ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም @joinchat_yonas_holet_debreedom Channel on Telegram

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

@joinchat_yonas_holet_debreedom

በዚህ ቻናሌ ላይ የኦርዶክስ ተዋህዶ መንፈሳዊ ትምህርቶች፣መዝሙሮች፣እንዲሁም የተለያዩ መረጃዎችን ያገኛሉ። ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም (Amharic)

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም ትምህርት ከምንጠቀማቸው በተመለከተ በየናው ዋናው ማህበረሰብ ውስጥ ላይ በሚሰራበት ስፖንት፣ አሳምና ነጠላ መንፈሳዊ ትምህርት እና ኦርዶክስ መዝሙርት ዝግጅት ለማደሬና እንዲሁም በመተከል እባኮት የሚከብድ መረጃዎችን መማር ሀብት ያግኙ። ስለዚህ ቻናሌና መሰልከት ይችላሉ ፤ ለመጫን በሚገኘው ማድረግ አስፈላጊ ነው። የሚኖርባትም ከሆነ መረጃዎችን ለመታወቅ የሚያገኙ ናቸው።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

12 Feb, 04:31

#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ አባታችን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ::

🔷👉 እነርሱም ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: ታዲያ አንድ ቀን አቅሌያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን #ንስኢ_ወልደ_ዘይትሌአል_ቀርኑ_እምኑኀ_ሰማይ " ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ የሚል ድምጽ ሰማች ::

በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ

🔴👉 ፃዲቁ አባታችን አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው " ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን " ብለው በማመስገናቸውና ኋላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ ።

🔵👉 ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመደ ብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ #ፍሱሐ_ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአርገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

🔷👉 በገድለህ በትሩፋትህ ከሞት ነፍስ ከርደተ ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? #ዘኬድከ_ጸበለ_እግረከ_ይልህሱ_ወበ_ውእቱ_ይጽግቡ ።" የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::

🔵👉 ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር ።

🔷👉 ከዚህ በኋላ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ " ወበህየኒ ሐልውከ ነፍሳተ ወታወጽኦሙ" ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ #ምድረ_ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ #ዝቋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር ::

🔴👉 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ #ዘገብረ_ተዝካርከ_ወዘጸውአ_ስመከ_እምህር_ለከ " ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከአልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ " #ተንስእ_ወጻእ_መሀርኩ_ለከ_ኵሎ_ኢትዮጵያ ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::

👉 ከዚህ በኋላ #ምድረ_ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትክል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል ::

🔴👉 ለ100 ዓመት ሕዝበ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው በዝቋላ ተራራ በሚገኘው ሐይቅ ተዘቅዝቀው ለምነው የምሕረት ቃልኪዳንን የተቀበሉበት እንዲሁም እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 5/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

10 Feb, 04:24

#ፆመ_ነነዌ_ለምን_ይፆማል?
🔵#መቼ_ይጀምራል?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

🔴👉 ፆመ ነነዌ ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን ፆሙ ሶስት ( 3 ) ቀን ብቻ ነው ። ቀኖቹም በየዓመቱ ሰኞ ማክሰኞ ረቡዕ ናቸው ። የነነዌ ፆም በመባቻ ሐሙስ ( አቆጣጠር ) ከፍ እና ዝቅ ስለሚል አንድ ጊዜ በጥር አንድ ጊዜ በየካቲት ይሆናል ።

🔵👉 እናም የ2017 ዓ.ም ፆመ ነነዌ #የካቲት 3 ሰኞ ይጀምራል። የቤተ ክርስቲያን አባቶች ይህን ፆም እንድንፆም የወሰኑት ልትጠፋ የነበረች ነነዌን በፆም ምክንያት እግዚአብሔር ይቅር ስላላት ይህን አምላካዊ ይቅርታውን ለዘለዓለም ለማሰብና ዛሬም በዚህ ዓለም ከነነዌ የከፋ ርኩሰትንና ኃጢያት ስላለ የነነዌን ሕዝብ ይቅር ያልክ አምላክ ዛሬም እኛን ይቅር በለን ለማለት ነው

🔴👉 የነነዌ ሰዎችም እግዚአብሔርን አመኑ ለፆም አዋጅ ነገሩ ከትልቁም ጀምሮ እስከ ትንሾቹም ማቅ ለበሱ ወሬውም ለነነዌ ንጉስ ደረሰ። እርሱም ከዙፋኑ ተነስቶ መጎናፀፊያውን አውልቆ ማቅንም ለበሰ። አመድ ላይም ተቀመጠ አዋጅ አስነገረ።

🔵👉 በነነዌም ውስጥ የንጉሱንና የመኳንቱን ትእዛዝ አሳወጀ እንዲህም አለ ሰዎችም እንስሶችም አንዳችም እንዳይቀምሱ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ። ሰዎችና እንስሳትም በማቅ ይከደኑ። ወደ እግዚአብሔርም በብርቱ ይጩሁ። ሰዎችም ሁሉ ከክፉ መንገዳቸውና በእጃቸው ካለው ግፍ ይመለሱ።

🔴👉 እኛ እንዳንጠፋ እግዚአብሔር ተመልሶ ይፀፀት እንደሄነ ከፅኑ ቁጣውስ ይመለስ እንደሆነ ምን ያውቃል በማለትም አሳሳበ። እግዚአብሔርም ከክፉ መንገዳቸውም እንደተመለሱ በስራቸውም አየ። እግዚአብሔር አምላክም ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተፀፀቶ አላደረገውም
ት ዮናስ ( 3፤ 5- 10)

🔴👉 የነነዌ ህዝብን በምህረቱ የጎበኘ ቸር አባት ለሀገራችንም ለህዝባችንም ምህረትና ቸርነቱን ያብዛልን ፆሙን የበረከት ፆም ያድርግልን አሜን ፫

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
የካቲት 3/2017 ዓ.ም

08 Feb, 08:27

የካቲት 1/2017 ዓ.ም

08 Feb, 03:03

https://youtu.be/nRpWSCejuqQ?si=3Uw__hocIntlPQqR

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

04 Feb, 06:29

#መድኃኔዓለም
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉እንኳን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን #ለኢየሱስ_ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን ዋጋ ለከፈለበት ወርሐዊ መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሰን

🔴👉 #መድኃኔ_ዓለም ማለት ዓለምን ያዳነ የዓለም መድኃኒት ማለት ነው።

🔶👉 ሰው በመበደሉ ምክንያት ከክብር ተዋርዶ ይኖር ነበር ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የተዋረደውን ሰው እርሱ በመስቀል ተሰቅሎ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው "ምን ዓይነት ፍቅር ነው ።

🔵👉 እራቁትን መሰቀል ምን ያህል አሳፋሪ ነገር እንደሆነ እናውቀዋለን ጌታ ግን እኛን ለማዳን ብሎ ራቁት መሰቀልን ናቀው እርሱ በፈጠራቸው ፍጥረታት ተተፋበት ።

🔴👉 እኛን ትህግስት ሊያስተምረን እነርሱን ማጥፋት እየቻለ እርሱ ግን በፍቅር እያየ የሚያረጉትን አያውቁምና አባት ሆይ ይቅር በላቸው ይል ነበር ክርስቶስ እኛን ለማዳን ሲሰድቡት አልተሳደበም ሲንቁት አልናቃቸውም ሲታበዩበት ሁሉ እርሱ ግን በትህትና ያያቸው ነበር ።

🔷👉 ታድያ እኛ ደግሞ ራሳችንን ለማዳን ሰዎች ሲንቁን ሲሰድቡን ሲታበዩብን በፍቅር በዝምታ ማለፍ ይጠበቅብናል ይህን ካደረግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር ተብለን እንጠራለን ።

🔴👉 በ5ቱ ቅንዋት (ችንካሮች) ነበር የቸነከሩት, በመስቀሉ ስር የተገኙት ድንግል ማርያምና ሐዋርያው ዮሐንስ ነበሩ እኛም በመስቀሉ ስር ለመገኘት ከፈለግን ትዕግስትን ፍቅርን ትሕትናን መለማመድ ይኖርብናል ።

🔴👉 አምላካችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ በፈቃድህ በተሰቀልክ ጊዜ በቀኝህ ለተሰቀለዉ የገነት መክፈቻን እንደሰጠኸዉ ወደ ገነትም እንዳስገባኸዉ በኃጢአት የወደቅነዉን ልጆችህን ነፍስና ስጋችንን አክብረህ ብርሀነ ፀጋህን አብራልን

🔴👉 መድኃኔዓለም ሆይ እኛን ለማዳን መከራን ለመቀበል ዘንበል ላለው ራስህ ሰላም እላለሁ

🔵👉 የቅዱሳንን ጥሪ ለሚሰማ እዝንህና ድሆችን ለሚመለከቱ አይኖችህ ሰላም እላለሁ

🔷👉 ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ በመስቀል ላይም በሰቀሉህ ጊዜና ጎንህንም በጦር በወጉህ ጊዜ አንዳችም የተቃውሞ ትንፋሽ ላልተነፈሰ እስትንፋስህም ሰላም እላለሁ

አቤቱ አምላኬ መድኅኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እኛ ልጆህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነብስ ጠብቀን

አቤቱ ጌታ ሆይ, እንደ በደላችን ሳይሆን እንቸርነትህ ኢትዮጵያን አስባት፣ ማራት፣ ይቅር በላት ስለድንግል ብለህ, ሠላምህን፣ ፍቅርህን፣በረከትህን አትንፈጋት

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 27 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Feb, 18:43

https://youtu.be/V4O7_WrIvKE?si=GXs_tzx-Awhgo2OP

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Feb, 05:16

#ጥር 24 #አባታችን_አቡነ_ተክለሐይማኖት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 #ጥር 24 የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት ስባረ አጽማቸው ነው፤ በረከታቸው ይደርብን፡፡

🔵👉 የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥ እግዚአብሔርም ከሁሉ ያድናቸዋል፡፡ መዝ 34፣19 አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ
ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል።

🔴👉 ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል።

🔵👉 ከዚያም ለ7 ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል። ዕረፍታቸውም በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ
24 ቀን ነው።

🔴👉 በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ዛሬ ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።

የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን

           ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

   ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 24 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Feb, 04:34

https://youtu.be/cbRGERS-_9E?si=TThjZ1Eh_9R_Ch1-

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

29 Jan, 07:25

የሀዘን መግለጫ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
በምዕራብ ሸዋ ሃገረ ስብከት የወልመራ ወረዳ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ክቡር አባታችን አባ ጴጥሮስ ከዚህ አለም ድካም አርፈዋል።

በረከታቸው ይደርብን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን እንመኛለን

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 21/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

29 Jan, 06:30

#ጥር_21_የእመቤታችን_በዓለ__ዕረፍት
       #አስተርእዮ_ማርያም
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 አስተርእዮ ማለት መታየት ፣ መገለጥ ማለት ነው። ቃሉ አስተርአየ ታየ ፣ ተገለጠ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ነው። ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት በሥጋ የተገለጠበት ( የታየበት ) ፣ አንድነት ሦስትነቱም የተገለጠበት ወቅት በመሆኑ ከልደት በዓል እስከ ጥር መጨረሻ በሙሉ ዘመነ አስተርእዮ በመባል ይታወቃል። የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር “ #አስተርእዮ__ማርያም ” ተብሏል።

🔵👉 ልቡናዋ በይኩነኒ የጸና ንጽሐ ሥጋ ፣ ንጽሐ ነፍስ ፣ ንጽሐ ልቡና አስተባብራ የያዘች ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በቃል መነገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ተንሥኢ ወንዒ”  የነፍሴ ደስታ የኾንሽ ውድ እናቴ ሆይ ተነሥተሽ ወደ እኔ ነዪ (መኃ ፪፥፲) ብሏታል።

#ሞታ_ለማርያም_የዐጽብ__ለኲሉ

🔵👉 ቅዱስ ዳዊት “ ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር ” መዝ.፹፮፥፫ እግዚአብሔር ማህጸንሽን ከተማ አድርጎ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የኖረብሽ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው የተደረገው ነገር ዕጹብ ድንቅ ነው እንዳለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ሆና ማረፏ ይደንቃል። ታላቁ የቤተክርስቲያናችን አባት ቅዱስ ያሬድ ሞቷ የሚያስደንቅ መሆኑን « ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የዐጽብ ለኲሉ ፤ ሞት ለማናቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል » በማለት ገልጾታል።

#ሞት_በጥር_ነሐሴ__መቃብር

🔴👉 የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ሞትና ትንሣኤ በነገረ ማርያም አበው እንደሚያስረዱት ዕረፍቷ በጥር ፳፩ እሑድ ነው። አባቶቻችን በጾመ ፍልሰታ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ሲተረጉሙ የእረፍቷን ነገር እንዲህ ብለው ይተርካሉ።

🔵👉 የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉ ስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር ፳፩ በእሑድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላእክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት። ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑህ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁን? አለችው። በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት። እሊህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው።

🔴👉 ቅድስት ሥጋዋን ከቅዱስ ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት። ደቀ መዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ስጋዋን በክብር አሳርፉ አላቸው። ሐዋርያት በአጎበር አድርገው ወደ ጌቴሰማኒ ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን በእሳት እናቃጥላታለን ብለው ተነሱ። ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሩን ጨበጠው። መልአክ መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው ከአጎበሩ ተንጠልጥሎ ቀረ። በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት እጁ ተመልሶለታል። ከዚህ በኋላ ዮሐንስን ጨምሮ በደመና ነጥቆ ከገነት አግብቶ ከዕፀ ሕይወት ሥር አኖራት።

🔵👉 ቅዱስ ዮሐንስን እንደምን ሆነች አሉት ከገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አለች አላቸው ቅዱስ ዮሐንስ አይቶ እኛ ሳናይ ብለው በነሐሴ መባቻ ጾም ጀመሩ ሁለት ሱባዔ ሲፈጸምም እሑድ አምጥቶ ሰጥቷቸው ቀብረዋታል በሶስተኛው ቀን ማክሰኞ “ ከመ ትንሳኤ ወልዳ ” እንደ ልጇ ተነሥታለች። ቅዱስ ቶማስ አልነበረም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ቀድሞ የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬም ደግሞ ያንችን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁን ብሎ “ ወፈቀደ ይደቅ እምደመናሁ ” ከሀዘኑ የተነሳ ሊወድቅ ወደደ እመቤታችንም አይዞህ አትዘን እሊያ ትንሳኤየን ዕርገቴን አላዩም አንተ አይተሃል ተነሣች ዐረገች ብለህ ንገራቸው ብላ የያዘችውን ሰበን ሰጥታ ሰደደችው። ከዚህ በኋላ ሂዶ የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ አላቸው አግችተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር ተው ይህ ነገር አይመስለኝም አላቸው።

🔴👉 ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ እንጅ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራልህ ብሎ ተቆጥቶ ወደ መቃብሩ ሂዶ ቢከፍተው አጣት ደንግጦ ቆመ ሐዋርያው ቶማስም አታምኑኝም ብየ እንጅ እመቤታችንስ ተነሣች ዐረገች አላቸው የያዘውንም ሰበን ሰጣቸው ለበረከትም ተካፍለውታል። በዓመቱ ሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ትንሣኤሽን ዕርገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው ጾም ጀመሩ በ፲፮ኛው ቀን እመቤታችንን መንበር አድርጎ ቅዱስ ጴጥሮስን ካህን ዘይትራድኦ ቅዱስ እስጢፋኖስን ሠራዒ ዲያቆን አድርጎ በዚያው ላይ ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ቤተክርስቲያንም ይህንን መታሰቢያ አድርጋ በየዓመቱ ታከብረዋለች።

#ድንግል_ሆይ
🔴👉 የኃጥአንን ለቅሶና ሐዘን አይተሽ ስለእነርሱ ድኅነት(መዳን) ዕረፍትሽን በሀሴት የተቀበልሽ እመቤታችን ሆይ ሐዋርያት በሱባዔ ትንሣዔሽን ለማየት በቅተዋልና እኛም በዓለ ዕረፍትሽን አክብረን ልጅሽ በሰጠሽ ቃል ኪዳን በቀኙ እንቆም ዘንድ ለምኝልን። አሜን

       ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

  ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 21/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

29 Jan, 02:59

https://youtu.be/zVRS6TUA1yg?si=wVlNfxpvhrnMQ5Cq

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

27 Jan, 03:19

ገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን ምሥጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ የምንልበትን ጸጋ አሰጠን።

🔵👉 ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን፤ የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን፣ ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች፣ ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን።

🔴👉 ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛ አገልጋዮችህም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን።

🔴👉 የሰይጠንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ እጠራሃለሁ፤ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ፡፡

🔴👉 ቅድስት ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበር ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ፡፡

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንን ለእኛ ከሠማይ ሠረገላ ናልን፡፡

🔴👉 የደስታንም ቃል አሰማን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት፣ የሞት፣ የክስረት፣ የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጎስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን፡፡

🔵👉 እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ማደሪያው የሆነችው ድንግል ማርያምን በጣም እንወዳታለን፤ በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን በመንግስተ ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን ለዘላለሙ

🔴👉ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 19/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Jan, 17:52

https://youtu.be/a4Qz1j9KcoU?si=XwPpiFteLmVe_buG

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Jan, 04:35

ጥር 18 ዝርወተ ዓጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ይህቺ ዕለት 70 ነገስታት ያፈሩበት እለት ነው። ጥር 18 " ዝርወተ ዓጽሙ " ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ይህቺ ዕለት ለሰማዕቱ 'ዝርወተ አጽሙ' ትባላለች::

🔴👉 ይህ ማለት በቁሙ 'አጥንቱ የተበተነበት' እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው:: 70 ነገሥታትን ከነ ሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ (በመቶ ሺ የሚቆጠሩ) አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ::

🔴👉 በዚህ የተበሳጨ ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ:: ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው: በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት:: ያለ ርሕራሔም አካሉን አሳረሩት:: ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት:: በአካባቢው ወደ ነበረው ትልቅ ተራራ ጫፍ (ደብረ ይድራስ) ወጥተውም በነፋስ በተኑት:: "ሐረድዎ ወገመድዎ: ወዘረዉ ሥጋሁ ከመ ዓመድ "እንዲል:: እነርሱ ይህንን ፈጽመው ዘወር ሲሉ ግን የቅዱሱ ዓጽም ባረፈባቸው ዛፎች: ቅጠሎችና ድንጋዮች ሁሉ "ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት" የሚል ጽሑፍ ተገኘ:: 

🔴👉 ስለዚህም ይሕቺ ዕለት ቅዱሱ አለቅነትን የተሾመባት ናት ማለት ነው:: ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸውና "በክርስቶስ እመኑ" ብሎ: አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው:: 70ው ነገሥታት ግን አፈሩ::

የሊቀ ሰማዕታት ቅ/ጊዮርጊስ በረከቱ ይደርብን ሼር በማድረግ ላላወቁት አሳውቁ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፈጥኖ ደራሹ በመከራ ግዜ ፈጥኖ ይድረስልን

  ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 17/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

25 Jan, 18:02

https://youtu.be/Uib7KEH1F6U?si=yXzd1GcOAf5P9xjC

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

24 Jan, 04:11

#ኪዳነ_ምህረት_ማለት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡

🔷👉 ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

🔵👉 እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡ « ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

🔴👉 ስሟን ለሚጠሩ፣በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል
ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።" ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

🔴👉 በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለን።

የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት ፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 16/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

23 Jan, 12:31

https://youtu.be/0t_wKY45_JE?si=ljDBT8i64W5kcVFb

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

23 Jan, 04:33

#ጥር 15 #ቅዱስ_ቂርቆስ_ወኢየሉጣ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 የሰማዕትነት ታላቅ ክብር ያገኘው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ በነበረበት ጊዜ የነበረው መኰንን ክርስቶስን በመካድ በክርስቲያኖች ላይ መከራ ያጸናባቸው ነበር፤ ሕፃኑ ቂርቆስንም ይዞ “ስምኽ ማነው” ብሎ በጠየቀው ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ይኽ ሕፃን ከንጹሕ ዐዘቅትና ከማይለወጥ ከማይጠፋ ውሃ የተገኘ ስሜ ክርስቲያን ነው ሞክሼ ስም ከፈለግኽ ደግሞ እናቴ የሠየመችኝ ቂርቆስ ነው በማለት መለሰለት፡፡

🔷👉 መኰንኑም ለአማልክት ከሠዋኽ ስታድግ እሾምኻለኊ ክርስቶስን ካድ ቢለው ቅዱስ ቂርቆስ ግን “የሰይጣን መልእክተኛ ለእውነትም ጠላቷ የኾንኽ ከእኔ ራቅ” አለው፡፡

🔴👉 መኰንኑም ይኽነን ሰምቶ በመቈጣት የቅዱስ ቂርቆስ ደሙ እንደ ውሃ እስኪፈስስ ድረስ እንዲጨምቁት እና ጨውና ሰናፍጭ በኹለቱ የአፍንጮቹ ቀዳዳዎች እንዲጨመሩ ቢያደርግበት፤ በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ የጠነከረው ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ግን “ትእዛዝኽ ለጒረሮዬ ጣፋጭ ኾነ ከማርና ከሥኳርም ለአፌ ጣመኝ” እያለ አምላኩ ክርስቶስን አመሰገነ፡፡

🔴👉 መኰንኑ በዚኽ ሳያበቃ እናትና ልጇ በክፉ አሟሟት እንዲሞቱ በማሰብ የረዘሙና የተሳሉ በእሳትም እንደ ፍም የጋሉ ዐሥራ አራት የብረት ችንካሮች እንዲመጡ አስደርጎ ሰባቱ በእናቱ አካላት፤ ሰባቱ በሕፃኑ ሰውነት ላይ እንዲሰካ ቢያስደርግም በጌታችን ትእዛዝ ግለቱ ጠፍቶ እንደ በረዶ በመቀዝቀዝ ምንም ምን ጒዳት ሳያደርስባቸው ቀረ፡፡

🔵👉 ከዚያም ወደ ወኅኒ ቤት እንዲገቡና እንዲዘጋባቸው አደረገ፤ ከዚያም ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ የሚሠቃዩበት ታላቅ መንኰራኲር ለ፵ ቀናት ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ኹለቱንም በደራቁ ራሳቸውን ላጭተው የእሳት ፍሕምን በላያቸው ላይ ቢያደርጉም የእግዚአብሔር መልአክ ሥቃዮቹን ኹሉ ከእነርሱ አራቀላቸው፡፡

🔷👉 የሕፃኑ ምላስ እንዲቈረጥ አዝዞ ቢያስቈርጠውም ጌታችን ምላሱን መልሶለታል፡፡ “ወአዘዘ ካዕበ ያፍልሑ ማየ ውስተ ጽሕርት ዐቢይ ወይደይዎሙ ለሕፃን ቂርቆስ ወለእሙ ኢየሉጣ” ይላል በታላቅ ጋን ውሃ አፍልተው ሕፃኑንና እናቱን እንዲጨምሯቸው ሲያዝዝ ከሚፍለቀለቀው ውሃ ድምፅ የተነሣ ለጊዜው እናቱ ፍርሀት ሥጋዊ ቢያገኛትም ልጇም ወደ ጌታችን በጸለየላት ጊዜ ፍርሃቱ ርቆላት ከልጇ ጋር ስትገባ መልአከ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ወርዶ ውሃውን አቀዝቅዞ ሐምሌ ፲፱ አውጥቷቸዋል፡፡

🔷👉 በመጨረሻም የሰማዕትነትን አክሊል የሚያገኝባት ጊዜ ሲደርስ ጌታችን ተገልጾለት "ምን ላድርግልኽ?" አለው፤ ሕፃን ቂርቆስም ለጌታ "ሥጋዬ በምድር ላይ አይቀበር፤ መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ ፍላጎታቸውን ስጣቸው፤ ስሜ በሚጠራበት በዚያች ቦታ የከብት ዕልቂት አይምጣ፤ በሰውም ላይ ተላላፊ በሽታ በእኽልም ላይ ድርቅ የውሃም ማነስ አይኹን" አለው።

