ስኬታማ ተማሪ @sketamatemari Channel on Telegram

ስኬታማ ተማሪ

@sketamatemari


❇️ሰቃይ ተማሪ የመሆን ህልማችሁን ከስኬታማ ተማሪ ጋር እውን አርጉ!
❇️Subscribe ያድርጉ ስኬታማ ተማሪ ይሁኑ👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCN7ohAHhgQ1KSWAMFXb-Tkw
❇️Tik Tok:- vm.tiktok.com/ZMjRnQD79/
ለማስታወቂያ:- @sketamamarket

ስኬታማ ተማሪ (Amharic)

በዚህ ጽሑፉ መረጃ ውስጥ ስዋዝ እና ስኬታማ ተማሪ እንዲሆን ያስቆምናል። ስኬታማ ተማሪ የተለያዩ መረጃዎችንና ታሪኮቶችን በሚያገኙበት ምክር ተመልከቱ። ስኬታማ ተማሪ፣ የሚያገኙ ታሪኮችን የምፅነት ከአጀንዳችሁ በፊት የምንገኘባት ነው። ስኬታማ ተማሪ፣ ከፍታን ውስጥ ያሉትን ሚስጥሮችን ለማሻሻል ምንም አይከናነትም ። ለማስታወቂያ በ @sketamamarket ተመልከቱ። እናም ለአንድ ብሄራዊ ለማስታወቂያ ይህንን መመሪያ ለመጨረስ ምርጫዎችና በትእዛዝ ለመረጃ መረጃ ያድርጉ የYouTube መረጃዎችን ወደ Tik Tokን ለማስማወቂያለው። እናንተም ከአርጉ እና ማግኘት የመዝገበ ልደት እውን ስኬታማ ተማሪ ይሁኑ።

ስኬታማ ተማሪ

19 Nov, 17:31


#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲ መምህራንን ፈተና ለመፈተን እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰማ።

ትምህርት ሚኒስቴር፤ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስተምሩ መምህራንን ብቃት ለመመዘን ፈተና ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል።

በሚኒስቴሩ የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት እዮብ አየነው(ዶ/ር ) ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ በሰጡት ቃል ፥ " የመምህራን ፈተና ከዚህ በፊት በአንደኛ ደረጃ በሚያስተምሩት ላይ ተሞክሮ ነበረ በመሆኑም አልተጀመረም ማለት አይቻልም " ብለዋል።

አሁን ግን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መምህራንን ለመፈተን ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዝግጅቱ እንዳለቀ በዚህ ዓመት ወይም በቀጣዩ 2018 ዓመት ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መመህራን ፈተና መሰጠት ይጀምራል ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

18 Nov, 18:20


#ጥቆማ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጥሪ ማስታወቂያ አውጥቷል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ የካቲት ወር በአፍሪካ ህብረት ጉባኤ የሚሳተፉ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት እያደረገች ነው።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከአቀባበል እስከ አሸኛኘት ባለው የመስተንግዶ መርሃግብር በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል ካዴቶችን በመቀበል አሰልጥኖ በተለያዩ የፕሮቶኮል ሥራዎች ላይ ማሰማራት እንደሚፈልግ ገልጿል።

በመሆኑም ፦

- የእንግሊዘኛ፣
- የፈረንሳይኛ
- የዓረብኛ ቋንቋዎችን መናገርና መጻፍ የሚችሉ እና ዕድሚያቸው ከ18-30 የሆነ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ከህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ እ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ምዝገባው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋናው መ/ቤት በአካል በመገኘት ነው የሚከናወነው።

ተመዝጋቢዎች ለምዝገባ ሲመጡ የትምህርት ማስረጃቸውን እና ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ ይዘው እንዲቀርቡ ተብሏል።

ሚኒስቴሩ " የአገራት መሪዎች፣ የዓለምአቀፍና ቀጠናዊ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች በሚሳተፉበት የአህጉራችን ትልቁ ጉባዔ ላይ በጎ ፍቃደኛ ፕሮቶኮል በመሆን የዚህ ታሪክ አካል ሆናችሁ አገራችሁን ያለ ክፍያ በኩራት እንድታገለግሉ " ሲል ጥሪ አቅርቧል።

Via : tikvah ethiopia

@sketamatemari
@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

18 Nov, 15:43


ዩኒቨርስቲዎች አዲስ ተማሪዎቻቸውን እየተቀበሉ ይገኛሉ።


እየተቀበሉ የሚገኙት :-
👉 WolaitaSodo University
           👉 Aksum University
           👉 Raya University
           👉 Madda walabu University

የ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛሉ።

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

12 Nov, 15:49


#JinkaUniversity

በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በጂንካ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፍያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በፍሬሽማን ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 11 እና 12/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3X4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ።

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

09 Nov, 04:26


#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።

የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።

ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 08/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ነው።

ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

ተጨማሪ መረጃዎች፣ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም የወጡ ማስታወቂያዎች በዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ይመልከቱ 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

@sketamatemari

ስኬታማ ተማሪ

06 Nov, 16:35


#ድሬዳዋ ዩንቨርስቲ

በድሬዳው ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐ ግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የመግቢያ ቀን ህዳር 16 እና 17/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩንቨርስቲው ገልጿል።

ምዝገባ ለማድረግ የሚያስፈልጉ፦

- የ8ኛ ክፍል ስርትፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
- የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
- ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
- አራት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
- አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል ተብሏል፡፡

@sketamatemari