ሙርሰል ሰይድ ጨፌ @murselseid Channel on Telegram

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

@murselseid


ሙርሰል ሰይድ ጨፌ (Amharic)

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ በአማርኛ የተጠናቋልና ከወገን እና ከስርዓቱ ጋር ያደርጋል። ይህ ሶስተኛ ርእስ በሙሉ እየተመረዘ እና ማጠናከር ለሚችሉ ሰዎች፣ በእርስዎ በሚገኝ ውይይት በመመልከት ለሶት ትምህርትና የተማረ መጽሀፍ በተዘጋ መረጃዎችን እና መረጃዎችን በተመለከታችው እንገናኝ። ሙርሰል ሰይድ ጨፌ የሰይድ ታሪኩን ለመጠቀም እና ለሶስተኛ ርእስ የተገለፀበት ስለናን ፍቃዱን ለመቃረብ እና ለማዘጋጀት የሚያችል ህገ መድረሻን እና በሀገሪታችን መቆየታቸውን ማቅረብ ያለብን መረጃዎች ብቻ ነን።

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 10:45


ተቀድማችሗል
ከዉጫሌ ጀመአዎች መካከል አንዷ እህታችን ከላይ የለጠፍኳትን ግጥም በፍጥነት ወደ ፅሁፍ ቀይራ ልካልኛለች።
ጀዛሀሏሁ ኸይረን‼️
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
የሰላም ጀመአዎች

👉 የሰላም  ጀመአ   ወጣት  አዛውንቱ
👉  ሴራ ተሰርቶበት ተዋሽቶበት ስንቱ
👉 ተውሂድ   በመያዙ  በሱና መፅናቱ
👉 መስጅደሰላምን ለሶላት መክፈቱ
👉  መረጃን   ሳያዩ   ሳይመለከቱ
👉 ዲናቸውን ስተው ስንቶች ሆኑ ከንቱ
👉 ሀሜትን  ሳይፈሩ  ከዲን  ሳይገቱ
👉 ሰላምን አስዋቧት ምንም ሳይታክቱ

👉  መስጅድ ሁና ሰላም የተውሂድ ባንዲራ
👉 ሱንዮች  አስዋቧት  ባንድላይ   በጋራ
👉  በበደዶው ምድር በደሽኞ ስፍራ

👉  የበደዶ ምድር የምንጮች መነሻ 
👉 ገና ትሆናለች የተውሂድ መንገሻ
👉 የሽርክ መቃብር የባጢል መፍረሻ
👉 የጀግና መፍለቂያ የሱና ማደሻ 
👉 ሽርክን የሚፈቱ  የተውሂድ መዶሻ

👉 እንደ በደዶ ምንጭ  እንደ ውሀዉ ፈሶ
👉 ተውሂድን አንግቦ ሽርክን አፈራርሶ
👉 ባጢልን በመርገጥ ሀቅን ተንተርሶ

👉  ለነብያት መንገድ ለመንሀጀሰለፍ
👉 እንኳን ሀሜት ቀርቶ ቢመዘዝብኝ ሰይፍ
👉 ቢከዳኝ ቤተሰብ ሂዝቢያም ቢሰለፍ
👉 ጥፍሬንም ቢነቅሉት ቆዳዬም ቢገፈፍ
👉  አንገቴንም ቢያንቁት ህይወቴ እስከምታልፍ
👉 እጄንም ቢቆርጡት እግሬ ቢኮለተፍ
👉  በየ ኮንፈረንሱ ውሸት ቢለፈለፍ
👉 መቼም አልመለስ ከመንሀጀ ሰለፍ

👉 ጀመአው ሲነሳ ገና ከጅምሩ
👉 ወንድሞች  ሲበዙ በሱና እያማሩ
👉  ተራ ወሬ ንቀው ኢልም እየተማሩ
👉  ሽርክ እና ቢድአን መቅበር ሲጀምሩ
👉  እንበትነው ብለው ሸይጦኖች መከሩ
👉 ሀቅን አለባብሰው ውሸት  ዘረዘሩ
👉 ኢልም ሳይኖራቸው ተውሂድ ሳይማሩ
👉 ስንቱን ቀጠፉብን ስንቱን ደሰኮሩ
👉 ለዲን ጠበቃ ነኝ እያሉ ጎረሩ
👉 የሰላም ወጣቶች ፊትም አላዞሩ
👉 መስጅዱን ከፈቱ ችቦውን አበሩ

👉 በሂዝቢዮች ውሸት የማይበገረው
👉 ለሀሜት ለውሸት ቦታ የማይኖረው
👉 ከመንሀጀ ሰለፍ ፊቱን ያላዞረው
👉 መንሀጁን በሁጃ የሚዘረዝረው

👉 ከቢድአ እርቀህ ከሽርክ ኮተታ
👉  መንሀጅህ ላይ ጠንክር በል ወንድሜ በርታ 
👉 መንሀጅህ ላይ ጠንክር በል ወንድሜ በርታ 

👉 ጥርዬን ላስተላልፍ ለሙስሊም ወገኔ በተለይ ወጣቱ
👉 ነገ ሳትፀፀት ሳይመሽብህ ወቅቱ
👉 ዛሬ መስጅድ ግቡ በዲናችሁ በርቱ
👉 ዛሬ መስጅድ ግቡ በዲናችሁ በርቱ

👉 እህቴም ጠንክሪ ኒቃቡን አጥብቂ
👉 በስውር ተኩላዎች እንዳትነጠቂ
👉 መንሀጅሽ ላይ ፅኒ ዲንሽን እወቂ

👉 ወንድሜም አደራ ይብቃህ መሸወዱ
👉 ፊልም እና ሙዚቃ ነሺዳ መውደዱ
👉 በቁማር በዝሙት በሱስ መጠመዱ
👉 በዚህ አያስኬድም የጀነት መንገዱ 
👉በዚህ አያስኬድም የጀነት መንገዱ 

👉የመስጅድ ዛውያ አማና ወሳጁ
👉 መስጅዱ ባዶ ነው የት አለ ሰጋጁ
👉 ዛውያው ወና ነው የት አለ ሰጋጁ
👉 ቀብርህ ሳይቆፈር ሳይዘጋ ደጁ
👉 አማናህን አድርስ ሳይፈርድህ ፈራጁ
👉አማናህን አድርስ ሳይፈርድህ ፈራጁ

👉 ውድ ወገኖቻችን እዚህ የመጣችሁ
👉 ፅናቱን ይስጥልን ከፍ ይበል አጅራችሁ
👉 እንወዳችኋለን አላህ ይውደዳችሁ
👉 ከጎናችን ሁኑ አለን ከጎናችሁ
👉 ግጥሜን በዚህ ጨረስኩ እኔ ወንድማችሁ

👉 በስተመጨረሻ  ሶላትና ሰላም
👉በነቢ ላይ ይዉረድ ወሰላሙ አለይኩም

በወንድም ሁሰይን በደዶ 8/3/2017
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 08:15


👌ወንድማችን አቡ ረያን ጥሩ ዳሰሳ አድርጓል አዳምጡት!!

🔖 ዑዝር ቢል'ጀህል

👉መስአላው ኺላፍ አለበት ስንል እየቀጠፍን ነውን? ወይስ ዑለማኦች ያረጋገጡት እውነታ ነው?

👉ዑዝር ቢል'ጀህል ባለመኖሩ እውነት ኢጅማዕ አለን?

👉ሙስጠፋ ኢጅማዕ አለ ሲል እየቀጠፈ ነው? ወይስ የሚያነበውን የማይረዳ ጃሂል ሁኖ ነው?

【 ክፍል 4 】

በወንድም አቡ ዒምራን ህዳር 6/2017
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 04:53


.
.
እስኪ ማነህ ጊዜ ያለህ ይህችን ግጥም ወደ ፅሁፍ ቀይረህ በዉስጥ የምትልክልኝ?

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 04:48


አዳምጧት በጣም ደስ የምትል በትላንትናዉ እለት በተሁለደሬ ወረዳ በ 01 ቀበሌ በበደዶ የደዕወህ ፕሮግራም ላይ በወንድም ሁሰይን በደዶ የተነበበች አጭር ግጥም ነች‼️

በሙርሰል ሰይድ ጨፌ 8/3/2017
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 04:45


اتباع السنة ــــ بأخينا عبد الرحمــن ــ

ሱናን መከተል በሚል ርእስ በትላንትናዉ እለት በተሁለደሬ ወረዳ በ 01 ቀበሌ በበደዶ የደዕወህ ፕሮግራም ላይ በወንድም አብዱረህማን የተደረገ ሙሀዶረህ‼️

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 04:39


أهمية الصلاة في الاسلام ــــ بالشيخ سعيد بن إبراهيم البوقي رئيس مجلس الشؤون الاسلامية في مديرية تهولدري ــ

የሶላት አሳሳቢነት በትላንትናዉ እለት በተሁለደሬ ወረዳ በ 01 ቀበሌ በበደዶ የደዕወህ ፕሮግራም ላይ በሸይኽ ሰይድ ቡቄ ــــ የተሁለደሬ ወረዳ እ/ጉ/ም/ ቤት ሰብሳቢ ـــــ የተደረገ ሙሀዶረህ‼️

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Nov, 04:26


‏التوحيد أولا ـــ بأخيكم مرسل بن سيد الچفي ـ

👉ቅድሚያ ለተዉሂድ በሚል ርእስ በትላንትናዉ እለት በተሁለደሬ ወረዳ በ01 ቀበሌ በበደዶ የተደረገ ሙሀዶረህ‼️

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

17 Nov, 08:33


በዛሬዉ የበደዶ ፕሮግራም ላይ በአንድ ወንድማችን የተነበበች ግጥም።

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

17 Nov, 06:58


👉ሸይኽ ሰይድ ሱዳን ( የመርከዝ ኢብኑ ኹዘይመህ መስራች) የመክፈቻ ንግግር እያደረጉ ነዉ
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

17 Nov, 06:52


💥በተነጋገር ነዉ መሰረት በጧቱ በደዶ ላይ ታድመናል። ፕሮግራሙም ሊጀምር ነዉ።
በአቅራቢያ ያለችሁ ገባ ገባ በሉ‼️

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 15:15


ይሄን ልበ ቀና የገጠሬ ህዝብ ወዴ ቀናው መንገድ ከማሳዬት የዘለለ ምንም ልንለው አይገባም ባይ ነኝ!!
ከነሱ የዓቂደህ መንጋዴድ ጋር የራሳችንም ክፍተት ሊያሳስበን ይገባል!!

አሏህ ሁላችንንም ይቅር ይበለን!

ኡስታዝ ሙሀመድ ዑመር
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 11:47


...በለሊት ደውዬ...

ከወንድሜ ጋር ደወልኩ
በለሊት ነበር አስብኩ..

በለሊት ለምን ደወልክ !
አለኝ ወንድሜ ምን ሆንክ !

ተስፋ እንዳለ ልነግርህ..,,
አብሽር መከራ እንዳይሰብርህ!

አልገባኝም ቃልህ ፈፅሞ!
ምን ማለት ነው ይሔ ደግሞ!

ወንድሜ ይነጋል እሺ..
አይቀርም እንድህ ጨልሞ...!!

ተስፋ ሰጭ ወንድም አያሳጣችሁ
     .....አሚን.......

✍️በኑረዲን አል ዐረቢ
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 10:48


👉አማረኛ

👈خطبة الجمعة في علو الله تعالى فوق الخلائق.

👌واعلم أن الاعتقاد بأن الله بائن من خلقه مستو على عرشه هو ما كانت عليه الرسل والأنبياء والملائكة والسلف الصالح جميعا‼️

👈في مسجد بلال في مدينة هيق.

بأخيكم الفقير مرسل بن سيد الچفي💥
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
👉 【 የጁሙዐህ ኹጥበህ】 አምሀረኛዉ ብቻ

💥አሏህ ከፍጥረታቱ ሁሉ በላይ መሆኑን ማፅደቅ  የሩሱሎች፣ የነቢያቶች፣ የመላኢኮች፣ የሰለፎች ሁሉ እምነት ነዉ‼️

👉በሀይቅ ከተማ ቢላል መስጂድ የተደረገ💫

በሙርሰል ሰይድ ጨፌ 6/3/2017
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 09:08


👉ወንድም ዐሊይ ሚሺንጋን አዳምጡት‼️

3 ደቂቃ የማትሞላ አጭር ድምፅ

የተሁለደሬ ወረዳ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ከኢብኑ ኹዘይማ መርከዝና ከሀይቅ ከተማ እ/ጉ/ም/ቤት ጋር እየተባበሩ መስራት የጀመሩት የገጠር ደእዋ እንቅስቃሴ እጅግ ደስ የሚልና ይቀጥል የሚያሰኝ ነዉ‼️

ከዚህ መልካም እንቅስቃሴ ጀርባ ያላችሁ ወንድምና እህቶች በሙሉ አሏህ የኸይርን በር ሁሉ ይክፈትላችሁ‼️

ገጠር ለገጠር እየዞሩ ደእዋ ለተጠማዉ ለየዋሁ የገጠር ማህበረሰብ ኢስላምን አስተምሮ መምጣት የነቢያቶች የተእኮ ምክኒያት ነዉ።

በተለይ በየሄዳችሁበት ለተዉሂድ ቅድሚያ የምትሰጡት ነገር ይበል የሚያሰኝ ነዉ‼️

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 08:32


خطبة الجمعة في علو الله تعالى فوق الخلائق.

👌واعلم أن الاعتقاد بأن الله بائن من خلقه مستو على عرشه هو ما كانت عليه الرسل والأنبياء والملائكة والسلف الصالح جميعا‼️

👈في مسجد بلال في مدينة هيق.