🔴👉 መድኀኔ ዓለምም ሕፃኑ ቂርቆስን "የለመንከኝን ኹሉ እሰጥኻለሁ ሥጋኽንም ኤልያስ ባረገበት ሠረገላ ውስጥ አኖርልኻለኊ" አለው፤ ይኽነን ቅዱስ ቂርቆስ በሰማ ጊዜ በእጅጉ ተደሰተ፤ ከዚኽም በኋላ ጥር 15 በሌሊቱ እኲሌታ ከእናቱ ጋር አንገታቸው ተቈረጠ፤ መድኃኒታችን ክርስቶስም በማይጠፋ አክሊል ጋረዳቸው፤ ነፍሶቻቸውም በታላቅ ክብር ዐረጉ የሰማዕትነትንም ክብር ተቀዳጁ።

ምንጭ :- ስንክሳር ዘወርኃ ጥር

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥር 15/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Jan, 20:40

https://youtu.be/_aMvsAhUWJ4?si=j5yY8y9d_W9Y5r4C

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Jan, 04:55

#ጥር 12 #ቃና #ዘገሊላ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቃና ዘገሊላ በቀጥታ ትርጉም የገሊላዋ ቃና ማለት ነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አስተምህሮ በጥምቀት በዓል ማግስት (ጥር 12) ቀን የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል፡፡

🔷👉 ይህ በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በድምቀት የሚከበር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዳራ ያለው በዓል ነው፡፡ በዓሉ ቃና ዘገሊላ የሚል ስያሜ ያገኘው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ሀገር ክፍል በምትሆን ቃና በተባለችው ቦታ በፈፀመው ተአምር መነሻነት ነው፡፡ የቃና ዘገሊላ ጥንተ ነገሩ ወይም ታሪኩ የተፈፀመው የካቲት 23 ቀን ነው፡፡

🔵👉 ነገር ግን አባቶቻችን የውኃን በዓል ከውኃ በዓል ጋር ለማክበር ብለው የየካቲቱን በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተውታል፡፡ ይህም ውኃ ወደ ወይን የተለወጠበትን በዓል ከጌታ ጥምቀት በዓል ጋር ለማስተሣሠር ለማስኬድ ነው፡፡ በመሆኑም የቃና ዘገሊላ በዓል ጥር 12 ቀን ይከበራል፡፡

🔴👉 በቃና ዘገሊላ ምን ተፈፀመ? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና በተደረገ ሠርግ ላይ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋር ተገኝቶ ነበር፡፡ ‹‹ወሀለወት ህየ እሙ ለእግዚእ ኢየሱስ›› ‹‹የጌታ የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች›› እንዳለ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ (ዮሐ 2÷1) እመቤታችን ለሠርገኞቹ ዘመድ ነበረችና ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ በሰርጉ ላይ ታድማ ነበር፡፡ እናትን ጠርቶ ልጅን መተው ሥርዓት ስላልሆነ፤ በተጨማሪ ደግሞ ደቀ መዛሙርቱ ከጌታ ጋር በሰርጉ ታድመዋል፡፡ ይህም መምህርን ጠርቶ ደቀ መዛሙርቱን መተው ሥርዓት ስላልሆነ (ተገቢ ስላልሆነ) ነው፡፡

🔵👉 የሠርጉ ሥነ-ሥርዓት በሠመረ ባማረ ሁኔታ እየተከናወነ ሳለ ድንገት የወይን ጠጅ አለቀ፡፡ አስተናባሪዎቹ በጭንቀት ባሕር ሰጥመው ምን እንደሚያደርጉ ግራ በገባቸው በጠበባቸው ጊዜ የችግር ጊዜ ደራሽ የኃዘን ጊዜ አፅናኝ የሆነችው የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ቅዱስ ገብርኤል እንደተናገረ በፀጋ የተሞላች ናትና (ሉቃ 1÷28) ማንም ሳይነግራት የልቦናቸውን ጭንቀት አይታ፣ ጎዶሎአቸውን ተመልክታ ወደ ልጃ_ ወደ ወዳጃ_ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወር ብላ ‹‹ወይንኬ አልቦሙ›› ‹‹ወይን ጠጅ እኮ አልቆባቸዋል›› አለችው፡፡ እርሱም መልሶ ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ‹‹ጊዜዬ ገና አልደረሰም›› አላት፡፡

🔴👉 እመቤታችንም ለአገልጋዮቹ ‹‹የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ›› አለቻቸው፡፡ ጌታም በቦታው የነበሩ ስድስት ጋኖች ውኃ ሞልተው እንዲያመጡ አዘዛቸው፡፡ ውኃውንም ወደ ወይን ለውጦ ለሊቀ ምርፋቅ (ለአሳዳሪው) እንዲሠጡት አዘዘ፡፡ አሳዳሪውም ወደ ወይን የተለወጠውን ውኃ በቀመሰ ጊዜ አደነቀ፡፡ ከወዴት እንደመጣ ስላላወቀ ሙሽራውን ‹‹ሰው ሁሉ አስቀድሞ መልካሙን የወይን ጠጅ ያቀርባል ከሰከሩም በኋላ መናኛውን ያቀርባል አንተ ግን መልካሙን እስከ አሁን አቆይተሃል›› አለው፡፡ ወይኑም በሰው እጅ ያይደለ በሠማያዊው አባት የተዘጋጀ ስለነበር ጣፋጭ እና ልብን የሚያስደስት ነበር፡፡

🔷👉 ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ይህንን የጌታችንን ንግግር ብዙዎች በዘመናችን ሲሣሣቱበት ይታያል ፡፡ ክብር ይግባውና አምላካችን ይህንን የተናገረው እናቱን ሊያቃልል ሽቶ አይደለም፡፡ ስለሆነም ከመጽሐፍ ቅዱስ አንፃር ይህን አረፍተ ነገር መመልከቱ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ በተናጠል ስንመለከት ‹‹አንቺ ሴት›› ሴት የሚል ቃል የፆታ መጠሪያ ነውና በፆታዋ አክብሮ ሲጠራት ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሔዋን ከአዳም በተፈጠረች ጊዜ አዳም እንዲህ ሲል ተናግሮ ነበር ‹‹ይህች አጥንት ከአጥንቴ ናት ሥጋም ከሥጋዬ ናት እርስዋ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል›› (ዘፍ 2÷23) በመሆኑም ጌታ አንቺ ሴት ማለቱ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍስዋ ነፍስ መንሣቱን ለማጠየቅ ነው፡፡

🔴👉 ‹‹ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለውን ዐረፍተ ነገር የንቀት ስለመሰለን ብቻ ‘ የዳቦ መልክ የያዘ ድንጋይ፤ ዳቦ ነው እንደማይባል’ የንቀት ንግግር ነው ልንል አይገባም፡፡ ጌታም እንዲህ ሲል ውኃውን ወይን አድርግላቸው ብትይኝ አላደርግም እልሽ ዘንድ ከአንቺ ጋር ምን ፀብ አለኝ ማለቱ ነው፡፡ ይህ ንግግር በመጽሐፍ ቅዱስ በብዙ ቦታ ተጽፎ እንደሚገኘው በዕብራውያን ዘንድ የተለመደ የአነጋገር ዘይቤ ነው፡፡

🔷👉 ለአብነት ይሆን ዘንድ ጥቂት ጥቅሶችን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንመልከት፡- የሰራፕታዋ ሴት በ 1ነገ 17÷18 ላይ እንደምናገኘው ልጇ በሞተባት ጊዜ ኤልያስን በሐዘን በለቅሶ እንዲህ ብላ ነበር ‹‹የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› ትወልጃለሽ ብለህ የወለድኩት ልጅ ምን በድዬህ ምንስ አስከፍቼህ ሞተብኝ? ስትል ነው እንጂ አባባሏ የንቀት ወይም የማቃለል አይደለም፡፡

🔴👉 በጌርጌሴኖን አንድ አጋንንት ያደረበት ሰው ወደ ጌታችን ቀርቦ ‹‹የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከአንተ ጋር ምን አለኝ?›› አለው፡፡ እውነት ይህ ቃል የንቀት ይመስላልን? የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ብሎ አምላክነቱን እየመሰከረ ሊያቃልለው ይችላልን? ደግሞስ ላለመጥፋት ፍፁም የሚፈልግ ሰው ሊያድነው ሥልጣን ያለውን ሊንቅ ይችላልን? አይችልም፡፡ ይህ ቃል የሚያመለክተው ምን አጠፋሁ ስለምን ልታጠፋኝ ወደድክ በማለት መፍራት መራዱን ነው፡፡ (ሉቃ 8÷28-29)

🔴👉 ስለሆነም ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› የሚለው የንቀት አለመሆኑን ከሁለቱ ጥቅሶች መረዳት እንችላለን፡፡ እመቤታችን እና ጌታ በንግግር አልተቃረኑም ንግግራቸው የፍቅር ነበር፡፡ ንግግራቸው የመግባባት ስለነበር ነው ‹‹አንቺ ሴት ከአንቺ ጋር ምን አለኝ?›› ካላት በኋላ ዘወር ብላ አገልጋዮቹን የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ ያለችው፡፡

🔴👉 ‹‹ጊዜዬ አልደረሰም›› ጌታ ይህን ቃል የተናገረው ስለ ብዙ ምክንያቶች ነው፡፡ ጊዜዬ አልደረሰም ማለቱ፡- እግዚአብሔር ነገሮችን የሚያከናውንበት የራሱ ጊዜ አለው፡፡ በመሆኑም ይህን ተአምር የምፈፅምበት ጊዜዬ አልደረሰም ሲል ነው፡፡ ጋኖቹ ውስጥ የቀረ ወይን ስለነበረ ባለው ላይ አበርክቶ እንጂ ውኃውን ወደ ወይን አልለወጠውም እንዳይሉ ወይኑ ከጋኑ ተንጠፍጥፎ እስኪያልቅ ድረስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡

🔵👉 ይሁዳ ከሠርግ ቤት ወጣ ብሎ ነበርና ወደ ሠርግ ቤቱ እሰኪመለስ ጊዜዬ አልደረሰም አለ፡፡ ይሁዳ በቃና የገለጠውን ምስጢር ለእኔ ስላላሣየኝ ተከፍቼበት ከተአምራቱ ቢያጎድለኝ በሞቱ ገባሁበት፤ ሸጥኩት እንዳይል ምክንያት ለማሳጣት እንዲህ አድርጓል፡፡ እውነተኛ የሕይወት ወይን የሆነውን ደሜን የምሠጥበት ጊዜ ገና ነው ሲል፡፡ የድንግል ማርያም አማላጅነት በገሊላ ቃና ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በሠርግ ቤት ሣለ የወይኑን ማለቅ የማይመለከት ሆኖ አይደለም፡፡

🔷👉 ነገር ግን የእናቱን የድንግል ማርያምን አማላጅነት ሊገልጥ ስለወይኑ ማለቅ እስክትነግረው ድረስ አንዳች ነገር አላደረገም፡፡ ኋላ ግን የጭንቀት አማላጅ ድንግል ማርያም ስለ ወይኑ አሰበች ልጇ ወዳጇን ለመነች፡፡ እርሱም የእናቱን ልመና ተቀብሎ ተአምራቱን ፈፀመ፡፡

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Jan, 04:55

🔴👉 እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሣይነግሯት በልብ ያለውን የምታውቅ የምትመረምር እናት ናትና የሠርጉ አስተናባሪዎች ይሄ ጎደለ ሣይሏት የልቦናቸውን ሐዘን ተመልክታ ከልጇ ከወዳጇ አማልዳ የጎደላቸውን ሞልታለች፡፡ ያስጨነቃቸውንም አርቃለች፡፡ በችግራቸው ደርሳላቸዋለች፡፡ ታዲያ ሳይነግሯት የልቡናን አይታ ከማለደች ስሟን ጠርተው ለሚለምኗትም እንዴት አብልጣ አታማልድ?

ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤቷን በረከቷን ያሳድርብን

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 12 /2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Jan, 18:09

https://youtu.be/ZYrB-RJlmEQ?si=D8vpEe2brBXgNWNi

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Jan, 18:09

የሆለታው ቅዱስ ገብርኤል
🔷 በሠላም ገብቷል
ሆለታ 2017 ዓ.ም

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Jan, 04:02

ጥር 11 በዓለ ኤዺፋንያ | በዓለ ጥምቀት
🔷👉 ጌታችን ለምን ተጠመቀ ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ጥር አስራ አንድ በዚች ቀን የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከአጥማቂው ዮሀንስ ዘንድ በዮርዳኖስ ወንዝ ውኃ ተጠመቀ። ይችም እለት በዮናኒ ቋንቋ ኤጲፋንያ ትባላለች ትርጓሜውም "መለኮት የተገለጠበት ማለት ነው።

🔴👉 ' ኤዺፋንያ' የሚለው ቃል ከግሪክ (ጽርዕ) ልሳን
የተወሰደ ሲሆን በቁሙ 'አስተርእዮ: መገለጥ' ተብሎ
ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤዺፋንያ ማለት 'የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት' እንደ ማለት ነው::

🔷👉 አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ
የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ 441ኤዺፋንያ
ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ33 ዓመታት ተመላልሷል::

🔴👉 ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር 10 ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::

🔷👉 10 ሰዓት መሆኑም ርግብ (መንፈስ ቅዱስ) ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::

🔵👉 መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: (ሉቃ. ማቴ. ) ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::

🔴👉 ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው:: ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ :: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ እያልክ አጥምቀኝ" አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::

🔷👉 ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ
ደነገጠች: ሸሸችም:: (መዝ) ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ
ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውሃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና:: ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::

🔴👉 አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::

🔷👉 ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተጠመቀ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ጌታችን እርሱ ባወቀ ለብዙ ምክንያቶች ተጠመቀ ጥቂቶቹን እንይ

👉 ትህትናን ሊያስተምረን -

🔵👉 ጌታችን በደቀመዝሙሩ በፍጡሩ በዮሐንስ እጅ ባህረ ዮርዳኖስ በሰላሳ ዘመኑ ተጠምቋል፡፡ ይህን ምስጢር የፈጸመው በደቀ መዘመሩ እጅ ለመጠመቅ ወደ ነበረበት ስፍራ በመሄድ ነውና መምህረ ትህትና ያሰኘዋል፡፡

👉 ሥርአትን ሊመሰርትልን-

🔵👉 ጌታችን ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን፤ አድርጎ አድርጉ እንደሚል ደገኛ መምህር ተጠምቆ ተጠመቁ አለን፡፡

👉 ምስጢር ሊገልጥልን-

🔴👉 በጌታችን ጥምቀት ሰማያት ተከፍተዋል ፤የአብ ምስክርነት መንፈስቅዱስ ስምረት በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ለዚህም የሥላሴ የአካል፣ የስም የግብር ሦስትነት ተገልጧል፡፡

👉 የእዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ-

🔴👉 በዲያብሎስ ሥራ ተሸሽጎ የኖረውን የዕዳ ደብዳቤ እንደ ሰውነቱ ረግጦ እንደ አምላክነቱ አቅልጦ ሊደመስስልን ጌታ ተጠመቀ፡፡

🔵👉 በመሆኑም በልደቱ ያገኘነውን ጸጋ በጥምቀት ልጅነት አጽንተን በመጠበቅ የመንግስቱ ወራሽ የክቡር ስሙ ቀዳሽ እንሆን ዘንድ የጌታችን ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን፡፡አሜን

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ
🔷👉 መልካም በዓል

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 11 /2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Jan, 03:31

https://youtu.be/KPwq_vxwOEI?si=mpkcoZQEHkDvgRTb

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

18 Jan, 15:48

ታቦታቱ በሠላም ገብተዋል
    🔷 ከተራ በሆለታ ከተማ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

18 Jan, 07:41

#ከተራ_ምን_ማለት_ነው?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ከተራ "ከበበ" ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

🔵👉 የጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰበ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላል፡፡ የምንጮች ውኃ ደካማ በመሆኑ እንዲጠራቀም ይከተራል ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ ይገደባል፡፡

🔴👉 በየዓመቱ ጥር 10 ቀን የምእመናኑ አብዛኛው ሥራ ውኃውን መከተርና መገደብ በመሆኑ ዕለቱ ከተራ የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

🔴👉 ውኃው የሚከተረው በማግሥቱ ጥር 11 ቀን የጥምቀት በዓል ስለሚከበር ለሕዝቡ መጠመቂያ እንዲሆን ነው፡፡ በየሰበካው ቦታ ተለይቶና ተከልሎ ታቦታቱ በዳስ ወይም በድንኳን የሚያድሩበት፣ የተለያዩ የውኃ አካላት ተጠርገው የሚከተሩበት ወይም ሰው ሠራሽ የግድብ ውኃ የሚበጅበት ስፍራ ‹‹ባሕረ ጥምቀት››፣ ‹‹የታቦት ማደርያ›› እየተባለ ይጠራል።

🔵👉 ከዚህም በተጨማሪ በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል፡፡

🔵👉 በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

🔴👉 ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና ክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል፡፡ የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ፡፡

🔴👉 ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ፡፡

🔵👉 ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት በዐዋጅ አስነግረው ነበር፡፡ ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ከአወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።

🔵👉 ታቦታተ ሕጉ በወጡበት ቦታ የማይመለሱበት ምክንያት ብዙ ምስጢር አለው፤ ይኸውም ‹‹ወተቀደሰት ምድር በኪደተ እግሩ ምድር በኪደተ እግሩ ተቀደሰች›› እንዳለ ሊቁ ያልተባረከ መሬት እንዲባረክ ነው፤ ዳግመኛም ያላየው እያየ ያልሰማው እየሰማ ሥርዓቱን አይቶ እንዲያምን ሃይማኖት እንዲሰፋ ነው። ነቢያት በመጡበት እንዳይመለሱ ሥርዓት ነበረና የዚያም ምሳሌ ነው፡፡ ሰብአ ሰገል ጌታን ካገኙ በኋላ በመጡበት ቦታ አልተመለሱምና የዚያም ምሳሌ ነው፡፡

🔴👉 የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዞ አክብሮ ወደ ወንዝ መውረድ በብሉይ ኪዳን የነበረ ሥርዓት ነው ኢያሱ በሙሴ ተተክቶ ሕዝበ እስራኤልን ሲመራ ታቦቱን አሸክሞ ሲሔድና ከዮርዳስ ወንዝ ሲደርስ ባሕሩ ከኹለት ይከፈልና ወራጁም ይቆም እንደነበረ ቅዱስ መጽሐፍ ይናገራል።

🔷👉 እስራኤል ወደ ምድረ ርስት ሲገቡ ታላቁን የዮርዳኖስ ወንዝ ሲሻገሩ ድንኳን ጥለው የቃል ኪዳን ታቦት ድንኳን ውስጥ አድርገው ሌዋውያኑ ዙሪያውን፣ ካህናቱ በውስጥ ሆነው እግዚአብሔርን እያመሰገኑ እንደተሻገሩ መፅሐፍ ይናገራል ዛሬም እንደ ዮርዳኖስ ከድህነት ወደ ብልጽግና፣ ከደዌ ወደ ጤና፣ ከከህደት ወደ ሃይማኖት ከድንቁርና ወደ ዕውቀት አላሻግር ያለን ባሕረ ኀጢአት በቃል ኪዳኑ አማካኝነት በጥምቀቱ በረከት ያደርቅልናል። ኢያሱ ፩ ፥ ፲፫ ፣ ኢያሱ ፫ ፥ ፰

🔴👉 በዓለ ከተራ የምን ምሳሌ ታቦታቱ ለምን ወደ ጥምቀተ ባሕር ሔደው እዛው ያድራሉ ቢባል :- ሐዋርያው ፊልጶስ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባውን ሊያጠምቀው ወደ ጋዛ ወንዝ የመውረዱ ምሳሌ ነው። ሐዋ ሥራ ፰ ፥ ፴፬

🔷👉 ዋናው ምሥጢሩ ግን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሐንስን አስከትሎ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱና ለመጠመቅ ተራ ሲጠብቅ እዛው የማደሩ ምሳሌ ነው። ጌታችን ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመጣው ጥር 10 አመማቴ ፫ ፥ ፲ በዚህ መሠረት ከጥንት ጀምሮ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘን ወደ ወንዝ ወርደን በዓለ ጥምቀትን የምናከብረው ከዚህ ታሪክ በመነሣት ነው።

🔴👉 ስለዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ ጥር ፲ ቀን ተቀራራቢ የሆኑትን ታቦታትን በየአቅራቢያቸው ወደሚገኘው ወንዝ በአንድነት እያወረደች ከከተራ ዕለት ጀምሮ የጥምቀትን በዓል በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብራለች። ሌሊቱን ከሚያነጋው ሕዝበ ክርስቲያን ጋር በመሆን ያሬዳዊ ማሕሌትና የወንጌል ጉባኤ ተዘርግቶ በመምህራን ወቅታዊ ትምህርት ሲሰጥ ይታደራል ይዋላል።

🔵👉 በበዓለ ጥምቀት ዋዜማ የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድና የባሕረ ጥምቀት መዘጋጀት የሚከተለው ሃይማኖታዊ ታሪክና ምሳሌ አለው። ታቦቱ የጌታችን፤ ታቦቱን አክብሮ /ይዞ/ የሚሄደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣ ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣ ታቦታቱን አጅበው የሚሄዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩ ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሠላም አደረሳችሁ
🔷👉 መልካም በዓል

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 10 /2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

18 Jan, 07:32

https://youtu.be/KPwq_vxwOEI?si=fvSW_DXEwC1-raoA

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

15 Jan, 16:27

https://youtu.be/gUEGCYQdcig?si=bXgv3OIk5KzBjPC9

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

15 Jan, 05:21

🔴ጥር 7 #በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ
🔵👉 ለምን ይከበራል ?
..........................................................
🔴👉 ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር
🔵👉 ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

🔴👉 ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

🔵👉 ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

🔴👉 መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

🔴👉 ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

🔵👉 ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት
🔴👉 ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

🔴👉 ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን: ሠራዊት: መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል:: በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል:: ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል: ደግ: ጥበበኛ: አስተዋይ: መናኝ ንጉሥ ነውና::

🙏 ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 7/2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Jan, 18:28

https://youtu.be/cCJBNqjfrCg?si=R3P3MKz0aS0Mkheo

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Jan, 14:33

https://youtu.be/wddUnEZyOX8?si=CmiGnoIkQhUcnEiz

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Jan, 05:32

ጥር 6 በዓለ ግዝረቱ ለክርስቶስ
🔵👉ለምን ይከበራል ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ጌታችን እና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዕለት ሰይማ የምታከብር ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጥር 6 ቀንን በየዓመቱ በልዩ ሁኔታ ታከብረዋለች!

ክብር ምስጋና ይድረሰውና የጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ግዝረት በየዓመቱ ጥር 6 ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ይከበራል፡፡ ጥር ፮ ቀን በሚነበበው መጽሐፈ ስንክሳር ተጽፎ የሚገኘውን የጌታችንን የግዝረት ታሪክም በሉቃስ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ ከተቀመጠው ትምህርት ጋር በማጣቀስ እንደሚከተለው አቅርበነዋል !

