Ankuaru Business News @ethcoffeenetworknews Channel on Telegram

Ankuaru Business News

@ethcoffeenetworknews


አስተማማኝ እና ጊዜውን የጠበቀ ትኩስ የቢዝነስ መረጃዎችን እዚህ ያገኛሉ።

ETH Coffee Network News (Amharic)

ኤትኤች ቡና ኔትዎሪክ ዜና ከአስተማማኝ ወደ ጊዜውን የጠበቀ ትኩስ የቡና መረጃዎችን ምንጮችን እና መረጃዎችን ማእከል የሚለውን የቦታ እዚህ ፣ እባኮት የቦታን ተወካዮችን እና ሙሉትን ለብሼ ካመለጠልዎ ጋር ለመመልከት ይረዳል። ኤትሬይን ብራሚቲን እስከ ተማሪናዊ መንነት እስቲ እንደሚያሳየን ከተማሪነት ቤት ተዳራሽ እና ማስተማሪዎችን ለውጤሞቼ መረጃዎቹን የሚያዳራግ ሳጥን ሊተረብር ያለባቸው መረጃዎችን ይጠቀሙ። ለቡና ኮፒ ኪማ መረጃዎችን እና ማሰልጠኞቹን ለማገኘት የሚመቻቹ እና ሁሉም አፈፃፀም የሚመጣቸውን መረጃዎችን የሚያመልኩ ሊገናኘው ይችላል። ማንኛውም ቦታን ቢያመለጥን ወይም ቅናሽ እና የሌሎች ኑሮችን የሚያከናውነው እባኮት። ገና ከሃገር ቤት የማስቀረቢያ እና መልሶችን ከገንዘብ ቤት እንዲሆን ማስተዳደር አለባቸው።

ETH Coffee Network News

30 Nov, 08:26


Building Material Related Tenders Nov-30/2024

አስተዳደሩ 3/4ኛ ጠጠር 5,750 ሜ.ኩ እና 3/8ኛ ጠጠር 5,787 ሜኩ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


The administration invites eligible bidders for the procurement of different types of inch crushed aggregate

ድርጅቱ የተለያዩ አይነት የ RHS እና SHS ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

The enterprise invites eligible bidders for the supply of various types of RHS) and SHS materials

ETH Coffee Network News

30 Nov, 08:25


የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ለኢትዮጵያ ሊሰጥ ስላዘጋጀው ተጨማሪ ብደር ምን አይነት አምለካከት አላችሁ?
ብለን ላቀርብነው ጥያቄ 95 ሰዎች ሃሳባችውን የሰጡ ሲሆን ከነዚያ ውስጥም 49 በመቶውቹ ተጨማሪ ብደሩ የረዥም ጊዜ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ብለው ሲያምኑ 28 በመቶዎቹ ደሞ ጠቃሚ እንደሆን እና ሃገሪቷ ገንዘቡ ያስፈልጋታል የሚል ሃሳብ አንጸባርቀዋል። የተቀሩት 23 በመቶዎቹ በበኩላችው ብድሩ ጥቅምም ጉዳትም ሊኖረው እንደሚችልን ያምናሉ።

Ankuaru

ETH Coffee Network News

29 Nov, 13:14


News Alert-Nov-29/2024

ብሔራዊ ባንክ በመደበኛው ገበያና በጥቁር ገበያ መካከል ያለው የውጭ ምንዛሪ ልዩነት እየጠበበ መምጣቱን ገለጸ
ተጨማሪ ያንብቡ.......

Forex Gap Shrinks: NBE's Bold Reforms Bridge Regular and Black-Market Rates

Click Here To Read More.....

የሲዳማ ክልል የግብርና ትራንስፎርሜሽን ፍኖተ-ካርታ ለ 10 አመት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ ተገለጸ

ተጨማሪ ያንብቡ.......

Sidama Region's 10-Year Agricultural Transformation Plan Unveiled
Click Here To Read More......