بأخيكم الفقير مرسل بن سيد الچفي💥
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
👉 【 የጁሙዐህ ኹጥበህ】 ዐረበኛዉ ብቻ

💥አሏህ ከፍጥረታቱ ሁሉ በላይ መሆኑን ማፅደቅ የሩሱሎች፣ የነቢያቶች፣ የመላኢኮች፣ የሰለፎች ሁሉ እምነት ነዉ‼️

👉በሀይቅ ከተማ ቢላል መስጂድ የተደረገ💫

በሙርሰል ሰይድ ጨፌ 6/3/2017
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 08:22


የደዕወህ ፕሮግራም ግብዣ‼️‼️

👉እነሆ ሳምንታዊዉ የገጠር ደዕወህ እንቅስቃሴ 01 በደዶ ላይ ደርሷል።

👉ከተሁለደሬና ከሀይቅ ከተማ መጅሊሶች ጋር በመተባበር በመርከዝ ኢብኑ ኹዘይመህ ኢስላሚክ ሴንተር አዘጋጅነት በገጠር ቀበሌዎች የሚደረገዉ የደዕወህ ፕሮግራ 01 ቀበሌ በደዶ ላይ የፊታችን እሁድ 08/03/2017 ከጧቱ 2:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

ተጋባዥ ዳዒዎች
👇👇👇
① ሸይኽ ሙርሰል ሰይድ ጨፌ 👉አተዉሂዱ  አወለን
② ሸይኽ ሰይድ ኢብራሂም ቡቄ 👉አሀሚየቱ ሶላት
③ አብዱረህማን አደም 👉 ኢቲባዑሱነህ 
④ ሸይኽ ሀሚድ ዐሊይ 👉ተቅወሏህ

በሚሉ ርእሶች ተዘጋጅተዉ ይጠብቋችሗል።

👌በየአካባቢያችሁ ሰዎችን በማነሳሳትና በማስታወስ  እንድትታደሙ ሁላችሁም ተጋብዛችሗል‼️

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Nov, 03:11


💥العذر بالجهل
بأخينا العزيز ابن منور ــ حفظه الله تعالى ـــ‼️

➦ዑዝር ቢል ጀህል

🎙በኡስታዝ ኢብኑሙነወር

{ ክፍል 4 }


👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

15 Nov, 16:50


👈تعلــــــــــــــــم ثم تكلــــــــــــــــــــم

ولاتتعجل إلى الكلام قبل أن تتعلــــــــــم‼️

👉ተማር ከዚያም ተናገር ከማወቅህ በፊት ለመናገር አትጣደፍ‼️

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Nov, 10:52


👉{ የቸኮለች አፍስሳ ለቀመች }

💫ጭነት የቀለለዉ መኪናና እዉቀት የቀለለዉ ሰዉ ተመሳሳይ ናቸዉ
ሁለቱም መንጓጓት ያበዛሉ!! ከልክም በላይ ይክለፈለፋሉ!!

💫በተቃራኒዉ በደንብ የጫነ መኪናና እዉቀትን የታጠቀ ሰዉ ተመሳሳይ ናቸዉ። ረጋ ብለዉ ይሽከረከራሉ ለአደጋ የመጋለጥ እድላቸዉም ያነሰ ይሆናል!!
ሰከን በል ወንድሜ!!

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Nov, 10:39


قال حذيفة:
وإياك والتلون في دين الله‼️ فإن دين الله واحد
👉አደራህን በአሏህ ዲን ላይ መለዋወጥን ተጠንቀቅ! የአሏህ ዲን አንድ ነዉና ይላሉ ሁዘይፈህ!!
እንድህ ነበር ሰለፎቻችን በዲን ላይ መለዋወጥን ሲፀየፉና ሲያስጠነቅቁ የነበረዉ‼️

👉ሙስጦፋ አብዲላህ ግን ባለፉት አስርት አመታት ዉስጥ ብቻ ስንት ጊዜ ተከረባበተ? ስንት አቋምስ አሳየን?
አሁን ደግሞ የህየል ሀጂሪይ ላይ መዝመት ጀምሯል።

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Nov, 07:39


—————— { እነ ቆርጠህ ቀጥል }

💥ሰሞኑን እንደ አድስ እየተራገበ ባለዉ የአልኡዝር ቢል ጀህል ጉዳይ የሸይኽ ፈዉዛንን ድምፅ እየቆራረጡና እየቀጣጠሉ ሸይኹ ኡዝር ቢልጀህል የለም ብለዋል እያሉ የተለመደ ቅጥፈታቸዉን የሚነዙ የኢንሷፍ ደሀዎች እንዳይሸዉዱህ ጠንቀቅ በል!!

💫በእርግጥ የሸይኽ ፈዉዛን ንግግር ደሊል አይሆንም። ቢሆንም ግን የእሳቸዉም አቋም ይህ ነዉ እያለ ከፊት ከሗላ ቆራርጦ እያቀረበ እንዳያምታታህ!!

ثم اعلم بأن الحكم على الناس شديد‼️

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Nov, 07:34


في هذا المسجل مع الجمهور في قضية التكفير المعين!
(الشيخ صالح الفوزان  حفظه الله )

በግለሰብ ላይ ኩፍርን የሚበይነዉ
( እንደሙስጦፋ አብደላህ ያለ ) ተራ ግለሰብ ነዉ ?
ወይስ የእዉቀት ባለቤቶች?

💥መልሱን ከሸይኽ ፈዉዛን ስሙት ሀፊዞሁሏሁ ተዓላ

ኡዝር ቢል ጀህል የለም ያልከዉ ወንድሜ ይህችንም ስማት!!

( ክፍል 2 )

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Nov, 03:54


مالفرق بين التكفير المعين والتكفير بالقاعدة والعموم
الشيخ العلامة محمد أمان الجا
مي .......

👉 ኡዝር ቢል ጀህል የለም ያልከዉ ወንድሜ!!

እስኪ ይህችን የሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚን ንግግር አዳምጣት !! ከዚያም ዉሳኔዉ የአንተ ነዉ!

( ክፍል 1 )

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

03 Nov, 16:08


ጌታየ ሆይ በምኗም የማልፀፀትባትና በምኔም የማትፀፀትብኝን!
በድኔ ጉዳይ ላይ የምታግዘኝንና የማግዛትን የምትወደኝንና የምወዳትን!
የትዳር አጋር ለግሰኝ!!

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

30 Oct, 16:20


በአዲስ አበባ ከተማ በአለባበስ ምክንያት የታገዱ ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጠይቋል።

በአዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኙ አራት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች “በኒቃባቸው ምክንያት” ከትምህርት ገበታ መታገዳቸው በሚዲያዎች ሲሰራጭ ቆይቷል።

ይህን ተከትሎ ምክር ቤቱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ትናንት በጻፈው ደብዳቤ፤ ካለፉት ሁለት ሳምንታት ወዲህ በአዲስ አበባ በሚገኙ እንዳንድ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ በአለባበሳቸው ምክንያት “ጫናና እንግልት” እየደረሰ ነው ብሏል።

