ፋሲል የኔዓለም @fasilyenealem2022 Channel on Telegram

ፋሲል የኔዓለም

@fasilyenealem2022


ፋሲል የኔዓለም (Amharic)

ፋሲል የኔዓለም በበቂ ተስፋ ጊዜ ሲባልላቸው ከአማርኛ ቋንቋ በላይ በነበሩ ሥራ አገናኝተርዚም ላይ አሉ። እንደሚረዱት እንጠንክራቸው፣ ግንባታ እና ድህረ ገጹን በተለያዩ የተለያዩ ብቃት እና ምርቶች በመካከል ያስቆጠሩበት አገልግሎት ይመልከቱ። ይህ አገልግሎት ለምስል የጊዜ ከሆኑ ብቃቶች ውስጥ ለሚሠሩ ብቃትና በሥራ ላይ ሆኖ በግንኙነት በመላክ እንዲጠቁ ይህን መረጃ የተረዳፈ ነው። ለበለጠ በሚያውቁ የቅርብ ሥራ አገናኝተርዚም በቆሞ ምንም እንላይ እንዳሰበዉ ማንኛውም ይህን አገልግሎት ወደብቃቱን በሚይዝበት ግንኙነት እንቀርባለን።

ፋሲል የኔዓለም

23 Apr, 17:20


በፈተና ውስጥ ማለፍ፣ መውደቅና መነሳት የተፈጥሮ ቋሚ ህግ ነው። ሁላችንም እንደ ግለሰብም ሆነ እንደ አገር የምንፈተንበት፣ የምንወድቅበትና የምንነሳበት ጊዜ አለ። የወደቀ የሚመስለው አይዘን፣ ከፊቱ መነሳት አለና። የተነሳ የሚመስለውም አይመጻደቅ፣ መውደቅ የሚሉት ነገር አለና። መጪው ጊዜ እንደ አገር የገጠመንን ፈተና አልፈን የጋራ መነሳታችንን የምናውጅበት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።

ለክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወገኖቼ በሙሉ እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ፋሲል የኔዓለም

14 Apr, 21:07


ጠ/ሚ አብይ " አማራ ኦሮሞ የሚሉ ጄኔራሎችን አንፈልግም" እንዳሉት ሁሉ፣ "አማራ ኦሮሞ የሚሉ የክልል መሪዎችንም አንፈልግም" ቢሉ፣ ኢትዮጵያ የብሄር ፖለቲካን "ቻው" ብላ ሰላሟን ታገኝ ነበር። በአንድ አገር ውስጥ የፖለቲካ አመራሩ በብሄር እያሰበ፣ መከላከያውን በብሄር አታስብ ማለት ከባድ ነው። የፖለቲካ አመራሩ ከብሄር አስተሳሰብ ከወጣ፣ መከላከያውም በፍጥነት ከዚሁ አስተሳሰብ ይወጣል። መከላከያ ፖለቲካውን ይከተላል እንጅ፣ ፖለቲካ መከላከያውን አይከተልም። እናም አሁን መከላከያ ላይ የተዘራው ዘር ጥሩ ፍሬ እንዲይዝ ከተፈለገ፣ የፖሊቲካ አመራሩ በመላ ከብሄር አስተሳሰብ ይውጣ።

ፋሲል የኔዓለም

12 Apr, 08:10


በዚህ ወቅት የሚካሄድ "የግፋ በለው" ፖለቲካ፣ አገርንና ራስን አደጋ ላይ ከመጣል ውጭ፣ የሚያስገኘው ትርፍ የለም። በተለይ የኦሮሞና የአማራ ብሄርተኞች በይዋጣልን የፖለቲካ አካሄዳቸው፣ የታሪካዊቷን አገር ምሰሶ እየነቀነቁ እንደሆነ ልብ ያሉት አይመስልም ። ቀደምቶቻቸው ያስረከቧቸውን አገር ካላፈረስናት ብሎ ልፊያ፣ የጤና አይመስለኝም።

ትናንት የመጣንበት መንገድ ለዛሬ አይሆነንም። የዛሬው መንገድ፣ እንቁላል በአናቱ ላይ ተሸክሞ እንደሚራመድ ሰው፣ በጥንቃቄ የሚሄዱበት እንጅ፣ ድንጋይ ተሸክሞ፣ "ቢወድቅም መሬቱ አይጎዳም" ብሎ በግዴለሽነት እንደሚራመድ ሰው የሚጓዙበት አይደለም።

ኢትዮጵያ በውስጥና በውጭ ጠላት ተይዛ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ላይ በምትገኝበት ሰዓት፣ ጉልኮስ እንኳን ማቀበል ባንችል፣ ተጨማሪ ህመም ባለመሆን ብንተባበር፣ ለፈውሷ እንዳገዝናት ይቆጠራል።

