Debtera Media @debteramedia Channel on Telegram

Debtera Media

@debteramedia


ደብተራ ሚዲያ የእውነት ድምጽ!
ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!👇

በዩቲዩብ 👉 https://bit.ly/3bMfT8D

በፌስቡክ 👉 fb.me/DebteraMedia

በቴሌግራም 👉 t.me/DebteraMedia

ማንኛውንም ሃሳብ አስተያየት ሆነ መረጃ በ t.me/DebteraMedia_Bot ማድረስ ትችላላችሁ።

Debtera Media (Amharic)

ደብተራ ሚዲያ አማርኛ በአልባራት መሳሪያ አስተማሪ ደምጽን መለየት አይችልም። ደምጹን እና እንዴት የሚደረስ ነገር ነው? ይህ ቦታ ሰብስክራይብ ቤተሰብ ነው ፡፡ ሁላችንም ሃሳብ እና መረጃዎትን አሳብ ማድረግ የሚፈጠርም አይሆንም። በማስታወሻው ቦታ የምንጠቀመውን በ t.me/DebteraMedia_Bot ላይ ይጠቀሙ። በዩቲዩብ ከፈለቀ የማቀራበሪያዎትን ለማዳረግ የጻፍኩት ከሆነ ሲሆን በ https://bit.ly/3bMfT8D ይግቡ፡፡ በፌስቡክ ላይ ፣ በ Facebook ላይ በ fb.me/DebteraMedia ለመጫን ይህን ይጫኑ። እና በቴሌግራም ላይ ምንም አልስማማም የአገልግሎት እና ማንኛውንም ሃሳብ በሚከተለው ስብስብ ወደ t.me/DebteraMedia ይደረሱ።

Debtera Media

08 Jan, 04:30


- ሚስቱ ግን በረከቱን ሽታ ልታየው ብትሞክርም አልተሳካም:: ሕገ ምናኔ አይፈቅድምና:: በዚህ ነገር ፈጽማ ማዘኗን በጸጋ ያወቀው አባ ዮሐንስ ግን በራዕይ ወደ እርሷ መጣ:: "ሚ ሊተ ወለኪ ብእሲቶ - አንቺ ሆይ! ለምን ካላየሁህ እያልሽ ትዘበዝቢኛለሽ? እኔ ነቢይ ወይ ጻድቅ አይደለሁ" ብሏት ባርኯ ተሠወራት:: እርሷም ደስ ብሏት ለባሏ ነገረችው:: ባሏ ወደ ጻድቁ ሲሔድም ገና ሳይነጋገሩአባ ዮሐንስ ሳቅ ብሎ "ሚስትህ ደስ አላት አይደል?" ብሎታል:: ጻድቁ በ፺ [ 90 ] ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

አምላከ ጻድቃን ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ በጐ ምኞታችንን ይፈጽምልን:: ከበረከታቸውም ያድለን::

🕊

[  † ታሕሳስ ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አባ ዮሐንስ አበ ምኔት
፪. አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
፫. አባ ዮሐንስ ብጹዕ
፬. ፻፵፬ ሺህ "144 ሺ" ሕጻናት [ ሔሮድስ የገደላቸው ]

[   † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፫. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፬. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፭. አባ ሣሉሲ ክቡር ጻድቅ

" ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና በመጠን ኑራችሁ : ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ:: እንደሚታዘዙ ልጆች ባለ ማወቃችሁ አስቀድሞ የኖራችሁበትን ምኞት አትከተሉ:: ዳሩ ግን 'እኔ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ' ተብሎ ስለ ተጻፈ የጠራችሁ ቅዱስ እንደ ሆነ እናንተ ደግሞ በኑሯችሁ ሁሉ ቅዱሳን ሁኑ::" [፩ዼጥ.፩፥፲፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

08 Jan, 04:30


🕊

[  † እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን ወገዳማውያን "አባ ዮሐንስ" : "አባ ዘካርያስ ወአባ ዮሐንስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

---------------------------------------------

🕊  †  አባ ዮሐንስ ዘአስቄጥስ  †  🕊

- ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

- ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [ በበርሃ ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

- ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ፵ ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ [ ኤሌዎን ዋሻ ] በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

- ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

- ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ፹ [ 80 ] ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

- ይህ ከሆነ ከ ፳ [ 20 ] ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

- እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

- አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::

- ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::

- በ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::

- በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::

- ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ : አባ አብርሃም : አባ ሚናስ : አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::

- አንድ ጊዜም ለልጆቻቸው መነኮሳት ቤዛ ሆነው በበርበር [ አረማውያን ] ተማርከዋል:: በዚያም ክፉዎች ባሪያ ቢያደርጉዋቸው እግዚአብሔር ድንቅን ሠርቶ ወደ ገዳማቸው መልሷቸዋል:: ከብዙ ተጋድሎ በሁዋላም በ90 ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈው በበዓታቸው ተቀብረዋል::


🕊  † አባ ዘካርያስ ገዳማዊ  †  🕊

- ይሕም ቅዱስ የተነሳው በዚያው በዘመነ ጻድቃን ነው:: ምንም ክርስቲያን ቢሆንም በቀደመ ሕይወቱ ገንዘብ የሚጥመው ነጋዴ ነበር:: በንግድ ሥራውም ሃብታም መሆን ችሎ እንደ ነበር ዜና ሕይወቱ ይናገራል::

- እግዚአብሔር ሁሉም የሰው ልጆች ወደ መንግስተ ሰማያት ቢገቡ መልካም ፈቃዱ ነው:: ያ ብቻ አይደለም:: ለእያንዳንዱ ሰው የድኅነት ጥሪን በተለያየ መንገድ ያቀርብለታል:: ድምጹን ለሰማ ወደ ወንጌል ወደብ ያደርሰዋል::

- አንዳንዴ "እንቢ" ስንለው እንደ በጐ አባትነቱ በተግሣጹ ሊጠራንም ይችላል:: ተግሣጹም በደዌ: በአደጋና በመሰል መንገዶች ሊሆን ይችላል:: ዋናው ቁም ነገር ግን ጊዜው ሳያልፍብን: ቀኑም ሳይመሽብን ድምጹን መስማት: ለቃሉ መታዘዝ: ጥሪውንና ተግሣጹን አለማቃለል ነው::

- አባ ዘካርያስም የቅድስና ሕይወት ጥሪ የደረሰው ለሥጋ ገበያ ሲታትር ነበር:: አንድ ቀን ንብረቱን ይዞ ለንግድ መንገድ ላይ ሳለ ሽፍቶች ያዙት:: ሊያርዱት አጋድመውት ሳለ ግን የገዳመ ዻኩሚስ አበ ምኔት በሥፍራው ነበርና ጮኸባቸው::

- ቅዱሱ አበ ምኔት አካሉ በገድል ያለቀ ቢሆንም ድምጹ እንደ ነጐድጉዋድ ሲመጣ ገዳዮቹ ደንግጠው በረገጉ:: ዘካርያስም ከሞት ተረፈ:: እንደ ገና ሃብቱን ይዞ ወደ ከተማ ሲገባ በሃገረ ገዢው ተይዞ ሞት ተፈረደበት:: ከገንዘቡ መብዛት የተነሳ ዘራፊ መስሏቸው ነበርና:: በዚህ ጊዜም እግዚአብሔር በመኮንኑ ልብ ርሕራሔን ጨምሮ አዳነው::

- በዚያች ሌሊት ግን ነገሮችን ያስተዋለው ዘካርያስ የተፈጠሩት አጋጣሚወች የፈጣሪው ጥሪ እንደ ሆኑ አስተዋለ:: ወዲያውም ለዓይነ ሥጋ የሚያሳሳውን ያን ሁሉ ንብረቱን መጽውቶ በርሃ ገባ:: በደብረ አባ ዻኩሚስም መንኩሶ በዓት ወሰነ::

- ከዚያች ቀን ጀምሮም በፍጹም አምልኮ: በጾምና በጸሎት እግዚአብሔርን እያገለገለ ከርኩሳን መናፍስት ጋር ታገለ:: በእግሩም ወደ ኢየሩሳሌም ተጉዞ ቅዱሳት መካናትን ተሳለመ:: አንድ ጊዜም ሰይጣን ሰው መስሎ "አባትህ ሳልሞት ልየው እያለህ ነው" አለው:: ውስጡ ግን ፈቃደ ሥላሴ ነበረበትና "እሺ" ብሎ ሒዶ: አባቱን ቀብሮ ተመልሷል::

- ቅዱስ አባ ዘካርያስ ከብቃቱ የተነሳ የሚኖረው ከግሩማን አራዊት ጋር ነበር:: ሁሉንም አራዊትም ይመግባቸው ነበር:: በተለይ ደግሞ ዘንዶዎች ሰውን እንዳይጐዱ አዝዞ እርሱ ይመግባቸው ነበር:: የተጋድሎ ዘመኖቹን ከፈጸመ በሁዋላም በዚህች ቀን በክብር ዐርፏል::


🕊  †  አባ ዮሐንስ ብጹዕ  †  🕊

- ይህም ቅዱስ በተመሳሳይ የዘመነ ጻድቃን ቅዱሳን ፍሬ ነው:: "ኢትርአይ ገጻ : ወኢትስማዕ ድምጻ" በሚለው ሕገ ተባሕትዎ ለ40 ዓመታት ተወስኖ ኑሯል::

- ይህም ማለት አንድ ወንድ ከመነነ በሁዋላ ሴቶችን እንዲያይና ከእነርሱም ጋር እንዲያወራ አይፈቀድለትም:: ሴትም ብትመንን ሕጉ ያው ነው:: [ ዛሬ እየተደረገ ያለውን ግን ፈጣሪ ይመርምረው ]

- አባ ዮሐንስ ብጹዕም እንዲህ ባለ ፈሊጥ: ማለትም በጾምና በጸሎት: ከዓለም ተለይቶ: ከሴት ርቆ: ንጽሕ ጠብቆ ሲኖር አረጀ:: በጊዜው በከተማ የሚኖር አንድ መስፍን ወዳጅ ነበረው:: ይህ መስፍን ዘወትር ወደ ጻድቁ እየመጣ ይባረካል::

Debtera Media

07 Jan, 03:52


🕊

✞ እንኩዋን ለዓለም ሁሉ ጌታ "ኢየሱስ ክርስቶስ" ዓመታዊ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

---------------------------------------------

🕊  †  ልደተ ክርስቶስ †  🕊

ዓለማትን : ዘመናትን : ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ : ወልደ አምላክ ነው:: የእግዚአብሔር አብ የባሕርይ ልጁ ሲሆን ራሱም እግዚአብሔር ነው:: በባሕርየ ሥላሴ መበላለጥ የለምና ወልድ ክርስቶስ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው እንጂ አይበልጥምም : አያንስምም::

- እርሱ ቅድመ ዓለም የነበረ : ማዕከለ ዓለም ያለና ዓለምን አሳልፎ የሚኖር ጌታ ነው:: ቀዳማዊና ደኃራዊው : አልፋና ኦሜጋ እርሱ ነው:: [ዮሐ.፩፥፩ , ራዕ.፩ ] ሁሉ በእጁ የተያዘ ነው::

- እርሱ እውነተኛ አምላክ [ ሮሜ.፱፥፭ ] : የዘለዓለም አባት : የሰላምም አለቃ ነው:: [ ኢሳ.፱፥፮ ] ቅድመ ዓለም ሲሠለስ : ሲቀደስ ኑሮ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እርሱ ሁሉን ያስገኛል እንጂ ለእርሱ አስገኝ የለውም::

" አንድ ክርስቲያን ከሁሉ አስቀድሞ ሊያውቀው የሚገባ መሠረተ እምነት ይሔው ነው !! "

- መድኃኒታችን ክርስቶስን በዚህ መንገድ የማያምንና የማያመልክ ሁሉ እርሱ ክርስቲያን አይደለም:: ምንም ሥጋችንን ተዋሕዶ ብዙ የትሕትና ሥራዎችን ቢሠራም : ቢሰቀል : ቢሞትም እርሱ እግዚአብሔር ነውና ፍጹም አምላክ ፍጹምም ሰው ብለን ልናመልከው ይገባል::

- እንደ አርዮስ: ንስጥሮስና ልዮን የማይገቡ ነገሮችን መናገር ጐዳናው የሞት: መዳረሻውም ገሃነመ እሳት ነው:: እንኩዋን የክብር ባለቤት መድኅን ክርስቶስ ላይ በፍጡር ላይ እንኩዋ የማይገባ ነገርን የተናገረ ሁሉ የገሃነም ፍርድ አለበት::

" ለእርሱ የዓለም ፈጣሪ : ጌታና ቤዛ ለሆነው መድኅን ኢየሱስ ክርስቶስ ለዘለዓለም ምስጋና : ጌትነት : ውዳሴና አምልኮ ይሁን !! "

- እግዚአብሔር አዳምን በ፯ ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ:: በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ : በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ : በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት:: በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ " ከ፭ ቀን ተኩል [ 5,500 ዘመን ] በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው::

- ከዚህ በሁዋላ ለ ፭ ሺህ ፭ መቶ [ 5,500 ] ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር:: ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር : ሱባኤ ይቆጠር : ምሳሌም ይመሰል ገባ::

- ከአዳም እስከ ሙሴ [ ዘመነ አበው ] ምሳሌያት ይበዛሉ:: ከሙሴ እስከ ዳዊት [ ዘመነ መሣፍንት ] ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ [ በዘመነ ነቢያት / ነገሥት ] ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል::

- ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል:: እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል::


🕊  †  ልደተ ክርስቶስ እምድንግል †  🕊

- "ጊዜው ሲደርስ አንባ ይፈርስ" እንዲሉ አበው መደኃኒታችን የጥልን ግድግዳ ያፈርስ ዘንድ: ከኃጢአትና ከሞት ቁራኝነት ይፈታን ዘንድ: ለሰዎች ቤዛ ይሆን ዘንድ: ትንቢተ ነቢያትን ይፈጽም ዘንድ: በቀጠሮ [ በ ፭ ቀን ተኩል ] ወደዚህ ዓለም መጣ::

- የሰማይና የምድር ጌታ በእንግድነት በመጣ ጊዜም እርሱን ለመቀበል በተገባ የተገኘች ንጽሕት ሙሽራ ድንግል ማርያም ሆነች:: ከእርሷ በቀር ለዚህ ክብር ሊበቃ የሚቻለው ፍጥረት: እንኩዋን ኃጢአት ካደከመው የሰው ልጅ ከንጹሐን መላእክት ወገን አልተገኘም::

- በጊዜውም መልአከ ትፍሥሕት ቅዱስ ገብርኤል መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን ወደ ድንግል ወርዶ የአምላክን ሰው የመሆን ዜና ከውዳሴና ከክብር ጋር ነገራት:: [ ሉቃ.፩፥፳፮ ] ድንግልም ለ9 ወራት ከ ፭ ቀናት ሰማይና ምድር የማይችሉትን መለኮትን ተሸከመች::

- ልክ ሙሴ በደብረ ሲና እንዳያት ዕጽ ድንግል ማርያምንም ባሕርየ መለኮቱ አላቃጠላትም:: ስለዚህም ነገር "ወላዲተ አምላክ: ታኦዶኮስ: ንጽሕተ ንጹሐን: ቅድስተ ቅዱሳን: ንግሥተ አርያም: የባሕርያችን መመኪያ . . ." እያልን እንጠራታለን::

- ግሩም ድንቅ ጌታን ጸንሳ ዘጠኝ ወራት እስኪፈጸሙ ድረስ ብዙ ተአምራትን ሠራች:: መላእክተ ብርሃን እየታጠቁ አገለገሏት: አመሰገኗት:: ልጇን አምላክ: እርሷን እመ አምላክ እያሉ ተገዙላት::

- ከዚያም በሮሙ ቄሣር በአውግስጦስ ዘመን ሰው ሁሉ ይቆጠር ዘንድ አዋጅ ወጥቷልና እመ ብርሃን ማርያም ከቅዱሳኑ ዘመዶቿ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር ወደ አባቷ ዳዊት ከተማ ወደ ቤተ ልሔም ሔደች::

- በዚያም ሳሉ የምትወልድበት ጊዜ ቢደርስ በፍጹም ድንግልና እንደ ጸነሰችው ሁሉ በፍጹም ድንግልና ወለደችው:: [ ኢሳ.፯፥፲፬ , ሕዝ.፵፬፥፩ ] ተፈትሖም አላገኛትም:: ልማደ አንስትም አልጐበኛትም:: ምጥም አልነበረባትም::

- ድንግል ማርያም ክርስቶስን በወለደች ጊዜ ልጇ አምላክ: እርሷም የአምላክ እናት መሆኗ ይታወቅ ዘንድ:-

፩. የብርሃን ጐርፍ ፈሰሰ:
፪. ፺፱ [ 99 ] ኙ ነገደ መላእክት ወርደው "ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም" እያሉ ዘመሩ:
፫. ትጉሐን እረኞች በቅዱስ ገብርኤል መሪነት መጥተው ክብሩን ተካፈሉ :
፬. በሰማይም ልዩ ኮከብ ድንግልና ልጇ ተስለውበት ዝቅ ብሎ ታየ:
፭. ቅድስት ሰሎሜም በድፍረት የድንግልን ሆድ ዳስሳ እጇ ቢቃጠል እንደ ገና በተአምራት ድኖላታል::

- በጊዜውም በምሥራቅ የፋርስ: የባቢሎንና የሳባ ነገሥት አስቀድሞ ከበለዓም: በሁዋላም ከዠረደሸት በተረዱት መሠረት ኮከቡን በማየታቸው ታጥቀው ተነሱ::

- ከምሥራቅ አፍሪቃና ከእስያም በተመሳሳይ ኮከቡን በማየታቸው ፲፪ ነገሥታት በየግላቸው ፲ ፲ ሺህ ሠራዊትን እየያዙ ድንግልንና ንጉሥ ልጇን ፍለጋ ወጡ::

- ፲፪ቱ ነገሥታት ከነ ሠራዊታቸው ሲሔዱ ስንቃቸው በማለቁ ፱ ነገሥታት ተስፋ ቆርጠው ተመለሱ:: ፫ቱ ግን በፍጹም ጥብዓት ከ፴ሺ ሠራዊት ጋር በኮከብ እየተመሩ ኢየሩሳሌም ደረሱ::

- እነዚህም መሊኩ የኢትዮዽያ [ የሳባ ንጉሥ ተወራጅ ] : በዲዳስፋና መኑሲያ [ ማንቱሲማር ] ደግሞ የፋርስና የባቢሎን ነገሥታት ናቸው:: ወደ ኢየሩሳሌም ሲደርሱም ሔሮድስና ሠራዊቱ ታወኩ::

- እነርሱ ግን የቤተ ልሔምን ዜና ከጠየቁ በሁዋላ በጐል ድንግል ማርያምን : ክርስቶስን : ዮሴፍና ሰሎሜን አገኙ:: ለ፪ ዓመታት እነርሱን ፍለጋ ደክመዋል : ተንከራተዋልና ደስታቸው ወሰን አጣ::

- በእመቤታችንና በልጇ ፊት በደስታ ዘለሉ:: " አንፈርዓጹ ሰብአ ሰገል " እንዲል:: ወርቁን: እጣኑንና ከርቤውንም ገብረው: በግንባራቸው በፊቱ ሰገዱ:: ፫ ጊዜም እየወጡ እየገቡ ቢመለከቱት በኪነ ጥበቡ አንዴ እንደ ሕጻን : በ2ኛው እንደ ወጣት : በ ፫ኛው እንደ አረጋዊ ሆኖ ታይቷቸው ፈጽመው አድንቀዋል::

- ወደ ሃገራቸው ሲመለሱም " ወአስነቀቶሙ ሕብስተ ሰገም " እንዲል የገብስ ዳቦ ጋግራ ድንግል ለሰብአ ሰገል ሰጠቻቸው:: እነርሱም ይህንን እየተመገቡ የ፪ ዓመቱን መንገድ በ፵ ቀን ሲጨርሱት ዳቦው ግን ያ ሁሉ ሺህ ሰው ተመግቦት አላለቀም:: ተአምራትንም ሠርቷል::

" የልደቱ ነገር እንዲሁ ተተርኮ የሚያልቅ አይደለምና ይቆየን:: የከርሞ ሰውም ይበለን:: "


🕊  †  ቅዱስ ላል-ይበላ ንጉሥ †  🕊

Debtera Media

07 Jan, 03:52


- በ፲፪ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ በሃገራችን የነገሠው ቅዱስ ላሊበላ :-

- በብሥራተ መልአክ ተወልዷል :
- ቅዱሳት መጻሕፍትን ገና በልጅነቱ አጥንቷል :
- የንጉሥ ዘር ቢሆንም በጾምና ጸሎት : በትሕርምት አድጉዋል::

- በወንድሙ ቢገረፍም ቂም አልነበረውም:
- ስለ ወዳጆቹ ፍቅር መርዝ ጠጥቷል:
- በዙፋን ላይ የኢትዮዽያ ንጉሥ ሆኖ ቢቀመጥም እርሱስ አኗኗሩ ገዳማዊ ነበር:
- ከተባረከች ሚስቱ ቅድስት መስቀል ክብራ ጋር አንዲት ማዕድ ብቻ በቀን ይቀምሱ ነበር:: ለዛውም ለምለሙን ለነዳያን ሰጥተው እነርሱ የሚበሉት የእንጀራውን ቅርፍት [ ጠርዝ ] ብቻ ነበር::

- በአካለ ሥጋ ወደ ሰማያት ተነጥቆ ብዙ ምሥጢራትን አይቷል :
- በምሳሌውም ሃገረ ሮሃን [ ላስታን ] ገንብቷል:
- ዛሬም ድረስ ምስጢር የሆኑት ፍልፍል አብያተ መቃድስ የእጆቹ ሥራዎች ናቸው::

- ሥራውን ከፈጸመ በሁዋላ መንግሥቱን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አውርሶ : በመንኖ ጥሪትና በቅድስና ኑሮ አርፏል:: ጌታችን ስምህን ያከበረ : ዝክርህን የዘከረ: ከቤትህ ያደረውን : ከርስተ መንግስተ ሰማያት አካፍለዋለሁ ሲል ቃል ኪዳን ገብቶለታል:: ይህቺ ዕለት ቅዱሱ ንጉሥ የተወለደባት ናት::

- እኛን ስለ ወደደ ሰው የሆነ ጌታ ፍቅሩን ይሳልብን:: ከድንግል እናቱና ከልደቱ በረከትም ያሣትፈን::

🕊

ታሕሳስ ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ልደተ ክርስቶስ ስቡሕ
፪. ታኦዶኮስ [ ድንግል ማርያም ]
፫. ቅዱስ ኢያሱ ነቢይ [ ልደቱ ]
፬. ቅዱስ ላሊበላ [ ልደቱ ]
፭. አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ [ ልደታቸው ]
፮. ጻድቅ አቃርዮስ [ ንጉሠ ሮሃ ]
፯. ቅዱስ ቆሪል ገመላዊ
፰. ሰብአ ሰገል
፱. ዮሴፍና ሰሎሜ
፲. ቅዱሳን ሰማዕታተ አክሚም

ወርኀዊ በዓላት

፩. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፪. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፫. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፬. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
፭. ቅድስት አርሴማ ድንግል

" እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራቹሃለሁና አትፍሩ:: ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት: እርሱም ክርስቶስ: ጌታ የሆነ ተወልዶላቹሃልና:: " [ ሉቃ.፪፥፲ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር  †


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

            †       †       †
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

💖                🕊                   💖

Debtera Media

06 Jan, 16:57


🕊                       

💖   እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ  💖


[    " ብርሃንሽ መጥቶአልና ፥ የእግዚአብሔርም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ ፥ አብሪ። "    ]

[ ኢሳ. ፷ ፥ ፩ - ፬ ] ]

💖                    🕊                     💖

❝ የሰማይ ሥርዓት በምድር ላይ ተሠራ። ቤተልሔም ሰማይን መሰለች : ስለ ፀሐይም በቅዱሳን ላይ የሚያበራ ለዘወትርም ጨለማ የማይቃወመው ኅልፈት ጥፋት የሌለበት ዕውነተኛ ፀሐይ በውስጧ ተገኘ።

የብርሃኑም ክበብ መምላትና መጉደልን ስለሚያፈራርቅ በጨረቃ ፈንታ በዕብራይስጥ ማሪሃም የተባለች የድንግልናዋም ምስጋና በሁሉ የመላ ነው። ለዘወትርም የማይጎድል እመቤታችን የተመረፀች ድንግል ማርያም ተገኘች : ስለ ከዋክብትም መላእክተ ብርሃን ታዩ።

ወደዚህ ማኅበር አንድነት እኖር ዘንድ ማን በከፈለኝ : ከመላእክት ጋር እንዳመሰግን : ካዋላጅቱም ጋር እንዳደንቅ : ከእረኞችም ጋር እንዳገለግል።

በረቱን እጅ እነሣ ዘንድ ማን በከፈለኝ : የሙታን ሕይወት የኃጥአንም ንጽሕና : የቅቡፃን ተስፋ የተጨነቁትንም የሚያድን ጌታ ወደተቀመጠበት።

የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ።

ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ። የብርሃን ልጅ ወደ ሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ : የእግሯን ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ። ❞

🕊 አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ  🕊 ]


                †       †       †
†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

01 Jan, 12:54


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

[             ክፍል  ስድሳ ስድስት             ]

                         🕊  

ስለ መንፈሳዊ ተጋድሎ ያስተማረው ! ]

🕊

❝   አንድ እኁ እንዲህ ሲል ቅዱስ መቃርዮስን ፦ “ አባቴ ሆይ ፣ በእግዚአብሔር ስለ መጽናት ንገረኝ” ሲል ጠየቀው፡፡ አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ “ ማሯን የምትሠራበትን ነገር እስክታጠራቅም ድረስ በአረንጓዴ ዕፅዋቶችና በመስክ ባሉ አበባዎች መካከል እንደምትበር ንብ ያለ ነው ፣ እርሷም በቀፎዋ ጭስ የሚያጨስባት እስከሌለ ድረስ ጣፋጭ የሆነ ማርን ከመሥራት አታቋርጥም፡፡ ” ያ እኁም ፦ “ አባቴ ሆይ ፣ ጭሱ ምንድን ነው ? ጣፋጩስ ምንድን ነው ? ” አለው፡፡

አባ መቃርዮስም እንዲህ አለው ፦ ነገረ ዝሙት ፣ ርኲሰት ፣ አስጸያፊ ነገሮች ፣ የቅናት ሃሳቦች ፣ ጥላቻዎች ፣ ከንቱ አስተሳሰቦችና ሌሎች ይህን የመሳሰሉት ሥጋዊና ጊዜያዊ ደስታዎችና ፍላጎቶች ጭሶች የተባሉት እነዚህ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል አበባዎቹ ደግሞ የቅድስና ሕይወት መንገዶችና ተግባራት ናቸው፡፡ ንቧ አምልኮተ እግዚአብሔር ናት ፣ ቀፎው ልብ ነው ፣ ጣፋጩ ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡

ስለዚህ ጽናትን የሚያሳይ ሰውና ነፍሱን በመልካም ሕይወት ሁሉና በንጽሕና ሁሉ የሚሞላ ሰው በእግዚአብሔር መጽናትን በተግባር የሚያሳይ እርሱ ነው፡፡ ልጄ ሆይ ፦ አሁን ሂድ አለው፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


💖                    🕊                     💖

Debtera Media

01 Jan, 08:25


                        †                           

🕊 💖 ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት 💖 🕊

                         🕊                         

❝  አቤቱ አመጣጥኽን ፤ ልደትኽንም ፤ ጥምቀትኽን መገለጽኽንም ፤ ስቅለትኽን ፣ ሕማማተ መስቀል መቀበልኽንና ሞትኽንም ፤ ትንሣኤኽን ዕርገትኽንና ዳግመኛ መምጣትኽን ትንቢት ስለተናገረ ስለአገልጋይኽ ዳዊት በምሕረትኽ ዐስበኝ ፤ ስለርሱም ብለኽ በቀን ከሚወረውር ፍላጻ ፤ በሌሊትም ከሚኼድ ክፉ ሥራ አድነኝ ፤ እኔን አገልጋይኽንም ዕድል ፈንታዬን ጽዋ ተርታዬን ከቅዱሳን ካህናት ጋር አድርግ ፤ አሜን። ❞

[  ተአምኆ ቅዱሳን  ]

🕊                        💖                      🕊

❝ አቤቱ ጕልበቴ ሆይ ፥ እወድድሃለሁ። እግዚአብሔር ዓለቴ ፥ አምባዬ ፥ መድኃኒቴ ፥ አምላኬ ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።። ❞

[  መዝሙረ ዳዊት . ፲፰ ፥ ፩ - ፫  ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

❝ እኔም ፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ። ❞

[   ፪ነገሥ.፲፱ ፥ ፴፬   ]

🕊

[  †  🕊  እንኳን አደረሳችሁ  🕊  †  ]


🕊                        💖                      🕊

Debtera Media

31 Dec, 23:20


🕊

[  † እንኩዋን ለጻድቅ: የዋሕና ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †

---------------------------------------------

🌷 ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ 🌷

- ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል :- "እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ: አይጸጸትም::"
[መዝ.፻፴፩፥፲፩]  አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" [መዝ.፹፰፥፳] ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን::

- እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ "ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ" [መዝ.፹፰፥፴፭] ይላል::

- አቤት አባታችን ዳዊት ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል እንላለን::

- ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት ፯ ሃብታት ሲኖሩት :-

፩. ሃብተ ትንቢት
፪. ሃብተ መንግስት
፫. ሃብተ ክህነት
፬. ሃብተ በገና [መዝሙር]
፭. ሃብተ ፈውስ
፮. ሃብተ መዊዕ [ድል መንሳት]
፯. ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::

- በ ፯ ቱ ስሞቹም :-

፩. ጻድቅ
፪. የዋህ
፫. ንጹሕ
፬. ብእሴ እግዚአብሔር
፭. ነቢየ ጽድቅ
፮. መዘምር እና
፯. ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::

†   🌷  ልደት  🌷   †

- ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለ ልደቱ ሲናገር "እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ-በኃጢአት ተጸነስኩ" ይላል [መዝ.፶፥፭]  አበው እንደ ነገሩን የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ነው::

- ሚስቱን ሰሊብን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዐይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር:: አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ግን ያንን ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል:: በዚያች በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና እንዲህ ብሏል::

†   🌷  ዕድገት   🌷   †

ቅዱስ ዳዊት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር:: ሕጸን ሳለ በእረኝነት በጐቹን አያስነካም ነበር:: አንበሳውን በጡጫ: ድቡን በእርግጫ: ነብሩን በሩጫ የያዙትን ያስጥላቸው ነበር:: በጥቂቱ በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእሥራኤል እረኛ ሊሆን ተመርጧል::

†   🌷 መቀባት   🌷   †

- እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ" ቢለው ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም ገብቷል::

- በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: ፯ ቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ:: ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ:: በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ ምርጫም በ፲፪ ዓመቱ ንጉሥ ተባለ::

†   🌷  ዳዊትና ጐልያድ  🌷   †

ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሱባቸው ጊዜም ጐልያድ የሚሉት የጌት ሰው እሥራኤልን ሲያስጨንቅ ለ፵ ቀናት ቆይቶ ነበር:: ለአምላኩ ስምና ክብር የሚቀና ቅዱስ ዳዊት ግን በድፍረት ገጥሞ በፈጣሪው ኃይል: በጠጠር ጥሎታል:: ከእሥራኤልም ሽሙጥን አርቁዋል:: ግን ቅዱሱ ብላቴና: ጐልያድ ደግሞ ፮ ክንድ [፫ ሜትር] የሚረዝም ሰው ነበር::

†   🌷   ስደት  🌷   †

- ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ዙፋን አልጠበቀውም:: ጠላታቸውን ጥሎ ስላዳናቸው ፈንታ: ሳዖልን በገና እየደረደረ ስለ ፈወሰው ፈንታም ሊገደል ተፈለገ:: ፈጣሪው ከእርሱ ጋር ባይሆንም ይገድሉት ነበር::

- እርሱ ግን ለ፲፰ ዓመታት በትእግስት ተሰደደ:: ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ጠላቱን ሳዖልን አሳቻ ሥፍራ ላይ አግኝቶ በምሕረት ተወው:: በዚህ የዋሕነቱም በብሉይ ሆኖ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" የምትለውን ሕግ ፈጸማት:: [ማቴ.፯፥፵፭, መዝ.፲፮፥፬]

†   🌷   ንግሥና  🌷   †

- ቅዱስ ዳዊት የስደት ዘመኑ ሲፈጸም ሳዖል ሞተ:: ምን ጠላቱ ቢሆን 'የሳዖል ገዳይ ነኝ' ያለውን ተበቀለ:: ስለ ጠላቱም አለቀሰ:: ፴ ዓመት ሲሆነው ነግሦ ለ፯ ዓመታት በኬብሮን: ለ፴፫ ዓመታት በኢየሩሳሌም [ጽዮን] ሕዝበ እግዚአብሔርን ጠብቁዋል::

- በዘመኑም ጠላቶቹን ሁሉ ድል አድርጉዋል:: በልጁ አቤሴሎም እጅ መሰደድን: በሳሚ ወልደ ጌራ መሰደብንም ታግሷል::

†   🌷   ንስሃ    🌷    †

- ቅዱሱ ንጉሥ ሁሉ ነገር የተሰጠው አባት ነው:: ሁሉ ሕይወቱም ለእኛ ት/ቤት ነው:: ሰው ነውና የኦርዮን ሚስት ቀምቶ: ኦርዮን አስገድሎ ነበር:: ጉዳዩን ነቢዩ ናታን በምሳሌ ሲነግረው ፍጹም ተጸጸተ::

- ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ አለቀሰ:: መሬትንም በእንባው ክንድ አራሳት:: ሐረግ እስከ ማብቀልም ደረሰ:: እግዚአብሔርም ንስሃውን ተቀብሎ ከፍ ከፍ አደረገው:: በንስሃ ለምትገኝ ጸጋም ምሳሌ ሆነ::

†    🌷    ነቢይነት   🌷   †

በቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ቅዱስ ዳዊትን የሚያህል ነቢይ [ምሥጢር የበዛለት] አልተገኘም:: 'ከዓለም በፊት እንዲህ ነበረ' ብሎ: ከዚያ ከስነ ፍጥረት እስከ ዳግም ምጽዓት የተናገረ እርሱ ነው::

- ስለ መላእክት: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግልና መነኮሳት ሁሉ መናገሩ ይደነቃል:: ስለ ድንግል ማርያምና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስም አምልቶ: አስፍቶ ተናግሯል:: ፻፶ ምዕራፎች ባሉት መጽሐፈ ትንቢቱ ኃላፍያትንና መጻዕያትን ተመልክቷል::

†   ስለዚህም አበው :-

"አልቦ ምስጢር ወአልቦ ትንቢት:
ዘኢተናገረ አቡነ ዳዊት" ይላሉ::

†   🌷   መዝሙር    🌷    †

ቅዱሱ ነቢይና ንጉሥ በጣም የሚታወቀው በዝማሬው ነው:: ለራሱ ባለ ፲ አውታር : ለመዘምራኑ ደግሞ ባለ ፰ አውታር በገናን አዘጋጅቶ ፈጣሪውን ያመሰግን ነበር:: ፳፬ ሰዓት ሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዳይቁዋረጥ ፪፻፹፰ መዘምራንን በአሳፍ መሪነት መድቦ ነበር::

- ራሱም በፍጹም ተመስጦ: ማር ማር እያለው እግዚአብሔርን ያመሰግነው ነበር:: "ቃልህ ለጉረሮየ ጣፋጭ ነው" እንዲል:: [መዝ.፻፲፰፥፻፫]  የዳዊት መዝሙሩ ለአጋንንት ትልቅ ጠላት ነው:: ቅዱሳን መላእክትም በዳዊት መዝሙር ይዘምራሉ::

"በዘቦቱ ይሴብሑ ሰማያውያን ወምድራውያን" እንዲል::

†   🌷   ዳዊትና ጽዮን   🌷    †

ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን አንጾ ጽላተ ኪዳኑን አመጣ:: ለአምላከ ያዕቆብ ማደሪያን ሊፈልግም ዐይኑ ከእንቅልፍ ተከለከለ:: [መዝ.፻፴፩፥፪] የፈጣሪውን ፈቃድ ሊጠይቅ ሱባኤ ቢገባ "አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ - አንተ ሳትሆን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው" አለው::

- አያይዞም የምሥጢረ ሥጋዌን ነገር ቢገልጥለት "ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ - እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ሲል ተናግሯል:: [መዝ.፻፴፩፥፮] የኪዳኑ ጽላት [ጽዮን] ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ከዙፋኑ ወርዶ: ከተራው ሕዝብ ጋርም ተቀላቅሎ በበገናና በመሰንቆ ተጫወተ::

- ስለ ፈጣሪው ክብሩን ተወ:: ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የሚገዛ ኃያል ንጉሥ ነበርና:: በጽዮን ፊት እየወደቀ: እየተነሳ: እየታጠቀ: እየፈታ ሲዘምርም ሚስቱ ሜልኮል ናቀችው:: እግዚአብሔር ግን ከፍ ከፍ አደረገው:: [ሳሙ.፮፥፲፮]

†    🌷  ክብረ ዳዊት   🌷    †

Debtera Media

31 Dec, 23:20


- እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ኢየሩሳሌምን ብዙ ጊዜ ታድጉዋል:: ሰሎሞንና ሕዝቅያስን [ነገሥታቱን] ይቅር ያላቸው ስለ ባለሟሉ ስለ ዳዊት ነው::

- የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ . . . " የምትል ናት:: [ማቴ.፩፥፩] ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና:: እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ" ሲል ተናግሯል:: [ራዕ.፳፪፥፲፮]

†  🌷   ዕረፍት    🌷   †

- ነቢየ ጽድቅ: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ፵ ዓመታት መርቶ አረጀ:: 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና::

- በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ አሥራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና [ዜና.፳፩፥፲፮] ሰውነቱ ደከመ:: በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ፸ ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት በዚህች ቀን ዐርፏል::

†   🌷  ዳዊት በሰማይ   🌷   †

በራዕየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል:: ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል:: በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው::

- በነገረ ማርያም ትምሕርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው::
- እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ:: ክብሩ ታላቅ ነውና::

" በእውነት . . . በእውነት . . . በእውነት . . . ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል "

አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን:: በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን::

🕊

[  †  ታሕሳስ ፳፫ [ 23 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
፪. አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
፫. አባ ሳሙኤል ጻድቅ
፬. አባ ስምዖን ጻድቅ
፭. አባ ገብርኤል ጻድቅ
፮. አባ ይስሐቅ ጻድቅ

[   †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
፪. ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን [ንጉሠ እሥራኤል]
፫. ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ

" ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ:: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት:: ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት:: እጄም ትረዳዋለች:: ክንዴም ታጸናዋለች:: ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም:: የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም:: ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ:: የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ::"  [መዝ.፹፰፥፳]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

31 Dec, 17:33


                        †                        

🕊        ል  በ    አ ም ላ ክ      🕊
                   

❝ እኔም ፥ ስለ ባሪያዬም ስለ ዳዊት ይህችን ከተማ አድናት ዘንድ እጋርዳታለሁ። ❞ [ ፪ነገሥ.፲፱ ፥ ፴፬ ]

💖                     🕊                     💖

[ የዋህ ሞገስን የተመላ ንጉሥና ነቢይ ለሚኾን ለቅዱስ ዳዊት ሰላምታ ይገባል ፤ መልካም ነገርን ለሚናገር አንደበቱ ፤ መዐዛ ያለው ምስጋናንና የታዘዘ መዝሙርን ለሚያነብቡ ከንፈሮቹ ሰላምታ ይገባል ፤ ዐጥንትን የሚያለመልም ፤ ድንቅ ጥፍጥ [ ደስ የሚያሰኝ ] ማሕሌትን በዜማ መንፈስ ለሚደረድሩ ለእጁ ጣቶች ሰላምታ ይገባል። ]

[ ተአምኖ  ቅዱሳን ]

🌹🍃 ቅዱስ ዳዊት ከእግዚአብሔር ሰባት ሀብታት ተሰጥቶታል

፩. ሀብተ_መንግሥት 
፪. ሀብተ_ክህነት 
፫. ሀብተ_ኃይል
፬. ሀብተ_በገና 
፭. ሀብተ_ፈውስ 
፮. ሀብተ_ትንቢት
፯. ሀብተ_መዊዕ ናቸው።

💖                     🕊                     💖

እንኩዋን ለጻድቅ : የዋሕና ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል ፤ እንዲሁም ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሐዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

27 Dec, 16:27


                          †                                     

[   † ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል   ]

🕊

" ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። " [ ዳን.፱፥፳፩ ]

" ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" [ዘፍ.፵፰፥፲፮]

💖                    🕊                      💖

† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል :-

- ከ፯ [ 7 ] ቱ ሊቃናት አንዱ::
- በራማ አርባብ በሚባሉ ፲ [10] ነገደ መላእክት ላይ የተሾመ::
- በመጀመሪያዋ የፍጥረት ቀን መላእክትን ያጸና::
- ቅዱሳንን ሁሉ የሚረዳ::
- ሠለስቱ ደቂቅን : ዳንኤልን : ሶስናን ከሞት የታደገ ታላቅ መልዐክ ነው::

ከምንም በላይ ግን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሱን መልዐክ "መጋቤ-ሐዲስ" ብላ ታከብረዋለች:: ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጉዋሜ "አምላክ ወሰብእ - እግዚእ ወገብር" ነውና ለሥነ ፍጥረት ሁሉ የሚሆን ሐዲስ ዜናን ወደ እመቤታችን ድንግል ማርያም አምጥቷል::

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅን ያዳነበት ነው፡፡

                          †                           

[     የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት    ]

       
🕊  በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ  🕊
             
" የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ፥ ያድናቸውማል። " [መዝ.፴፬፥፯]

🕊

"ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ" [ዘፍ.፵፰፥፲፮]

† ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በክንፈ ረድኤቱ ከክፉ ሁሉ ይጠብቀን::


†                        †                         †
💖                    🕊                      💖

Debtera Media

27 Dec, 15:02


                       †                       

[   🕊   † †   ዋዜማ   † †   🕊   ]


💖 የራማው ልዑል ቅዱስ ገብርኤል 💖

[  † እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

💖                    🕊                     💖

[ የአቡነ አብርሃም ደቀ መዝሙር በመንበረ መንግስት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ የተቀኙት ቅኔ ]


ገብርኤል አረጋዊ ይትዐጸፍ ምንተ ?
አመ ወርኃ ጥምቀት አልጸቀ
እስመ ነድ ልብሱ በሕጽበት ኀልቀ
ኅልቀተ ልብሱሰ ነድ ኢያስተኃዝኖ ጥዩቀ
አምጣነ እግዝእቱ ድንግል ትፈትል ወርቀ
ወእግዚኡ ያለብስ መብረቀ

ትርጉም  ፦

[ አረጋዊው ገብርኤል የጥምቀት ወር በደረሰ ጊዜ ምን ይለብስ ይሆን
እሳት የሆነ ልብሱ በመታጠብ አልቋልና
የልብሱ ማለቅ ግን ፈጽሞ አያሳዝነውም
ድንግል እመቤቱ ወርቅን ትፈትላለችና
ጌታውም መብረቅን የሚያለብስ ነውና ]

ምስጢር  ፦

[ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ታህሳስ ፲፱ ሠለስቱ ደቂቅን ከነደደው እሳት ሊያድናቸው ከአምላኩ ተልኮ ወደ እቶኑ ሲገባ "ለሠለስቱ ደቂቅ ዘአውረድከ ጠለ" ይለዋል እሳቱ ውኃ ሆነላቸው እርሱም በዚያ አብሯቸው ታይቷል ነገር ግን "ገብርኤል ነደ ወነበልባለ" እንዲለው እሳታዊ ልብሱ በውሃ ቢታጠብ አልቋልና [እሳት ውሃ ቢነካው እንዲጠፋ] ..... ይህስ የልብሱ ማለቅ "ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ...." ይባላልና ..... ምን ለብሼ እታያለሁ ብሎ አይጨንቀውም ከጥምቀቱ አስቀድሞ ታህሳስ ፳፪ ጽንሰት[ብሥራት] ይታሰባልና "ተፈስሒ" ብሎ ያበሰራት እመቤቱ ድንግል በእሳት ቢፈተን የሚነጥረውን ወርቅ ፈትላ ታለብሰዋለች

"አስተርአያ ገብርኤል ግብተ ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ" ይላል ..... ጌታውም ቢሆን "እለ ይትለአክዎ መባርቅት ወየአውድዎ ነጎድጓድ" የተባለለት መብረቅን ያለብሰዋል....መልአኩን "ልብሱ ዘመብረቅ" ይለዋልና ለተልእኮ እንደመብረቅ የሚፋጠን ስለሆነ አንድም ዜና ብስራቱ እንደመብረቅ ስለሚሰማ ..... ለዚያ ነው በዚህ ክብር ተገልጾ በትንሳኤው ያየነው፡፡

"እነሆም ፥ የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለ ወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ ፤ ቀርቦም ድንጋዩን አንከባሎ በላዩ ተቀመጠ። መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ።" [ማቴ. ፳፰፥፪ ]

† † መልካም በዓል ይሁንላችሁ † †

[  ዲ/ን ዶ/ር ቴዎድሮስ በለጠ ]

💖

[ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጥበቃው አይለየን። ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

27 Dec, 12:43


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

[               ክፍል  ስድሳ ሦስት               ]

                         🕊  

[ እግዚአብሔር ለተነሳሒ የሚሰጠው ጸጋ ! ]

🕊

❝  ታላቁ አባ መቃርዮስ እንዲህ አለ ፦ “አንድ ሰው እግዚአብሔርን ለማወቅና ለመፈለግ ቢጀምርና ባለማወቁ ዘመን ስላደረጋቸው ነገሮች ንስሐ ቢገባ እግዚአብሔር ስላደረጋቸው ነገሮች የሚያዝንና የሚጸጸት ልብ ይሰጠዋል፡፡

ወደ ኋላም በቸርነቱና በርኅራሄው እግዚአብሔር ከሥጋ ዘመዶቹ የበለጠ በጸሎታትና በአጽዋማት ፣ በብዙ ትጋህ ፣ ቁሳዊ ነገርን በመካድና በመናቅ ፣ ራስን በመካድና በማቃለል ፣ ሥጋዊ ዕረፍትን በመጥላትና አንብዕን በመውደድ ጸጋ ይጎበኘዋል፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

27 Dec, 09:56


                         †                                    

[  † የታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤል ሥርዓተ ማኅሌት   ]

🕊


ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፲ወ፱ ለታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤል

🟢             🟡            🔴

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

27 Dec, 06:44


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

       [    መለኮት በሥጋ ሞተ !    ]

🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❝ [ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ] እንዴት ታመመ ? ነገር ግን ምሥጢሩን ከላከው ከአባቱ ፤ ከመንፈስ ቅዱስም ጋር እርሱ ብቻ ያውቃል ፥ ይህንን ነገር መርምሮ ወደማወቅ ይደርስ ዘንድ ይረዳውም ዘንድ የሚቻለው ልቡና የለም። አባ አመኀፅን ነፍስየ ብሎ ነፍሱን ከሥጋው ለየ በዓለመ ሥጋ በዓለመ ነፍስ ያሉትን ያድን ዘንድ።

የሞትን ሥልጣን የሚያጠፋ መለኮት በሥጋ ሞተ ፥ ሞትም የተባለ ዲያብሎስ ነው ፥ እንደ ተጻፈ ምሥጢሩን ማንም ማን የሚያውቀው ሳይኖር ያድነን ዘንድ ያደረገውን እርሱ ያውቃል። [ ዕብ.፪፥፲፬ ። ቈላ.፩፥፳ ]

በአባቱ ጌትነት ተነሣ ፣ በሲዖል ተግዘው የነበሩ የቅዱሳንን ነፍሳት አዳነ ፥ ንጉሥ ድል የማይነሣ ገዥም ነውና በፍጹም ክብር ጌትነት ወደ ሰማይ ዐረገ ፥ በማይመረመር በማይታወቅ ምሥጢር ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በነሣው በከበረው ሥጋው ከአብ ጋር በዕሪና ተቀመጠ። [ ሮሜ.፮፥፬ ። ፩ጴጥ.፫፥፲፱-፳፪ ። ፩ጢሞ.፮፥፲፭ ና ፲፮ ] ❞

[    ቅዱስ ጎርጎርዮስ  ዘእንዚናዙ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                         †                         †
💖                      🕊                      💖

Debtera Media

27 Dec, 03:01


- ፍሬምናጦስ ምንም የመጡበት ዓላማ ስብከተ ወንጌል ባይሆንም በአክሱም ቤተ መንግስት አካባቢ ይሰብኩ ነበር:: ያን ጊዜ በጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ የተቀጣጠለው የክርስትና ችቦ ውስጥ ውስጡን በሃገሪቱ ነበረና ፍሬምናጦስ አልተቸገሩም:: በተለይ ኢዛናና ሳይዛናን ከልጅነት ስላስተማሯቸው ነገሮች የተሳኩ ሆኑ::+ንጉሥ ታዜር እንደ ሞተ2ቱ ሕጻናት በመንበሩ ተቀመጡ:: ፍሬምናጦስንም ወደ ግብፅ ዻዻስና ጥምቀት ከመጻሕፍት ጋር እንዲያመጣላቸው ላኩ:: ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "ሰላማ" ብሎ ሰይሞ: በዽዽስና: በንዋየ ቅድሳትና በመጻሕፍት ሸልሞ መለሳቸው::

- አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ እንደተመለሱ ከነገሥታቱ ጀምረው ለሕዝቡ ጥምቀትን አደሉ:: ኢዛናና ሳይዛናም አብርሃ እና አጽብሃ ተብለው ስማቸው ተደነገለ:: ከዚያ በሁዋላ ድንቅ በሚሆን አገልግሎት ነገሥታቱ: ዻዻሱ ሰላማና ሊቀ ካህናቱ እንበረም ለክርስትና መስፋፋት በጋራ ሠርተዋል::

የአቡነ ሰላማ ትሩፋቶች :-

፩. ዽዽስናና ክህነትን ከእውነተኛ ምንጭ አምተዋል::
፪. ክርስትናና ጥምቀትን በሃገራችን አስፋፍተዋል::
፫. ቅዱሳት መጻሕፍትን ከውጭ ልሳኖች ተርጉመዋል::

፬. ገዳማዊ ሕይወትን ጀምረዋል::
፭. አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
፮. ግዕዝ ቁዋንቁዋን አሻሽለዋል::

ሀ. ከግራ ወደ ቀኝ እንዲፃፍ
ለ. እርባታ እንዲኖረው
ሐ. ከ"አበገደ" ወደ "ሀለሐመ" ቀይረዋል::

- ባላቸው ንጹሕ የቅድስና ሕይወት ለሕዝቡ ምሳሌ ሆነዋ:: "ወበእንተዝ ተሰይመ ከሳቴ ብርሃን" እንዲል በነዚህ ምክንያቶች "ከሣቴ ብርሃን" [ብርሃንን የገለጠ] ሲባሉ ይኖራሉ:: በመጨረሻም ከመልካሙ ገድል በሁዋላ በ፫፻፶፪ ዓ/ም ዐርፈው ተቀብረዋል:: ቅዱሱ ለሃገራችን ዻዻስ ሆነው የተሾሙት በዚህች ዕለት ነው::

አምላከ አበው ቅዱሳን በመጽናታቸው ያጽናን:: ከበረከታቸውም ያድለንና።

🕊

[  †  ታሕሳስ ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ [ፍልሠቱ]
፪. ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ [ፍልሠቱ]
፫. አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
፬. ቅዱስ ፊልሞና ባሕታዊ
፭. ቅዱስ ኢርቅላ

[    † ወርሐዊ በዓላት     ]

፩. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
፪. አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ
፫. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ]
፭. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ]

" የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ዻውሎስ . . . መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ: ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ: በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ለሚሆን ልጄ ቲቶ:: ከእግዚአብሔርም አብ: ከመድኃኒታችንም ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት: ሰላምም ይሁን:: " [ቲቶ.፩፥፩]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

27 Dec, 03:01


🕊

[  † እንኩዋን ለቅዱሳን "ሐዋርያት ቶማስ ወቲቶ" እና "አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ †  ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።  †

---------------------------------------------

🕊 †  ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ † 🕊

ከ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ ብዙ መከራን በማሳለፉና የጌታችንን ጐን በመዳሰሱ ይታወቃል::

- ቅዱስ ቶማስ እንደ ሌሎቹ ሐዋርያት በእሥራኤል ተወልዶ በዚያውም በሥርዓተ ኦሪት አድጐ ገና በወጣትነቱ የሰዱቃውያንን ማሕበር ተቀላቅሏል:: ሰዱቃውያን ሰው ከሞተ በሁዋላ አይነሳም [አልቦ ትንሳኤ ሙታን] የሚሉ ናቸው:: መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ሲጀምር ግን ቅዱስ ቶማስ ከነበረበት ማሕበር ወጥቶ ጌታችንን ተከተለ:: ጌታችንም ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ ይሆን ዘንድ ሾመው:: የቀደመ ስሙ "ዲዲሞስ" ሲሆን ጌታችን "ቶማስ" ብሎታል::

- ቅዱስ ቶማስ ጌታ አልዓዛርን ለማስነሳት በሔደ ጊዜ ሌሎች ሐዋርያት ጌታን "አይሁድ ይገድሉሃል ቅር" ሲሉት እርሱ ግን "እንሒድና አብረን እንሙት" ሲል ፍቅሩን አሳይቷል:: [ዮሐ.፲፩፥፲፮]

- ጌታችን ትንሳኤውን ለደቀ መዛሙርቱ በገለጠ ጊዜ ያልነበረው ቶማስ ካላየሁ አላምንም አለ:: ምክንያቱም :-

፩. ለጌታችን ከነበረው ፍቅር የተነሳ እውነት አልመስልህ ቢለው::

፪. አንድም "ሌሎቹ ሐዋርያት ትንሳኤውን አየን እያሉ ሲያስተምሩ እኔ ግን ሰማሁ ብየ ማስተማሬ ነው" ብሎ በማሰቡ ነበር::

- ለጊዜው ጌታ ተገልጾ ቢገስጸው "እግዚእየ ወአምላኪየ [ጌታየና አምላኬ]" ብሎ ፍጹም ሃይማኖቱን ገልጿል:: ለፍጻሜው ግን የጌታችንን ጎን [መለኮትን] ይዳስስ ዘንድ ባለቤቱ እንዳደለው ያጠይቃል:: መለኮትን የዳሰሰች ይሕቺ ቅድስት እጁ ዛሬም ድረስ ሕያው ናት::

- ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ተቀብለው ሐገረ ስብከት ሲከፋፈሉ ለቅዱስ ቶማስ ሕንድና በዙሪያዋ ያሉ ሃገራት ደረሱት::

- ከዚህ በሁዋላ ነው እንግዲህ ዘርዝረን የማንጨርሰውን ተጋድሎ የፈጸመው:: ቅዱሱ በነበረው ፍጹም ትጋት አባቶቻችን "ዘአሠርገዋ ለብሔረ ሕንደኬ [ሕንድን በወንጌል ያስጌጣት]" ሲሉ ያከብሩታል::

- ቅዱስ ቶማስ ንጉሥ ሉክዮስንና የሃገሩን ሕዝብ ለማሳመን በችንካር መሬት ላይ ወጥረው ቆዳውን ገፈውታል:: ቆዳውንም እንደ ገና ሰፍተው: አሸዋ ሞልተው አሸክመውታል:: በየመንገዱ የተገፈፈ ገላውን ጨው ቢቀቡት በጎች መጥተው ግጠው በልተውታል:: በዚሕ ምክንያት :-

"ኩሉ የአኪ እንዘ የአኪ ዘመኑ::
አባግዒሁ ለቶማስ እስመ አራዊተ ኮኑ::" ብለዋል ሊቃውንቱ::

- በሁዋላ ግን ከፎቅ ወድቃ የሞተችውን የንጉሡን ሚስት በተገፈፈ ቆዳው በማዳኑ ሁሉም አምነው ተጠምቀዋል::

- ቅዱሱ ሐዋርያ ልክ እንደ ቅዱስ ዻውሎስ አንዳንዴ በፈሊጥ: ሌላ ጊዜም በመከራ ለወንጌልና ለቤተ ክርስቲያን ተጋድሏል:: ያለ ማቁዋረጥም ከሕንድ እስከ ሃገራችን ኢትዮዽያ ድረስ ለ፴፰ ዓመታት ወንጌልን ሰብኩዋል:: በመጨረሻም በ፸፪ ዓ/ም በሰማዕትነት አርፏል:: መቃብሩና ቅድስት እጁ ዛሬ ድረስ ሕንድ ውስጥ አሉ:: ከኘሮቴስታንቶች በቀር መላው ዓለም ያከብረዋል:: ዛሬ የቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ነው::


🕊  †   ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ  †   🕊

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ቲቶ ከ፸፪ቱ አርድእት አንዱ ሲሆን በተወሰነ መንገድም ቢሆን የተዘነጋ ሐዋርያ አይደለም:: በተለይ ደግሞ ቅዱስ ዻውሎስ ከጻፋቸው ፲፬ መልእክታት መካከል አንዷ የተላከችው ለዚህ ቅዱስ በመሆኗ ታሪኩ እንኩዋ ባይነገር ስሙ አይረሳም:: ቅዱስ ዻውሎስም በመልዕእክታቱ በጐ ስሙን እየደጋገመ ያነሳዋል::

ለመሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ ማን ነው?

- ቅዱስ ቲቶ የተወለደው በ፩ኛው መቶ ክ/ዘ እስያ ውስጥ ቀርጤስ በምትባል ከተማ ነው::

- መዳን በእውቀት ይመስላቸው ስለ ነበር የአካባቢው ሰዎች የግሪክን ፍልስፍና ጠንክረው ይማሩ ነበር:: ቅዱስ ቲቶም በወጣትነቱ ወደ ት/ቤት ገብቶ የግሪክን ፍልሥፍናና የዮናናውያንን ጥበበ ሥጋ ተማረ:: በጥቂት ጊዜም የሁሉ የበላይ ሆነ::

- ቅዱሱ ምክንያቱን ሳያውቀው ለእኔ ቢጤዎች ያበላ: ያጠጣ: ይንከባከባቸውም ነበር:: እግዚአብሔር ግን የዚህ ቅን ሰው በጐነቱ እንዲሁ እንዲቀር አልወደደምና አንድ ቀን በራዕይ ተገለጠለት::

- በራዕይም አንድ ምንነቱን ያልተረዳው ነገር "ቲቶ ሆይ! ስለ ነፍስህ ድኅነት ተጋደል:: ይህ ዓለም ኃላፊ ነው" ሲለው ሰማ:: ከእንቅልፉ ነቅቶ በእጅጉ ደነገጠ:: የሚያደርገውንም አጣ:: ያናገራቸው ሁሉ ምንም ሊገባቸው አልቻለም::

- ድንገት ግን በዚያ ሰሞን ከወደ ኢየሩሳሌም አዲስ ዜና ተሰማ:: "ክርስቶስ የሚሉት ኢየሱስ: እርሱም የባሕርይ አምላክ የሆነ ወደ ምድር ወርዶ: ስለ እግዚአብሔር መንግስትም እየሰበከ ነው" ሲሉ ለቲቶ ነገሩት::

- "ሌላስ ምን አያችሁ?" አላቸው:: "በእጆቹ ድውያን ይፈወሳሉ: ሙታን ይነሳሉ: እውራን ያያሉ: ለምጻሞች ይነጻሉ: ሌሎች ብዙ ተአምራትም እየተደረጉ ነው" አሉት:: የወቅቱ የሃገረ አክራጥስ መኮንን ፈላስፋ ነበርና ስለ ክርስቶስ ሲሰማ ሊመራመር ወደደ::

- "ብልህ ጥበበኛ ሰው ፈልጉልኝ" ብሎ ተከታዮችን ቢልካቸው ከቲቶ የተሻለ በአካባቢው አልነበረምና እርሱኑ አመጡት:: መኮንኑ ቲቶን "ነገሩ ትክክል ወይም ስሕተት መሆኑን በጥልቅ መርምረህ ምላሽ አምጣልኝ" ብሎ ላከው::

- ቅዱስ ቲቶም ፈጥኖ ተነስቶ ወደ ኢየሩሳሌም ገሰገሰ:: ወደ ከተማዋ እንደገባም ጌታችንን አፈላልጐ አገኘው::

፩. ጌታችን ክርስቶስ በሥልጣነ ቃሉ ደዌያትን ሲያርቅ: አጋንንትን ሲያሳድዳቸው ተመልክቶ ይህ ሥራ የፍጡር እንዳልሆነ ተረዳ::

፪. ጌታችን የሚያስተምረው ትምሕርት ከግሪክ ፍልሥፍና እጅግ ርቆና መጥቆ አገኘው:: ጌታ በጣዕመ ቃሉ የሚያስተምረው ሰማያዊ: በዚያ ላይ ዘለዓለማዊ የሆነ ትምሕርት ነው:: በራዕይ "ስለ ነፍስህ ተጋደል" ያለው ምሥጢር አሁን ተተረጐመለት::

- በዚህ ምክንያትም ጊዜ አላጠፋም:: ወዲያውኑ አምኖ ተከታዩ ሆነ:: ጌታም ከ፸፪ቱ አርድእት ደመረው:: የአክራጥስ መኮንን "ምነው ዘገየህ?" ቢለው ያየውን ሁሉ ጽፎ: እንደማይመለስም አክሎ ደብዳቤ ላከለት::

- ከዚህ በሁዋላ ቅዱስ ቲቶ ከጌታችን እግር ለ፫ ዓመታት ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ: በመላው እስያ ወንጌልን ሰብኩዋል:: ቅዱስ ዻውሎስ ባመነ ጊዜ ደግሞ የእርሱ ደቀ መዝሙር ሆኖ ለ፳፭ ዓመታት አስተምሯል::

- ቅዱስ ዻውሎስ ሰማዕት ከሆነ በሁዋላ ደግሞ ወደ አክራጥስ ተመልሶ: ሕዝቡን አሳምኖና አጥምቆ: ቤተ ክርስቲያንን አንጿል:: ዕድሜው በደረሰ ጊዜም መምሕራንን: ካህናትን ሹሞላቸው: ባርኩዋቸውም ዐርፏል:: ዛሬ የቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ነው::


🕊 † አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን  †  🕊

ቅዱሱ በትውልዳቸው ግሪካዊ ቢሆኑም ሶርያ አካባቢ እንዳደጉ ይታመናል:: በቀደመ ስማቸው ፍሬምናጦስ የሚባሉት አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአደጋ ምክንያት ቢመስልም ውስጡ ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበት::

- በድንበር ጠባቂዎች ከባልንጀራቸው ኤዴስዮስ ጋር ተይዘው ወደ አክሱም የመጡት በንጉሥ ታዜር [አይዛና] እና በሚስቱ ሶፍያ [አሕየዋ] ዘመን ነው:: ጊዜው በውል ባይታወቅም በ፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::

Debtera Media

26 Dec, 18:47


                         †                                    

[  † የታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤል ሥርዓተ ማኅሌት   ]

🕊


ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፲ወ፱ ለታኅሣሥ ቅዱስ ገብርኤል

🟢             🟡            🔴

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

24 Dec, 21:35


🕊

[  ✞ እንኩዋን ለኃያል "መሥፍነ እሥራኤል ቅዱስ ጌዴዎን" እና "ማርያም እህተ ሙሴ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ]

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።  †

---------------------------------------------

🕊   †  ኃያል ጌዴዎን   †   🕊

- እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን: ፳፪ [22] ቱን ሥነ ፍጥረትን ፈጥሮ አዳምን ገዢ አደረገው:: አክሎም በነፍስ ሕያው አድርጐ: በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ: ነቢይና ካህን አድርጐ: ካንዲት ዕፀ በለስ በቀር በፍጥረት ሁሉ ላይ አሰለጠነው::

- አባታችን አዳም ግን ስሕተት አግኝቶት ከገነት ወጣ:: መከራና ፍዳም አገኘው:: በሁዋላም ለ፻ [100] ዓመት አልቅሶ ንስሃ ገባ:: ጌታም ንስሃውን ተቀብሎ "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ተስፋ ድህነትን ሰጠው::

- ስለዚህም ምክንያት ለ፭ ሺህ ፭ መቶ [5500] ዓመታት ትንቢት ሲነገር: ሱባኤ ወደ ታች ሲቆጠር: ምሳሌም ሲመሰል ኖረ:: ከደግ ፍጥረት አዳም እስከ ኖኅ ድረስ: የሴት ልጆች እግዚአብሔርን በንጽሕና ሁነው በደብር ቅዱስ አመለኩ::

- ትንሽ ቆይተው ግን ስለተቀላቀሉ ከቃየን ልጆች ጋር በማየ ድምሳሴ ጠፉ:: በጻድቅ ሰው ኖኅ የተጀመረው ትውልድም እግዚአብሔርን ለመዘንጋት ጊዜ አልፈጀበትም:: ነገር ግን ከሴም ዘር ቅንና ጻድቅ ሰው አብርሃም ተገኘ::

- ከእርሱም ይስሐቅ: ከዚያም ያዕቆብ [ደጋጉ] ተገኙ:: ያዕቆብም "እሥራኤል" ተብሎ: በልጆቹ "ሕዝበ እግዚአብሔር" የተባለ ነገድ ተመሠረተ:: በተስፋይቱ ምድር በከነዓን እንዳይኖሩም ረሃብ ምድረ ግብጽ አወረዳቸው::

- በዚያም ለ፪ መቶ ፲፭  [2015] ዓመታት በጭንቅ የባርነትን ሕይወትን አሳለፉ:: እግዚአብሔርም ስለ ወዳጁ አብርሃም ሲል እሥራኤልን አሰባቸው:: የዋሕና ጻድቅ ሰው ሙሴን አስነስቶ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አዳናቸው::

- ይኸውም በጸናች እጅ: በበረታችም ክንድ: በ፱ መቅሰፍት: በ፲ኛ ሞተ በኩር: በ፲፩ኛ ስጥመት ግብጻውያንን አጥፍቶ ነው:: በየመንገዱም ጠላቶቻቸውን እየተበቀለላቸው ነው:: ከዚህ ዘመን ጀምሮም እሥራኤል በመሳፍንትና በካህናት የሚተዳደሩ ሆኑ::

- አስቀድሞ ሙሴ በምስፍና: አሮን በክህነት መሯቸው:: ቀጥሎም በቅዱስ ሙሴ ኢያሱ: በአሮን አልዓዛር ተተኩ:: እንዲህ እንዲህ እያለም ከኃያል ሰው ጌዴዎን ደረሱ:: ይኸውም ከዓለም ፍጥረት ፬ ሺህ ፩ መቶ ፶፩ [4151] ዓመታት በሁዋላ መሆኑ ነው::