👉መረጃዉ ከዋሱ ሙሀመድ ገፅ የተቀዳ ነዉ

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

30 Oct, 09:24


ከሐጁሪ ጋር በተያያዘ
~
ሸይኽ የሕያ አልሐጁሪ የየመን ዓሊም ነው። በየመንም ውስጥ ከየመንም ውጭ ከብዙ ዓሊሞች ጋር አለመግባባት ውስጥ መግባቱ ይታወቃል። በዚህ የተነሳ ጠንካራ ውንጀላዎችን ተወራውረዋል። አንዳንዶቹ ሂሶች ታዲያ ልክ ያለፉ ናቸው። የሚታዩ ትችቶች ድንበር ማለፍ የለባቸውም ወይ? የሚለውን ማሰብ ራስን ከጥፋት ለመጠበቅ ይጠቅማል። ለሐጁሪ በመደገፍ ሌሎች ላይ ድንበር ማለፍ እንደማይገባ ሁሉ በሐጁሪም ላይ እንዲሁ በጥላቻ ድንበር ማለፍ አይገባም።
1- እንደተሳሳተ አምኖ የተመለሰባቸውን ጉዳዮች ለትችት ማንሳት ድንበር ማለፍ ነው። ይሄ በዚህ ዘመን ብዙዎች ላይ የሚታይ አስቀያሚ ባህሪ ነው። አንድን ሰው በተመለሰበት ጉዳይ መወንጀል የራስን ነውረኝነት ነው የሚያጋልጠው።
2- ፊቅሃዊ ስህተቶችን ወይም ልዩነቶችን የመንሀጅ ወይም የዐቂዳ ስህተት ያክል ማስጮህም ተገቢ አይደለም። በፊቅህ ጉዳይ ላይ ሌሎች ወገኖች ዘንድ ስህተት ተብሎ የሚቆጠር አቋም የሌለው ማን አለ?
3- በሌሎች ዓሊሞች ጭምር የሚስተጋቡ አቋሞችን ሐጁሪ ሲናገራቸው ጊዜ በተለየ ማራገብም ከሚዛናዊነት የራቀ አካሄድ ነው። በአንድ ጉዳይ የተለያየ መስፈሪያ መጠቀም አይገባም።
4- በግልፅ የዐቂዳ ጥመቶቻቸው የተነሳ ከአህለ ሱና አቋም እጅግ የራቁ ከሆኑ አንጃዎች በላይ ጥላቻ መደቀንም ሌላ ስህተት ነው።

ይህን ማለቴ የሚያስከፋቸው አልፎም ነገር በመጠምዘዝ ያልተባለውን እየለጠፉ የሚጮሁ ሊኖሩ ይችላሉ። እነዚህን ጉዳዮች በልክ መያዝ ራስን ነው የሚጠቅመው። በማንም ላይ ድንበር ልናልፍ አይገባም። በጥላቻም ይሁን በውዴታ ድንበር ማለፍ ራስን ነው የሚጎዳው።
በተረጋገጡ ጥፋቶች ወይም ስህተቶች ላይ እርምት መስጠት ያለና የነበረ ነው። ሐጁሪም ሆነ ሌላ የሚበልጥም የሚያንስም ማንም አካል ከሂስ በላይ አይደለም። ኢማሙ ማሊክ "ሁላችንም አራሚዎች እና ታራሚዎች ነን" ይላሉ።
አላህ ሐጁሪን ከክፉ ይጠብቀው። የሳተውን ያቃናው። ከዑለማኦች ጋርም ያግባባው።
=
በ ኡስታዝ IbnuMunewor
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

30 Oct, 09:21


ስለ ፎቶ እና ቪዲዮ
(ለብዙኛ ጊዜ)
~
ለተለያዩ አላማዎች ፎቶ እና ቪዲዮ መጠቀምን በተመለከተ፡
- በደፈናው የከለከሉ ዓሊሞች አሉ።
- በደፈናው የፈቀዱም አሉ።
- ለደዕዋ፣ ለእርዳታና መሰል ስራዎች ለይተው የፈቀዱም አሉ።
- ለአስገዳጅ ሁኔታዎችና አንገብጋቢ ጉዳዮች ግን ሁሉም ይፈቅዳሉ።

* አንድ ሰው በደፈናው ፎቶ እና ቪዲዮ መጠቀም ክልክል እንደሆነ በማመኑ ብቻ በጠርዘኝነት የሚሳልበት ምንም አግባብ የለም።
* በሌላ በኩል በደፈናው የሚፈቅድን ሰው በዚህ ሰበብ መንሀጁን ጥያቄ ውስጥ ማስገባትም የሚያስኬድ አይደለም። መተራረሙና የሚያምኑበትን ማሳየቱ ያለና የነበረ ነው።
ከዚህ አልፎ አንድ ሰው ስሜቱን ተከትሎ እንዳይሆን እንጂ በጉዳዩ ላይ የቀደመ አቋሙን መቀየሩ ፈጽሞ የሚያስተቸው አይደለም። እንዲያውም መነጋገሪያ የሚሆን ርእስም አይደለም። በየትኛውም ርእስ ላይ የሚያጋጥም ነው። በአንድ ጉዳይ ላይ ከአንድ በላይ አቋም ያንፀባርቁ በርካታ ዓሊሞችን መዘርዝር ይቻላል። ይሄ ጠለቅ ያለ እውቀት የሚፈልግ አይደለም። የኢስላማዊ እውቀትን ሀ ሁ ያንቧተረ ሁሉ የሚረዳው ነው። ችግሩ የወጣው ጉዳዩ ለመፈራረጃ በመዋሉ ምክንያት ነው።
ለራሴ ከልካዩ የተሻለ ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ አምናለሁ። ለሐጃ መጠቀሙ ይቻላል ብዬ ስለማስብ ከፊትም ጀምሬ ለተለያዩ ጉዳዮች ላይ ማስረጃ አድርጌ አያይዛለሁ። በኛ ሃገር ተጨባጭ በደፈናው ከልካዮቹም ይህንን ሲያደርጉ ማየት የተለመደ ነው። በምስል ምክንያት ሰዎችን የሚነቅፉ ሆነው ሳለ የሚጠሉትን አካል ለማብጠልጠል የሚጠቅም ሆኖ ካገኙት ፎቶ አያይዘው ረድ ሲያደርጉ ይታያሉ።

መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው።
1ኛ፦ ጉዳዩን ስሜትን ሳይሆን መረጃን ተከትሎ አቋም መያዝ ነው።
2ኛ፦ ምርጫችን የትኛውም ቢሆን ጉዳዩን ለብሽሽቅና ለመበቃቀል ሳይሆን አላህን በማሰብ ዓሊሞቹ በሚይዙት መጠን መያዝ።

ኒያው መማማር የሆነ ሰው በአደብ ሃሳብ መሰንዘር ይችላል። ከዚህ ውጭ የሆነን ሃሳብ እንዳስፈላጊነቱ ልሰርዝ እችላለሁ።

=
በ IbnuMunewor
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

28 Oct, 19:32


1ኛ፦ አሉባልታ ሳይሆን ትልቁ ሺርክ እንደሚፈፅም የተረጋገጠን ኢማም ተከትለህ አትስገድ።

2ኛ፦ የተሻለ አማራጭ ካለህ ጥፋቱ ሺርክ ላይ ባይደርስ እንኳ ቢድዐ ያለበት ሰው ባትከተል የተሻለ ነው።

3ኛ፦ ተጨባጭ ምክንያት በሌለበት በግል ወይም በቡድን ስለተደባበርክ ብቻ አንድን ሰው አልከተልም አትበል። ዲንን ለብልሹ አመልህ ማወራረጃ አታድርግ። በውሃ ቀጠነ ጀማዐ አታሳልፍ፤ ጀማዐም አትገንጥል።
=
በ IbnuMunewor
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