ሁሉም ይስማ። ብሄርተኞችም ሰከን በሉ። መንግስትም አይንህን ግለጥ፤ ጆሮህን ክፈት።

ፋሲል የኔዓለም

10 Apr, 19:55


በዶ/ር አብይ ላይ ካሉኝ ቅሬታዎች አንዱ፣ ምናልባትም ዋናው፣ ሌብነትንና ሌባን ለመከላከል ከወሬ በዘለለ እርምጃ መውሰድ አለመቻሉ ነው። ምናልባት አብዛኛው ሌባ ሆኖበት ተቸግሮ ይሆናል። ወይም ጊዜ እየጠበቀ ይሆናል። ወይም እንደ መለስ ዜናዊ የፖለቲካ ታማኝነትን ለማግኘት ሲል ሌቦችን አይቶ እንዳላየ እያለፋቸውና ሲያፈነግጡ የስርቆት ካርዳቸውን ለመምዘዝ አስቦ ይሆናል ። ወይም የስርቆት መከላከያ መንገዱ ጠፍቶበት ይሆናል። ወይም ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም ብሎ ንቆት ይሆናል ። ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን፣ ዶ/ር አብይ ባለፉት አራት ዓመታት ብሄር፣ ሃይማኖት፣ ታማኝነት፣ ምህረት ወዘተ ሳይል ሌብነት ላይ ሰይፉን ቢያነሳ ኖሮ፣ አሁን የሚታዩት ችግሮች ቢያንስ አርባ በመቶ ይቀንሱ ነበር። ህዝቡም ጆሮ በመቁረጥ ይተባበረው ነበር። የግጭቶችና የኑሮ ውድነት መንስኤዎችን ብንተረትራቸው የሚያደርሱን የሌብነት ስር ላይ ነው።

ለነገሩ ካመኑበት አሁንም አልረፈደም።

ፋሲል የኔዓለም

08 Apr, 19:41


የደርግ መንግስት በቅድሚያ ወያኔን እንምታ ወይስ ሻዕቢያን በሚለው ጥያቄ ዙሪያ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እንደነበር በቅርቡ የታተመው የሌ/ጄ ሐዲስ ተድላ መጽሃፍ በዝርዝር ያስረዳል። ኮ/ል መንግስቱ ወያኔን በመናቅ፣ የሰራዊቱ ሃይል ሁሉ ሻዕቢያ ላይ ማረፍ እንዳለበት ጽኑ አቋም በመያዛቸው፣ ወያኔ እየተጠናከረ መምጣቱን ጄኔራሉ ጽፈዋል። አሁን ደግሞ የብልጽግና መንግስት በኦነግ ሸኔና በወያኔ መካከል ውጥረት ውስጥ መግባቱን እያየን ነው። ኦነግ ሸኔ ተራ ዜጎችን ከመግደልና ማፈናቀል አልፎ፣ ለማዕከላዊ መንግስቱና ለኢትዮጵያ ህልውና ስጋት እየሆነ ነው። የመከላከያ ሃይላችን ያለውን አብዛኛውን ሃይል ማን ላይ ያሳርፈው የሚለው ጥያቄ የወደፊቱን የወያኔን የሸኔን እንዲሁም የአገራችንን እጣ ፋንታ የሚወስን ይሆናል።

በደርግ የመጨረሻዎቹ ጊዜያት "ስፖርታኬድ" የሚባል ጸረ ሽምቅ ወታደራዊ ስልጠና በሰሜን ኮሪያዎች ይሰጥ እንደነበርና ይህም ስልጠና ውጤት ማምጣት ጀምሮ እንደነበር ጄ/ል ሐዲስ ይናገራሉ። መንግስት የህዝቡን ልብ ለመግዛት ከሚሰራው የፖለቲካ ስራ በተጨማሪ እንዲህ አይነት ጸረ ሽምቅ ስልጠናዎች የሚጠናከሩበትን መንገድ መፈለግ ያለበት ይመስለኛል።

በደርግ ውስጥ ተሰግስገው የነበሩት የውስጥ ፍልፈሎች መረጃ በማቀበል ወታደራዊ ዘመቻዎች እንዳይሳኩና መንግስት እንዲወድቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ። አሁንም ብልጽግና ውስጥ ያሉ ፍልፈሎች ተመሳሳይ ስራ በመስራት ጸረ-ሸኔ ወታደራዊ ዘመቻዎች እንዳይሳኩ እየሰሩ መሆኑን ባለስልጣናቱ እየተናገሩ ነው። እነዚህን ፍልፈሎች መንጥሮ የማውጣት ቅድሚያ ሃላፊነት የደህንነቱ ቢሆንም፣ ህዝብ ካልተባበረ መስሪያ ቤቱ ብቻውን ምንም ማድረግ አይችልም።

ይህ ጊዜ የአገራችንን ህልውና ለማስከበር በጋራ የምንቆምበት እንጅ፣ በፓለቲካ ልዩነት እየተወዛገብን መጥፊያችን የምናመቻችበት መሆን የለበትም። ልብ ያለው ልብ ይበል።