- በጊዜው እሥራኤል ጣዖትን እያመለኩ እግዚአብሕርን ስላሳዘኑት ለጠላቶቻቸው አሳልፎ ይሰጣቸው ነበር:: የአካባቢው መንግስታት እነ አሞን: አማሌቅ: ኢሎፍሊ ስንኩዋ ያኔ ዛሬም ቢሆን እንደምትመለከቱት ዶሮና ጥሬ ናቸው::

- ከክርስቶስ ልደት ፩ ሺህ ፫ መቶ ፵፱ [1349] ዓመታት በፊትም በእሥራኤል ላይ ምድያማውያን [ይህቺ ሃገር የኢትዮዽያ ግዛት ነበረች ይባላል] በጠላትነት ተነስተውባቸው ተጨነቁ::

- አምላካችን እግዚአብሔርም ሊያድናቸው ወዶ መልአኩን ወደ ጌዴዎን ላከው:: ቅዱስ መልአክም ወደ እርሱ ቀርቦ "ኃያል የእግአብሔር ሰው" ሲል ጠራው:: ጌዴዎን ግን "ባሮች ስንሆን ምን ኃይል አለን!" ሲል መለሰለት::

- መልአኩም "እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነውና ሒድ! እሥራኤልን ከምድያም እጅ አድናቸው" አለው:: ጌዴዎን ምልልሱን ቀጠለ:: "እግዚአብሔር ከእኔ ጋር መሆኑን በምን አውቃለሁ?" ሲል ጠየቀው::

- ጌዴዎን ይህንን ያለው ፈጣሪውን ተጠራጥሮት አይደለም:: ይልቁኑ ጥበበ እግዚአብሔር ይገለጥ ዘንድና በሁዋለኛው ዘመን የሚፈጸመውን ምሥጢረ ሥጋዌ ሊያስረዳ እንጂ::

- መልአኩም መስፍኑ የሰዋውን መስዋዕት አሳረገለት:: ቀጥሎም ጌዴዎን "ጸምር [ብዝት ጨርቅ] ልዘርጋ:: ጠል [ዝናብ] በጸምሩ ላይ ይውረድ:: ዳር ዳሩ ግን ይቡስ [ደረቅ] ይሁን" አለ:: በጠዋትም እንዳለው ሆኖ አገኘው::

- በጸምሩ ላይ የወረደውን ጠል ጨምቆ በመንቀል ሞልቶ ቢጠጣው ሰማያዊ ኃይል ወረደለት:: ጥያቄውን አሁንም ቀጠለ:: "ጌታ ሆይ! እንደ ገናም ነገሩ ይቀየርልኝ:: ጠል በጸምሩ ላይ አይውረድ:: ዳር ዳሩ ግን ይውረድበት" አለ::

- እንዳለውም ሆነ:: ይህ ሁሉ ምሳሌ ነው:: ለጊዜው ጸምር የእሥራኤል: ጠል የረድኤት: ምድር የአህዛብ ምሳሌ ነው:: ጠል በጸምር እንጂ በምድር ላይ እንዳልወረደ ረድኤተ እግዚአብሔር ለእሥራኤል እንጂ ለአሕዛብ ያለ መደረጉ ምሳሌ ነው::

- አንድም ምሳሌውን ይለውጧል:: ጠል የሚለውን ብቻ እንቀይረውና ጠል የመቅሰፍት ምሳሌ: በ፪ኛው ጠል በምድር ላይ እንጂ በጸምር ላይ እንዳልወረደ: መቅሰፍቱም እሥራኤልን ትቶ በአሕዛብ ላይ ወርዷልና:: [ይህ ጊዜአዊ ምሥጢሩ ነው::]

- አማናዊ ምሥጢሩ ግን ወደ ሐዲስ ኪዳን ያመጣናል:: ጸምር የእመቤታችን: ጠል የጌታ ምሳሌ:: ጠል በጸምር እንጂ በምድር ላይ አለመውረዱ ጌታ ከድንግል ማርያም ብቻ መወለዱን ያሳያል::

- በ፪ኛው ምሳሌ ደግሞ ጠል የፍዳ: የመርገም ምሳሌ ይሆናል:: ጠል በምድር ላይ እንጂ በጸምር ላይ አለመውረዱ ድንግል ማርያም ፍዳ መርገም የሌለባት ንጽሕት መሆኗን ያሳያል::

- ይህ ሁሉ የተደረገለት ጌዴዎንም በወገኖቹ መካከል አዋጅ አስነግሮ ፴፪ [32] ሺ ሠራዊትን ሰበሰበ:: ግን እግዚአብሔር የእሥራኤላውያንን ክፋት [ማለትም በራሳችን ኃይል አሸነፍን] እንደሚሉ ያውቃልና "የፈራ ይመለስ በል" አለው::

- ፳፪ ሺ [22,000] ሠራዊት ፈርቶ ተመለሰ:: ምክንያቱም የምድያም ሠራዊት ከ፻ [100,000]  ሺ በላይ ነበርና:: አሁንም "፲ ሺው [10,000] ብዙ ነው:: ወደ ወንዝ አውርደህ ለያቸው" አለው:: ጌዴዎንም ወደ ወንዝ አውርዶ "ውሃ ጠጡ" አላቸው::

- ከ፲ ሺው ፫ [10,300] መቶው በእጃቸው እየጠለፉ ሲጠጡ ፱ ሺህ ፯ መቶ [9,700] ያህል ሰራዊት ግን ተጐንብሰው በአፋቸው ጠጡ:: በዚህም "ሌሎቹን [የተጐነበሱትን] አስመልሰህ በ፫ መቶው [300] ው ተዋጋ" ተባለ::

- እርሱም ፫ መቶ [300] ውን ተከታዮቹን ይዞ: መለከትና መብራት በሸክላ ይዞ በምድያም ሠራዊት አካባቢ አደረ:: በዚያች ሌሊትም ጌዴዎንና ሠራዊቱ በምድያም መካከል ገብተው እንስራቸውን ሰበሩ::

- መለከቱንም ነፉ:: እንደ አንበሳም "ኃይል ዘእግዚአብሔር: ኩዊናት ዘጌዴዎን - ኃይልን ከእግዚአብሔር: ጦርን ከጌዴዎን" እያሉ ገጠሙ::

- በድንጋጤ የተመቱት ምድያማውያንም እርስ በርሳቸው ተዋግተው በአንድ ሌሊት ብቻ መቶ ሁለት ሺህ [102,000] ሠራዊት አለቀባቸው:: ቀሪዎቹም ወገኖቻቸው አፈሩ:: እሥራኤል ግን በፈጣሪያቸው ኃይል ተፈሩ:: ጌዴዎንም ለ ፵ [40] ዓመታት እሥራኤልን አስተዳድሮ በዚህች ቀን ዐርፏል:: [መሣ.፮፥፩ - ፰፥፴፭] [6:1---8:35]


🕊  † ማርያም እህተ ሙሴ †   🕊

ይህች እናት የሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴና የሊቀ ካህናቱ ቅዱስ አሮን ትልቅ እህት ስትሆን ወላጆቿ እንበረምና ዮካብድ ይባላሉ:: እሥራኤል ከግብጽ ባርነት እንዲወጡ የእርሷን ያህል አስተዋጽኦ ያደረገች ሴት የለችም::

- ከመነሻውም ቅዱስ ሙሴን የጠበቀች: በሕግ በሥርዓት እንዲያድግ ከእናቱ ጋር ያገናኘች: ወገኖቿ ከግብጽ ሲወጡም ሴቶችን የመራች እናት ናት:: ወንድሞቿን ሙሴንና አሮንንም ታገለገላቸው ነበር:: በተለይ እግዚአብሔር ባሕረ ኤርትራን የብስ ሲያደርጋት ከበሮን አንስታ "ንሴብሖ ለእግዚአብሔር" ብላ ፈጣሪዋን አመስግናለች:: [ዘጸ.፲፭፥፳] [15:20]

Debtera Media

24 Dec, 21:35


- አንድ ጊዜም "ኢትዮዽያዊቷን ሲፓራን ለምን አገባህ" በሚል ስለ ተናገረችው እግዚአብሔር ተቆጥቶ በለምጽ መቷታል:: [ዘኁ.፲፪፥፩] [12:1] ቆይቶም በቅዱሱ ምልጃ ምሯታል:: ማርያም በመንገድ ሳሉ: ወደ ርስት ሳይደርሱ ዐርፋ ተቀብራለች:: [ዘኁ.፳፥፩] [20:1]

አምላከ ኃያላን መንፈሳዊ ኃይልን ልኮ ጠላትን ያድክምልን:: ከወዳጆቹ በረከትም ይክፈለን::

🕊

[ † ታሕሳስ ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ጌዴዎን ኃያል
፪. ማርያም እህተ ሙሴ

[   † ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም]
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ
፬. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፭. ቅዱስ አኖሬዎስ ጻድቅ
፮. አባ ዳንኤል ገዳማዊ
፯. አባ አቡናፍር ገዳማዊ

" እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . ." [ዕብ.፲፩፥፴፪]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

24 Dec, 17:15


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊       [   ምክረ ቅዱሳን   ]        🕊


▷   "  የ ኅ ሊ ና ዳ ኛ    !   "


💖  በቅዱስ ዮሐንስ-አፈወርቅ  💖 ] 

[                        🕊                        ]
-------------------------------------------------

❝ ዳሩ ግን የነገር ሁሉ መጨረሻ ቀርቦአል። እንግዲህ እንደ ባለ አእምሮ አስቡ ፥ ❞

[  ፩ጴጥ . ፬ ፥ ፯  ]


🕊                       💖                     🕊

Debtera Media

24 Dec, 15:16


                        †                         

🕊  አስደናቂው የልደት ምስጢር  🕊 

💖

[  የአዳኛችንን በሥጋ መወለድ በተመለከተ በልደቱ ውስጥ ያለው አስደናቂ እና ጥልቅ መገለጥ  ]

💖                     🕊                     💖

❝ ጌታዬ ሆይ ዝናኽ አስፈሪ በመኾኑ እኔ ብቁ ያልኾንኁ እንዲኹም ኮልታፋ ነኝ። የውዳሴኽ ቅኔ ጥልቅ ነው፡፡ አንደበቴም መናኛ ነው ፥ በምን ብልኀት ልገነዘብኽ እችላለኁ ? ፍለጋኽ በእርጋታ የሚኾን ነው ፣ አእምሮዬ ግን ችኩል ነው እናም እንዴት ብቁ እኾናለኍ ?

ክብርኽ ያበራል ፤ አእምሮዬ ግን የጨለመ ነው ፤ ስለዚኽ እንዴት አይኻለኍ ? ዝምታን ልምረጥ ይኾን ? ግን ርሱ ደግሞ ስንፍና በመኾኑ ጉዳትን ይወልጻል።

ተነሥቼ ልናገር ይኾን ? ግን ርሱም የሚያስደነግጠኝ አስፈሪ ነገር ነው፡፡ በእነዚኽ በኹለቱ መኻከል አጣብቂኝ ውስጥ ነኝ ፣ እና የትኛውን ልያዝ ? ዝም ማለትንም ፈርቻለኍ ለመናገርም ፈርቻለኍ ፤ ስለዚኽ ምን ላድርግ ? የቃሎቼን በገና ላንተ አሳልፌ እየሰጠኍ ነኝ ፣ እናም ያንተን ጣቶች ልዋሳቸው ፣ እና በዚኽ ባንተው ዜማ ድምፅም ለክብርኽ በለኆሳስ ይናገር፡፡

አእምሮዬ በመንፈስ ግፊት ኾኖ ለምስጋናኽ ቅኔን ያምጣ ፤ እኔ ላንተ ልቀኝ ያልበቃኁ ነኝና እባክኽን አንተ በኔ ውስጥ ተናገር። ቃልኽ እስትንፋስ ታሪክኽም ድምፅ ሲኾን እኔ ግን ዋሽንት ነኝ ፤ እባክኽን አንተ ተቈጣጠረው እና ያንተ የኾነውን ነገር ተጠቅመን ባንተው መንገድ ላንተ እንዘምራለን [ እንቀኛለን ]፡፡ ❞

🕊 ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ  🕊 ]

💖

ድንግል ሆይ ቅድስት ሆይ ጌታን የወለድሽ ሆይ እኛን ለማዳን ድንቅ ምሥጢር [ ተዋሕዶ ] በአንቺ ቢደረግ ንጉሥን ወልደሽልናልና ፍጥረታትን በብዙ ድንቅ መልክ የፈጠረ የርሱን የግናንነቱን ነገርም ፈጽመን መናገር አይቻለንምና ዝም እንበል ቅድስት ሆይ ለምኝልን፡፡ ❞ [ የማክሰኞ ውዳሴ ማርያም ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

24 Dec, 12:51


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

[                  ክፍል  ስድሳ                   ]

                         🕊  

     [ ጌታን በጸሎት ደጅ ስለ መጽናት ! ]

🕊

❝ ታላቁ አባ መቃርዮስ እንዲህ አለ ፡- “ጸሎት ስትጸልይ ማሰሮዎችህን በጠላቶችህ እጅ እንዳትጥላቸው ለራስህ ተጠንቀቅ፡፡ እነርሱ [ አጋንንት ] ማሰሮዎችህን ማለትም የነፍስህን ሃሳቦች መስረቅ ይፈልጋሉና። እግዚአብሔርን የምታገለግልባቸው የተከበሩ ማሰሮዎች እነዚህ ናቸው፡፡

እግዚአብሔር ሃሳብህ በዓለም ውስጥ እየተንከራተተና እዚህና እዚያ እየባከነ በከንፈርህ ብቻ እንድታከብረው አይሻምና ፤ ነፍስህና ሃሳቦቿ ሁሉ ያለ መከፋፈልና መበታተን ሆነው እርሱን ማየትን እንዲጠብቁና እንዲናፍቁ ይፈልጋልና፡፡ እርሱ የነፍስና የሥጋ ፈዋሽ የሆነ ታላቅ መድኃኒት ነውና፡፡

የነፍሳችንን ሕማም እንዲፈውሰንና ለሰው ያለውን ታላቅ ፍቅርና በዚህ ዓለም ስለ እኛ የተቀበለውን መከራ እንድንረዳ ፣ እንዲሁም እኛ የሚገባን ባንሆንም እርሱ ጌታችንና መድኃኒታችን ነውና በየዕለቱ የሚያደርግልንን መልካም ነገር ለመረዳት እንድንችል ሃሳባችንንና ልቡናችንን ብሩህ እንዲያደርግልን እንለምነው፡፡ ❞

🕊

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

24 Dec, 08:29


        †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

[ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል ! ]


" አስማተኛም ፥ መተተኛም ፥ በድግምት የሚጠነቍልም ፥ መናፍስትንም የሚጠራ ፥ ጠንቋይም ፥ ሙታን ሳቢም በአንተ ዘንድ አይገኝ። ይህንም የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው ፤ ስለዚህም ርኵሰት አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ ያሳድዳቸዋል።

አንተ ግን በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍጹም ሁን።" [ ዘዳ.፲፰፥፲፩ ]

🔔

በቤተክርስቲያን የማዕረግ ስም እንደ እንጉዳይ የፈሉ ጠንቋዮች ፣ መተተኞችና አስማተኞች የቤተክርስቲያን መከራዎች ናቸው።

እነዚህ የእግዚአብሔር ተቃዋሚዎችና የዲያብሎስ አገልጋዮች በእጃቸው የብዙ ንጹሐን እንባና ደም አለ። በነዚህ ክፉ ሠራተኞች የተነሳ ብዙ ምስኪኖች በየጸበሉና በየሆስፒታሉ ይሰቃያሉ። ብዙዎች ሕይወታቸውን ፣ ጤናቸውንና ሰላማቸውን አጥተዋል። ብዙዎችም ሃይማኖታቸውን ክደው ጠፍተዋል። በነሱ ጠንቅ ቤተክርስቲያን ትሰደባለች። ክብረ ክህነት ይደፈራል። ምዕመናን ንጹሕና እውነተኛ የነፍስ እረኞች ካህናትን እንዲጠሉና እንዲርቁ ይሆናሉ። በነዚህ ግለሰቦች የተነሳ ብዙ የዋሃን ገንዘባቸውን ይጭበረበራሉ። ይታለላሉ። ወደ ልዩ ልዩ አጋንንታዊ አሠራሮች ተስበው ይገባሉ።

ስለዚህም በዘመናችን ቤተክርስቲያን በመናፍቃን እንድትሰደብ ፤ ክብረ ክህነትም እንዲደፈር በማድረግ አባቶቻችን ካህናትን ከምዕመናን ለመለየት ሰይጣን ያዘጋጃቸውን እንዲህ ያሉ የዲያብሎስ ሠራዊቶችን ከእኛ ዘንድ እናርቅ ! እንዲህ ያሉት የክፋት ሠራተኞች ለሐሰተኛ አጥማቂያን የገበያ ምንጭ በመሆን እየተመጋገቡ እንደሚሠሩም እናስተውል !

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬

Debtera Media

23 Dec, 21:20


ደቀ መዛሙርቶቻቸውም ባሕሩ ላይ በተነጠፈው ኩታ ላይ ከበው ተቀመጡ:: ከሰማይም ጌታችን ወርዶ በመካከላቸው ቆመ:: ሚካኤል በቀኝ ገብርኤልም በግራ ቆሙ:: ጻድቁ ደግሞ ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው: ይተረጉሙላቸው ገቡ::

በመካከል ግን አንዱ [የማነ ብርሃን ይሉታል በቅኔ ቤት] በመጠራጠሩ እርሱ የተቀመጠባት ብቻ ተቀዳ ሰጠመ:: በሁዋላ ግን ጻድቁ ተመልሰው አውጥተው: ከሞት አስነስተውታል:: በዚህም ምክንያት 'ዘአደወ ባሕረ-ማዕበልን የተሻገረ' ይባላሉ::

አቡነ ኤዎስጣቴዎስ በአርማንያ ለዘመናት ሰብከው: ሕይወተ ገዳምን አስፋፍተው: ብዙ ተአምራትን ሠርተው: በተወለዱ በ፹ ዓመታቸው: በ፩ ሺህ ፫ መቶ ፵፭ [1345] ዓ/ም ዐርፈዋል:: በብዙ ዝማሬ በመቅደሰ መርምሕናም ተቀብረዋል:: በኢትዮዽያ: ኤርትራ: ግብጽና አርማንያ ይከብራሉ:: ዛሬ ጻድቁ ማዕበሉን የተሻገሩበት መታሰቢያ ቀን ነው::

አምላከ ቅዱሳን ስለ አባቶቻችን ሲል በምሕረቱ ይጐብኘን:: ከበረከታቸውም ያሳትፈን::

🕊

[  † ታሕሳስ ፲፭ [ 15 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሊቅ [ዘአርማንያ]
፪. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
፫. ቅዱስ ሉቃስ ዘዓምድ
፬. አባ ይምላህ

[    † ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ [አፈ በረከት]
፪. ቅድስት እንባ መሪና
፫. ቅድስት ክርስጢና
፬. ቅዱስ ሚናስ ሰማዕት
፭. ቅዱስ ቂርቆስ ሰማዕት
፮. ብጽዕት ኢየሉጣ ሰማዕት

" ጻድቃን ጮሁ:: እግዚአብሔርም ሰማቸው::
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው:: እግዚአብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው:: መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል:: የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው:: እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል:: እግዚአብሔር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል::
"
[መዝ.፴፫፥፲፯]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

09 Dec, 16:33


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  ❝  ሰ ው ን አ ት ከ ተ ል  !   ❞


💖  አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ    ] 💖

[                        🕊                        ]
---------------------------------------------------

❝ እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም ፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።  ❞

[ መዝ . ፴፬ ፥ ፰ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

Debtera Media

09 Dec, 15:26


                         †                        

  [      🕊   ፍኖተ ቅዱሳን    🕊      ]

[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ሁል ጊዜ በትጋትና በጥንቃቄ መሆን እንደሚገባ !  ]

🕊

እኛ እያለቀስን አንተ ለምን እንደ ሳቅህ ንገረን? "
........

- ሰባት መነኰሳት በአባ እንጦንዮስ ገዳም ይኖሩ ነበር፡፡ የአዝመራ ወቅት በደረሰ ጊዜ በየተራ ወፍ ይጠብቁ ነበር፡፡ ከእነርሱ አንዱ እህሉን ከወፎች ሲጠብቅ ፦ "እናንተ ክፉ ሃሳቦች ከውስጥ ፣ እናንተ ወፎች ደግሞ ከውጭ ወግዱልኝ" ብሎ ጮኸ፡፡

- በአስቄጥስ አንድ አረጋዊ ነፍሱ ልትወጣ ሳለ አኃው በዙሪያው ቆመው እያለቀሱ ነበር፡፡ እርሱ ግን ዓይኖቹን ክፍት አደረገና ሳቀ ፤ ከዚያም ሁለተኛ ጊዜ ሳቀ ፣ አሁንም እንደገና ሦስተኛ ጊዜ ሳቀ። እነርሱም ፦ "አባ ፣ እኛ እያለቀስን አንተ ለምን እንደ ሳቅህ ንገረን?" አሉት፡፡

እርሱም ፦ "መጀመሪያ የሳቅሁት እናንተ ሁላችሁም ሞትን ስለምትፈሩ ነው ፣ ሁለተኛ ጊዜ የሳቅሁት ስላልተዘጋጃችሁ ነው ፣ ሦስተኛ ጊዜ የሳቅሁት ደግሞ ድካምን ትቼ ወደ ዕረፍት እየሄድሁ በመሆኔ ነው።" አላቸው፡፡ አረጋዊው ይህን ብሎ ወዲያውኑ ዐረፈ፡፡ ❞


የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

09 Dec, 12:55


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ቅዱስ መቃርዮስ ካስተማረው ትምህርት ]

[             ክፍል  ሃምሳ አንድ            ]

                         🕊  

[ የአንድ እኁ አስደናቂ ትሕትና ተገለጠለት ]

🕊

❝  በሌላኛው ገዳም ስለሚኖርና በዚያው ገዳም አብሮት የሚኖር ሌላ እኁ ስለ ነበረው አንድ እኁ ከገዳሙ ተግባር ቤት ትንሽ ምንቸቶችን እንደ ሰረቀ ተነገረ:: ምንቸቶቹን የሰረቀው እኁ በኬሻ ውስጥ አድርጎ እንደ ተሰረቁ በማያውቀዉና የሌባው የራሱ ንብረቶች እንደ ሆኑ በመሰሉት እኁ ዘንድ አስቀመጣቸው፡፡

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምንቸቶቹ መጥፋታቸው ስለ ታወቀ በገዳሙ ውስጥ ያሉትን አኃው በኣታት በሙሉ የእያንዳንዳቸውን መፈተሽ ተጀመረ፡፡ የሰረቀው እኁ ምንቸቶቹን የራሱ አስመስሎ ጥሏቸው ከወጣበት እኁ በኣት ገቡና ሲፈትሹ ዕቃዎቹን በእርሱ ዘንድ ባገኟቸው ጊዜ ያ ባለ በኣቱ እኁ ራሱን መሬት ላይ ጥሎ ከእግራቸው ላይ ወድቆ ፦ “በድያለሁ፣ ይቅር በሉኝ ፣ የሰይጣን መሳለቂያ ሆኛለሁ ” አላቸው፡፡

ያ ምንቸቶቹን ሰርቆ በዚህ እኁ በኣት ያስቀመጣቸው እኁ በዚህ በበኣቱ በተገኙበት እኁ ላይ አብዝቶ አፌዘበት ፡ ነቀፈውም ፣ ፊቱንም በጥፊ መታው ፤ ከገዳሙ ሊያስወጣውም ፈለገ፡፡ በዚህ ሁሉ ነገር ያ የተወነጀለው እኁ ምንም ነገር አልካደም [አላደረግኩም አላለም] ፣ ይልቁንም ከዚያ ከሰረቀው እኁ ፊት ራሱን ዝቅ አድርጎ ፦ “በድያለሁና ይቅር በለኝፈ” አለው፡፡

በበኣቱ ምንቸቶቹ የተገኙበት እኁ በገዳሙ አበምኔትና በሁሉም በገዳሙ መነኰሳት ዘንድ በጣም የተጠላ ሆነ፡፡ በተለይም ደግሞ ያ የሰረቀውና በበኣቱ ጥሎበት የሄደው እኁ ኣብዝቶ ጠላው ፤ በእያንዳንዱ ቀን ባሉት ሰዓታት ሁሉ በአኃው መካከል “ሌባ” እያለ ይሰድበውና ይነቅፈው ነበር፡፡ ያ በስርቆት ተከሳሽ የሆነው እኁ ግን ያን ሁሉ ከባድ የሆነ ነቀፋና መጠላት እየታገሠ በእንዲያ ዓይነት ሁኔታ ሁለት ዓመት በገዳሙ ካሳለፈ በኋላ እግዚአብሔር ይህን ነገር ለአባ መቃርዮስ በአስቄጥስ ገለጠለት፡፡

አባ መቃዮርስም ያን እኁ ለማየት ወደ ግብጽ ሄደ፡፡ ወደዚያ ገዳም በደረሰም ጊዜ ሁሉም አኃው በአንድ ላይ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው እርሱን ለመቀበል ተሰበሰቡ፡፡ ያ ሰርቋል ተብሎ የተወነጀለውም እኁ ፦ “እኔ የተዋረድሁ ነኝ ፡ የዘንባባ ዝንጣፊ አልይዝም ፣ እርሱን ለመቀበልም ከእናንተ ጋር አልሄድም ፣ እናንተ ራሳችሁ እንደምታዩኝ በኃፍረት የተሞላሁ ነኝና አላቸው፡፡

አኃው አባ መቃርዮስን ሊቀበሉት በወጡና በፊቱ በቆሙ ጊዜ ሁሉንም እያንዳንዳቸውን ሰላም አላቸው፡፡ ሆኖም በስርቆት የተወነጀለውን እኁ ከእነርሱ መካከል ባላየው ጊዜ የት እንደ ሆነ ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም ሌባው እኁ ለምን እርሱን መጥቶ ለመቀበል እንዳፈረና እንዳልወጣ ነገሩት፡፡ ኣባ መቃርዮስም ይህን ሲሉት በሰማ ጊዜ ሳቀና ወደ ገዳሙ ገባ፡፡

ያ በሌብነት የተወነጀለው እኁም በትሕትናና በተዋረደ ሁኔታ ሆኖ አባ መቃርዮስን ሰላም ይለው ዘንድ መጣና ኣረጋዊው አባ መቃርዮስ እርሱን ይቅርታ እንደ ጠየቀው ሁሉ እርሱም አረጋዊውን ይቅርታ ጠየቀ ፤ እርስ በርሳቸውም አንዳቸው ከሌላቸው ይቅርታን ተቀባበሉ:: አባ መቃርዮስም አኃውን እንዲህ አላቸው ፦ “እኔም ሆንሁ እናንተ የዚህን እኁ ያህል የከበርን አይደለንም፡፡ ታላቅ ነቀፌታን የታገሠ ብቻ አይደለም ፣ የሸክላዎቹን ዕቃዎች የሰረቀውን እኁ ኃጢአትም በራሱ ላይ ተሸክሟል እንጂ፡፡” ከዚያም አባ መቃርዮስ ያን እኁ ወደ ቀደመ ቦታው መለሰው:: ያ ዕቃዎቹን የሰረቀው እኁ ግን አጽፉን ጠቅልሎ ከገዳሙ ወጣ ፣ ዳግመኛም ወደዚያ ገዳም አልተሰመለም፡፡  ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

09 Dec, 07:53


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ በሥጋ የታመመ እግዚአብሔር ቃል ነው ! ]

🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❝ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ አይደለም ፤ ወልድ ዋሕድ አንድ ነው እንጂ ፤ አንድ ከሆነም በኋላ አይለይም መለኮትና ትስብእት አንድ ከሆነ በኋላ አይቀላቀልም።

የመለኮት ባሕርይና የትስብእት ባሕርይ ተዋሐደ ፥ አንድ መልክም ሆነ ፤ በዚህ በአንዱ አካል መለወጥ የለም ፤ በሥራው ሁሉ ፍጹም ነው እንጂ ፥ ነፍስ ዕውቀት ገንዘቡ ነው ፤ ከኃጢአት ሁሉ የተለየ ነው። [ ዕብ.፯፥፳፯ ]

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተራበ በተጠማ ጊዜ ፤ መንገድም በመሔድ በደከመ ጊዜ ፥ በሐሰት መከራ አልተቀበለም ፥ የተጠሉ የተነቀፉ ሰዎች እንደ ተናገሩ ፤

በእውነት መከራ ተቀበለ እንጂ

እኛ ግን ሕማም የሚስማማው የሥጋ ሕማም ፤ ሕማም ለማይስማማው ለመለኮት እንዲነገር እንናገራለን ፥ በባሕርዩስ ሕማም የሌለበት ነው ፤ መለኮት የማይታመም ነውና።

ደፍረው በተነሡበት በአይሁድ መከራን ተቀበለ ፤ በሥጋ የታመመ እግዚአብሔር ቃል ነው ፥ መለኮትን ግን በባሕርዩ ሕማም አያገኘውም ፤ ቃል በመስቀል ላይ በሥጋ ተቸነከረ ፥ ቃል በፈቃዱ መከራ ከተቀበለበት ሥጋ አልተለየም።

በሥጋ የተቀበለው ሕማምንም ወዶ አልተቀበለም አይባልም ፥ ደስ ብሎት በፈቃዱ ተቀበለ እንጂ ፥ ራሱን ዘንበል አድርጎ ነፍሱን ከሥጋው በለየ ጊዜም ሕይወትን የሚሰጥ ሞትንና ሙስና መቃብርን ድል የሚነሣ የመለኮት ባሕርይ ከሥጋ አልተለየም

ቃል ሥጋውን በመቃብር አልተወም ፤ በሲዖልም ካለች ከነፍሱ አልተለየም ፤ ከነፍስ ከሥጋ በአንድነት ነበረ እንጂ ፤ ለዘለዓለም ክብር ምስጋና ይግባው።

[ መዝ.፲፮ ፡ (፲፭) ፥፲ ። ግብ.ሐዋ.፪፥፳፬-፴፫። ዮሐ.፲፱፥፴ ] ❞

[    ቅዱስ ጎርጎርዮስ  ዘእንዚናዙ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

08 Dec, 21:08


🕊  †  ቅዱስ አካክዮስ  †   🕊

ይህ ቅዱስ በ፭ ኛው መቶ ክ/ዘመን ከተነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት አንዱ ነው:: ተወልዶ ያደገው በቁስጥንጥንያ ሲሆን ትምሕርተ ሃይማኖትንም እዚያው ተምሯል:: በ፬፻፶፩ ዓ/ም ጉባኤ ኬልቄዶን [ጉባኤ አብዳን] ሲጠራ እሱም ጥሪ ደርሶት ነበር::
ነገር ግን ከመጀመሪያው ንጉሡ መርቅያንና ዻዻሱ ልዮን የተበተቡትን ሴራ ያውቅ ነበርና ሳይሔድ ቀረ:: ጉባኤው ተጠናቆ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ መገደሉንና ሃይማኖት መካዱን [በተሰብሳቢዎቹ] ሲሰማ አዘነ::

ንጉሡን ረግሞ "ጌታ ሆይ! ከዚህ ከረከሰ ጉባኤ ያልደመርከኝ ተመስገን" አለ:: ከጥቂት ዓመታት በሁዋላም ምዕመናን ሃይማኖቱ የቀና መልካም እረኛ መሆኑን ሲረዱ የታላቂቱ ቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: ብዙ ድርሳናትንም ደረሰ:: ወዲያው ግን ከመሪዎች ተዋሕዶን እንዲተው ትዕዛዝ መጣለት:: እንቢ በማለቱም ስደት ተፈርዶበት በስደት ላይ ሳለ ዐርፏል::

አምላከ ነገሥት ጻድቃን ቅኑን መሪ በሁሉም ሥፍራ ያድለን::ከወዳጆቹ በረከትም አይለየን::


[  † ኅዳር ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አፄ ገብረ መስቀል ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፪. ቅዱስ አካክዮስ ሊቅ
፫. ቅዱሳን ቆዝሞስ ወድምያኖስ
፬. ቅዱስ አናንዮስ ዘዓምድ
፭. አባ መርቆሬዎስ ሰማዕት

[  † ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ [ሐዋርያ]
፪. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፫. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት

" አቤቱ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል:: በማዳንህ እጅግ ሐሴትን ያደርጋል:: የልቡን ፈቃድ ሰጠኸው:: የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም:: በበጐ በረከት ደርሰህለታልና:: ከከበረ ዕንቁ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ:: ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም:: ለረጅም ዘመን ለዘለዓለሙ:: በማዳንህ ክብሩ ታላቅነው:: " [መዝ.፳፥፩-፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

08 Dec, 21:08


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[ † እንኩዋን ለጻድቅ ንጉሥ "አፄ ገብረ መስቀል" እና "ቅዱስ አካክዮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችህ † ]

" ኅዳር ፴ [ 30 ] "


🕊  † ጻድቅ አፄ ገብረ መስቀል †  🕊

የኢትዮዽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በብዙ ነገሮቿ የታደለች ናት:: ከእነዚህም መካከል በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ከደርዘን በላይ የሚሆኑ ነገሥቶቿ [መሪዎቿ] ቅዱሳን [ጻደቃን] ናቸው:: ለአንዲት ሃገር የመሪዎቿ ጥሩ ክርስቲያን መሆን እጅግ ወሳኝ ነው::

ባለፉት ፵ ዓመታት እንኩዋ የደረሰብንን የመንፈስ ዝለትና የሞራል ዝቅጠት ስንመለከት አንድም ችግሩ ከመሪዎቻችን እንደ ሆነ እናስተውላለን:: የሃገራችንን ታሪክ ስንመለከት ግን በእሳትና በጦርነት መካከል ሆነው ለፈጣሪ የተገዙ ብዙ ነገሥታትን እናገኛለን::