በቻይና ዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ዐውደ-ርዕይ ላይ የኢትዮጵያ ምርቶች እየተዋወቁ ነው
ተጨማሪ ያንብቡ.......

Ethiopian Products Showcased at China's Global Supply Chain Expo

Click Here To Read More......

ETH Coffee Network News

29 Nov, 12:17


News Alert Nov-29/2024

ETH Coffee Network News

29 Nov, 11:19


ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም በ2ኛ ዙር በኢትዮጲያ ያደረገው የባለሙያ ግምገማ ውጤት መግለጫ!

ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ ተያይዟል

ETH Coffee Network News

29 Nov, 09:13


November 29, 2024 Dollar Transaction

#Ankuaru

ETH Coffee Network News

29 Nov, 08:14


News Alert Nov-29/2024

ማዕከሉ ካቦዴ እና አላሞራ የተሰኙ የብርቱካናማ ስኳር ድንች ዝርያዎች አስተዋወቀ
ተጨማሪ ያንብቡ......

Wondo Genet Agricultural Research Center Unveils orange- fleshed Sweet Potato Varieties
Click Here To Read More....

ባንኩ በበጀት ዓመቱ ካዘዋወረው ገንዘብ ውስጥ 80 በመቶ በዲጂታል እንደሆነ አስታወቀ
ተጨማሪ ያንብቡ......

CBE Achieves 80% Digital Banking Transactions
ተጨማሪ ያንብቡ

ETH Coffee Network News

29 Nov, 07:08


Agriculture Related Tender N0v-29/2024

ድርጅቱ የተለያዩ የግብርና እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

The organization invites eligible bidders for the procurement of different agricultural material

ኢንስቲትዩቱ ጥራጥሬና የእህል ውጤቶች እንዲሁም ሌሎች የምግብ አይነቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

The institute invites eligible bidders for the procurement of food item supply including grain crops

ETH Coffee Network News

29 Nov, 07:08


Building Material Related Tenders Nov-29/2024

መ/ቤቱ ለድልድይ ግንባታ ስራ አገልግሎት የሚሆኑ ሲሚንቶና ፌሮ ብረት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

The office invites eligible bidders for the procurement of cement and reinforcement steel bars for bridge construction

ጽ/ቤቱ የግንባታ እቃዎችን ጨምሮ የተለያዩ ግብአቶችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

The Office invites bids for the procurement of different supplies including construction materials

ጽ/ቤቱ የህንጻ መሳሪያዎችን ከአቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

The office invites eligible bidders for the procurement of building materials for sector offices

ETH Coffee Network News

28 Nov, 16:08


News Alert Nov-28/2024

ETH Coffee Network News

28 Nov, 14:07


News Alert Nov-28/2024

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የእስያ መሰረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸው ተገለጸ

ተጨማሪ ያንብቡ....

Ministry of Finance and Asian Infrastructure Investment Bank Forge Partnership
Click Here To Read More.....

ዓለም አቀፍ የቡና ዋጋ በግማሽ ምዕተ ዓመታት ውስጥ ያልታየ ከፍተኛ ጭማሪ አስመዘገበ
ተጨማሪ ያንብቡ....

Ministry of Finance and Asian Infrastructure Investment Bank Forge Partnership
Click Here To Read More.....

ETH Coffee Network News

28 Nov, 08:47


November 28, 2024 Dollar Transaction

#Ankuaru

ETH Coffee Network News

28 Nov, 08:08


Event Alert Nov-28/2024

ETH Coffee Network News

28 Nov, 07:40


News Alert Nov-28/2024

ETH Coffee Network News

28 Nov, 07:40


Agriculture Related Tenders Nov-28/2024

ድርጅቱ የባልትና ጥራጥሬ እህሎች እና ሌሎች እቃዎችን በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

The organization invites eligible bidders for the supply of grains and other products

The commission invites eligible bidders for the procurement of wheat flour

ጽ/ቤቱ የእርሻ ትራክተር እና ሞተር ሳይክል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

The office invites eligible bidders for the sale of agricultural tractors and motorcycles

ETH Coffee Network News

28 Nov, 07:40


Building Related Tender Nov-28/2024
ማህበሩ የተለያዩ የህንጻ መሳሪያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ተጨማሪ ያንብቡ .....

