዙ እንዲያግዝልን እናመሰረቃለን። የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ በመሆን እንደገና እንዲከበረ በዘርፉ ላይ መለያ እና የስለው አስተካከል ትምህርት ቅድሚያውን ተቀኖ እንቤተልሃለን።

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

21 Nov, 10:37

#DDR

" ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረት ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " - የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር 

የመጀመሪያ ዙር የትግራይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ዲሞቢላይዝድ በማድረግ ወደ  ተሃድሶ ስልጠና ማዕከላት የማስገባት ስራ በይፋዊ ስነስርዓት ተጀምሯል።

ዛሬ በተካሄደ ይፋዊ ስነስርዓት ላይ የተገኙት የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ አመራር ብርጋዴር ጀነራል ደርቤ መኩሪያው ፤ " የዴሞብላይዜሽን አሰራር ሴት ተዋጊዎችን ፣ አካል ጉዳተኞችን እና በአደረጃጀት ውስጥ ያሉ አመራሮችን በማስቀደም ይፈፀማል " ብለዋል።

በዴሞብላይዜሽን አሰራር በየቀኑ 320 ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማእከላት የማስገባት ስራ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።

በመጀመሪያ ዙር 75 ሺህ ታጣቂዎች እንደሚስተናገዱ አክለዋል።

" ማንኛውም ትጥቅ ከሀገር መከላከያ ሰራዊት ውጭ መያዝ የሀገሪቱ ህገ-መንግስት ይከለክላል ስለሆነም በትግራይ እየተፈፀመ ያለው የዴሞብላይዜሽን አፈፃፀም ህግና ስርዓት ተከትሎ የሚፈፀም ነው " ሱሉ ተናገረዋል።

ብ/ጄነራሉ ፤ " ትጥቅ መፍታት መሸነፍ ፣ መዋረድ ወይም ራስን ዝቅ ማድረግ ማለት አይደለም። ትጥቅ መፍታት ማለት የሀገር አንድነትና ሰላም በፅኑ መሰረይ ላይ ከማቆም አንፃር መታየት አለበት " ብለዋል።

" ትጥቅ ማስረከብ ማለት ያለችን እንዲት ሀገር ከሚጋረጡባት የውጭ ስጋቶች መታደግ መሆኑን መገንዘብ ያሻል " ያሉት ጀነራሉ  " ትጥቅ የማስፈታት ተግባሩ የትግራይ እና በክልሉ ደንበር አከባቢ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት ተፈፃሚ ይሆናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

የትግራይ የፀጥታ እና የሰላም ቢሮ ሃላፊ ጀነራል ፍስሃ በበኩላቸው ፤ " ትጥቅ የመፍታቱ ተግባር እርምጃ ለትግራይና ለሀገር ሰላም የተከፈለ ውድ እና ሁሌ በታሪክ ድምቆ የሚታወስ ፍፃሜ ነው " ብለዋል።

ዛሬ ትጥቃቸው ያስረከቡ 320 የቀድሞ ተዋጊዎች ሲሆኑ ወደ ተዘጋጀላቸው የስልጠና ማእከላት ማምራታቸው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ስነ-ስርዓቱ ከተከናወነበት ቦታ በላከው መረጃ ገልጿል።

#TikvahEthiopiaFamilyMekelle
አዲስ መረጃን ከቻናላችን ያግኙ👇
👇Telegram
https://t.me/Commando_And_Airborne_Command
👉YouTube 👇

https://www.youtube.com/@Ethio_Commandos

#WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029VaWOSZgLY6dED9IVqO36

Facebook 👇
https://www.facebook.com/Comando.and.airborne.forces

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

20 Nov, 17:25

ከነገ ጀምሮ 75 ሺህ የቀድሞ የትግራይ ተዋጊዎችን መልሶ የማቋቋም ሥራ በይፋ ይጀመራል ተባለ

የቀድሞ ታጣቂዎችን በዘላቂነት ለማቋቋም ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ተሃድሶ ማዕከላት የማስገባት ሥራ በነገው ዕለት ህዳር 12 ቀን 2017 ዓም እንደሚጀምር የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ከሰባት ክልሎች ከ371 ሺ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ በማስፈታት ወደ ማዕከላት ለማስገባት የመለየት ሥራ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡

በ2 ዓመታት ውስጥ በሚከናወነው የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ሥራ ከ760 ሚሊየን ዶላር በላይ በጀት መያዙንም አንስተዋል፡፡

በዚህም መሰረት መንግስት በመደበው 1 ቢሊዮን ብር እና ከአጋሮች በተገኘ 60 ሚሊዮን ዶላር በመጀመሪያው ምእራፍ በትግራይ ክልል የሚገኙ 75ሺ የቀድሞ ታጣቂዎችን ትጥቅ የማስፈታትና በዘላቂነት የማቋቋም ስራ ይጀመራል ብለዋል።

በክልሉ በመቀሌ፣ እዳጋሀሙስ እና አድዋ ሶስት ማዕከላት ተለይተዋል ያሉት ኮሚሽነሩ በመቀሌ ማዕከል በዚህ ሳምንት 320 የቀድሞ ታጣቂዎችን መቀበል እንጀምራለን በማለት ገልጸዋል።

የቀድሞ ታጣቂዎች ከዛሬ ህዳር 11 ቀን 2017 ጀምሮ በስፍራው የሚገኘው የአፍሪካ ህብረት ስር ሂደቱን የሚቆጣጠር፣ የሚያረጋግጥና የሚያስከብር የተልዕኮ ቡድን አባላት በሚታዘቡበት ለመከላከያ ሰራዊት ትጥቃቸውን ማስረከብ ይጀምራሉ ብለዋል።

በዚህም በቀጣይ 4 ወራት 75ሺ የቀድሞ የትግራይ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት፣ በዘላቂነት በማቋቋም ወደ ማህበረሰቡ የመቀላቀል ስራ ይከናወናል ሲሉ አረጋግጠዋል።

በ2 አመታት ውስጥም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ 371, 971 የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለው በዘላቂነት ለማቋቋም መታቀዱን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

18 Nov, 14:54

https://youtu.be/qdVMWMXAKzg?si=rls6TP1HfU-xMBDB

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

18 Nov, 11:19

ባይደን ዩክሬን ከአሜሪካ በተላኩላት ሚሳኤሎች ሩሲያን እንድትመታ ፈቀዱ፡፡

-  ቭላድሚር ፑቲን በበኩላቸው እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም ብለዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ዩክሬን ከአሜሪካ በተላኩላት ሚሳኤሎች በሩሲያ ላይ ጥቃት እንድትፈጽም ፈቅደዋል።

ባይደን ኬቭ ለወራት ስታነሳው የነበረውን ከድንበሯ ውጭ (በሩሲያ መሬት ውስጥ) የአሜሪካን ሚሳኤሎች የመጠቀም ጥያቄ የተቀበሉት በጥር ወር ዋይትሃውስን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት ነው።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮልድሚር ዜለንስኪ “እንዲህ አይነት ጉዳዮች በይፋ አይገለጹም፤ ሚሳኤሎቹ ራሳቸው ይናገራሉ” በማለት ከዋሽንግተን ፈቃድ ማግኘታቸውን በተዘዋዋሪ አረጋግጠዋል።

የባይደን አስተዳደር ከሞስኮ በሚነሱ ቅሬታዎች እና ማሳሰቢያዎች ምክንያት አሜሪካ ለዩክሬን የላከቻቸው ረጅም ርቀት ሚሳኤሎች በሩሲያ ግዛት ውስጥ ጥቃት ለማድረስ እንዳይውሉ ሳይፈቅድ ቆይቷል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንም ምዕራባውያን ሀገራት መሰል ውሳኔ ካሳለፉ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት(ኔቶ) በዩክሬኑ ጦርነት “በቀጥታ እንደተሳተፈ ይቆጠራል”፤ የኒዩክሌር ጦርነትም ሊያስነሳ ይችላል በሚል በተደጋጋሚ ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው።

የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ፤ ፕሬዚዳንት ባይደን ዩክሬን በሚሳኤሎቹ የሩሲያን ግዛት እንድትመታ ፈቃድ መስጠታቸውን የሚገልጽ መረጃ መውጣቱን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ፑቲን በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠታቸውን ገልጸዋል።

ቃል አቀባይዋ ፕሬዚዳንቱ ሰጡት ባሉት ምላሽ፥ “ባይደን በሩሲያ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ፈቃድ ሲሰጡ እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም”  ማለታቸውን ተናግረዋል ፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

18 Nov, 05:03

የተከሰከሰም ሆነ ችግር ያጋጠመው ሄሊኮፕተር የለም
            የመከላከያ ሚኒስቴር

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 08 ቀን 2017 ዓ.ም

የኢፌዴሪ አየር ኃይል ካሉት "ቤዞች" አንደኛው ምድብ የሆነው ባህርዳር የሚገኘው የምዕራብ አየር ምድባችን ነው። በትላንትናው ዕለት በነበረው የአየር ኃይል የምድብ ልምምድ ምክንያት መደበኛ የአየር መንገድ በረራ ለጥቂት ጊዜያት ተቋርጦ የነበር መሆኑን የኢፌዴሪ መከላከያ ማኒስቴር አስታውቋል።

ይሁን እንጅ የአየር መንገድ ተሳፍሪዎች የተወሰነ መጉላላትን አጋጣሚ በመጥቀስ ሄሊኮፕተር ተበላሸ፣ ተከሰከሰ በሚል የማደናገሪያ ሃሳብ በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያ እየተራገበ ይገኛል።

መደበኛ በረራ ለውስን ጊዜያት ተቋርጦ የነበረው በተገቢው መንገድ ስራ የጀመረ ሲሆን የምዕራብ አየር ምድብም ልምምዱን ስኬታማ በሆነ መንገድ አጠናቋል።

አሁን እያየን ያለነው ምናልባትም የጠላት ሁለንተናዊ አቅምና የፕሮፖጋንዳ መስክ መክሰርና መከስከስ ካልሆነ በስተቀር የተከሰከሰ ሄሊኮፕተር እንደሌለ ማሳወቅ እንወዳለን።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር

አዲስ መረጃን ከቻናላችን ያግኙ👇
👇Telegram
https://t.me/Commando_And_Airborne_Command
👉YouTube 👇

https://www.youtube.com/@Ethio_Commandos

#WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029VaWOSZgLY6dED9IVqO36

Facebook 👇
https://www.facebook.com/Comando.and.airborne.forces

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

16 Nov, 08:19

https://youtu.be/qdVMWMXAKzg?feature=shared

የፅንፈኛው ፋኖ ገመና ሲገለጥ😭😭😭😭

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

15 Nov, 16:43

#ሰበር_ዜና #ጁባላንድ

ጁባላንድ፣ ከሞቃዲሾ ፌደራል መንግሥት ጋር ያላትን የሥራ ግንኙነት ማቋረጧን አስታውቃለች

ጁባላንድ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግንኙነቷን ያቋረጠችው፣ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሐመድ በመላዋ ሱማሊያ የቀጥተኛ ምርጫ ሥርዓት ተፈጻሚ እንዲኾን ያወጡትን ሕግ ውድቅ በማድረግ ቀጥተኛ ያልኾነ ምርጫ ለማድረግ መወሰኗን ተከትሎ ነው።

የጁባላንድ አስተዳደር፣ የአገሪቱ ጦር አልሸባብን ከጁባላንድ እንዳያጸዳ ፌደራል መንግሥቱ እንቅፋት ፈጥሯል በማለትም ከሷል። ራስ ገዟ ፑንትላንድ ቀደም ሲል ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ግንኙነቷን ማቋረጧ አይዘነጋም።