እንደ ምሳሌም :-

፩. ንግሥተ ሳባ
፪. ቀዳማዊ ምኒልክ
፫. አብርሐ ወአጽብሐ
፬. ካሌብ
፭. ገብረ መስቀል
፮. ሐርቤ
፯. ላሊበላ
፰. ይምርሐ
፱. ነአኩቶ ለአብ
፲. ዳዊት
፲፩. ቴዎድሮስ ቀዳማዊ
፲፪. ዘርዓ ያዕቆብ
፲፫. በእደ ማርያም
፲፬. ናዖድ
፲፭. ልብነ ድንግል
፲፮. ገላውዴዎስ
፲፯. ዮሐንስ
፲፰. ኢያሱ ቀዳማዊና
፲፱. ተክለ ሃይማኖት መናኔ መንግሥትን እናገኛለን::

ከእነዚህ መሪዎቻችን መካከል እኩሉ መንግስታቸውን ትተው በርሃ የገቡ ሲሆኑ እኩሉ ደግሞ በዙፋናቸው ላይ ሳሉ በጐ ሠርተው የተገኙ ናቸው:: አንዳንዶቹ ደግሞ በጥፋታቸው ተጸጽተው ንስሃ የገቡ ናቸው::

ከነገሥት ጻድቃን መካከልም ይህች ዕለት የአፄ ገብረ መስቀል መታሰቢያ ናት:: ጻድቁ ንጉሥ የአፄ ቅዱስ ካሌብ ልጅ ሲሆን በኢትዮዽያ የነገሠው በ፭ መቶ ፲፭  ዓ/ም ነው:: ሲነግሥም እጅግ ወጣት ነበረ:: ምክንያቱም አባቱ ካሌብ ከናግራን ጦርነት መልስ በመመነኑ በዙፋኑ የተቀመጠ ልጁ እርሱ ነበርና::

ከዚህ ቅዱስ የመጀመሪያ የምናደንቀው ስሙን ነው:: የዛሬ ፩ ሺህ ፭ መቶ ዓመት እንኩዋ በመስቀል የሚመኩ: ለመስቀል የሚገዙ መሪዎች መኖራቸው በዘመኑ የነበረውን የክርስትና ደረጃ ያሳያል:: "ገብረ መስቀል" ማለት "የመስቀል አገልጋይ [ባሪያ] " ማለት ነውና::

አፄ ገብረ መስቀል በጐ ንጉሥ እንዲሆን የቅዱስ አባቱ ማንነት የረዳው ይመስላል:: ያ ኃያል: ብርቱና ዓለም የፈራው አባቱ ሲጀመር በፍቅረ ክርስቶስና በድንግል እናቱ ፍቅር የተያዘ ደግ ሰው መሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መንግስቱን እንደ ጨርቅ ትቶ ሲሔድ መመልከቱ እርሱንም ያው አድርጐታል::

እርሱም ከአባቱ እንዳየው በአክሱም ላይ በነገሠባቸው ዓመታት በጾምና በጸሎት: ፍትሕ ርትዕ ሳደያጉዋድል: ድሃም ሳይበድል ይኖር ዘንድ ጥረት አድርጉዋል::


🕊  †   አፄ መስቀል   †    🕊

ይህ ጻድቅ ንጉሥ ለእኛ ከተወልን ትሩፋቶቹ አንዱ በዓለ መስቀልን በአደባባይ ማስከበሩ ቅድሚያውን ይይዛል:: በዓሉ መስከረም አካባቢ የሚደረግ ሲሆን "አፄ መስቀል" ይባላል:: ሕዝቡ: ካህናቱና መሳሣፍንቱ አድዬ አበባ እየዘነጠፉ ወደ ንጉሡ አደባባይ ይተማሉ:: በዚያም በያሬድ ዝማሬ ለቅዱስ መስቀሉ ታላቅ በዓል ይከበራል:: ይህ በዓል ይኼው ዛሬ በUNESCO ተመዝግቧል::

†   ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ

ሃገራችን ታላቁን ሰማያዊ ዜማ ያገኘችው በአፄ ገብረ መስቀል ዘመን ነው:: ቅዱስ ያሬድ ከሰማይ ያገኘውን ማኅሌት ለመጀመሪያ ጊዜ በአክሱም ጽዮን :-

"ሃሌ ሉያ . . .! ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ:: ወበዳግም አርአዮ ለሙሴ ዘከመ ይገብር ግብራ ለደብተራ::" ብሎ ከ፫ቱ ጸዋትወ ዜማ በአንዱ በአራራይ ሲያዜም ንጉሡ በዜማው ተመስጦ እየሮጠ ወደ ጽዮን ደርሷል::

ከዜማው ጥፍጥና [ጣዕም] የተነሳ ሁሉም ተደመሙ:: ንጉሡም ከዚያች ቀን ጀምሮ ከቅዱስ ያሬድ የማይለይ ሆነ:: ስብሐተ እግዚአብሔርንም ለብዙ ጊዜ ከቅዱሱ ሊቅ በጥዑም ዜማ ተቀምሞለት ተመገበ:: እንዲያውም አንዴ ሊቁ ሲያዜምለት ጻድቁ አፄ ገብረ መስቀል የቅዱስ ያሬድ እግር ላይ በትረ መንግስቱን ተክሎበታል:: ሁለቱም ከተመስጧቸው ሲነቁ ግን ንጉሡ ደንግጦ "ምን ልካስህ?" ቢለው "ወደ በርሃ አሰናብተኝ" አለው::
አፄ ገብረ መርስቀልም እያዘነ ፈቅዶለታል:: ቅዱስ ያሬድም ከመሬት ክንድ ከፍ ብሎ ተንሳፎ: የመሰናበቻ ምስጋናን :-

"ውዳሴ ወግናይ: ለእመ አዶናይ: ቅድስት ወብጽዕት . . ."
ብሎ አንቀጸ ብርሃንን: በሚጣፍጥ ዜማ ሰተት አድርጐ አደረሰ:: ይህንን ሲሰማ ንጉሡ ፈጽሞ አለቀሰ:: እስከ መንገድ ድረስ ከሕዝቡና ሠራዊቱ ጋር ከሸኘው በሁዋላም ቅዱስ ያሬድ ጸለምት ላይ ሲደርስ በዜማ አሰምቶ "ሰላም ለኩልክሙ" አለ:: አፄ ገብረ መስቀልና ሕዝቡም "ምስለ መንፈስከ" ብለውት ቀና ሲሉ ከዓይናቸው ተሰወረ:: ንጉሡም በዘመኑ ማኅሌተ ሰማይ እንዲስፋፋ ብዙ ጥሯል::

† ንጉሡና ፱ኙ ቅዱሳን

ተስዓቱ ቅዱሳን በሃገራችን ወንጌልን እንዲሰብኩ: መጻሕፍትን እንዲተረጉሙና ገዳማዊ ሕይወትን እንዲያስፋፉ አፄ ገብረ መስቀል ትልቅ ጥረት አድርጉዋል:: በተለይ ከአባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል ጋር ልዩ ቅርበት ነበረው:: ዘወትርም ከእነርሱ ይባረክ ነበር:: አቡነ አረጋዊንም በየጊዜው ይጐበኛቸው እንደ ነበር ይነገራል::

†  ንጉሡና ታቦት

ልክ እንደ ቅዱስ መስቀሉ ሁሉ ታቦተ እግዚአብሔር በዑደት እንዲከበር ያደረገ ይህ ንጉሥ ነው ይባላል:: መነሻው ደግሞ የደብረ ዳሕሞ መታነጽ ነው:: አንድ ቀን አቡነ አረጋዊን ምን እንደሚሹ ቢጠይቃቸው "የድንግል እመቤታችን ማርያምን መቅደስ አንጽልኝ" አሉት::
በደስታ አንቆጥቁጦ አነጻት:: የምርቃቱ ዕለትም ንጉሡ: ጻድቁና ሊቁ [ማለትም ገብረ መስቀል: አረጋዊና ያሬድ] ከሌሎች ቅዱሳን ጋር ተገኙ:: በጊዜውም ታቦቱ ሲነግሥ ቅዱስ ያሬድ ባቀረበው ማኅሌታዊ ዜማና አበው ባደረጉት ዝማሬ: ታቦቱ እየዞረ ታላቅ መንፈሳዊ ሐሴት ሆነ::
ደብረ ዳሞ ያኔ መወጣጫ ደረጃ ነበረው:: ንጉሡና ቅዱስ ያሬድ ከበዓል ሲመለሱ በአቡነ አረጋዊ ጥያቄ መወጣጫው ተደርምሷል::
ጻድቁ "ዳሕምሞ [ደርምሰው]" ስላሉት ቦታው ዳሕሞ [ዳሞ] ተብሎ ቀርቷል:: ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ገብረ መስቀል ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን አንጾ በዚህች ቀን ዐርፎ ተቀብሯል::

Debtera Media

08 Dec, 15:53


                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ ጕልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል ? ቃልህን በመጠበቅ ነው። ❞  [ መዝ . ፻፲፱ ፥ ፱  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬


[ ሕይወተ ወራዙት [ የወጣቶች ሕይወት ! ]

               [   ክፍል -  አንድ  -    ]

          💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬


የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]


🕊                        💖                      🕊
                             👇

Debtera Media

08 Dec, 11:42


🕊                    💖                   🕊

[       🕊   ክብርት ሰንበት   🕊        ]


[  ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ !  ]

                        🕊                       

❝ ወዮ ይህች ዕለት አብ የቀደሳት ወልድ የባረካት መንፈስ ቅዱስ ከፍ ከፍ ያደረጋት ናት ፤ በርሷ ደስ ይበለን በርሷም ሐሤት እናድርግ ፣ ትከብሩባት ዘንድ አክብሯት።

ዘመን ወር ለመባል በርሷ የታወቃችሁ ሌሎች ዕለታት ሆይ የበዐላትን በኵር ኑ አመስግኗት ይህችውም የከበረች ሰንበተ ክርስቲያን ናት።

ወዮ ይህች ዕለት ያረጀችዋ ያለፈችባት አዲሲቱ የጸናችባት ናት ፤ ወዮ ይህች ዕለት እስረኞች [ ነፍሳት ] የተፈቱባት ባሮች [ ደቂቀ አዳም ] ነጻ የወጡባት ናት። ወዮ ይህች ዕለት የፈረሰ የታነጸባት ሰይጣንም የጠፋባት ናት።

ዳግመኛም ይህች ዕለት በምትሠለጥንበት ጊዜ [ አመ ትሰፍን ወይም ለዘለዓለም ጸንታ በምትኖርበት ጊዜ ] አዲስ ሥራ አዲስ ነገርም ይሆናል ፤ ያን ጊዜ የፀሐይና የጨረቃ የከዋክብትም ብርሃን ፣ ወይም ፀዳል [ ማንም ዓይነት ብርሃን ] ፣ ክረምት ወይም በጋ የለም።

... ክብርት የምትሆን ይህች ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ ! እንደ አብ የሠለጠነች እንደ ወልድ የምትገዛ እንደ መንፈስ ቅዱስ [ ለዘለዓለም ] የምትኖር ናት ፤ ይህች ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ ! ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምኝልን ፣ ስለኛም አማልጂ ለዘለዓለሙ። ❞

[   ቅዱስ  አትናቴዎስ    ]


🕊                        💖                       🕊

Debtera Media

07 Dec, 08:10


💛

🕊     ቅ ዱ ስ አ ማ ኑ ኤ ል     🕊

❝ ሰላም ለአስተርእዮቱ በሥጋ
ዘአስተርአየ ገሃድ ከመ የሀበነ ጸጋ ❞

[  በግልጽ ጸጋን ያድለን ዘንድ በሥጋ የተገለጠ ለኾነ ለእርሱ አገላለጥ ሰላምታ ይገባል ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል ፤ እነሆ ፥ ድንግል ትፀንሳለች ፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። ❞

[ ኢሳ.፯፥፲፬ ]

" Therefore the Lord himself shall give you a sign; Behold, a virgin shall conceive, and bear a son, and shall call his name Immanuel."

[ Isaiah 7:14 ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

Debtera Media

06 Dec, 21:35


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

†  እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "አባ ሊቃኖስ ወአባ ሰረባሞን ሰማዕት" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ †

" ኅዳር ፳፰ [ 28 ] "


🕊  †  አባ ሊቃኖስ ዘደብረ ቆናጽል  †   🕊

ጻድቁ ገድላቸውን የፈጸሙት በኢትዮዽያ ቢሆንም ሃገረ ሙላዳቸው የጥንቱ የሮም ግዛት የሆነችው ታናሽ እስያ ናት:: አባ ሊቃኖስ ከዘጠኙ [ተስዓቱ] ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ዘጠኙ ቅዱሳን ተወልደው ያደጉት ምንም በአንድ የሮም ግዛት ሥር ቢሆንም መነሻ ቦታቸው ግን የተለያየ ነው::

ሁሉንም አንድ ያደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ በኪነ ጥበቡ ነው:: በምክንያት ደረጃ እንግለጸው ከተባለ ደግሞ የአንድነታቸው ምሥጢር :-

፩. የቀናች ሃይማኖታቸው ተዋሕዶ
፪. ዓላማ [የእግዚአብሔር መንግስት] እና
፫. ገዳማዊ ሕይወት ነው::

አባ ሊቃኖስን ጨምሮ ሁሉም ቅዱሳን ዘራቸው ከቤተ መንግስት ነው:: እነርሱ ግን ምድራዊውን ክብር ንቀው ሰማያዊውን ክብር ገንዘብ ማድረግን መርጠዋል:: አስቀድመው ቅዱሳት መጻሕፍትን ያጠኑት አበው በተለያየ ጊዜ እየመነኑ ከሮም ግዛት ወደ ግብጽ በርሃዎች ወርደዋል::

በምናኔ ቅድሚያውን አባ ዸንጠሌዎንና አቡነ አረጋዊ ይይዛሉ:: ዘመኑ የተዋሕዶ አማኞች የሚሰደዱበት ፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ነበርና እምነትን ላለመለወጥ ዘጠኙ ቅዱሳን ስደትን መረጡ::

በወቅቱ ደግሞ ለስደት መጠለያ የምትሆንና ከኢትዮዽያ የተሻለች ሃገር አልነበረችም:: ስለዚህም በ፬ መቶ ፸ ዎቹ ዓ/ም አልዓሜዳ በኢትዮዽያ ነግሦ ሳለ ቅዱሳኑ በአረጋዊ መሪነት መጡ::

ንጉሡም ሲጀመር የእግዚአብሔር እንግዳ ስለሆኑ: ሲቀጥል ደግሞ ቅድስናቸውን ተመልክቶ መልካም አቀባበልን አደረገላቸው:: ማረፊያ ትሆናቸውም ዘንድ አክሱም ውስጥ አንዲት ቦታን ወስኖ ሰጣቸው:: ይህች ቦታ ቤተ ቀጢን ትባላለች::

አባ ሊቃኖስና ፰ቱ ቅዱሳን ወደ ሃገራችን እንደ ገቡ የመጀመሪያ ሥራቸው ቋንቋን መማር ነበር::

ልሳነ ግዕዝን በወጉ ተምረው እዛው አክሱም አካባቢ ሥራቸውን አንድ አሉ:: በወቅቱ በአቡነ ሰላማ: በአብርሃ ወአጽብሐና በአቡነ ሙሴ ቀዳማዊ የተቀጣጠለው ክርስትና በተወሰነ መንገድ ተቀዛቅዞ ነበርና እነ አባ ሊቃኖስ እንደ ገና አቀጣጠሉት::

ሕዝቡን በራሱ ልሳን ለክርስትና ይነቃቃ ዘንድ ሰበኩት::የካደውን እየመለሱ: የቀዘቀዘውን እያሟሟቁ ለዓመታት ወንጌልን ሰበኩ:: ቀጣዩ ሥራቸው ደግሞ መጻሕፍትን መተርጐም ሆነ::

ከሃገራቸው ያመጧቸውን ቅዱሳት መጻሕፍት ተከፋፍለው ወደ ግዕዝ ልሳን ተረጐሟቸው:: በዚህም ለሃገራችን ትልቁን ውለታ ዋሉ:: ይህ ሁሉ ሲሆን እነ አባ ሊቃኖስ የሚመገቡትም ሆነ የሚጸልዩት በማኅበር ነበር:: በመካከላቸውም ፍጹም ፍቅር ነበር:: ጸጋ እግዚአብሔር አልተለያቸውም::

የነ አባ ሊቃኖስ ቀጣዩ ተግባራቸው ደግሞ ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋት ሆነ:: ይህንን ለማድረግ ግን የግድ መለያየት አስፈለጋቸው:: እያንዳንዱም መንፈስ ቅዱስ ወደ መራው ቦታ ሔደ::

- ዸንጠሌዎን በጾማዕት:
- ገሪማ በመደራ:
- አረጋዊ በዳሞ
- ጽሕማ በጸድያ
- አባ ይምዓታ በገርዓልታ
- ሌሎችም በሌላ ቦታ ገዳማትን መሠረቱ::

ልክ እንደ ባልንጀሮቻቸው ፰ቱ ቅዱሳን አባ ሊቃኖስም ከጻድቅነታቸው ባሻገር ለሃገራችን ትልቅ ባለውለታ ናቸው::በነገራችን ላይ 'አባ ሊቃኖስ' የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን በትምሕርታቸው [በእውቀታቸው] የተደመመ የአክሱም ሕዝብ ያወጣላቸው ስም ነው::

ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጐሙልን አበው አሉና:: ይሕስ በምን ይታወቃል ቢሉ :- ፱ኙ ቅዱሳን የማኅበር አገልግሎታቸውን ፈጽመው ወደየ ራሳቸው ገዳማት ሲሔዱ አባ ዸንጠሌዎንና አባ ሊቃኖስ እዚያው አክሱም አካባቢ በመቅረታቸው ይሏል::

ምክንያቱም ሕዝቡና ንጉሡ ፪ቱን አበው "አትራቁን" ብለው ለምነዋቸው ነበርና:: በዚህም የተነሳ አባ ዸንጠሌዎን ከአክሱም ከተማ በላይ ባለች ጾማዕት [እንዳባ ዸንጠሌዎን] በሚሏት ተራራ ላይ ሲያርፉ: አባ ሊቃኖስ ደግሞ ከዚያው ከጾማዕት ፩ ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ደብረ ቆናጽል [የቀበሮዎችተራራ] ላይ ዐርፈዋል::

በመካከላቸው ደግሞ የቅድስት ማርያም መግደላዊት ቤተ ክርስቲያን ይገኛል:: አባ ሊቃኖስ በአታቸውን ካደራጁና ገዳም ካነጹ በኋላ ደቀ መዛሙርትን አፈሩ: አስተማሩ::

እጅግ ከበዛው ተጋድሏቸው ባልተናነሰ መንገድ ለ፳፩ ዓመታት ያህል ከተራራው እየተነሱ ወንጌልን ሰብከዋል:: መጽሐፍ ቅዱስና ሌሎች መጻሕፍትንም ከሱርስት [የሶርያ ልሳን] እና ከጽርዕ [የግሪክ ልሳን] ተርጉመዋል::

ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን አይለዩም ነበር:: ሲሰብኩም: ሲጸልዩም ተደግፈውባት ነበር:: ታዲያ ከዘመን ብዛት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን አበው :-"ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ::

ዳግመኛ ማታ ማታ ለጸሎት እጆቻቸውን ሲያነሱ እንደ ፋና ቦግ ብለው ሲያበሩ ይታዩ ነበር:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ሥሙር በሆነ ሕይወታቸው በእግዚአብሔር ብቻ ሳይሆን በነገሥታቱና በሕዝቡ ዘንድም ሞገስን አግኝተዋል:: ዛሬም ድረስ የአክሱም ሕዝብ ከልቡ ያከብራቸዋል::

አንድ ወቅትም ሳይገባን [በቸርነቱ] ሒደን ገዳማቸውን ተመልከተናል:: አበው እንደሚሉት በደብረ ቆናጽል ላይ ያለው ደን የብዙ ሥውራን መኖሪያ ነው:: ለ፩ ሺህ ፭ መቶ ዓመታት ተከብሮ ቢኖርም በ፲፱፻፳፰ቱ የጣልያን ወረራ ግን እንዳልነበረ ሆኖ ነበር::

ዛሬም በቀድሞ ገጽታው አይደለም:: በገዳሙም ያገኘነው አንድ አባትን ነው::

ዐይናችን ግን ብዙ ነገሮችን ተመልክቶ አድንቋል:: እንደ ሰማነውም ዛሬም መካነ ቅዱሳን በመሆኑ የጽዮን አገልጋዮችም ማረፊያ ነው:: ጻድቁ አባ ሊቃኖስ ያረፉት ሕዳር ፳፰ ቀን ነው::

Debtera Media

06 Dec, 21:35


🕊  † ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት †  🕊

ቅዱሱ ሰው የዘመነ ሰማዕታት ፍሬ ሲሆን የቅዱሳን ሐዋርያት ዘመድ ነው:: እርሱ ተወልዶ ያደገው በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢየሩሳሌም ነው:: የዘር ሐረጉ ሲቆጠርም በቀጥታ ከሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስና ከስምዖን ቀለዮዻ ይደርሳል::

በልጅነቱ ያደገው በሥርዓተ ኦሪት ነው:: ወጣት በሆነ ጊዜ ግን ፈጣሪ በሰጠው ሕሊና ተመራምሮ በክርስትና ለመኖር ወሰነ:: የወቅቱን የኢየሩሳሌም ኤዺስ ቆዾስ ሒዶ "አጥምቀኝ" ቢለው "ልጄ! ደስ ይለኝ ነበር:: ግን ወገኖችህ አይሁድ ይገድሉኛል" ሲል መለሰለት::

አክሎም "ወደ ግብጽ ሒደህ ግን ብትመጠመቅ የተሻለ ነው" ስላለው ከኢየሩሳሌም ግብጽ ገባ:: ግብጽ ደርሶ: ከቅዱስ ቴዎናስ [፲፮ኛ ፓትርያርክ] ክርስትናን ተምሮ ተጠመቀ::ቀጥሎም ወደ ገዳም ገብቶ ከመጀመሪያዎቹ መነኮሳት አንዱ ሆነ:: ምናኔን ከአባ እንጦንስ ተምሮ ስም አጠራሩ ከፍ አለ::

በተጋድሎውና በንጽሕናው ስለ ወደዱትም የኒቅዮስ ዻዻስ አደረጉት:: በዘመነ ሲመቱም ጣዖት አምልኮን ከአካባቢው አጥፍቷል:: ስለዚህ ፈንታም በዲዮቅልጢያኖስ ተይዞ በዚህች ቀን ተገድሏል:: ሲገደልም ልክ እንደ ቅድመ አያቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፊቱ ያበራ ነበር::

አምላከ አበው ቅዱሳን መዓዛ ቅድስናቸውን
ያሳድርብን::ከበረከታቸውም ይክፈለን::

 🕊

[ ኅዳር ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አባ ሊቃኖስ ጻድቅ [ከተስዓቱ ቅዱሳን]
፪. ቅዱስ ሰረባሞን ሰማዕት

[ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አማኑኤል ቸር አምላካችን
፪. ቅዱሳን አበው /አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ/
፫. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፬. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፭. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ [ሰማዕት]

" ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ:: በእርስዋም ለዘለዓለም ይኖራሉ:: የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል:: አንደበቱም ፍርድን ይናገራል:: የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::በእርምጃውም አይሰናከልም::" [መዝ.፴፮፥፳፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

06 Dec, 17:11


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷ ❝  ነገር ሁሉ ለበጎ ነው !  ❞


💖  አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ    ] 💖

[                        🕊                        ]
---------------------------------------------------

❝ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።  ❞

[ ሮሜ . ፰ ፥ ፳፰ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

Debtera Media

06 Dec, 16:19


                         †                        

  [      🕊   ፍኖተ ቅዱሳን    🕊      ]

[ የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ሁል ጊዜ በትጋትና በጥንቃቄ መሆን እንደሚገባ !  ]

🕊

" በክርስቶስ ቸርነትም ቤትህ ንጹሕ ይሆናል ! "
........

❝ አንድ አረጋዊ ለአንድ ወንድም እንዲህ አለው ፦ "ዲያብሎስ ጠላትህ ነው ፣ አንተ ደግሞ ቤት ነህ፡፡ ጠላት ያገኘውን [ክፉ] ነገር ሁሉ ወደ ቤትህ መወርወሩን አያቆምም ፣ ያገኘውን ቆሻሻ ነገር ሁሉ ያከማችብህ ዘንድ ይወረውርብሃል፡፡ እነዚህን መልሰህ እያወጣህ መጣል ደግሞ ያንተ ፋንታ ነው::

እንዲህ ካላደረግህ ግን ቤትህ በሁሉም ዓይነት ቆሻሻ ይሞላና ለመግባት የማትችልበት ደረጃ ላይ ትደርሳለህ፡፡ ነገር ግን እርሱ ወዳንተ የሚጥለውን ነገር ሁሉ ጥቂት በጥቂት መልሰህ እያወጣህ መጣል ይኖርብሃል ፣ በክርስቶስ ቸርነትም ቤትህ ንጹሕ ይሆናል፡፡


የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

06 Dec, 08:55


                           †                           

🕊  💖    ቀኑ አርብ ነው !    💖   🕊

🕊

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ❝ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ ! ❞ ]

💖

ሕሊናቸው የክርስቶስን ሕማም ከማሰብ አቁሞ የማያውቀው አባ መብዓ ጽዮን መድኃኔዓለምን ፦ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የዕለተ ዓርቡን መከራህን አሳየኝ፡፡ ስለ ራሴ ፈጽሞ አለቅስ ዘንድ " ሲሉ ለመኑት፡፡ ጌታም ፦ "መከራ መስቀሌን ለማየት ትፈቅዳለህን ? " ብሎ ጠየቃቸው። ጻድቁ አባ መባዓ ጽዮንም ፦ "አዎ ! አይ ዘንድ እወዳለሁ" አሉት።

ያን ጊዜም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ እጆቹና እግሮቹ ተቸንክረው ታየ ፣ በራሱም ላይ የእሾህ አክሊል ደፍቶ ነበር፡፡ እንዲህ ሆኖ በሮም አደባባይ ለቅዱስ ጴጥሮስ እንደታየው ታያቸው። ይህን የመድኃኔዓለም መከራ የተመለከቱ የጻድቁ ዓይኖችም ፈዝዘው እስኪጠፉ ድረስ ትኩስ እንባዎችን ሲያዘንቡ ኖረዋል

🕊

❝ ሰው ስለመሆኑ ፤ መከራ ስለመቀበሉ መድኅንን የሚከፍለው [ ሁለት የሚያደርገው ] ፤ እግዚአብሔር ነው ብሎ ስለመስገድ ፈንታ ዕሩቅ ብእሲ ነው የሚል ፤ የተሰቀለውንም ከመለኮት የተለየ ሰው ነው የሚል ፤ መለኮትንም ሥጋ ወደመሆን ተለወጠ የሚል ቢኖር እግዚአብሔር ሰው በመሆን ያደረገለትን ድኅነት አያገኝም። [መዝ.፲፪ (፲፩)፥፭  ፣ ፸፬(፸፫)፥፲፪ ፣ ፻፲፩(፻፲)፥፱] ❞ [ አቡሊዲስ ]

 
❝ ኃይልየ ወጸወንየ ውእቱ እግዚእየ ❞  [ ኃይሌና መጠጊያዬ እርሱ ጌታዬ ነው ! ]

🕊

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


💖                    🕊                     💖

Debtera Media

06 Dec, 08:27


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ አምላክ ሰው ሆነ እንጂ .... !   ]

🕊

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

❝ [ አምላካችን ] ሰውም በሆነ ጊዜ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ አልተወለደም ፥ አምላክ ሰው ሆነ እንጂ ፤ እንደ ዕሩቅ ብእሲ በዘር በሩካቤ ተወልዶ ቢሆንስ ብዙ ሰዎች በተሳሳቱ ነበር ፥ አምላክ ሰው መሆኑንም ሐሰት በአደረጉት ነበር።

ዛሬ ግን ከድንግል ብቻ ተወለደ ፤ ድንግልናዋንም ባለመለወጥ አጸና ፤ ድንቅ የሚሆን መፅነስዋ የታመነ ይሆን ዘንድ ቅድመ ዓለም ከአብ እንደ ተወለደም ለማመን መሪ ይሆን ዘንድ።

የክብር ባለቤት ሲሆን ለሕፃናት እንደሚገባ በየጥቂቱ አደገ ፥ እርሱም ከአብ አንድነት ወደዚህ ዓለም መጥቼ ሰው ሆንኩ ወደ እግዚአብሔር እሔዳለሁ ፤ በእርሱ ፈቃድ ሰው ሆንኩ እንጂ በእኔ ፈቃድ ብቻ ሰው የሆንኩ አይደለም አለ። [ ዮሐ.፯፥፳፰ ። ፲፮፥፳፯—፳፱ ]

ይህም ከአብ ተወልዶ ሰው ለመሆን እንደመጣ ማርያም ለወለደችው አካል ምስክር ነው ፥ ወደ አብ የሔደውም ሌላ አይደለም ፥ በባሕርዩ አንድ የሚሆን እርሱ ነው እንጂ ፥ ከተወለደም በኋላ ሁለት አልሆነም ፤ ሁለት አካል ፤ ሁለት ባሕርይ አይደለም ፥ በሥራው ሁሉ አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንጂ ፤ ሙት በማስነሣት ድውይ በመፈወስ ፤ መከራ በመቀበል አንድ ነው እንጂ

[ ማቴ.፬፥፳፫-፳፭ ። ፲፩፥፬—፮ ] ❞

[    ቅዱስ ጎርጎርዮስ  ዘእንዚናዙ    ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

28 Nov, 10:10


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[            ክፍል  አርባ አምስት           ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[ 🕊   የቅዱስ መቃርዮስ ዕረፍት  🕊 ]

                         🕊      

ያን ጊዜም ነፍሱን ሰጠ ..... !       