24 Oct, 17:09


የኢትዮጵያ ነገር እዚህ ደርሷል
~
መርካቶ ሸማ ተራ ተከስቶ በነበረው አውዳሚ የእሳት አደጋ ወቅት አንዳንድ የእሳት አደጋ አጥፊ ቡድን አባላት ከባለሱቆች ጋር የገንዘብ ድርድር ሲያደርጉ እንደነበር ሰምቻለሁ፣ ከአንድ እና ከሁለት ሳይሆን 8 ሰዎች አረጋግጠውልኛል

በስፍራው ከደረሱ በኋላ እሳቱን ከማጥፋት ይልቅ "ማንን ነው ምናናግረው?" በማለት ለረጅም ደቂቃዎች ማጥፋት እንዳልጀመሩ እነዚህ የአይን እማኞች ይናገራሉ።

"ማለት የፈለጉት ብር እንዲሰጣቸው ከማን ጋር ነው ምንደራደረው ነው። ይህ ነገር የተለመደ ቢሆንም ይሄ ሁሉ ንብረት እስኪወድም ግን በዚ ደረጃ አይመስለኝም ነበር" ያለኝ አንድ የአደጋው ተጎጂ ቤተሰብ ይህን መረጃ በስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች እንደሚያውቁ ነግሮኛል።

መሠረት ሚድያ ደግሞ በደረሰው መረጃ በስፍራው ቀድመው በአምቡላንስ የደረሱ የእሳት አደጋ ቡድን አባላት 4 ሚልዮን ብር በመቀበል በድርድር ተስማምተዋል።

ብር ከፋዮቹ በጊዜው የነበሩ የሱቅ ባለቤቶች ሲሆኑ የብዙ ሚሊዮን ብር ንብረት ሱቆቹ ውስጥ ላይ ስለነበራቸው የተጠየቁትን ለመክፈል ምርጫ ስላልነበራቸው አላቅማሙም ነበር፣ ጠያቂዎቹ ደግሞ በጊዜው ቀድመው አምቡላንስ ይዘው የደረሱ የእሳት አደጋው ሰራተኞች ናቸው ተብሏል።

ይህን ድርጊት የፈፀሙት ሁሉም ሳይሆኑ በእሳት አደጋ ሰራተኞች መሀል የሚገኙ የሰው ንብረት ውድመት ሳይታያቸው እና ሙያቸውን የካዱ ጥቂቶች እንደሆኑ ይሰማኛል።

ጉዳዩን "ውሸት" ምናምን ብሎ ለማለፍ ሊሞከር ይችላል፣ የሚያዋጣው ግን አጣሪ ቡድን ወደስፍራው በመላክ እነዚህን አሳፋሪ ጥፋተኞች በህግ መጠየቅ ነው።

አሳፋሪ ነው!
(ኤልያስ መሰረት)

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

24 Oct, 07:47


اسمع أيها المتعالِ على العلماء ويا من لم تعرف قدرك............
.
.
.
.
【قم عني ولا أراك تدنو من مجلسي】

عن أبي عاصم، يقول:

سمعت سفيان الثوري، وقد حضر مجلسه شاب من أهل العلم، وهو يترأس، ويتكلم، ويتكبر بالعلم على من هو أكبر منه، قال: فغضب سفيان وقال: لم يكن السلف هكذا كان أحدهم لا يدعي الإمامة، ولا يجلس في الصدر ‌حتى ‌يطلب ‌هذا ‌العلم ‌ثلاثين سنة، وأنت تتكبر على من هو أسن منك، قم عني ولا أراك تدنو من مجلسي.

(صحيح)
المدخل للبيهقي ١٧٧٦

قلت:

غضب سفيان لله تعالى، وغضب احتراما للعلم وحملته الكبار، فكيف لو رأى سفيان رحمه الله زماننا، كيف لو رأى الشباب الفارغ الذي لم يعرف إلا بكتابات فارغة في صفحات الفيس ووسائل التواصل، وهو يخوض مع الخائضين ويعلق على كل نازلة قائلا: وأنا أرى وأنا أرى، فليتك ما كتبتَ ولا رأيتَ ولا جلستَ في الصدارة، رحم الله الإمام سفيان وأنزله منزلة الأبرار.

منقول :ــــ
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

24 Oct, 07:43


اللهم سلمنا مع السالمين نجنا مع الناجين ولا تهلكنا مع القوم الظالمين !!

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

24 Oct, 04:04


ሀቂቃ መጥፎ ጎኑ እንዳለ ሁኖ የሶሻል ሚዲያ ጥቅም ቀላል የሚባል አይደለም።

በአማራ ክልል ከአንድ አመት በላይ የኢንተርኔት አግልግሎት በማቋረጡ ምክኒያት ከብዙ ወንድምና እህቶች ጋር ተራርቀን ከርመናል።

ከብዙ ኡስታዞች ደርስና ሙሀዶራዎችም ተገድበን አሳልፈናል።
ከአያሌ መረጃዎችም ታቅበን ነበር።
አሁን አልሀምዱ ሊላህ በከፊልም ቢሆን የተሻለ ነገር አለ!!

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

23 Oct, 18:10


ወላሂ አሊሞች የተናቁበትና የረከሱበት አላዋቂ ጃሂሎች ደግሞ የነገሱበትና የገነኑበት አስከፊ ዘመን እንደዚህ እንዳለንበት ዘመን አይነት ዘመን ያለፈ አይመስለኝም!!

መድረኮች ሁሉ በጃሂሉ ተወረዋል
በአብዘሀኛዉ መድረኮች ላይ አሊሞች ቢታደሙም ሰዉን ለመሳቢያና በስማቸዉ ለመቸርቸር ያክል እንጂ የነርሱ ሚና የጎላ እንድሆን ታልሞ አይደለም!!
إنا لله وإنا إليه راجعون
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

23 Oct, 17:46


የሰዎች ትንኮሳ መቼ ነው የሚጎዳህ?
~
ሰዎች በንግግር፣ በፅሁፍ፣ በሃሜት፣ በየትኛውም አይነት ክፉ ቃል ሲፈትኑህ እየተብከነከኑ ጤናንም፣ ሰላምንም፣ እንቅልፍንም ማጣት አይገባም። ቢቻል አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ነው። ካልሆነ ግን የሚፈትሉትን ክፋት እዚያው እነሱው እንዲጠመዱበት መተው ነው። በመርሳት ሰላምህን ጠብቅ። ካልሆነ ግን ክፋታቸው ሳይሆን ማብሰልሰልህ ይጎዳሀል። ሰዕዲይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦

"የሰዎች ትንኮሳ አይጎዳህም። ይልቁንም እነሱኑ ነው የሚጎዳቸው። ትኩረት በመስጠት ራስህን  ካልጠመድክ በስተቀር። ያኔ እንደሚጎዳቸው አንተንም ይጎዳሀል። ቦታ ካልሰጠኸው ግን ምንም አይጎዳህም።"
[አልወሳኢሉል ሙፈደህ ሊልሐያቲ ሰዒደህ፡ 30]