The company invites eligible bidders for the sale of building equipment
Click Here To Read More.....

ፋብሪካው የተጋቡ የኬሚካል የብረት በርሜሎችን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ተጨማሪ ያንብቡ .....

The factory invites eligible bidders for the sale of used metal barrels for recycling
Click Here To Read More.....

The organization invites eligible bidders for the supply, transport, install, and commission solar PV systems, pumps, and accessories
Click Here To Read More.....

ETH Coffee Network News

28 Nov, 06:00


NYCE Market Closing

Date: 27/11/2024
Arabica = +16.95 US cents lb.                      
                      (5.435%)
    328.79 Closing

#Ankuaru
@Ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

27 Nov, 12:53


Event Alert Nov-26/2024

ETH Coffee Network News

21 Nov, 11:36


November 21, 2024 Dollar Transaction

#Ankuaru

ETH Coffee Network News

21 Nov, 11:35


News Alert Nov-21/2024
የቡና ዋጋ በአለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ

ETH Coffee Network News

19 Nov, 13:56


የሐረር ቡናን ወደቀደመ ዝናው ለመመለስ ትልቅ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
ተጨማሪ ይመልከቱ...

በከተማዋ ከታሪፍ በላይ ባሰከፈሉ ከአንድ ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ተወሰደ
ተጨማሪ ይመልከቱ...

የጥራጥሬና የቅባት እህሎች ላይ እሴት በመጨመር የዘርፉን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሰራ ነው ተባለ
ተጨማሪ ያንብቡ…

Ethiopia Envisions to Penetrate Pulses and Oilseeds Global Market Potentials
Click Here To Read More....

የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ሥርዓት የሚደነግግ ረቂቅ አዋጅ ቀረበ
ተጨማሪ ይመልከቱ....

ETH Coffee Network News

19 Nov, 13:54


News Alert Nov-19/2024

ETH Coffee Network News

15 Nov, 08:51


NYCE Market Closing

Date: 14/11/2024
Arabica = +5.9 US cents lb.                      
                      (2.2%)
    272.61 Closing

#Ankuaru
@Ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

14 Nov, 10:22


News Alert Nov-13/2024

ETH Coffee Network News

14 Nov, 10:22


ሙሉ ሪፖርቱን ከላይ አያይዘናል

ETH Coffee Network News

14 Nov, 10:21


News Alert Nov-13/2024

ETH Coffee Network News

14 Nov, 10:20


News Alert Nov-13/2024

ETH Coffee Network News

14 Nov, 10:20


News Alert Nov-14/2024

ETH Coffee Network News

11 Nov, 12:49


News Alert Nov-11/2024

ETH Coffee Network News

11 Nov, 06:51


News Alert Nov 09/2024

ETH Coffee Network News

11 Nov, 06:49


News Alert Nov-11/2024

ETH Coffee Network News

06 Nov, 12:45


ሳምንታዊ የሃገር ውስጥ ቡና ቀጥተኛ(Vertical) ግብይት የአነስተኛ እና ከፍተኛ ዋጋ ማንፃፀሪያ
ከጥቅምት 26  እስከ  ህዳር 30/2017
(November 5  - 11/2024)