❝ ይህ ቅዱስ እንደ ልማዱ በመሬት ላይ ወድቆ ከደዌው ጽናት የተነሣ መነሣት የማይችል ሆነ ፤ ሰውነቱም እንደ እሳት የሚያቃጥል ሆነ፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በታዩት በስምንተኛው ሌሊት ፣ ይኸውም በመጋቢት ሃያ ሰባት ቀን ፣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ከእርሱ የነበረ ኪሩባዊ ከቅዱሳን አባቶች ማኅበር ጋር ሆኖ ወደ እርሱ መጥቶ ፦ “እነዚህ ሁሉ ቅዱሳን እየጠበቁህ ነውና ወደ እኛ ና” አለው፡፡ ያን ጊዜ ኣባታችን ቅዱስ መቃርዮስ በታላቅ ድምጽ እንዲህ በማለት ጮኸ ፦ “አቤቱ ነፍሴ የምትወድህ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፣ ነፍሴን ወደ አንተ ተቀበል፡፡" ያን ጊዜም ነፍሱን ሰጠ፡፡

እንደ ወትሮው ይመክራቸውና የሚያጸናቸውን መንፈሳዊ ነገር ይነግራቸው ስለ ነበር ሕማሙ ቢያደክመውም ብዙዎችም ዕረፍቱ ያን ጊዜ መሆኑን አላወቁም ነበርና ወደ እርሱ አልመጡም ነበር፡፡ በተራራው በአራቱ ገዳማት ውስጥ የነበሩት መነኰሳት ሁሉ በሰሙ ጊዜ እያለቀሱና ልባቸው አዝኖ ሁሉም ተሰበሰቡ፡፡ ሁሉም ከእርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ አውቀዋልና ፣ እግዚአብሔርን መፍራትንና መልካም ምግባርን ከእርሱ ከሕይወቱ በተግባር ተምረዋልና ፣ የሰይጣናትን ኃይል ይቃወሙና በሰልፍ የጸኑ ቀዋምያን እንዲሆኑ የተጋድሎን ፈሊጥ አስተምሯቸዋልና ፣ በማይነዋወጽ ጽኑ መሠረት ላይ አንጾዋቸዋልና፡፡

ሌሎችም ሁሉ ማረፉን በሰሙ ጊዜ ከእርሱ ስለ መለየቱ በታላቅ ኃዘን ሆነው ከየበአታቸው እየወጡ መጡ:: መነኰሳትም መጥተው የከበረ ሰውነቱን አወጡት፡፡ ከዚያ በኋላ አባ እንጦንዮስንና የቅዱሳንን አንድነት ማኅበር ፣ ሰማያውያን የሆኑ የመላእክትንም ሠራዊት በእግዚአብሔር እጅ ነፍሱን እስከሚሰጥ ድረስ ያዩ ነበር፡፡

የቅዱስ መቃርስ ነፍስ ከሥጋው በተለየች ጊዜ ከፀሐይ ብርሃን ሰባት እጅ እያበራች ፍጹም ብርህት ሆና ከሰማይ የወረደው ኪሩባዊ በእጁ እንደ ተቀበላትና ከኪሩባዊውም ጋር ማንም ማን ክብራቸውንና ግርማቸውን ሊተረጉመው በማይችል በብዙ ሰማያውያን ኃይላት ታጅባ ወደ ሰማይ ስታርግ እንዳዩ ፣ ሰይጣናትንም ደቀ መዝሙሩ አባ በብኑዳ የናቅዮስ ኤጲስ ቆጶስ ፣ አባ ሰራጵዮን እና በዚያ የነበሩ ብዙ ቅዱሳን አረጋውያን እንደ ሰሟቸው ምስክር ሆኑ፡፡

ሰይጣናት ነፍሱን እንዲህ ሆና ባዩዋት ጊዜ እየተከተሉ ፦ “መቃርዮስ ሆይ ፣ ከእጃችን ዳንክ እመለጥክም” እያሉ ይጮኹ ጀመር፡፡ እርሱም ፦ “ገና አላመለጥኩም” አላቸው፡፡ አየር ላይ በደረሰ ጊዜ ሰይጣናት አሁንም እየጮኹ ፦ “መቃራ ሆይ ሄድክ እኮ” አሉት፡፡ እርሱም ፦ “የለም ገና ነኝ” አላቸው፡፡ አንድ እግሩ ወደ ውስጠኛው በር በደረሰ ጊዜ ሰይጣናት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው እየጮኹ ፦ “መቃራ ሆይ ፣ ገባህ” አሉት ፤ እርሱም ፦ “ገና ነኝ” አላቸው፡፡ በደረሰ ጊዜ እና ሁለት እግሩን ወደ ውስጥ ባስገባ ጊዜ ፈጽመው እያለቀሱ ፦ “መቃራ ሆይ ፣ ደረስክ እኮ” እያሉ አብዝተው ጮኹ፡፡ ያን ጊዜ ቅዱስ መቃርዮስ በታላቅ ድምጽ እንዲህ ሲል አሰምቶ ተናገረ ፦

የአምላኬና የመድኃኒቴ የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ተቀብያለሁ ፣ እኔም ከእጃችሁና ሥፍር ቁጥር ከሌለው ወጥመዳችሁ ያዳነኝን ፣ በምሕረቱ በቸርነቱና ሰውን በመውደዱ የጠበቀኝን አምላኬን እግዚአብሔርን ፈጽሞ አመሰግነዋለሁ::” ያን ጊዜ ኪሩባዊው ከእነርሱ ሰወረው ፣  ከዚያም በፍጹም ልቡ ወደ ወደደው ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማኅደረ ስብሐት ገባ፡፡

ይህ በእውነት ቅዱስ የሆነ አባትም ከመልካም ነገር ሁሉ ወደ ተመላች ሰማያዊ ማደሪያ ሄደ፡፡ በበአታት ሁሉ እየዞሩ የቅዱሱን ዕረፍት በነገሯቸው ጊዜ የሁላቸው አጽናኝና መካሪ ፣ እንዲሁም መንፈሳዊ ምግብን የሚመግባቸው መጋቢያቸው የነበረው አባታቸው ከእነርሱ ዘንድ በመታጣቱ ሁሉም አረጋውያን እያዘኑና እያለቀሱ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጡ፡፡ እያለቀሱ ከቅዱሱ ሥጋ ይባረኩ ዘንድና ይስሙት ዘንድ ዙሪያውን ቆሙ:: የሥጋ በሽታ የነበረባቸው ሁሉ እግዚአብሔር ያን ጊዜ ፈውስን ሰጣቸውና ዳኑ:: ስለ እርሱም ብዙ ጸሎትን አደረሱ ፣ ቅዳሴ ቀድሰውም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ተቀበሉ፡፡ ሥጋውንም በቤተ ክርስቲያኑ አጠገብ ባነጸው በአት ውስጥ ቀበሩት ፤ ከእርሱ ስለ መለየታቸው በታላቅ ሐዘን ሆነው ወደየ በአታቸው ተመለሱ፡፡ የዕረፍቱ ቀንም መጋቢት ሃያ ሰባት ቀን ነው:: ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

28 Nov, 02:43


🕊

[  † እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት ሰርጊስ ወቴዎፍሎስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †


🕊  †  ቅዱሳን ባኮስ ወሰርጊስ  †  🕊

† ሰማዕትነት በክርስትና ለሃይማኖት የሚከፈል የመጨረሻው ዋጋ [መስዋዕትነት] ነው:: ሰው ለፈጣሪው ሰውነቱን ሊያስገዛ: ሃብት ንብረቱን ሊሰጥ ይችላል:: ከስጦታ በላይ ታላቅ ስጦታ ግን ራስን አሳልፎ መስጠት ነው::

ራስን መስጠት በትዳርም ሆነ በምናኔ ውስጥ ይቻላል:: የመጨረሻ ደረጃው ግን ሰማዕትነት ነው:: "አማን መነኑ ሰማዕት ጣዕማ ለዝ ዓለም: ወተዓገሡ ሞተ መሪረ በእንተ መንግስተ ሰማያት" እንዳለው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሰማዕትነት ማለት መራራውን ሞት ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲሉ መታገስ ነው::

እርሱ ቅሉ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሰማይና የምድር ጌታ ሲሆን ኃፍረተ መስቀልን ታግሦ ሙቶልን የለ! በዓለም ያሉ ብዙ እምነቶች ስለ መግደል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ያስተምራሉ:: ክርስትና ግን መሞትን እንጂ መግደልን የሚመለከት ሕግ የለውም::

እርሱ ባለቤቱ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ:: የሚረግሟችሁን መርቁ:: ስለሚያሳድዷችሁ ጸልዩ::" ብሎናልና:: [ማቴ.፭፥፵፬] ነገር ግን ዕለት ዕለት ራሳችንን በሃይማኖትና በምግባር ካልኮተኮትነው ክርስትና በአንድ ጀምበር ፍጹም የሚኮንበት እምነት አይደለምና በፈተና መውደቅ ይመጣል::

በተለይ የዘመኑ ክርስቲያን ወጣቶች ልናስተውል ይገባናል:: የቀደሙ ወጣት ሰማዕታት ዜና የሚነገረን እንድንጸና ነውና:: እስኪ ለዛሬ ደግሞ በአጭሩ የቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስን ዜና እንካፈል::

እነዚህ ቅዱሳን የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ባኮስ እና ሰርጊስ [ሰርግዮስ] ከልጅነት ጀምሮ ባልንጀሮች ናቸው:: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር መክስምያኖስና ዲዮቅልጢያኖስ እስከ ነገሡበት ዘመን ድረስ በአንጻሩም ቢሆን ሰላም ነበር::

ታዲያ በዚህ የሰላም ጊዜ ሁለቱ ቅዱሳን ሥራ አልፈቱም:: ጾምን: ጸሎትንና በጐ ምግባራትን ሁሉ ይከተሉ ነበር:: ለመከራ ዘመን ስንቅ የሚሆነን በሰላሙ ዘመን የተያዘ ስንቅ ነውና::

በዚያው አንጻር ደግሞ ሠርቶ መብላት ይገባልና ሥራ ሲፈልጉ መክስምያኖስ ሠራዊት መሰብሰብ ጀመረ:: እነርሱም ከሠራዊቱ ዘንድ ተቆጥረው የምድራዊ ንጉሥ ጭፍሮች ሆኑ:: በእርግጥ በዘመናችን ለክርስትና አይመቹም ከሚባልላቸው ሥራዎች አንዱ ውትድርና ነው::

ነገር ግን ብዙ ቅዱሳንን ስትመለከቷቸው ሙያቸው ይሔው ነበር:: ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ ጊዜው የሰላምም ይሁን የጦርነት ይጾማሉ:: ይጸልያሉ:: ይመጸውታሉ:: እንዲህ እንዲህ እያሉም ዘመናት አለፉ::

ከቆይታ በኋላ ግን ሰይጣን ያደረበት ንጉሡ መክስምያኖስ ጣዖት አመለከ:: አዋጅም አውጥቶ ክርስቲያኖችን ያሰቃይ: ይገድልም ያዘ:: ቅዱሳኑ ይህንን ሲሰሙ አዘኑ::

ቁጭ ብለውም ተወያዩ:: በልባቸው ፍቅረ ክርስቶስ ይነድ ነበርና ወጣትነታቸው: መልካቸው: ተወዳጅነታቸው ሁሉ ሊያታልላቸው አልቻለም:: እንደ አንድ ልብ መካሪ: እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ስለ ሃይማኖት ሊሰው ወሰኑ::

በማግስቱም ንጉሡ ወደ ሾመው የቅርብ አለቃቸው ቀረቡና "የምንነግርህ ነገር አለን" አሉት:: "እሺ" ሲላቸው በወገባቸው ያለውን የክብር መታጠቂያና የክብር ልብሳቸውን በፊቱ ወረወሩለትና "እኛ የክርስቶስ ጭፍሮች ነንና ከዚህ በኋላ ላንተ: ለጣዖት አምላኪው አንታዘዝም" አሉት::

መኮንኑ ነዶታልና አስገረፋቸው: አሳሰራቸው:: በረሃብና በጥም: በብዙ መክፈልተ ኩነኔም አሰቃያቸው:: እነርሱ ግን ጽኑዓን ነበሩና አልቻሏቸውም:: ጥቅምት ፬ [4] ቀን በሆነ ጊዜ ግን ሁለቱን ለያዩዋቸው:: ቅዱስ ባኮስን ለብቻው ወስደው ትልቅ ድንጋይ በአንገቱ ላይ አሠሩበትና ባሕር ውስጥ አሰጠሙት::

ነፍሱም ከስጋው ስትለይ ባሕር ወደ ዳር አስወጣችው:: በአካባቢውም "ባባ" እና "ማማ" የሚባሉ ባሕታውያን ነበሩና እግዚአብሔር እንዲገንዙት አዘዛቸው:: ሲሔዱም ቅዱስ ሥጋውን አንበሳና ተኩላ ሲጠብቁት አግኝተው: በታላቅ ዝማሬ ገንዘው: በራሳቸው ተሸክመው ወስደው: በበዓታቸው ውስጥ ቀበሩት::

ቅዱስ ሰርጊስን ደግሞ ለ፮ ቀናት ካሠሩት በኋላ እጁንና እግሩን በእንጨት ላይ ቸንክረው: በእንስሳት ጭራ ላይ አስረው ሲጐትቱት ውለዋል:: አንገቱን በሰየፉት ጊዜም አንዲት ወጣት ደሙን ተቀብላ በረከትን አግኝታለች:: የመከራ ዘመን ካለፈ በኋላም ለቅዱሳኑ ቤተ ክርስቲያን ታንጾ በዚህች ቀን ተቀድሷል: ተአምራትም ታይተዋል::


🕊  † ቅዱስ ቴዎፍሎስና ቤተሰቡ †  🕊

† ቅዱስ ቴዎፍሎስ በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን በሮም ግዛት ሥር ይኖር የነበረ ጽኑዕ ክርስቲያን ነው:: እግዚአብሔር ሲያድለው ደግሞ ጸንታ የምታጸና: በርትታ የምታበረታ ሚስትን ሰጠው:: ስሟም ጰጥሪቃ ይባላል::

በክርስትናዋና በፈጣሪዋ ፍቅር ላይ ይሉኝታና ድርድርን የማታውቅ ብርቱ ሴት ናት:: ሁለቱ ተጋብተው በሕጉና በሥርዓቱ ሲኖሩ እግዚአብሔር በረድኤት ጐበኛቸውና ቅድስት ጰጥሪቃ ጸነሰች:: በወለደችውም ጊዜ "ደማሊስ" ስትል በሃገራቸው ልሳን ስም አወጣችለት::

ልክ ግን ከአራስነት አልጋዋ በተነሳችበት ወራት ያ የመከራ ዘመን [ዘመነ ሰማዕታት] ድንገት ደረሰ:: እሷም አካሏ አልጸናም: ልጇም ገና ፭ ወሩ ነው:: ባሏ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ደግሞ በጨካኙ ንጉሥ እጅ መውደቁን [መታሠሩን] ሰማች::

ይኼ እጅግ ከባድ ፈተና ቢመስልም እርሷ ግን ልጇን አዝላ ወደ እሥር ቤት ሔደች:: ባሏንም "ወንድሜ! እኔና ልጅህን በክርስቶስ ዘንድ ስለምታገኘን ጽና:: ክብርህን እንዳትተው" አለችው:: እርሱም ደስ ብሎት ብዙ መከራን ተቀበለ::

ግርፋቱ: እሳቱ ስለቱ ሁሉ ሲያልፍበት በተአምራቱ አሕዛብን ማረከ:: ቅዱስ መልአክም ከሰማይ ወርዶ ማርና ወተትን መገበው:: ከዚያም በዚህ ቀን ለአንበሳ ተሰጠ:: አንበሳውም ለቅዱሱ ሰግዶ: እግሩንም ስሞ: አንገቱን ተጭኖ ገደለው::

ወዲያው ሚስቱ ቅድስት ጰጥሪቃ ተይዛ እርሷም ከነ ልጇ ለአንበሳ ተሰጠች:: በዚህ ጊዜ የ፭ ወር ሕጻን ቅዱስ ደማሊስ አፉን ከፍቶ "እኔስ በሥላሴ አምናለሁና አንበሳን አልፈራም" ሲል እየሳቀ ጮኸ:: ወዲያውም እናትና ልጅን አንበሳው ገደላቸው:: ቅዱሱ ቤተሰብም ለክብር በቃ::

† አምላከ ሰማዕታት ጽንዐታቸውን: ትእግስታቸውንም ያድለን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፲፱ [ 19 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ሰርጊስ ሰማዕት
፪. ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሰማዕት
፫. ቅዱሳን ጰጥሪቃና ደማሊስ [የቅዱሱ ሚስትና ልጅ]
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ [ልደቱ]

[   †  ወርሐዊ በዓላት  ]

፩. ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
፪. ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
፫. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
፬. አቡነ ስነ ኢየሱስ
፭. አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም
፮. ቅዱስ ይምርሐነ ክርስቶስ

† "እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::" † [ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

27 Nov, 16:32


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  " ሦስቱ የቅዱሳን ማዕረጋት ! "

[   " በሶርያ ቅዱሳን አባቶች ... ! "   ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

-▷ የእግዚአብሔር ፍቅር ብልጭታ
-▷ ነፍስን መቀደስ
-▷ ተመሥጦና ፍጹም ደስታ


❝ እንግዲህ ፥ ወዳጆች ሆይ ፥ የዚህ ተስፋ ቃል ካለን ፥ በእግዚአብሔር ፍርሃት ቅድስናን ፍጹም እያደረግን ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ሁሉ ራሳችንን እናንጻ። ❞ [ ፪ቆሮ . ፯ ፥ ፩ ]


🕊                        💖                     🕊
                             👇

Debtera Media

27 Nov, 11:14


✝️የጾም ቁርሳችን፣ ለወገኖቻችን✝️ +++
በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ባጋጠመው ማኅበራዊ ቀውስ ብዙ ወገኖቻችን ለችግር ተጋልጠዋል።
እርስዎም ለእነዚህ ወገኖች የጾም ቁርስዎን በመለገስ ቸርነትን ያድርጉ!
ድጋፍ ለማድረግ
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለበለጠ መረጃ
09 84 18 15 44 ወይም
09 20 27 42 98 ይደውሉ።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት

Debtera Media

27 Nov, 02:56


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

[  ✞ እንኩዋን ለቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ: ለቅዱስ ኤላውትሮስ እና ለደናግል አጥራስስ ወዮና ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]


🕊  † ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ †   🕊

እንደ አባቶቻችን ትርጉም 'ፊልዾስ' ማለት 'መፍቀሬ አኃው ወንድሞችን የሚወድ' ማለት ሲሆን ከ፲፪ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት አንዱ ነው:: [ማቴ.፲፥፫] በዚህ ስም የሚጠራ ሐዋርያ ከ፸፪ቱ አርድእት ውስጥ ነበር:: እርሱም ጃንደረባውን ባኮስን ያጠመቀው ነው::

አንዳንዴ የ፪ቱ ታሪክ ሲቀላቀል እንሰማለን:: ለሁሉም ይህኛው ቅዱስ ፊልዾስ ቁጥሩ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት ሆኖ ምሑራነ ኦሪት ከሚባሉትም አንዱ ነበር:: በወቅቱ ገማልያል የሚሉት ክቡርና ምሑረ ኦሪት በርካታ ምሑራነ ኦሪትን አፍርቶ ነበር::

እንደ ምሳሌም ቅዱሳኑን "ዻውሎስን: ኒቆዲሞስን: ናትናኤልን: እስጢፋኖስንና የዛሬውን ሐዋርያ ቅዱስ ፊልዾስን" መጥቀስ እንችላለን:: ቅዱስ ፊልዾስ ነገዱ ከእሥራኤል ሲሆን ተወልዶ ያደገው በቤተ ሳይዳ ነው:: ኦሪትን ተምሮ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ 'መሲሕ ቀረ' እያለ ሲተክዝ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ እርሱ ደረሰ::

ትክ ብሎ አይቶት "ተከተለኝ" አለው:: [ዮሐ.፩፥፵፬] ቅዱስ ፊልዾስም ያለ ማመንታት: ሁሉን ትቶ በመንኖ ጥሪት ተከተለው:: በዚህ ዓይነት ጥሪ መድኃኒታችን ቅዱስ ማቴዎስንም ጠርቶታል:: [ማቴ.፱፥፱] ቅዱስ ፊልዾስ ጌታን ከተከተለ በሁዋላ ሥራ አልፈታም:: ወዲያውኑ ሒዶ ለናትናኤል [ቀናተኛው ስምዖን] ሰበከለት እንጂ::

"ሙሴ በኦሪት: ነቢያትም የተነበዩለትን መሲሕን አግኝቸዋለሁ" አለው:: ይሕ አነጋገሩም ምሑረ ኦሪት እንደ ነበር በእርግጥ ያሳያል:: [ዮሐ.፩፥፵፮] ቅዱስ ናትናኤልም ምሑር ነውና "ከናዝሬት ደግ እንዴት ይወጣል?" ቢለው ቅዱስ ፊልዾስም መልሶ "ነዐ ትርአይ-ታይ ዘንድ ና" አለው::

ናትናኤልም ሒዶ በጌታ አመነ:: ቅዱስ ፊልዾስ አገልጋይ እንደ መሆኑ መጠን በዮሐንስ ወንጌል ተደጋግሞ ስሙ ተጠቅሷል:: በተለይ ደግሞ ጌታ የ፭ ገበያ ሕዝብን አበርክቶ ሲመግብ አስቀድሞ ጥያቄ ቀርቦለት ነበር:: እርሱ ግን "ጌታ ሆይ! የ፪፻ ዲናር እንጀራ ብንገዛም አንዘልቀውም" ብሎ ነበር::

በሁዋላ ግን የጌታን ድንቅ ተአምር ተመለከተ:: [ዮሐ.፮፥፭]  በተለይ ደግሞ በሐዋርያት አበው መካከል ለጌታ እንደ እንደራሴ ሆኖ ያገለግል እንደ ነበርም ተጠቅሷል:: ሰዎች ጌታን ማግኘት ሲፈልጉ እሱና እንድርያስን ያናግሩ ነበር:: [ዮሐ.፲፪፥፳]  አንድ ጊዜ ግን እስካሁን ሊቃውንትን የምታስደምም ጥያቄ ጠይቆ ነበር::

አጠያየቁ ደግሞ ፍጹም የዋሕ እንደ ሆነ ያሳያል:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ባሕርይ አባቱ አብ እየነገራቸው ሳለ ቅዱስ ፊልዾስ ከመካከል ተነስቶ "እግዚኦ አርእነሁ ለአብ ወየአክለነ": ልክ ወልድን በዐይኑ እንዳየ ሁሉ አብን ሊያይ ቸኩሎ "አቤቱ ስለ አብ የሰማነው ይበቃልና አሳየን" ብሎታል:: [ዮሐ.፲፬፥፰]

ጌታችን ግን "ዘርእየ ኪያየ ርዕዮ ለአብ-እኔን ያየ አብን አይቷል" [ዮሐ.፲፬፥፱] ብሎ ምሥጢረ ባሕርዩን: አንድነቱን ሦስትነቱን አስረድቶታል:: ቅዱስ ፊልዾስም ጌታን እስከ ሕማሙ አገልግሎ: ቅድስት ትንሳኤውን አይቶ: ለ፵ ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምሮ: ቅዱስ መንፈሱን ከ፸፪ ልሳን ጋር ነስቶ ለስብከተ ወንጌል ወጥቷል::

ቅዱሳን ሐዋርያት ዓለምን በእጣ ሲካፈሉ ለእርሱ አፍራቅያ [አፍሪካ] ደርሳዋለች:: ስለዚህም በምድረ አፍሪካ ወንጌልን ከሰበኩ ሐዋርያት አንዱ ነው:: በአፍራቅያና በቀድሞው የኃምስቱ አሕጉር ግዛት ድንቅ ድንቅ ተአምራትን አድርጐ ብዙዎችን ወደ መንጋው [ወደ ክርስትና በረት] ቀላቀለ::

ለበርካታ ዓመታትም በተለያዩ የዓለም ክፍሎች እየተዘዋወረ ወንጌልን ሲሰብክ: ብርሃነ ክርስቶስን ሲያበራ: ነፍሳትንም ሲማርክ ቆየ:: ገድለ ሐዋርያት እንደሚለው የቅዱስ ፊልዾስ ፍጻሜው በሰማዕትነት እንደ ሆነ ቢታወቅም የትኛው ሃገር ውስጥ እንደ ሆነ መለየት አልተቻለም::

ዜናው ግን እንዲህ ነው:- በአንዲት ሃገር ውስጥ ገብቶ ሰበከ:: ብዙዎችንም አሳመነ:: ያላመኑት ግን ይዘው አሰቃዩት: ገረፉት:: "በክርስቶስ እመኑ እባካችሁ!" እያለ እየለመናቸው ዘቅዝቀው ሰቅለው ገደሉት::

ከዚያም በእሳት እናቃጥላለን ሲሉ ቅዱስ መልአክ ከእጃቸው ነጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ወሰደው:: በዚህ የደነገጡት ገዳዮቹ ለ፫ ቀናት ጾሙ: ተማለሉ:: በዚህ ምክንያት የቅዱሱ ሥጋ ተመልሶላቸው: ገንዘው ቀብረውት በክርስቶስ አምነዋል::


🕊 † ቅዱስ ኤላውትሮስ ሰማዕት †  🕊

ቅዱሱ ሰማዕትና ቅድስት እናቱ [እንትያ ትባላለች] የዘመነ ሰማዕታት ፍሬዎች ናቸው:: ቅድስት እንትያ መልካም እናት ናትና ቅዱስ ኤላውትሮስን በሃይማኖት በሥርዓት አሳደገችው:: በ፲፯ ዓመቱ ዲቁናን ተሾመ:: በ፲፰ ዓመቱ ቅስና: በ፳ ዓመቱ ደግሞ ዽዽስናን ተሾመ::

ያን ጊዜ ሃገራቸው ሮም የግፍ ቦታ ነበረችና የቅዱሱ ዜና ሕይወት: ብርሃንነቱ: ስብከቱ: ንጹሕ ሕይወቱ በሃገረ ገዢው ዘንድ ተሰማ:: አንዱን መኮንን ጠርቶ "ሒድ አምጣው" አለው:: መኮንኑ ሲደርስ ቅዱስ ኤላውትሮስ እየሰበከ ነበርና በጣዕመ ስብከቱ ተማርኮ ከነ ተከታዮቹ አምኖ በዚያው ቀረ:: አገረ ገዢውም ሌላ መኮንን ልኮ አስመጣውና ቅዱሱን "ለምን የተሰቀለውን ታመልካለህ?" አለው::

ቅዱሱም መልሶ "ማስተዋል የተሳነህ! ቢገባህ ኑሮ የተቀለው እኮ ለእኔና ለአንተ ነው" አለው:: ሞት ተፈርዶበት ቅዱሱን ብዙ አሰቃይተው እሥር ቤት ሲጥሉት ርግብ መጥታ መገበችው::

እግሩን ቸንክረው በመንገድ ላይ ሲጐትቱት መልአክ ወርዶ ፈታው:: ወደ በርሃም ወሰደው:: ከጊዜያት በሁዋላ እንደ ገና ይዘው አምጥተው: ብዙ አሰቃይተው በዚህች ዕለት: ከእናቱ ቅድስት እንትያ ጋር በጦር እየወጉ ገድለዋቸዋል::

ሊቃውንትም የሰማዕታቱንና የሐዋርያውን ተጋድሎ እያደነቁ እንዲህ ጸልየዋል :-

"ሰላም ለፊልዾስ ጽዑረ አባል በመቅሰፍት:
ወለኤላውትሮስ ርጉዝ በብልኃ ኩናት:
ምስለ እንትያ እባእ ኀበ ተርኅወ ገነት:
ያሩጸኒ መዓዛሆሙ ወጼናሆሙ ዕፍረት:
ለዝ ሐዋርያ ወለዝ ሰማዕት::" [አርኬ]


🕊  † ደናግል አጥራስስ ወዮና †  🕊

እሊህ ቡሩካት ሴት ወጣቶችም ምድራቸው ሮም ናት:: ቅድስት አጥራስስ የንጉሥ ልጅ ስትሆን ቅድስት ዮና ደግሞ የታላላቆች ልጅ ናት:: 2ቱ ቅዱሳት አንስት አይተዋወቁም ነበር:: ዮና ገና በልጅነቷ ክርስትናን አጥንታለች::

አጥራስስ ግን አባቷ ጣዖት አምላኪ በመሆኑ ቤት ሠርቶ: በወርቅ አንቆጥቁጦ ጣዖቶችን እንድታመልክ: ሰውም እንዳታይ አደረጋት:: እርሷ ግን ጣዖቱ እንደ ማይረባ ተመራምራ አውቃ ጣለችው::

"የማላውቅህ እውነተኛው አምላክ ተገለጽልኝ?" ስትልም ጸለየች:: ያን ጊዜ ቅዱስ መልአክ "ዮና የምትባል ሴት ታስተምርሽ" ስላላት አስፈልጋ አስመጣቻት:: ቅድስት ዮናም ክርስትናን ከጥንቱ ጀምራ አስተማረቻት::

Debtera Media

27 Nov, 02:56


፪ቱ ቅዱሳት አብረው እየዋሉ: አብረው እያደሩ በጾምና በጸሎት ቢጠመዱ ድንግል ማርያም እመቤታችን ተገለጠችላቸው:: ከልጇ ዘንድ አቅርባም አስባረከቻቸው:: ይህ ሁሉ ሲሆን የቅድስት አጥራስስ አባት ንጉሡ በሃገር አልነበረም:: ሲመለስ ግን የሆነውን ሁሉ አወቀ:: ሕዝቡን ሰብስቦ በአንዲት ልጁ አጥራስስና በወዳጇ ዮና ላይ በእሳት እንዲሞቱ ፈረደባቸው:: እሳቱ ብዙ እጥፍ ነዶ ሕዝቡ ሲያለቅስላቸው ፪ቱ ደናግል እርስ በርስ ተቃቅፈው ተሳሳሙ:: እየጸለዩም ወደ እሳቱ ተወረወሩ:: በዚያም ለፈጣሪያቸው ነፍሳቸውን ሰጡ:: እሳቱ ግን ልብሳቸውን እንኩዋ አላቀነበረውም::

አምላከ ቅዱሳን ስለ ወዳጆቹ ሲል ቸርነቱን: ምሕረቱን ይላክልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[  † ኅዳር ፲፰ [ 18 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ]
፪. ቅዱስ ኤላውትሮስና እናቱ እንትያ [ሰማዕታት]
፫. ቅዱሳት ደናግል አጥራስስ ወዮና [ሰማዕታት]
፬. ቅዱስ አትናቴዎስ የዋሕ

[   †  ወርሐዊ በዓላት   ]

፩. አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ረባን
፪. አቡነ አኖሬዎስ ዓቢይ
፫. ማር ያዕቆብ ግብጻዊ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ከ፸፪ቱ አርድእት]

" እኔንስ ብታውቁኝ አባቴን ደግሞ ባወቃችሁ ነበር:: ከአሁንም ጀምራችሁ ታውቁታላችሁ:: አይታችሁትማል አለው::

ፊልዾስ :- 'ጌታ ሆይ ! አብን አሳየንና ይበቃናል' አለው:: ጌታ ኢየሱስም አለው :- 'አንተ ፊልዾስ ! ይህን ያህል ዘመን ከእናንተ ጋር ስኖር አታውቀኝምን? እኔን ያየ አብን አይቷል:: እንዴትስ አንተ አብን አሳየን ትላለህ? እኔ በአብ እንዳለሁ: አብም በእኔ እንዳለ አመታምንምን?
" [ዮሐ.፲፬፥፯]


† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

26 Nov, 17:07


💛
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊

▷  " የመንፈሳዊነት ጥንካሬ ምንጮች ! "

[   " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ... ! "   ]

[                        🕊                        ]
-----------------------------------------------

-▷ የእምነት ኃይል ጥንካሬ
-▷ የጸሎት ኃይል ጥንካሬ
-▷ የንስሐ ኃይል ጥንካሬ
-▷ ራስን የመግዛት ጥንካሬ
-▷ በቃል ፣ በስብከትና በመንፈሳዊ አገልግሎት ውስጥ ያለ ጥንካሬ

❝ ንቁ ፥ በሃይማኖት ቁሙ ፥ ጎልምሱ ጠንክሩ። ❞
[ ፩ቆሮ . ፲፮ ፥ ፲፫ ]


🕊                        💖                     🕊
👇

Debtera Media

26 Nov, 13:21


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[              ክፍል  አርባ አራት               ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[ ቅዱስ እንጦንስና ቅዱስ ጳኲሚስ ቅዱስ መቃርዮስን በራእይ እንደ ጐበኙት ]

                         🕊             

❝ አኃው ከተመለሱ በኋላ ፈጽሞ ታመመ ፣ ብቻውንም ወደ በአቱ ግብቶ ተኛ፡፡ መላ የዕድሜው ዘመን ዘጠና ሰባት ዓመት ሆነ፡፡ ከቀኑ ሰባት ሰዓት በሆነ ጊዜ እንደ ልማዱ በልቡ ከዚህ ዓለም ወጥቶ ስለሚሄድባት ሰዓት የሚያስብ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርን እንዴት ብሎ ፊቱን እንደሚያየውና እንደሚገናኘውያን ጊዜ ስለ እርሱ ከእግዚአብሔር ዘንድ ስለሚወጣው ፍርድየሚሄድበት ቦታ ወዴት ስለ መሆኑ ያስብ ነበር፡፡ እንዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች በማሰብ ላይ እያለ እግዚአብሔር ከዚህ ዓለም መከራ ሊያሳርፈው በወደደ ጊዜ ሁል ጊዜ የሚጎበኘውን ኪሩብ ወደ እርሱ ላከው::

ኪሩባዊውም ፦ “እኔ ወደ አንተ መጥቼ እወስድሃለሁና” ተዘጋጅ አለው:: ያን ጊዜም በአምላካዊ ብርሃንና በታላቅ ክብር የሚያበሩ ሁለት ቅዱሳን ተገለጡለት፡፡ ከእነርሱም አንዱ ስለ ሌላው ደስ እያለው ፈገግ ይል ነበር፡፡ አረጋዊው ቅዱስ መቃርዮስም ትንሽ አሰበ፡፡ ከሁለቱ አንዳቸው ቅዱስ መቃርዮስን ፦ “እኛ እነ ማን እንደ ሆንን አውቀኸናልን?” አለው፡፡ እርሱም ባየው ጊዜ በፊቱ ከነበረው ብርሃን ብዛት የተነሣ ሊያውቀው አልቻለም፡፡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ “አባቴ ቅዱስ እንጦንስ ሆይ ፣ አወቅሁህ” አለ፡፡ ቅዱስ እንጦንስም ፦ “ይህ ሌላኛውስ ማን እንደ ሆነ አላወቅህምን?" አለው:: እርሱም ፈጥኖ መናገር አይወድምና ዝም አለ፡፡

ቅዱስ እንጦንስም ፦ “ይህ የዳውናስ መነኰሳት አባት አባ ጳኲሚስ ነው ፣ እነሆ ጌታ እንጠራህ ዘንድ ወደ አንተ ላከን ፣ እስከ ሰባት ቀን ድረስ የዚህን ዓለም ልብስ አውልቀህ ከእኛ ጋር ትሆን ዘንድ ወደ እኛ ትመጣለህና ፤ ዓይንህን ወደ ላይ አንሣና ደስ ይልህ ዘንድ ፣ በዕረፍትህም ሐሴት ታደርግ ዘንድ የተዘጋጀልህን አዳራሽ ተመልከት” አለው፡፡ እንዲህ እያሉት እያለ ከእርሱ ዘንድ ተሰወሩ፡፡

አረጋዊው ቅዱስ መቃርዮስም አኃው እንዳያዝኑና እርሱንም መልሰው እንዳያሳዝኑት ይህን ያየውን ነገር ለማንም አልተናገረም፡፡ ኣኃው ቅዱስ መቃርዮስን የሚያዩት በሠራዊቱ መካከል እንዳለ የሠራዊት አለቃ በመሆኑ አለቃቸው ከእነርሱ ቢወሰድ ራሳቸው ከሰውነታቸው እንደ ተቆረጠ ያህል ይሰማቸው ነበርና፡፡ መሪያቸው ከሌለ በጦርነት ውስጥ ኃይል አይኖራቸውምና፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ብቻ ሳይሆኑ በተለያዩ ቦታዎች የሚኖሩ መነኰሳትም በሙሉ እርሱን የሚያዩት እንዲህ ነበር ፤ እርሱ ያጽናናቸውና ያበረታቸው ነበርና፡፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

11 Nov, 21:56


🕊

[ †  እንኩዋን ለቅዱሳን ጻድቃን "አቡነ መድኃኒነ እግዚእ" : "ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል" እና "ቅዱስ ኪርያቆስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]


🕊  †  አቡነ መድኃኒነ እግዚእ  †  🕊

መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጽያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ [አዲግራት] ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::

ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል [የምሥጢር] መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::

ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::

በኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን [በተለይ ከ፲፫ኛው እስከ ፲፭ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው] የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ ፦

- ክርስትና ያበበበት::
- መጻሕፍት የተደረሱበት::
- ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
- ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ :-

- አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
- አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
- አባ ሰላማ ካልዕ::
- አቡነ ያዕቆብ::
- ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
- አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
- አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

