የ መፅሀፍት ዓለም @ethiopian_amharic_pdf_books Channel on Telegram

የ መፅሀፍት ዓለም

@ethiopian_amharic_pdf_books


ምርጥ ምርጥ የአማርኛ መፅሀፍቶችን ከዌብሣይታችን ላይ በpdf Download በማድረግ ያንብቡ። ይደሰቱ 👇https://typicalethiopian.com/ethiopian-books/
አስተያየት ካሎት @Ethbookworld_00

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም (Amharic)

ከመፅሀፍት መነሻ በኋላ አማርኛ ፕድፊ መፅሀፍት የሚለው ላይ ያለው የመፅሀፍ ቤተሰብ ነው። ይህ መፅሀፍት የእንቅስቃሴ ዋጋውን ለመብረር እና በምርጥ ቡድንም እንዲያስተካት ይመልከቱ። የእባኮ መፅሀፍት የፈተና ዘጋችንን አወዳድረን ለመስጠት እና ማስተካከል የሚሆንበትን እና በአጭር ፕድፊ የሚያስወግዱበትን የማዋሉንም መፅሀፍት ይቀርባል። ይህንን መልክቱን በላይ ያንብቡ። በተጨማሪም @Ethbookworld_00 ይደሰቱ።

የ መፅሀፍት ዓለም

20 Feb, 16:28


የሰማዕታት ሐውልትን የቀረጹት ሁሉቱ

#Ethiopia | ከታች በምስሉ ላይ የሚታዩት የየካቲት ፲፪ የሰማዕታት ሐውልትን የቀረጹት ሁሉቱ የክሮኤሽያ (የያኔው ዩጎዝላቪያ) ዜጎች ሲሆኑ Antun Augustinčić እና Frano Kršinić ይባላሉ።

የ መፅሀፍት ዓለም

20 Feb, 05:41


የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም
#በዛሬዋ_ዕለት
ከ 88 ዓመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በአብርሃም ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶም መሪነት በኢጣልያኑ የጦር አዛዥ ጄነራል ግራዚያኒ ላይ በቦንብ ያደረጉት የግድያ ሙከራ ምክንያት የኢጣሊያን ወታደሮች በቂም በቀል በመነሳት በሺዎች የሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችን ለ 3 ተከታታይ ቀናት ዘግናኝ እና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በህዝቡ ላይ ጭፍጨፋ ያደረሱበት ዕለት ነበር።
የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም በፋሺስት ኢጣሊያ በግፍ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያውያን ሰማዕታት ሲታወሱ......
የካቲት 12 ቀን በኢትዮጵያ ታሪክ የተለየ ቀን ነው፡፡ የኢጣሊያዋ ኔፕልስ ግዛት ልዑል ልጅ መውለዱን ለመዘከር ግራዚያኒ በዚህ ቀን የአዲስ አበባን ደሃዎች ሰብስቦ ለመመጽወት ባደረገው ጥሪ መሰረት ከ 3ሺ የሚበልጡ አቅመ ደካሞች በጥዋቱ በ 6 ኪሎው ቤተመንግስት ተገኝተዋል፡፡

የ መፅሀፍት ዓለም

20 Feb, 05:41


በዚህ ቀን ኢትዮጵያውያን ጥቃት ሊያደርሱ ይችላሉ የሚለው መረጃ እስከ ሮም በመሰማቱ የቤተመንግስቱ ውስጥና ዙሪያ መትረየስ በታጠቁ ልዩ ወታደሮች እንዲጠበቅ ተደርጓል፡፡ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ይህንን ጠንካራ ጥበቃ አልፈው ውስጥ ገብተዋል፡፡
ከቀኑ ለስድስት ሩብ ጉዳይ አካባቢ ሲሆን ከፍተኛ ፍንዳታ በቤተ መንግስቱ ተሰማ፡፡ ከፍ ወዳለው የቤተመንግስቱ ደረጃ የተወረወረው ቦምብ ደግሞ ግቢውን በጩሀት አናጋው፡፡ የመጀመሪያው ቦምብ ባለመትረየስ ጠባቂውን አስወገደው፡፡ 2ኛው ቦምብ ከግራዚያኒ አጠገብ የነበረውን ምሰሶ አፈራረሰው፡፡ ግራዚያኒ ወደ ውስጥ ሲሸሽ ጀርባው፣ ትከሻውና የቀኝ እግሩን ከ 350 በሚበልጥ የቦምብ ፍንጣሪ ቆሰለ፡፡ የካሜራ ባለሙያውና ወታደሮች ግራዚያኒን ከወደቀበት አንስተው በመኪና በመጫን ወደ ሆስፒታል ይዘውት በረሩ፡፡
ሶስተኛው ቦምብ ፖጊያሊ ፊት በመውደቅ ፍንጣሪው አቡነ ቄርሎስን ሲያቆስላቸው ጃንጥላ ያዣቸውን ደግሞ ገደለው፡፡ የኢጣሊያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጄኔራል ሊዮታ በቦምብ እግሩን አጣ፡፡ የፋሺስት ፓርቲ ዋና ጸሀፊና የቤተመንግስቱ ጠባቂዎች በድንጋጤ ለምጽዋት በ6 ኪሎ በተሰበሰበው ህዝብ ላይ እሩምታ በመተኮስ ከ1ሺ የሚበልጡትን ገደሉ፡፡ የጥቃቱ ዋና ፈጻሚዎች ሞገስ አስገዶምና አብርሃ ደቦጭ ከጊቢው በመውጣት ተሰወሩ፡፡
በቀጣይ ሰአታት ጥቁር ከነቴራ ለባሽ የኢጣሊያ ልዩ ወታደሮች የቴሌፎንና የፖስታ አገልግሎትን ዘጉ፡፡ ወዲያው መሃል ፒያሳ አራዳ ባለው የፋሽስት ዋና ጽ/ቤት የነበረው ጎዶ ኮርቴሌ የፋሽስት ወታደሮች ለሚቀጥሉት 3 ቀናት ኢትዮጵያውያንን እንዲጨፈጭፉ ትእዛዝ ሰጠ፡፡ በዚሁ ምሽት አዲስ አበባ የእርድ ቄራ ሆነች፡፡
ነዋሪዎቿ ቤት ከውጭ እየተቆለፈባቸው ከውጭ በሚለኮስ እሳት እንዲነዱ ተደረገ፡፡ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የተገኙት ደግሞ እየታፈሱ በመኪና ተጭነው ተወስደው በግራዚያኒ ዋና መምሪያ ተረሸኑ፡፡ ከሚነዱት ቤቶች አምልጦ ለመውጣት እድል ያገኘውን ደግሞ የኢጣሊያ ወታደሮች ከደጅ ሆነው በጥይት ለቀሙት፡፡
የጥቃቱ አቀናባሪዎችንና አድራሾችን ለመያዝ ጥብቅ ምርመራና አሰሳ ተጀመረ፡፡ የኢጣሊያ ደህንነቶች ከምሽቱ በ 2 ሰአት የአብረሃ ደቦጭን ቤት ሰብረው ሲገቡም እጀታው አረንጓዴ፣ቢጫ እና ቀይ በሆነው የኢትዮጵያ ባንዲራ ቀለማት በተቀባ ሳንጃ የኢጣሊያ ባንዲራ ተቦጫጭቆ አገኙ፡፡ በመቀጠል የሞገስና የአብርሃ ጓደኞችን ማደን ተጀመረ፡፡
አብርሃና ሞገስ ከምሽቱ 1:00 ሰአት አካባቢ ወደ ጀርመን ሚሽን በመሄድ ጓደኛቸው ስብሀትን በአጥር ቢያስጠሩትም ስብሀት አብሯቸው ለመሄድ ዝግጁ ስላልነበር ብቻቸውን ከተማውን ለቀው ሸሹ፡፡ ከጥቂት ሰአታት በኋላ የኢጣሊያ ወታደሮች የጀርመንን ሚሽን በመክበብ ስብሀትን እያዳፉ ወሰዱት፡፡ አርበኛ ሸዋ ረገድ ገድሌንም በማታ ወስደው በኤሌክትሪክ ንዝረት ቢያሰቃይዋትም ሚስጥር ሳታወጣ ቀረች፡፡
ቅዳሜ ጥዋት በድንጋጤ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ሲሯሯጡ የተገኙ ነዋሪችም ታፍሰው ፒያሳ ራስ መኮንን ድልድይ አጠገብ ተረሸኑ፡፡ በአሜሪካ ኤምባሲ ተሸሽገው የነበሩ በ 100ዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን ኤምባሲው አሳልፎ እንደሰጣቸው ኤምባሲው በር ላይ እንደ ውሻ እየተቀጠቀጡ ተገደሉ፡፡
ይህ ለአሜሪካ ህዝብ ይፋ ከሆነ በኋላ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር እና ኢትዮጵያ የሚገኘው አምባሳደር ዜናውን በማግስቱ አስተባበሉ፡፡ ምኒልክ አደባባይ አቅራቢያ ሆኖ ይህንን ግፍ ይመለከት የነበረው ወጣቱ ልጅ እምሩ ዘለቀም ከሰአታት በኋላ ቤቱን ሰብረው በገቡ የኢጣሊያ ወታደሮች ከእናቱና 2 እህቶቹ ጋር ተይዞ ታሰረ፡፡
እሁድ እለት የ 3 ቀኑን ጭፍጨፋ ለማስቆም በአዲስ አበባ የተለያዩ ቦታዎች የሚከተለው አዋጅ ተለጠፈ፣
“ ሞሶሎኒ እንደ ፈጣሪ ሃያል ነው፡፡ ፈጣሪም ሆነ ሞሶሎኒ ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፡፡ ሞሶሎኒ ተበሳጭቶባችሁ ነበር፡፡ አሁን ግን ቁጣው በርዷል፡፡ ወደ የቤታችሁ በመሄድ እለታዊ ተግባራችሁን ቀጥሉ፡፡”
ይሁን እንጂ ከዚህ አዋጅ በኋላም ግድያው ቀጥሎ ነበር፡፡ የበቀል ቅጣቱን ለማምለጥ ከቤታቸው ከወጡት ወደ 5ሺ የሚጠጉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ውስጥ ብዙዎቹ የአርበኞችን ትግል ተቀላቀሉ፡፡ በሁለት ቀን ተኩል በኢጣሊያ የግፍ ጭፍጨፋ የተገደሉትን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር አንዳንድ ወገኖች እስከ 30ሺ እንደሚደርስ ሲገልጹ ሌሎች ደግሞ ቁጥሩን ከላይ 17ሺ - 18ሺ ያደርሱታል፡፡
©️ የአርበኞች ጀብዱ፣ Jeff Pearce እንደጻፈው፣ ኤፍሬም አበበ እንደተረጎመው፣ ገጽ 205-212
ክብና ዘላለማዊ ዕረፍት ለሰማዕታት 🙏
#ታሪክን_ወደኋላ