የሰዎች ትንኮሳ መቼ ነው የሚጎዳህ?
~
ሰዎች በንግግር፣ በፅሁፍ፣ በሃሜት፣ በየትኛውም አይነት ክፉ ቃል ሲፈትኑህ እየተብከነከኑ ጤናንም፣ ሰላምንም፣ እንቅልፍንም ማጣት አይገባም። ቢቻል አላህን እንዲፈሩ ማስታወስ ነው። ካልሆነ ግን የሚፈትሉትን ክፋት እዚያው እነሱው እንዲጠመዱበት መተው ነው። በመርሳት ሰላምህን ጠብቅ። ካልሆነ ግን ክፋታቸው ሳይሆን ማብሰልሰልህ ይጎዳሀል። ሰዕዲይ - አላህ ይዘንላቸውና - እንዲህ ይላሉ፦

"የሰዎች ትንኮሳ አይጎዳህም። ይልቁንም እነሱኑ ነው የሚጎዳቸው። ትኩረት በመስጠት ራስህን  ካልጠመድክ በስተቀር። ያኔ እንደሚጎዳቸው አንተንም ይጎዳሀል። ቦታ ካልሰጠኸው ግን ምንም አይጎዳህም።"
[አልወሳኢሉል ሙፈደህ ሊልሐያቲ ሰዒደህ፡ 30]
=
በ IbnuMunewor

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

23 Oct, 06:40


ይህን 【 ከዐርሹ በላይ 】 የተሰኘዉን የኢብኑ ሙነወርን መፅሀፍ ያልገዛችሁና ያላነበባችሁ ካላችሁ እንደምንም ብላችሁ እጃችሁ አስገቡት።

ወላሂ በጣም ጠቃሚ መፅሀፍ ነዉ። በተለይ አህባሾች ለሚያነሷቸዉ የተሳሳቱ ዉዢንብሮች በቂ መልስ ሰጥቶበታል።

በተለይ በርእሱ ላይ ብዥታ ያለባችሁ ወንድምና እህቶች ብታነቡት ትጠቀማላችሁ!!

👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

06 Sep, 03:07


ሰሞኑን ደሴ ላይ በነበረዉ ልዩ የወሎና የሰሜን ሸዋ ዞን ኡለማኦች ኮርስ ላይ በመሳተፌ ካስደሰቱኝ ነገራቶች መካከል ከታላላቅ የሀገራችን መሻይኾች ጋር መገናኘቴ አንዱ ነዉ።

በመገናኘቴ ከተደሰትኩባቸዉ መሻይኾች መካከል ደግሞ

1 ኛ ከዚህ በፊት በስምና በድምፅ እንጂ በአካል የማላዉቃቸዉ 【ሸይኽ ሙሀመድ አወል ከባህርዳር】

2 ኛ ከዚህ በፊት በአካል ባዉቃቸዉም እንደ አሁኑ ግን በሰፊዉ ያልተገናኘዃቸዉ 【 ሸይኽ ሀሰን ቃዲ ከደሴ】

3 ኛ ከአመታት በፊት አርባ ምንጭ እያለሁ ሲያስቀሩን የነበሩት 【 ሸይኽ ጀማል አብዱሰላም ከመኮይ】

4 ኛ ከዚህ በፊት ባዉቃቸዉም በሰፊዉ አግኝቻቸዉ የማላዉቀዉ 【 ሸይኽ ጀማል አዝዘሀቢይ ከደሴ】

5 ኛ ሸይኽ አብዱል አዚዝ ከሰሜን ወሎ ጊራ
እና ሌሎችም ከዚህ በፊት የማዉቃቸዉም የማላዉቃቸዉም መሻይኾች ጋር በመገናኜቴ እጂግ ደስ ብሎኛል።

በተለይ ሸይኽ ሙሀመድ አወል ባህርዳር ወላሂ አይጠገቡም!! ቀልድና ጨዋታቸዉ፣ ፈገግታቸዉ፣ ፊታቸዉ ላይ የሚታየዉ  የሚያሳሳ ኑር፣  ብቻ በጣም ደስ ይሉ ነበር። አልሀምዱ ሊላህ‼️

በተረፈ ከላይ እስከታች ያሉ የፕሮግራሙ አዘጋጆች፣ ኡስታዞችና መሻይኾች፣ የደሴ ወጣቶች፣ ኡስታዝ ኑረዲን፣ ወንድም ሰይድ ሙሀመድ፣ ወንድም ሙሀመድ አሚን፣ ወንድም ኢብራሂም አህመድ እና ሌሎችም በመስተንግዶዉ ላይ ሲሳተፉ የነበሩ ወንድሞች  ሊመሰገኑ ይገባል!  አሏህ ጀዛአቸዉን ይክፈላቸዉ!! እናመሰግናለን!

👉ሙርሰል/አንሷር ሰይድ ጨፌ ጷግሜ 1/2016
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Sep, 02:57


(ኢብኑ ሙነወር፣ ታህሳስ 2007)
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

04 Sep, 02:56


መኖር እንደ ዘበት
~
👉የቱን ነበር … “አለ” ያልከኝ?
👉እኔ ራሴ ባዶ ሆኜ  በባዶዎች የኮፈስከኝ

👉“ጥራኝ ቅርብ ነኝ” የሚል ሀያል ጌታውን ጥሎ
👉“ማን አለ የሚጠይቀኝ” ሲል አረሕማንን ችላ ብሎ

👉ሙታን ሰፈር የሚኳትን ጨርቁን ማቁን አግተልትሎ
👉ለመቃብር የሚሐጅጅ  ፍየል በጉን አስከትሎ
👉እጣን ከርቤ መጋረጃ ጂኒ ቁልቋል ዘባተሎ።

👉ስማኝ እስኪ … አንድ በለኝ ይህን ነበር … “አለ” ያልከኝ?
👉ግሳንግሶች ሆነን ሳለ  በግሳንግስ የፎገርከኝ?

👉በቢድዐ ህብረ-ድግስ  የሺርክ ቅኝት የሚቀኝ
👉ከሙታን የሚቀላውጥ ..ከድኩማን የሚመኝ

👉ይሄን ነው “አለ” ‘ምትለኝ?
👉እንደሌለ እየነገረኝ
👉በተግባሩ እያሳመነኝ?

👉ካሉት ጋራ የሚጋፋ ... ከሞቱት ዘንድ የሚደፋ
👉ተንቀሳቃሽ በድን ሆኖ …አለ” ሲሉት የሚጠፋ
👉ቀብሩን በእጁ የሚቆፍር … ለጥፋቱ የሚለፋ።

👉ምኑ ላይ ነው ህልውናው  የቱስ ላይ ነው ሰውነቱ?
👉በሺርካሺርክ ተወሮ  ከራስ ጥፍሩ እስከ ‘ግር ጣቱ!!

