Gospel @gospelfornation Channel on Telegram

Gospel

@gospelfornation


ትክክለኛውንና እውነተኛውን ወንጌል የምስራች ለአለም ሁሉ የሚያበራውን #ኢየሱስ ብቻ ሚሰበክበት
contact us @tsegamulat

Gospel Channel for Nations (Amharic)

የኢየሱስ ስም መልእክትና በሚሰበክበት የሚመጣው የእስኪን ጣቢያ መሆንን ታሳቢ የአለም ሁሉን ለአለም ለምስጋናና ውና እንዲህም በተመለከተ ቁልፎዎች መግብያ ለማሳለፍ የተለያዩ አማራጮችና የተከሰቱ ኢየሱስ አሞሌዎችን ማግኘት ይችላሉ። እኛ ሁላችን ከሁላችንም ጋር ሊሞላ ሲሆን ለሁለቱም ኢየሱስ ማሰማር እንዲስጡ ረመዳንና አለም ካሜለንን እና ሌሎችን ለምስራች እናገኘባለን። ስድስነቱን ፋይላችን @tsegamulat ላይ በቀላሉ መረጃዎችን ለማስተናገድ እንዲረዳን ሰላም።

Gospel

16 Nov, 21:56


ሙሴ ክብሩን እንዲያሳየው እግዚአብሔርን በጠየቀ ጊዜ ጌታ ምናለው ሰው አይቶኝ በህይወት አይድንምና በሰንጣቃው ዓለት መሀል ትሆናለህ! እጄንም እጋርዳሁ ጀርባዬንም ታያለህ ፊቴ ግን አይታይም።
አስቡት እራሱ እግዚአብሔር በፊቱ ቁዳሳንና ያለነውር እንድንሆን ደግሞ በክርስቶስ መረጠን!!
አቤት ፍቅር!በኢየሱስ ያልሆንነው ምናለ?!ሰንጣቃው አለታችን አብን ያየንብህ፣መንፈሳዊው አለታችን በመከራህ የህይወትን ውሃ ያፈለቅክልን፣ራስ ሆነኸን አካልህ ያደረከን በአብ ቀኝ የሰወርከን ኢየሱስ ክርስቶስ!!እንወድሀለን! ሌላማ ምን ማለት እንችላለን።

“ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”
  — ኤፌሶን 1፥4

© ጌዴዎን ጡሚሶ (ዶ/ር)

Gospel

14 Nov, 11:00


ያን ያህል አፍቃሪ አይደለሁም።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቃላቶቼ ፍጹምነት ሲያጠቃቸው ፈራኃቸው፣ በዝምታ ልተካቸው ሞከርኩኝ፣ ካንተ የሚሠወር ሚሥጢር የለኝም ታውቃለህ።

"እወድሃለሁ" እልህና ግን ደግሞ "የምር እወደዋለሁ?" ብዬ ሳስብ ላንተ ያለኝን ፍቅር በከንፈሬ እንጂ ከተግባሬ ውስጥ ፈልጌ አጠዋለሁ።

ያ'ላንተ እኔነቴ ትርጉሙ ምንም መሆኑን ጠንቅቄ ባውቅም በተግባሬ ግን ያን ያህል የ አንተ ጥገኛ አይደለሁም።

ሆኖም ግን ዝምታዬን ጥሼ ስምህን ሳልጠራ የማልውለው ነፍሴ የዳነችበቱ፣ የስምህ በከንፈሬ ላይ መጣፈጡ፣ ጣዕሙ ዕረፍት ነስቶኝ ነው እንጂ ስምህን ልጠራ እንኳ የተገባሁ ሆኜ አይደለም።

ልርቅህ ያልቻልኩ ልኖርልህም፣ እኔ መቼ ይሆን "እወድሃለሁ" በምትል ቃሌ ልክ ልወድህ የምችለው ጌታዬ!?