የ መፅሀፍት ዓለም

19 Feb, 07:51


የካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ

"አዲስ አበባን ቄራ አደረጓት"

የዕለቱን ሁኔታ ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ 'የኢትዮጵያ ታሪክ ከ1847 እስከ 1983' በሚለው መፅሐፋቸው እንዲህ ይተርኩታል።

" ... "ጥቁር ሸሚዝ" እየተባሉ የሚታወቁት የፋሽስት ደቀመዛሙርት በፋሽስቱ አገዛዝ አይዞህ ባይነት አዲስ አበባን ቄራ አደረጓት። የሠው ልጅ ጭንቅላት እንደ ዶሮ እየተቀነጠሰ ወደቀ። ቤቶች ከነነዋሪዎቻቸው ጋዩ። እርጉዝ ሴቶች በሳንጃ ተወጉ። የጭፍጨፋው ተቀዳሚ ዒላማ የተማሩ ኢትዮጵያውያን ነበሩ።

በተለይም የጥቁር አንበሳ አባላት ከራስ እምሩ ጋር እጃቸውን ከሰጡ በኋላ በከተማይቱ ይገኙ ስለነበር በወረንጦ እየተለቀሙ ተረሸኑ። ይህ የምሁራን ጭፍጨፋ አንድ ትውልድ እንዳለ ያጠፋ በመሆኑም በሃገሪቱ የፖለቲካና ምሁራዊ ታሪክ ላይ የማይሻር ቁስል ጥሎ አለፈ።"

በዚህ ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሶስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን መስዋዕትነት ተቀበሉ። በሌላ በኩል ይሄ ጭፍጨፋ ሲወላውል የነበረውን፣ መሃል ሠፍሮ የነበረውን፣ "ጣልያኖች ቢያስተዳድሩን ምን ችግር አለው?" ..... ይል የነበረውን ኢትዮጵያዊ በሙሉ ለአንድ ዓላማ አብሮ እንዲቆምና 'ዱርቤቴ' እንዲል ያደረገ ክስተትም ነበር።

#ክብር_ለሰማዕታት!

የ መፅሀፍት ዓለም

18 Feb, 09:37


**"The greatest pain a person can endure is not hunger, poverty, or even death, but to love in a world that does not acknowledge their love—to give their heart completely and receive only emptiness and silence in return.

Within us, we carry a terrifying contradiction: we seek love, yet we fear it; we long for closeness, yet we flee from it; we adore the other, yet we doubt them. What absurdity is this, that makes us cling to those who leave and neglect those who stay?

I wonder: Is love a test of our strength or a revelation of our weakness? And is the loneliness we escape from nothing more than the natural consequence of every love that was never reciprocated?"**

— A quote from the novel "The Brothers Karamazov"


✍🏼 Fyodor Dostoevsky

የ መፅሀፍት ዓለም

13 Feb, 08:41


"" እሱ እኰ ከባድ ሠው ነው""

"የመቄዶንያ መሥራች ቢኒያም በለጠ"

መቄዶንያ የተሰኘ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል የተሰኘ የበጎ አድራጎት ማኅበር በመመሥረት በመላው ኢትጵያዊያን ልብ ውስጥ ተቀምጧል።

ቢኒያም በለጠ ከእናቱ ጽጌ በቀለ እና ከአባቱ በለጠ አዲስ በአዲስ አበባ ነው የተወለደው።

ቢኒያም በትምህርቱም ምስጉን የሚባል ተማሪ ነበር።

ጥሩ ውጤት በማምጣት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ገብቶ ሕግ አጥንቷል።

ለሦስት ዓመታት በሕግ ባለሞያነት በሀገር ውስጥ አገልግሏል።

ቢኒያም በትምህርት ዓለም ስኬታማ ቢኾንም በውስጡ የሚያረካው እና እረፍት የሚሰጠው ኾኖ ግን አላገኘውም።

ቢኒያም በመንገዱ ላይ ወድቀው አጋዥ ያጡ ሰዎችን እያየ ልቡ ይሠበር ነበር።

በምን መንገድ ሊያግዛቸው እንደሚችል ሁሌም ያስብ ነበር።

በመኃል ወደ ሀገረ አሜሪካ አቀና...