በተጨማሪም :-

- ፲፪ ቱ ንቡራነ ዕድ::
- ፯ቱ ከዋክብት::
- ፵፯ቱ ከዋክብት::
- ፭ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ፯ቱ እና የ፵፯ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው ፫ቱ ሳሙኤሎች [ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ] : የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም [ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው] የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::

ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር ፫ ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም ፻፹ ነው::

" መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" [መጽሐፈ ሰዓታት]

" ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" [አርኬ]


🕊  †   ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል  †  🕊

የዚህ ቅዱስ ኢትዮዽያዊ ዜና ሕይወት ለሁላችንም ትልቅ ትምርትነት ያለው ነው:: በተለይ በምክንያት ከቅድስና ሕይወት እንዳንርቅ ያግዘናል ብየም ተስፋ አደርጋለሁ:: የቅዱሱ ወላጆች ገላውዴዎስና ኤልሳቤጥ ሲባሉ በምድረ ሽዋ በበጐ ምጽዋታቸው የተመሰከረላቸው ነበሩ::

ፈጣሪ ሰጥቷቸው ኅዳር ፰ ቀን [በበዓለ አርባዕቱ እንስሳ] ወልደውታልና "ዓምደ ሚካኤል - የሚካኤል ምሰሶ" ሲሉ ሰይመውታል:: ገና በልጅነቱ ብዙዎችን ያስገርም የነበረው ቅዱሱ አንዴ በ ፫ ዓመቱ ከቅዳሴ መልስ ጠፋቸው::

ወላጆቹ እያለቀሱ በሁሉ ቦታ ፈለጉት:: ግን ሊገኝ አልቻለም:: በ3ኛው ቀን የሞቱን መታሠቢያ ሊያደርጉ ካህናትና ምዕመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡ ግን ባዩት ነገር ተገረሙ:: ሕጻኑ ዓምደ ሚካኤል ከቤተ መቅደሱ መሃል: ከታቦቱ በታች ካለው መንበር [ከርሠ ሐመር ይሉታል] ቁጭ ብሎ ይጫወታል::

ያየ ሁሉ "ዕጹብ ዕጹብ" ሲልም አደነቀ:: ምክንያቱም በተፈጥሮ ሥርዓት ሕጻን ልጅ ያለ ምግብ ፫ ቀን መቆየት ስለማይችልና ሕጻኑ በዚያ የቅድስና ሥፍራ ላይ ምንም ሳይጸዳዳ በመገኘቱ ነው::

ብጹዕ ዓምደ ሚካኤል ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እየተማረ: በጾምና በጸሎት አደገ:: በ፲፭ኛው ክ/ዘመን አጋማሽ ላይ ንጉሥ የነበረው ጻድቁ አፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅዱሱን የሠራዊት አለቃ [ራስ ቢትወደድ] : ወይም በዘመኑ አገላለጽ የጦር ሚኒስትር አድርጐ ሾመው::

መቼም እዚህ ቦታ ላይ ተቀምጦ መልካምን መሥራት ልዩ ነገርን ይጠይቃል:: በተለይ ደግሞ በዙሪያው የሚከቡትን ተንኮለኞች ድል መንሳቱ ቀላል አልነበረም:: ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ግን በዘመነ ሲመቱ እነዚህን ሠራ:-

፩. በጠዋት ተነስቶ ነዳያንን ይሰበስብና ቁርስ: ምሳ ያበላቸዋል:: ይሕም ዕለት ዕለት የማይቁዋረጥ በመሆኑ ሃብቱ አልቆ ደሃ ሆነ::

፪. ከቀትር በሁዋላ ዘወትር ቆሞ ያስቀድስና ጸበል ተጠምቆ ይጠጣል:: ማታ ብቻ እህልን ይቀምሳል::

፫. ሽፍታ ተነሳ ሲባል ወደ ዱር ወርዶ: ጸልዮ: ሽፍታውን አሳምኖት ይመጣል እንጂ አይጐዳውም::

፬. ጦርነት በሚመጣ ጊዜ ክተት ሠራዊት ብሎ ይወርዳል:: ግን ለምኖ: ጸልዮ: ታርቆ ይመጣል እንጂ ጥይት እንዲተኮስ አይፈቅድም ነበር::

በዚህ መንገድ በ፫ቱ ነገሥታት [በዘርዐ ያዕቆብ: በዕደ ማርያምና እስክንድር] ዘመን ሁሉ አካባቢውን ሰላም አደረገው:: ዓለም ግን ዓመጸኛ ናትና በአፄ እስክንድር ዘመን (በ፲፬፻፸ዎቹ) በሃሰት ተከሶ ስደት ተፈረደበትና ወደ በርሃ ተጋዘ::

በዚያም ቅዱስ ሚካኤል ሰማያዊ መናን እየመገበው: ሥጋ ወደሙን እያቀበለው ኖረ:: ትንሽ ቆይቶ ግን የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በንጉሡ አደባባይ ተገደለ:: ለ፴ ቀናትም በመቃብሩ ላይ የብርሃን ምሰሶ ወረደ በዚህም ንጉሡ በእጅጉ ተጸጸተ::


🕊  †   ቅዱስ ኪርያቆስ  †    🕊

ሊቅነትን ከገዳማዊ ሕይወት የደረበው ቅዱስ ኪርያቆስ የቆረንቶስ ሰው ሲሆን አበው "ጥዑመ ቃል - አንደበቱ የሚጣፍጥ" ይሉታል:: ገና በልጅነቱ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሲያነብ ከአንደበቱ ማማር: ከነገሩ መሥመር የተነሳ ከዻዻሱ እስከ ሕዝቡ ድረስ ተደመው ያደምጡት ነበር::

በወጣትነቱ ጣዕመ ዓለምን ንቆ ከቆረንቶስ ኢየሩሳሌም ገብቷል:: ቀጥሎም ወደ ፍልስጥኤም ተጉዞ የታላቁ አባ ሮማኖስ ደቀ መዝሙር ሁኖ መንኩሷል:: በገዳሙ ለበርካታ ዘመናት ሲኖርም እጅግ ብዙ ተአምራትን ሠርቷል::

Debtera Media

11 Nov, 21:56


በ፫፻፹፩ ዓ/ም መቅዶንዮስ: አቡሊናርዮስና ሰባልዮስ በካዱ ጊዜም ለጉባኤው ወደ ቁስጥንጥንያ ከሔዱ ሊቃውንት አንዱ ይሔው ቅዱስ ኪርያቆስ ነው:: ወደ ጉባኤው የሔዱትም ከታላቁ ሊቅና የኢየሩሳሌም ሊቀ ዻዻሳት ቅዱስ ቄርሎስ መንፈሳዊ ጋር ነው::+ሁለቱ እጅግ ወዳጆች ነበሩና:: በጉባኤውም መናፍቃንን ረትተው: ሃይማኖትን አጽንተው: ሥርዓትን ሠርተው ተመልሰዋል:: ቅዱስ ኪርያቆስም በተረፈ ዘመኑ በቅድስና ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል:: አምላከ አበው የወዳጆቹን የቅድስና ምሥጢር ለእኛም ይግለጽልን:: በረከታቸውንም አትረፍርፎ ይስጠን::

[ ኅዳር ፫ [ 3 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ጻድቅ [ዘደብረ በንኮል]
፪. ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ጻድቅ [የሠራዊት አለቃ]
፫. ቅዱስ ኪርያቆስ ሊቅ
፬. ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ንጉሥ [ልደቱ]
፭. ቅዱሳን አትናቴዎስና እህቱ ኢራኢ [ሰማዕታት]
፮. አቡነ ፍሬ ካህን

[ ወርኀዊ በዓላት ]

፩. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው [ዘካርያስና ስምዖን]
፬. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ
፭. አቡነ ዜና ማርቆስ
፮. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ [ዓምደ ሃይማኖት]

"በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል::" [ምሳሌ.፲፥፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

11 Nov, 17:36


                       †                       


አጽናኑ ፥ ሕዝቤን አጽናኑ ❞ [ ኢሳ.፵፥፩ ]


❝ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ፥ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ። ❞ [ መዝ.፳፯ ፥ ፲፬ ]

በሌላ ስፍራም

❝ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ ፤ አበረታሃለሁ ፥ እረዳህማለሁ። ❞ [ ኢሳ.፵፩ ፥፲ ]


💖                    🕊                     💖

Debtera Media

11 Nov, 15:58


                          †                          

💖  [    የትሕርምት ሕይወት !    ]  💖

🕊                      💖                      🕊

[   በፈተና መጽናትን በተመለከተ  !   ]

------------------------------------------------

በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል !

" ተወዳጆች ሆይ በሰው ፊት በአግባቡ ተመላለሱ ፤ በእግዚአብሔርም የበረታችሁ ሁኑ፡፡ እርሱ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፡፡

ተወዳጆች ሆይ ! ሰዎች ከቤተሰቦቻችሁ ስለምትወርሱት ሀብት ያነሱባችሁ እንደሆነ ፦ “አንተ ሰነፍ ፥ በዚች ሌሊት ነፍስህን ከአንተ ሊወስዱአት ይፈልጓታል ፤ ይህስ የሰበሰብኸው ለማን ይሆናል?” ተብሎ ተጽፎአል በሏቸው፡፡ [ሉቃ.፲፪፥፳]

ጨምራችሁም ፦ “ብልሃተኞች እንዲሞቱ ፥ ሰነፎችና ደንቆሮች በአንድነት እንዲጠፉ ፥ ገንዘባቸውንም ለሌሎች እንዲተዉ አይቶአል” ተብሎ ተጽፎአል በሏቸው፡፡ ስለዚህ ገንዘብ መውደድ ለእኔ ጥፋትና የኃጢአት ሥር ነው፡፡

ጌታችንም ፦ “ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትስብስብ፡፡ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ ፤ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” ብሎ አስተምሮኛል በል” ብሎ ይመክራል፡፡ [ማቴ.፮፥፲፱]  "

🕊

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  ]


🕊                        💖                    🕊

Debtera Media

11 Nov, 14:49


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[            ክፍል  ሠላሳ አምስት          ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[  የአጋዘን ግልገሎችን እንደ ፈወሰ !  ]

                         🕊                         

❝ አባ መቃርዮስ እንዲህ አለ ፡- “ አንድ ወቅት በበረሓው የሰሌን ቅርንጫፍ እየሰበሰብኩ ሳለ አንዲት አጋዘን ወደ እኔ መጣችና ፀጉሯን እየነጨች ዕንባዋ ወደ መሬት እስኪወርድ ድረስ ታለቅሳለች፡፡ ራሷን መሬት ላይ ጥላ ከእግሬ ጫፍ ላይ ወድቃ በዕንባዋ እግሬን አራሰችው፡፡ እኔም በዕንባዋ መፍሰስና በሁኔታዋ ተገርሜ ቁጭ አልኩና ፊቷን ዳስሼ በእጆቼ ቀባኋት ፣ እርሷም ትኩር ብላ ታየኝ ነበር፡፡ ከዚያም አጽፌን ያዘችና ትጎትተኝ ጀመር፡፡ እኔም ተከተልኳት፡፡

“ወደ ምትኖርበት በወሰደችኝ ጊዜ በዚያ ሦስት ልጆቿ ተኝተው አገኘሁ፡፡ ቁጭ ባልሁ ጊዜ እነዚያን ልጆቿን በየተራ እያመጣች ጭኔ ላይ አደረገቻቸው፡፡ በነካኋቸው ጊዜም አካላቸው የተበላሸና ችግር ያለበት መሆኑን ተረዳሁ ፣ ፊታቸው ወደ ኋላቸው የዞረ ነበር፡፡ እናታቸው እያለቀሰች ነበር ፡ እኔም አሳዘኑኝና እንዲህ እያልሁ ስለ እነርሱ ወደ አምላኬ ጮኽኩ ፡-

'እጅግ ብዙ የሆነ የምሕረት መዝገብ ያለህና ለፍጥረቱ ሁሉ የምታስብ አምላክ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እባክህ በፈጠርካቸው ፍጥረታትህ ላይ ምሕረትህን አድርግላቸው ፤ እዘንላቸው፡፡ በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እነዚህን ቃላት በዕንባ ሆኜ በተናገርኩ ጊዜ እጆቼን ዘርግቼ በአጋዘኗ ልጆች ላይ አዳኝ የሆነ የመስቀልን ምልክት አደረግሁ [ አማተብሁ ] ፣ ያን ጊዜም ተፈወሱ፡፡ ከጭኔ ባወረድኳቸው ጊዜ እናታቸው ወዲያውኑ ተቀበለቻቸውና ትንከባከባቸው ጀመረች፡፡

እነርሱም ወደ ጡቶቿ ሄደው ይጠቡ ጀመር፡፡ እርሷም በእነርሱ መፈወስ እጅግ በጣም ደስ አላት፣ በታላቅ ደስታ ሆና ዓይን ዓይኔን ትክ ብላ ትመለከተኛለች፡፡ እኔም ለእኔ ባደረገው ቸርነትና ለሚያስብላቸው ለሌሎች እንስሳትም ባለው መጋቢነት እግዚአብሔርን አደነቅሁ፡፡ እግዚአብሔርን ስለ ደግነቱና ቸርነቱ ፣ ለእያንዳንዱ ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ስላለው የቸርነት ብዛት እያመሰገንሁ ተነሥቼ ሄድኩ፡፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

11 Nov, 08:26


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[     የሦስቱ ፈቃድ አንድ ነው እንጂ !     ]

🕊

❝ ከሁሉ አስቀድሞ በአካል ልዩ በክብር አንድ የሚሆን ሦስትነትን እናስተምራለን ፥ እሊህም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው ፤ ሥላሴ በመለኮት አንድነት መለየት የለባቸውም ፤ አካላት ግን በባሕርይ መለየት ሳይኖር እያንዳንዱ አካል በገጽ ፥ በመልክ ፍጹም ነው።

ለአብ የአባትነት ስም ፤ የአባትነት ክብር አለው ፤ ለወልድም በባሕርይ ክብሩ ከአብ ሳያንስ የልጅነት ስም ፤ የልጅነት ክብር አለው ፤ መንፈስ ቅዱስም እንዲህ በክበር አይለይም ፤ ነገር ግን ተለውጦ አብ ወልድ አይባልም ፤ በዚህ ጊዜ ተገኘ አይባልም ፤ በመለኮት እንደ አብ እንደ ወልድ ነው እንጂ ፤ እስትንፋሳቸው ነውና ሦስቱም ትክክል ናቸውና።

ማንም ማን የጌትነታቸውን ነገር መፈጸም አይችልም ፤ የሦስቱን አካላት ባሕርይ ይለይ ዘንድ ማንም ማን አይድፈር ፤ ሦስቱን አንድ የሚያደርጋቸው ባሕርይ አንድ ነው እንጂ።

ዳግመኛም በየስማቸው በየገጻቸው ሦስቱን አካላት እንወቅ ፤ ከመለኮት ባሕርይ የተለየ አካል የለም ፤ በአካላትም በማይመረመር ክብር መለየት የለም ፤ የሦስቱ ሥልጣን የሦስቱ ፈቃድ አንድ ነው እንጂ። ❞

[      ቅዱስ ኤጲፋንዮስ      ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

10 Nov, 15:48


                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞

[ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]

               [   ክፍል - ፴፫ -    ]

          💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                        👇

Debtera Media

10 Nov, 11:43


                        †                     

[   🕊  እርሷ የሕይወት በር ናት ! 🕊  ]

❝ ኩላዊት ቤተ ክርስቲያን በዓለሙ በሙሉ የተቀበለችው እምነት አንድ ነው፡፡ ስለዚህ እውነትን ከራሳችን ቤተ ክርስቲያን እንጂ ከሌሎች መፈለግ አይኖርብንም።

ሐዋርያት ገንዘቡን በባንክ እንዳስቀመጠ ሀብታም ሰው በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስቀምጠውልናል፡፡ ከዚህ መዝገብ የሚፈልግ ሁሉ ከሕይወት ውኃ እየቀዳ ገንዘቡ ሊያደርገው ተፈቅዶለታል:: ውርሱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፤ ኑዛዜው የመድኅን ክርስቶስ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ሐዋርያት ፣ አሰረ ፍኖታቸውን ተከትለው የተጓዙ ሐዋርያነ አበውና ሊቃውንት ሁሉ ነው፡፡

እርሷ የሕይወት በር ናት። ሌሎች ሌባና ወንበዴዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በእውነተኛ ትምህርታችን ልናስወግዳቸው ያስፈልጋል። ለቤተ ክርስቲያን ጠቃሚ የሆነውን ነገር እንመርጣለን፡፡ እርሱም እውነትን ገንዘብ የማድረግ በርሱም የመጓዝ ትውፊት ነው:: ❞

[   ቅዱስ ሄሬኒዎስ    ]


💖                    🕊                     💖

Debtera Media

10 Nov, 07:50


                       †                        

  [    🕊    ክብርት ሰንበት     🕊   ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

❝ ወዮ ይህች ዕለት ያረጀችዋ ያለፈችባት አዲሲቱ የጸናችባት ናት ፤ ወዮ ይህች ዕለት እስረኞች [ ነፍሳት ] የተፈቱባት ባሮች [ ደቂቀ አዳም ] ነጻ የወጡባት ናት። ወዮ ይህች ዕለት የፈረሰ የታነጸባት ሰይጣንም የጠፋባት ናት።

ዳግመኛም ይህች ዕለት በምትሠለጥንበት ጊዜ [ አመ ትሰፍን ወይም ለዘለዓለም ጸንታ በምትኖርበት ጊዜ ] አዲስ ሥራ አዲስ ነገርም ይሆናል ፤ ያን ጊዜ የፀሐይና የጨረቃ የከዋክብትም ብርሃን ፣ ወይም ፀዳል [ ማንም ዓይነት ብርሃን ] ፣ ክረምት ወይም በጋ የለም።

ክብርት የምትሆን ይህች ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ ! እንደ አብ የሠለጠነች እንደ ወልድ የምትገዛ እንደ መንፈስ ቅዱስ [ ለዘለዓለም ] የምትኖር ናት ፤ ይህች ቅድስት ሰንበተ ክርስቲያን ምን ትደንቅ ! ከአምላካችን ከእግዚአብሔር ዘንድ ለምኝልን ፣ ስለኛም አማልጂ ለዘለዓለሙ ! ❞

[ ቅዱስ ያሬድ ]

                           †                          


❝ አንተ ግን ከሆድ አውጥተኸኛልና ፥ በእናቴ ጡት ሳለሁም በአንተ ታመንሁ። ከማኅፀን ጀምሮ በአንተ ላይ ተጣልሁ ፤ ከእናቴ ሆድ ጀምረህ አንተ አምላኬ ነህ። ❞

[ መዝ.፳፪፥፱ ]

    [   🕊  ክብርት ሰንበት !  🕊   ]


†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Debtera Media

09 Nov, 22:53


🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †  

†  ኅዳር ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   †


🕊  †    ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ   †    🕊

ሃገራችን ኢትዮዽያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት:: በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጐልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው::

ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው::

- እርሱ ንጉሥ ነው: ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው::
- ሁሉ በእጁ ነው: እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው::
- እርሱ የጦር መሪ ነው: ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም::

- እርሱን 'ወደድንህ: ሞትንልህ' የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት:: ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት ክርስቶስ ነበር::
- የሃገር መሪ: የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ [busy] ነው:: ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም::

እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት [ለመሳለም] እንኳ 'ጊዜ የለኝም' ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል: ያንጽ: በክህነቱ ያገለግል: ማዕጠንት ያጥን: ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር::

እኛ 'ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል' ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ: ጦር በፊት: በኋላ: በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውሃ በምድር ላይ ፈሷል:: ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮዽያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው::

"ለመሆኑ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ማን ነው?"

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ ፲፩ ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም ፪ኛ ነው:: እርሱን በ፲፪ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ [ገብረ ማርያም] እና መርኬዛ ናት:: ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው::

እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር:: ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ [ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ] ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች:: ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው::

እዚያው ላይም 'ነአኩቶ ለአብ' [አብን እናመስግነው] ስትል ስም አወጣችለት:: ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ::

የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ [ቅድስት መስቀል ክብራ] ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ:: በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና:: ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው ፴ ደረሰ::

በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ:: ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት:: ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ::

በውስጡም በ፬ አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው:: ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር: ቅዳሴ ሲቀድስ: በጾም ይውላል:: ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቁዋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል::

ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል:: ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል:: እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል:: በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ: እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር:: እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና::

ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር:: በተለይ በ፲፪፻፲፩ አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት:: እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት: ይቀድስባትም ነበር::

ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ:: እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መወጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት:: በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን [አሸተን] ማርያም" ስትባል ትኖራለች::

ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው:: ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ፴ ዓመቱ ነው:: ለ፵ ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ ፸ ዓመት ሞላው:: በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ሰላምታንም ሰጠው::

"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ፵ ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም:: ከፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና:: የሚያከብርህን አከብረዋለሁ:: ደጅህን የሳመውን: ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን: መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::

ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው:: እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጸበል ይንጠበጠባል:: ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን:: ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና::

ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል:: የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር ፩ ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ፫ ነው ይላሉ:: በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል::

አምላከ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከበረከቱም አትረፍርፎ ይስጠኝ::

🕊

[ ኅዳር ፩ [ 1 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮዽያ]
፪. ቅዱሳን መክሲሞስና ባልንጀሮቹ [ሰማዕታት]

[ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ
፪. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
፫. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት
፬. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
፭. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር


"ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን: ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን:: ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን::" [ሮሜ.፮፥፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

09 Nov, 18:13


                           †                           

      [   🕊 ድንግል ሆይ ፦  🕊    ]  

🌼▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🌼

🌹 ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ 🌹

🕊

❝ ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር ❞


[ የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው ፤ እነሆ የተወደደ [ መልካም ] ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ [ በዕቅፍሽ ] እንዲጠጋ [ እንዲደገፍ ፣ እንዲንተራስ ] በርሱ ዐማጽኚ፡፡ ]

[ አባ ጽጌ ድንግል [ ማህሌተ ጽጌ ] ]

🕊

" ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ! " [መሓ. ፯:፩]

†                       †                      †
💖                    🕊                   💖

Debtera Media

09 Nov, 16:56


                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞

[ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]

               [   ክፍል - ፴፪ -    ]

          💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                        👇

Debtera Media

09 Nov, 11:09


                        †                           

🕊    💖  ቅዱስ   ማርቆስ   💖    🕊

                         🕊                         

❝  አቤቱ የሐዋርያት ተከታዮቻቸው ስለኾኑ ስለ ሰባ ኹለቱ አርድእት ብለኽ በምሕረትኽ ዐስበኝ። ... ስለ እነርሱ ማረኝ ፤ እኔን አገልጋይኽንም በሀገራቸው ውስጥ ከነርሱ ጋር ዕድል ፈንታዬን ጽዋ ተርታዬን አድርግ ፤ አሜን።   ❞

[   ተአምኆ ቅዱሳን   ]

▬▬▬▬▬▬   ♱    ▬▬▬▬▬▬

        [        ከማርቆስ ወንጌል        ]

❝ ወደ ተራራም ወጣ ፥ ራሱም የወደዳቸውን ወደ እርሱ ጠራ ፥ ወደ እርሱም ሄዱ። ከእርሱም ጋር እንዲኖሩና ለመስበክ እንዲልካቸው ፥ ድውዮችንም ሊፈውሱ አጋንንትንም ሊያወጡ ሥልጣን ይሆንላቸው ዘንድ አሥራ ሁለት አደረገ፤ ❞ [ ማር . ፫ ፥ ፲፫ ] 

🕊

[  † እንኳን ከ፸፪ [ 72 ] ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]


🕊                        💖                      🕊

Debtera Media

08 Nov, 20:47


ከዚሕ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱስ ዮሐንስ ራስ የማስተማር ስልጣን ሰጥቶ አሰናበታት:: በመላው ዓለም ለ፲፭ ዓመታት ስትሰብክ ኑራ ዓረቢያ ውስጥ ዓርፋለች::

ይህች ዕለት ለቅዱሱ 'አስተርዕዮተ ርዕሱ' ወይም ቅድስት ራሱ ከተወረችበት የተገለጠችበት ነው::

🕊

ጥቅምት ፴ [ 30 ]ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

፩. ቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያ
፪. ቅዱስ አርስጥቦሎስ [አባቱ]
፫. ቅድስት ማርያም [እናቱ]
፬. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት
፭. አባ አብርሃም ገዳማዊ
፮. ቅዱስ ይስሐቅ ንጉሥ

ወርኃዊ በዓላት

፩. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት
፪. ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት
፫. አባ ሣሉሲ ጻድቅ

" ... እጅግ ሰዎች ተከማችተው ይጸልዩበት ወደ ነበረው ማርቆስ ወደ ተባለው ወደ ዮሐንስ እናት ወደ ማርያም ቤት መጣ:: ዼጥሮስም የደጁን መዝጊያ ባንኳኳ ጊዜ ሮዴ የሚሏት አንዲት አገልጋይ ትሰማ ዘንድ ቀረበች:: የዼጥሮስ ድምጽ መሆኑንም ባወቀች ጊዜ ከደስታዋ የተነሳ ደጁን አልከፈተችም:: ነገር ግን ወደ ውስጥ ሮጣ ዼጥሮስ በደጅ ፊት ቆሞ እንዳለ አወራች::" [ሐዋ.፲፪፥፲፪-፲፭]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †


[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

💖                  🕊                   💖

Debtera Media

08 Nov, 20:47


🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  †

† ጥቅምት ፴ [ 30 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †


🕊  †   ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ     †       🕊

በዚሕች ዕለት ከ፸፪ ቱ አርድእት አንዱ የሆነ: ወንጌላዊ: ሐዋርያ: ሰማዕት: ዘአንበሳና ርዕሰ ሊቃነ ዻዻሳት የተባለ ቅዱስ ማርቆስ ተወልዷል ::

ቅዱስ ማርቆስ እናቱ ማርያም: አባቱ አርስጥቦሎስ ይባላሉ:: በልጅነቱ ኦሪትንና የዘመኑን ጥበብ ሥጋዊ በሚገባ ተምሮ ክርስቶስን ከቤተሰቦቹ ጋር ተከትሏል:: የመጀመሪያ ስሙ ዮሐንስ ሲሆን ከ፻፳ው ቤተሰብ በእድሜ በጣም ትንሹ /፳ ዓመት/ እርሱ ነበር::

ለ፫ ዓመታት ከጌታ እግር ሥር ተምሮ: በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ብዙ ደክሟል:: በተለይ የግብፅና የኢትዮዽያ ቤተ ክርስቲያን አባት ነው:: ክህነትን ያገኘን ከርሱ ነውና::

ቅዱስ ማርቆስ ፲፮ ምዕራፍ ያለውን ወንጌሉን ሲጽፍ ኪሩብ ገጸ አንበሳ በቀኙ: ሊቀ ሐዋርያት በግራው ሆነው ይራዱት ነበር:: ቅዱሱ ክቅዱስ ዻውሎስ: ከበርናባስና ዼጥሮስ ጋር ተጉዟል:: ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ሰሜን አፍሪካ አካባቢ አረማውያን ገድለውታል:: ይህቺ ዕለት የልደቱ መታሠቢያ ናት::

ዳግመኛ በዚህ ቀን የቅዱስ ማርቆስን ወላጆችን እናስባቸው ዘንድ ይገባል:: ቅዱስ አርስጥቦሎስ [አባቱ] የጌታ ቅን አገልጋይ የነበረ: ቅድስት ማርያም [እናቱ] ከ፴፮ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ: ጌታችንን ያገለገለች ቤቷን ለሐዋርያትና ለጌታ በስጦታ ያበረከተች ቅድስት ናት::

ቤቷም [ጽርሐ ጽዮን] የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ይህች ቤት መንፈስ ቅዱስ ወርዶባታል:: የእመቤታችን ግንዘትም ተከናውኖባታል::

እግዚአብሔር ከሐዋርያዊው ቅዱስ ቤተሰብ በረከትን ያድለን::


🕊  †   ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ    †     🕊

ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የነዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ ወንጌሉን የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ሉቃ.፩፥፮]

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ [አድናቆት] ይገባል!
እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ የዘካርያስ ፻ ደግሞ ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በኋላ በዚህች ቀን [ሰኔ ፴] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ ዓመት ከ፮ ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕጻናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕጻን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕጻን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕጻኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ፫ [፭] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [፯] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕጻኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [፳፫] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ ፴ ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጀን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሃ ሰበከ: ለንስሃም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ፮ ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ 'አጥምቀኝ' ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

"እንቢ ጌታየ! አንተ አጥምቀኝ" አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ ቀናት አሠረው::

በዚህች ቀንም ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩, ማር.፮፥፲፬, ሉቃ.፫፥፩, ዮሐ.፩፥፮]

ርጉም ሔሮድስ አንገቱን ካስቆረጠው በኋላ የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራሱ የጸጋ ክንፍ ተሰጥቷት ጌታችን ወዳለበት ደብረ ዘይት ሔዳ በፊቱ ሰገደች:: ቅዱሳን ሐዋርያት በአዩት ነገር ተገርመው ራሱን እጅ ነሷት::

Debtera Media

08 Nov, 17:49


                        †                        

[    🕊  እናታችን ማርያም   🕊    ]

" ኢየሱስም እናቱን ይወደው የነበረውንም ደቀ መዝሙር በአጠገቡ ቆሞ ባየ ጊዜ እናቱን። አንቺ ሴት ፥ እነሆ ልጅሽ አላት። ከዚህ በኋላ ደቀ መዝሙሩን። እናትህ እነኋት አለው። ከዚህም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝሙሩ ወደ ቤቱ ወሰዳት።"

[ ፲፱፥፳፭-፴ ]

🕊

[ ጻድቅ ሰው ፍርድ ሲመለስ ባየ ጊዜ ደስ እንዲለው ፤ ጠላትን [ አጋንንትን ] በመበቀል የታምራትሽን ኃይል ግለጪ አሳዪ፡፡ የአምላክ እናት ማርያም አንቺን የሰደበ እንዴት በሕይወት ሊኖር ይገባዋል? በእናት በአባቱ ላይ ክፉ ቃልን የተናገረ በልጅሽ ፍርድ ይሙት ተብሏልና፡፡ (ዘዳ.፳፯፥፲፮) ]
                
[ አባ ጽጌ ድንግል ]

†                       †                        †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

08 Nov, 15:42


                          †                          

💖  [    የትሕርምት ሕይወት !    ]  💖

🕊                      💖                      🕊

[     በፈተና መጽናትን በተመለከተ  !    ]

አጋንንት እንደ ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው  !

" ሰዎች ከዚህ ዓለም አስተሳሰብ ወጥተው ስለ ሰማያዊው ሕይወታቸው መጨነቅ ሲጀምሩ ለመንፈሳዊው ሕይወት የምናደርገውን ተጋድሎ አጋንንት መቋቋም ሲያቅታቸው የሰውን አእምሮ በልዩ ልዩ ሐሳቦች እንዲረበሽ በማድረግ ሰውን ከመንፈሳዊው ተጠምዶው ለማውጣት አቅደው ይንቀሳቀሳሉ፡፡

ለዚህ የተዘጋጀ በእምነቱ ያልጠነከረ እና ተጠራጣሪ ሰው ካገኙ ግን ከመንገዱ ያስቱታል፡፡ ነገር ግን ከእነርሱ የመጣብንን ፈተና በጽናት ከታገልን እግዚአብሔር አምላክ እነርሱን ከእኛ አስወጥቶ ይሰዳቸዋል፡፡ እኛም እንደ አዲስ የወይን ጠጅ ሆነን በመንፈስ ቅዱስ ጣፍጠን እንገኛለን፡፡

አጋንንት እንደ ነጣቂ ተኩላዎች ናቸው፡፡ እነርሱ በትሕርምት ሕይወት ወደሚኖረው ተሐራሚ በአት ለመግባት ትንሽ ቀዳዳ እስከሚያገኙ ድረስ ያደባሉ፡፡ መግቢያ ቀዳዳን ሲያገኙ ፈጥነው በመግባትና አእምሮን በመለወጥ ነፍስን ወደ ጥፋት ይመሯታል፡፡

በዚህ ፈተና ውስጥ ያለ ተሐራሚ ግን አጋንንት ወደ እርሱ ይገቡ ዘንድ አንዳች ክፍተት ካልተወ ተስፋ በመቁረጥ ከእርሱ ይርቃሉ፡፡ ስለዚህ የአጋንንትን ውጊያ በመፍራት ከጽድቅ ሕይወት አትውጡ ፣ በኃጢአት ያሳድፉኛል ብላችሁም አትስጉ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናንተን ይረዳችኋል ምንም ሊጎዷችሁ አይቻለውም፡፡

እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “ እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና፡፡” [፪ጢሞ.፩፥፯] ጌታችንም ለሐዋርያት ፦ “ ሰይጣንን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ። እነሆ ፥ እባቡንና ጊንጡን ትረግጡ ዘንድ ፥ በጠላትም ኃይል ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጥቻችኋለሁ ፥ የሚጐዳችሁም ምንም የለም፡፡ [ሉቃ.፲፥፲፰] በማለት ከእንግዲህ በእኛ ላይ ስልጣን እንደሌላቸው አስተምሮናል፡፡ "

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  ]


🕊                        💖                    🕊

Debtera Media

08 Nov, 12:12


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[               ክፍል  ሠላሳ አራት             ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[ ድውያንን መፈወሱና ሙት ማስነሣቱ ! ]

                         🕊                         

............. በልቡ ይጸልይ ነበር ! ..........