🔵👉 ልሳነ ዕፍረት ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ጌታ ክርስቶስ በሥጋው ግዝረትን ተቀበለ፡፡ ለአባቶች የተሰጠውን ቃል ኪዳን ይፈጽም ዘንድ፤›› በማለት እንደ ተናገረው /ሮሜ.፲፭፥፰/፣ የክብር ባለቤት መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተ ግዝረት በመግባት የኦሪትን ሕግ ፈጽሟል፡፡ በቅዱስ ወንጌል እንደ ተጻፈ በስምንተኛው ቀን እንደ ኦሪቱ ሥርዓት ግዝረት ይፈጸምለት ዘንድ ሕፃኑ ጌታችንን ወደ ቤተ መቅደስ ወሰዱት፡፡

🔴👉 ስሙም ገና በሥጋ ሳይፀነስ የእግዚአብሔር መልአክ ባወጣለት ስም ‹‹ኢየሱስ›› ተብሎ ተጠራ /ሉቃ.፪፥፳፩-፳፬/፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ሲገረዝ የሊቀ ካህን ልጅ ነው ብለው ሊገርዙት ወደ እርሱ መጡ፡፡ ጌታችን ግን ወደ ምድር የመጣው ለትሕትና ነው እንጂ ለልዕልና አይደለምና ወሰዱት አለ /ትርጓሜ ወንጌለ ሉቃስ/፡፡

🔵👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም አረጋዊው ዮሴፍን ‹‹እንደ ሕጉ ልጄን እንዲገርዘውና ስሙንም እንድንሰይመው ብልህ የኾነ ገራዥ ሰው አምጣልኝ፤›› አለችው፡፡

🔴👉 ጻድቁ ዮሴፍም እንዳዘዘችው የሚገርዝ ባለሙያ ይዞ መጣ፡፡ ባለሙያውም በእናቱ በንጽሕት ድንግል ማርያም ክንድ ላይ ሕፃኑ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ባየው ጊዜ ‹‹እንድገርዘው በጥንቃቄ ያዙት›› አላቸው፡፡ ጌታ ኢየሱስም ‹‹ባለሙያ ገራዥ ሆይ! ደሜ ሳይፈስ ልትገርዘኝ ትችላለህን? በዕለተ ዓርብ በመስቀል ስሰቀል ካልኾነ በስተቀር ደሜ አይፈስምና፡፡ ጐኔን በጦር ሲወጉኝ ያን ጊዜ ውኀና ደም ይፈሳል፡፡ ይኸውም ለአዳምና ለሚያምኑ ልጆቹ መድኀኒት ይኾናል፤›› አለው፡፡

🔵👉 የክብር ባለቤት ጌታችን የተናገረውን ይህን ቃል ባለሙያው በሰማ ጊዜም አደነቀ፡፡ ዕቃውንም ሰብስቦ ተነሣና ከጌታችን እግር በታች ወድቆ ሰገደ፡፡ ያንጊዜም ምላጮቹ በእጁ ላይ እንዳሉ እንደ ውኀ ቀለጡ፡፡ ክብርት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም ‹‹ከሴቶች ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ፡፡ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው፡፡ ይህ ልጅሽ ስለ እርሱ ነቢያት ትንቢት የተናገሩለት የሕያው አምላክ ልጅ ነው፤›› አላት፡፡

🔷👉 ጌታችንም ባለሙያውን ‹‹እኔ ነኝ! ትገዝረኛለህን ወይስ ተውክ? ወይስ የአባቶቼ አባቶች እንዳደረጉ ላድርግ?›› አለው፡፡ ባለሙያውም መልሶ ‹‹የአባቶችህ አባቶች እነማን ናቸው?›› ሲል ጠየቀው፡፡ ጌታችንም አብርሃም፣ ይስሐቅ፣ ያዕቆብ የሕዝቡ ዅሉ አባት እንደ ኾኑ ካስገነዘበው በኋላ ‹‹ለእነርሱም ይህ ግዝረት አስቀድሞ ከአባቴ ዘንድ ተሰጣቸው›› በማለት የግዝረትን ሕግ አስረዳው፡፡

🔴👉 ባለሙያውም ይህን ምሥጢር ሲሰማ ‹‹እኔ ከአንተ ጋር እነጋገር ዘንድ አልችልም፡፡ በአንተ ህልውና መንፈስ ቅዱስ አለና፤›› ብሎ የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት መሰከረ፡፡

🔴👉 በዚህ ጊዜ ጌታችን ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ ‹‹አባት ሆይ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅ፣ ለያዕቆብ አስቀድሞ ግዝረትን የሰጠሃቸው፤ ያቺን ግዝረት ዛሬ ለእኔ ስጠኝ›› አለ፡፡ ያንጊዜም ያለ ሰው እጅ በጌታችን ላይ ግዝረት ተገለጠ (የግዝረት ምልክት ታየ)፡፡

🔵👉 ከዚህ ላይ ጌታችን ወደ አባቱ ወደ እግዚአብሔር አብ ልመና ማድረሱ የለበሰው ሥጋ የአብርሃም፣ የይስሐቅ፣ የያዕቆብ መኾኑንና ጸሎት ማቅረብ የሚስማማው ሥጋን መልበሱን ለማጠየቅ ነው እንጂ በእርሱና በአብ መካከል ልዩነት ኖሮ አይደለም፡፡

🔵 ጌታችን ድንግልናዋን ሳያጠፋ ከድንግል ማኅፀን እንደ መውጣቱ ግዝረቱም አይመረመርም፡፡ በተዘጋ ቤት ወደ ሐዋርያት እንደ ገባና እንደ ወጣ ዅሉ እርሱ በሚያውቀው ረቂቅ ጥበብ ከሥጋው ምንም ምን ሳይቈረጥ፣ ምንም ደም ሳይፈሰው መገረዙ ተገለጠ፡፡

🔴👉 ገራዡም የጌታችንን ቃል ከመስማቱ ባሻገር በሥጋው ላይ የተደረገውን ተአምር ባየ ጊዜ እጅግ አደነቀ፡፡ ከክብር ባለቤት ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እግር በታች ወድቆም ሦስት ጊዜ ሰገደና ‹‹በእውነት አንተ የእግዚአብሔር ልጅ፣ የእስራኤልም ንጉሥ ነህ!›› በማለት በክርስቶስ አምላክነት አመነ፡፡ ከዚህ በኋላ ያየውንና የሰማውን ዅሉ እየመሰከረ ወደ ቦታው ተመለሰ፡፡

የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ኅብረት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት ያለ ጥርጥር በፍጹም ልባችን ከምናምን ምእመናን ጋር ይኹን! /፪ኛቆሮ.፲፫፥፲፬/፡፡

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 6/2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

13 Jan, 16:28

https://youtu.be/NwYPZX2shpU?si=GjoYK_Ue44dzvibP

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Jan, 18:40

🔴👉 ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ የ ዘብድዮስ እና የማርያም ባውፍልያ ልጅ ነው። እርሱም ወንጌል ራዕይ መልዕክታት የጻፈ፣ ጌታ እናቱን በአደራ የተሰጠው ፣ የተሰወረው፣ ወር በገባ በ4 የሚታሰበው ነው።

#የቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ
🙏በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን🙏

   #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥር 3/2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Jan, 18:40

#ጥር 4 #ቅዱስ_ዮሐንስ_ወንጌላዊ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 በዛሬው ዕለት #ጥር_4 ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ሞትን ሳያይ የተሰወረበት ወይም የፍልሰቱ መታሰቢያ የሆነበት ዕለት ነው።

🔵👉 የቅዱስ ዮሐንስ አባቱ ዘብዴዎስ ሲባል እናቱ ማርያም ባውፍልያ ትባላለች። #ቅዱስ_ዮሐንስ የጌታችን ደቀ መዝሙር ከመሆኑ አስቀድሞ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር ነበር ገና በወጣትነቱም የመሲሁን የክርስቶስን መምጣት ከመምህሩ ከመጥምቀ መለኮት ስለተረዳ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆኗል፤ ዕድገቱም በገሊላ ነበር።

🔵👉 ሐዋርያነቱንም በደስታ እና በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከክርስቶስ ሳይለይ በመከራውም ሰዓት እስከ መስቀሉ ድረስ አብሮት ነበር አልተለየውምም። ፍቁረ እግዚእ መባሉም ከጌታችን ባለመለየቱ ጌታችንም ይወደው ስለነበር ነው።

🔴👉 በክርስቶስ መስቀል አጠገብ ከእመቤታችን ጋር በሀዘን እና በልቅሶ ቢገኝ ጌታችን እነኋት እናት ብሎ በእርሱ አንጻር ለእኛ እናታችን ትሆነን ዘንድ ሰጥቶናል፤ እንዲሁም ለእናቱ እነሆ ልጅሽ ብሎ በእርሱ አንጻር ለእርሷ ልጇቻ እንሆን ዘንድ ሰጥቶናል።

🔵ቅዱስ ዮሐንስ በመጽሐፍ ቅዱስ
👉 የዮሐንስ ወንጌል
👉 3 መልእክታት
👉 የዮሐንስ ራዕይ
እነዚህን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ጽፏቸዋል።

🔴👉 ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ከሆነው ከደቀመዝሙሩ አብሮኮሮስ ጋር የሐዋርያነት ተጋድሎውን የፈጸመው፤ ያስተማረው በቀደመችው ኤፌሶን በአሁኗ ቱርክ ነው። ታሪኩም ከብዙ በጥቂቱ እንዲህ ነው👇

🔴👉 ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌልን ለመስበክ ዕጣ የደረሰው እስያ ስለነበር ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን አስከትሎ ሄደ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ኤፌሶን ለመሄድ በመርከብ ሲሳፈር መርከቡ በማዕበል ተሰበረ፡፡ ደቀ መዝሙሩን አብሮኮሮስን ማዕበሉ ወደ አንዲት ደሴት አደረሰው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በመርከቡ ስባሪ ተንጠልጥሎ በባሕሩ ማዕበል መካከል 40 ቀንና 40 ሌሊት ከኖረ በኋላ ማዕበሉ ተፍቶ አብሮኮሮስ ካለበት ደሴት አደረሰውና ተያይዘው ኤፌሶን ከተማ ገቡ፡፡

🔵👉 የከተማይቱም ሰዎች እጅግ ክፉዎች ስለነበሩ መጀመሪያ ላይ ቅዱስ ወንጌልን መስበክ አልቻሉም ነበር፡፡ እነርሱም እጅግ ክፉዎች መሆናቸውን ስላወቀ ቅዱስ ዮሐንስ ገና ዕጣው ሲደርሰው በሀዘን አልቅሶ ነበር፡፡ አሁንም ከተማው በገቡ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመፍጠር ሮምና ለምትባል ሴት የውሽባ ቤቷ እሳት አንዳጅ ሆኖ አብሮኮሮስም ዕቃ አጣቢ ሆነው ተቀጠሩ፡፡ የቀጠረቻቸው ሴትም እጅግ ታሠቃያቸው ጀመር፡፡ ባሮቿ እንደሆኑ ተስማምተው ስለጻፉላት ትደበድባቸውም ነበር፡፡

🔷👉 እነርሱም በታላቅ ጉስቁልና ውስጥ እየኖሩ እያለ በአንዲት ዕለት የአገረ ገዥው ልጅ ለመታጠብ ወደ ውሽባው ቤት ገባ፡፡ በውሽባ ቤቱም የሰይጣን ኃይል ስለነበረበት የመኰንኑን ልጅ አንቆ ገደለው፡፡ የአገሪቱም ሰዎች ሁሉ ለሞተው የመኰንን ልጅ ሊያለቅሱ ሲሰበሰቡ ቅዱስ ዮሐንስም አብሮ ቆሞ ሲመለከት ሮምና መጥታ ‹‹በጌታዬ ልጅ ሞት ልትደሰት መጣህን›› እያለች ረገመችው፡፡

🔴👉 እርሱም ‹‹አይዞሽ አትዘኚ›› አላትና ወደ ሞተው ልጅ ቀርቦ በመስቀል ምልክት ካማተበበት በኋላ በፊቱ እፍ አለበት፡፡ የሞተውም ልጅ ድኖ ተነሣ፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች እጅግ ደነገጡ፡፡ ሮምናም ደንግጣ ‹‹እግዚአብሔር የሚሉት አምላክ አንተ ነህን›› ብላ ጠየቀችው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ‹‹በፍጹም እኔ አምላክ አይደለሁም፣ እኔ የእርሱ አገልጋዩና ሐዋርያው ነኝ እንጂ›› አላት፡፡ ሮምናም ስለበደለቻቸው በደል ሁሉ መሪር ዕንባን እያለቀሰች ይቅር እንዲሏት ለመነቻቸው፡፡ እነርሱም አረጋጉዋት፡፡ ከሕዝቡም ውስጥ ብዙዎቹ በጌታችን አመኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ሌሎች ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን እያደረገ ወንጌልን እየሰበከ ከጣዖት አገልጋዮች በቀር ሁሉንም አሳምኖ አጠመቃቸው፡፡ አገልጋዮችን ኤጲስቆጶሳትን፣ ቀሳውስትንና ዲያቆናትን ከሾመላቸው በኋላ ወደ ሌሎች አቅራቢያ አገሮች ሄደ፡፡

🔷👉 በመጨረሻም በከሃዲውና በጨካኙ በድምጥያኖስ ዘመን በጣዖት አምላኪዎች ተከሶ ለፍርድ ቀረበ፡፡ በፈላ ውኃ ካሠቃዩት በኋለ በፍጥሞ ደሴት አጋዙት፡፡ በዚያም ሳለ ራእዩን ተመልክቶ ጻፈው፡፡ ድምጥያኖስም ከተገደለ በኋላ ከግዞቱ ተመልሶ ሦስቱን መልእክታቱንና ቅዱስ ወንጌሉን ጽፏል፡፡ ጌታችንም አስቀድሞ ሞትን እንደማይቀምስ ለዮሐንስ ቃል ገብቶለት ነበርና (ዮሐ 21፡22) ጥር 4 ቀን እንደ ኤልያስና ሄኖክ ሞትን እንዳያይ ወደ ብሔረ ሕያዋን ወስዶታል፡፡

🔵👉 #የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያሰበ ፣ እያዘነ ፣ እያለቀሰ 70 ዘመን ቁጽረ ገጽ ሆኖ ኖሯል። በቅድሥት ሥላሴ ሥዕል ላይ ካሉት አራቱ እንስሳ አንዱ ንሥር ነዉ፡፡ ንስር በእግሩ ይሽከረከራል በክንፉ ይበራል፡፡ #ንሥር በእግሩ እንደመሽከርከሩ ፤ ቅዱስ ዮሐንስም የክርስቶስን ምድራዊ ታሪኩን ጽፏል፡፡

🔵👉 ንሥር በክንፉ መጥቆ እንደሚበር ቅዱስ ዮሐንስም ከሌሎቹ ወንጌላዉያን ለየት ብሎ የመለኮትን ሰማያዊ አኗኗር ጽፏል፡፡ ንሥር አይኑ ንጹህ ነዉ ሽቅብ ወጥቶ ቁልቁል ሲመለከት ቅንጣት የምታክል ሥጋ የታመልጠዉም፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ወንጌል ሲጀምር እጅግ ርቆና መጥቆ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት የአካላዊ ቃልን (የእግዚአብሔር ወልድን)በቅድምና መኖር ተናግሯል በዚህም #ዮሐንስ_ዘንሥር ተብሏል።

🔵👉 ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡ ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ " #ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ? " ( ዮሐ 21፡20 ) ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡ በማቴ 16፡18 ላይ " ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ " ያለዉ ቃል ለ#ቅዱስ_ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡

🔷👉 ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡ በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር ‹‹ፍቁረ እግዚእ›› ተባለ፡፡ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል ‹‹ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ›› ተባለ፡፡ ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ ‹‹ወልደ ነጎድጓድ›› ተብሏል፡፡ ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ ‹‹ነባቤ መለኮት ወይም ታኦሎጎስ›› ተብሏል፡፡ ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ ‹‹አቡቀለምሲስ›› ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡ የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ 70 ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ ‹‹ቁዱረ ገጽ›› ተብሏል፡፡

🔵👉 አስተውሉ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እና ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ የተለያዩ ናቸው ። መጥምቁ ዮሐንስ የካህኑ ዘካርያስና የቅድስት ኤልሳቤጥ ልጅ ነው። ጌታን ያጠመቀው ፣ አንገቱን የተሰየፈው ፣ በዓመት አንድ ጊዜ መስከረም ሁለትና ወር በገባ በ30 የሚታሰብ ነው።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Jan, 16:07

https://youtu.be/NruHWozXTLo?si=OGjmZCG3J4yTFl1y

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Jan, 06:53

https://youtu.be/OWXFwOTkie8?feature=shared

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

10 Jan, 14:39

https://youtu.be/5fwzuRirpfk?si=C4uXUgmZQRcmVmQl

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

09 Jan, 04:42

🔷#ልደታ_ለማርያም
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ይህ ዕለት ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም ‹‹የመመኪያችን ዘውድ፣ የንጽሕናችንም መሰረት›› ያላት ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም የተወለደችበት ነው፡፡

🔵👉 ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ ‹‹ድንግል ትጸንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች (ኢሳ 7፡14)›› ብሎ ትንቢት የተናገረላት ያቺ ድንግል በዚህች ዕለት ተወለደች፡፡

🔶👉 ይህች ቀን ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ‹‹ የወርቅ ልብስ ተጎናጽፋ ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች (መዝ 44፡9)›› ብሎ የተናገረላት ንግሥት የተገኘችባት ዕለት ናት፡፡

🔵👉 ቅዱስ ዮሐንስም በራዕዩ ‹‹ፀሐይን የተጎናጸፈች፣ ጨረቃን የተጫማች፣ አስራ ሁለት የክዋክብት አክሊል በራሷ ላይ ያላት (ራዕ 12፡1)›› ብሎ የመሰከረላት የብርሃን እናቱ ድንግል ማርያም የተወለደችባት ቀን ናት፡፡

🔴👉 የእርስዋም ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ  እንደ ውኃ ፈሳሽ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን አስቀድሞ በትንቢት፣ በምሳሌና በራዕይ የሰውን ልጅ ድኅነት በጉጉት ሲጠባበቁ ለነበሩ ቅዱሳን ሲገለጽ የነበረ ነው፡፡

🔷ድንግል ሆይ የልደትሽ ቀን ልደታችን🔷

🔴👉 ድንግል ሆይ ሰማይ ትልቅ ነው ቢሉ ከአንቺ ጋር አይስተካከልም ፤ ሰማይና ምድርን የሞላው በማህፀንሽ ሞልቶአልና ::

🔵👉 ሰዎች ከአንቺ ይልቅ ምድርን ትልቅ ናት ቢሉኝ ምድርማ የእግሩ መረገጫ ብቻ ናት እላቸዋለሁ :: የኖህ መርከብ ነሽ ይሉሻል፤ የኖህ መርከብ ግን ያዳነችው ኖህን እና ቤተሰቦቹን ነው :: በአንቺ ግን ዓለም ዳነ::

🔷👉 ታቦት ነሽ ይሉሻል ፤ ታቦቱ የያዘው በእግዚአብሔር ጣቶች የተፃፉ ሁለት ፅላትን ነበር :: አንቺ ግን የዓለማትን ጌታ በኃይሉ ፀነስሽው::

🔴👉 ፍቅርን ጸንሳ ፍቅር የወለደች
የምትስግድለትን በጀርባዋ ያዘለች ሰማይ እና ምድር የማይወስኑትን በማህጸኗ የወሰነች ሰው ሆና የአምላክ እናት የተባልሽው .....የሊባኖሷ ሙሽራ ሆይ
ወደ እኛ ነይልን !

“ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም፤ በማርያም ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ!” (ቅዱስ ያሬድ)

     #ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

     ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
          ጥር 1/2017 ዓ.ም
                     ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

07 Jan, 11:01

https://youtu.be/HL2bTRJa6hY?si=OYuBjdWAMIBCI9JK

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

06 Jan, 16:23

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ
🔷👉 ክርስቶስ የልደት በዓል በሠላም
አደረሳችሁ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

05 Jan, 11:59

ተጀምሯል
https://www.youtube.com/live/Ud1j8vSobkc?si=g8F-9fXUOKr4Bnd8

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

05 Jan, 07:46

የአእላፋት ዝማሬ ቅድመ ዝግጅት
🔷👉 8:00 ሰዓት ላይ ነጭ ለብሰን እንገናኝ
ማርፈድ ክልክል ነው

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

04 Jan, 19:16

https://youtu.be/-rM_6HyW4so?si=dNUaQ7c5QfbAaq6b

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

04 Jan, 09:09

የአእላፋት ዝማሬ በሆለታ ከተማ
🔷 1 ቀን ብቻ ቀረው
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 የአእላት ዝማሬ የፊታችን ታህሳስ 27 | 2017 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በወልመራ ወረዳ ቤተ ክህነት በሆለታ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ተዘጋጅቷል።

🔴👉 ስለዚህ እናንተም ላልሠሙት በማሰማት በዕለቱ ሁላችንም ነጭ በመልበስ እና ጧፍ ይዘን በመምጣት ሁላችንም በአንድነት ፈጣሪን እናመሰግን ዘንድ የጌታችንን ልደት የልደቱ ባለቤት ባለበት ስፍራ እናከብር ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

🔷👉 በዕለቱ መገኘት ለማትችሉ በዩትዩብ ቻናሌ ላይ በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የማደርስ ይሆናል።

አይቀርርርርርርርርርርርርርም

🔴👉 ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉ !
አሁኑኑ ሼር ሼር ሼር ይደረግ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 26/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

03 Jan, 13:06

የአእላፋት ዝማሬ በሆለታ ከተማ
🔷 ደረሰ ደረሰ ደረሰ ሼር
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 የአእላት ዝማሬ የፊታችን ታህሳስ 27 | 2017 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት በወልመራ ወረዳ ቤተ ክህነት በሆለታ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ተዘጋጅቷል።

🔴👉 ስለዚህ እናንተም ላልሠሙት በማሰማት በዕለቱ ሁላችንም ነጭ በመልበስ እና ጧፍ ይዘን በመምጣት ሁላችንም በአንድነት ፈጣሪን እናመሰግን ዘንድ የጌታችንን ልደት የልደቱ ባለቤት ባለበት ስፍራ እናከብር ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

🔷👉 በዕለቱ መገኘት ለማትችሉ በዩትዩብ ቻናሌ ላይ በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የማደርስ ይሆናል።

አይቀርርርርርርርርርርርርርም

🔴👉 ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉ !
አሁኑኑ ሼር ሼር ሼር ይደረግ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 25/2016 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

03 Jan, 04:37

#ቅዱስ_መርቆሬዎስ_ሰማዕት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ መርቆሬዎስ የነበረበት ዘመን በሶስተኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ንጉስ ዳክዮስ የሮም ገዥ ሆኖ የነገሰበት ዘመን እንደመሆኑ በዘመኑ የተከበረ የተባለ የውትድርናን ትምህርት ተምሮ ለንጉሱ አገልጋይ ሁኖ ነበር ።

🔵👉 አባቱ በአደን ላይ ሳለ ሊበሉት ከመጡ ገጸ ከለባት እግዚአብሔር ስላዳነውና እንዲያውም አገልጋዮች ስላደረጋቸው በዚህ ተአምር መነሻነት ቤተሰቡ ሁሉ በክርስትና ሐይማኖት አምነው ተጠምቀዋል ።

ከጥምቀት በኋላ
አባቱ 🔴 ኖኅ
እናቱ 🔴 ታቦት
ተብለው ተሰይመዋል

ቅዱሱም ፕሉፓዴር ከሚባል ከቀድሞ ስሙ መርቆሬዎስ ተብሏል። ትርጓሜውም የአምላክ አገልጋይ ማለት ነው።

🔴👉 ባርባርያን በሮም ላይ በጠላትነት በተነሱ ጊዜ ቅዱስ መርቆሬዎስ የጦር አዛዥ ነበርና የእግዚአብሔር መልአክ በሰጠው ሰይፍ በመዋጋት ድልን ተቀዳጅቷል። የባርባርያንን ንጉሥም ገድሎታል።

🔵👉 ንጉስ ዳኬዎስ ግን " ድልን የሰጡን ጣዖታቴ ናቸው። " በማለት ለጣዖታቱ በዓል አደረገ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ይህንን ድርጊት በአደባባይ ተቃወመ በንጉሱም ፊት ትጥቁንና ልብሱን ማዕረጉንም አውልቆ ወረወረው።

🔴👉 በዚህ የተቆጣው ንጉሡም በወታደሮች አስይዞ መከራን ያደርሱበት ዘንድ ወደ ቂሳሪያ ( ቀጰዶቅያ ) ላከው ።በዚያም የሰማዕትነት ስቃይን ከተቀበለ በኋላ ፦

በኅዳር 25 ቀን አንገቱን ተሰይፎ የሰማዕትነት ተጋድሎውን ፈጸመ ።

🔵👉 ቅዱስ መርቆሬዎስ ከዕረፍቱ በኋላ ጸሊም (ጥቁር) የሆነ ፈረሱ ለሰባት ዓመታት በየሀገሩ እየዞረ ስለ ክርስቶስ መስክሯል።

🔴👉 በንጉሡ በዑልያኖስ ዘመን ክርስቲያኖች መከራና ስቃይ በበዛባቸው ጊዜ ሊቀ ጳጳስ ባስልዮስና ጎርጎርዮስ በቅዱስ መርቆሬዎስ #ሥዕል ፊት ሲጸልዩ ሳለ
" #አድነነ_ሥዕል_ከመ_ዘይብል_ኦሆ "
/ #ስዕሉም_እንደሚታዘዝ_ዘንበል_አለ።/