እዚያም የተለያዩ ሥራዎችን ሲሠራ ቆይቶ በነን ፕሮፊት ማኔጅመንት ኤንድ ዴቨሎፕመንት ተምሮ ተመረቀ።

“ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው” በሚለው መሪ ቃሉ የምናውቀው ቢኒያም በለጠ ቀደም ሲል ሲያስበው የነበረው ሀሳብ አይሎበት በሀገረ አሜሪካ የተማረውን እውቀት እና ያጠራቀመውን ገንዘብ ይዞ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።

የተወሰኑ ደጋፊ ያጡ ሰዎችን "መቄዶንያ" የተሰኘ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከልን በሚል ወላጆቹ ቤት በማኖር የበጎ ሥራ ሀሳቡን አንድ ብሎ ጀመረ።

መቄዶንያ አሁን ትልቅ የሰብአዊ እርዳታ አገልግሎት መስጫ ኾኖ ከ8000 በላይ ሰዎችን በተለያዩ 44 ከተሞች ያግዛል።

ቢኒያም በለጠ አጋዥ ለሌላቸው፣ የአካል ጉዳት ያለባቸው፣ጎዳና የወደቁ አረጋውያን እንዲሁም ለአዕምሮ ሕሙማን በሜቄዶንያ አዲሳባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ድጋፍ እየሰጠ ይገኛል።

የ መፅሀፍት ዓለም

11 Feb, 08:38


መጫሚያ አልባው ንጉስ
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

GET THE BOOK

የ መፅሀፍት ዓለም

09 Feb, 15:17


❤️ Beautiful Day family ❤️

የ መፅሀፍት ዓለም

07 Feb, 06:12


War and Peace
By - Leo Tolstoy
#theorginals
#classics
#share

❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት ዓለም

06 Feb, 18:49


ሁለት ሴቶች ሲያወሩ ምንም ነገር መናገር አይችሉም። አንዲት ሴት ስታወራ ግን ሙሉ ሕይወትን ልትናገር ትችላለች፡፡

🖊️ ካህሊል ጂብራን

የ መፅሀፍት ዓለም

05 Feb, 18:34


3. ያሉበትን ቦታ አመልካች (ጂፒኤስ)

የቦታ አመልካችን (ጂፒኤስ) ማብራትም ባትሪ የሚጨርስ ነገር ነው። እንደ ትዊተር ያሉ አፕልኬሽኖች ደግሞ እርስዎ ሳያውቁት ሁሉ ያሉበትን ቦታ መዝግብው ይይዛሉ።

ስለዚህ ያሉበትን ቦታ የሚመዘግቡ መተግበሪያዎችን ቁጥር ለመቀነስ የማይፈልጓቸውን እንዳይሰሩ ማድረግ ይቻላል።

4.ከፍተኛ ሙቀት

ሊቲየም ባትሪዎች ለከፍተኛ ሙቀት ከተጋለጡ በደንብ አይሰሩም። ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው አየን ባትሪው ቶሎ ቶሎ ቻርጅ እንዲደረግ ያስገድዳልና።

ስለዚህ ስልክዎ ለከፍተኛ ሙቀት ወይም ለከፍተኛ ቅዝቃዜ እንዳይጋለጥ ማድረግ አይነተኛ መፍትሄ ነው።

5. ትልልቅ ስክሪኖች

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስልኮች ትልልቅ ስክሪኖች እንዲኖራቸው እየተደረገ ነው። ይህ ትልቅ ስክሪን ሲከፈትና ሲበራ ባትሪ ይጨርሳል። ስለዚህም የስክሪኑን የብርሃን መጠን መቀነስ ጠቃሚ ነው።

ስክሪኑን ማጥፋትና ቶሎ ቶሎ ስልክዎን አለመመልከትም ሌላው መፍትሄ ነው።

6. ከፍተኛ ድምፅ

የመተግበሪያዎች ወይም የስልክ ጥሪዎች ድምፅ ከፍተኛ ከሆነ ባትሪ ይጨርሳል። አብዛኛውን ጊዜ የድምፅ ነገር ስልክዎ ባለው ስፒከር የሚወሰን ይሆናል።

የጆሮ ማዳመጫ መጠቀምና በሚያዳምጡበት ወቅት የሌሎች መተግበሪያዎችን ድምፅ ማጥፋትም ጥሩ ነው።

7. ቶሎ ቶሎ ቻርጅ ማድረግ

በፊት በፊት ስልክዎ ባትሪ እስኪጨርስ ከተጠቀሙ በኋላ ቻርጅ ማድረግ ነበር ተመራጩ። አሁን ግን ማድረግ የሚጠቅመው ተገላቢጦሹን ነው።

ይህ ማለት ደግሞ ከስር ከስር ባትሪ ሳይጨርስ ስልክን ቻርጅ ማድረግ መልካም ነው። ባትሪዎ መጠን ከግማሽ በታች ዝቅ እንዳይል ቻርጅ ቢያደርጉ የባትሪዎን እድሜ እንደሚያረዝም የሞባይል ስልኮች ባለሙያዎች ይመክራሉ።

እርግጠኛ መፍትሄዎች

ሁሉም የሞባይል አምራቾች የሚስማሙበት ዋነኛ መፍትሄ ስልክዎን ባትሪ ሃይል ቆጣቢ ሞድ ላይ ማድረግን ነው። ይህ ማለት ደግሞ የስልክዎ ስክሪን ብርሃን ይቀንሳል፣ ስልክዎ ንዝረት ያቆማል፣ ብዙ ማሳወቂያዎች (ኖቲፊኬሽን) አይደርስዎትም። ያሉበትን ቦታ አመልካች አገልግሎት አይሰጥም።

ነገር ግን ባትሪዎ በአሁኑ ወቅት የደከመ ከሆነ እነዚህ ነገሮችን ማድረግ ብዙም ለውጥ አያመጣም፤ ያለው አማራጭ የስልክዎን ባትሪ መቀየር ብቻ ነው።

[ምንጭ BBC Amharic]

የ መፅሀፍት ዓለም

05 Feb, 18:33


የስልክዎን ባትሪ ለረዥም ጊዜ ለመጠቀም የሚያግዙ ነገሮች

የስማርት ስልኮች ባትሪ ቶሎ ቶሎ ማለቅ የቴክኖሎጂው ትልቁ ድክመት ሆኗል። አፕል ከቀናት በፊት የባትሪዎችን እድሜ ለማርዘም ሲባል የስልኮቹን የአሰራር ሥርዓት (ኦፕሬቲንግ ሲስተም) ዝግ እንዲል ማድረጉን ይፋ አድርጓል።

ምንም እንኳ ኩባንያው ምርቶቹን እያሻሻለ ቢሆንም በአሜሪካ ብዙ ክሶች ተመስርተውበታል።

ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት በቶሎ የሚሞሉ ሊቲየም አየን ባትሪዎችን ሲሆን ዲዛይናቸውም ባትሪዎቹ ተጠጋግተው እንዲቀመጡ የሚያደርግ ነው።