👉ይልቅ ፉገራህን ተውና  እጁን ያዘው ከጥፋቱ
👉በነብዩ ብሩህ ሱና … ይመለስ ዘንድ ህይወቱ

👉ይቺን ነበር “አለች” ያልከኝ በቁሟ የሞተች ምስኪን?
👉ከደካማው ጠንቋይ ሰፈር ልጅ ፍለጋ የምትኳትን

👉ጥራ ግራ ለፍታ አፍርታ … ለገሪባ የምትበትን
👉ለሺርክ አውራ እጅ ነስታ የሺርክ ጋን የምታጥን
👉ለ'ንቶ ፈንቶ የምትከንፍ ለኹራፋት የምትፈጥን

👉ይሄ ነው ወይ ህይወት ያለው የሚባዝን ያለፋይዳ
👉ሸይኽ አትጥራ” ስትመክረው ሸይኹን ጥላ” የሚረዳ

👉ለተውሒድ ጀርባውን ሲሰጥ በህሊናው የተከዳ፡፡
👉በሺርክ እግሩን የሚያቀጥን ገታ መጂት አና ዳና

👉በዳንግላ በቃጥባሬ ጫሊ አብሪቲ አናጂና
👉ካሸለቡት በላይ ሞቶ ከቀብር ደጅ የሚጠና
👉ከቁርኣን ጋር ተኳርፎ …ከሐዲሥ ጋር ከህሊና

👉ይሄ ነው ወይ … መኖር ማለት?
👉ኑሮ እንዲሉት … እንደዘበት

👉ይሄው ሆነ ወይ ጥቅሙ?
👉የመኖራችን ትርጉሙ

👉መኖር “መሄድ” ቢሆንማ ሳያጣሩ እያጋሩ
👉ከመቃብር ለሚያንኳኩ ሙታኖችን ለሚያዋሩ

👉ላንቃቸው እስኪበጠስ ላይስሰሙ ለሚጣሩ
👉ቤሳ ቤስቲን የሌላቸው ጣኦታትን ለሚያባሩ

👉ሰማያዊ ቅዱስ ቃሉን የማይሰሙ እማይማሩ፡፡
👉መኖር እንዲህ ቢሆንማ ለጠፋበት ቅጥ አንባሩ
👉ላቱስሚዑል መውታ” ብሎ ባልሰየማቸው ጀባሩ፡፡

(ኢብኑ ሙነወር፣ ታህሳስ 2007)
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

31 Aug, 02:45


👉ጥቆማ ከኢብኑ ሙነወር 【አሏህ ይጠብቀዉና】

ጥቂት ነጥቦች ለመጅሊስ
(በየትኛውም እርከን ላይ ላላችሁ ሁሉ!)
~
1- መቼም ኃላፊነታችሁ ላይ ሁሌ እንደማትቆዩ የሚታወቅ ነው። ስለሆነም እስካላችሁ ድረስ በኢኽላስ መስራት ላይ አደራችሁን። ለኢትዮጵያ ሙስሊም የምትውሉት ትልቁ ውለታ ዐቂዳውን መጠበቅ ነው። ስለዚህ በተውሒድ ላይ ከልብ ሆናችሁ ብትሰሩ መልካም ነው፣ አላህ ያግዛችሁና። ከአሕ -ባሽ ይጠበቅ ዘንድ መሬት የረገጠ ስራ ቢሰራ። በራሳችሁ ባይመቻችሁ በየ አካባቢያችሁ ሌሎች እንዲሰሩት ብታመቻቹ። በአዲስ አበባ አንዳንድ ሰፈሮች ላይ ማህበረሰቡን ባገለለ መልኩ መስጂዶች በአሕ - ባሽ በብቸኝነት እንዲያዙ የተደረጉበትን ስህተት ቢስተካከል። በዚህ ላይ ጣልቃ የሚገቡ ሰዎችን ጥግ እንዲይዙ ቢደረግ።
2- ለመስጂድ መስሪያ የተሰጡ ቦታዎች እንደምንም ብላችሁ ግንባታ እንዲካሄድ ብታደርጉ። የፖለቲካው ንፋስ ሲቀያየር ምን እንደሚመጣ አይታወቅም። የመስጂድ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች ደግሞ መስሪያ ቦታዎችን መጠየቁ ሊጠናከር ይገባል።
3- በፌደራልና በአዲስ አበባ መጅሊስ የሚናፈሱ አሉባልታዎችን ብተቆጣጠሩ። ወሬ የሚያናፍሱ አካላትን ማራቅ ይገባል። እስከ መቼ ነው የማህበራዊ ሚዲያ አጀንዳ የምትሆኑት? እንዲሁ እየፈጠሩ እያወሩ ከሆነ ምንም ማድረግ አይቻልም።
4- አንዳንድ በመጅሊስ አመራሮች ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ንግግሮች የሚያሳቅቁ ናቸው። አድማጭን የሚያሳቅቅ ወይም ከዲን ጋር የሚጋጭ ንግግር ከሚወጣ ወይ ቀድሞ መዘጋጀት አልያ ፅፎ ማንበብ ይሻላል።
5- ከፌደራል ጀምራችሁ በየትኛውም ክልል ያላችሁ እባካችሁን ዘረኝነት ላይ አጥብቆ መስራት ይገባል። ለመስጂድ ኢማምነት ብሄር የሚታይባቸው አካባቢዎች አሉ። ይሄ በጣም ደስ የማይል ነገር ነው። ሳዑዲ እርስ ቤት ውስጥ በአስከፊ ሁኔታ ላይ ያሉ ወገኖቻችን በዘር ተቧድነው እየተደባደቡ ነው። መላ ብትፈልጉ። በክልሎች በዘር ግጭት እየተጎዱ ላሉ ወገኖች ለሌሎች በሚታይ መልኩ ከጎናቸው ብትቆሙ ጥሩ ነው። በዚህ ላይ ህዝብ ማስተባበር ይገባል።
6- በመጨረሻም የሸይኽ ዐብዱ ግድ.ያ ምርመራው ምን ላይ እንዳለ ብታሳውቁ መልካም ነው። ጉዳዩ እንደ ዋዛ ችላ ተብሎ የቀረ ይመስላል። ምናልባት ትኩረት ተነፍጎት ከሆነ ብታስቡበት መልካም ነው።
አላህ በኢኽላስ የምትሰሩ፣ ለተውሒድ የምትቆረቆሩ ያድርጋችሁ። ኣሚን።
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

20 Aug, 09:43


يا أخي المسلم! ان كنت مريدا أن تعيش سليما مستريحا في هذه الدنيا
اقرأ هذه الأبيات الجميلة للغاية ثم اعمل بها مادمت حيا عسى أن تنفعك في حياتك!! 

🎙والأبيات لإمامنا الشافعي المبجل. وهو يقول ــ رحمه الله تعالى ــ
ــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
👈إذا شئت أن تحيا سليما من الأذى *** وحظُّك موفور وعرضك صَيِّنُ

👈لسانك لا تذكر به عورة امــــــــرئ *** فكلك عورات وللناس ألســـــنُ

👈وعينك إن أبدت إليك معايِبــــــاً *** فصنها وقل ياعين للناس أعينُ

👈وعاشر بمعروف وسامح من اعتدى *** وفارق ولكن بالتي هي أحسنُ.