🔵👉 በስእሉ ላይ ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሀዲውን ንጉስ ዑልያኖስን ሲገድለው ከጦሩም ጫፍ ትኩስ ደም ሲንጠባጠብ ታየ።

🔴👉ባስልዮስና ጎርጎርዮስም ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር እጅግ ተደሰቱ ። ቅዱስ መርቆሬዎስ ከሐዲውን ንጉሥ ዑልያኖስን ስላጠፋላቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ ።

🙏 የቅዱስ መርቆሬዎስ ረድኤት በረከት አይለየን ከመከራ ከመከራ ነፍስ ይጠብቀን 🙏

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድር

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

02 Jan, 04:43

ታህሳስ 24 በዓለ ልደቱ ለአቡነ ተክለኃይማኖት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉ተክለሃይማኖት ማለት
የሐይማኖት ተክል ተክለ አብ ተክለ ወልድ ተክለ መንፈሰ ቅዱስ ማለት ነው።

🔵👉 እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቅ ናቸው።

🔵👉 አባታችን ተክለ ሐይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀርያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታህሳስ 24 ቀን 1197 ዓ/ም ተወለዱ።

🔴👉 ጻዲቁ በተወለዱ በሦሥተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው "አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱሰ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ" ማለትም አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱሰ ነው አንዱ መንፈሰ ቅዱስ ነው በማለት የፈጠራቸው አምላካቸውን አመሰግነወታል።

🔵👉 አባታችን ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አሰቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል።

🔷👉 ለዓመታት ከቆሙበት ሳይቀመጡ ከፊት ከኋላ ከጐን እና ከጐን ምንም ሳይደገፉ በአንድ ቦታ በመወሰን ለ22 ዓመታት ደብረ ሊባኖስ በሚገኘው ደብረ አስቦ ዋሻ ውስጥ ሲፀልዩ ከመቆም ብዛትም እግራቸውን አጥተዋል።

🔴👉 ከዚያም ለ7 ዓመታት በአንድ እግራቸው ቆመው ፀሎታቸውን ቀጠሉ። ስለ ክብራቸውም ከእግዚአብሔር
ክንፍ ተሰጥቷቸዋል። በአጠቃላይ ለ29 ዓመታት በጸሎት ቆይተዋል። ዕረፍታቸውም በተወለዱ በ99 ዓመት ሲሆን ቀኑም ነሐሴ 24 ቀን ነው።

🔷👉 በዚህም መሠረት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ለዕረፍታቸው በእግዚአብሔር ፊት ለከበረና ብዙ ክብር ለተሰጣቸው አባታችን በየዓመቱ ነሐሴ 24 ቀን በዓለ ዕረፍታቸውን ታህሳስ 24 ቀን በዓለ ልደታቸውን ጥር 24 ደግሞ ስባረ አፅማቸውን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች።

የአባታችን የፃድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ጸሎታቸው እና አማላጅነታቸው ቤተክርስቲያናችንን አገራችንን ኢትዮጵያን እና እኛን ህዝቦቿን ከፈተና ይጠብቀን ዘንድ በቃልኪዳናቸው ያስቧት አሜን

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድር

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 24/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Jan, 14:49

👆👆👆👆👆👆
በሆለታ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ታህሳስ 27 ቀን በአእላፋት ዝማሬ መርሃ ግብር ላይ የሚዘመሩ
መዝሙሮች እነሆ👆

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Jan, 14:12

https://youtu.be/CN7qKQVzqAc?si=7qzgbR87UeFYLq3x

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Jan, 03:52

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

01 Jan, 03:52

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 #ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብርህ ሐረገ ወይን #ፀሐይ "ማለት ነው። ሊቀ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 22 ቀን በ 277ዓ/ም ተወለደ ሃገሩ ፍልስጤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይበላል። አባቱ አንስጣስዮስ ይባላል። ከልዳ መኻንንት ተሹሞ ይኖር ነበር፥እናቱ ቴዎብስታ (አቅሌስያ ትባላለች።ማርታና እስያ እህቶች ነበሩት።

🔵👉 #10አመት ሲሞላው አባቱ ስለ ሞተ ሌላ ደግ ክርስትያናዊ መስፍን ከቤቱ አሳደገው። በጦር ሃይልም አሰለጠነው። 20 ዓመት ሲሞላው የ 15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቤሩት ሄደ።

🔴👉 በቤሩት ጣዖትን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል።

🔷👉 #ወደፍርስ ቢመለ ዱድያኖስ ሰባ ነገስታትን እና ጣኦታት ሰብስቦ ሲሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖት ቀናዒ ነውና ከቤተ መንግስቱ ገብቶ እኔ ክርስቲያን ነኝ በእየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ አለው።

🔶👉 እርሱንም ማንነቱን ከተረዳ በኃላ አንተ እማ የእኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ አለው።ቅዱስ ጊዮርጊስም ሹመት ሽልማትክ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ እየሱስ ክርስቶስ አልክድም አለ"።

👉 በዚ ግዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት እርሱ ግን"ይህን ከሀዲ እስከማሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ"በማለት እግዚአብሔርን ለመነና እንደ ጸሎቱ በእምነቱ ጽናት የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይቻለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው።

የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ በረከቱ ረድኤቱ ጥበቃው ሁሉ አይለየን

🔷👉 ሊጠናቀቅ ነው ሳያልቅባችሁ ተሳተፉ
ይህን የ100 ብር ቻሌንጅ ሁላችንም እንሳተፍ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩትን እቤታቸው ድረስ በመሔድ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን አድርገናል ነዳያንንም አንድ ቦታ ሰብስበን መግበናል። አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደግሞ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናለ ! ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል። በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ። አሁንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የልደት በዓል (የገና በዓል) ምክንያት በማድረግ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ይላልና ቃሉ በየ ሆስፒታሉ በህመም ምክንያት ከሚሰቃዩ እህት ወንድሞች ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል ! ወገኖቼ ስንቱ ወየ ሆስፒታሉ ጤና አጥቶ መታከሚያም አጥቶ የሚሰቃይ አለ ።

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የታመሙ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል ! ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ70 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇
1000614809683 ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የታሰሩ መጠየቅ
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የተራቡ ማብላት

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 23 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Dec, 05:21

ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት፡- እስጢፋኖስ ማለት ‹‹መደብ›› ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ‹‹አክሊል›› ማለት ነው፡፡

🔵👉 ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ ሁለት ወንድ ልጆችንም ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ይህ ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡

🔴👉 እስጢፋኖስም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ7ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡

🔵👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጀመሪያ ከታላቁ የኦሪት ምሑር የእነ ቅዱስ ጳውሎስ መምህር ከነበረው ከገማልያል የኦሪትን ሥርዓት ጠንቅቆ የተማረ ምሑረ ኦሪት ነው፡፡ ትንቢተ ነቢያትን ያውቅና የአዳኙን መሢሕ መምጣት በጸሎትና በተስፋ ሲጠባበቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችንን መንገድ ሲጠርግ ቢያገኘው ደቀ መዝሙር ሆነና በትጋት ሲያገለግለው ቆየ፡፡

🔴👉 ከ6 ወራት በኃላ ክብር ይግባውና ጌታችን በዮሐንስ እጅ ተጠመ፡፡ ከጌታችንም ጥምቀት በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ይመጣ ዘንድ ያለው መሢሕ እርሱ መሆኑን በአንክሮ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስንም ቅዱስ እስጢፋኖስ ራሱን ጌታችንን አግኝቶት የአንደበቱን ቃል የእጁን ተአምራት አይቶ ይመን በማለት ወደ ጌታችን ዘንድ ላከው፡፡ ሉቃ 7:16-19፡፡

🔵👉 ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ እርሱም አስቀድሞ ጌታችን ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተምሯልና ጌታችንም 72ቱን አርድእት ለስብከተ ወንጌል ሲያሰማራቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኃላ ወንጌልን በአዋጅ ይሰብክ ጀመረ፡፡ ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታችን ዕርገት በሁኃላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህ ማኅበርተኞቹን እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ክርስትናን አስፋፋ፡፡

🔴👉 የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡ በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› እያለ ስለገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡

🔵👉 ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ ‹‹የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ›› ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ 22፡20፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

🔴👉 ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና ‹ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና› የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት፡፡›› ሐዋ 6፡8-15፡፡

🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡

🔴👉 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡

🔵👉 እስጢፋኖስም ‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል› ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም ‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው› ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ 7:52-60፡፡

🔴👉 የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር 1 ቀን ነው፡፡ መእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀብረውታል፡፡ ጥቅምት 17 የተሾመበት በዓሉ ሲሆን መስከረም 15 ቀን ደግሞ ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡

(ምንጭ፡- የመስከረምና የጥቅምት ወር ስንክሳር)

የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ምልጃ ተራዳኢነቱ በረከቱ ሁሉ በሁላችን ላይ ይደርብን

🔷👉አንብበው ጨርሰዋል? እንግዲያውስ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ሼር በማድረግ ወንጌን ያዳርሱ!!

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 17/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

25 Dec, 04:48

#ኪዳነ_ምህረት_ማለት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

🔵👉 እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡ « ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

🔴👉 ስሟን ለሚጠሩ፣ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል
ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።" ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

🔴👉 በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለን።

የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት ፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

ይህን የ100 ብር ቻሌንጅ ሁላችንም እንሳተፍ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩትን እቤታቸው ድረስ በመሔድ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን አድርገናል ነዳያንንም አንድ ቦታ ሰብስበን መግበናል። አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደግሞ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናለ ! ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል። በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ። አሁንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የልደት በዓል (የገና በዓል) ምክንያት በማድረግ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ይላልና ቃሉ በየ ሆስፒታሉ በህመም ምክንያት ከሚሰቃዩ እህት ወንድሞች ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል ! ወገኖቼ ስንቱ ወየ ሆስፒታሉ ጤና አጥቶ መታከሚያም አጥቶ የሚሰቃይ አለ ።

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የታመሙ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል ! ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ70 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇
1000614809683 ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የታሰሩ መጠየቅ
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የተራቡ ማብላት

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 16 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

25 Dec, 04:48

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

24 Dec, 04:40

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 15 /2017 ዓ.ም

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ቂርቆስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሚስ ፣ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ። ሀገራቸውም ሮም ነበር። በዘመነ ሰማዕታት በጨካኙ እና በአረመኔው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግስት አዋጅ ታውጆ ነበር፡፡ይህም በ303 ዓ.ም ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙ ክርስትያኖች ተሰደዱ ፤ ቅድስት እየሉጣም የሦስት አመት ልጇን ይዛ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች፡፡
.
🔷👉 ንጉሥ እለ እስክንድሮስ አስጠርቶ ክርስቶስን ካጅ ለጣዖት ስገጅ አላት። በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም አለች እምቢ ካልሽ በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ አስፈራራት ፤ እርሷ ግን ምንም አልፈራችም - እምነታቸው ጠንካራ ነውና።
.
🔷👉 በብረት ጋን ውኃ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሎአቸው ብሎ አዘዘ። የውኃው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ ከ4 -15 ክንድ ያህል ይፈላ ነበር። በፈላው ውኃ ሊጨምሮቸው ሲወስዷቸው የኢየሉጣ ልብ በፍርሀት ታወከ በዚህ ግዜ በቅዱስ ቂርቆስ ላይ መንፈስ ቅዱስ አድሮ የእናቱን ፍርሀት አስወገደ፡፡እናቴ ሆይ በርች ፤ ጨክኝ ፤ አናንያን ፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነን የለምን እያለ እናቱን እያደፋፈረ ከእሣቱ ቀረበ ፤ እርሷም ጨክና በፍጹም ልቧ ተያይዘው ከፈላው ውኃ ገብተዋል፡፡
.
🔴👉 ልዑል እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አዳናቸው፡፡
.
🔷👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛ አገልጋዮችህም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሣት አጥፋልን ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን። የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን።
.
🔴👉 ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15(፲፭) ቀን በሰይፍ ተመትተው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።

23 Dec, 17:31

ዲያቆን ድንግል ያልሆነችውን ሴት
🔷👉 ማግባት ይችላልን ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 የዲያቆን ጋብቻን በተመለከተ የእኔ ድንግልና ለአንቺ ይበቃል የሚል ሐሳብ ያላቸው ሰዎች አሉ። ይህ ንግግራቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እንዴት ይታያል። ዲያቆን ድንግልና የሌላትን ሴት ማግባት ይችላል? ድንግልና የሌላት ሴት ቢያገባስ በክህነቱ መቀጠል ይችላል?

🔴👉 ካህን የሚለው ቃል አገልጋይ የሚል ትርጉም አለው። እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ የክህነት ደረጃዎች በሦስት ይከፈላሉ። ከእነዚህ የክህነት ደረጃዎች መካከል አንደኛው ዲቁና መሆኑን በክህነት ዙሪያ የተጻፉ የቤተ ክርስቲያን መጽሐፍቶችን በማንበብ የምንረዳው ጉዳይ ነው።

🔵👉 ዲያቆን የሚለው ቃል ዲያኮኖስ ከሚለው የግሪክ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ረዳት አገልጋይ ማለት ነው። ዲያቆን ከእርሱ በላይ ላሉት የክህነት ደረጃዎች ላይ ላሉ አባቶች የሚረዳ የሚላክ በቤተ መቅደስ የሚያገለግል የክርስቶስን ደም ለምዕመናን የሚያቀብል መንፈሳዊ አገልጋይ ነው።

🔴👉 ዲያቆንነት ወደ ሌሎቹ መንፈሳዊ የክህነት ደረጃዎች ለመግባት በር እንደመሆኑ መጠን ለዲያቆን የሚነገረው ሥርዓት ሁሉ ወደ ሌሎቹ የክህነት ደረጃዎች መወጣጫ መሰላል መሆኑን ማወቅ ይገባናል። ዲያቆን ሳይሆኑ ቅስና ቁምስና ከዚህም በላይ ያሉ መንፈሳዊ የአገልግሎት ደረጃ ላይ መድረስ አይቻልም። በመሆኑም ዲያቆን ወደ ሚቀጥለው መንፈሳዊ ማዕረግ ለማደግ ወይ ሊመነኩስ ወይም ሊያገባ ያስፈልገዋል። ጋብቻን ከመረጠና በዚህ መንፈሳዊ ተቆም /ትዳር/ ውስጥ ሁኖ እግዚአብሔር ማገልገል ከፈለገ ጋብቻውን እንደ እንደ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ሊመሰርት ይገባዋል።

🔴👉 ጋብቻን በተመለከተ ለካህናት የተሰራው ሥርዓት ለምዕመናን ከተሰራው ሥርዓት ይለያል። ካህን የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልጋይ ተንስኡ ለጸሎት እያለ ለአምልኮተ እግዚአብሔር የሚያነቃቃ ለምዕመናን የክርስቶስን ሥጋና ደም የሚያቀብል ነውና ከምዕመናን የተለየ ሥርዓት ቢሰራለት ብዙም አይገርምም። ከአገልግሎቱ ክቡርነት አንጻር ለምዕመናን የተፈቀደ ለእርሱ ይከለከላል።

🔷👉 ለምሳሌ ምዕመናን በሞት ምክንያት ወይም በዝሙት ሚስቶቻቸውን ወይም ባላቸውን ቢያጡ ሌላ ሁለተኛ ማግባት ተፈቅዶላቸዋል። ይህንንም ፍትሃ ነገሥት ሲናገር እንዲህ ይላል ፦ ለወንዶች ግን ተክሊል የማይደርስበት ሁለተኛ ጋብቻ ይገባቸዋል ይፈጸምላቸዋል/። 24:901 ለካህናት ግን ሁለተኛ ጋብቻ አልተፈቀደላቸውም። አንድ ካህን ሚስቱ ብትሞትበት ሌላ ሴት ቢያገባ ከክህነቱ እንጂ ወደ ቤተ መቅደስ ለአገልግሎት አይገባም። ይህንን በተመለከተ ፍትሃ ነገሥት እንዲህ ይላል ፦ " ሁለተኛ የሚያገቡት ወንዶች ካህናት ቢሆኑ ከሹመታቸው ይሻሩ።" 24:902

🔴👉 ሰለዚህም የካህናት ጋብቻ ከምዕመናን የጋብቻ ሕግ ልዩ መሆኑን መረዳት ተገቢ ይሆናል። ቤተ ክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ የቀዳችው በብሉይና ሐዲስ የተቀመመ ሥርዓት አላት። የካህናት ጋብቻንም በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሥርዓትና ድንጋጌ አላት።

🔷👉 የካህናት ጋብቻን በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ፦" የአምላኩም ቅባት ዘይት ቅዱስነት በላዩ ነውና ከመቅደስ አይውጣ የአምላኩንም መቅደስ አያርክስ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። እርሱም ሚስትን በድንግልናዋ ያግባ። ባልዋ የሞተባትን ወይም የተፋታችውን ወይም ጋለሞታይቱን አያግባ ነገር ግን ከሕዝቡ ድንግሊቱን ያግባ።" (ኦሪት ዘሌዋውያን 21:12-14 ) ካህን ሰለ ክብረ ክህነቱ ሲባል ድንግሊቱን እንጂ ጋለሞታይቱን (ፈት የሆነችውን) እንዳያገባ በሕግ ተከልክሏል። ስለዚህም ዲያቆን ካህን እንደመሆኑ መጠን ከኦርቶዶክሳዊያን አንስት መካከል አንዷን መርጦ በማግባት የእግዚአብሔር ቃል እና ሥርዓት ሊያከብር ይገባዋል።

🔷👉 ይህንን ቃል አክብረን በሕይወታችን ልፈጽመው ሲገባን አንዳንድ ዲያቆናት ግን " የእኔ ድንግልና ለአንቺ ይሆናል" በማለት ከዚህ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ፈቀቅ ለማለት የግል ፍልስፍናቸውን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሲያራምዱ ይሰማሉ። በእውነት ይህ ስንፍና ነው የሥጋ ሐሳብን ለመፈጸም ይህንን ያህል መድከም ሳያንስ ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የወጣን ሐሳብ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አስመስሎ መናገር ስንፍና ካልተባለ ሌላ ምን ይባላል?

🔵👉 እነዚህ ሰዎች ያነሱት ሐሳብ የግል ፍልስፍናቸው ቢሆንም በዚህ ሐሳባቸው የሚሳብ ይኖራልና ላነሱት ሐሳብ እንደ የቤተ ክርስቲያን የድንግልና አስተምህሮ መሰረት በማድርግ ምላሽ ልንሰጣቸው ይገባናል።

🔴👉 በግዙፍ ያለ ድንግሌ ሥጋ አንድ ብቻ ነው። ድንጋሌ ሥጋ አንዴ በኃጢአት ምክንያት ከጠፋ እንደ ተሰበረ የሸክላ እቃ እንደ ሞተ ሰው ነው። በባሕታዊ ጸሎት በፓትርያርክ ብራኬ እንኳን አንመለስም። ታዲያ በምን ምክንያት ነው የሥጋ ድንግልና የሌላት ሴት ድንግል ከሆነ ዲያቆን ጋር በመጋባቷ ብቻ ድንግል ሳትሆን ለደናግልና የሚፈጸመው ተክሊል የሚፈጸምላት? የዲያቆኑስ ድንግልና በምን ሒሳብ ነው ለእርሷ የሚሆነው?

🔴👉 ድንግልና የግል ሩጫ ነው። ቤተ ክርስቲያን ይህንን የንጽሕና ሩጫ እስከ ጋብቻ ድረስ የጠበቀ ልጇን ተክሊል ሸልማ ታከብረዋለች እንጂ የአንተ ድንግልና ለምታገባት ሚስትህም ይበቃል የሚል አስተምህሮ የላትም። የአንዱ ድንግልና ለሌላዋ ይሆናል የሚል የመጽሐፍ ምስክርም የለም። ይልቁንም ድንግልና የግል እንጂ ለሌላው የምናጋራውም አለመሆኑን ፍትሃ ነገሥት እንዲህ ሲል ይመሰክራል ፦ " የሚያገቡ ፈቶች ቢሆኑ ተክሊል አያድርጉላቸው። ይህ ተክሊል በጋብቻ ጊዜ ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት ይገባቸዋልና። ከሚያገቡት አንዱ ድንግል ቢሆን ብቻውን ይባረክ።" 24:906

🔵👉 በዚህ የፍትሃ ነገሥት አንቀጽ ወደ ቤተ ክርስቲያን ጋብቻ ለመፈጸም ሦስት አይነት ጥንዶች እንደሚመጡ መረዳት እንችላለን። የመጀመሪያዎቹ ሁለቱም ድንግልና የሌላቸው ሲሆኑ ለእነዚህ ጥንዶች ቤተ ክርስቲያን ተክሊል ሳይሆን የማአስባን የጋብቻ ሥርዓት እንዲፈጸምላቸው ያዛል። ሁለተኞቹ ደግሞ ሁለቱም ድንግልና ያላቸው መሆናቸውን ጠቅሶ " ይህ ተክሊል በጋብቻ ጊዜ ለድንግል ወንድና ለድንግል ሴት ይገባቸዋልና" ብሎ ለእነዚህ ደናግላን ጥንዶች ተክሊል እንዲፈጸምላቸው ይደነግጋል።

🔴👉 በሦስተኛ ደረጃ አንዱ ድንግል ሁኖ ሌላይቱ ድንግል ባትሆን የእርሱ ድንግልና ለእርሷም ይሆናልና ተክሊል ለሁለቱም ይፈጸምላቸው አይልም። የሚለው "ከሚያገቡት አንዱ ድንግል ቢሆን ብቻውን ይባረክ።" ከጥንዷቹ መካከል ድንግል የሆነ በተክሊል ጸሎቱ ተባርኮ ያግባ በማለት የድንግልና ብድር እንደሌለ ያስገነዝባል።

🔴👉 ሰለዚህ ምክንያት እየፈለግን የአባቶቻችን የድንበር ምልክት ከምናፈርስ ዲያቆን ድንግልና ያላትን ያግባ የሚለውን የቤተ ክርስቲያንም ሥርዓት አጥብቀን እንያዝ።

🔷👉 ተፃፈ :- በመ/ር አቤል ተፈራ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 14 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

23 Dec, 17:31

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

23 Dec, 05:13

🔷 #አቡነ_አረጋዊ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

🔴👉 አረጋዊ ማለት ሽማግሌ ወይም የልጅ አዋቂ ማለት ሲሆን አባታቸው ይስሃቅ እናታቸው እድና ይባላሉ:: በቈስጥንጥንያ ወይም በሮም በታህሳስ ፲፬ ፫፻፸፭ ዓ.ም ተወለዱ::

🔵👉 አባታችን በቀደመ ስማቸው ዘሚካኤል ሲባሉ ከዘጠኙ ቅዱሳን መካከል አንዱ ናቸው። የንጉስ ልጅ ሆነው ሳለ የዓለምን ነገር ስለናቁ ወደ አባ ጳኩሚስ ዘንድ በመሄድ በአስራ አራት ዓመታቸው ስርዓት ምንኩስናን ተቀብለዋል።

🔷👉 እናታቸውም ንግስት እድና የምናኔው ሕይወት ስለሳባት ወደ ገዳሙ በመምጣት እንደ ልጇ መንኩሳለች።

🔴👉 ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ በመጻሕፍት ስላነበቡ እንዲሁም ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የአስራት ሀገር ሆና መሰጠቷን ከተረዱ በኋላ ይህችን ቅድስት ሀገር ለመጎብኘ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ጎብኝተው ወደ ሮም ተመለሰዋል።

🔷👉 ከዚያም ተመለሰው ለስምንት ባልንጀሮቻቸው ሃገርስ ባሳየኋችሁ ሐዋርያ ሳያስተምራት በህጉ በስርዓቱ ጸንታ የምትኖር ብለው ከስምንቱ ጋር ከኬልቄዶን ጉባኤ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል ።

🔵👉 አባታችን አቡነ አረጋዊ በዓት ፍለጋ ለብዙ ጊዜ ደክመዋል ኋላም በእግዚአብሔር ፍቃድ ደብረ ዳሞ በሚባለው ቦታ ደርሰዋል፤ በተራራውም ጫፍ ብርሃን ቢታያቸውም ተራራማ ስለነበር መውጫው ቢቸግራቸው የታዘዘላቸው ዘንዶ ተራራው ጫፍ አውጥቷቸዋል።

🔴👉 ከ፰ ቅዱሳን ጓደኞቻቸው ጋር በ፬፻፷፮ ዓ.ም ወደ ታላቂቷ ሀገር ኢትዮጵያ መጥተዋል። ደብረ ዳሞ የቀድሞ ስሙ ሃሌ ሉያ ይባል ነበር:: ከዚያ ተራራ ስር ማን ያውጣኝ እያሉ ሲፀልዩ መልዓኩ ቅዱስ ሚካኤል ዘንዶ ላከለት ዘንዶም ቁመቱ 60 ክንድ ነበር።

🔵👉 30 ክንድ ወደፊት 15 ክንድ ወደ ኋላ ከመሀል ያለው 15 ክንድ ወገባቸው ላይ ተጠምጥሞ ጥቅምት ፲፪ ቀን መልዓኩ ዘንዶውን እያዘዘው ተራራውን ላይ ወጡት:: ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በተወለዱበት በ150 ዓመታቸው ወደ ደብረ ዳሞ ገዳም ወጥተዋል።

🔷👉 ዘጠና ዘጠኝ አመት ሲሞላቸው ጌታችን በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾላቸው ምድራዊ መንግስትን ትተህ ስላገለገልኝ ህልፈት ሽረት የሌለባትን ሰማያዊ መንግስቴን አወርስሀለው ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል።

🔴👉 በስምህ የተማጸነውን እስከ አስራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሀለው አንተም ከሞት ኃይል ትሰወረላህ ብሏቸዋል። እነደ ተነገራቸውም አንደ ሄኖክና ኤልያስ በሞት ሳያዩ በሞት ፋንታ በጥቅምት፲፬ ቀን ፭፻፳፭ ዓ.ም #ተሰውረዋል::

የጻድቁ አባታን አቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከት አይለየን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 14 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Dec, 07:22

https://www.youtube.com/live/mDBvD3x2skw?si=qr2vHt4K74JQe8JT

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Dec, 03:45

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Dec, 03:45

#ታህሳስ_13_ቅዱስ_ሩፋኤል
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ታኅሣሥ ዐስራ ሦስት በዚህች ቀን በዚህች ዕለት ፈታሄ ማህጸን ሊቀ መልአክት ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱና ተአምር ያደረገበት ዕለት ነው፡፡

🔷👉 ሰማያውያን ከሆኑ ከመላአክት አለቆች ከቅዱስ ሚካኤልና ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥሎ 3ተኛ ነው፡፡ "ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል፡፡ ጦቢት 12፡15፡፡ ሩፋኤል የሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል መልአከ የሰላምና የጤና መልአክ ይባላል፡፡ በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ሆነ ቁስል ይፈወስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” መጽሐፈ ሄኖክ 6፡3፡፡

🔴👉 ቅዱስ ሩፋኤል የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ሁሉ ላይ በሰው ልጆችም ቁስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል፡፡ ሄኖክ 10፡13፡፡ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ በማኅፀን ላለ ችግርና ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም፡፡

🔷👉 ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት በማሕፀን እያለ ማለትም በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በመውለጃቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነት ያለን ረቂቅ ርኩስ መንፈስ ያውቃል፡፡ አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ጭን ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሠቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል ጦቢት 3፡8-17፡፡

🔴👉 ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ሄኖክ 3፡5-7፡፡ በዚህ መሠረት ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሄኖክ 2፡18፡፡ ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠብቃቸው እግዚአብሔር እንዳዘዘዉ የሚከፍታቸዉ የሚዘረጋቸዉ ይህ ታላቅ መልአክ ነዉ፡፡

🔷👉 የምህረትና የረድኤት መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሥራዎቹ አንፃር በተለያየ ስም ይጠራል፡፡ "ፈታሄ ማህጸን" ይባላል-እናቶች ሲወልዱ ምጥ እንዳይበዛባቸዉ የሚራዳ መልአክ ስለሆነ አያሌ ክርስቲያኖች ማርገዛቸዉን ካወቁ ጀምሮ ድርሳኑን በማንበብ መልኩን በመድገም ጠበሉን በመጠጣት ሰዉነታቸዉን በመቀባት ይለምኑታል፡፡ እንደ እምነታቸዉ ጽናት ይደረገላቸዋል፡፡

🔵👉 ዳግመኛም "ዐቃቤ ኖኀቱ ለአምላክ" ይባላል-ሰማያዉያን መዛግብት በእጁ የሚጠበቅ ስለሆነ ነው፡፡ ዳግመኛም "መራሔ ፍኖት" ይባላል-ጦቢትን በቀና መንገድ መርቶታልና ነው፡፡ እንዲሁም "መላከ ክብካብ" ይባላል-ጦቢያና ሣራን ያጋባ ጋብቻቸዉን የባረከ በመሆኑ ነው፡፡

🔴👉 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ያደረገው ተዓምር ይህ ነው፡፡ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል በዓል እስኪፈፀም ድረስ በከበረ ሊቀ ጳጳስ አባ ቴዎፍሎስ ዘመን በምድረ ግብጽ ውስጥ ከእስክንድርያ ውጭ በታናፀች አንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በአንድነት ተሰበሰቡ፡፡ ይህች ቤተ ክርስቲያን ከአሳ አንበሪ ላይ የታነፀች ነበር፡፡ ነገር ግን በወደቡ አጠገብ ከነበረ ግዙፍ አንበሪ ጀርባ ላይ መታነጿን ቀድሞ ያነጿት ሰዎች ቢሆኑ ከካህናትም ቢኾን ያወቀ አልነበረም፡፡

🔷👉 ያ አንበሪም የቤተክርስቲያኑ ህንጻ በከበደው ጊዜ ፈጽሞ ተንቀሳቀሰ፡፡ ከአሸዋማው መሬት ላይ በባህሩ ዳርቻ የታነፀች ይህች ቤተ ክርስቲያንም ከመሰረቷ አናወጻት፡፡ ያን ጊዜ ትልቁም ትንሹም ወንዱም፣ ሴቶችም፣ የተሾሙ ዲያቆናት፣ ካህናት፣ ሕዝቡም ሁሉ ደነገጡ ታወኩ፡፡ አሣ አንበሪው ግን መንቀሳቀሱን አልተወም፡፡ በመንቀሳቀሱም የቤተ ክርስያኗ ሕንፃ እኩሌታ ይሰነጠቅ ዘንድ ጀመረ፣ ምድርን ተናወፀች፣ ንጉስና፣ ሊቀ ጳጳሳቱም፣ ካህናቱም፣ ዲያቆናቱም፣ ህዝቡም፣ ሁሉም ካሉበት በባህሩ ወደብ ከተሰራች ከዚህች ቤተ ክርስቲያን መናወጥ የተነሳ ፍርሃት መንቀጥቀጥ በላያቸው ወረደ፡፡

🔴👉 ያ አንበሪ ግን በባህሩ ውስጥ ወደፊት መንቀሳቀስ ጀመረ፡፡ ቤተ ክርስቲያኗም በጀርባው ላይ ነበረች፡፡ በቤተ ክርስቲያኗ ውስጥ የሉትም ሁሉ ያ አሳ አንበሪ ወደ ባሕሩ ውስጥ ሊያሰጥመን ነው ሲሉ አሠቡ፡፡ ያን ጊዜም በሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ስዕል ፊት በጽኑ አለቀሱ፡፡ በአንድ ቃልም "ገናናው የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ሆይ ርዳታህ ፈጥኖ ይደርስልን ዘንድ በቅድስት ቤተክርስቲያን ወደተሰበሰብን ወዳጆችህ ተመልከት" እያሉ ይጸልዩ ጀመር፡፡ ያንጊዜም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ከሰማይ ወርዶ ያችን ቤተክርስቲያን በብሩሃት ክንፎቹ እንደደመና ጋረዳት፡፡

🔷👉 በእጁ በተያዘ የብርሃን በትረ መስቀሉ ያን ኣሣ አንበሪ ወገቶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይል ከቦታህ ሳትንቀሳቀስ እስከትውልድ ፍፃሜ ዘመን ለዘለአለም ትኖር ዘንድ አዝዝሃለሁ" አለው፡፡ ከዚህም በኋላ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያኗን ከነመዓዘኗ ከግርግዳዎቿ ከመሠዊያዋ በውስጧ ተተክለው ካሉት ሁሉ ጋር ከጀርባው ላይ እያለች ያንን አሳ አንበሪ ወግቶ በያዘበት ብርሃናዊ በትረ መስቀሉ ወደቀድሞው የባሕሩ ወደብ ጎተተው፡፡ ያንጊዜም ግንቡ ቦታውን ሳይለቅ እርስ በእርሱ ተጣበቀ፡፡

🔴👉 ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል አሣ አንበሪውን በቀድሞ ሥፍራው ያቺን ቤተክርስቲያን በቀደመ መሠረቷ ላይ አጽንቷቸዋልና፡፡ ሊቀመላእክት ቅዱስ ሩፋኤልም አዳኝ የሆነ የጌታው የኢየሱስ ክርስቶስን ስም ጠርቶ ከሞት እንዳዳናቸው ሁሉም አስተዋሉ፡፡ በድንቅ ተዓምራቱ የዳኑ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ በሊቀመላእክቱ ቅዱስ ሩፋኤል ላይ አድሮ ድንቅ ተዓምራቱን ስለገለጸላቸው የቅዱስ ሩፋኤልን አምላክ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ የዚህች ቤተክርስቲያን ታሪክም በዓለም ሁሉ በየአውራጃዎቹም ተሰማ፡፡

🔴👉 የቅርብም የሩቅም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል የለመኑትን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ የነገሩትን ያማልዳቸው ዘንድ በውስጧ ይጸልያሉ፡፡ በዚችም ቤተክርስትያን ብዙ ውስጥ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራት ተደረጉ፡፡ ታኅሣሥ 13 ቀንም ተአምራቶቹ ከተፈጸመባቸው ዕለታት አንዷ ናት፡፡ ቅዳሴ ቤቱም በዚሁ ዕለት ተከናውኗል፡፡

🔷👉 ምንጭ ;- ስንክሳር_ዘወርኀ ታህሣሥ እና ከገድላት አንደበት

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ታህሳስ 13 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Dec, 15:08

https://youtu.be/yAFlBYIPUyY?si=xE6Wt1lKIP3fz9V8

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Dec, 06:26

https://www.youtube.com/live/ana0WiM_o_A?si=Jt3MgH7kwgEBKVin

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Dec, 03:29

https://youtu.be/vRfVac1t9uo?si=sNltB1F9FUju3N_k

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

30 Nov, 04:59

#ጽዮን_ማርያም
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ጽዮን» ተብላ ትጠራለች። ምክንያቱም ጽዮን ማለት አምባ መጠጊያ ማለት እንደ ሆነ ሁሉ እመቤታችንም፦ ለነፍስና ለሥጋ ፥ለኃጥአንና ለጻድቃን፥ አምባ መጠጊያ ናትና።

🔴👉 ቅዱስ ዳዊት፦ «እስመ ኀረያ እግዚ አብሔር ለጽዮን ፥ ወአብደራ ከመ ትኩኖ ማኅደሮ ፥ ዛቲ ይእቲ ምእራፍየ ለዓለም፤ ዝየ አኅደር እስመ ኅረይክዋ። እግዚአብሔር ጽዮን መርጧታልና ፥ ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና ፥ ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፤ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።» ያለው እመቤታችንን ነው። መዝ ፩፻፴፮ ፥ ፲፫።

🔵👉 ምክንያቱም ፦ ለእናትነት መርጦ ያደረው በእርሷ ማኅፀን ነውና። «ለ ዘላለም መረፊያዬ ናት፤» ማለቱም፦ እርሱ የዘለዓለም አምላክ እንደሆነ ፥ እርሷም ለዘለዓለም ወላዲተ አምላክ ተብላ እንደምትኖር የሚያመለክት ነው።

#ጽዮን_ቤተ_ክርስቲያን

🔴👉 ቤተ ክርስቲያንም ጽዮን ትባላለች። ደብረ ጽዮን የሚሠዋበት መሥዋዕተ ኦሪት ነበር። በደብረ ጽዮን ዘሐዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያን ግን የሚሠዋው መሥዋዕተ ሐዲስ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። « በጽዮን መለከት ንፉ፤ በቅዱሱም ተራራ ላይ ዓዋጅ ንገሩ፤» እንደተባለ፦ ሐዲስ ሕግ ወንጌል ይታወጅባታል። ኢዩ ፪፥፩። በተጨማሪም፦ «በጽዮን መለከትን ንፉ፤ ጾምንም ቀድሱ፤ ምሕላንም ዓውጁ፤» የሚል አለ። ኢዩ ፪ ፥፲፭።

🔷👉 በመሆኑም ሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት ይታወጅባታል። ጸሎተ ምሕላ ይያዝባታል። ጡት ከሚጠ ቡት ሕፃናት ጀምሮ እስከ ሽማግሌዎቹ ድረስ ሕዝቡን ሰብስቡ፤ እንደተባለ፦ ሁሉም ለቅዳሴ፥ለማኅሌት፥ ለሰዓታት ፥ ለመዝሙር ይሰ በሰቡባታል። ሕፃናት በአርባ በሰማኒያ ቀን እየተጠመቁ አባል ይሆኑባታል።

🔴👉 ጌታችን በወንጌል፦ «ሕፃናትን ተዉአቸው፤ ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሉአቸው፤» ያለው ለዚህ ነው። ማቴ ፲፱ ፥፲፬። ለሐዋርያው ለቅዱስ ጴጥሮስም፦ ሕፃናቱን ፥ ወጣቶቹን እና አ ረጋውያኑን፦ በግልገሎች ፥ በጠቦቶችና በበጎች መስሎ ጠብቃቸው ብሎታል። ዮሐ ፳፩፥፲፭።

ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል
ማርያም ረድኤትና በረከት ይክፈለን!!!

🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 21/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

29 Nov, 17:18

#ህዳር 21 #ጽዮን_ማርያም
🔷#ለምን_ትከበራለች ??🔷
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 "ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡

🔴👉 ኅዳር 21 ቀን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዓመታዊ በዓል በተለየ መልኩ የምናከብርበት ምክንያት :-

🔷👉 1. ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ዕለት በማሰብ። ታቦተ ጽዮን ንጉሥ ሰሎሞን ወደ ሠራላት ቤተመቅደስ በክብር የገባችበትን ዕለት በማሰብ

🔴👉 2. ቀዳማዊ ምኒልክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገደ እስራኤል የበኲር ልጆች ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛርያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበት ዕለት መሆኑን በማሰብ

🔷👉 3. በሦስት መቶ ሠላሳ ዓመተ ምሕረት በአብርሃ ወአጽብሃ ዘመነ መንግሥት ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ይሁን ተብሎ ዐዋጅ የታወጀበትን በማሰብ

🔴👉 4. የቀደሙ ነብያት ስለእመቤታችን በተለያየ አምሳል ያዩበት ለምሳሌ፦ ነብዩ ዕዝራ በሃገር መንፈሳዊት፣ ሕዝቅኤል በተዘጋች ቤተመቅደስ፣ ዘካርያስ በተቅዋመ ወርቅ ወዘተ ያዩበትን ዕለት በማሰብ

🔷👉 5. አብርሃና አጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተመቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበትን በማሰብ

🔴👉 6. በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያናትን ስታቃጥል ታቦተ ጸዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሐይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበትን ዕለት በማሰብ

🔵👉 በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ከፍ ባለ መንፈሳዊ በዓል እናከብራለን፡፡ ይኽ ሲባል ግን በዓሉ የሚከበረው በአክሱም ጽዮን ማርያም ብቻ ነው ማለት ሳይሆን ታቦተ እግዝእትነ ማርያም ባለችበት ቦታ ሁሉ መከበሩን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡

ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል
ማርያም ረድኤትና በረከት ይክፈለን!!!

🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 21/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

29 Nov, 13:43

https://youtu.be/QtVcP6pUF5g?si=s6i-87OSrkPuoMGc

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

28 Nov, 10:14

ቅዱስ ገብርኤል ማን ነው
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ገብርኤል ማለት " እግዚእ ወገብር”፦ የእግአብሔር አገልጋይ ማለት ነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበት በዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፦ማን ፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹ ጊዜ “የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅ በያለንበት ጸንተን እንቁም ብሎ ያረጋጋቸው መልአክ ነው።

🔵👉 በዚህም ምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ለብስራት የሚላክ ከሰዎች ጋር ታላቅ ግንኙነት ያለዉ ተወዳጅና ፈጣን መልአክ ነዉ ።

🔵👉 ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደምትወልድ እመቤታችንን ያበሰራት እና ለመጀመርያ ጊዜ ከሰዎች በፊት ያመሠገናት ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ።

🔴ስለስቱ ደቂቅን ናቡከደነጾር በእሳት ላይ በጣላቸዉ ጊዜ ፈጥኖ በመድረስ ከእሳት ያዳናቸዉ ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔵እንዲሁም ኢየሉጣና ቂርቆስ በፈላ ዉኃ ዉስጥ በተጣሉ ጊዜ ዉኃዉን በማቀዝቀዝ ያዳናቸዉ ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔵👉 ሳጥናኤል ሥላሴን በካደ ጊዜ መላእክትን በቃሉ ያጽናናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔴👉 ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔵👉 በጨለማና በሞት ጥላ ውስጥ ለሚኖሩ ብርሃን የገለጸና የሰበከ ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔵👉 ዳንኤልን ከአናብስት ያዳነው ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔵👉 ወደ ዘካርያስ የተላከ የዮሐንስን ልደት ያበሰረ ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔴👉 ሰብአ ሰገልን በኮከብ ምልክት የመራቸው ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔵👉 ድንግል ማርያምና ሕፃኑን ክርስቶስን በምድረ በዳ በስደታቸው የመራ ቅዱስ ገብርኤል ነዉ ::

🔴👉 የብርሃን ራስ ወርቅ የተቀዳጀ መላኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው !

የመልአኩ ጥበቃ እና ረድኤት አይለየን

#ፎሎው_ማድረግ_እንዳይረሳ
፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 19/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

27 Nov, 19:43

https://youtu.be/wCiyZ13kBYs?si=G0l-9G0u7dRrXbRP

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

27 Nov, 18:54

ገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን ምሥጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ የምንልበትን ጸጋ አሰጠን።

🔵👉 ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን፤ የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን፣ ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች፣ ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን።

🔴👉 ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛ አገልጋዮችህም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን።

🔴👉 የሰይጠንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ እጠራሃለሁ፤ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ፡፡

🔴👉 ቅድስት ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበር ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ፡፡

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንን ለእኛ ከሠማይ ሠረገላ ናልን፡፡

🔴👉 የደስታንም ቃል አሰማን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት፣ የሞት፣ የክስረት፣ የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጎስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን፡፡

🔵👉 እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ማደሪያው የሆነችው ድንግል ማርያምን በጣም እንወዳታለን፤ በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን በመንግስተ ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን ለዘላለሙ

🔴👉ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 19/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Nov, 04:24

ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት፡- እስጢፋኖስ ማለት ‹‹መደብ›› ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ‹‹አክሊል›› ማለት ነው፡፡

🔵👉 ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ ሁለት ወንድ ልጆችንም ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ይህ ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡

🔴👉 እስጢፋኖስም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ7ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡

🔵👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጀመሪያ ከታላቁ የኦሪት ምሑር የእነ ቅዱስ ጳውሎስ መምህር ከነበረው ከገማልያል የኦሪትን ሥርዓት ጠንቅቆ የተማረ ምሑረ ኦሪት ነው፡፡ ትንቢተ ነቢያትን ያውቅና የአዳኙን መሢሕ መምጣት በጸሎትና በተስፋ ሲጠባበቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችንን መንገድ ሲጠርግ ቢያገኘው ደቀ መዝሙር ሆነና በትጋት ሲያገለግለው ቆየ፡፡

🔴👉 ከ6 ወራት በኃላ ክብር ይግባውና ጌታችን በዮሐንስ እጅ ተጠመ፡፡ ከጌታችንም ጥምቀት በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ይመጣ ዘንድ ያለው መሢሕ እርሱ መሆኑን በአንክሮ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስንም ቅዱስ እስጢፋኖስ ራሱን ጌታችንን አግኝቶት የአንደበቱን ቃል የእጁን ተአምራት አይቶ ይመን በማለት ወደ ጌታችን ዘንድ ላከው፡፡ ሉቃ 7:16-19፡፡

🔵👉 ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ እርሱም አስቀድሞ ጌታችን ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተምሯልና ጌታችንም 72ቱን አርድእት ለስብከተ ወንጌል ሲያሰማራቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኃላ ወንጌልን በአዋጅ ይሰብክ ጀመረ፡፡ ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታችን ዕርገት በሁኃላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህ ማኅበርተኞቹን እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ክርስትናን አስፋፋ፡፡

🔴👉 የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡ በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› እያለ ስለገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡

🔵👉 ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ ‹‹የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ›› ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ 22፡20፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

🔴👉 ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና ‹ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና› የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት፡፡›› ሐዋ 6፡8-15፡፡

🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡

🔴👉 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡

🔵👉 እስጢፋኖስም ‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል› ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም ‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው› ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ 7:52-60፡፡

🔴👉 የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር 1 ቀን ነው፡፡ መእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀብረውታል፡፡ ጥቅምት 17 የተሾመበት በዓሉ ሲሆን መስከረም 15 ቀን ደግሞ ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡

(ምንጭ፡- የመስከረምና የጥቅምት ወር ስንክሳር)

የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ምልጃ ተራዳኢነቱ በረከቱ ሁሉ በሁላችን ላይ ይደርብን

🔷👉አንብበው ጨርሰዋል? እንግዲያውስ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ሼር በማድረግ ወንጌን ያዳርሱ!!

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 17/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

25 Nov, 08:22

#ኪዳነ_ምህረት_ማለት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

🔵👉 እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

🔴👉 ስሟን ለሚጠሩ፣በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል
ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።" ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

🔴👉 በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለን።

የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት ፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 16/2017 ዓ.ም

25 Nov, 03:40

https://youtu.be/gt0cfy_hsZw?si=H9KT58gYPD73ewlX

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

24 Nov, 15:00

https://youtu.be/zb29CpnnP78?si=hRPcJcmMp3U26cHW

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

24 Nov, 10:30

3ኛ ዙር 🔷👉 ሳታነቡ አትለፉ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩትን እቤታቸው ድረስ በመሔድ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን አድርገናል ነዳያንንም አንድ ቦታ ሰብስበን መግበናል። አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደግሞ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናለ ! ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል። በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ። አሁንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የልደት በዓል (የገና በዓል) ምክንያት በማድረግ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ይላልና ቃሉ በየ ሆስፒታሉ በህመም ምክንያት ከሚሰቃዩ እህት ወንድሞች ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል ! ወገኖቼ ስንቱ ወየ ሆስፒታሉ ጤና አጥቶ መታከሚያም አጥቶ የሚሰቃይ አለ ።

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የታመሙ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል ! ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ150 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇
1000614809683 ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የተራቡ ማብላት
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የታሰሩ መጠየቅ

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 15/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

23 Nov, 16:57

ፆመ ነቢያትን እኛ ለምን እንፆማለን ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ነቢያት ጌታ "ይወርዳል ይወለዳል" ብለው የተናገሩት ትንቢት እንዲፈጸም ተመኝተው ጾሙ ጸለዩ:: እኛ ስለምን እንጾማለን? ክርስቶስ ተወልዶ ፣ ተጠምቆ ፣ አስተምሮ ፣ ተሰቅሎ ፣ ሞቶ ፣ ተነሥቶ ፣ ዐርጎ ፣ በአባቱ ቀኝ አይደለምን? አሁን ለምን እንጾማለን? ብለን እናስባለን::

🔷👉 ጌታ በእኔና አንተ ልብ ውስጥ እውነት ተወልዶአልን? እውነት የእኛ ልብ እንደ ቤተልሔም ግርግም ለክርስቶስ ማደሪያ ሆኖአል? ማደሪያ አሳጥተን ከእናቱ ጋር አልመለስነውም?