ፋሲል የኔዓለም

07 Apr, 18:50


የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ የሩስያን ከተመድ የሰብዓዊ መብት ጉባኤ መባረር በመቃወም ድምጽ ሰጥቷል። የኤርትራ መንግስትም ተመሳሳይ እርምጃ ወስዷል። የኢትዮጵያ ውሳኔ የተመድን የሰብዓዊ መብት ጉባኤ አሰራር ከመቃወም የመነጨ እንደሆነ አስባለሁ። በሩስያ ላይ የተላለፈው ውሳኔ ነገ በኢትዮጵያና በኤርትራ ላይ ሊደገም እንደሚችል መገመትም አይከብድም። ከዚህ አንጻር ከታየ ኢትዮጵያ ተቃውሞዋን መግለጿ ተገቢ ይመስላል ። ግን አሁን ካለንበት የፖለቲካና የአለማቀፍ ግንኙነት አንጻር ድምጸ ታዕቅቦ ማድረግ አይሻልም ነበር ወይ የሚል ጥያቄ አነሳለሁ። የመንግስትን ምክንያት ለመስማት ቸኩያለሁ። ምዕራባውያን የሚከፍቱብንን የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ለመመከትስ ተዘጋጅተናል?

ፋሲል የኔዓለም

06 Apr, 09:00


በዲፕሎማሲው ዓለም የካሮትና ዱላ ምሳሌ በደንብ የሚታወቅ ነው። ባጭሩ፣ ጥሩ ስትስራ "ካሮት" ፣ መጥፎ ትስስር ደግሞ " ዱላ" ይከተልሃል ማለት ነው። አስተሳሰቡ በአገሮች መሃል የአዛዥና ታዛዥ፣ የጌታና የሎሌ፣ ወይም የበላይና የበታች ግንኙነት መኖሩን የሚያሳይ ነው። ጥሩ ባህሪ ስታሳይ የሚሸልምህ፣ መጥፎ ባህሪ ስታሳይ ደግሞ የሚቀጣህ አለቃ ወይም ጌታ እንዳለህ እንድትገነዘብ ያደርግሃል። በሌላ አነጋገር ጌታህ የሚፈልገውን ከፈጸምክ፣ የምትበላው ካሮት፣ እምቢ ካልክ ደግሞ የሚበላህ ዱላ ይከተልሃል ማለት ነው።

የአሜሪካ ባለስልጣናት የኢትዮጵያ መንግስት የሚሉትን ከፈጸመ HR 6600 የተባለውን ህግ ውድቅ እንደሚያደርጉለት ፣ እምቢ ካለ ግን ህጉን አጽድቀው እንደሚቀጡት ገልጸው፣ ህግ የማጽደቅ ሂደቱን ለጊዜው ገታ አድርገውታል።

ደሃነት እና ኩራት አብሮ አይሄድም እንጅ፣ ይህን ጊዜ፣ ከሉዓላዊነታችን የሚበልጥ ነገር የለምና የፈለጋችሁትን ህግ አውጡ ብለን፣ የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን ለማስፈጸም እንነሳ ነበር። ደሃነታችን ግን ይህን ለማድረግ አልፈቀደልንም። ስናሳዝን።

ደሀ ሙሉ ነጻነት ኖሮት የሚከበረው ራሱን ሲችል ነው። እነአሜሪካ ከፈጠሩልን የጌታና ሎሌ ግንኙነት መውጣት የምንችለው፣ በወሬ፣ በእርስ በርስ ንቁሪያና ግጭት ሳይሆን፣ በጋራ ስራ ብቻ ነው። ይህ የጋራ የስራ መንፈስ በእያንዳንዳችን ላይ ሰርጾ፣ ራሳችንን ካልቻልን፣ ሲጨብጡን የምናለቅስ፣ ሲለቁን የምንደሰት፣ ነጻነት ያለን የምንመስል፣ ነጻነት አልባ ህዝብ ሆነን እንቀጥላለን።

ፋሲል የኔዓለም

03 Apr, 08:21


በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ እያደረገለን ላለው ድጋፍ እጅግ እናመሰግናለን። በኢትዮጵያ ያለው ወገናችን የሚልክልን የሞራል ማበረታቻ ደግሞ በቃላት ለመግለጽ የሚቸግር ነው። ይህ ድጋፍ ሸክማችን ያከብደዋል። ሸክሙን የምንሸከምበት ብርታቱን ፈጣሪ ይስጠን። ባላገሩ ቲቪ ላይ አጣናችሁ እያላችሁ ለምትጠይቁን ወገኖች፣ የ ኢ ኤም ኤስ ባልደረቦቼ በተደጋጋሚ እንደገለጹት፣ አንድ እርምጃ ስንሄድ አንድ እንቅፋት ያጋጥመናል፣ እሱን ዘለነው ስናልፍ፣ ሌላ ግንድ ተጋድሞ ይጠብቀናል። አሁን ዘለን ዘለን፣ የመጨረሻውን እቅፋት ላይ የደረስን ይመስለኛል። እናያለን።