በቅዱሳን ህብረት ውስጥ ተቀምጬ ቃልህ ሲነገር፣ ምን ያህል እንደወደድከኝ፣ ምን ያህል ይቅር እንዳልከኝ፣ ማዳንህን በመንፈሴ ነፍሴ ስትዳስስ፣ ጥርሴን ነክሼ እያነባሁ፦

"የምትወደውን ልወድ የምትጠላውን ልጠላ፣ እንደማርከኝ ልምር እርዳኝ እንጂ! ቃልህን በየዕለቱ አነበዋለሁ፣ ለተ ቀን በፊትህ ጸሎት አደርጋለሁ፣ እንደወደድከኝ እወድሃለሁ" ያላልኩህ ጊዜ ጥቂት አይደለም።

አንተ ግን በነዚያ ክዳኖቼ ውስጥ ከ ፉከራ የዘለለ አንዳች የህፃን ፍቅር፣ በዛለ በተፍረከረከ ጉልበት አንተን ለማስደሰት መፍጨርጨሬን አይተህ ካልሆነ በቀር፦

ሽንገላዬ ምን ያህል አቁስሎህ ይሆን?

መውደዴ እያለቀብኝ ይሁን ወይ እየደበዘዘብኝ አላውቅም ብቻ ዘውትር አልወድህም፣ የምጠላህም ቀን አለ፣ የምትመቸኝም ቀን አለ፣ ስላንተ መስማትም መናገርም የሚያስጠላኝ ጊዜ አለ፣ ያንተ ፍቅር ብቻ የሚቆጣጠረኝም ጊዜ አለ።

አንተ ዘውትር መልካም ሆነህ ሳለህ እኔ ዘውትር ልወድህ አለመቻሌ እና እኔ ክፉ ሆኜ አንተ እኔን ዘውትር መውደድህ ሁሌም ይገርመኛል።

ስለወደድከኝ አመሠግናለሁ!

© ብሩክ ጴጥሮስ

Gospel

13 Nov, 19:46


°ፍቅር ግድ ይለዋል°

ብዙ ጊዜ ከመተኛቴ በፊት እና ጠዋት ከእንቅልፌ ሲነቃ ራሴን ቆንጆ መዝሙር የመጋበዝ ልምዱ ነበረኝ፤ከዶ/ር ደረጄ መዝሙሮች ዝም ብዬ አንዱን መዥረቅ አድርጌ ማጫዎት ጀመርኩ...

ገና ቢቱ ሲጀምር ከሁሉም መገጣጠሚያዎቼ ጋር ላላሁ፤ልክ መዝሙሩን ሲጀምር አቅሜ ከዳኝ፣እንደት ከተቀመጥኩበት ሙሽሽ ብዬ ከወንበሩ ላይ ወርጄ ከመሬት እንደተነጠፍኩ አላውቅም...ስስ በሆነ Old ሜሎዲ ከብዙ ትዝታ ጋር የግጥሞቹ ክብደት ሁለንተናዬን ጠፍሮ ይዞታል።

"ፊቱን መለስ አርጎ እምባዬን ባ'ይኑ ሲያይ ፈውስ ይሆንልኛል
እሩሩህ ነው ፍፁም ነፍሴን ካ'ንድ ሁለቴ አድኖ ሠጥቶኛል"

.. ሲል ቃል በቃል ግጥሙን እያስተዋልኩ፣ ድምጽ አውጥቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ፣ንፍርቅ እያልኩ።

(ፊቱን መለስ አርጎ ዕንባዬን በዓይኑ ሲያይ ፈውስ ይኾንልኛል)

ከምል ዜማ ጋር ነፍሴ ሲቃዋን ጮኻ ታሰማለች፣ ድንገት ነፍሴ ቆሽቴዋ ተነካ፣ለካ ክፉኛ ተጎድታ ነበር፤ ፊቱ እንደራባት፣ የለመደችው ምቾት እንደራቃት፣ በደንብ ታሳብቃለች፣ፊቱ ፈውስዋ መኾኑን ጠንቅቃ ታውቃለች፣ እንደዚያ ቦታ የትም ምቾት የሰጣት እንደለለ እየጮኸች ነገረችኝ።

በገሃዱ ዓለም ስስቅ የተደላደልኩ የመሰለኝ ለካ መስሎኝ ነው፤ ነፍሴ ታማብኛለች፤እርር አለች በገነች፣ባዕንባዋ የኾዱዋን ብሦት ዝርግፍ ታደርጋለች፣ ደረጄ ቀለል አድርጎ መዝሙሩን ይዘምረዋል፣ እኔ ግን እኔን አይደለሁም።

የኾነ ቁጥር አለ ደግሞ ስሜን መጥራት የቀረው፣ ይኼ ቁጥር Shocked ያረገኛል፣ ደንግጬ ዝም ነው ያልኩት።

"የኃጢአቴን መጠን
ቆጥሮ ቢመዝነው
ምህረት አይገባኝም
በውድቅት ለሊት
የከበረ ሥሙን
መጥራት መብት የለኝም"

ይኼ ስንኝ በቃ ከአቅሜ በላይ ነበር፣ በቅጽበት ስንት ጊዜ እንደማረኝ ትውስ ይለኝ ነበር፤ ከበደሌ ብዛት ሁሌ ማረኝ ታክቶኝ ጥቂት ቀናትን ብሪቅ፣ በጽድቄ አፍሬ ብሸሸው፣ ስሙን ልጠራ ክንድ ሳጣ፦

ግን ደግሞ ከርሱ በቀር ከነ ግሳንግሴ የሚያስጠጋኝ እንደሌለኝ ስገባኝ…ስንቴ በዕምባ ፉቱ ድፍት እንደምል፣ስንቴ እቅፍ አድርጎኝ እንዳስጠጋኝ ትዝ ስለኝ፣የዕንባዬ መዓት ከጉንጮቼ ዘልቆ ልብሴን እስኪያያረጥበው ይጎርፍ ነበር።

በእንባዬ መሓል እኔ <<ዛሬ እንኳን እንደኹል ጊዜዬ ይቅር በለኝ የምልህ ድፍረት የለኝም፤ ይህን ኹሉ ጊዜ ፍቅርህን ቀምሼ፣ አጠገቤ ካለው ሰው ይልቅ ዳስሼኽ፣ግን ደጋግሜ እልፍ ጊዜ ስበድልኽ፦ እንደት እስካሁን አላጠፋኸኝም?፣ እስከመቼ ትታገሰኛለኽ?>>

እያልኩ ድክመቴ አድክሞኝ ስንሰቀሰቅ ደግሞ እንዲህ ይላል…

ነገር ግን አምላኬ
እንደ ሠው አይደለም
ዘላለም የሚጥል
አልተኛም ለሊቱን
ደጁን አንኳኳለሁ
እጅ እግሬ እስከሚዝል"

ኦኦ ጌታ ኾይ ይኼን የዘመረው የደረጄ ሕይወት ከኔ ሕይወት በእጥፍ እንደሚሻል ተስፋ አደርጋለሁ፣ እሱ ሌላው ቢቀር፦ ብዙ መዝሙሮቹ ውስጥ እንዳየኹት ለሊት እንቅልፉን ሰውቶ ላምላኩ ጉዋዳውን የሚያስጎበኝ ጠንካራ ሰው ነው፤ ድካሙን በአደባባይ የሚዘምር ትሁትም ነው፤ እኔ ግን ዘውትር ስለ ጉብዝናዬ እንዲወራልኝ የሚሻ፣ ጥቂት ሳልተጋ ብዙ የምሰብክ ሸንጋይ ነኝ።

ብቻ እንቅልፌን እስኪሰዋልኽ እኔንም ሰዋኝና ወድጄህ ልሙት፣ ዕድሜዬ ያልሆንኩትን በማውራት አይለቅብኝ፤ የሆንክልኝን በማውራ፣ የሆንኩልህን በመደበቅ አሳድገኝ።

….
ተስፋ ያጣሁ መስዬ
ማን ይቀበለኛል
ወዴት እሄዳለሁ

ግድ ያለው ለነፍሴ
ኢየሱስ ነውና
ሥሙን እጠራለሁ

ዶሮ ሲጮህ ያኔ
እጁ ይዳስሠኛል
ፍቅር ግድ ይለዋል

መድኃኒት የሆነኝ
እድሜዬን ቀጣዩ
መቼ ያስችለዋል…

አሜን!

© ብሩክ መስፍን

Gospel

09 Nov, 05:45


ዛሬ 28ኛው መርሃ ግብራችን ይደረጋል ይምጡ!

Gospel

08 Nov, 09:37


ግጥም የምትወዱ ተጋበዙልን እስቲ https://youtu.be/THdpuIKEjXU

Gospel

07 Nov, 19:55


አንዳንድ ጊዜ በብዙ ነገር ግራ ተጋብተን አቅጣጫ ሲጠፋብን የሕይወት ውጣ ውረድ ልባችንን አዝሎ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ተቀምጠን እናቃለን።

ነቢዩ ኤርሚያስ እንዳለው ተሰምቶንም ይሆናል

"ሕይወቴን በጕድጓድ አጠፉ፥ በላዬም ድንጋይ ጣሉ። በራሴ ላይ ውኆች ተከነበሉ፤ እኔም፦ ጠፋሁ ብዬ ነበር።" (ሰቆ 3:53-54)

ጠፋን ያልንባቸው ጊዚያቶች ሁሉ የተሻገርናቸው ሊያጠፉን ስላልቻሉ ሳይሆን የሚደግፈን የሚሟገትልን ስላለ ነው። አይታለፍም ባልነው አስፈሪ በመሠለን ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ሆነን እንኳን ልንጠራው የምንችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

" አቤቱ፥ በጠለቀ ጕድጓድ ውስጥ ሆኜ ስምህን ጠራሁ። ድምፄን ሰማህ፤ ጆሮህን ከልመናዬ አትመልስ። በጠራሁህ ቀን ቀርበህ፦ አትፍራ አልህ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ።" (ሰቆ 3:55-58)

በጠለቀ ጉድጓድ ውስጥ እንሆን ይኾናል። በሚያስደነግጥ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ እናልፍ ይኾናል። ተስፋ በሚያስቆርጥ ዘመን ውስጥ ተስፋ ልናደርግበት የምንችለው እግዚአብሔር ግን አለ። በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ ላለ ቀርቦ አይዞህ የሚል ድምፁን የሚያሰማ አትፍራ የሚል የሚቤዥ።

በሕይወታችን ብዙ ብዙ ሆኖ ይኾናል። በተራራውም በሸለቆውም በብርሃኑም በጨለማውም በከፍታውም በዝቅታውም በደስታችንም በሀዘናችንም አብሮን የነበረ አብሮን የቀረ በጠለቀ ጉድጓድ ውስጥ ሆነን ስንጠራው ድምፃችንን የሰማ ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው።

"እንዴት ይታለፋል፥ እንዴት ይዘለቃል
ያልኩትን ተራራ አደላድለኸዋል
ያልኩትን ጨለማ ጌታ ገፈኸዋል
ኩራቴ ማረፊያ እወድሃለሁ
ሌላማ ምን እልሃለሁ" የሚል ድንቅ መዝሙር አለች የዘማሪ Denberu Bayleyegn

© ቢት ነኝ

Gospel

07 Nov, 06:51


በአማኑኤል ካቦድ አጥቢያ እንገናኝ 🙏🙏🙏

Gospel

06 Nov, 06:52


ጊዜው ግን እንዴት አባቱ ነው የሚሮጠው . . . . እስቲ ከዛሬ አስር አመት በፊት ከሰራነው ስራ አንድ ስራ ተጋበዙልን
«ይናገር ቀራኒዮ. . . .» ግጥማዊ ማይም ነው
https://youtu.be/pdScxRiuwQ8

Gospel

04 Nov, 18:26


የዚህን ልጅ ዝማሬ ግን እየሰማችሁት ነው? እኔ ወድጄው እየሰማሁት ነው።

ያ ስሰማው ሰማይ የሚያስናፍቀኝ «በሰማይ ታላቅ ምስጋና ይሆናል» የሚለውም ዝማሬ ተካቷል

«የሰማይን ኮከብ» የሚለውን ዝማሬ ስትሰሙት «ልቤ ቀራኒዮ መክተም ጀምሯል» አኹንማ «ቃል የለኝ ለስጦታህ» "እኔም ስጦታህን መቁጠር አይከብደኝ አንተም መስጠት አታቆም" ያስብላችኋል

«ወደ መስቀል ወጥተህ ከመስቀል ወረድኩኝ
ለሞት ታዘዝክና በሞት ጀርባ ቆምኩኝ
ላማ ሰበቅታኒ ያልክልኝ ኤሎሄ
ፍቅርን ያስቆጠርከኝ የመውደድን ሆሄ»
እያላችሁ አብራችሁ እያቀነቀናችሁ እውነትም «አንተን ቀምሼ ወደ ኋላ አልልም» ትላላችሁ

ደግሞ «የንጋት ኮከቤ» የሚለው ዝማሬ ስትሰሙ እፎይታችሁ የሆነውን ክርስቶስን እያሰባችሁ አብራችሁ እንዲህ ታቀነቅናላችሁ

«ምስክሬ አዲስ ዜናዬ
ማወድስህ በማለዳዬ
አንተ እንድትልቅ አንስልኻለሁ
በመዝሙሬ እሰብክኻለሁ»
(ማነህ ሰምተኸኛል መዝሙር የሆነ የፕሮግራም ማዳመቂያና ማስጨፈሪያ አይደለም ወይም የናይት ክለብ አምሮትህን በዳንስ የምትወጣበት አይደለም ክርስቶስን በዜማ የምትሰብክበትና የምትገልጥበት ነው)

«ሰማይ» የሚለው ዝማሬው ደሞ ምን ይልሃል መሰለህ «አዲስ ምድር አለ አዲስ ሰማይ አለ ሙሽራህን ክርስቶስን የምታይበት በደሙ የተገነባ ሰማይ አለ» ይልሃል «ልኖር ነው የምሞተው፤ ያመንኹት ልነሳ ነው» የማለት አቅሙ ካለህ ና "ሰማይ" የሚለውን መዝሙር አብረን እንዘምር

«በትግሉ ሜዳ በመስቀል ውሎ
ነጻ አወጣኝ ገዳዬን ገድሎ
ይኸው መዳኔን አረጋገጥኩኝ
በጨረሰው ላይ ኑሮ ጀመርኩኝ»
የሚለውን ስትሰማማ እውነትም ምንም የምቆጥበው የለኝም ብለህ በገናህን ከሰቀልክበት አውርደህ

«መዝሙሬ ለካህኔ ለመካከለኛዬ
ከሞት ፍርድ ላስመለጠኝ ለሆነኝ ዋስትናዬ» ትላለህ ምነው ሲሉህ በነፍሱ ተወራርዶ ያዳነህ አምላክ እንዳለህ እንዲህ ትተርካለህ
«ብይን አግኝቷል የጥንቱ ክሴ
ሊቀካህኔ ሆኖልኝ ዋሴ»

ደሞ... ደሞ
«ስለኔ የደማው መዳፉ
የጀርባው ቁስል የጅራፉ
በደም የተሸፈነው ፊቱ
የእጁ ችንካር እትራቱ
የተከፈለው ለነፍሴ ካሳ
የደሙ ዋጋ እንዴት ሊረሳ» የሚለውን ስትሰማማ በቃ ነፍስም አይቀርልህም

«ልጅ ነኝ» ይልህና ደሞ «ወራሽ» መሆንህን ይነግርሃል እናም አትጠራጠር «ካስማህ» ክርስቶስ ነው ብሎህ ልብህን ያፀናዋል ብቻ ግን ያ የተሰቀለውን ክርስቶስን የሚሰብክ ዝማሬ ነው ይዞልን የመጣው። «አይነጥፍም ዜማዬ» ቢልም እውነት አለው «ከሕይወት ውሃ ምንጭ ከሆነው ከክርስቶስ የቀዳ» አገልጋይ ዜማው አይነጥፍም ዜማውም ክርስቶስ ነው።

ዝማሬዎቹን እንድታደምጡ አለመጋበዝ ንፉግነት ነው።

ብቻ ብቻ የሚደመጡ የዝማሬ ሰንዱቆች እየበዙልን ነው መሰለኝ . . . ጆሮኣችንን ከኳኳታና ከጩኸት የሚያሳርፉ ዝማሬዎች እየቀረቡልን ነው። እግዚአብሔር ይመስገን🙏🙏🙏

እና ይህችን መዝሙሩን ደሞ ጋበዝኳችሁ

"በሠንሰለቱ የታሠረልኝ
በርባንነቴን ሻረልኝ
30 ዲናር ነበር ዋጋዬ
ተቤዥኝ እንጂ ቤዛዬ
እንደፍቅሩ ማያባራ
እንደመልኩ የሚያበራ
በእሳት መሀል ሰጠኝ ቅኔ
የሚንኳለል ከልሳኔ"

https://youtu.be/15J3fpB1Wag?si=TqbJfker0uJjuYKj

Habtamu Shibru ፀጋ ይብዛልህ🖤🙏🖤

Gospel

29 Oct, 13:00


https://youtu.be/qz6bcXtDHP4

Gospel

23 Oct, 06:35


በተሞላ ነገር ላይ ለመጨመር መሞከር ትርፉ ማፍሰስ ነው!ዓለማዊነት እና ምኞቱ  የማይዘልቀን በእግዚአብሔር ቃል ስንሞላ ነው!ጌታ ኢየሱስ የዲያብሎስን ፈተና አሸንፎ ያሳየን ጥቅስ እየጠቀሰ ነው...''እንዲህ ተብሎ ተፅፏል''...።ጌታን ለመምሰል የሚያስፈልገን ፀጋ እና ሁሉ ነገር ተሰቶን ሳለ ደካማ የሆነው ለምን ይመስላችኃል?ዋርካ ትልቅ ዛፍ ከመሆኑ በፊት ዘር ነበር!ያለዘር ዕድገት ሆነ ፍሬ የለም!ስለዚህ ነው ጳውሎስ እኔ ተከልኩ አጵሎስ አጠጣ እግዚአብሔር ያሳድጋል ያለው።እምነት በቃሉ ነው ጊዜ ይጠብቅ እንጂ ዕድገትም በቃሉ ነው!!
ያለ እናት ጡት ወተት ህፃን እንዴት ያድግ ይሆን??

“ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።”
  — 1ኛ ጴጥሮስ 2፥2-3

ዓለማዊ ምኞትን የምናሸንፈው በትግል ሳይሆን ቃሉን በመሞላት ነው!!

© ጌዴዎን ጡሚሶ (ዶ/ር)

Gospel

21 Oct, 10:16


ዛሬም ይቀጥላል

Gospel

17 Oct, 13:54


በብዙ ከተጠቀምንበት ፤ አኹንም እየተጠቀምንበት ካለው ከተወደደው ወንደማችንና አገልጋይ ፋሲል ጥጋቡ (ፋዮ) ጋር ልዩ የስልጠና ጊዜ ተዘጋጅትዋል፡፡ አንገብጋቢ በሆኑ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችና ተያያዥ ሀሳቦች ጋር ስልጠና ይሰጠናል፡፡ እግዚአብሔር መልካም ጊዜ ይሰጠናል ታዳጊዎችና ወጣቶች በፍፁም አይቀርም፡፡

Gospel

11 Oct, 08:19


ነገ መልካም ጊዜ ይኖረናል ይምጡና ይካፈሉ
ግጥሞች
ወግ
ፅሁፎች
የአንድ ሰው ጭውውት እና ዝማሬ አሰናድተን እንጠብቃኋለን

Gospel

08 Oct, 09:54


ወርሃዊው መርሃ ግብራችን ይቀጥላል

Gospel

05 Oct, 19:07


https://youtu.be/v7iOC9FI7JA

Gospel

26 Sep, 10:31


...ፈቃድህ...