የስማርት ስልኮች ግፅታና ዲዛይን ቶሎ ቶሎ መቀያየር ማሻሻያውን እንዳከበደውም እየተነገረ ነው። በርግጠኝነት ይህ ነው የሚባል ነገር ባይኖርም የስማርት ስልኮችን እድሜ ለማርዘም የሚረዱ ነገሮች አሉ።

1.ደካማ በይነ መረብ

ስልኮዎ በየሄዱበት ጥሩ የበይነ-መረብ (ኢንተርኔት) መስመርን ለማግኘት ይሞክራል። በተለይም ደካማ የበይነ-መረብ አገልግሎት ባለበት ወይም አንድ ቦታ ላይ ብዙ ሰዎች የገመድ አልባ ኢንተርኔትን (ዋይ ፋይ) ለመጠቀም ሲሞክሩ ስልክዎ ሙከራውን ያከረዋል።

ምርጥ የሚባል መፍትሄ ባይሆንም ስልክዎን ኤርፕሌን ሞድ ላይ ማድረግ ጥሩ ኢንተርኔት ለማግኘት እየታገለ ያለው ስልክዎ ባትሪ እንዳይጨርስ ይረዳዋል።

2. አንዳንድ መተግበሪያዎች (አፕልኬሽኖች)

አንዳንድ መተግበሪያዎች ባትሪ ይጨርሳሉ። ስለዚህ የማይፈልጓቸውን መተግበሪያዎችን መዝጋት የባትሪን እድሜ ያረዝማል።

በተጨማሪም ባትሪ የሚለው ክፍል ውስጥ በመግባት በከፍተኛ ሁኔታ ባትሪ እየጨረሰ ያለውን መተግበሪያ መለየት ያስፈልጋል።

የ መፅሀፍት ዓለም

30 Jan, 04:40


Anna Karenina
Author - Leo Tolstoy
#theorginals
#classics
#share

🔱GET THE BOOK 🔱

የ መፅሀፍት ዓለም

28 Jan, 12:57


ዙቤይዳ / zubeyda
ከአሌክስ አብርሃም
👇👇👇
🔱GET THE BOOK🔱

የ መፅሀፍት ዓለም

19 Jan, 16:54


ለሁሉም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ መልካም የጥምቀት በዓል

የ መፅሀፍት ዓለም

17 Jan, 22:02


.
.
.
....እንዴታ
.
.
አንቺዬ...
ከመሽታ ቤቱ፣
ቁልቁል ተደፍቼ መሽጌ ዘወትር
ስካር ተሸሽጌ፣በንውዘት ስማትር
( ...ገባኝ አንዳች ምስጢር ....)

"አንቺ የሌለሽበት የሕይወት ዘመኔ
'ንጋት ነው' ቢሉኝ እነኳን፣ሌሊት ነበር ለ' ኔ!"

[ተስፋሁን ከበደ( ፍራሽ አዳሽ) - ከሞት ጥቁር ወተት ]

የ መፅሀፍት ዓለም

14 Jan, 00:25


መፅሐፈ ቅንጭብ

"... እግዚአብሔር ፈጠነም ዘገየም ወደ እያንዳንዱ ሰው ህይወት ዉስጥ ይመጣል።ሲመጣ የእግዜርን እርምጃ የእግሩንም ዳና የሚቋቋም መንገድ የሚሰራው 'መከራ' በሚባል ኮንክሪት ነው።ዙሪያህን የከበበህን ችግርና እልህ አስጨራሽ የሕይወት ፈተና ስታልፍ ፣ የእግዜር የመጀመሪያ እርምጃ ትጀምራለች።ያኔ ታድያ ርሀብን ብቻ ሣይሆን ጥጋብንም የምትችል አድርጎ እንዳነፀህ ይገባሃል...."

❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት ዓለም

13 Jan, 11:16


ቆንጆዎቹ 🫥 ለ አስቀያሚዎቹ
""እያንዳንዱ ትውልድ ሃላፊነቱን ሊገነዘብ ይገባል፤
ሊፈፅመው አልያም ሊከዳው::[
ፍራንዝ ፋነን]""

"ቆንጅዬ .. ለምን አብረን አናድርም?"
" ቆንጅዬ .. ለምን ቤቴ አታደርሰኝም?"


ቆንጆ ማለት ደካማ ማለት አይደለም፤ቆንጆ ማለት አቅም የለሽ ማለት አይደለም... ራሱን የማይከላከል ቁንጅና የቀትር ፀሀይ ሲወጣ ይረግፋል.... ቆንጆዎች ነን፤ ጠንካሮችም ነን።

"መጀመሪያ አፍሪካ ማለት አለብን:መጀመሪያ አንድነታችና.... ርብቃ ያ ጊዜ መጥቶ እልሄን ና ቁጭቴን እንድወጣ ነው ፈጣሪን የምለምነው.... ያ ነው ጸሎቴ::"
🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥🫥
ቆንጆዎቹ ገና አልተወለዱም
The beautiful aren't yet born

❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት ዓለም

12 Jan, 21:40


#Mondayinspiration@ethiopian_amharic_pdf_books

🌼 መልካም የስራ ሳምንት 🌼

የ መፅሀፍት ዓለም

12 Jan, 16:26


ከንቱ አይደለም መፈጠሬ


አንድን ቅስም ከቅጭት ካዳንኩ

ከንቱ አይደለም መፈጠሬ፡፡

ያንድን ህይወት ቁስል ካከምኩ
ወይ አንድ ስቃይ ካቃለልኩ
ወይ አንድዋን የወደቀች ወፍ ጎጆዋ መልሼ ባተርፍ

ትርጉም ያገኛል መኖሬ፡፡

ከንቱ አይደለም መፈጠሬ


(ሽሽግ ወርቁ፤ ከኤሚሊ ዲኪንሰን ግጥም የተተረጎመ)

የ መፅሀፍት ዓለም

12 Jan, 08:22


"ትንሽ ትንሽ ማንበብ መዳን ነው"

ትንሽ ትንሽ ማንበብ መዳን ነው ይላሉ በአያሌው ከመጻሕፍት ጋር ተፋቅረው በቅጡ የዘለቁበት አንባቢያን::
እነዚህ ድንቅ የመጻሕፍት አፍቃሪያን " ዓለማችን ድንቅ ድንቅ ደራሲያንን ፈጥራልናለች ፤ እነሱም ከልብ ተጠበውልን ነበር። የሚያሳዝነው ሁሉንም ለማንበብ በቂ እድሜ የለንም" ሲሉ ይቆጫሉ። አንደ መታደል ይህንን በመረዳት በዚህች አጭር እድሜ የተቻላቸውን ያህል አውቀው እንዲያልፉ ከሆነም ውጤቱ የሚያጽናና ነው።

[አዲስ አድማስ ጥር 3 ቀን 2017
የ 25ኛ ዓመት ልዩ ዕትም]


መልካም የእረፍት ቀን

የ መፅሀፍት ዓለም

11 Jan, 13:33


"ኦሮማይ" መጽሐፍ ወደ እንግሊዝኛ ተተረጎመ

| ሰሞኑን የስመጥሩው ደራሲ የበዓሉ ግርማ የመጨረሻ ልቦለድ የሆነው "ኦሮማይ" መጽሐፍ ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የመተርጎሙ ዜና በአለም አቀፍ ደረጃ እየተነገረ ነው።