❝ ወደ ቅዱስ መቃርዮስ የተለያዩ በሽተኞችን ከግብጽ ሀገር ብቻ ሳይሆን ከተለያዩ ሀገሮችም ያመጧቸው ነበር፡፡ እርሱም አስቀድሞ ቅዱስ እንጦንዮስ ፦ “ እግዚአብሔር ለአባት መቃርዮስ የመፈወስ ጸጋን ሰጥቶታል ” ብሎ እንደ ተናገረ ሁሉንም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ይፈውሳቸው ነበር፡፡ ሁል ጊዜ በበኣቱ ዙሪያም በሽተኞችና ርኲሳን መናፍስት ያለባቸው ሰዎች አይጠፉም ነበር፡፡ እርሱም እውነተኛ አምላክ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሲጸልይላቸው ሁሉንም በሽተኞች ይፈውሳቸውና ርኲሳን መናፍስትንም ያሳድዳቸው ነበር፡፡ ሌሎች የተለያየ በሽታ ያለባቸውንና የአእምሮ በሽተኞችን ሁሉ በኃይለ እግዚአብሔር እየፈወሳቸው እነርሱም እግዚኣብሔርን እያመሰገኑ ወደየ መጡበት ይመለሱ ነበር፡፡ ሙታንንም ያስነሣ ነበር ፤ በአጠቃላይ ቅዱስ መቃርዮስ በአምላኩ ኃይል ሊያደርገው ያልቻለው ነገር አልነበረም፡፡

መስማት የተሣነውንና አንደበቱ ዲዳ የሆነውን ፈወሰው

በአንድ ወቅት ርኲስ መንፈስ ያደረበትንና አንደበቱ ዲዳ የሆነ ምንም የማይናገርን ሰው ወደ እርሱ አመጡት፡፡ ያ ሰውም ከታሰረበት ገመድ በተፈታ ጊዜ በሚያገኘው ሰው ሁሉ ላይ ጉዳት ለማድረስ ያስቸግር ነበር፡፡ ወደ እርሱ ባመጡት ጊዜም ቅዱስ መቃርዮስ ይዘው ያመጡትን ሰዎች ፦ “ ተውት ልቀቁት ” አላቸው፡፡ እነርሱም ፦ “ አባታችን ሆይ ፣ ከለቀቅነውማ በዚህ በተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ላይ ጉዳት ያደርሳል” አሉት፡፡ እርሱም ፦ “ዳግመኛ እኔ የምላችሁን ስሙ ፣ ልቀቁት ” አላቸው፡፡ በለቀቁት ጊዜም ታስሮበት የነበረውን ሰንሰለትና ገመድ ራሱ ፈታው፡፡ ከዚያም በኃይል እየጮኸ ወደ ተራራ ይሮጥ ነበር፡፡ ያመጡት ሰዎችም ቅዱስ መቃርዮስን ፦ " አባታችን ሆይ ፣ እነሆ አሁን ሁላችንንም ሊያጠፋን ነው” አሉት፡፡ እርሱም ፦ “አትፍሩ ኣይዟችሁ” ብሏቸው በልቡ ይጸልይ ነበር። በሽተኛውም በተራራው ላይ ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይዘዋወር ነበር፡፡

እንዲያ ከዞረ በኋላ ተመልሶ ወደ ቅዱስ መቃርዮስ መጣ፡፡ አባት መቃርዮስም ፦ “ስምህ ማነው?” አለው ፤ ርኲስ መንፈሱም ፦ “ስሜን ትጠይቃለህን ? ሌጌዎን ነኝ ፣ ብዙዎች ነን” አለው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ፦ " የሁሉ አምላክ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አሁን ከዚህ ሰው ውጣ ፤ ወደ እርሱም መቼም ቢሆን ፈጽመህ አትግባ ፤ አምላኬ እንዲህ ያዝሃልና” አለው፡፡ ያን ጊዜም ያ ሰው መሬት ላይ ተዘረጋ ፣ እንደ ሞተ ሰውም ሆነ፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ጸሎት ያደረገበትን ውኃ በፊቱ ላይ ረጨው፡፡ በጆሮውና በአፉ ላይ በመስቀል ምልክት አማተበ ፣ ከዚያም ትንሽ ይተኛ ዘንድ ተወው፡፡ በዘይት ላይ በመጸለይ ሰውነቱን ቀባውና “ወደ ማደሪያህ ሂድ” አለው:: በተነሣ ጊዜም ከደዌው ሁሉ ተፈውሶ መስማትና መናገር የሚችል ሆነ ፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግን ነበር፡ ፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

08 Nov, 08:25


🕊                      †                        🕊

[ ተዋሕዶ ፍጽምት የቅዱሳን ሃይማኖት ]
▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ እምነታችንም በዕሩቅ ብእሲ አይደለም ! ]

🕊

ድኅነታችንም በዕሩቅ ብእሲ አይደለም ፥ እምነታችንም በዕሩቅ ብእሲ አይደለም ፥ መጽሐፍ በዕሩቅ ብእሲ የሚያምን ርጕም ይሁን ብሏልና" [ዘዳግ.፳፯፥፲፭]

ክርስቶስ ዕሩቅ ብእሲ እንደሆነ ስለሚናገሩ ሰዎች ምን እንላለን ? እርሱ እግዚአብሔር ቃል እንደሆነ በሁሉ ዘንድ የታወቀ የተረዳ ሲሆን ፥ እኛ ግን እግዚአብሔር ቃል ሰው እንደ ሆነ ያለመጠራጠር እናምንበታለን ፥ በእውነት ሰው ኾነ እንጂ በሐሰት አይደለም

ዕሩቅ ብእሲ ሆኖ ከዚህ በኋላ መለኮት ያደረበት አይደለም ፥ አለኝታችን ደኅንነታችን ከዕሩቅ ብእሲ የተገኘ አይደለም።

ከአዳም ጀምሮ እስከ ዛሬ ከተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ማንም ማን ሊያድነን አልቻለም ፤ ከእግዚአብሔር ቃል በቀር ፥ በሰው ቢሆን አለኝታችን ከንቱ እንዳይሆን የባሕርይ አምላክ እርሱ ሰው ኾነ እንጂ። ❞

[      ቅዱስ ኤጲፋንዮስ      ]

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፤ ወለወላዲቱ ድንግል ፤ ወለመስቀሉ ክቡር። አሜን።


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

07 Nov, 20:12


" በእሸቅድምድም ሥፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ: ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ:: የሚታገልም ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል:: እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው:: እኛ ግን የማይጠፋውን::" [፩ቆሮ.፱፥፳፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

07 Nov, 20:12


🕊

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ †

[  እንኩዋን ለአበው ቅዱሳን "ሳሙኤል ዘወገግ": "ጸቃውዐ ድንግል" እና "ድሜጥሮስ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።   ]


🕊  † አባ ሳሙኤል ዘወገግ  †  🕊

ሃገራችን ኢትዮዽያ ማኅደረ ቅዱሳን [ምዕራፈ ቅዱሳን] እንደ መሆኗ ፍሬ ክብር: ፍሬ ትሩፋት ያፈሩ ብዙ አባቶችና እናቶችን አፍርታለች:: ብርሃን ሁነው ካበሩላት ቅዱሳን መካከል አንዱ ደግሞ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::

በእኛው ሃገር ብቻ ብዙ "ሳሙኤል" የሚባሉ ቅዱሳን በመኖራቸው ስንጠራቸው "ዘእንትን" እያልን ነው:: ለምሳሌም:

- ሳሙኤል ዘዋሊ
- ሳሙኤል ዘወገግ [የዛሬው]
- ሳሙኤል ዘጣሬጣ
- ሳሙኤል ዘቆየጻ
- ሳሙኤል ዘሃሌ ሉያና
- ሳሙኤል ዘግሺን መጥቀስ እንችላለን:: ሁሉም የመካከለኛው ዘመን ሐዋርያዊ አባቶች ናቸው::

ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ የተወለዱት በ፲፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው የብዙ ቅዱሳን ቤት የሆነችው ሽዋ ናት:: መንደራቸውም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ብዙም አይርቅም::

የጻድቁ ወላጆች እንድርያስና አርሶንያ የሚባሉ ሲሆን ደጐች ነበሩ:: ጻድቁ በተወለደ ጊዜ የቤታቸው ምሰሶ ለምልሞ ተገኝቷል:: አቡነ ሳሙኤል ከልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው በጉብዝናቸው ወራት ይህችን ዓለም ንቀዋል::

የታላቁ ጻድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው በደብረ ሊባኖስ መንነዋል:: ከ፲፪ቱ ኅሩያን [ምርጦች] አርድእት አንዱ ነበሩና በክህነታቸው ደብረ ሊባኖስን ተግተው ያጥኑ ነበር:: በዚያውም በንጹሕ ልቡና በጾምና ጸሎት ይተጉ ነበር::

አቡነ ተክለ ሃይማኖት ካረፉ በሁዋላ በደጉ ዻዻስ በአቡነ ያዕቆብ ዘመን ፲፪ቱ ንቡራነ እድ ተመረጡ:: እነዚህ አባቶች በወንጌል አገልግሎት: በተለይ ደቡብና ምሥራቁን የሃገራችን ክፍል ያበሩ ናቸው:: ቅዱሳኑ ሲመረጡም ከአቡነ ፊልዾስ ቀጥለው በ፪ኛ ደረጃ የተመረጡ አቡነ ሳሙኤል ዘወገግ ናቸው::

ሃገረ ስብከታቸውም ሐረርና ሱማሌ ነበር:: ጻድቁ በሃገረ ስብከታቸው ወርደው በሐረርና ሱማሌ አካባቢ ለዘመናት የወንጌልን ዘር ዘርተው እልፍ ፍሬን አፍርተዋል:: አካባቢውንም መካነ ቅዱሳን አድርገውታል::

ቀጥለው ገዳማዊ ሕይወትን ያጸኑ ዘንድ በምሥራቁ የሃገራችን ክፍል በአፋር ሱባኤ ገቡ:: ቦታውም ደብር ሐዘሎ ነበር:: በቦታው ለ፻፶፭ ቀናት ከቆሙ ሳያርፉ: ከዘረጉ ሳያጥፉ: እህል ውሃ ሳይቀምሱ ጸለዩ::

በሱባኤያቸው ፍጻሜ ግን ቅዱስ መልአክ መጥቶ "ሳሙኤል ወደዚያ ተራራ ሒድ:: የስምህ መጠሪያ እርሱ ነውና:: ይህ ግን የሌላ ሰው [የአባ አንበስ ዘሐዘሎ] ርስት ነው" አላቸው:: ጻድቁም ወዳላቸው ተራራ ሒደው ቢጸልዩ ከሰማይ ብርሃን ወረደላቸው::

በመንፈቀ ሌሊት የበራው ብርሃን እስከ ጐረቤት መንደር ሁሉ በመድረሱ የአካባቢው ሰው "ወገግ አለኮ-ነጋ" ብለውዋል:: በዚህ ምክንያት ዛሬም "ደብረ ወገግ" ይባላል:: ይህ ቦታ ዛሬም ድረስ ንጹሕ ልብ ላላቸው አበው በብርሃን ተከቦ ይታያል::

ጻድቁ የወለዷቸው ብዙ ሥውራንም በሥፍራው ይገኛሉ:: ቦታው የአንበሶች መኖሪያ በመሆኑ ጠላት መናንያኑን ማጥቃት አይችልም:: ሳሙኤል ዘወገግም የሚጸልዩት በአናብስት ተከበው ነበር:: በቦታው አንዳንዴም አንበሶች ሲሰግዱ ይታያል ይባላል:: ጻድቁ አቡነ ሳሙኤል ግን እንዲህ በቅድስና ተመላልሰው በ፲፬ኛው መቶ ክ/ዘመን ሱማሌ ክልል ውስጥ በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: የጻድቁ ልደት ሐምሌ ፱ : ፍልሠታቸው ደግሞ ግንቦት ፳፯ ነው::


🕊 † አባ ጸቃውዐ ድንግል † 🕊

እኒህ ጻድቅም ኢትዮዽያዊ ናቸው:: የስማቸው ትርጉም "የድንግል ማርያም ወለላ ማር" ማለት ሲሆን ዜና ሕይወታቸው እንደ ስማቸው ጣፋጭ ነው::

የእኒህ ጻድቅ አባታቸው የተመሰከረላቸው ሊቅና የገዳም መምሕር ናቸው:: ምክንያቱም ጸቃውዐ ድንግልን ከወለዱ በሁዋላ መንነዋልና:: አባት የደብረ ዘኸኝ መምሕር ሳሉ ልጃቸው ጸቃውዓ ድንግልን ወደ ገዳሙ ወስደው አሳደጉዋቸው::

በዚያውም ጾምና ጸሎትን: ትዕግስትና ትሕርምትን አስተማሯቸው:: ቅዱሳት መጻሕፍትንም በወጉ አስጠኗቸው:: አባ ጸቃውዐ ድንከግልም በጐውን የምናኔ ጐዳና ከተማሩ በሁዋላ መዓርገ ምንኩስናን ተቀበሉ::

፵ ዓመት ሲሞላቸው ግን አባታቸው ዐረፉ:: መነኮሳት አበውም ተሰብስበው "ከአንተ የተሻለ የለም" ሲሉ ጸቃውዐ ድንግልን የደብረ ዘኸኝ መምሕር አድርገው ሾሟቸው:: ጻድቁም ቀን ቀን ሲያስተምሩ ይውሉና ሌሊት ባሕር ውስጥ ሰጥመው ሲጸልዩ ያድሩ ነበር::

በሌሊትም ከባሕሩ ወጥተው የአካላቸው ርጥበት ደርቆ ላበታቸው እስኪንጠፈጠፍ ድረስ ይሰግዱ ነበር:: በዚህ መንገድም ራሳቸውን ገዝተው: መነኮሳትንም ገርተው ያዙ:: እግዚአብሔርም ክብራቸውን ይገልጽ ዘንድ ብዙ ተአምራትን በእጃቸው አሳይቷል::

አንድ ቀን አባ ጸቃውዐ ድንግል መንገድ ሲሔዱ ሁለመናው በቁስል የተመታ አንድ መጻጉዕ ነዳይ ወድቆ አዩ:: ወደ እርሱ ሲደርሱ ምጽዋትን ለመናቸው:: ጻድቁ ግን "የምሰጥህ ነገር የለኝም:: ግን የፈጣሪየን ስጦታ እሰጥሃለሁ" ብለው: በውሃ ላይ ጸልየው ረጩት::

ያ መጻጉዕም አካሉ ታድሶ: እንደ እንቦሳ ዘሎ ተነሳ:: ደስ እያለው: ፈጣሪውንም እያከበረ ወደ ቤቱ ሔዷል:: አባ ጸቃውዐ ድንግልም በዚህች ቀን ዐርፈው በገዳማቸው ተቀብረዋል::


🕊 † ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት † 🕊

ይህ ቅዱስ በዘመነ ሰማዕታት: በ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ከነበሩ ክርስቲያኖች አንዱ ነው:: ቅዱስ ድሜጥሮስ ስቅጣር ከሚባል ደግ ባልንጀራው ጋር በበጐው ጐዳና ሲኖሩ የመከራው ዘመን ደረሰ:: መወሰን ነበረባቸውና ፈጣሪያቸውን ከሚክዱ ሞትን መረጡ::

አስቀድሞም ሲያስተምር በመገኘቱ ቅዱስ ድሜጥሮስ በንጉሡ እጅ ወደቀ:: ንጉሡ መክስምያኖስም እሥራትን አዘዘበት:: በዚያ ወራት ደግሞ የንጉሡ ወታደር የሆነና በጣዖት የሚመካ አንድ ጉልበተኛ ነበር::

ማንም በትግል አሸንፎት ስለማያውቅ ጣዖታዊው ንጉሥ ይመካበት ነበር:: አንድ ቀን ግን አንድ ክርስቲያን ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቅዱስ ድሜጥሮስን "ባርከኝና ያንን ጣዖታዊ ጉልበተኛ እጥለዋለሁ" አለው::

የቅዱሱን ጸሎትና በረከት ተቀብሎም በንጉሡ አደባባይ ታግሎ ጣለው:: ንጉሡና የጣዖቱ ካህናትም በእጅጉ አፈሩ:: በሁዋላ ግን ይህንን ያደረገው ቅዱስ ድሜጥሮስ መሆኑ በመታወቁ ከባልንጀራው ቅዱስ ስቅጣር ጋር በዚህች ቀን ገድለዋቸዋል::

አምላከ አበው ቅዱሳን ጸጋ ክብራቸውን ያብዛልን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

🕊

[ † ጥቅምት ፳፱ [ 29 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አቡነ ሳሙኤል ጻድቅ [ዘደብረ ወገግ]
፪. አባ ጸቃውዐ ድንግል [ዘደብረ ዘኸኝ]
፫. ቅዱስ ድሜጥሮስ ሰማዕት
፬. ቅዱስ ስቅጣር ሰማዕት

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. የፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት
፪. ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
፬. ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
፭. ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ
፮. ቅድስት አርሴማ ድንግል

Debtera Media

26 Oct, 19:23


+ በሐረገ ትንቢቷም :-

"ኢይጻእ ዐቢይ ነገር እምአፉክሙ: እስመ እግዚአብሔር አምላክ ማዕምር ውዕቱ - እግዚአብሔር ሁሉን አዋቂ አምላክ ነውና ከአንደበታችሁ [ጽኑዕ] ነገርን አታውጡ" ስትል ተናግራለች:: [ሳሙ.፪፥፫] (2:3]

አምላከ ቅዱሳን የእስጢፋኖስን ጸጋ: የፊልያስን ማስተዋልና የሐናን በጐነት ያሳድርብን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

[  †  ጥቅምት ፲፯ [ 17 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት [ ወቀዳሜ ሰማዕት ]
፪. ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት
፫. ቅድስት ሐና ነቢይት
፬. ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘኑሲስ
፭. የደብረ ሊባኖስ ሰማዕታት [ካቶሊካውያን የገደሏቸው]
፮. ቅዱሳን ሔራን ሰማዕታት
፯. አባ ዲዮስቆሮስ ካልዕ

[   †  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ ዘብዴዎስ]
፪. ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ
፫. አባ ገሪማ ዘመደራ
፬. አባ ዸላሞን ፈላሢ
፭. አባ ለትጹን የዋህ
፮. ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ [ዘደሴተ ቆዽሮስ]

" እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር . . . አንዳንዶቹ ተነስተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር:: ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም:: በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ: በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሱ . . . በሸንጐም የተቀመጡት ሁሉ ትኩር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት::" [ሐዋ.፮፥፰-፲፭] (6:8-15)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

26 Oct, 19:23


🕊

[  እንኩዋን ለቅዱስ "እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት": ለቅዱስ "ፊልያስ" እና ለቅድስት "ሐና ነቢይት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ  ]


† 🕊 ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት 🕊 †

በሕገ ወንጌል [ክርስትና] የመጀመሪያው ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳሚው ሰማዕት ይህ ቅዱስ ነው:: ቅዱሱ በመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን አስገራሚ ማንነት ከነበራቸው እሥራኤላውያን አንዱ ነበር:: ይህስ እንደ ምን ነው ቢሉ :-

+ የቅዱስ እስጢፋኖስ ወላጆቹ ስምዖንና ማርያም ይባላሉ:: [ሌሎች ናቸው የሚሉም አሉ] ገና ከልጅነቱ ቁም ነገር ወዳድ የነበረው ቅዱስ በሥርዓተ ኦሪት አድጐ እድሜው ሲደርስ ወደ ት/ቤት ገባ:: የወቅቱ ታላቅ መምሕር ገማልያል ይባል ነበር:: ይህ ሰው በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ ፭፥፴፫ [5:33] ላይ ተጠቅሷል::

+ በትውፊት ትምሕርት ደግሞ ይህ ደግ [ትልቅ] ሰው በርካታ ቅዱሳንን [እስጢፋኖስን: ዻውሎስን: ናትናኤልን: ኒቆዲሞስን . . .] አስተምሯል:: በጌታችን መዋዕለ ስብከት ጊዜም ከፈጣሪያችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እየቀረበ ይጨዋወት ነበር:: በፍጻሜውም አምኗል::

+ ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና ቅዱስ እስጢፋኖስ ከዚህ ምሑር ዘንድ ተምሮ: ኦሪቱን ነቢያቱን ጠንቅቆ ወጣ:: ወቅቱ አስቸጋሪና ለኃጢአት ሕይወት የተመቸ ቢሆንም ቅዱሱ ግን የመሲህን መምጣት በጸሎትና በተስፋ ይጠባበቅ ነበር::

+ በወቅቱ ደግሞ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ የንስሃ ጥምቀትን እየሰበከ መምጣቱን የተመለከተ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነገሩን መረመረ:: ከእግዚአብሔር ሆኖ ቢያገኘው የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: ለ፮ [6] ወራትም በትጋት ቅዱስ ዮሐንስን አገለገለ::

+ ለ፮ [6] ወራት ከቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ከተማረ በሁዋላ ለስም አጠራሩ ስግደት ይድረሰውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተጠመቀ::
በወቅቱ የተደረገውን ታላቅ ተአምር ልብ ያለው ቅዱስ እስጢፋኖስ መምሕሩን ቅዱስ ዮሐንስን እንዲያስረዳው ጠየቀው::

+ "ከእኔ ይልቅ ከፈጣሪው አንደበት ይስማው" በሚል ላከው:: ቅዱሱም ከጌታ ዘንድ ሔዶ: እጅ ነስቶ ተማረ:: [ሉቃ.፯፥፲፰] (7:18) በዚያውም የጌታ ደቀ መዝሙር ሆኖ ቀረ:: ጌታም ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት አንዱ አድርጐት ለአገልግሎት ላከው:: አጋንንትም ተገዙለት:: [ሉቃ.፲፥፲፯] (10:17)

+ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን መድኃኔ ዓለም ከዋለበት እየዋለ: ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተማረ:: ምሥጢር አስተረጐመ:: ጌታ በፈቃዱ ስለ እኛ ሙቶ ከተነሳ በሁዋላ ሲያርግ ደቀ መዛሙርቱን በአንብሮ እድ ባርኩዋል::

+ በዚህ ጊዜም ቅዱሱ እንደ ወንድሞቹ ሐዋርያት ቅስናን [ዽዽስናን] ተሹሟል:: በበዓለ ሃምሳም መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት የእርሱን ያህል ልሳን የበዛለት: ምሥጢርም የተገለጠለት የለም:: በፍጹም ድፍረትም ወንጌልን ይሰብክ ገባ::

+ በመጀመሪያይቱ ዘመን ቤተ ክርስቲያን ከማዕድ ሥርዓት ጋር በተያያዘ ፈተና ሲመጣ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ፯ [7] ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: አልፎም የ፮ [6]ቱ ዲያቆናት አለቃ እና የ፰ [8]ሺው ማሕበር መሪ [አስተዳዳሪ] ሆኗል::

+ ፰ [8] ሺ ሰውን ከአጋንንት ፈተና መጠበቅ ምን ያህል ከባድ እንደ ሆነ ለማወቅ አባቶቻችንን መጠየቅ ነው:: አንድን ሰው ተቆጣጥሮ ለድኅነት ማብቃት እንኩዋ እጅግ ፈተና ነው:: መጽሐፍ እንደሚል ግን "መንፈስ ቅዱስ የሞላበት: ማሕደረ እግዚአብሔር" ነውና ለእርሱ ተቻለው:: [ሐዋ.፮፥፭] (6:5)

+ አንዳንዶቻችን ቅዱስ እስጢፋኖስ "ሊቀ ዲያቆናት" ሲባል እንደ ዘመኑ ይመስለን ይሆናል:: እርሱ በመጀመሪያ ሐዋርያና ካህን ነው:: ዲቁናው ለእርሱ "በራት ላይ ዳረጐት" ነው እንጂ እንዲሁ ዲያቆን ብቻ አይደለም::

+ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታ ዕርገት በሁዋላ ለ ፩ [1] ዓመት ያህል ፰ [8]ሺውን ማሕበር እየመራ: ወንጌልን እየሰበከ ቢጋደል ኦሪት "እጠፋ እጠፋ": ወንጌል ደግሞ "እሰፋ እሰፋ" አለች:: በዚህ ጊዜ "ክርስትናን ለማጥፋት መፍትሔው ቅዱስ እስጢፋኖስን መግደል ነው" ብለው አይሁድ በማመናቸው ሊገልድሉት አስበውም አልቀሩ ገደሉት::

+ እርሱ ግን ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ፈጣሪውን በብዙ ነገር መሰለው:: በመጨረሻውም ስለ እነሱ ምሕረትን እየለመነ በድንጋይ ወገሩት:: ደቀ መዛሙርቱም ታላቅ ለቅሶን እያለቀሱ ቀበሩት::

+ይህች ዕለት ለቅዱስ እስጢፋኖስ በዓለ ሲመቱ ናት:: ቅዱሱ መጽሐፍ እንደሚል "ምሉዓ ጸጋ ወሞገስ-ሞገስና ጸጋ የሞላለት" [ሐዋ.፮፥፭ [6:5], ቅዳሴ ማርያም] ነውና የ፮ [6]ቱ ዲያቆናት አለቃና የ8ሺው ማሕበር መሪ ሆኖ ተመርጦ እንደሚገባ አገልግሏል:: በሰማይ ባለችው መቅደስም የሚያገለግለው በዚሁ ማዕረጉ ነው::


† 🕊   ቅዱስ ፊልያስ ሰማዕት   🕊 †

ሰማዕቱ የነበረበት ዘመን ፫ [3]ኛው መቶ ክ/ዘ [ዘመነ ሰማዕታት] ሲሆን ቀምስ ለምትባል የግብጽ አውራጃም ዻዻስ ነበር:: ቅዱሱ እጅግ ጻድቅ በዚያውም ላይ ክቡርና ተወዳጅ ሰው ነበር:: የመከራው ዘመን ሲመጣ በቃሉ ያስተማራቸውን እንደ በጐ እረኝነቱ በተግባር ይገልጠው ዘንድ ወደ መኮንኑ ሔደ::

+ ሕዝቡ በአንድነት ተሰብስበው ሳለ መኮንኑ ቁልቁልያኖስ ቅዱስ ፊልያስን ፬ [4] ጥያቄዎችን ጠየቀው:: ምላሾቹ ለእኛ ሕይወትነት ያላቸው ናቸውና እንመልከታቸው::

፩. "የእናንተ እግዚአብሔር ምን ዓይነት መስዋዕትን ይሻል?" ቢለው "ልበ ትሑተ: ወመንፈሰ የዋሃ: ወነገረ ሕልወ: ወኩነኔ ጽድቅ: ዘከመዝ መስዋዕት ያሠምሮ ለእግዚአብሔር-እግዚአብሔርን ትሑት ልቦና: የዋህ ሰብእና: የቀና ፍርድና ቁም ነገር ደስ ያሰኘዋል" ሲል መለሰለት::

፪. "የምትወዳቸው ሚስትና ልጆች የሉህም?" ሲለው ደግሞ "እምኩሉ የአቢ ፍቅረ እግዚአብሔር - ከሁሉ የእግዚአብሔር ፍቅር ይበልጣል" አለው::

፫. "ለነፍስህ ትጋደላለህ ወይስ ለሥጋህ?" ቢለው "ለ2ቱም እጋደላለሁ:: አምላክ በአንድነት ፈጥሯቸዋልና:: በትንሳኤ ዘጉባኤም ይዋሐዳሉና" ብሎታል::

፬. "አምላካችሁ የሠራው ምን በጐ ነገር አለ?" ብሎትም ነበር:: ቅዱስ ፊልያስ መልሶ: "አስቀድሞ ፍጥረታትን በጥንተ ተፈጥሮ ፈጠረ:: በሁዋላም በሐዲስ ተፈጥሮ ያከብረን ዘንድ ወርዶ ሞተልን: ተነሣ: ዐረገ" ቢለው መኮንኑ "እንዴት አምላክ ሞተ ትላለህ!" ብሎ ተቆጣ:: ቅዱሱም "አዎ! በለበሰው ሥጋ ስለ እኛ ሙቷል" ብሎ እቅጩን ነገረው::

+ ወዲያውም "እስከ አሁን የታገስኩህ በዘመድ የከበርክ ስለሆንክ ነው" ቢለው ቅዱሱ መልሶ "ክብሬ ክርስቶስ ነው:: መልካምን ካሰብክልኝ ቶሎ ግደለኝ" አለው:: በዚያን ጊዜ የሃገሩ ሰዎች "አትሙትብን! እባክህን ለመኮንኑ ታዘዘው?" ሲሉ ለመኑት::

+ ቅዱስ ፊልያስ "እናንተ የነፍሴ ጠላቶች ዘወር በሉ ከፊቴ! እኔ ወደ ክርስቶስ ልሔድ እናፍቃለሁና" ብሎ ገሰጻቸው:: መኮንኑም ወስዶ ከብዙ ስቃይ ጋር ገድሎታል::

† 🕊   ቅድስት ሐና ነቢይት   🕊 †

"ሐና" ማለት "የእግዚአብሔር ስጦታ" ማለት ነው:: እጅግ ከሚታወቁ ሴት ነቢያት አንዷ የሆነችው ቅድስት ሐና ከክርስቶስ ልደት ፲፻፩፻ [1,100] ዓመታት በፊት በዚህች ቀን እንደ ተወለደች ይታመናል:: ቅድስቲቱ ልጅ በማጣት ተቸግራ: ከጐረቤት እስከ ሊቀ ካህናቱ ኤሊ ድረስ ሽሙጥና ስድብን ታግሣ ታላቁን ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤልን ወልዳለች::

Debtera Media

26 Oct, 17:15


                          †                          

💖  [    የ ኅ ሊ ና ድ ም ጽ !    ]  💖

🕊                      💖                      🕊


❝ አቤቱ ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ። እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው ? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል። ❞

[  መዝ . ፳፭ ፥ ፲፩  ]


🕊                        💖                    🕊

Debtera Media

26 Oct, 15:07


                       †                       

  [  🕊  ድምፀ ተዋሕዶ   🕊  ]  

🍒▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🍒               

[  ሕይወት የሚገኝባቸው የቅድስት ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በድምፅ ይቀርባሉ።  ]

[   ሳምንታዊ መርሐ-ግብር   ]

🕊             
             
❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ፤ ነፍስን ይመልሳል ፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው ፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።

የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ፥ ልብንም ደስ ያሰኛል ፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው ፥ ዓይንንም ያበራል። ❞

[ መዝ . ፲፱ ፥ ፯  ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[ ❝ የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ! ❞  ]

              [   ክፍል - ፳፰ -    ]

          💖   ድንቅ ትምህርት  💖

[ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል። ❞ [ ምሳ.፩፥፴፫ ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                        👇

Debtera Media

26 Oct, 09:03


🕊                

[  ኦርቶዶክሳዊ የተቀደሰ ያሬዳዊ ዝማሬ ሰዓት  ]

[ ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ]

🕊

በስመ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን፡፡

ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር የተቀደሰ ነው ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋናና ልመና የሚቀርብበት ፣ ይቅርታና ምሕረት የሚጠየቅበት ፣ ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት የሚዘጋጅ ንጹሕ መስዋዕት ነው ፥ በአበው ጸሎት ይዘጋጃል ፥ ከስጋዊና ከደማዊ ሀሳብ የራቀ ነው ፥ ልቦናን ወደ ንስሐ ይጠራል ፥ ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የመለየት ኃይል አለው ፥ ክፉ መንፈስን ከሰው ልብ ያርቃል ፥ መረጋጋትን ልቦናን ዘልቆ የሚሰማ ውስጣዊ ሰላምን ይሰጣል ፥ በአሚነ ሥላሴ ያጸናል ፥ የክርስቶስን የባህርይ አምላክነትና መሃሪነት ይመሰክራል ፥ የእመቤታችንን ፍቅር በልቦና ያሳድራል ፥ በምልጃዋና በእናትነቷ እንድንታመን ያደርጋል ፥ በቅዱሳን ጸሎትና በቃል ኪዳናቸው ያጸናል ፥ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እናውቅ ዘንድ መንገድ ይመራናል ፥ ፈሪሐ  እግዚአብሔርንና ፍቅረ እግዚአብሔርን ያጎናጽፈናል፡፡

†                       †                       †

ተወዳጆችሆይ ፦ በተቀደሰ ሰማያዊ ያሬዳዊ ዜማ ነብሳችንን እናስጊጣት፡፡ ከደጋጎቹ አባቶቻችን ጋር ከዓለም ርኩሰት በተለየ የተቀደሰ ዝማሬ አምላካችን እግዚአብሔርን እናመሥግን፡፡ ለስጋዊ ጆሮዎች ከሚመች የተሃድሶ የኑፋቄ እርሾ ልቦናችንን እንጠብቅ፡፡ ከሥጋዊ ሥራ ፈጽሞ እንለይ፡፡

🕊

❝ ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ ፤ ❞

[ የድኅነት ምክንያት የሆነው ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት ፣ መርገም [ኀጢአት] ባጠፋን ነበር ]

[ አባ ጽጌ ድንግል ]

[ 🕊 ኪዳነ ምህረት 🕊 ]

- ❝ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ
- በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ
- የተራቆተውን ለሚያለብሱ
- የተራበውን ለሚያጠግቡ
- የተጠማውንም ለሚያጠጡ
- የታመመውን ለሚጐበኙ
- ያዘነውን ለሚያረጋጉ
- የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ
- ምስጋናዬን ለሚጽፉ
- ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም
- በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰውም ልቡና ያልታሰበውን በጎ ዋጋ ስጣቸው።

በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃቡንና ጥማቱን ፤ መከራውን ሁሉ አስብ አለችው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽም ቃል ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት። ❞

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጣዕሟን በአንደበታችን ፤ ፍቅሯን በልባችን ያሳድርልን። ጽኑ ቃል ኪዳኗ በአማላጅነቷ ከምናምን ከህዝበ ክርስቲያን ጋር ለዘላለም ጸንቶ ይኑር