ETH Coffee Network News

01 Nov, 08:21


አዲስ የቡና ምርምርና ማሻሻያ ፕሮግራም ተጀመረ

የኮርኔል ዩኒቨርሲቲ እና የዓለም የቡና ምርምር (WCR) በዓለም ዙሪያ የሚገኙ አነስተኛ የቡና መሬት ያላቸው ገበሬዎችን ምርታቸውን በማሻሻል ላይ ያተኮረ አዲስ ፕሮግራም በማውጣት ላይ ይገኛሉ፡፡ የቡና ማሻሻያ ፕሮግራሙ በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USAID) ከ5 ሚሊዮን ዶላር በላይ እገዛ ተደርጎበታል፡፡ ፕሮግራሙ የቡና ገበሬዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እይገጠማችው የመጣውን የምርት መቀነስ ችግር ለመፍታትና በዓለም አቀፍ ደረጃ አስፈላጊ የሆኑ የቡና አቅርቦት ሰንሰለቶችን ለማጠናከር ያስችላል ተብሏል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ12 ሚሊዮን በላይ የአነስተኛ መሬት ቡና አምራቾች፣ የእያንዳንዳቸው እርሻ ከ5 ሄክታር ያነሰ ቢሆንም የዓለማችን 60 በመቶ የሚሆነውን ቡና የማምረት ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ገበሬዎቹ ለገበያው አስፈላጊ አስተዋጽኦ ቢያበረክቱም በአየር ንብረት ለውጥና በአዳዲስ የአመራረት ዘዴ ግኝቶች ማነስ ሳቢያ ለአደጋ የተጋለጡ እየሆኑ መጥተዋል። ይህም የገበሬውን መተዳደሪያም ሆነ ሰፊውን የቡና አቅርቦት ሰንሰለት አደጋ ላይ ይጥላል።

ምንጭ፡- ኮርኔል ክሮኒክል (CORNELL CHRONICLE)
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

31 Oct, 18:11


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች እርስ በርሳቸው የሚበዳደሩበት የገንዘብ ገበያ ይፋ አደርገ

ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ ስደስት ነጥቦችን በዋነኝነት ዘርዘሯል፣ እነሱም:-

ንግድ ባንኮች የአጭር ጊዜ ማለትም
ለአንድ ቀን ወይም ለሰባት ቀናት መቆየት የሚችሉ ገንዘብ መበደርና ማበደር የሚችሉ መሆናቸውን፡፡

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት በኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የግብይት መድረክ ላይ ብቻ እንደሚካሄድ።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የገንዘብ ገበያ መመሪያ እና የሥነ ምገባር ደንብ መሠረት ይከናወናል። ማለትም ሁሉም የንግድ ባንኮች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ማግኘት እና የሚጠበቅባቸውን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።

በባንኮች መካከል የሚደረግ የገንዘብ ግብይት የወለድ ተመን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው የፖሊሲ የወለድ-ተመን ክልል ውስጥ እንደሚሆን ይጠበቃል። ይህም ማለት ይህ የወለድ ተመን ክልል የብሔራዊ ባንክ ፖሊሲ ነክ የወለድ ተመንን መሠረት ያደረገ ሆኖ ከዚህ የፖሊሲ የወለድ ተመን በ3 በመቶ ከፍ ወይም በ3 በመቶ ዝቅ ሊል የሚችል ነው።

ሁሉም ንግድ ባንኮች በባንኮች መካከል በሚደረግ የገንዘብ ግብይት ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እና አዲሱን የንግድ መድረክ እንዲጠቀሙ ብሔራዊ ባንክ ምክሩን ይለግሳል፡፡

