ከ10,000(አስር ሽህ) በላይ አማራ የሆኑ ወታደሮች በአብይ አህመድ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ታስረዋል። በርካቶችም በየቀኑ እየተረሸኑ ነው።
ከ10,000(አስር ሽህ) የሚበልጡ የአማራ ልጅ የሆኑ ወታደሮች በአማራ ህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እንዲፈጽሙ ቀጥተኛ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ግዳጅ ቀጠና ላይ የነበሩ እና በሌሎች የሐገሪቱ አካባቢዎች የነበሩ ሲሆኑ ለአማራ ህዝብ እና ለፋኖ ከፍተኛ አቅም መፍጠር ተባባሪ ናችሁ የሚል ምክንያት የተነሳባቸው ሲሆን ከእስረኞቹ መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት በየ ቀኑ እየተረሸኑ ይገኛል።
የአብይ አህመድ ስርዓት ትክክለኛ አማራን ለማጥፋት የተቋቋመ መሆኑን ባለመገንዘብ ጠመንጃ ተሽከመው የአብይን ስርዓት ሲያስቀጥሉ የነበሩ እና ከእግረኛ እሰከ ከ ብርጌዳል ጀኔራል ድረስ ማዕረግ ያላቸው የአማራ ልጆች የአብይ አህመድ ቀጥተኛ ሰለባ መሆናቸው ሌሎች በመከላከያ ውስጥ ላሉ የአማራ ልጆች ሁነኛ ማስተማሪያ ነው።
በመሆኑም አማራ ሆናችሁ በመናጆ ሳንቲም ተታላችሁ መከላከያ ውስጥ ያላችሁ የአማራ ልጆች በሰዓቱ ፋኖን ከተቀላቀሉ ወንድሞቻችን ተምራችሁ በፍጥነት ፋኖን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን ።
አብይ አህመድ ከህወሓት ጋር ጦርነት በገጠመ ጊዜ በርካታ የትግራይ ተወላጅ ወታደራዊ መኮንኖችን አስሮ ሲያሰቃያቸው እንደነበር ይታወቃል ።
ከዚህ ድርጊት ያልተማሩ የአማራ ልጆች መከላከያ ውስጥ ምን ይሰራሉ !?
በነገራችን ላይ የትግራይ ተወላጅ የሆናችሁ አሁን ክፍለጦር እና ሬጅመንት በመምራት ላይ ያላችሁ የጦር መኮንኖች አብይ አህመድ በፈለገ ጊዜ አስሮ ሲያሰቃያችሁ እንደነበር ዘንግታችሁ እሱ በፈለገ ጊዜ ፈቶ ንፁሐን ትገድሉ ዘንድ ወደ አማራ ክልል መጥታችሁ በማታውቁት እና በማይመለከታችሁ ጦርነት እየተሳተፋችሁ በመሆኑ ከዚህ ጨፍጫፊ ስርዓት ራሳችሁን እንድታገሉ እናሳስባለን ።
ሌሎች በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ ደግሞ የአማራ ጥያቄ በሐይል እንደማይቀለበስ ተገንዝባችሁ የፋኖ ወንድማችሁን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን ።
አማራም ሆነ ኢትዮጵያ ነፃ የሚወጡት ህዝባዊ መንግስት ሲመሰረት እንጅ ከእንግዲህ በኋላ በኢትዮጵያ ምድር በታንክ ጋጋታ የሚፀና መንግስት እንደማይኖር ልናስገነዝባችሁ እንወዳለን ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀጣይ የሚያወጣውን የምህረት አዋጅ ተጠቅማችሁ የህልውና ፤ የነፃነት ፤ የእውነት እና የሐገር ክብር እና የሐገር ፍቅር ስሜት የሚያንገበግበውን የአማራ ፋኖን እንድትቀላቀሉ ስንል ከወዲሁ እናሳስባለን።
አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
[የአማራ ፋኖ በጎጃም]