ለምሳሌ The Guardian የተሰኘው የታወቀውና ከሁለት መቶ አመታት በላይ ያስቆጠረው እለታዊው የእንግሊዝ ጋዜጣ ስለ በዓሉ ግርማ ሕይወትና ሕይወቱን ስለከፈለበት መጽሐፍ ሰፋ ያለ ዳሰሳ አስነብቦናል።

ስለዚህ ስለምንወደው ደራሲ በዚህ ልክ ሽፋን እንዲሰጠውና የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ በተቀረው አለም እንዲታወቅ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኙት ተርጓሚዎቹ David De Gusta እና Mesfin Fellkeን ማድነቅ ተገቢ ነው። ደ ጉስታን በአንድ ወቅት አሜሪካ አገር ተገናኝተን በነበረ ጊዜ ይህን ልቦለድ ለመተርጎም ስለሄዱበት ርቀት አጫውቶኝ ነበረ።

ደራሲ እንዳለጌታ ከበደ ( ዶ/ር )

የ መፅሀፍት ዓለም

09 Jan, 21:36


ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ
ከ - ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት ዓለም

09 Jan, 05:53


Ethiopian Books (Free PDF Download & Book Review) - Typical Ethiopian
https://typicalethiopian.com/ethiopian-books/

የ መፅሀፍት ዓለም

08 Jan, 10:16


ቤዛ ኩሉ፤ ደማቁ ሥርዓት።
ለዚህ እንኳን በእግር በደረት እየተሳቡ ቢመጣስ?
***
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም - ለድሬ ቲዩብ)

ልደትን ላሊበላ መጣሁ። የሀገሬ ሰው "ሞትና ላሊበላ አይለመድም። ሁሌም አዲስ ነው።" ይላል። ላሊበላን በልደት ደርሶ ላየው "ሞትስ ይለመዳል፤ ሁሌም አዲስ፣ ላሊበላ እንጂ" ማለቱ አይቀርም።

በላስታ ደብረ ሮሐ የገና በዓል እጅግ በተለየ ደማቅ መንፈሳዊ ሥነ-ሥርዓት እንደ ሺህ ዓመታቱ ሁሉ ዛሬም በድምቀት ተከብሯል፡፡ ገና ቃሉ የግሪክ ነው፡፡ ገናና እንደማለት ነው፡፡ ገናናው የልደት በዓል በገነነው ስፍራ ሲከበር ማየት መታደል ነው።

ያለፈውን ሳምንት ላሊበላ እንግዳ ስትቀበል ሰንብታለች፡፡ ከመላ ኢትዮጵያ የሚመጣ እንግዳን እግሩ ላይ ወድቃ የምትቀበል መናገሻ። "ላሎ መንገዱን አለስልሰው" እያሉ ብዙዎቹ ለቀናት በእግራቸው ተጉዘው ደርሰዋል። ቤዛ ኩሉን ለተመለከተ እንኳን በእግር በደረትስ ተስቦ ቢመጣ ማለቱ አይቀርም።

እንደ ሰብአ ሰገል ልደቱን ለማብሰር፤ ተራራ ሰንጥቀው፣ ወንዝ አቋርጠው፣ ሜዳ ገስግሰው፣ የሚመጡትን እንግዶች ላስታ መሬት ወድቆ፤ እግር አጥቦ ይቀበላቸዋል፡፡
ሰኔ 12 ቀን የሚነበበው ስንክሳር “ወደ ቤተ መቅደስህ የሄደ በኢየሩሳሌም ወደአለው ቤተ መቅደሴ እንደሄደ ይሆንለታል።” ይላል። እናም የሀገሬ ሰው ዳግማዊ ኢየሩሳሌም ወደሚለው ደብረ ሮሐ በዚህ ስሜት ይጓዛል።
ይህንኑ ሀሳብ ዶክተር ስርግው ሀብለ ስላሴ የአማርኛ የቤተ ክርስቲያን መዝገበ ቃላት ላይ አስፍረውታል። ስርግው "ቅዱስ ላሊበላ እነኚህን አብያተ ክርስቲያናት በአንድ አካባቢ ለማሠራት ያቀደበት ምክንያት ለኢትዮጵያ ተሳላሚዎች ቅድስት ሀገርን ለመፍጠር ነው" ይላሉ።

ቀሲስ ዶክተር መንግስቱ ጎበዜም ላሊበላ በሚለው መጽሐፋቸው አብያተ ክርስቲያናቱን በሮሃ ላይ ያነፀበት ዋናው ምክንያት እየሩሳሌምን ኢትዮጵያ ላይ ለመድገም አስቦ መሆኑ ከኢየሩሳሌም ጋር የነበረውን ግንኙነት ብቻ ሳይሆን በአካል ማወቁን ያጠይቃል። ይሉናል።

የቅዱሱና የምድራዊው ንጉሥ፤ ከሰማያዊው ንጉሥ ልደት ጋር የገጠመበት በዓል፡፡ የእናቶች ዜማ አስተጋባ፡፡ ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት እያሉ ሀገራቸው ያዩትን የነፍስ ቦታ ድንቅ ስራ ያወድሳሉ። እኔም ነፍሴን ሀገሯን አሳየኋት።

ቅዱስ ላሊበላ እንኳን የልደት በአዘቦትም መድረስ ተአምር ነው፡፡ ገና ሲሆን ሁሉ ነገር ይለያል፡፡ ድባቡ አይረሴ ነው፡፡ የካህናቱ ያሬዳዊ ዜማ እድሜ ልክ ተከትሎ ይኖራል፡፡
እነኚህ ሩቅ ተጓዥ የሀገሬ ሰዎች፣ ሞትና ላሊበላ አይለመድም የሚሉ፤ በዓመት በዓመት አይተውት ደግሞ መልሶ እንግዳ የሚሆንባቸው፤ እናም "ዓይኔ ዓለም አየ እግሬ ደርሶ" ይላሉ፡፡ እንኳን እግሬ ደረሰ። እንኳን መጣሁ። እንኳን ልደት ላስታ ሆንኩ።


ቤዛ ኩሉ ልደትን ከላሊበላ ያስተሳደረ ሥርዓት ነው፡፡ ሥርዓቱ ቤተ ማርያም ይከናወናል፡፡ ቤተ ማርያም ከቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንዷ ናት፡፡ ልዩ የሚያደርጋት ቀዳሚዋም መሆኗ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ርዕሰ አድባር ይሏታል፡፡

ንጉሥ ላሊበላ እና ባለቤቱ መስቀል ክብራ መንፈሳዊ ስነ ስርዓት የሚካፈሉባት መንበረ መንግስትም ናት፡፡ ወደ ቤተ ማርያም የሚያስገቡ ሁለት በሮች አሉ፡፡ ከቤተ መድሃኒዓለም በስተምዕራብ የሚገኘው እና ቤተ ማርያምን በከበበው አለት አጥር ስር ያለው ጠባብ መሹለኪያ አንዱ በር ነው፡፡ እኔ በቤተ መድኃኔዓለም መግቢያ በኩል ቆሜያለሁ።