🔴👉 የጥምቀቱ ትሕትና በእኛ ልብ መቼ ደረሰ? የስቅለቱ ሕማም መች በእኛ ሕሊና ተጻፈ? የትንሣኤው ተስፋ የዕርገቱ ልዕልና በእኛ ልቡና መቼ ዐረፈ?

🔷👉 ስለዚህ ነቢያት "ውረድ ተወለድ" ብለው የጾሙትን ጾም እንጾማለን:: ጌታ ሆይ በእኔ ሕይወትም ውስጥ ውረድ ተወለድ የእኔን ሰውነት ማደሪያህ አድርገው:: ሕዋሳቶቼ ከኃጢአት አርፈው እንደ ቤተልሔም ግርግም ማደሪያህ ይሁኑ::

🔴👉 የቤተልሔም እንስሳት ትንፋሽ ገበሩልህ ፣ የቢታንያ ድንጋዮች ዘማሪ ቢጠፋ ሊዘምሩ ዝግጁ ነበሩ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ለክብርህ ተቀደደ ፣ ጨረቃ ላንተ ደም ለበሰች ፣ ፀሐይ ስላንተ ጨለመች ፣ ከዋክብት ለስምህ ረገፉ ፣ ዓለቶች ለፍቅርህ ተሰነጠቁ::

🔷👉 ከቤተልሔም እንስሳት ፣ ከቢታንያ ድንጋዮች ፣ ከቤተ መቅደስ መጋረጃ እኔ እንዴት አንሼ ልገኝ? የቢታንያ ድንጋይ ያወቀህን ያህል ሳላውቅህ ፣ የቤተ መቅደስ መጋረጃ የተረዳህን ያህል ሳልረዳህ እንዴት ልኑር?

🔴👉 ዓለት ላንተ ሲሰነጠቅ የኔ ልብ ለምን ከዓለት ደነደነ? ጨረቃ ደም ስታለቅስ እኔ መከራህ ለምን አልተሰማኝም?
ሙታን በሞትህ ሲነሡ እኔ ምነው ከኃጢአት ሞት መነሣት ተሳነኝ?

ለዚህ ነው በእኔ ሕይወት ገና አልተወለድክም የምለው

🔷👉 ስለዚህ ጌታ ሆይ የነቢያትህን ጾም ጸሎት ሰምተህ የወረድህ የተወለድህ ጌታ ሆይ በእኔም ሕይወት ውረድ ተወለድና እኔም ከመላእክት ጋር አብሬ ልዘምር ፣ ከሰብአ ሰገል ጋር ሥጦታህን ልቁጠር ፣ ከእረኞች ጋራ ልደነቅ:: ልደትህ ሳይገባኝ ምጽዓትህ እንዳይደርስብኝ እርዳኝ::

በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ የተጻፈ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 14/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Nov, 17:29

#ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል??
#ለምንስ_እንፆማለን?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

🔴👉 የዘንድሮ የ2017 ዓ.ም ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም እሁድ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 ይፈታል።

🔷👉 ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

🔶👉 ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

🔴👉 ስለዚህ የፆመ ነብያት ቅበላ እስከ ህዳር 14 ቀን ድረስ ነው። ብዙ ሰዎች የቅበላን ስርዓት የሚያከናውኑበት መንገድ ፍፁም ስህተት ነው። ለመሆኑ ቅበላ ምንድን ነው የቅበላ ስርዓቱስ እንዴት ነው የሚለውን በአጭሩ እንመልከት !

🔴👉 ቅበላ ማለት በእንግድነት ለሚመጣው እንግዳ ለእንግዳው የሚመጥነውን ያህል ክብር ለመስጠት አዘጋጅቶና ተዘጋጅቶ መቀበል ነው::

🔵👉 ቅበላው መንፈሳዊ ከሆነ በመንፈሳዊ ሕይወት ጸድቶ መዘጋጀት ነው:: መጪው ጾም ከሆነ ለዚህ እንግዳ ንስሐ መግባትን በመጾም በመስገድ በጾሙ ወቅት ለሚፈጸሙ ሥርዓቶች ራስን አዘጋጅቶ መቀበል ነው:: በዚህም ምክንያት ቅበላን በመብል በመጠጥ ሳይሆን ጾምን ሯሷን ጹመው ቅበላ ያደርጉባታል አበው::

🔴👉 ምክንያቱም በጉጉት የሚጠብቋት የሚጠቀሙባት በዓመት የሚናፍቋትን የጾም እንግዳ ሊቀበሉ ነውና! እንግዳ ሲመጣ እንደ እንግዳው ክብር መዘጋጀት ይገባልና:: እኛ ልጆቻቸው ዛሬ እንደሚታየው እንደነርሱ ባንሆን እንኳ እነርሱ የሰሩትን ሥራ ሠርተን ልንመስላቸው ይገባናል እንጂ መጠጥ ቤቱን ጭፈራ ቤቱን የዝሙት መንደሩን ልናጨናንቅ አይገባም::

🔵👉 መፅሐፍ ከእንደዚህ ካለ ግብርም መንደርም ራቁ ተለዩ ነው የሚለው። ቅበላ ምግብን በመበቀል አልነበረም አይደለምም:: በጾም እንደ አበው ነው::
መንፈሳዊ ዝግጅትን በማድረግ ነገር ግን ለክርስቲያኖች በማይገባ በመብል በመጠጥ በዝሙት በጭፈራ በዳንኪራ ጾምን መቀበል ነውር ነው:: ኽረ ኃጢአትም ነው።

🔵👉 አንድ መንፈሳዊ ሰው ክርስቶስን ነው የተሸከመው በክርስቶስ ነውና ክርስትናን ያገኘው እና ክርስቲያን መሆን አለበት:: አንድ ክርስቲያን እኔ ክርስቲያን ነኝ እኔ በክርስቶስ ክርስቲያን ነኝ የሚለው በክርስትናው ሲመላለስ ነው። ክርስትና ደግሞ በፍቅር ሕግ ተገዝቶ በሥርዓት መኖር ነው። ሁሉ ተፈቅዶልናል ነገር ግን ሁሉ አይጠቅመንም እንደተባለ።

🔴👉 አብዝቶ መብላትና መጠጣትን በማንኛውም ቀን ቢሆን ለክርስቲያን በዚህ ግብር መታደም መታየትም ማሰብም አይገባም:: በክርስቶስ ደም የከበረን ሰውነት በዝሙት፣ በሥካር፣ በጭፈራ በእንደዚህ ያሉ ግብር ማቆሸሽ የአሕዛብ ሥራ ነው ለክርሲቲያን ግን ተገቢ አይደለም::

👉 ክርስቲያኖች ቅበላቸው በየደብሩና በየገዳሙም ሱባኤ በማሰብ ንስሐ በመግባት የበደልነውን በመካስ የቀማውን በመመለስ በፊት ከሚበላው ከሚጠጣው ቀንሶ በመጥን ብቻ ሳይሆን በዓይነትም ቀንሶ ለመጪው ጾም ይዘጋጃል ትክክለኛው የቅበላ ስርዓት ይህ ነውና ይህንን እንድናደርግ ይርዳን።

🔴👉 ይህ ፆም ፆመ ነብያት ፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።

🔷👉 #ፆመ_ድህነት
የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።

🔷👉 #ፆመ_ማርያም
የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

🔷👉 #ፆመ_አዳም
የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡

🔷👉 #ፆመ_ፊሊጶስ
የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

🔷👉 #ፆመ_ስብከት
የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡

ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Nov, 06:02

#ኅዳር_13 #አእላፍ_መላእክት (፺፱ኙ ነገደ መላእክት)
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,

🔴👉 ኅዳር ዐሥራ ሦስት በዚህች ቀን የአእላፍ መላእክትን የበዓላቸውን መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙን ። እሊህም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን የሆኑ ለዓለሙ ሁሉ የሚማልዱ ናቸው ።

🔷👉 ኄኖክም ስለእርሳቸው እንዲህ አለ በሰማይ እያለሁ ነፋሳት በደመና ውስጥ አወጡኝ በእሳት ላንቃም ወደታነፀ ቤት አደረሱኝ በዚያም አእላፋት መላእክትን አየሁ እነርሱም በእሳት ላቦት ላይ የቆሙ ልብሳቸውም እንደ በረድ ነጭ ነው አለ።

🔴👉 ያዕቆብም እንዲህ አለ ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላልን አየሁ የእግዚአብሔርም መላእክት በውስጥዋ ይወጡ ይወርዱ ነበር። ሁለተኛም ከሶርያ መመለሻው በሆነ ጊዜ የመላእክት ሠራዊትን አየሁ አለ ።

🔷👉 ሙሴም እንዲህ አለ እግዚአብሔር አሕዛብን በቦታ እንደለያቸው የአዳምን ልጆች እንደበተናቸው እግዚአብሔርን በሚያገለግሉ መላእክት ቁጥር የአሕዛብን አውራጃዎች እንደ ወሰናቸው ። ሁለተኛም እግዚአብሔር ከሲና ተራራ መጥቶ በሴይር ታየኝ ረቂቃን መላእክቶቹም ከእርሱ ጋር ነበሩ አለ ።

🔴👉 ዳዊትም እንዲህ አለ መላእክቱን መንፈስ አገልጋዮቹንም የእሳት ነበልባል የሚያደርግ እርሱ ነው ። ሁለተኛም የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሽህ ናቸው አለ ። ኤልሳዕም የእሳት ሠረገሎችና የእሳት ፈረሶች በዙሪያው ቁመው ሲጠብቁት አየ ።

🔷👉 ዳንኤልም እንዲህ አለ ዙፋኖችን እስቲዘረጉለት ድረስ ደርሶ አየሁ ብሉየ መዋዕል እግዚአብሔር በላያቸው ተቀመጠ ልብሱም እንደ በረድ ነጭ ነው የራሱም ጠጉር እንደ ብዝት ነጭ ነው ዙፋኑም የሚነድ እሳት ነው ሠረገላውም የሚንቦገቦግ ፍም ነው ። የእሳትም ጐርፍ በፊቱ ይፈሳል የብዙ ብዙ የሆኑ መላእክትም ያገለግሉታል የእልፍ እልፍ መላእክትም በፊቱ ይቆማሉ በአደባባይም ተቀምጦ መጻሕፍትን ገለጠ ።

🔴👉 ሉቃስም እንዲህ አለ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ ሠራዊት መጡ እግዚአብሔርንም ሲያመሰግኑ በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በምድርም ሰላም ለሰው ልጅ በጎ ፈቃድ እያሉ ።

🔷👉 ማቴዎስም እነሆ መላእክትም ሊአገለግሉት መጡ አለ ። ሁለተኛም የሰው ልጅ ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በጌትነቱ በሚመጣበት ጊዜ ያን ጊዜ በጌትነቱ ዙፋን ላይ ይቀመጣል ። ዮሐንስም ጌታችን ከተናገረው ቃል እንዲህ አለ እውነት እውነት እላችኋለሁ ከእንግዲህ ወዲህ ሰማዮች ሲከፈቱ የእግዚአብሔርም መላእክት ወደ ሰው ልጅ ሲወርዱና ሲወጡ ታያላችሁ አላቸው የሚል ነው ።

🔴👉 ሐዋርያው ይሁዳም እነሆ እግዚአብሔር ይፈርድ ዘንድ አእላፋት የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን አስከትሎ ይመጣል አለ። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም የመዓርጋቸውን ደረጃ ወይም አይነት እንዲህ ብለው ተናገሩ መላእክት አጋዕዝት ሥልጣናት ኃይላት መናብርት መኳንንት ሊቃናት አርባብ ኪሩቤል ሱራፌል ብለው ተናገሩ።

ምንጭ :- ስንክሳር ዘወርኃ ህዳር

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 13/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Nov, 19:27

https://youtu.be/u0cepeN49m8?feature=shared

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Nov, 06:25

https://www.youtube.com/live/ldyiV3dhJZA?si=mnAfOH6zLccx3zNu

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Nov, 16:24

#ህዳር_12 #ቅዱስ_ሚካኤል
🔷 #ለምን_ይከበራል??🔷
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር 12 የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል አመታዊ ክብረ በዓላት ከሚከበሩበት ቀናቶች ውስጥ አንዱ ሲሆን በዚህ ዕለት ለምን እንደምናከብር እና በዕለቱ ምን ምን የተደረገበት ዕለት እንደሆነ በአጭሩ እንመለከታለን።

1 👉 በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል

🔷👉 ህዳር 12 በዚህ እለት መላእኩ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው በአራተኛይቷ ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው፡፡

🔴👉 እግዚአብሔር ሳጥናኤልን በትዕቢቱ ምክንያት ከሥልጣኑ ገፍፎ ወደ ምድር ሲጥለው ቅዱስ ሚካኤል በእርሱ ቦታ በዐሥሩ ከተማ በመቶውም ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ ተሹሟል፡፡ (ይህንም አክሲማሮስ በሚባለው የቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ላይ ሰፍሮ አናገኛለን፡፡)

2 👉 ቅዱስ ዱራታዎስ ቴዋብለት(ቴውብስታ) ቤት የተገለጠበት እና ቤታቸውን የባረከበት ዕለት ነው።

🔷👉 የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ፡፡ የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው፡፡ እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር፡፡ ከዚህምወ በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ፡፡ በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ፡፡ ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ፡፡

🔴👉 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው፡፡ መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው፡፡ ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ፡፡

🔷👉 ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ፡፡ የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ፡፡

🔷👉 ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው፡፡ ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ፡፡ በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል፡፡›› ብሎ ባርኳቸው ከእንርሱ ተሰወረ።

3 👉 የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በባህር ሲጓዙ የተጨነቁትን የተራዳበት ዕለት ነው።

🔴👉 በአንድ ዘመን ብዙ ሰዎች ከግብፅ አውራጃ መጥተው ወደ ባሕር ማዶ ሄዱ፡፡ ከባሕሩም በደረሱ ጊዜ በመርከብ ላይ ተሳፍረው ከየብሱ ጥቂት በራቁና ወደ ባሕሩ መካከል በደረሱ ጊዜ ጽኑ ነፋስ ተነሳባቸው ለመስጠም እስኪ ደርሱ ድረስ፡፡
የማዕበሉ ሞገድ እየጨመረ እየጸና ከፍ አለ፡፡ ታላቅም ማዕበል መጥቶ ሊገለብጣቸው ደረሰ፡፡ ፍጹም ጥፋትና ክፉ ሞት እንደ መጣባቸው ባዩ ጊዜ ጽኑ ሐዘን ያዛቸው፡፡ የሚያድናቸው የሚያጽናናቸው አጥተው ተስፋ ቆረጡ፡፡ ያን ጊዜ እንዲህ ብለው ጮኹ፡፡ ‹‹የመላእክት አለቃቸው ግሩም ገናና የምትሆን ሚካኤል ሆይ የተአምራትና የይቅርታ መልአክ ነህና፡፡ ልዑል ቸርነቱን የሚገልጥብህ መልአክ ሆይ! እግዚአብሔር ፍቅሩን የሚያስታውቅብህ መልአክ ሆይ ወደኛ ተመልከት እርዳን፡፡ የተጨነቅን እኛን አድነን፡፡ ከመጣብን ሞትና ጥፋት እንድን ዘንድ ስለኛ ወደ ፈጣሪህ ወደ ፈጣሪያችን ወደ እግዚአብሔር ለምንልን፡፡ አሁን የሞት መጋረጃ ዓይናችንን ሸፍኖታልና፡፡ ፍጹም የጥፋት ጥላንም አይተናታልና›› ብለው በፍጹም ልቦናቸው ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፡፡

🔷👉 በመርከብ ውስጥ ያሉት ሁሉ ጽኑ ለቅሶ እያለቀሱ መራራ እንባ እያፈሰሱ ጮኹ፡፡ ከባሕር ጽኑ ማዕበል ከሞት ያድናቸው ዘንድ ያን ጊዜ በዚያች ሰዓት እግዚአብሔር የልቦናቸውን ሐዘንና ልመናቸውን ሰማቸው፡፡ ያን ጊዜም ይገዳቸው ዘንድ ቸር መልአኩን ሚካኤልን ላከላቸው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወረደ መርከቡን በእጁ ይዞ ሳበው፡፡ በመርከቡ ውስጥ ያሉትንም ወደ የብስ አወጣቸው፡፡ በደኅናቸው ተሻገሩ፤ ክፉ ነገር ጥቂትስ ስንኳ ፈጽሞ አላገኛቸውም፡፡

4 👉 እስራኤልን ከግብፅ እየመራ ወደ ሀገራቸው ያስገባበት ዕለት የሚታሰብበት እለት ነው

🔴👉 ከባርነት ቤት ከግብፅ የወጡትን ሕዝብ እግዚአብሔርን ቀኑን በደመና ዓምድ ሌሊቱን ደግሞ በብርሃን ዓምድ መርቷቸዋል እስራኤል ዘሥጋን በመንገዳቸው ሁሉ የጠበቃቸው መና ከሰማይ ያወረደላቸው ተአምራትን ያደረገላቸው ማርና ወተት ወደምታፈስሰው ርስታቸው የመራቸው በደመና መጋረጃ የጋረዳቸውበክንፎቹም የሸፈናቸው መጋቤ ብሉይ የተባለ ቅዱስ ሚካኤል ነው።

🔷👉 ስለዚህም እኛ የተዋህዶ ልጆች ህዳር 12 ቀን በየዓመቱ በማኅሌት እና በቅዳሴ የምናከብረው በዓለ ሹመቱን በማሰብ ቴዎብስታ ዱራታዎስ ያደረገው ታምረ እና በባህር የተጨነቁትን ያዳነበትን እና ሌሎችም በቀኑ የተደረጉትን ለመዘከርና ለማሰብ ነው። በተጨማሪም ከገናናው መልዓክ ከቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከቱን ለማግኘት ነው።

የሊቀ መላዕክት የቅዱስ ሚካኤል ምልጃና ፀሎት ከሁላችን ጋር ይሁን በዓሉም የሠላም የፍቅር ያድርግልን። አሜን

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Nov, 11:38

https://youtu.be/dx-UE7Ddmgs?si=mygwDRHTs2FrKoU_

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Nov, 10:17

#ታላቅ_የንግስ_ክብረ_በዓል_ጥሪ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ታላቁ እና ጥንታዊው የወልመራ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ነው ፡፡

🔷👉 ይህን መልዕክት ያነበባችሁ ሁላችሁም ሼር በማድረግ ጐደኞቻችሁን ጋብዛችሁ መጥታችሁ ነገ ማለትም ህዳር 12 የቅዱስ ሚካኤልን ዓመታዊ ክብረ በዓል በወልመራ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እንድታከብሩና ከታላቁ መልአክ ከቅዱስ ሚካኤል በረከትን ትቀበሉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ።

🔴👉 እኛም ቤተ ክርስቲያኗ ባቀረበችልን ጥሪ መሠረት በቦታው ተገኝተን መምጣት ለማትችሉ በዩትዩብ ክብረ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

🔶ህዳር 12 እንገናኝ ባላችሁበት ሁሉ አምላከ ቅዱስ ሚካኤለ ይጠብቃችሁ አሜን።🔶

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 11 /2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Nov, 19:15

#ህዳር"11" #ቅድስት_ሐና
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የዕረፍቷ መታሰቢያ ነው።

🔷👉 ይችም ቅድስት ከኢየሩሳሌም አገር ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ትውልድ የሌዊ የሜልኪ ልጅ ለሆነ ለማጣት ልጁ ናት። ለማጣትም ሦስት ሴቶች ልጆች አሉት የታላቂቱም ስሟ ማርያም ናት ሁለተኛዋም ስሟ ሶፍያ ሦስተኛዪቱም ስሟ ሐና ናት ታላቂቱ ማርያምም ለባል ተድራ አዋላጅ የሆነች ሰሎሜን ወለደቻት እርሷም መድኃኒታችንን ከወለደችበት ጊዜ ጀምሮ በስደቷም ወራት ከአረጋዊ ዮሴፍ ጋር እመቤታችንን ድንግል ማርያምን ያገለገለቻት ናት።

🔴👉 ሶፍያም ለባል ተድራ ለመጥመቁ ዮሐንስ እናቱ የሆነች ቅድስት ኤልሳቤጥን ወለደቻት። ይችንም ቅድስት ሐናን ከይሁዳ ነገድ ለሆነ ጻድቅ ስሙ ኢያቄም ለሚባል አጋቧትና እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን ወለደቻት እሊህም ሰሎሜና ኤልሳቤጥ ለቅድስት ሐና የእኅትማማች ልጆች ናቸው።

🔷👉 የዚችንም የቅድስት ሐናን በሥውር የምትሠራውን ገድሏንና ትሩፋቷን እንዳናስታውሰው አናውቀውም ግን ከሴቶች ሁሉ እንደምትበልጥና እንደምትከብር እናውቃለን እንረዳለን እርሷ አምላክን በሥጋ ለወለደችው ወላጅዋ ትሆን ዘንድ የተገባት ሁናለችና ከሴቶች ሁሉ የሚበልጥና የሚበዛ ትሩፋትና ተጋድሎ ባይኖራት ይህ ታላቅ ጸጋ ባልተገባት ነበር።

🔴👉 ይህችም ጻድቅት ሐና መካን በመሆንዋ ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር በጸሎት ትማልድ ነበር እግዚአብሔርም በእርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተደረገባትን ይቺን የተባረከችና የከበረች ልጅን ሰጣት እርሷም አምላክን የወለደች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት።

🔷👉 ስለዚህም ይህን ታላቅ ጸጋ ስለሰጣት የበዓሏን መታሰቢያ በደስታ ልናከብር ይገባናል። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን በጸሎቷ የሚገኝ በረከቷም ከእኛ ጋር ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

ምንጭ :- ስንክሳር ዘወርኃ ህዳር

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 11/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Nov, 14:05

ህዳር 12 የቅዱስ ሚካኤልን ዓመታዊ ክብረ በዓል
🔷👉 በወልመራ ደብረ መዊ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ን
🔴አይቀርም

በዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 10/2017 ዓ.ም
ሆለታ

🔴ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉ!