ህዝብን ይዞ የሚረታ የለምና ድጋፋችሁ አይለየን።

እናመሰግናለን ።

ፋሲል የኔዓለም

02 Apr, 21:06


በዚህ ወቅትም ይሁን በማንኛውም ጊዜ፣ ኢትዮጵያ ልትጣላት ቀርቶ ልታስቀይማት እንኳ የማይገባ አገር ብትኖር፣ ኤርትራ ናት። ኤርትራ የሰሜን እዝ በተመታ ጊዜ ከዋለችው ውለታ በተጨማሪ ሱዳንና ግብጽ አብረው ሊያጠቁን በተነሱበት ጊዜ፣ ከጎናችን ተሰልፋ እውነተኛ ወዳጅነቷን አሳይታናለች። የኤርትራ መንግስት የቱንም ያክል ዋጋ ያስከፍለው፣ ያመነበትን ነገር ያለምንም ማወላወል ያስፈጽማል፤ የሚነበብ፣ የሚገመትና የሚታመን የውጭ ፖሊሲ ያራምዳል።

ኤርትራ እና ኢትዮጵያ እጣ ፋንታቸው አንድ ስለሆነ ተከባብረውና ተደጋግፈው መጓዝ ምርጫቸው ሳይሆን ግዴታቸው ነው። ኤርትራ በኢትዮጵያ ላይ፣ ኢትዮጵያም በኤርትራ ላይ ቅሬታ ቢኖራቸው፣ ጎረቤት ሳይሰማ ቁጭ ብለው ተነጋግረው መፍታት አለባቸው።

መንግስታችን የሚነበብና የሚታመን የውጭ ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል። አንዴ የአፍሪካ ቀንድን እናጣምራለን ስንል፣ ሌላ ጊዜ ፖን አፍሪካኒዝም እናራምዳለን ስንል እንደገና ምዕራባውያን ደጅ ሄደን ስንለማመጥ ስንታይ፣ ሌሎች አገሮች እኛን አምነው ለመከተል ይቸገራሉ። ጠላቶቻችንም ይንቁናል። የውጭ ፖሊሲያችን፣ የአስር፣ የሃያ፣ የሃምሳ ዓመት እየተባለ ሊቀረጽ ይገባዋል። በዘላቂነት የማንፈጽመውን አጀንዳ በስሜት ተነድተን ወይም ለአጭር ጊዜ የፖሊቲካ ትርፍ ብለን፣ ለአንድ ሳምንት አንስተን በሁለተኛው ሳምንት ላይ አንጣለው። ከልብ ያመንበትን አጀንዳ ብቻ ይዘን እስከመጨረሻውን እንጓዝ።

በግሌ በአፍሪካ ጥምረት ( በፖን አፍሪካኒዝም) ከልብ የማምን ሰው ነኝ። የዶ/ር አብይ መንግስት ፖን አፍሪካኒዝምን ማቀንቀን ሲጀምር ከልቤ ተደስቼ ነበር፣ ግን መልሶ አቀዘቀዘውና ሃሞቴን አፈሰሰው። አሁን ፖን አፍሪካኒስቶችን ፍለጋ አይኔን ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ እየወረወርኩ ነው።

ለማንኛውም አፍሪካን ባናጣምር እንኳ ከኤርትራ ጋር እንዳንጣላ መንገዳችን ሁሉ ብልጠትና ጥንቃቄ የተሞላበት ይሁን።

ፋሲል የኔዓለም

01 Apr, 21:17


በኢትዮጵያ ውስጥ አሉን ከምንላቸው አንድ ሁለትገለልተኛ ተቋማት ውስጥ ግንባር ቀደሙ፣ በዶ/ር ዳንኤል በቀለ የሚመራው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( ኢሰመኮ) ነው። ኮሚሽኑ የምንጃር ሽንኮራውን ጉዳይ በፍጥነት አጣርቶ እስኪነግረን ድረስ ፍርድ ከመስጠት መታቀቡ፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍትት ያግዛል።

በሺ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የምንገኝ እኔንና እኔን የመሳሰሉ ሰዎች፣ የምንሰጠው አስተያየት፣ ግጭቱ እንዳይባባስ፣ የተጎዱት እንዲረዱና ፖለቲካዊ መፍትሄዎች እንዲመጡ ከማሳሰብ ያለፈ ባይሆኑ ይመረጣል። አማራም ይሙት ኦሮሞ የሞተው ኢትዮጵያዊ ወገንችን ነው። ሃዘኑ የሁላችንም ነው። የአንድ ኢትዮጵያዊ ሞት ሁላችንንም ካላመመን፣ ኢትዮጵያዊነታችን የከንፈር እንጅ የልብ አይደለም ማለት ነው። በእርግጥ በጥጋባቸውና ኢትዮጵያዊነትን አንፈልግም እያሉ እየገድሉ የሚሞቱ አሉ። ለእነሱ ልብ ይስጣቸው ከማለት ውጭ ሌላ የምለው ነገር የለም። ኢትዮጵያዊነቱን አክብሮ የሚኖረው ግን ሁሉም ወገኔ ነው።