ከደቡብ ወደ ሰሜን አቅጣጫ በአለቱ ስር የቤተ ደናግልን ቤተ ክርስቲያን ተጠግቶ ወይም ታክኮ የሚያልፈው በር ደግሞ ሁለተኛው ወደ ቤተ ማርያም የሚያስገባ በር ነው፡፡

አራት መአዘን ቅርጽ ያላት ቤተ ማርያም ዙሪያዋን በአለት አጥር ተከባለች፡፡ ይህ አለት አጥር ማሜ ጋራ ይባላል፡፡ ማሜ ጋራ የልደት በዓል የሚከበርበት የሥነ ሥርዓቱ ስፍራ ነው፡፡ አንጋጥጬ እመለከታለሁ።

"ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ" ዝማሬው አስተጋባ።
ይህ ምሳሌው መላእክት በሰማይ እረኞች በምድር ሆነው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ በጋራ መዘመራቸውን ይወክላል።

ቤዛ ኩሉ ዓለምን ከየዓለበት የሚያመጣ ሥርዓት ነው፡፡ እነሆ ልደትም ሆነ፡፡ ሰውና መላእክት አብረው ዘመሩ፡፡

እንኳን አደረሳችሁ።
ለፎቶው ቱሪዝም ሚኒስቴርን አመሰግናለሁ።

የ መፅሀፍት ዓለም

07 Jan, 11:20




ለ መላው የ ክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለ ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓሉ በሰላም አደረሳችሁ

የ መፅሀፍት ዓለም 📚

የ መፅሀፍት ዓለም

03 Jan, 23:08


ስለ አዳም ከ አዳም

የ መፅሀፍት ዓለም

30 Dec, 12:59


Channel name was changed to «የ መፅሀፍት ዓለም»

የ መፅሀፍት ዓለም

30 Dec, 11:13


#MondayInspiration:

Haile Gerima, an Ethiopian-born and U.S.-educated filmmaker, has dedicated his career to creating and distributing films outside the traditional studio system. He gained recognition for his narrative works such as Bush Mama (1979), Ashes and Embers (1982), and Sankofa (1993).

In 1996, Gerima established the Sankofa Video and Bookstore in Washington, D.C., a cultural and intellectual hub offering opportunities for self-expression, interaction, discussion, and analysis through community events.

Gerima continues to distribute and promote his films, including his most recent festival success, Teza (2008), which earned the Jury and Best Screenplay awards at the Venice Film Festival.

Additionally, he lectures and conducts workshops on alternative screenwriting and directing both in the United States and internationally.
[From - US EMBASSY Addis Ababa]

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

27 Dec, 06:48


"የእኔ የምንግዜም ምርጥ መፃህፍት"
👤አርቲስት አበበ ባልቻ


" ለተሻለ ነገ እናንብብ"

ባለፈው ዓመት በ FM ADDIS 97.1 በተደረገው የንባብ ዘመቻ
በ አንጋፋው አርቲስት አበበ ባልቻ የተመረጡ 4ት ምርጥ መፃህፍት

📚 ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ /ደራሲ አዳም ረታ
📚 እንቅልፍ እና ዕድሜ /ደራሲ በእውቀቱ ስዩም
📚 የትሮይ ፈረስ /ደራሲ አሳምነው ባረጋ
📚 ከአድማስ ባሻገር /ደራሲ በዓሉ ግርማ

🔅የእናንተስ የምንግዜም 3ት ምርጥ መፃህፍት እነማናቸው በ COMMENT👇 ላይ ያጋሩን

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

24 Dec, 21:20


Who is your finest mind person???

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

23 Dec, 20:54


ሰላም ለ ኢትዮጵያ
🌼🔅🌼🔅🌼🔅🌼

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

23 Dec, 06:19


ናፍቆት የወለደው ናፍቆት ~ የናፍቆት ኑዛዜ
💔💔 ❤️‍🩹❤️‍🩹

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

18 Dec, 11:50


አድጌያለሁ😞😞😞

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

16 Dec, 06:02


ተነስ ተነስ ተነስ
ገጣሚ - ዘውደአክሊል

🔅መልካም የስራ ሳምንት🔅
Happy Monday

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

16 Dec, 05:29


ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ተመዝግበዋል? እንግዲያውስ ይህን ያስተውሉ።

#ፋይዳ #ፋይዳለኢትዮጵያ #Fayda #DigitalID

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

11 Dec, 15:59


Show Here

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

09 Dec, 19:16


ለ ደጃፍ PODCAST ወዳጆች
ከ ደጃፉ ይጠብቁ

Season 3
Coming soon 🔜
Check mic 🎙️🎙️🎙️

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

09 Dec, 07:21


እናንተስ ምን ትላላችሁ
Comment 👇 አድርጉልን እስቲ

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

08 Dec, 19:09


ደራሲ አዳም ረታ ከኢቢሲ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ባደረገው ቆይታ፤ "መዝሙረ ሄላዊ" የተሰኘ አዲስ መፅሐፍ ይዤ እየመጣው ነው ብሏል።

በስነፅሁፍ ዓለም ውስጥ ተፅዕኖ ለማድረግ ጥሩ ስራ አስፈላጊ ነው የሚለው አዳም፤ የመፅሃፍቱ ስያሜዎች የታሪኩን ይዘት አስታከው የወጡ ስለመሆናቸው ተናግሯል።

የአሁኑ ትውልድ ላይ የሚታየው የስነፅሁፍ መነቃቃት የሚደንቅ እንደሆነም ጠቅሷል።

"መፃፍ እንጂ መናገር ላይ እንብዛም ነኝ" የሚለው አዳም ባለትዳር እና የሁለት ልጆች አባት ነው።

የእቴሜቴ የሎሚ ሽታ መፅሀፍ ወደ ፊልም በመቀየሩ ቅር አለመሰኘቱንም ነው የጠቀሰው።

"መፅሀፍቶቼ ከተፃፉ ዘመናት በመቆጠሩ ወደ ፊልም መቀየር የሚፈልግ ካለ መቀየር ይችላል" ሲልም ተናግሯል፡፡

በሜሮን ንብረት

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

08 Dec, 18:42


ብዕሩ የማይነጥፈው አዳም ረታ በአዲስ መፅሐፍ እየመጣ ነው - መዝሙረ ሄላዊ

#Ethiopia | አንጋፋው ደራሲ አዳም ረታ በኢትዮጵያ የስነ-ፅሁፍ ታሪክ ጉልህ ሚና ካላቸው ፊት ተሰላፊዎች መካከል ነው።

መረቅ፣ ከሰማይ የወረደ ፍርፍር፣ የስንብት ቀለማት፣ እቴሜቴ የሎሚ ሽታ፣ ይወስዳል መንገድ ያመጣል መንገድ፣ አፍ፣ ግራጫ ቃጭሎች ከፃፍቸው መፅሀፍት መካከልም ናቸው።

አዳም 1977 ዓ.ም "አባ ደፋርና ሌሎች ታሪኮች" የተፃፈ መድብል ላይ የራሱን ስራዎች አበርክቶ ከህዝብ ጋር ተዋወቀ።

በመቀጠል 1981 ዓ.ም የፃፈው "ማህሌት" የተሰኘው አጭር ልቦለድ የአማርኛ የአጭር ልብወለድ ቁንጮ እንደነበርም ይነገራል።

ቋንቋ ለአንድ ደራሲ መሳሪያው እንደመሆኑ የአዳም ረታ የቋንቋ ክህሎት የሚደነቅ ስለመሆኑ ብዙዎች ይገልፃሉ።

የአዳም ድርሰቶችና እይታዎቹ አንድ ነገር ስናየው ከነበረበት ምልከታ ወደ ሌላ እይታ የመቀየርም ሀይል አላቸው።

አዳም የራሱ የሆነ የአፃፃፍ ዘዬ እንዳለውም ይነሳል።

የአፃፃፍ ዘዬው እና የሚያነሳው የሀሳብ አምድ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት እና አድናቆትን አጎናፅፎታል።

አዳም ልብወለድ ብቻ ሳይሆን ግጥሞችንም ፅፎ በተለያዩ መፅሄቶች ታትመዋል:: ያልታተሙ ስራዎች እንዳሉትም ይነገራል።

የ67 ዓመቱ ጎልማሳ አዳም ዛሬም እንደወጣት ነው። ብዙ ወጣቶችም ይከተሉታል:: አዳም ከሚኖርበት ባህር ማዶ ለእረፍት ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያዊ መጥቷል።

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

08 Dec, 07:07


ሰውመሆን ይስማው [ፊልም ሰሪ]

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

03 Dec, 17:39


ቁስለት ብርሃን
የሚገባበት መግቢያ ነው::
[ሩሚ]

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

30 Nov, 10:45


" 'ለኔ ያድርገው ለኔ' "
እንደምትል የዋህ እናት
ነፍሴ በዚህ ሰዓት
ላንቺ ሲሆን እንደሷ ናት።

[ሰሎሞን ሳህለ]

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

29 Nov, 10:51


የጋሽ ማህሙድ ዝግጅት ያጫረብኝ ጥያቄ.......
የጋሽ ማህሙድን የምስጋናና የመድረክ ስንብት ትኬት ማለቅ ተከትሎ፣ አጠገቡ ለመገኘት ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችና ከአሜሪካ ውጪ ጭምር የሚደርሱን የስልክ ጥሪወች እጅግ በሚገርም ሁኔታ ብዙ ናቸው። ብዙ ጊዜ የመድረክ ዝግጅቶች ሲሰናዱ ያዘጋጆች ጭንቀት በቂ ሰው ይመጣ ይሆን ወይ የሚለው ነው። በዚህ የጋሽ ማህሙድ ዝግጅት ላይ ያየነው ግን ከዛ የተለየ ነው። እንዳውም “ራሱ ጋሽ ማህሙድም ትኬት አላገኘም” እየተባለ ተቀልዷል።
ይሄ ሁሉ የሆነው ግን ሌላ አዲስ ነገር ኖሮ፣ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ አርቲስት መጥቶ፣ ወይም አንዳች ታምር ተፈጥሮ አይደለም። ይሄ ሁሉ የሆነው ህዝቡ ለጋሽ ማህሙድ ባለው ፍቅር፣ በዚች መድረክን በሚሰናበትባት፣ በሚከበርባት፣ በሚመሰገንባት ምሽት አጠገቡ መሆን የታሪክ ባለቤት መሆን፣ መከበር ጭምር ስለሆነ ነው።
ጋሽ ማህሙድ ዘመን፣ ትውልድና ሁነት ከማይሽረው የሙዚቃ ብቃቱ በተጨማሪ፣ ግሩም የሆነ ስበዕናው፣ ደግነቱ፣ መልካምነቱ፣ የዋህነቱ፡ ብቻ ሰውነቱ በሁሉም ሰው ልብ ውስጥ እንዳስገባው ለመናገር ምስክር መጥራት አያስፈልግም።
ይሄ ክስተት ዛሬ ላይ እኛ እንዲህ ያለውን ክብርና ፍቅር የሚያስገኝ ስራ ምን ያህል እየሰራን ይሆን የሚለውን ጥያቄ አጭሮብኛል። አሁን ካለንበት ሞያ፣ ከምናገለግልበት ቦታ፣ ከወጣንበት ማማ፣ ከተሸከምነው ሃብት፣ ከደርብነው ዝና፤ ነገ ስንወርድ፣ ስንሰናበትና ስንለይ እንደጋሽ ማህሙድ በፍቅር እንሸኛለን ወይስ "ተገላገልን” እንባላለን? ሁላችንም ራሳችንን አጥብቀን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ!
ዘመናችን በአገልግሎታችን፣ በጽናታችን፣ በበጎነታችንና በመልካም ስብዕናችን የተሰናሰለ ሆኖ ልክ እንደ ጋሽ ማህሙድ አይነት የፍቅርን በረከት ለእድሜ ማምሻችን ይሰንቅልን ዘንድ ጸሎቴና ምኞቴ ነው።

አበበ ፈለቀ

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

28 Nov, 06:14


<< ውድነሽ በጣሙ >>
..
( ሙሉጌታ ተስፋዬ )
....
እቴ እንዴት ከርመሻል
ውዴ እንዴት ይዞሻል
የሙታነት ሰገነት
አፈሩ ድንጋዩ....የመቃብር ዓለም
የቀብር ቤተ እምነት
እንዴት ነው ቅዳሴው...ውዳሴ ማህሌቱ
እንዴት ነው ገበያው...መስፈርቱ ስሌቱ
ከዚህ ከኖርሽበት ሁለን ካየሽበት
ከሰው አራዊቱ ከቀን ሰራዊቱ አለው ይሆን ነገር
አለወይ በዛብህ ያ መከራ ትርፉ
ቀይ እንዳይት ሻማ ባለ ጥበብ ዘርፉ
ምን ይላል አንዳንዴ
ያለፈ ትዝታ ድንገት ሽው እያለው
እያንጠራወዘው እየወዘወዘው
የልጅነት ሰሜት ግለቱ ንዝረቱ ግርሻ ግርሻ ሲለው
ቀዞ ሲያስተክዘው
አንዳንዴም እንደሰው እንደማንኛው ሰው
ግራ እየተጋባ እያደናበረው እያዥበረበረው
ቅጡን እያሳጣው ሌላውን አክብሮ
መድፈር ሳይሆንለት ብይን ሊያደላድል ራሱን ሊቀጥፍ
ምን ይላል አንዳንዴ
ከራሱ ተፈልሞ
ከራሱ ተጋጥሞ
ልፊያ ከንፈር ሽሚያ
አፍ ገጥሞ ጨዋታ
ደሞ ልቧን ሊቀምስ
እንደ ጭዳ ዶሮ ቆልምመው ጥለውት
ውጪ ነፍስ ግቢ ነፍስ እያንስፈሰፈው
ልብ ወዳጁን አይስት
ስብለ ሰብለ እያለ
ስሟን እየጠራ በስሟ እየማለ
ስንቱን የቅኔ ቤት ስንቱን ቤት ዘረፈው
ስንቱን ነይ ነይ ጾም በሐምሌ ገደፈው
...
.
.
.[ የሚቀጥል]

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

27 Nov, 07:20


🎶 ብናቆየው ታሪክ ቢያልፍም ትዝታ ነው [ ተረሳሽ ወይ - ጋሽ መሐሙድ አህመድ]

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

26 Nov, 07:59


ስለ ከንፈርና ስለ መሳም ከተገጠሙት ግጥሞች ውስጥ ልቤ አብዝቶ ከሚወዳቸው አንደኛው ግጥም ይሄ ነው
ጄኒ ስማኛለች

ያኔ ስንገናኝ
ጄኒ ስማኛለች
ጄኒዬ የኔዋ፤
ከወንበሯ ዘላ ከመቀመጫዋ።

... ዋ ጊዜ አንተ ሌባ!
ባሕረ - መዝገብህ ስንቱን ሸጋ ጣፈው?
መቼም ቆንጆ ስትወድ እንዳንድ ነገር ነው።
ሆኖም እንካ መዝግብ እኔም ላክልልህ፤
እንዴት እንደታከትኩ
እንዴት እንደከፋኝ
አዱኛና ዝና እንዴት እንደራቁኝ
ማርጀት መጃጃቴን በኮጲህ ጻፍ ዘግብ
ግን እንዳትዘነጋ፥ የሚከተለውን ጨምርና ክተብ ፦
ጄኒ ስማኛለች።

Jenny kissed me.