አዲስ መረጃን ከቻናላችን ያግኙ👇
👇Telegram
https://t.me/Commando_And_Airborne_Command
👉YouTube 👇

https://www.youtube.com/@Ethio_Commandos

#WhatsApp
https://whatsapp.com/channel/0029VaWOSZgLY6dED9IVqO36

Facebook 👇
https://www.facebook.com/Comando.and.airborne.forces

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

13 Nov, 21:25

https://youtu.be/eOlVfozVz5w?si=BbNBvY7eUjFpgqZE

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

13 Nov, 20:52

https://www.facebook.com/Comando.and.airborne.forces

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

13 Nov, 17:02

https://youtu.be/gMFWR_qwEvI?feature=shared

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

11 Nov, 09:20

የክልሉ የግብርና ልማት የተረጋገጠው በሠራዊቱ ማስዋዕትነት ነው፡፡
    ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ህዳር 02 ቀን 2017 ዓ.ም

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አረጋ ከበደ የክልሉ የግብርና ልማት የተረጋገጠው በሀገር መከላከያ ሠራዊት ማስዋዕትነት መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ ይህንን የገለፁት ከክልሉ እንዲሁም  ከኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆኑ በሰሜን ሸዋ ዞን በኩታ ገጠም የለማውን ከፍተኛ የስንዴ ምርት በጎበኙበት ዕለት ሲሆን በክልሉ ያለውን የግብርና ልማት የተመለከተ ሰው ሠራዊታችን በትክክል ተዋጊ ብቻ ሳይሆን ቁልፍ የልማት ሀይል መሆኑን ከመገንዘቡም በላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ለሀገሩና ለህዝቡ የሚከፍለውን መስዋዕትነትና የላቀ ህዝባዊነቱን እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በየመንደሩ በተግበር ያረጋገጠበት ነው ብለዋል፡፡

አቶ አረጋ ከበደ ሠራዊት ባይኖር ኖሮ የክልሉ ህዝብ በሰው ሰራሽ ድርቅ ተመትቶ ከመራብ አይድንም ነበር፤ በመሆኑም የግብርና ምርትን መስዋዕትነት ድረስ በመክፈል ለአርሶ አደሩ በማድረስ ይህንን አደጋ በመቀልበስ ግብርናውን ለውጤታማነት ያበቃው መከላከያ ሠራዊት ነውና አርሶ አደራችን ይህንን ውለታውን መቼም አይዘነጋውም ነው ያሉት፡፡ ብቻም ሳይሆን ጠላት እንደሚያወራው ሳይሆን ህዝባችን ለሠራዊቱ የላቀ ክብር አለው ብላዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የተሳተፉት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኃይለማርያም ከፍያለው በበኩላቸው ክልሉ በ2016 /17 ዓ.ም የምርት ዘመን 5.2 ሚሊየን ሄክታር መሬት በሰብል በመሸፈን 169 ሚሊዮን ኩንታል የግብርና ምርት ለመሰብሰብ አቅዶ የሰራ ቢሆንም እቅዱ ያለ ሀገር መከላከያ ሠራዊት እንደማይሳካ ተናግረዋል። 

ፅንፈኛው ሀይል የግብርና ግብዓት ለአርሶ አደሩ እንዳይደርስ በማድረግ ከህዝብ እየዘረፈና እየቀማ ሲበላ አርሶ አደሩ የግብርና ስራውን ሳይሰራ ቀርቶ ለችግር እንዳይጋለጥ መስዋዕትነት በመክፈል ይህንን ሁኔታ ቀልብሶ ዛሬ ለአጥጋቢ ውጤት ያበቃን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ነው ብለዋል፡፡ እያየነው የለነው የስንዴ ጫካም የእሱ መስዋዕትነት ውጤት ነውና አርሶ አደራችንም ይህንን አይዘነጋም ሲሉ ተናግረዋል፡፡
 
https://youtu.be/NPfZYeC9Rvg?si=T2O0iYiz-j6-KX1_

11 Nov, 06:41

https://www.youtube.com/@Ethio_Commandos