ፋሲል የኔዓለም

26 Mar, 23:00


ብልጽግና ያካሄዳቸውን ህዝባዊ ስብሰባዎች ተከታተልኳቸው። በመላ አገሪቱ ያለው ህዝብ ተማሯል- በሰላም እጦት፣ በኑሮ ውድነት፣ በሌብነት፣ በስራ እጦት፣ በአገልግሎት እጦት ወዘተ። ፖርቲው ስልጣን በያዘ በ4 ዓመታት ውስጥ ወይም በተመረጠ ሰባት ወራት ውስጥ ህዝቡ በዚህ ደረጃ ከተማረረ፣ እጅግ አሳሳቢ የሆነ ችግር አለ ማለት ነው። ብልጽግና የሰላም እጦቱንና የኑሮ ውድነቱን ችግር ከህወሃትና ከሸኔ ጦርነት እንዲሁም ከኮቪድና ዓለማቀፍ ፖለቲካው ጋር እያያያዘ ምክንያት ለመስጠት ቢሞክር እንኳ፣ ከስርቆትና ከብልሹ የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚነሳበትን ችግር፣ ምንም ምክንያት ቢያቀርብ፣ ህዝብን በበቂ ሁኔታ ማሳመን የሚችል አይመስለኝም።

ህዝቡ ምሬቱን ገልጿል፤ ምሬትን በማስተንፈስ ደግሞ ትንሽ መጓዝ ይቻል ይሆናል፣ ብዙ ርቀት መጓዝ ግን አይቻልም። መንግስት መጠንቀቅ ያለበት ህዝቡ ወደ " ብንናገር ምን ዋጋ አለው" አይነት ስሜት ውስጥ እንዳይገባ ነው። ህዝብ ወደዚህ ስሜት ውስጥ ከገባ መመለሻ የለውም።

የህዝቡን ቀዳሚ ጥያቄዎች መሬት ላይ በሚታይ ስራ ለመፍታት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን በፍጥነት ማሳየት ይገባል። በተስፋ የተሞላ ህዝብ ተስፋው የተሟጠጠ ጊዜ የሚያቆመው አይኖርምና።

ፋሲል የኔዓለም

25 Mar, 18:05


ትክክለኛው የኢሳት ኢንተርናሽናል የዩቱብ ቻናል https://www.youtube.com/channel/UCCJbY4YdJIUk7Lygrkg5IRA

ፋሲል የኔዓለም

25 Mar, 09:01


ውድ የኢሳት ኢንተርናሽናል ቤተሰቦች

እያሳያችሁን ላለው ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን ። ከኢሳት የተለየንበትን ምክንያት ከብዙ በጥቂቱ ገልጸናል። በአጭሩ የተቃወምነው እንደ ደርግና ኢህአዴግ፣ "ጊዜያዊ" ብለው፣ ቋሚ የሆኑትን፣ "አሸጋጋሪ" ብለው ገብተው ተሸጋጋሪ የሆኑትን አካሎች ነው። ለሶስት ዓመታት ያነታረከን፣ የህግ፣ የመርህና የነጻ ተቋም ምስረታ ሂደት እንጅ፣ የገንዘብ ጉዳይ አልነበረም። ያው የቀድሞው ትውልድ ዋናውን አጀንዳ ለማስረሳት ሲል፣ ጥቃቅኑን አጀንዳ ዋና አጀንዳ አድርጎ ማስቀየስ እንደሚችል ከመለስ ዜናዊ ድርጊት በቂ ትምህርት የወሰድን በመሆኑ፣ እንዲህ አይነቱ አጀንዳ ማዛባትና ፍረጃ ብዙ አይገርመንም።

ለማንኛው እኛ የራሳችንን መንገድ መርጠናል። እነሱም የራሳቸውን መንገድ መርጠዋል፤ እንዲሳካላቸው ምኞቴ ነው። የእኛን ራዕይ የምትደግፉ በዚህ የቀጥታ የባንክ አካውንታችን ገንዘብ መላክ እንደምትችሉ በአክብሮት እገልጻለሁ

Bank of America

Account number 4350 53871437

ACH routing number 051000017

Swift code BOFAUS3N

ABA REUTING (wire) 026009593
Account Title: Corporation for Public Media INC .