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

18 Nov, 19:24

https://youtu.be/O0suJbrr9mI?si=PoqiqCd7J4KY96e-

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

17 Nov, 03:50

#ጻድቁ_አባታችን_አባ_ኪሮስ
................................................................
🔴👉 አባታቸው ንጉሥ ዮናስ
እናታቸው አንስራ ይባላሉ።

🔷👉 የቀደመ ስማቸው ዲላሶር የተሰኘ ሲሆን
ሁለተኛ ስማቸው ደግሞ ❖ #ኪሮስ ❖

🔴👉 በታህሳስ 8 ቀን ተወልደዋል
በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ከወንድማቸው ጋር በመካፈል ወደ አባ በብኑዳ ገዳም ገብተዋል።

👉 እስከ 17 ዓመታቸው ረድዕ ሆነው እያገለገሉ ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩ፤ ከተረዱ በኋላ የምንኩስናን ማዕረግ ተቀብለዋል።

🔵👉 ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲሁም ስለ ሰው ልጆች ይቅርታ 40 ዓመት በመሬት ላይ ተኝተው ስጋቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ ሣር እስኪበቅልባቸው ድረስ ጸልየዋል።

🔵👉 ጌታችንም ስለ መታመናቸው እና ስለ ተጋድሏቸው አክብሯቸዋል ።

👉 ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡

🔷👉 በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ ሐምሌ 8 አርፈዋል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ ምልጃና በረከታቸው አይለየን

በዕለተ ቀናቸው ይህንን የበረከት ስራ ተሳተፉ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩትን እቤታቸው ድረስ በመሔድ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን አድርገናል ነዳያንንም አንድ ቦታ ሰብስበን መግበናል። አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደግሞ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናለ ! ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል። በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ። አሁንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የልደት በዓል (የገና በዓል) ምክንያት በማድረግ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ይላልና ቃሉ በየ ሆስፒታሉ በህመም ምክንያት ከሚሰቃዩ እህት ወንድሞች ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል ! ወገኖቼ ስንቱ ወየ ሆስፒታሉ ጤና አጥቶ መታከሚያም አጥቶ የሚሰቃይ አለ ።

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የታመሙ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል ! ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ60 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇
1000614809683 ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የተራቡ ማብላት
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የታሰሩ መጠየቅ

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 8/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

17 Nov, 03:50

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

16 Nov, 18:39

#ህዳር_8 #አርባዕቱ_እንስሳ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ህዳር ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣

🔵👉 እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

🔶👉 የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

🔷👉 የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

🔴👉 ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

🔵👉 የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

👉 ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

🔵👉 በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

🔴👉 እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

🔷👉 ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

🔷👉 ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

🔵👉 በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

🔴👉 ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው።

🔷👉 ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

🔵👉 ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።

መንፈሳውያን አመስጋኞችና መዘምራን የምትሆኑ አራቱ እንስሳት ስለ አኛ ለምኑ

አርባዕቱ እንስሳ መንፈሳውያን ሰባሕያን ወመዘምራን ሰዐሉ በእንቲአነ
( አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመጽሐፈ ሰዓታት )

🔷👉 ቅዱስ ጄሮም እንዲህ አለ ፦
አርባዕቱ እንስሳት የድኅነታችን ምሥጢር የሆኑትን አራት ደረጀዋች ያስረዳሉ ።

🔷👉ገጸ ሰብእ ፦ ሥጋዌውን ( ቃል ስጋ መሆኑን )
🔷ገጸ አንበሳ ፦ ትንሣኤውን
🔷ገጸ ላህም ፦ ንጹሕ መሥዋዕት ( ቤዛ ) መሆኑን
🔷ገጸ ንሥር ፦ ዕርገቱን

🔴የእግዚአብሔርን ባሕርያት ያመለክታሉ።
ገጸ ሰብእ ፦ ጥበቡንና ዕውቀቱን
ገጸ አንበሳ ፦ ግርማውንና ኃይሉን
ገጸ ላህም ፦ ትዕግስቱን ፈታሒነቱን
ገጸ ንሥር ፦ ክብሩን ልዕልናውን

🔴አንድም አርባዕቱ እንስሳት
በአራቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ።

🔵#አርባዕቱ_እንስሳት #በእመቤታችን_ድንግል_ማርያም_ይመሰላሉ። እነሱ መንበሩን ለመሸከም እንደተመረጡ ፤ ሰማይና ምድር የማይችሉትን አምላክ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ ተሸክማዋለችና ።

፨፨፨ #ወስብሐት_ለእግዚአብሔር ፨፨፨
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 8/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

16 Nov, 10:37

https://youtu.be/N0PPumQm8cc?si=EJ3ze7D3-5eAZgA6

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

16 Nov, 04:22

#ሚስጥረ_ስላሴ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴.1 ማን ፈጠረን?
መልስ 👉 ቅድስት ስላሴ።

🔵.2 ስላሴ ስንት ናቸዉ?
መልስ 👉 አንድም ሶስትም ናቸዉ።

🔴.3 ሶስትነታቸዉ በምን በምን ነዉ?
መልስ 👉 በስም በአካል በግብር።

🔴.4 አንድነታቸዉስ በምንድነዉ?
መልስ 👉 በባህሪይ በህልዉና በመለኮት በፈቃድ ሰዉን በመፍጠር አለምን በማሳለፍ በዘለአለማዊ ስልጣን!

🔵.5 የስም ሶስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ 👉 አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ።

🔴.6 የአካል ሶስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ
👉ለአብ ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ!
👉ለወልድም ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ!
👉ለመንፈስ ቅዱስም ፍፁም ገፅ ፍፁም አካል ፍፁም ሰዉነት አለዉ።

🔵.7 የግብር ሶስትነታቸዉ እንዴት ነዉ?
መልስ 👉 አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራፂ ነዉ።

🔴.8 አብ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መልስ 👉 አባት።

🔵.9 ወልድ ማለት ምን ማለት ነዉ?
መልስ 👉 ልጅ።

🔴.10 መንፈስ ቅዱስ ማለትስ?
መልስ 👉 ሰራፂ
🔵.11 ከማን የሰረፀ?

መልስ 👉 አብን አክሎ ወልድን መስሎ ከአብ የተገኘ ወይም የሰረፀ።

ሚስጥረ_ስላሴ አይመረመርም ጥልቅና ሰፊ ነዉ ከረጅሙ በአጭሩ ከብዙ በጥቂቱ ከመለኮታዊ ስፋቱ የገለፀልን የአቦቶቻችን አምላክ ልኡል እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን አሜን

🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
ሼር አድርጉ !

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 7/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia1

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

15 Nov, 05:43

ኑ የጀመርነውን እንፈፅም
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 ታላቅ መንፈሳዊ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር የመናገሻ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ዓመታት ሲያስገነባ የነበረውን ህንፃ ቤተ ክርስቲያን ከፍፃሜ ለማድረስ "የጀመርነውን እንፈፅም" በሚል መሪ ቃል በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ የፊታችን ህዳር 8 ከቀኑ 7 ሰዓት ጀምሮ ልዩ ጉባኤ አዘጋጅቷል።

🔴👉 በመሆኑም እናንተም ላልሰሙት በማሰማት በዕለቱ በቦታው በመገኘት የበኩላችሁን በመወጣት የበረከቱ ተካፋይ ትሆኑ ዘንድ ህንፃ ቤተ ክርስቲያኗንም ከፍፃሜ እናደርስ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።

🔷👉 እኛም ቤተ ክርስቲያኗ ባቀረበችልን ጥሪ መሠረት በዕለቱ በቦታው በመገኘት በአካል መገኘት ለማትችሉ ባላችሁበት ሆናችሁ መርሃ ግብሩን ትከታተሉና የበረከት ስራው ላይ ትሳተፉ ዘንድ በYoutube እና በ facebook በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

🔷👉 የደብሩ አካውንት :- 1000033842434 ንግድ ባንክ

ለሁሉም እንዲደርስ ሼር አድርጉ አይከፈልበትም

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 6/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

15 Nov, 04:13

#ህዳር 6
#ደብረ_ቁስቋም_ለምን_ይከበራል ?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉በከበረች በኅዳር ስድስት ቀን የሚታሰበው በዓለ ደብረ ቁስቋም በመላው ዓለም በሚገኙ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ይከበራል። ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡

🔵👉 ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡

🔷👉 ‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡

👉 የዚህ በዓል መሠረታዊ መታሰቢያው እንደሚታወቀውና መጽሐፈ ስንክሳር ላይም ተመዝግቦ እንደምናገኘው ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብርት እናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም፣ ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በስደት ከነበሩበት ከግብጽ ሀገር ተመልሶ ደብረ ቁስቋም የገባበት ነው፡፡

🔴👉 ከሦስት ዓመትና ከስድስት የስደት ወራት በኋላ አሳዳጃቸው ኄሮድስ በመሞቱ መልአኩ ለዮሴፍ በነገረው መሠረት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ በደብረ ቁስቋም ተራራ ላይ ዐርፈዋል።

🔷👉 ጌታችንም ካረገ ከዘመናት በኋላ ደግሞ በኅዳር ስድስት ቀን በዚህ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰብስቧቸዋል፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል፡፡

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን፤ አሜን

ምንጭ፤ መጽሐፈ ስንክሳር ዘወርኃ ኅዳር

🙏ሼር አድርጉ አይከፈልበትም🙏

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 6/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Nov, 15:26

https://youtu.be/sFjsT0UPr3E?si=VpdJx_jmzhrp4LHn

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Nov, 04:07

#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ አባታችን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ::

🔷👉 እነርሱም ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: ታዲያ አንድ ቀን አቅሌያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን #ንስኢ_ወልደ_ዘይትሌአል_ቀርኑ_እምኑኀ_ሰማይ " ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ የሚል ድምጽ ሰማች ::

በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ

🔴👉 ፃዲቁ አባታችን አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው " ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን " ብለው በማመስገናቸውና ኋላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ ።

🔵👉 ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ምኔት ወስዶ ከበሩ አኖራቸው :: አበመኔቱም አባ ዘመደ ብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ #ፍሱሐ_ገጽ ሆነ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአርገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

🔷👉 በገድለህ በትሩፋትህ ከሞት ነፍስ ከርደተ ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? #ዘኬድከ_ጸበለ_እግረከ_ይልህሱ_ወበ_ውእቱ_ይጽግቡ ።" የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::

🔵👉 ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር ።

🔷👉 ከዚህ በኋላ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ " ወበህየኒ ሐልውከ ነፍሳተ ወታወጽኦሙ" ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ #ምድረ_ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ #ዝቋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጽልዩ ነበር ::

🔴👉 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ #ዘገብረ_ተዝካርከ_ወዘጸውአ_ስመከ_እምህር_ለከ " ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ ከአልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ " #ተንስእ_ወጻእ_መሀርኩ_ለከ_ኵሎ_ኢትዮጵያ ምሬልሀለው ውጣ ብሏቸው ወጥተዋል ::

👉 ከዚህ በኋላ #ምድረ_ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7አመት እንደ ትክል አምድ ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ሳይከድኑ ቆመው ጸልየዋል :: ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አድነዋቸዋል ::

🔴👉 ለ100 ዓመት ሕዝበ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው በዝቋላ ተራራ በሚገኘው ሐይቅ ተዘቅዝቀው ለምነው የምሕረት ቃልኪዳንን የተቀበሉበት እንዲሁም እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 5/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

13 Nov, 15:05

https://youtu.be/-FNVZszpiBM?si=z8u-o2X8SmwUqScr

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

12 Nov, 07:26

https://youtu.be/w3d0X-TPgsI?si=i6qQnnVPp2sWjHnP

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

12 Nov, 04:19

በዓታ ለማርያም

🔴👉 ድንግል ሆይ ቅዱሳን መላእክት በሰማይ ካለው ሰፊ መቅደስ ይልቅ በምድር ያለሽውን ጠባቧን መቅደስ አንችን ማየት ወደዱ፤ የማደሪያቸው ማደሪያ፣ የመቅደሳቸው መቅደስ ኾነሻልና።

🔷👉 በሰማይ ያሉ ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ይልቅ ምድር የቀረባቸው ባንች ነው፤ በሰማይ ከተሸከሙት ቅርብ ዙፋን ይልቅ ርኅቀት ባለው ዙፋን-ማኅጸንሽ ረቂቁ ቃል ገዝፎ አይተውበታል፤ ከሚኖሩበት ሰማይ ይልቅ የምትኖሪበትን ምድር ወደዱ፤ ለረቂቁ ቃል ፊደሉ ኾነሻልና፤ ያነቡሻል፤ ይገልጡሻል፤ እጽብት ይሉሻል።

🔴👉 በሰማይ መቅደሱን የሚያጥኑት ቅዱሳን ሱራፌልና ኪሩቤል የፈጣሪያቸውን ዙፋኑን ተሸከሙ እንጅ ረቂቅ አካሉን በረቂቅ ዐይናቸው አላዩም፤ የአማኑኤል ምድራዊ መቅደሱ ትኾኝ ዘንድ ወደ መቅደስ በገባሽ ጊዜ ግን መላእክት በኹለት ክንፋቸው የጋረዱት ዐይናቸውን ገልጠው ከተፈጠሩ ጀምረው ያላዩትን ኀያል አምላክ በተደሞ በአንክሮ እንዲያዩ ያይናቸው ብርሃን የኾንሽ አንች ነሽ!

🔷👉 "ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር" ብለው አዲስ ዝማሬ እንዲዘምሩ፣ የምስጋና ቃላቸው ምድር ላይ እንዲያርፍ ማመስገኛ መቅደሳቸው አንች ነሽ።

🔴👉 ድንግል ሆይ የእሳት ዙፋኑን በመሸከም የሚቀድሙሽ መላእክት ረቂቅ አካላቸው የሚፈራውን እሳት በቤተ መቅደስ በጸነስሽው ጊዜ እንደምን አላቃጠላትም ብለው መላእክቱ የጮኹትን ቃለ ጽራሕ ቅዱስ ኤፍሬም ላንች ሰጥቶ፣ "ማርያም ድንግል ትጸርሕ በቤተ መቅደስ" ብሎ ተናገረልሽ።

🔴👉 ድንግል ሆይ ዕለት ዕለት ወደ መቅደሱ እየገቡ የሥርየት ደም ይረጩ የነበሩ ካህናት የሲኦልን እሳት የሚያሻግር የገነትን በር የሚከፍት መስዋዕት ሊያቀርቡልን አልቻሉም፤ አንች ግን ወደመቅደስ በገባሽ ጊዜ ለነፍስ ለሥጋችን ቤዛ የኾነ ነባቢ በግዕ የተባለ ክርስቶስን ጸንሰሽልናልና እናመሰግንሻለን፤ እንወድሻለን።

🔷👉 ውኀ ሳያጠጧት ለምልማ አብባ አፍርታ የተገኘች የአሮን በትር አንች ነሽ። ዘኍ 17:1 ያች በትር ቤተ መቅደስ በገባች በዐሥራ ኹለት ሰዓት ያለ ዘር ለምልማ እንዳፈራች፣ ድንግል ማርያምም ቤተ መቅደስ በገባች በዐሥራ ኹለት ዓመት ያለወንድ ዘር አማኑኤልን ጸንሳ ወለደች፤

🔷👉 ያች በትር ለ12 ነገደ እስራኤል ምስክር ልትኾን፣ አማናዊት በትረ ሃይማኖት ድንግል ማርያም ደግሞ ለ12 ሐዋርያት ስብከት የሚኾን ጌታችንን ለመውለድ 12 ዓመት በቤተ መቅደስ ኖረች።

የቃል ኪዳንሽ መቅደስ ወደኾነው ልባችን ትገቢ ዘንድ እንማጸንሻለን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 3/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Nov, 04:07

3ኛ ዙር 🔷👉ሳታነቡ አትለፉ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔵👉 ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው እንዳለ። ሐዋ, 20፥35

🔴👉 ውድ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች መፅሐፍ እንደሚለው ስንቶቻችን ከመቀበል ይልቅ ለመስጠት ዝግጁዎች ነን ? ስንቶቻችንስ በምፅዓት ቀን ለምንጠየቀው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ሳይመሽብን ተዘጋጅተን ይሆን ?

🔵👉 በውኑ በምፅዓት ቀን ምንድን ነው የምንጠየው ትሉኝ ይሆናል እስቲ ከነ ፍርዱ መፅሐፍ የሚለውን እንመልከት 👇👇

🔴👉 ማቴዎስ 25
³⁴ ንጉሡም በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
³⁵ ተርቤ አብልታችሁኛልና፥ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፥ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፥ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፥
³⁶ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።
³⁷ ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ?
³⁸ እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ?
³⁹ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን?
⁴⁰ ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።

🔴👉 ⁴¹ በዚያን ጊዜ በግራው ያሉትን ደግሞ ይላቸዋል፦ እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ።
⁴² ተርቤ አላበላችሁኝምና፥ ተጠምቼ አላጠጣችሁኝምና፥ እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝምና፥
⁴³ ታርዤ አላለበሳችሁኝምና፥ ታምሜ ታስሬም አልጠየቃችሁኝምና።
⁴⁴ እነርሱ ደግሞ ይመልሱና፦ ጌታ ሆይ፥ ተርበህ ወይስ ተጠምተህ ወይስ እንግዳ ሆነህ ወይስ ታርዘህ ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ መቼ አይተን አላገለገልንህም? ይሉታል።
⁴⁵ ያን ጊዜ፦ እውነት እላችኋለሁ፥ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ለአንዱ ስላላደረጋችሁት ለእኔ ደግሞ አላደረጋችሁትም ብሎ ይመልስላቸዋል።
⁴⁶ እነዚያም ወደ ዘላለም ቅጣት፥ ጻድቃን ግን ወደ ዘላለም ሕይወት ይሄዳሉ።

🔴👉 ወዳጆቼ እኛ የትኛውን ይሆን የምንፈልገው ? የአባቴ ብሩካን ኑ የሚለውን ነው ወይስ እናንተ ርጉማን ከኔ ሂዱ የሚለውን ነው ? እርግጠኛ ነኝ ሁላችንም የአባቴ ብሩካን ኑ መባልን መንግስቱን መውረስን ነው የምንፈልገው !

🔵👉 ታዲያ ይህንን እንድንባል የተራበ አብልተን ይሆን የተጠማ አጠጥተን ይሆን የታረዘ አልብሰን ይሆን የታሰረ ጠይቀን ይሆን ? የታመመ ጠይቀን ይሆን ? መቼስ ነው ይህንን የምናደርገው ? ወዳጆቼ መጠሪያችን አይታወቅምና ሳይመሽብን ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንስራ !

🔴👉 እግዚአብሔር ፈቅዶልን ከዚህ በፊት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተቸገሩትን እቤታቸው ድረስ በመሔድ ለበዓሉ የሚያስፈልገውን አድርገናል ነዳያንንም አንድ ቦታ ሰብስበን መግበናል። አንዲስ አመትን ምክንያት በማድረግ ደግሞ ከ700 በላይ የሚሆኑ የታሰሩ ወገኖቻችን ጠይቀናል በዓሉን አብረናቸው አክብረናለ ! ይህ የሆነው ደግሞ እናንተው አነሰ በዛ ሳትሉ ከ100 ብር ጀምሮ በሰጣችሁት ገንዘብ ነው ይህንንም በቪዲዮ ወደ እናንተ አድርሰናል። በዚህም ለነብሳችን የሚበጃትን ስራ እንድሰራ የፈቀደልን አምላክ ስሙ ለዘላለም የተመሰገነ ይሁንልን ። አሁንም እግዚአብሔር ቢፈቅድ ከፊታችን የሚመጣውን የጌታችንን የልደት በዓል (የገና በዓል) ምክንያት በማድረግ ታምሜ አልጠየቃችሁኝም ይላልና ቃሉ በየ ሆስፒታሉ በህመም ምክንያት ከሚሰቃዩ እህት ወንድሞች ጋር ለማሳለፍ ፕሮግራም ይዘናል ! ወገኖቼ ስንቱ ወየ ሆስፒታሉ ጤና አጥቶ መታከሚያም አጥቶ የሚሰቃይ አለ ።

🔵👉ስለዚህ እኛ በዓሉን በቤታችን ሁሉ ሞልቶልን ስናከብር ቃሉ እንደሚለው የታመሙ ወንድም እህቶቻችንም ማሰብ ተገቢ ነውና ሁላችሁም አነሰ በዛ ሳትሉ እዚህ የበረከት ስራ ላይ ልትሳተፉ ያስፈልጋል ! ቢያንስ እዚህ መንፈሳዊ ቻናል ላይ ከ3 ሺ ሰው በላይ አለ ሁሉም መቶ መቶ ብር እንኳን ቢያዋጣ ትልቅ የበረከት ስራ መስራት ይቻላል እናንተ የምትሰጡት መቶ ብር ትልቅ ስራ መስራት ይችላል ስለዚህ ይህንን ያነበባችሁ እዚህ የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ በ 0902829657 በኢም, በዋትስአፕ , በቴሌግራም , አናግሩኝ ! ቃል መግባት የምትችሉም ቃል መግባት ይቻላል !

🔴👉 እንዲሁም ለዚሁ አላማ ተብሎ በሶስት ሰው ስም በተከፈተው ንግድ ባንክ አካውንትም ማስገባት ትችላላችሁ 👇👇
1000614809683 ደሳለኝ እጅጉ & በረከት & ዋሲሁን

በሚጠፋው ገንዘባችን የማይጠፋውን ሰማያዊ ቤታችንን እንስራ

በዚህ ቻናላችን ላይ በአመት ሶስት ቋሚ የነብስ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ።
👉 ለአዲስ ዓመት :- የተራቡ ማብላት
👉 ለገና በዓል :- የታመሙ መጠየቅ
👉 ለፋሲካ በዓል :- የታሰሩ መጠየቅ

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ህዳር 1/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

09 Nov, 06:39

https://www.youtube.com/live/YmV3uJOz9Ps?si=6Q9Mysmb0O29H_4y

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

08 Nov, 16:51

https://youtu.be/1kDE-XzXu8Q?si=CNfd1TC7G-Ct5lTG

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

07 Nov, 15:40

#ታላቅ_የንግስ_ክብረ_በዓል_ጥሪ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ይህ በምስሉ ላይ የምትመለከቱት  ታላቁ እና ጥንታዊው ገዳም የመናገሻው መንበረ መንግስት ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን ነው ፡፡

🔷👉 ይህ ታላቅና እድሜ ጠገብ ቤተክርስቲያን በግብፃዊው ሊቀ ጳጳስ በአቡነ ማቲዎስ 1878 ዓ/ም ተመሰረተ።

🔴👉  እነሆ ይህ የበረከት ቦታ ከከተማው ገባ በማለቱ ምመናን አላወቁትም ስለዚህ ሁላችንም የተዋህዶ ልጆች ይህን ታላቅ ገዳም በምንችለው ሁሉ ሼር በማድረግም ጭምር እንድናስተዋውቅ በትህትና እንጠይቃለን ።

🔷👉 ይህን መልዕክት ያነበባችሁ ሁላችሁም ሼር በማድረግ ጐደኞቻችሁን ጋብዛችሁ መጥታችሁ አሁን የፊታችን ጥቅምት 30 የቅዱስ ማርቆስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ስለሚከበር እናንተም በግሩፕ ወይም በግል መታችሁ ከታላቁ አባት ከቅዱስ ማርቆስ በረከትን ትቀበሉ ዘንድ ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች ። እናም ቤተ ክርስቲያኗ ባቀረበችልን ጥሪ መሠረት በቦታው ተገኝተን በዩትዩብ እና በፌስቡክ ክብረ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል።

🔶ጥቅምት 30 እንገናኝ ባላችሁበት ሁሉ አምላከ ቅዱስ ማርቆስ ይጠብቃችሁ አሜን።🔶

🔴 የደብሩ አካውንት :- 1000466478117 ንግድ ባንክ

       ።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
     ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

       ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
           ጥቅምት 28/2017 ዓ.ም
                    ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

30 Oct, 04:56

#ጥቅምት_20 #ታላቁ_ነቢይ_ኤልሳዕ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ዳግመኛም በዚህች ቀን የስሙ ትርጓሜ ጠባቂና አዳኝ የሆነ የታላቅ ነቢይ የኤልሳዕ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

🔵👉 እርሱም አሜሁላ ከሚባል አገር ከይሳኮር ነገድ ነው ብዙ ትንቢትን ተናግሮአል ብዙ ተአምራትንም አድርጓል። የኢያሪኮም ሰዎች ኤልሳዕን ጌታችን እንደምታያት የዚች አገር ኑሮዋ ያማረ የተወደደ ነው የአገሩ ውኃ ግን ክፉ ነው ሴቶች ሲጠጡት ይመክናሉ አሉት ኤልሳዕም ጨው ጨምራችሁ አዲስ ሸክላ አምጡልኝ አላቸው እነርሱም አመጡለት ።

🔷👉 ኤልሳዕም ወደ ውኃው ምንጭ ሒዶ ያንን ጨው በውስጡ ጨመረውና እግዚአብሔር እንዲህ አለ እርሱን ከመጠጣት የተነሣ የሚሞት እንዳይኖር የሚመክንም እንዳይኖር ይህን ውኃ ለውጥኩት አለ አላቸው ።

🔴👉 ከዚያችም ቀን በኋላ ኤልሳዕ እንደተናገረ እስከ አሁን ድረስ ያ ውኃ ተለወጠ። የዚህ የነቢይ ኤልሳዕ ተአምራቱ ብዙ ነው የሶርያውን ሰው ንዕማንን ከለምጹ ያነጻው እርሱ ነው ሁለት ሙታንን አንዱን በሕይወት ሳለ ሌላውንም ከሞተ በኋላ አስነሥቷል። የትንቢቱንም ወራት ፈጽሞ በሰላም አረፈ።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ጥቅምት)

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

30 Oct, 04:20

https://youtu.be/eN95EJNSods?si=IDiJzQQHD17rcR8f

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

29 Oct, 03:54

ገናናው መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እጅግ አጽናኝና አስደሳች የሆነውን ምሥጢረ ሥጋዌን ዜና ይዘህ ከሰማይ ወደ ምድር እንደወረድክ ድንግል ማርያም የአምላክ እናት ለመሆን ፈቃድዋ ሆኖ በተፈጸመ ጊዜ ደስ እንዳለህ እኛም እግዚአብሔርን በማክበርና ግዴታችንን በመፈጸም ደስ የምንልበትን ጸጋ አሰጠን።