أخوك مرسل بن سيد الچفي
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

18 Aug, 11:01


መሀል ሰፋሪ የመውሊድ ጠበቆች
~
መውሊድ ከነሷራዎች ተኮርጆ በባጢኒያ ሺዐዎች የተጀመረ እምነትን የሚያናጉና የሚያጠለሹ ብዙ ጥፋቶችን (ሺርካሺርክ፣ ቢድዐዎችንና ብልግናዎችን) ያጨቀ ቢድዐ ነው። ስለሆነም ስለዚህ የቢድዐ ድግስ ወገንን ማንቃት እና መረጃዎችን ማሰራጨት ይገባል።
እንደሚታወቀው ረቢዕ በተቃረበ ቁጥር ሱፊዩ ለዚህ ቢድዐ ወጥሮ ሲሟገት፣ ሱኒዩ ደግሞ አጥብቆ ይኮንናል። ሌላ ደግሞ የመውሊድ ተቃውሞ የሚረብሸው መሀል ሰፋሪ የሆነ ሶስተኛ ቡድን አለ። "ለምንድነው መውሊድ በመጣ ቁጥር የምትጨቃጨቁት?" እያለ ለደዕዋ እንቅፋት ሊሆን ይነሳል። የምንጨቃጨቀው መውሊድ የሺርክ፣ የቢድዐ እና የብዙ ጥፋት መናሀሪያ መሆኑን በማስገንዘብ ወገንን ከጥፋት ለመጠበቅ ነው። የምንጨቃጨቀው ጥፋትን ማውገዝ፣ ወገንን ከጥፋት መከላከል፣ ሃይማኖታችንን ከሚያጠለሹ ሰርጎ ገብ አመልካከቶች መጠበቅ ኢስላማዊ ኃላፊነት ስለሆነ ነው። የምንጨቃጨቀው እንዳንተ አይነቱን ሳይነቃ እንደነቃ የሚያስብ ምስኪን ወገን ለማንቃት ነው። እንጂ ለክፋት አይደለም። እንጂ የጭቅጭቅ ሱስ ስላለብን አይደለም።
"የፈለገ ያክብር፣ የፈለገ ይተው" የሚለው የመሀይም ፈትዋ ነው። ለመሀይም ጩኸት ደግሞ መደንገጥም መቀዝቀዝም አይገባም። ይሄ ሁሉ ጉድ የማይጎረብጠው በመልካም ብንገምተው መሀይም ስለሆነ ነው። ያለበለዚያ ግን ምርጫው ሌላ ነው። ለማንኛውም የማንም ጩኸት ሳይበግረን የመውሊድን ቢድዐነት አጉልተው የሚያሳዩ የዑለማኦችን ስራዎች ማሰራጨት ላይ ልንተጋ ይገባል። አደራ!
=
በ ኢብኑ ሙነወር
👉https://t.me/murselseid

ሙርሰል ሰይድ ጨፌ

16 Aug, 05:15


ፍጡር አይመለክም
~
የአብሬትም ይሁን የቃጥባሬ ሸይኽ፣ የጫሊም ሆነ የዳና፣ ... ማንም የትኛውም ፍጡር ልጅም፣ ዝናብም አይሰጥም። በእንዲህ አይነት ጉዳዮች ላይ ለተቸገረ መርዳት፣ ለሚለምናቸው መድረስ አይችሉም። እንኳን ለሌሎች ለራሳቸውም አይሆኑም። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا یَسۡتَطِیعُونَ نَصۡرَكُمۡ وَلَاۤ أَنفُسَهُمۡ یَنصُرُونَ }
"እነዚያም ከእርሱ ውጭ የምታመልኳቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፡፡ ነፍሶቻቸውንም አይረዱም። " [አልአዕራፍ፡ 197]

ፍጡር ፍጡር ነው። የፈለገ ከፍ ቢደረግ የፍጡራንን ወሰን አይሻገርም።
{ أَیُشۡرِكُونَ مَا لَا یَخۡلُقُ شَیۡـࣰٔا وَهُمۡ یُخۡلَقُونَ (191) وَلَا یَسۡتَطِیعُونَ لَهُمۡ نَصۡرࣰا وَلَاۤ أَنفُسَهُمۡ یَنصُرُونَ (192) }
"ምንንም የማይፈጥሩትንና እነርሱም የሚፈጠሩትን (በአላህ) ያጋራሉን? ለእነርሱም መርዳትን የማይችሉትን ነፍሶቻቸውንም የማይረዱትን (ያጋራሉን?)" [አልአዕራፍ፡ 191-192]

ልጅ፣ ዝናብ፣ አዱኛ ቀርቶ የማይረቡ መናኛ ነገሮችን እንኳ ማድረግ አይችሉም።
{ وَٱلَّذِینَ تَدۡعُونَ مِن دُونِهِۦ مَا یَمۡلِكُونَ مِن قِطۡمِیرٍ (13) إِن تَدۡعُوهُمۡ لَا یَسۡمَعُوا۟ دُعَاۤءَكُمۡ وَلَوۡ سَمِعُوا۟ مَا ٱسۡتَجَابُوا۟ لَكُمۡۖ وَیَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِ یَكۡفُرُونَ بِشِرۡكِكُمۡۚ وَلَا یُنَبِّئُكَ مِثۡلُ خَبِیرࣲ (14) }
"እነዚያም ከእርሱ ሌላ የምትግገዟቸው የተምር ፍሬ ሽፋን እንኳ አይኖራቸውም። ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም፡፡ በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም።" [አልፋጢር፡ 13-14]

"በትንሣኤም ቀን (እነርሱን በአላህ) ማጋራታችሁን ይክዳሉ" የሚለውን አስምሩበት። የሚመለኩት ግኡዛን ነገሮች ብቻ እንዳልሆኑ ይጠቁማል። ነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "ዱዓእ (ተማፅኖ) አምልኮት (ዒባዳ) ነው" ይላሉ። ሙታኖችን እየተጣሩ፣ እየተማፀኑ ያሉ አካላት አመኑም አላመኑም እያመለኳቸው ነው ያሉት። አምልኮት ደግሞ ለአብሬት፣ ለቃጥባሬ፣ ለአንይ፣ ለዳንይ፣ ... ቀርቶ ለነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አይስሰጥም። እንዲህ አይነቱ ባእድ አምልኮ የነብያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መንገድ አይደለም። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ وَلَا یَأۡمُرَكُمۡ أَن تَتَّخِذُوا۟ ٱلۡمَلَـٰۤىِٕكَةَ وَٱلنَّبِیِّـۧنَ أَرۡبَابًاۗ أَیَأۡمُرُكُم بِٱلۡكُفۡرِ بَعۡدَ إِذۡ أَنتُم مُّسۡلِمُونَ }
"መላእክትንና ነቢያትን አማልክት አድርጋችሁ እንድትይዙ አያዛችሁም። ሙስሊሞች ከሆናችሁ በኋላ በክህደት ያዛችኋልን?" [ኣሉ ዒምራን፡ 80]

በ IbnuMunewor
👉https://t.me/murselseid

1,681

subscribers

76

photos

37

videos