DBA ESAT International

በጎ ፈንድ ሚ ለመርዳት የምትፈልጉ ደግሞ፣ ይህን ሊንክ ተጠቀሙ።

https://www.gofundme.com/f/esat-international-satellite-support-fund

በአጠቃላይ በሞራል፣ በሃሳብና በገንዘብ ስለምታደርጉልን ድጋፍ ከልብ እናመሰግናለን።

ፋሲል የኔዓለም

24 Mar, 06:54


ለኢሳት ኢንተርናሽናል ድጋፋችሁን ለገለጻችሁ ወገኖቻችን ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ተመልሰን ለመምጣት፣ እንደ ወትሮው ሁሉ፣ ዛሬም ድጋፋችሁ ያስፈልገናል። ያለን አንድ ራዕይ ነው- ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ተከባብረው የሚኖሩባትን ነጻ ኢትዮጵያ ተመስራታ ማየት። ራዕያችንንና አላማችንን የምትደግፉ ወገኖች በሚከተለው የጎ ፈንድ ሚ አካውንት ድጋፋችሁን እንድትለግሱን በአክብሮት እንጠይቃለን።

https://www.gofundme.com/f/esat-international-satellite-support-fund

ከዛሬ ጀምሮ ዕለታዊና ሌሎችንም ዝግጅቶች በዩቲዩብ አካውንታችንን መከታተል ትችላላችሁ።
ስለሚደረግልን ድጋፍ እናመሰግናለን።

ፋሲል የኔዓለም

23 Mar, 18:59


https://m.youtube.com/watch?v=w68GGExlNtk&feature=youtu.be

ፋሲል የኔዓለም

23 Mar, 18:58


ከኢሳት መለየት ወልደው ካሳደጉት ልጅ የመለየት ያክል ቢሰማም፣ ከባዱን ውሳኔ ለመወሰን ሁኔታዎች ግድ ብለውን፣ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከተቋሙ ጋር ተለያይተናል። እስከዛሬ ለደገፋችሁን ወገኖች ሁሉ ምስጋናችን ይድረሳችሁ። ከኢሳት ጋር በጋራ ታሪክ ጽፈናል፤ ከኢሳት ኢንተርናሽናል ጋር ደግሞ አዲስ ታሪክ እንጽፋለን።
ዩቲዩባችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ደግፉን። ራዕያችን የምትደግፉ ሁሉ፣ ጉዟችሁ ከእኛ ጋር ይሁን።

ፋሲል የኔዓለም

22 Mar, 12:43


የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ባረቀቁት ኤች አር 6600 እና 3199 በተባሉ ህጎች ላይ ያላከተቱት ነገር ቢኖር፣ የመንግስትን ስልጣን ለህወሃትና ኦነግ አስረክቡ የሚለውን ዓረፍተነገር ብቻ ነው። "ተኩስ አቁሙ፣ ተደራደሩ፣ እርዳታ ለትግራይ እንዲሰጥ መንገዶችን ክፈቱ፣ ወዘተ" የሚሏቸውን ቅድመ ሁኔታዎች "እሽ" ብለን ብንቀበል እንኳን፣ "መንግስት ምንም አይነት የሃይል እርምጃ ከመውሰድ መታቀብ አለበት" የሚለውን ቅድመ ሁኔታ እንዴት ልንቀበለው እንችላለን? " The Government of Ethiopia has ceased all offensive military operations associated with the civil war and other conflicts in Ethiopia." መንግስትን መንግስት የሚያሰኘው እንዳስፈላጊነቱ የሃይል እርምጃ በመውሰድ፣ የዜጎችን ደህንነት የማስከበር ተፈጥሯዊ መብት ስላለው አይደለም ወይ? ህወሃትና ኦነግ ሸኔ ዜጎቻችንን በጠራራ ጸሃይ ሲገድሉ፣ መንግስት እጁን አጣጥፎ ከተቀመጠ ምኑን መንግስት ሆነ?

በአብይ መንግስት ላይ የሚቀርበው ትችት በህወሃትና በኦነግ ሸኔ ላይ ተገቢውን የሃይል እርምጃ ወስዶ ዜጎችን ከግድያ፣ መፈናቀልና የንብረት ዝርፊያ መታደግ አልቻለም የሚል እንጅ፣ ከበቂ በላይ የሃይል እርምጃ ወስዷል የሚል አይመስለኝም። የአሜሪካ ባለስልጣናት መንግስት ህወሃትና ኦነግ አዲስ አበባ እስከሚደርሱ እጁን አጣጥፎ ይቀመጥ እያሉን ነው? የ አሜሪካ የኮንግረስ አባላት ለኢትዮጵያ ከተቆረቆሩ፣ ለምን ህወሃትንና ኦነግን በስም ጠቅሰው፣ ጦርነት እንዲያቆሙ ካልሆነም በሽብር ወንጀል እንዲፈረጁ አይነግሯቸውም?

