…………………………………………….
የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈጻጸም ዙሪያ በየደረጃዉ የሚገኙ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም በቅ/ጽ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዉይይት አካሄደ፡፡
"ለገቢ ዕቅድ አፈጻጸሙ ስኬት ባለቤቶች መላዉ የቅ/ጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች በመሆናቸዉ ያለኝን ልባዊ ምስጋና እገልጻለሁ!" ያሉት የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮንን ለሙሳ - በቀጣይ ወራት ለሚጠበቀዉ የተሻለ የገቢ ዕቅድ አፈጻጸም የአሰራር ክፍተቶችን በማረም ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡
የፕላኒንግና ለውጥ ስራዎች ስራ ሂደት የሆኑት ወ/ሮ አየለች ጠምደሎ የ2017 የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የገቢ ዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ ባቀረቡት ጽሁፍ - በ6 ወራት ውስጥ 17,762,167,996.78 ብር ለመሰብሰብ ታቆዶ 18,434,774,204.58 ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 103.79% ማሳካት ተችሏል፤ ከባለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 10,268,426,895.06 ብር ወይም 125.74 በመቶ ብልጫ ያለው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በመጨረሻም የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮንን በአጽንኦት እንደተናገሩት በገቢ አፈጻጸም ዕቅዶች ላይ ትኩረት በማድረግ ከተሰጠን ተቋማዊ እቅድ በላይ ማስመዝገብ ይገባል ብለዋል፡፡
………………..
የደንበኞች ትምህርት ቡድን
ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም