ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ @dbugg21 Channel on Telegram

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

@dbugg21


ይህ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የቀን ግቢ ጒባኤ ይፋዊ የቴሌግራም መገናኛ ነው።

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ (Amharic)

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰ/ ት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ደ/ብ ማዕከል የቀን ግቢ ጒባኤን እና የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲየቴሌግራም መገናኛ አድርገናል። ስለሆነ, ይህ ተደጋጋሚ የቴሌግራም መገናኛ ህመም መገናኛ ነፃነትን ለመስራትና ለመጠቀም የፈለጉ ነው። በተጨማሪም, ይህ ቅሬታ ደግሞ ለክርስትያኑ እና እናት አሰፋ መዝገብን እና ህመምን ማስተዋወቅ ይፈልጋል።

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

22 Aug, 02:36


እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!!

▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
           የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

19 Aug, 17:26


<<ሰኞ ,ነሐሴ13>>>>>>>>

         †††      ስንክሳር     †††

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡

          †   እንኳን አደረሳችሁ   †

     🕊 ደብረ ታቦር🕊


አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው :: በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው ። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ ። ስለ እነርሱም ጌታችን የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ አለ ። ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ ። ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ ። በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት ። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው ። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው ። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና ። ሰለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያን ጊዜ ፍጹማን አልሆኑምና ። እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው ። የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት ። ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው ። ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያን ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና ። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሣው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያመጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና ። በሰማይና በምድር ሥልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም ።

ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና ። የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግምባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደ ሙታንም ሆኑ ። ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስም ወደ ቦታው ተመለሱ ። ሐዋርያትንም በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም ። ከባሕርያችን የተዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ ። እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታቸንን ድንግል ማርያምን በአበሠራት ጊዜ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው እንዴት አላት ። አምላክ ካልሆነስ ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም እንዴት አላት ። ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት ። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው እያሉ እንዴት አመሰገኑ ። ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውኃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆነ አልዓዛርን ከመቃብር እንዴት ሊያስነሣው ቻለ ። ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው እንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለ መለየት አንድ አካል አንድ ባሕርይ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን ። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ ሁል ጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን ።

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

09 Jul, 09:21


👨‍🎓🧑‍🎓የ2016 ዓ/ም ተመራቂዎች
                     💐💐  እንኳን ደስ አላችሁ 💐💐
ቀሪውም ጊዜያት ያማረ የሰመረ መንገድ ያድርግላችሁ በርቱ አይዟችሁ በሄዳችሁበት ሁሉ ሃያሉ ልዑል እግዚአብሔር ይከተላችሁ ከፊት ይቅደምላችሁ ❤️❤️❤️
የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

01 Jul, 21:45


የ2016 ዓ/ም ተመራቂዎች ለዚህች ቀን 1 ቀን ቀረው
                       እንኳን አደረሳችሁ
የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

01 Jul, 21:39


የ2016 ዓ/ም ተመራቂዎች ለዚህች ቀን 1 ቀን ቀረው
                       እንኳን አደረሳችሁ
የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

27 Jun, 20:15


የ2016 ዓ/ም ተመራቂዎች ለዚህች ቀን 6ቀን ቀረው
እንኳን አደረሳችሁ
የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

20 Jun, 14:53


📌ውድ ተመራቂዎቻችን እንደምን አላችሁ ? ለመውጫ ፈተና ዝግጅት እንዴት ነው? መቼም በጣም ጥሩ ነው እንደምትሉኝ እና በደንብ እየተዘጋጃችሁ እንደሆነ አልጠራጠርም።
✍️ከዚህ ቀጥዬ የማሳስባችሁ ሰኔ 26 ማህበረ ቅዱሳን ደ/ብርሃን ማዕከል መርሃግብር አዘጋጅቶ በታላቅ ድምቀት ያስመርቀናል። በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ማንም ተመራቂ መቅረት የለበትም።
👉ከወዲሁ  አስቡበት ሌላ መርሃግብር እንዳትይዙ
📅 ቀን   26/10/2016
ሰዓት  10:00
📍ቦታ ደ/ብ/ደ/ኃ/ቅ/ገ/የቀ/ግ/ጉባኤ ዋናው አዳራሽ

#share #join                                                              
የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

13 Jun, 06:43


#Remedial_ፈተና

ዛሬ የማጠቃለያ ፈተና ለምትጀምሩ  የRemedial ተማሪዎች ግቢ ጉባኤያችን  መልካም ምኞቷን ትገልፃለች ።


በፈተናችሁ ሁሉ አምላከ ቅዱሳን አይለያችሁ፣
ድንግል ማርያም ብርታት ትሁናችሁ ፣

በፈተና ወቅት መርሳት ያሌለባችሁ ነገሮች

🍀ጸሎታችሁ ሳይታጎል ይቀጥል

🍀ስታነቡም ሆነ ፈተና ስትጀምሩ እና   
ስትጨርሱ መጸለይ ፣

🍀 በሁሉም ማመስገን

🍀 ሌሎች እህት ወንድሞችን በጸሎት ማሰብ እና መረዳዳት

ሥራህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ አሳብህም ትጸናለች።”
  ምሳሌ 16፥3

መልካም ዕድል
#share #join የደ/ብ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ
# https://t.me/dbugg21group
Join us on telegram @dbugg21
And our group @dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

03 Jun, 12:59


አስቸኳይ የሥራ ማስታወቂያ

ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤ ምሩቃንን ተጠቃሚ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ግንኙነት እያደረገ ይገኛል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ  የግቢ ጉባኤ ምሩቃን  በማኅበሩ ሕንጻ 2ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ቢሮ በአካል በመቅረብ እና የትምህርት ማስረጃችሁን በመያዝ እንድታመለክቱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት መስክ ፡- በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ተዘማጅ ዘርፍ ከታወቀ የትምህርት ተቋም በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/የተመረቀች
የሥራ ልምድ ፡- ዜሮ ዓመት
የሥራው አድራሻ፡- አዲስ አበባ
ብዛት ፡- 15
የማመልከቻ ቀን፡- ከግንቦት 27 ቀን እስከ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም በሥራ ሰዓት ብቻ

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

28 May, 17:40


.....🕯❷❶.......🕯
እመቤታችን ግንቦት 21 ደብረ ምጥምቅ በሚባል ቦታ ለተከታታይ ለአምስት ቀን በግልፅ የታየችበት ታላቅ በዓል ነው እንካን አደረሰን🤍

ግንቦት 21 እመቤታችን ማርያም /እመቤታችን በድብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ ወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ነው።ይህም በዓል ከ33ቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ሲሆን በዚህ ቀን ግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ትገለጽላቸው ነበር።

👉እስላምም ክርስቲያንም በግልጽ ይመለከቷት ነበር። ከየአገሩ ያሉ ሰዎች ይሰበሰባሉ ድንኳን ተክለው ሰቀላ ሰርተው አጎበር ጥለው ይከትማሉ ፤ ድንግልም ከግንቦት 21 ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት ሳታቋርጥ ትገለጽላቸው ነበር፤

👉ህዝቡ የተለያየ ጥያቄ ይጠይቃታል አዳም አባታችንን አሳይን ይሏታል ገሚሱ ነብዩ ዳዊትን ገሚሱ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሳይን ይሏታል አንዳንዱም ከዚህ ቀደም የሞተ ዘመዱን እንድታሳየው ይጠይቃታል ፤እርሷም ለሁሉም ፍቃዳቸውን ትፈጽምላቸው ነበር፤ አዳምን ስትጠራው ከሔዋን ጋር ዳዊትን ስትጠራው ከበገናው ጋር ቅዱስ ጊዮርጊስን ስትጠራው ከጸአዳ ፈረሱ ጋር ነው።

ለእናቱ ለቅዱስተ ቅዱሳን ለንፅህተ ንፁሀን ለአዛኝቷ ድንግል እመቤቴ ለቅድሳን እናታቸው ለነቢያት ትንቢታቸው ለሰማእታት እክሊላቸው ለሆነች ለእናቱሲል ይማረን በቃቹህ ይበለን ከመጣብን ከዚህ ክፉ መቅሰፍት ይሰውረን🙏🤍

@dbugg21
@dbugg21group

የደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባኤ

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

28 May, 17:37


እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዝክረ ድንግል ማርያም
✥ 21✥
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የጽዋ መርሐግብር

በዕለቱም
➨ ጸሎት በአባቶች
➨ መዝሙር
➨ ትምህርተ ወንጌል በተጋባዥ መምህር
➨ የእመቤታችን ዝክር

📆 ረቡዕ 21/09/2016 ዓ.ም
⌚️ ከቀኑ 10:00
⛪️በግቢ ጉባኤው አዳራሽ

"ሁላችንም ተቀሳቅሰን በሰዓቱ እንገኝ።"

📱join our telegram channel @dbugg21
📱 Our group @dbugg21group

ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት @dbugg21bot

የደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ የቀን ግቢ ጉባኤ

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

24 May, 04:33


የተከፋፈለ ልብ💔
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው በመዝሙር እና ሥነጥበብ ክፍል የተዘጋጀው ትያትር በነገው እለት ቅዳሜ 9:00 ሰዓት ጀምሮ ይቀርባል ስለሆነም በዚህ ቀን በፍፁም እዳይቀሩ።

ባታ፦በደ/ዩ/የቀ/ግ/ጉባኤ አዳራሽ
መግቢያ ፦10birr
ከመዝሙር እና ስነ ጥበብ ክፍል


@dbugg21group

ደብረ ብርሃን ዩ/የቀን ግቢ ጒባኤ

19 May, 11:38


የግቢ ጉባኤያችን 17ኛ አመት የምስረታ በዓል ላለፋት ሦስት ቀናት ባማረና በደመቀ ሁኔታ ሲከበር ቆይቶ በዛሬው እለት የመጨረሻውን መዝጊያ በማድረግ ከተለያየ ቦታ ለመጡ እንግዶችም ሽኝት በማድረግ ፍፃሜውን አድርጓል።

በምስረታ በዓሉ ላይ የተገኙ እንግዶች በአጠቃላይ 96 የቀድሞ ምሩቃን እህት ወንድሞቻችን ሲሆኑ ካሉት አባላት አንፃር በፐርሰንት ሲሰላ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ክፍል 6 አባላትን በመቀስቀስና እንዲገኙ በማድረግ ቀዳሚው ክፍል ሲሆን አባላት እንክብካቤ ክፍል 30 አባላትን በመቀስቀስ ቀጣዩን ደረጃ የያዘ ሲሆን መዝሙርና ሥነጥበባት ክፍል ደግሞ 12 አባላትን በመቀስቀስና እንዲገኙ በማድረግ በሦስተኛነት ተቀምጧል።
የመጨረሻውን ደረጃ የያዘው ክፍል ደግሞ ቋንቋና ልዩ ፍላጎት ሲሆን ምንም አባል ያልተገኘበት ብቸኛው ክፍል ነው።

በመጨረሻም የምስረታ በዓል ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ዲ/ን ክብሩ ለበዓሉ መሳካት የራሳችሁን ድርሻ ለተወጣችሁ የግቢው ተማሪዎች፣የቀድሞ ምሩቃን እህት ወንድሞች፣የምስረታ በዓል ኮሚቴዎች ውለታችሁን ልዑል እግዚአብሔር ይቁጠርላችሁ የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በቀጣይም ከአርብ ጀምሮ የነበሩትን መረሐግብሮች በፎቶና በቪዲዩ የምናደረሳችሁ ይሆናል። እናንተም በራሳችሁ ስልክ ለማስታወሻነት ያስቀራችሁት ፎቶና ቪዲዮ ካለ በሀሳብ መስጫችን @dbugg21bot በኩል ብታደርሱን መልሰን ወደእናንተ የምናደርስ ይሆናል።

@dbugg21
@dbugg21group