ይህ ረቂቅ ህግ የኢትዮጵያን ህልውናና ነጻነት የሚዳፈር ብቻ አይደለም፤ በአጠቃላይ ማዕከላዊው መንግስት ተዳክሞ ኢትዮጵያ የእነ ሊቢያን መንገድ እንድትከተል ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ኢትዮጵያ ደህንነቷን ለማስጠበቅ ከዓለም የጦር መሳሪያ ገበያ ሸመታ እንድትታደግ ብቻ ሳይሆን፣ ከኢኮኖሚና የልማት ገበያዎች በማስወጣት፣ በድህነት ብዛት እርስ በርሳችን እንድንተላለቅ ታስቦ የተዘጋጀ አደገኛ ህግ ነው። በዚህ ህግ የሚጠቀሙት ህወሃት፣ ኦነግ ሸኔ፣ ግብጽና ሱዳን ናቸው። ዋና ተጎጂው ደግሞ መንግስት አይደለም፣ የኢትዮጵያ ህዝብ እንጅ። በዚህ ህግ መንግስት ይወድቃል ብለው የሚያስቡ ሰዎች ካሉ፣ ስለማዕቀብ ጥቅምና ጉዳት የተጻፉ መጽሃፍትን ያላነበቡ ወይም የእነ ህወሃት ሃሳብ አቀንቃኞች ናቸው ። ይልቅ መንግስትን የጎዳን መስሎን፣ አገራችንን በማፍረስ ሂደት አንተባበር። የለሁበትም ማለትም ከወቀሳ አያድንም።

ልብ በሉ አሜሪካኖች ብቻቸውን የፈለጉትን አይነት ማዕቀብ ቢጥሉ፣ ያው ቢጎዳም፣ መቋቋም ይቻል ነበ፣፤ ነገር ግን ሩስያ ላይ እንዳደረጉት፣ ሌሎችን አገሮች አስተባብረው ኢትዮጵያን ለማድቀቅ ማሰባቸው ረቂቅ ህጉን አምርረን እንድንቃወም ያደርገናል። በነገራችን ላይ ይህ በኢትዮጵያ ላይ የተሰነዘረ አደገኛ ጥቃት ካላሰባሰበን፣ ሌላ ምን ሊያሰባስበን እንደሚችል አላውቅም።

ፋሲል የኔዓለም

19 Mar, 20:26


እውነትን መኖር የማይችል የሐይማኖት መሪ፣ "እውነትን ኑሩ" ብሎ የመስበክ ሞራል የለውም። እውነትን በመኖርና ለእውነት በመሞት አርአያ የሆኑ አባቶች ያሉባት ታላቋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን፣ እውነትን ተጸይፈው ሐሰትን ባፈቀሩ ሰዎች ስትመራ ማየት ልብን ያደማል። ለመኮነንም፣ ለማውገዝም ወይም ለመቆጣትም እኮ እውነትን መታጠቅ ያስፈልጋል።

ከዚህ በታች የተገለጸውን፣ ቃል በቃል፣ የተናገሩት አቡነ ማትያስ ናቸው፦

" ትግሬዎችን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ተብሎ የተጀመረ ጦርነት ነው፤ ትግሬዎች የሚባሉ ሰዎች ለምን ተፈጠሩ፣ እግዚአብሔር ለምን ፈጠራቸው፣ ትግራይ የሚባል ሃገር ፣ ትግርኛ የሚባል ቋንቋ ለምን ተፈጠረ በማለት ከእግዚአብሔር ጋር ነው ጸቡ፣ ከእግዚአብሔር ጋር ጸብ ደግሞ የሚያዋጣ አይደለም። ይህ ሁሉ ተፈጽሟል፤ እየተፈጸመም ነው። "

ለሰብዓዊ መብት መከበር መጮህ ተገቢ ነው፤ በሃሰት ላይ ቆሞ ለሰብዓዊ መብት እጮሃለሁ ማለት ግን ራሱን ሰብዓዊ መብትን መግደል ነው። ምዕመኑ እንኳን ባይከበር፣ የተያዘው የእውነት መስቀል እንዴት አይከበርም?

እውነት ሆይ ወዴት ነሽ?

ፋሲል የኔዓለም

18 Mar, 23:04


ጥሩ ሹፌር ማለት ወደ ኋላና ወደፊት፣ መታጠፊያ ላይ ደግሞ ወደ ግራና ወደቀኝ በጥንቃቄ እያየ የሚነዳ ነው። ወደፊት ብቻ የሚያይ ከሆነ፣ ድንገት ፍሬን ቢይዝ፣ ከኋላው ያለ መኪና ሊመታው ይችላል፤ የኋላውን ብቻ እያየ የሚሄድ ከሆነ ደግሞ ከፊት ካለው መኪና ጋር ሊጋጭ ይችላል ። የኢትዮጵያ የብሄር ፖለቲካ ከሁለቱ በአንደኛው ሹፌር የሚዘወር ነው።

ብዙዎች የኦሮሞ፣ ትግሬና ሌሎችም ብሄርተኛ ሊህቆች፣ ወደ ኋላ ሳያዩ ወደ ፊት ብቻ መንዳት የሚፈልጉ ናቸው። ብዙዎች የአማራ ብሄርተኞች ደግሞ ወደ ፊት ሳያዩ ወደ ኋላ ብቻ መንዳት የሚሹ ናቸው። ሁለቱም የመኪና መሪ ቢጨብጡ መኪናውን ያጋጫሉ፤ ራሳቸውንም ለአደጋ ያጋልጣሉ።

አርቲስት ቴዲ አፍሮ እንዳለው፣ የትናንቱ ከሌለ የፊቱም አይኖርም፤ የፊቱ ከሌለም፣ የትናንቱ አይኖርም። ሹፌሩ የኋላውንና የፊቱን ሚዛን አስጠብቆ ከተጓዘ፣ ተሳፋሪውንና መኪናውን ከታሰበበት ቦታ ማድረስ ይችላል። የአንዱ ሚዛን ከፍ ብሎ፣ የሌላኛው ዝቅ ካለ ግን፣ ተሳፋሪውም ሆነ መኪናው ገደል መግባታቸው አይቀርም።

ጥሩ የፖለቲካ ሹፌር ወደፊትና ወደኋላ፣ ወደቀኝና ወደ ግራ እያየ በመንዳት፣ ህዝቡን ከታሰበበት ቦታ የሚያደርስ ነው። ህግ አክብሮ የሚያሽከረክር ሹፌሩ በጭብጨባ አይተብትም፣ በጫጫታም አይረበሽም።

ኢትዮጵያ በየተቋማቱ እንዲህ አይነት፣ ፊትና ኋላ እያዩ የሚነዱ፣ ሹፌሮች በብዛት ያስፈልጓታል።

ፋሲል የኔዓለም

14 Mar, 22:02


ካድሬን ያመነ ጉም የዘገነ እንዳይሆን

በሶሻሊስት አገሮች የሚገኙ ካድሬዎች እድገት የሚያገኙት ያልተሰራውን እንደተሰራ፣ የተሰራውን ደግሞ ከልክ በላይ እንደተሰራ አድርገው ሪፖርት በማቅረብ ነው። አንዱ አለቃ ለሌላው ይህንን ሪፖርት እያስተላለፈ፣ በመጨረሻም መሪው ጋ ይደርስና መሪውም ይህን ሪፖርት አምኖ ለህዝብ ሪፖርት ያደርጋል።

መለስ ዜናዊ አንድ ወቅት "በምግብ ራሳችንን ችለን እህል ወደ ውጭ መላክ እንጀምራለን" ብሎ ቃል ገባ። እንደ አጋጣሚ በአንደኛው ዓመት ዝናቡ አማረና ብዙ የበቆሎ ምርት ተገኘ። ወዲያውኑ ምርቱ ለኬንያ ተሸጠ። ያን ሰሞን ኢቲቪና ፋና ኢትዮጵያ እህል ወደ ውጭ መላክ ጀመረች እያሉ ዓመቱን ሙሉ ጆሯችንን በፕሮፖጋንዳ ሲጠልዙት ሰነበቱ። በዓመቱ ተፈጥሮ ፊቷን አዞረችብን። ድርቅ ገባ። ድምጻችንን አጥፍተን ከኬንያ በቆሎ እየገዛን ማስገባት ጀመርን።

በምግብ ራስን ለመቻል መመኘትና ምኞትን ለማሳካት ጥረት ማድረግ ጥሩ ሆኖ ሳለ፣ በካድሬ ሪፖርት በመታለል ስህተት ላይ ላለመውደቅ መጠንቀቅ ይገባል። ቃል የተገባው እውን ሆኗል ለማለት ብቻ፣ ዶ/ር አብይ የመለስን ስህተት እንዳይደግም መጠንቀቅ አለበት ብዬ አስባለሁ።

ትርፍ ምርት ከተገኘም ትልልቅ ጎተራዎችን ሰርቶ ማከማቸት እንጅ ወደ ውጭ መላክ አያስፈልግም። ወደ ውጭ መላክ ያለብን ድርቅ ቢከሰት ቢያንስ ለሰባት ዓመታት መኖር የሚያስችለንን የእህል ምርት ካከማቸን በሁዋላ መሆን አለበት። የመጽሃፍ ቅዱሱን ዮሴፍን የኢኮኖሚ ጥበብ መጠቀም ለዚህ ጊዜ ይጠቅማል። ለጊዜው መጨነቅ ያለብን የታቀደው በትክክል መመረቱን ስለማረጋገጥ፣ ህዝባችን በበቂ ሁኔታ ገዝቶ መጠቀም እንዲችል ሁኔታዎችን ስለማመቻቸትና ካስፈለገም ስለማከማቸት ነው። ስለ ውጭ ገበያ ለማሰብ ግን ጊዜው ገና ልጅ ነው ።