†                       †                       †
💖                    🕊                    💖

Debtera Media

25 Oct, 21:10


+ ፓትርያርክ ሆነው ከተሾሙ በሁዋላ ብዙ ጭንቅ ያሳለፉ ሲሆን እግዚአብሔር አቅሎላቸዋል:: ከማረፋቸው በፊትም ከእርሳቸው ቀጥለው የሚሾሙትን በጸጋ ተናግረዋል:: አባ ያቃቱ ለግብጽ ፵፱ [49]ኛ ሊቀ ዻዻሳት ናቸው::

በረከታቸው ይደርብን::

[  † ጥቅምት ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት
፪. ጻድቃን እለ ድርቂ
፫. አባ ዻውሊ ገዳማዊ
፬. አባ ማርቆስ መስተጋድል
፭. አባ አሮን መስተጋድል

[   †  ወርኀዊ በዓላት   ]

፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም]
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ (የመጥምቁ ዮሐንስ እናት)
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ [የቅ/ላሊበላ ወንድም]
፬. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፭. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፮. አባ ዳንኤል ጻድቅ
፯. ቅዱስ አባ ዮሐንስ ጻድቅ [ወንጌሉ ዘወርቅ]

🕊

" የምድር ባለጠጐች አሕዛብ በፊትሽ ይማለላሉ:: ለሐሴቦን ንጉሥ ልጅ ሁሉ ክብሯ ነው:: ልብሷ የወርቅ መጐናጸፊያ ነው:: በሁዋላዋ ደናግሉን ለንጉሥ ይወስዳሉ . . . በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ:: በምድርም ሁሉ ላይ ገዥዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ:: ለልጅ ልጅ ሁሉ ስምሽን ያሳስባሉ::" [መዝ.፵፬፥፲፪-፲፯] (44:12-17)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

25 Oct, 21:10


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖ ጥቅምት ፲፮ [ 16 ] ❖

🕊 ✞ እንኩዋን አደረሳችሁ ✞ 🕊

† ፯ [7]ቱ ኪዳናት ወአባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት †

† 🕊  ፯ [ 7 ] ቱ ኪዳናት   🕊 †

"ተካየደ" ማለት "ተስማማ: ተማማለ" እንደ ማለት ሲሆን "ኪዳን" በቁሙ "ውል: ስምምነት" እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::

እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ ፯ [7] እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን ፯ [7] ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን:: "ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" [መዝ.፹፰፥፫] (88:3)

[ ፩ ] † 🕊  ኪዳነ አዳም  🕊 †

አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: [ዘፍ.፫፥፩] (3:1)

አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: [ቀሌምንጦስ: ገላ.፬፥፬] (4:4)

[ ፪ ]  † 🕊  ኪዳነ ኖኅ  🕊 †

ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት ፲ [10] ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: [ዘፍ.፱፥፲፪] (9:12)

[ ፫ ] † 🕊 ኪዳነ መልከ ጼዴቅ  🕊 †

መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ፲፭ [15] ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር::

እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: [ዘፍ.፲፬፥፲፯] (14:17), [ዕብ.፯፥፩] (7:1)

[ ፬ ] † 🕊 ኪዳነ አብርሃም  🕊 †

ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: [ዘፍ.፲፪፥፩] (12:1) የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: [ዘፍ.፲፯፥፩-፲፬] (17:1-14)

[ ፭ ] † 🕊  ኪዳነ ሙሴ  🕊 †

ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት [የዋህ] ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ፵ [40] ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: [ዘጸ.፳፥፩] (20:1), [፴፩፥፲፰] (31:18)

[ ፮ ] † 🕊  ኪዳነ ዳዊት  🕊 †

ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" [መዝ.፻፴፩፥፲፩] (131:11) ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: [መዝ.፹፰፥፴፭] (88:35)

[ ፯ ] † 🕊  ኪዳነ ምሕረት  🕊 †

በብሉይ ኪዳን የነበሩ ፮ [6]ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::

+ በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት [የምሕረት ኪዳን] የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::

+ የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::

+ የእርሷ ኪዳን የ፮ [6]ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ "የኪዳናት ማሕተም" ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::

+ እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ ፪ [2] ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::

* " ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ፡፡
ማርያም እሙ ለእግዚእነ፡፡
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ::" *

"ድንግል ሆይ ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"

ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን::


† 🕊  አባ ያቃቱ ሊቀ ዻዻሳት  🕊 †

በምድረ ግብጽ ከተነሱና ለመንጋው ከራሩ አበው ዻዻሳት አንዱ አባ ያቃቱ ናቸው:: አባ ያቃቱ መጻሕፍትን የተማሩ: በገዳምም የኖሩ በመሆናቸው እንደ ቀደምቶቻቸው ቤተ ክርስቲያኗን በቅን መርተዋል::

Debtera Media

25 Oct, 17:54


                           †                           

  [   🕊 ዕፅ ድንግል ማርያም 🕊   ]  

🌼▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🌼

"ሥዕልኪ ጽግይተላህይ ዘከመዝ ትኤድም በዓለም
እፎ ይሤኒ በሰማይ ላህየ [ሥነ] ገጽኪ ማርያም
ሐሤተት እምርትኪ እጽገብ አስተርእዪኒ በሕልም
እስመ አውዐየኒ ነደፍቅርኪ ፍሕም
አጥፍኦቶ ዘኢይክል ዝናም"

🕊

[ ማርያም ሥዕልሽ በዓለም እንዲህ የምታበራ ከሆነ በሰማይ የፊትሽ መልክ ምን ያምር ! አንቺን ከማየት የሚገኘውን ደስታ እጠግብ ዘንድ በሕልም ተገለጪልኝ፡፡ ዝናብ ሊያጠፋው የማይቻለው የፍቅርሽ እሳት አንድዶኛልና፡፡ ] [ መኃ.፰፥፯ ] "

🕊

[  አባ ጽጌ ድንግል  ]


†                       †                      †
💖                    🕊                   💖

Debtera Media

23 Oct, 20:42


✞ አምላከ ቅዱሳን ለእነርሱ ካደለው ፍቅራቸው ለእኛም አይንሳን:: በረከታቸውንም ያብዛልን::

🕊

[  † ጥቅምት ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. አቡነ ዘሚካኤል [አረጋዊ]
፪. ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ [ከ፸፪ [72] ቱ አርድእት]
፫. ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ
፬. ቅዱስ ሙሴ መርዓዊ
፭. ቅድስት እድና [የአረጋዊ እናት]
፮. አባ ማትያስ [የአረጋዊ ረድዕ]

[   †  ወርሃዊ በዓል  ]

፩. አባ ዮሐንስ ጻድቅ
፪. እናታችን ቅድስት ነሣሒት

" ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል:: ጻድቅን በጻድቅስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል:: ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውሃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላቹሃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም::" [ማቴ.፲፥፵፩] (10:41)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

23 Oct, 20:42


🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

✞ ጥቅምት ፲፬ [ 14 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞

† 🕊  አቡነ አረጋዊ ዘደብረ ዳሞ  🕊 †

✞ በሃገራችን ስም አጠራራቸው ከከበረ አባቶች አንዱ እኒህ ጻድቅ ናቸው:: ጻድቁ የተወለዱት በ፭ [5]ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ኣካባቢ ሲሆን ወላጆቻቸው ንጉሥ ይስሐቅና ቅድስት እድና ይባላሉ:: የተለወለዱበት አካባቢም ሮም ነው::

ስማቸው ብዙ ዓይነት ነው:: ወላጆቻቸው ዘሚካኤል ሲሏቸው በበርሃ ገብረ አምላክ ተብለዋል:: በኢትዮዽያ ደግሞ አረጋዊ ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆኑም በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው ነበርና ጠፍተው ገዳም ገቡ::

በዚያም በገዳመ ዳውናስ [ግብጽ] የታላቁ ቅዱስ ዻኩሚስ ደቀ መዝሙር ሆነው ከነ አባ ቴዎድሮስ ጋር ሥርዓተ መነኮሳትን ተምረዋል:: ከመነኮሱ ከዓመታት በኋላም ወደ ሃገራቸው ሮም ተመልሰው በማስተማር ፯ [7] ያህል የቤተ መንግስት ሰዎችን ወደ ምናኔ ማርከዋል::

"የት ልሒድ" ብለው ሲያስቡም ቅዱስ መልአክ በክንፉ ጭኖ ወስዶ ኢትዮዽያን አሳያቸው:: ተመልሰውም ለ፰ [8] ባልንጀሮቻቸው "ሃገርስ ባሳየሁዋችሁ! ሐዋርያ ሳያስተምራት በሕጉ በሥርዓቱ ጸንታ የምትኖር" ብለው ከ፰ [8]ቱ ጋር ወደ ኢትዮዽያ መጡ::

በዚህ ጊዜም እናታቸው ቅድስት እድናና ደቀ መዝሙራቸው አባ ማትያስ አብረው ነበሩ:: ወደ ሃገራችን የመጡ በ፬፻፸ [470]ዎቹ አካባቢ ሲሆን አልዓሜዳ በክብር ተቀብሏቸዋል:: በቤተ ቀጢን [አክሱም] ተቀምጠውም መጻሕፍትን እየተረጐሙ: ወንጌልን እየሰበኩ ቆይተዋል::

ለሥራ በተለያዩ ጊዜም አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ብዙ ደክመዋል:: በመጨረሻ ግን ደብረ ዳሞን [ደብረ ሃሌ ሉያን] አይተው ወደዷት:: የሚወጡበት ቢያጡም ጅራቱ ፷ [60] ክንድ የሚያህል ዘንዶ ተሸክሞ ከላይ አድርሷቸዋል::

እንደ ወጡም "ሃሌ ሉያ ለአብ: ሃሌ ሉያ ለወልድ: ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ" ብለው ቢያመሰግኑ ከሰማይ ሕብስት ወርዶላቸው ተመግበዋል:: በዚህም ቦታዋ "ደብረ ሃሌ ሉያ" ተብላለች:: ጻድቁ ቦታውን ከገደሙ በኋላ ከተለያየ ቦታ መጥተው ፮ [6]ሺ ያህል ሰዎች በእጃቸው መንኩሰዋል::

ምናኔን በማስፋፋታቸውና ሥርዓቱን በማስተማራቸውም "አቡሆሙ ለመነኮሳት ዘኢትዮዽያ-የኢትዮዽያ መነኮሳት አባት" ይባላሉ:: አቡነ አረጋዊ በሕይወታቸው ከተጋድሎ ባሻገር በወንጌል አገልግሎትና መጻሕፍትን በማዘጋጀትም ደክመዋል::

ቅዱስ ያሬድና አፄ ገብረ መስቀልም ወዳጆቻቸው ነበሩ:: በተራራው ግርጌ ያለችውን ኪዳነ ምሐረትን ለሴቶች ሲገድሟት ቀዳሚዋ መነኮስ እናታቸው ንግስት እድና ሁናለች::

ጻድቁ ንጹሕ ሕይወታቸውን ፈጽመው በተወለዱ በ፺፱ [99] ዓመታቸው በዚህ ቀን በገዳሙ በስተምሥራቅ አካባቢ ተሰውረው ብሔረ ሕያዋን ገብተዋል:: ጌታም ፲፭ [15] ትውልድን የሚያስምር የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል::


† 🕊  ቅዱስ ፊልዾስ ሐዋርያ  🕊 †

✞ በዘመነ ሐዋርያት በዚህ ስም የሚጠሩ አባቶች ፪ [2] ነበሩ:: አንደኛው ከ፲፪ [12]ቱ ሐዋርያት ሲቆጠር ዛሬ የምናከብረው ደግሞ ከ፸፪ [72]ቱ አርድእት ይቆጠራል:: ቅዱስ ፊልዾስ ያደገው የኖረውም በቂሣርያ አካባቢ ሲሆን ባለ ትዳር የልጆች አባት ነው::

ጌታ ሲጠራው እንኩዋ ፬ [4] ደናግል ሴቶች ልጆች ነበሩት:: ከጌታ ሕማማት በፊት ተልኮ አስተምሯል:: ከበዓለ ሃምሳ በኋላም ፯ [7]ቱ ዲያቆናት ሲመረጡ አንዱ እርሱ ነበር:: [ሐዋ.፮] (6) በቅዱስ እስጢፋኖስ መሪነትም ፰ [8] ሺውን ማሕበር አገልግሏል::

ቅዱስ እስጢፋኖስ ተገድሎ ፰ [8]ሺው ማሕበር ሲበተንም ቅዱስ ፊልዾስ ፬ [4]ቱን ልጆቹን አስከትሎ ወደ ሰማርያ ወርዷል:: በዚያም መሠሪ ስምዖንን ጨምሮ የሃገሪቱን ሰዎች አሳምኖ አጥምቁዋል::

መቼም ቢሆን እኛ ኢትዮዽያውያን የማንዘነጋው ግን ጃንደረባውን ባኮስን ማጥመቁን እና ለሃገራችን የወንጌልን ብርሃን መላኩን ነው:: ጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ ከጉዞ መልስ ትንቢተ ኢሳይያስን [ኢሳ.፶፫] (53) ሲያነብ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ቀርቦ ምሥጢረ ሥጋዌን አስረድቶታል::

ሠረገላውም ቁሞለት ቅዱስ ባኮስን አጥምቆት ተነጥቆ ሔዷል:: [ሐዋ.፰፥፳፮] (8:26) ቅዱስ ፊልዾስ በቀሪ ዘመኑ ከተባረኩ ፬ [4] ደናግል ልጆቹ ጋር ሲሰብክ ኑሮ በዚህች ቀን ዐርፏል::

†  🕊  ሙሽራው ቅዱስ ሙሴ  🕊  †

✞ የዚህ ቅዱስ ወጣት ታሪክ ደስ የሚልም: የሚገርምም ነው:: በሮም ከተማ በምጽዋት: በጾምና በጸሎት ከተቃኙ ሃብታሞች [መስፍንያኖስና አግልያስ] ተወልዶ: በሥርዓቱ አድጐ: መጻሕፍትን ተምሮ በተክሊል አጋቡት::

በሠርጉ ማግስት ሙሽሪትን ቢያያት በጣም ታምራለች:: "ይህ ሁሉ ውበትና ምቾት ከንቱ አይደለምን!" ብሎ በሌሊት ጠፍቶ: ነዳያንን መስሎ ከሮም ሃገረ ሮሆ [ሶርያ አካባቢ] ሔደ::

በዚያም በፍጹም ምናኔ: በ፯ [7] ቀን አንዲት ማዕድ እየበላ: በረንዳ ላይ እየተኛና እየለመነ ለዓመታት ኖረ:: ሁሌም ቀን የለመነውን ማታ ለነዳያን አካፍሎ እርሱ ሲጸልይ ያድር ነበር:: በአካባቢው ክብሩ ሲገለጽበትም የሐዋርያውን የቅዱስ ዻውሎስን በረከት ፍለጋ ወደ ጠርሴስ ሔደ::

ነገር ግን ጥቅል ነፋስ መርከቧን ገፍቶ ሮም አደረሳት:: ቅዱስ ሙሴም "የአምላክ ፈቃድ ነው" ብሎ በወላጆቹ ደጅ ተኝቶ ለ፲፪ [12] ዓመታት ተጋደለ:: ወላጆቹ ፈልገው ስላጡት በበራቸው የወደቀው ነዳይ እርሱ ይሆናል ብለው አልጠረጠሩም::

ከብዙ ተጋድሎም በኋላም ዜና ሕይወቱን ጽፎ በዚህች ቀን: በዕለተ እሑድ ዐርፏል:: ጌታችንም "መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ ካልተጠራጠረ እምረዋለሁ" ብሎታል::

በዚያም ሕዝቡ: ካህናቱና ሊቀ ዻዻሳቱን ጌታ አዟቸው አግኝተውታል:: ወላጆቹ ማንነቱን በለዩ ጊዜም ታላቅ ለቅሶን አልቅሰዋል:: ሥጋውም ብዙ ተአምራትን አድርጉዋል::


† 🕊 ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ መርዓዊ  🕊 †

✞ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ በሃገራቸው ልሳን 'አብደል መሲሕ' ይባላል:: ለቅዱስ ሙሴና ለሌሎችም ሙሽርነትን ትቶ መመነንን ያስተማረ እርሱ ነው:: አባቱ ታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ሲሆን እናቱ መርኬዛ ትባላለች:: የጻድቃን ትውልድ የተባረከ ነውና [መዝ.፻፲፩፥፩] (111:1) ታላቁ አቡነ ኪሮስ አጐቱ ናቸው::

ስለዚህ ቅዱስ ምን እነግራቹሃለሁ! ሙሉ ታሪኩ ከቅዱስ ሙሴ ጋር ተመሳሳይ ነውና:: ልዩነቱ ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ በገዛ ፍቃዱ አካሉ በመቁሰሉ ምክንያት ሰዎች ሊለዩት አልቻሉም ነበር::

በአርማንያ: በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ደጅ ለ፲፭ [15] ዓመታት ሲጋደል ወደ ወላጆቹ ሃገር ቁስጥንጥንያ ተመልሶ ለ፲፭ [15] ዓመታት ተፈትኗል:: ምንም የንጉሥ ልጅ ቢሆንም የአባቱ ባሮች በጥፊ ይመቱት: ጽሕሙን [ጺሙን] ይነጩት: ቆሻሻ ይደፉበት: ሽንታቸውንም ይሸኑበት ነበር::

ለእርሱ ወዳጆቹ ውሾች ነበሩ:: በአባቱ ደጅ ለ፲፭ [15] ዓመታት መከራን ከተቀበለ በኋላ "ጌታ ሆይ! የአባቴ አገልጋዮች በእኔ ላይ ያደረጉትን ሁሉ በደል አድርገለህ አትቁጠርባቸው" አለ:: በዚህች ቀን ሲያርፍም ጌታችን ፯ [7]ቱን ሊቃነ መላእክት ከነ ሠራዊታቸው አስከትሎ ወርዶ በክብር አሳርጐታል:: አጠቃላይ የገድል ዓመታቱም ፴ [30] ናቸው::

Debtera Media

23 Oct, 17:16


                           †                           

  [   🕊 እ መ አ ም ላ ክ 🕊    ]  

🌼▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🌼


❝ አጽምዕ ሰማይ ዘእነግረከ ወስምዒ ምድር እምዜና ስደታ ንስቲተ ለእመ መለኮት ክቡር ዘልበ ይከፍል ወኅሊና ያንቀለቅል ሶበ ይትነገር ሕማማ ለድንግል፡፡ አመ ወፅአት በፍርሃት እምሀገረ ዳዊት ዘይሁዳ በብሥራተ መልአክ እንግዳ ኢረከበት ማየ በፍኖት ዘታሰትዮ ለወልዳ። ❞

🕊

[ ሰማይ የምነግርኽን ስማ ፤ ምድርም በሚነገር ጊዜ ልብን የሚከፍልና ኅሊናንም የሚያነዋውጥ የድንግልን መከራ በሚነገር ጊዜ ከክቡር መለኮት እናት ከስደቷ ዜና ጥቂት ስሚ፡፡ በእንግዳ መልአክ ብሥራት የይሁዳ ክፍል ከምትኾን ከዳዊት ከተማ ከይሁዳ በፍርሀት በወጣች ጊዜ ለልጇ የምታጠጣው ውሃ በመንገድ አላገኘችም፡፡ ]

[ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ]


†                       †                      †
💖                    🕊                   💖

Debtera Media

23 Oct, 15:43


                          †                          

💖  [    የትሕርምት ሕይወት !    ]  💖

🕊                       💖                      🕊


[       “ አገልግሎትን በተመለከተ ! "       ]

[ ሥራን አስመልክቶ የሰጠው ትምህርት ! ]

--------------

❝ ወደጄ ሆይ ! በምትሠራው ሥራ ምክንያት አትዘን፡፡

በምትሠራው ሥራ ላይ በፍጹም ስኬታማ ልሆን አልቻልኩም፡፡ እኔ ስንፍናን የተሞላሁ ፣ የደነዘዝሁ ነኝና በፍጹም ይህን ተግባር ልፈጸም አልችልም፡፡ እጆቼ ያለ ፍሬ ከሥራው ብዛት የተነሣ ዝለዋል፡፡ ሥራውን ለመሥራት አሁን አቅሙ የለኝም ስለዚህ ወደመጣሁበት እመለሳለሁ ... የሚል ሐሳብ በአእምሮህ ውስጥ ከቶ አይመላለስ::

እንደ አንድ አማኝ በእግዚአብሔር ታመን ፥ እንዲህ ባለ ነገርም ተስፋ አትቁርጥ፡፡ ነገር ግን ወደ መንግሥቱና ወደ እርሱ ደስታ ስለጠራህ ስለ ጌታችን ስለ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብለህ መከራውን ሁሉ ታግሠህ ኑር፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “እውነት እላችኋለሁ ፥ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያህል እምነት ቢኖራችሁ ፥ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ እለፍ ብትሉት ያልፋል ፤ የሚሳናችሁም ነገር የለም፡፡” [ማቴ.፲፯፥፳]

ስለዚህ ተወዳጆች ! ሆይ እምነት ይኑረን ፤ እኛ ተስፋ ያደረግናቸው ከቶ ሊያድኑን የማይችሉ ሰዎችን ሳይሆን እግዚአብሔርን ነው፡፡ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ፦ “በእግዚአብሔር የታመኑ እንደማይታወክ ለዘላለም እንደሚኖር እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው::” [መዝ.፻፳፬፥፩] የኃያላን ጌታ ሆይ በአንተ ተስፋ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፡፡ ❞

[  ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  ]


🕊                       💖                   🕊

Debtera Media

23 Oct, 13:12


                          †                          

[    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ]

▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬

[  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ]

[                ክፍል  ሃያ ስድስት                 ]

💛

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

[  እግዚአብሔር የአባ መቃርዮስን ጩኸት እንደ መለሰለት  ]

                         🕊                         

❝ በአንድ ወቅት ታላቁ አባ መቃርዮስ ከአስቄጥስ ወደ ግብፅ እየሄደ ሳለ ትንሽ ቅርጫቶች ተሸክሞ ነበር፡፡ እርሱም በደከመው ጊዜ ቁጭ አለ፡፡ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ፦ " ጌታ ሆይ ፣ ምን ያህል እንደ ደከመኝና እንደዛልኩ የምታይ አንተ ነህ " አለ፡፡ ይህን ካለ በኋላ ወዲያውኑ ራሱን ከቅርጫቶቹ ጋር በዓባይ ወንዝ ዳር ላይ ደርሶ አገኘው፡፡

የቅዱስ መቃርዮስ ደቀ መዝሙር የነበረው አባ በብኑዳ እንዲህ አለ ፦ " አንድ ቀን ቅዱስ መቃርዮስ ቆሞ ሲጸልይ ሳለ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ተናገረው ፦ ' መቃራ ሆይ ፣ እገሌ በምትባል ሀገር ያለማቋረጥ በትጋት የሚያገለግለኝንና የሚያመሰግነኝን አንድ ገበሬ ምሰል፡፡ ' ይህን በሰማ ጊዜ ከመጀመሪያዎቹ አርድእት አንዱ የሆንኩትን እኔን በብኑዳን ፦ ' ተነሥና ምርኩዝህን ይዘህ ከእኛ ጋር እገሌ ወደምትባል ሀገር እንሂድ ' አለኝ፡፡ ወደዚያ ሄደን ከወንዙ ሐይቅ ዳር ደረስን ፣ የሚያሻግረን በፈለግን ጊዜ አላገኘንም ነበርና ስፋቱን እየተመለከትን ሁላችንም ዝም ብለን በዚያ ተቀምጠን ነበር፡፡ ቅዱስ መቃርዮስ ግን በተመሥጦ ሆኖ ራእይን እያየ ነበር፡፡

እኔም አባታችን ፣ እግዚአብሔር ጸሎትህን እንደሚሰማ አውቃለሁና ይረዳን ዘንድ ጸልይ አልኩት፡፡ ያን ጊዜም እየማለደ ጸለየ፡፡ ወዲያውኑ ታላቅ አዞ ከባሕሩ ወጣ ፤ ቅዱሱም ' እግዚአብሔር ከወደደና አዝዞህ ከሆነ አሻግረን ' አለው፡፡ ያ አዞም ተሸከመንና ወደ ማዶ አሻገረን፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ያንን አዞ ' እግዚአብሔር ዋጋህን እስከሚሰጥህ ድረስ ወደ ውኃው ግባ ' አለው፡፡ እርሱም እራሱን ወደ ውኃው አጠለቀ፡፡

ወደ ሀገሩ በወጣንና ወደዚያ በደረስን ጊዜ በሀገረ ገዢው እርሻ ላይ ተሰማርተው የሚሠሩ ብዙ ገበሬዎችን አገኘን፡፡ አረጋዊው መቃራም እነዚያን ገበሬዎች እያንዳንዳቸውን እየተመለከተ በበሩ አንጻር ተቀመጠ፡፡ እግዚአብሔር ስለ እርሱ ያመለከተው ያ ገበሬ በመጣ ጊዜ በዙሪያው ከብባው ያለችውን ጸጋ እግዚአብሔር ተመለከተ ፣ በትዕግሥት የተከደነ መሆኑንም አየ፡፡ ሰላምታ ሰጥቶ የተቀደሰች መሳምን ሳመው፡፡ ከዚያም እርሱን ይዞ ለብቻው ገለል አደረገውና ፦ 'እግዚአብሔርን የምታገለግልበት ሥርዓተ ተልእኮህ ምንድን ነው ? ' አለው፡፡ ያ ገበሬም ፦ ' እኔ በዚህ ዓለም ለቀሲስ [ ለካህን ] እላላካለሁ ፣ ጌታዬ ሰማያዊ ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስም ዋጋዬን ይሰጠኛል፡፡ ስለዚህም ይህን ያህል ዘመን ሁሉ ዘወትር አገለግላለሁ ፣ እኔም ልቤ የቀና ነው ' አለው፡፡

መቃርዮስም ፦ ' ይህን ሃሳብ ከየት አገኘኸው?' አለው፡፡ እርሱም ፦ " ሠራተኞቹን አምጧቸውና ደመወዛቸውን ስጧቸው " ካለው ከጌታ ቃል ነው ' አለው፡፡ ቅዱስ መቃርዮስም ይህን ነገር ከእርሱ በሰማ ጊዜ ሳመውና መከረው ፣ በላዩም ላይ ማሕየዊ በሆነ በትዕምርተ መስቀል ባረከው፡፡ ከዚያም ሲመለስ ነፍሱን ፦ ' መቃራ ሆይ ወዮልህ ፣ የዚህን ዓለማዊ ወንድም ያህል እንኳን አእምሮ የለህም ፣ ብታውቅበትና በምግባርህ እግዚአብሔርን ብታገለግል እርሱ ዋጋህን ይሰጥሃል' እያለ በመንገድ ላይ ሁሉ ታላቅ ለቅሶን ያለቅስ ነበር፡፡ "

" ወደ ወንዙ በደረስን ጊዜ የሚያሻግረን ስላጣን አባት መቃርዮስ በዚያ ጸለየ፡፡ እኛንም ፦ ' ልጆቼ ሆይ እግዚአብሔር እስኪረዳን ድረስ ተቀመጡ ' አለን፡፡ እኔም በዚያ ትንሽ ተኛሁና በነቃሁ ጊዜ እኔና እርሱን በበኣታችን በር ፊት ቆመን አገኘሁት፡፡ እኔም 'ይህ ነገር እንዴት ሆነ? አልኩት፡፡ እርሱም ፦ 'ልጄ ሆይ ነቢዩ እንባቆምን ከይሁዳ ምድር ወስዶ  ባቢሎን ከነቢዩ ዳንኤል ዘንድ እንደ ዓይን ጥቅሻ አድርሶ እንደ ገና ወደ ቦታው የመለሰው እርሱ ነውና እግዚአብሔርን አመስግን ፤ እኛንም ከዚህ ያደረሰን እርሱ ነው' አለው፡፡ ❞

የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡

ይቆየን !


†                       †                         †
💖                    🕊                     💖

Debtera Media

23 Oct, 10:53


🕊                        💖                       🕊   

[   🕊  የሥነ-ሥዕል ዐውደ ርእይ   🕊   ]

    ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

       [           በእንተ ሉቃስ          ]

- ከጥቅምት ፲፯ - ፳፬ [ 17 - 24 ]


የላፍቶ ፥ ፈለገ ብርሃን : ቅድስት ሥላሴ እና ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ፍ/ብ/ሰ/ት/ቤት የአቅሌሲያ ሕፃናት ሥነ-ሥዕል ክፍል

            [       ተጋብዛችኋል !       ]

[ ሳሪስ 58 ኪዳነ ምሕረት ጠበል 100 ሜትር ገባ ብሎ ]


🕊                        💖                       🕊

Debtera Media

22 Oct, 21:22


በነዚህ ዓመታት ሁሉ ይህ አካሉ የተለወጠ ሕጻን ቅዱስ ዘካርያስ መሆኑን ያወቀ የለም:: እንዲህ የቆሰለውም አሲድነት ካለው የጉድጉዋድ ውሃ ውስጥ ሰጥሞ ለ፵ [40] ቀናት በመጸለዩ ነው::

በመጨረሻ ግን አባቱ በምልክት ለይቶት አለቀሰ:: "ልጄ! አንተ ለእኔ አባቴ ነህ" ብሎታል:: አበው መነኮሳትም ተሰብስበው እጅ ነስተውታል:: በ፯ [7] ዓመቱ የመነነው አባ ዘካርያስ በ፶፪ [52] ዓመቱ በዚህች ቀን ዐርፎ በክብር ተቀብሯል::

አምላከ አፈ ወርቅ ዮሐንስ የድንግል እመ ብርሃንን ፍቅሯንና ውዳሴዋን ይግለጽልን:: ከአባቶቻችን ክብርና በረከትንም ያሳትፈን::

[  † ጥቅምት ፲፫ [ 13 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
፪. አባ ዘካርያስ ገዳማዊ
፫. አባ ማርዳሪ ጻድቅ
፬. ቅዱስ አብጥማዎስ ሰማዕት

[    †  ወርኀዊ በዓላት    ]

፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት
፫. ፺፩ "99ኙ" ነገደ መላዕክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. ፲፫ "13ቱ" ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

" እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ::" [ማቴ.፭፥፲፫-፲፮] (5:13-16)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖

Debtera Media

22 Oct, 21:22


 🕊

✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞

❖ ጥቅምት ፲፫ [ 13 ] ❖

[  ✞ እንኩዋን ለዓለም ሁሉ መምሕር "ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ" እና ለአባ "ዘካርያስ ገዳማዊ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞  ]

†   🕊  ዮሐንስ አፈ ወርቅ  🕊   †

ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር "አፈ ወርቅ" መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?

ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ፫፻፵፯ [347] ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ [ፍልስፍና] ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ፲፭ [15] ዓመቱ ነበር:: በ፪ [2] ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::

ቅዱሱ ገና በ፲፮ [16] ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::

ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::

ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል "አፈ ወርቅ" ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው "አፈ ወርቅ" የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ ፲ [10] ዓመት አቁሞታል::

ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ "አልመልስም" በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ፬፻፯ [407] ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ፷ [60] ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::

ከዕረፍቱ አስቀድሞ አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ
አርቃድዮስ ግብር አገባ:: [ግብዣ አዘጋጀ]

በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ ከሰማይ ፲፪ [12] ቱ ሊቃነ መላእክት [እነ ቅዱስ ሚካኤል] ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::

ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::

በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::

"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ-የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ [ማቴ.፩፥፳፭] (1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::

"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::

'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::

አሁን ግን ልጇ አምላክ ዘበአማን: እርሷም ወላዲተ አምላክ መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::

ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::

ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው :-

¤ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
¤ አፈ በረከት
¤ አፈ መዐር [ማር]
¤ አፈ ሶከር [ስኩዋር]
¤ አፈ አፈው [ሽቱ]
¤ ልሳነ ወርቅ
¤ የዓለም ሁሉ መምሕር
¤ ርዕሰ ሊቃውንት
¤ ዓምደ ብርሃን [የብርሃን ምሰሶ]
¤ ሐዲስ ዳንኤል
¤ ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ [እውነተኛው]
¤ መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
¤ ጥዑመ ቃል - - -


†  🕊  አባ ዘካርያስ ገዳማዊ  🕊  †

ይህ ታላቅ ጻድቅ ባለ ጥዑም ዜና ነው:: ወላጆቹ እሱንና አንዲት ሴትን ከወለዱ በሁዋላ አባቱ መንኖ ገዳም ገባ:: ከዘመናት በሁዋላ ረሃብ በሃገሩ ሲገባ እናቱ ወስዳ ለአባቱ ሰጠችው:: ይህን ጊዜ ዕድሜው ፯ [7] ዓመት ነበር::

በገዳም ከአባቱ ጋር ሲኖር ከመልኩ ማማር የተነሳ አባቶች መነኮሳት "ይህ ልጅ ይህን መልክ ይዞ እንዴት መናኝ መሆን ይችላል!" ሲሉ ሰማ:: በሌሊትም ተነስቶ በሕጻን አንደበቱ "ጌታየ! መልኬ ካንተ ፍቅር ከሚለየኝ መልኬን አጠፋዋለሁ" አለ:: ከገዳሙም ጠፋ::

አባትም በጣም አዘነ:: ከ፵ [40] ቀናት በሁዋላ ግን ሊያዩት የሚያሰቅቅ: አካሉ ሁሉ የቆሳሰለ አንድ ነዳይ ሕጻን መጥቶ ወደ ገዳሙ ተጠጋ:: ይህ ሕጻን በጾም: በጸሎትና በትሕትና ተጠምዶ ለ፵፭ [45] ዓመታት አገለገለ::