🔵👉 ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሦስቱን ወጣቶች ከሚያቃጥል እሳት እንዳዳንካቸው እኛንም በዚህ ዓለም ከሚወራው ከሚታየውና ከሚሰማው ክፉ ቀንና እለት ሁሉ አድነን እየነደደ የሚለበልበንን የኃጢያት እሳትም አጥፋልን፤ የኑሯችንን ቀጠሮ በክንፈ ረድኤትህ ከልለው ሰይጣን እንዳይሰለጥንብን፣ ክፉ አድራጊዎች፣ ሟርተኞች፣ ሰላቢዎች፣ ዘረኞችና ነፍሰ ገዳዮች እንዳያጠቁን ከልለን።

🔴👉 ያንተን የእሳት አጥር ዘሎ ጠላት ያጠቃን ዘንድ ጠላት አይችልምና ጥበቃ ከእኛ ከባርያዎችህ አይለየን።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛ አገልጋዮችህም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሳት አጥፋልን ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን።

🔴👉 የሰይጠንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን።

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በደል በተገኘብኝ ቁጥር እያለቀስሁ እጠራሃለሁ፤ ጎስቋላ የምሆን በጥቃትና በሀዘን ውስጥ የምገኝ ልጅህ የአንተን ማፅናናትና ረዳትነት ያሻኛልና ፈጥነህ ናልኝ፡፡

🔴👉 ቅድስት ማርያምን ያበሰርክ ለዓለም ሁሉ የምታበር ገብርኤል ሆይ በሰራዊት አምላክ ይዤሃለሁ በዚህች ሰዓት ፀሎቴንና ልመናዬን ስማ፡፡

🔵👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ቀድመህ የደስታ የምሥራች ቃልህን ልታበስር ወደ ገሊላ እንደወረድህ ዛሬም ለአዘንን ለእኛ ከሠማይ ሠረገላ ናልን፡፡

🔴👉 የደስታንም ቃል አሰማን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያበሰርክ ተወዳጁ ቅዱስ ገብርኤል ሆይ በምህረትና በይቅርታ ወደ እኛ ናልን ዓለም የጥፋት፣ የሞት፣ የክስረት፣ የውድመትና የተስፋ መቁረጥ ድምፅን ያሰማናልና አንተ ግን ጎስቁልናችንን የሚያነሳ ስብራታችንን የሚጠግን እንባችንን የሚያብስ የብስራት ድምፅህን አሰማን እንድንፅናናም አድርገን፡፡

🔵👉 እውነተኛ ጠባቂያችን ቅዱስ ገብርኤል ሆይ እኛን ለማዳን ሰው የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን፣ ማደሪያው የሆነችው ድንግል ማርያምን በጣም እንወዳታለን፤ በዚህ ዓለም የምሥጢረ ሥጋዌ ተካፋዮች በመሆናችን በመንግስተ ሰማያትም ተካፋዮች ለመሆን ሁላችንንም በምልጃህ አብቃን ለምንልን ለዘላለሙ

🔴👉ለአብ ምስጋና ይገባል፤ ለወልድ ዋህድ ኢየሱስ ክርስቶስ ምስጋና ይገባል፤ ለመንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Oct, 19:15

ጥቅምት 17 | ቅዱስ እስጢፋኖስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ
ጥቅምት 17 ማዕረገ ዲቁናን በሐዋርያት እጅ በአንብሮተ እድ የተሾመበት ዕለት ነው።

🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት፡- እስጢፋኖስ ማለት ‹‹መደብ›› ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ‹‹አክሊል›› ማለት ነው፡፡

🔵👉 ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ ሁለት ወንድ ልጆችንም ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ይህ ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡

🔴👉 እስጢፋኖስም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ7ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡

🔵👉 ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጀመሪያ ከታላቁ የኦሪት ምሑር የእነ ቅዱስ ጳውሎስ መምህር ከነበረው ከገማልያል የኦሪትን ሥርዓት ጠንቅቆ የተማረ ምሑረ ኦሪት ነው፡፡ ትንቢተ ነቢያትን ያውቅና የአዳኙን መሢሕ መምጣት በጸሎትና በተስፋ ሲጠባበቅ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ የጌታችንን መንገድ ሲጠርግ ቢያገኘው ደቀ መዝሙር ሆነና በትጋት ሲያገለግለው ቆየ፡፡

🔴👉 ከ6 ወራት በኃላ ክብር ይግባውና ጌታችን በዮሐንስ እጅ ተጠመ፡፡ ከጌታችንም ጥምቀት በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጌታችን ይመጣ ዘንድ ያለው መሢሕ እርሱ መሆኑን በአንክሮ ጠየቀው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስንም ቅዱስ እስጢፋኖስ ራሱን ጌታችንን አግኝቶት የአንደበቱን ቃል የእጁን ተአምራት አይቶ ይመን በማለት ወደ ጌታችን ዘንድ ላከው፡፡

🔵👉 ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆነ፡፡ እርሱም አስቀድሞ ጌታችን ከዋለበት እየዋለ ካደረበት እያደረ ወንጌልን ተምሯልና ጌታችንም 72ቱን አርድእት ለስብከተ ወንጌል ሲያሰማራቸው ከእነርሱ ውስጥ አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ነበር፡፡ በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስን ከተቀበለ በኃላ ወንጌልን በአዋጅ ይሰብክ ጀመረ፡፡ ከዚህም በኃላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ከጌታችን ዕርገት በሁኃላ ለአንድ ዓመት ያህል ስምንት ሺህ ማኅበርተኞቹን እየመራ ወንጌልን እየሰበከ ክርስትናን አስፋፋ፡፡

🔴👉 የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡ በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› እያለ ስለገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡

🔵👉 ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ ‹‹የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ›› ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ 22፡20፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡

🔴👉 ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና ‹ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና› የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት፡፡›› ሐዋ 6፡8-15፡፡

🔴👉 ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡

🔴👉 መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡

🔵👉 እስጢፋኖስም ‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል› ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም ‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው› ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ የሐዋ 7:52-60፡፡

🔴👉 የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር 1 ቀን ነው፡፡ መእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀብረውታል፡፡ ጥቅምት 17 የተሾመበት በዓሉ ሲሆን መስከረም 15 ቀን ደግሞ ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡

(ምንጭ፡- የመስከረምና የጥቅምት ወር ስንክሳር)

የቀዳሜ ሰማዕት የቅዱስ እስጢፋኖስ ምልጃ ተራዳኢነቱ በረከቱ ሁሉ በሁላችን ላይ ይደርብን

🔷👉አንብበው ጨርሰዋል? እንግዲያውስ ጠቃሚ ነው ብለው ካሰቡ ሼር በማድረግ ወንጌን ያዳርሱ!!

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 17/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Oct, 19:15

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Oct, 14:38

https://youtu.be/W0ogVaVAUag?si=ogowgORtHDmiUfsH

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Oct, 13:39

ማኅሌተ ጽጌ 4ኛ ሳምንት

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

26 Oct, 05:33

#ኪዳነ_ምህረት_ማለት
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃልኪዳን ማለት ነው፡፡ በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው፡፡እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ ክርስቶስ መካነ መቃብር ጎለጎታ እየወረደች ትፀልይ ነበር፡፡ ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ የምህረት ቃል ኪዳን ገባለት ፡፡

🔵👉 እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ፣ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ ቃልኪዳን አደረገ፡፡
« ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ። … » መዝ, 89 : 3 እንዲል መፅሐፉ፡፡

🔴👉 ስሟን ለሚጠሩ፣በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት ቃልኪዳን ሰጥቷታል ፡፡

ታላቁ መፅሐፍ እንዲህ ይላል
ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች፤በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም ቃል ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ።" ኦሪት ዘፍ. 9 : 16

🔴👉 በዚህም መሠረት ቃልኪዳኗን ምክንያት በማድረግ ኪዳነ-ምህረት እያልን እንጠራታለን።

የእመቤታችን ምህረት እና ረድዔት ፤በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን!

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 16/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

25 Oct, 04:27

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_ቂርቆስ
…………………………………………
እንኳን ለሰማዕቱ ሕፃን ቅዱስ ቂርቆስ ወኢየሉጣ ወርሃዊ ክብረ-በዓል በሰላም አደረሳችሁ ! አደረሰን !!

🔴👉 ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ አባቱ ቆዝሚስ ፣ እናቱ ኢየሉጣ ይባላሉ። ሀገራቸውም ሮም ነበር። በዘመነ ሰማዕታት በጨካኙ እና በአረመኔው በዲዮቅልጥያኖስ ዘመነ መንግስት አዋጅ ታውጆ ነበር፡፡ይህም በ303 ዓ.ም ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ብዙ ክርስትያኖች ተሰደዱ ፤ ቅድስት እየሉጣም የሦስት አመት ልጇን ይዛ ወደ ኢቆንዮን ሸሸች፡፡
.
🔷👉 ንጉሥ እለ እስክንድሮስ አስጠርቶ ክርስቶስን ካጅ ለጣዖት ስገጅ አላት። በእጅህ ሠርተህ ላቆምከው ምስል አልሰግድም አለች እምቢ ካልሽ በሰይፍ ትቀጫለሽ ብሎ አስፈራራት ፤ እርሷ ግን ምንም አልፈራችም - እምነታቸው ጠንካራ ነውና።
.
🔷👉 በብረት ጋን ውኃ አፍልታችሁ ከዚያ ውስጥ ጣሎአቸው ብሎ አዘዘ። የውኃው ፍላት እንደ ክረምት ነጎድጓድ ከ4 -15 ክንድ ያህል ይፈላ ነበር። በፈላው ውኃ ሊጨምሮቸው ሲወስዷቸው የኢየሉጣ ልብ በፍርሀት ታወከ በዚህ ግዜ በቅዱስ ቂርቆስ ላይ መንፈስ ቅዱስ አድሮ የእናቱን ፍርሀት አስወገደ፡፡እናቴ ሆይ በርች ፤ ጨክኝ ፤ አናንያን ፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነን የለምን እያለ እናቱን እያደፋፈረ ከእሣቱ ቀረበ ፤ እርሷም ጨክና በፍጹም ልቧ ተያይዘው ከፈላው ውኃ ገብተዋል፡፡
.
🔴👉 ልዑል እግዚአብሔር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ልኮ በበትረ መስቀሉ እሳቱን አጥፍቶ የፈላውን ውኃ አቀዝቅዞ አዳናቸው፡፡
.
🔷👉 ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ሕፃኑን ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት እየሉጣን በንፍር ውኃ ከመቀቀል እንዳዳንካቸው እኛ አገልጋዮችህም በማናውቀው ሁኔታ የተዘጋጀልንን የጥፋት ወጥመድ ሁሉ አስወግድልን በላያችን ላይም በክፉ ሰዎች ምክንያት የተነሳብንን እሣት አጥፋልን ለእውነተኛ ሃይማኖት የጨከንንና የቆረጥንም አድርገን። የሰይጣንን ፈተና የምናልፍበት እውነተኛውን ጥበብ እንደ ነብዩ ዳንኤል አስተምረን።
.
🔴👉 ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15(፲፭) ቀን በሰይፍ ተመትተው ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

24 Oct, 19:25

https://youtu.be/ziEkGY70hvs?si=A5_KGTFPWGunArr3

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

23 Oct, 17:54

https://youtu.be/Lqn3Pftztmk?si=QPX5H7BSinKdC-Y3

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

22 Oct, 05:40

# ቅዱስ ሚካኤል
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ ቋንቋ ሚ-መኑ’ ካ-ከመ’ ኤል- አምላክ ማለት ሲሆን በአንድነት ሲነበብ መኑ ከመ አምላክ (እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው) ማለት ነው፡፡

🔷👉 ይህ ታላቅ መልአክ ዮሐንስ ወንጌላዊ በራዕዩ ‹‹ በእግዚአብሔር ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ›› ብሎ ከተናገረላቸው መላእክት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የሰባቱም ሊቃነ መላእክት አለቃ እንዲሆን እግዚአብሔር መርጦ ሹሞታል፡፡

🔵👉 ይህ ታላቅ መልአክ ያደረጋቸው የሠራቸው እጅግ ብዙ የሆኑ ተአምራት አሉት፡፡

🔴👉 በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።
በፊቱ ተጠንቀቁ፥ ቃሉንም አድምጡ ስሜም በእርሱ ስለ ሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት።
( ኦሪ ዘፀ 23፥20–21)

🔶👉 በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

👉 ሚካኤል ማለት “ከመ እግዚአብሔር እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው?” ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው?
መልሱ የለም ነው፡፡

🔵👉 ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል ፣መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ ናቸው፡፡

🔴👉 መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ፣ ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡

🔵👉 መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

👉 መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

🔷👉 ለዝክረ ስምከ፦

የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ እኔንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልኝ።

🔶👉 ለአዕይንቲከ፦
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! ለሰው ልጅ ይቅርታን ለማስገኝት ወደ ልዑል እግዚአብሔር አሻቅበው ለሚማልዱ ዓይኖችህ ሰላምታ ይገባል።

🔴👉 ለገጽከ፦
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ! መሬትና ውኃ ያልተቀላቀለበት ከነፋስና ከእሳት ብቻ ለተፈጠረው መልአካዊ ገጽታህ ሰላም እላለሁ።

👉 ለርእስከ፦
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ ፍጹም የማዳንህን ትድግና በኔ ላይ ትገልጽ ዘንድ፥ በስተቀኜ ቁመህ አለሁልህ በለኝ እንጂ በሩቅ ሆነህ አትመልከተኝ።

👉 ለስእርተ ርእስከ፦
የእግዚአብሔር ባለሟል ሆይ፤በእግዚአብሔር ፊት በጐ መዓዛ ያለውን መሥዋዕት የምታሳርግ አንተ ሚካኤል ነህና።

የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ፣ጸሎትና ጥበቃው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 12/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

21 Oct, 20:04

https://youtu.be/Zt_nyTmKtM4?si=75AFQ-GnPCWjGyf4

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

20 Oct, 03:45

https://youtu.be/JbrWaH8nej4?si=V9wz4p4Fs6Qqu6GX

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Oct, 19:06

https://youtu.be/KvXp7B06iJ4?si=otzBbVFozTT0tCvH

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

19 Oct, 14:59

ሆለታ ደብረ ኤዶም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

18 Oct, 06:25

#ጻድቁ_አባታችን_አባ_ኪሮስ 
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
  🔴👉 አባታቸው ንጉሥ ዮናስ
            እናታቸው   አንስራ   ይባላሉ።

   🔷👉  የቀደመ ስማቸው ዲላሶር የተሰኘ ሲሆን
    ሁለተኛ ስማቸው ደግሞ ❖ #ኪሮስ ❖

            🔴👉 በታህሳስ 8  ቀን ተወልደዋል
በ8 ዓመታቸው ያላቸውን ገንዘብ ከወንድማቸው ጋር በመካፈል ወደ አባ በብኑዳ ገዳም ገብተዋል።

👉 እስከ 17 ዓመታቸው ረድዕ ሆነው እያገለገሉ ስርዓተ ምንኩስናን ከተማሩ፤ ከተረዱ በኋላ የምንኩስናን ማዕረግ ተቀብለዋል።

🔵👉 ስለ እግዚአብሔር ፍርድ እንዲሁም ስለ ሰው ልጆች ይቅርታ 40 ዓመት በመሬት ላይ ተኝተው ስጋቸው ከመሬት ጋር ተጣብቆ ሣር እስኪበቅልባቸው ድረስ ጸልየዋል።

🔵👉 ጌታችንም ስለ መታመናቸው እና ስለ ተጋድሏቸው አክብሯቸዋል ።

👉 ቃል ኪዳናቸውም ፡-  መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡

🔷👉 በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ  ሐምሌ 8 አርፈዋል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ኪሮስ
  🔹ምልጃና በረከታቸው አይለየን
       
።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
    ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

  ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
      ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም
                 ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

17 Oct, 16:57

https://youtu.be/8L8wb3RaPd8?si=4YQlnIWfj3jt9cyp

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

17 Oct, 04:35

#ስላሴን_ለምን_ቅድስት_ስላሴ
               🔴#እንላለን?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔷👉 ሥላሴን  ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር፡-

🔶👉 አንድም ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብሎ አይጠረጠሩም፡፡

🔵👉 አንድም ሴት በባህሪዋ ልጅን ታስገኛለች፣ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንጻር ቅድስት ተብለው ይጠራሉ፡፡

🔴👉 አንድም ሴት አዛኝ ናት፣ለታናሹም ሆነ ለታላቁ ትራራለች ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ፣ ይራራሉ፣ ምህረትን ይሰጣሉ፡፡

🔵👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል ”ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንፃር
ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ የምህረት ወንዶች ሥላሴ" በማለት ያመሰጥራል፡፡

🔶👉 ስለእዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው፣ ርህራሄያቸውና፣ ይቅር
ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን፡፡
አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም፣ ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያቢሎስ እጅ ተይዞ በሐጥያት እንዲታመሙ አይወዱም፣ አይፈቅዱም በመሆኑም “ቅድስት” ይባላሉ፡፡

🔴👉 አንድም ሴት የልጇን ነውር አትፀየፍም ልጄ ቆሽሿል፣ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም፣ ሥላሴም የሰውን በሐጥያት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተው ለንስሐ ያደርሱታል ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን በሥላሴ ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንጻር ቅድስት እንላቸዋለን፡፡

🔴👉 አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች ሥላሴም እነደዛው ናቸው በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብስለው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ፡፡ ስለእዚህ ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንፃር ቅድስት ይባላሉ፡፡

በዚህ ምክንያት ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን በፍቅር እንጠራለን፡፡

🔷የቅድስት ሥላሴ ረድኤት በረከት አይለየን🔷

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
    ።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

  ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
      ጥቅምት 7/2017 ዓ.ም
                 ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

16 Oct, 04:25

https://youtu.be/gt0cfy_hsZw?si=Pr094Y2XutXHC-Y4

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Oct, 17:52

#ጥቅምት_5 #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 የቅዱስ አባታችን 👉 አባታቸው ስምዖን
👉 እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ::

🔷👉 እነርሱም ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል :: ታዲያ አንድ ቀን አቅሌያስ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከስዕለ ስላሴ ስር ወድቃ ስትማጸን " ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበልጥ ልጅ እንኪ ተቀበዪ የሚል ድምጽ ሰማች ::

በዚህም መሰረት አባታችን መጋቢት 29 ቀን ተጸንሰው ታህሳስ 29 ቀን ተወለዱ

🔴👉 ፃዲቁ አባታችን አይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፍ ሁሉ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለው ተነስተው " ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስቅዱስ ዘአውጻእከኒ እምጽልመት ውስተ ብርሐን " ብለው በማመስገናቸውና ኋላም ምድራዊ መብል እና መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላእክትን ይመስላሉ ። አባታችን ገና በተወለዱባት ዕለት ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ በማለት ለሥላሴ ምስጋና አቅርበዋል።

🔵👉 ሶስት አመት ሲሆናቸው መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከእመቤታችንና በገነት ካሉ ቅዱሳን ዘንድ አስባርኮ ገዳማውያን ካሉበት ከአንድ አበምኔት ደጃፍ ወስዶ አኖራቸው :: አበምኔቱም አባ ዘመደ ብርሐን ምልክት ተነግሮት ቢሄድ #ፍሱሐ_ገጽ ሆኖ አግኝተዋቸዋል :: አበመኔቱም አሳድጎ አስተምሮ ከመአርገ ምንኩስና አድርሰዋቸዋል።

🔷👉 በገድለህ በትሩፋትህ ከሞት ነፍስ ከርደተ ገሀነም የሚድኑ ብዙ አሉና ከሰው ተለይተህ ወደ ጫካ ግባ :: ኑሮህም ከስልሳ አናብስትና ከስልሳ አናብርት ጋር ይሁን አለው :: ጌታዬ ምን ተመግበው ይኖራሉ አሉት ? " #ዘኬድከ_ጸበለ_እግረከ_ይልህሱ_ወበ_ውእቱ_ይጽግቡ ።" የረገጥከውን ትቢያ ልሰው ያ ምግብ ሆኗቸው ይኖራሉ :: ብሏቸው ውሳጤ ገዳም ገብተው ከአናብስትና ከአናብርት ጋር ይኖሩ ጀመሩ ::

🔵👉 ዳንኤል ከአናብስት ጉድጉዋድ በተጣለ ጊዜ አናብስቱ እንደ ድመት ከእግሩ በታች ሆነው እንደተገኙ አባታችን የረገጡትን ትቢያ እየላሱ እየታዘዙዋቸው ይኖሩ ነበር ።

🔷👉 ከዚህ በኋላ ሑር ምድረ ኢትዮጵያ " ወበህየኒ ሐልውከ ነፍሳተ ወታወጽኦሙ" ወደ ኢትዮጵያ ሂድ አላቸው :: ቅዱስ ገብርኤል በሰረገላ ነፍስ ጭኖ #ምድረ_ከብድ አድርሷቸዋል :: ዳግመኛም ወደ #ዝቋላ (ደብረቅዱስ ) ወስዷቸው ከዚያ ሆነው በንጹሀ ልቦና የኢትዮጵያን ሕዝብ ሐጢያት ከባህሩ ውስጥ ራሳቸውን ዘቅዝቀው ለ 100 አመት ይጸልዩ ነበር ::

🔴👉 40 ቀን ሲሆናቸው መልአኩ መጥቶ #ዘገብረ_ተዝካርከ_ወዘጸውአ_ስመከ_እምህር_ለከ " (ስምህን የጠራውን መታሰብያህን ያደረገውን ምሬልሃለው ) ብሎሀል አላቸው :: እሳቸው ግን መላ ኢትዮጵያን ካልማረልኝ አልወጣም ብለው 100 አመት በባህሩ ውስጥ በጭንቅላታቸው ተዘቅዝቀው ሲጸልዩ ኖረዋል :: ከ 100 አመት ቡሐላ ጌታ " #ተንስእ_ወጻእ_መሀርኩ_ለከ_ኵሎ_ኢትዮጵያ ( ተነስተህ ውጣ መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ ) ብሏቸው ወጥተዋል ::

🔷👉 ከዚህ በኋላ #ምድረ_ከብድ ወርደው ከምድር በላይ ከሰማይ በታች ሆነው 7 አመት እንደ አምድ ተክል ሆነው አይናቸውን ሳይከድኑ እጃቸውን ሳያጥፉ ራሳቸውን ዝቅ ሳያደርጉ 7 አመት ሙሉ አይናቸውን ወደ ሰማይ አቅንተው ቆመው ጸልየዋል ::

🔴👉 ሰይጣን ግን ለምቀኝነት አያርፍምና ቁራ መስሎ ( በቁራ ተመስሎ) መጥቶ አይናቸውን አንቁሮ አሳወራቸው :: 2 ሱባኤ ሲፈጽሙ ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል መጥተው እፍፍ ብለው አይናቸውን አድነዋቸዋል ::

🔴👉 ለ100 ዓመት ሕዝበ ኢትዮጵያን ማርልኝ ብለው በዝቋላ ተራራ በሚገኘው ሐይቅ ተዘቅዝቀው ለምነው የምሕረት ቃልኪዳንን የተቀበሉበት እንዲሁም እረፍታቸው መጋቢት 5 ቀን ነው። ነገር ግን ይህ ዕለት በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ስለሚውልና ፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ስለሚከለክል።

🔵👉 ዓብይ ፆም የጽሞና የጸሎት ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ ደስታ የለም ስለዚህም መጋቢት 5 ይከበር የነበረው የአባታችን የዕረፍታቸው መታሰቢያ ወደ #ጥቅምት_5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተወስኖልናል።

የጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን

።።።።#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
።።።።። #ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
።።።።። #ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም
ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም
ሆለታ

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
       👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
      👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

14 Oct, 12:14

https://youtu.be/khHD0Nuw1wU?si=aY55oJXOfSWq_4F5

ዲ/ን ዮናስ ዘ ሆለታ ደብረ ኤዶም

11 Oct, 14:11

ማኅሌተ ጽጌ 2ኛ ሳምንት

ፔጁን #Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/joinchat_yonas_holet_debreedom

🔴👉 በዋትስአፕ | whatsapp
👇👇👇👇👇
https://whatsapp.com/channel/0029Va4Ter67T8bV5NlRGJ2w

🔴👉 1ኛ ዩትዩብ | 1st YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@yonastube

🔴👉 2ኛ ዩትዩብ | 2nd YouTube
👇👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@yonasmedia16

4,189

subscribers

1,829

photos

21

videos