ሊያነግሱት ፈልገው - ሊጠግቡ እንጀራ
ሊበሉ ሊጠጡ - እንዳይጎል ጎተራ
ሹመት ቢክቡለት - ከላዪ ደርበው
ከመንበሩ ወጥቶ - ዘውዱን እንዲያጠልቀው
"ካባህንም ደርብ - በትርህን ጨብጥ
ከቤተመንግስቱ - ከዙፋን ተቀመጥ"
ብለው ቢማፀኑት - ሊገዙለት ወደው
ክብር ካሉት ይልቅ - መስቀሉን ቢወደው
መራራውን ፅዋ - ከንግስና መርጦ
አብን አከበረው - ፈቀዱን አብልጦ
ደስታው ያ ነበረ - ክብሩ ያ ነበረ
በመስቀሉ ስቃይ - የልቡ ሰመረ
ወዳጆቹን እንኳ - ግራ የገባቸው
እንጀራ ሲሰጡት - ጠገብኩ ሚላቸው
ቢጠረጥሩትም - ከሠው እንዲበላ
መብሉ መጠጡ - የነፍሱ ተድላ
ዓላማው ስኬቱ - አይደለም ምቾቱ
የአባቱ ፈቃድ - ነበረ ምኞቱ

שמיים shamayim 🌄

Gospel

22 Sep, 10:40


ልጅህ አይደለሁ?
ወላጅ የሌለው፣ አሳዳጊም የበደለው ወደል መስዬ በጎዳና እንዲህ ስጎፈላ ለምን ዝም ትላለህ? ከስርዓትህ ስፈታ፣ አላዋቂነትም ሲፋንንብኝ አባት አይደለህ ለምን ገረፈህ አትመልሰኝም? ዝምታህ እኮ ያነቅዛል። በኖራ የተለሰነ መቃብር ኾኜ ሳሸረግድ በትርህን አንስተህ ስንፍናዬን ከላዬ ስለምን አትፍቅም? ከጉረኖ የወጣ፤ እረኛም የሌለው በገ ይመስል ስቅበዘበዝ ድምጽህን አንስተህ ስለምን ተመለስ አትለኝም? ግኡዝ እንኳ ይታዘዝሃል እኮ። ትዕቢት ልቤን ወጥሮ ሊያደቀኝ ሲቋምጥ ከልካይን ስለምን አትልክም?

በእርኩሰት ለሚዛብር፣ በአመጻም ለሚሰባ ሰው ከዝምታህ የከፋ ቅጣት ምን አለ? አባት አይደለህ ቁንጥጫህ የት ነው? ወንድም ጋሼ አይደለህ ኩርኩምህ ወዴት ነው? ተግሳጽህ ቅዱስ ነው በደልን ያርቃል። ዝምታህ ግን ያጎድላል!!! ለካ ቁጣህ ምሕረት ነው?! ለካ ዘለፋህ ርኅራሄ ነው! ለካ ዝምታህ ለራስ መተው ነው! መገረፍ እኮ የልጅ ነው። ዲቃላ ነው ማይቀጣ። ዕብ 12: 7-8

አልቃሻው ነብይ እንዳለ ፈጽመኽ ካልጣልክ በቀር መመለስ ያንተ ነው። ሰቆ 5:22። ወዳንተ ስትመልሰን ዘመናችን ይታደሳል። እንደ ተወደዱ ልጆችም መልሰን በአምላክትህ ሐሴት እናደርጋለን። ተግሳጽህ ሕያዋን ያደርገናል። እናም አባት ሆይ ግርዱን በበትርህ አስወግደህ፣ ብዙም ያፈራ ዘንድ ግንዱን ገረዘህ ለሕይወት አትርፈን!

© ኢብሳ ቡርቃ

Gospel

21 Sep, 12:53


The greatest sin of Christ-rejecters and the most damning work of Satan is #misrepresentation of the truth and its consequent deception.

~John MacArthur

Gospel

18 Sep, 13:44


‼️‼️‼️