(by LEIGH HUNT)

Jenny kissed me when we met,
Jumping from the chair she sat in;
Time, you thief, who love to get
Sweets into your list, put that in:
Say I'm weary, say I'm sad,
Say that health and wealth have missed me,
Say I'm growing old, but add,
Jenny kissed me.

ጋሽ ነብይ፤ ከሌይ ሀንት የተረጎመው!

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

25 Nov, 05:33


ማህሌት / mahlet
ደራሲ - አዳም ረታ
ዘውግ - ልብወለድ

❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

22 Nov, 06:29


የ መፅሀፍት ዓለም

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

17 Nov, 08:59


ሰው ሁሉ ለአገሩ የሚሞተው መንደሩን እያለመ ነው

አጥቢያ / axbiya
ደራሲ - ዓለማየሁ ገላጋይ

Download ⬇️

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

15 Nov, 10:26


There are worse crimes than burning books,
One of them is not reading

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

30 Oct, 09:40


A Banker is a fellow,who lends you his umbrella when the sun is shining ,but wants it back the minute it begins to rain

#ቤባንያ
የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

መልካም ቀን 🏖️

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

28 Oct, 03:35


📍 Location ADDIS ABABA
📲 0974807893
Contact us @Digitalmarket0617

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

22 Oct, 05:07


Download PDF

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

16 Oct, 15:01


The Man Who Never Was
ይራሲ - Ewen Montagu
ሰላዩ ሬሳ
ተርጓሚ - ማሞ ውድነህ
አስገራሚው የእንግሊዞች የስለላ ታሪክ
❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

11 Oct, 08:41


📍 Location ADDIS ABABA
📲 0974807893

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

10 Oct, 06:50


እናት
ደራሲ - ማክሲም ጎርኪ
ተርጓሚ - ዮሐንስ ክፍሌ ዳዲ

❇️ Download PDF

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

06 Oct, 14:06


ከመፅሐፉ የተቀነጨበ ...
የሸክላ ማጫወጫው አጠንጥኖ ላንቃውን ከፈተ ...🎵" የሺ ሀረጊቱ የክቲቱ ..."🎵
ሌሊት ሆኗል፡፡ የሺ ሀረጊቱ ክፍሏ ውስጥ አልጋዋ ላይ እንደ ተኛች ትገላበጣላች፤ እንቅልፍ ሊወስዳት አልቻለም። ውስጧ የተፈጠረው ስሜት ከባድ ነበር። ተራምዳ መስኮቱን ከፈተችው ... ቀዝቃዛው አየር ፈቷን ሲገርፋት ነፃነቷን አረጋገጠላት።
🎵 " የሺ የሺ የሺ ሀረጊቱ ..." 🎶
Download

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

03 Oct, 16:42


ምርጥ ምርጥ የአማርኛ መፅሀፍቶችን በ pdf በአንድ የቴሌግራም ቻናል ያግኙ።

ቴሌግራም 👉 የመፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም
ዌብሳይት 👉 Ethiopian books

ለአንባቢ ዘመድ ወዳጅዎ ሼር ያድርጉ።

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

03 Oct, 08:00


ከመፅሐፉ የተቀነጨበ ...
' ፈገግ አልኩላት ፈገግ አላች! ፈገግታዋ ዉስጥ እርካታ ከነ ሙሉ ክብሩ ነግሷል። በብልጣብልጥነት አልታገለችም፤ ያደረገችው ብቸኛ ነገር ማፍቀር ነበር። በዝምታ አፈቀረችኝ::
"ሐኑን አይኝ ! ቀና ብለሽ እይኝ! አፍቅርሻለሁ!!!... መጀመሪያ ቡና ልታደርሽልኝ ወደ ቤቴ ከገባሽበት ቀን ጀምሮ እስካሁን ልቤ ላይ ያለሽው አንቺ ብቻ ነሽ"
... ሐኑን-ጣፋጭ ሕመም
👇Download

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

16 Sep, 12:26


ቀኝ እጁ ቀኝ እጇን፥ ትኩስ ትንፋሹ ጆሮዋን፥ አንገትዋን ሲነካት፥ ልዩ ሙቀት፥ የወንድነቱ ሙቀት፥ በዚህ ሁሉ በኩል፥ እንደ ኤሌክትሪክ ማዕበል በሰራካላትዋ ጎርፎ አጋላት። ያ ለምለም፥ ያ ውብ አካላትዋ ከማር ሰፈፍ እንደ ተሰራ ሁሉ፥ ሙቀት እንደሚፈራ ሁሉ፥ ትንሽ በትንሽ መቅለጥ፥ ትንሽ በትንሽ መፍሰስ ጀመረ። ሰውነቷን መግዛት፥ በሰውነቷ ማዘዝ ተሳናት። ወዲያው ሳታስበው፥ ሳታዝዘው፥ ራስዋ ቀና፥ ፊቷ ወደ ፊቱ ዘወር አለና፥ አፏ ተከፍቶ የሱን አፍ ፍለጋ ሲሄድ በመንገድ ተገናኙ። ከዚያ እጆቿ አንገቱን፥ የሱም እጆች የሷን ተጠምጥመው ይዘው፥ አፏ ባፉ፥ አፉ ባፏ ውስጥ ቀለጡ። እሱ በሷ፥ እሷ በሱ ውስጥ ጠፉ። […] ወደ ሌላ ዓለም፥ ወዳንድ አዲስ ዓለም ገቡ።
ትንሽ ዝም ብለው፥ ዓይን ላይን ተያዩና፥ ደግሞ እንደገና ዓይናቸውን ከድነው፥ ደግሞ እንደገና አፍ ላፍ ተያይዘው፥ ደግሞ እንደገና አንድ ላይ ተዋህደው፥ ደግሞ እንደገና ወዳገኙት አዲስ ዓለም ሄዱ።
—ፍቅር እስከ መቃብር | ከሐዲስ ዓለማየሁ | ገጽ 317-318

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

23 Apr, 09:40


World Book Day 📚📖📚
23 APR

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

06 Apr, 15:15


ብዕሩ አትነጥፍም🙏

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

30 Dec, 23:39


A Banker is a fellow,who lends you his umbrella when the sun is shining ,but wants it back the minute it begins to rain

#ቤባንያ
የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

መልካም ቀን 🏖️

የ መፅሀፍት 🇪🇹 ዓለም

24 Dec, 07:09


እንኳንም የማንችለው ፍቅር ተጫነን