#Ankuaru
@ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

28 Oct, 07:47


አይ ኤም ኤፍ ከሰሃራ በታች ስላሉ ሃገራት የቀጣዩን ዓመት የኢኮኖሚያው ትንብያ የሚያሳይ ሪፖርት አወጣ

አይ ኤም ኤፍ ከሰሃራ በታች ስላሉ ሃገራት የቀጣዩን ዓመት የኢኮኖሚያው ሁኔታ የሚያሳይ ሪፖርት ያወጣ ሲሆን በ2025 የኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት መጠን በ6.5 በመቶ እንደሚያድግ፣ የዋጋ ግሽበቱ 23.3 በመቶ እንደሚሆን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ እንደ ግብር መጨመር ወይም የገንዘብ ኪሳራን ለመቆጣጠር የሚያስችል የገንዘብ ድጎማ መቀነስን የመሳሰሉ የማክሮኢኮኖሚያዊ መረጋጋትን ለማሻሻል የሚደረግ የፖሊሲ ማስተካከያ ማድረግ ከማህበረሰቡን ፍላጎት ሊቃረን ይችላል ሲል አይኤምኤፍ ጥቅምት 25 ቀን 2024 ዓ.ም. ባወጣው ዘገባ አመልክቷል። በተጨማሪም ሪፖርቱ እንደገለጸው በዩክሬንና በመካከለኛው ምሥራቅ ግጭት እንደ ማዳበሪያና ነዳጅ የመሳሰሉ ሸቀጦች ዋጋ እንዲጨምር አስተዋጽኦ ሊያደርግ እንደሚችል ዘግቧል።

የሪፖርቱን ሙሉ ክፍል ከላይ አያይዘናል።

#Ankuaru
@ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

26 Oct, 08:43


ቻይና የኢትዮጵያን ቡና ለመግዛት እና ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት እያሳየች መሆኑ ተነገረ

የቻይናየተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ተወካዮች እና ባለሀብቶች የልዑካን ቡድን ከክቡር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ ጋር ተወያይዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ በዛሬው ዕለት ከአስር በላይ ከሚሆኑ የቻይና የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ተወካዮች እና ባለሀብቶች የልዑካን ቡድን አባላት ጋር በጽህፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ዋና ዶ/ር አዱኛን ጨምሮ ሚስተር ዋንግ ቢን በቻይና ንግድ ሚ/ር ሰርኩለኤሽን እንደስትሪ ፕሮሞሽን ዳይሬክተር፣ ቻይና የተለያዩ የቡና ኩባንያዎች ተዋናይ የሆኑ እና ንቁ ተሳትፎ ያላቸው ባለሀብቶች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ የተቋማት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የቡና ማህበራት ፕሬዝደንቶች፣ ሌሎች የቡና ባለሙያዎች እና እሴት ጭመራ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶች ተገኝተውበታል፡፡
ቻይናውያኑ እንደገለጹት በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለዝና የሆነውን የኢትዮጵያን ቡና በስፋት ለመግዛት ያላቸውን ፍላጎት የገለጹ ሲሆን ወደፊት በተጠናከረ ሁኔታ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል።

ምንጭ፡ የቡናና ሻይ ህዝብ ግንኙነት
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

26 Oct, 08:43


ወደ ውጪ ከተላኩ ምርቶች ከ1.5ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ የሶስት ወራት አፈጻጸም፤ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ83 በመቶ በመጨመሩ፤ 1.5 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል፡፡ በአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ጭማሪ ቢታይም፤ ወደ ውጭ ከተላኩ የጫት እና የጥራጥሬ ምርቶች የተገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር መቀነሱን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሐሙስ ጥቅምት 14፤ 2017 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ላይ ተነግሯል። በዚሁ ስብሰባ ላይ የዘንድሮ በጀት ዓመት የሶስት ወራት የወጪ ንግድ እቅድ አፈጻጸም ለተሰብሳቢዎች ቀርቦ በአዲሱ የጥራጣሬ እና የቅባት እህሎች የቀጥታ ግዢ መመሪያ ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡

በንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የወጪ ንግድ ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ አቶ በረከት መሰረት፤ በዘንድሮ በጀት ዓመት ሶስት ወራት ከወጪ ንግድ ሊገኝ ታቅዶ የነበረው አጠቃላይ ገቢ 1.12 ቢሊዮን ዶላር እንደነበር ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። በሩብ ዓመቱ ሀገሪቱ ከዘርፉ ያገኘችው ገቢ በእቅድ ከታየዘው በ385 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ብልጫ ያለው እንደሆነም አመልክተዋል።

ምንጭ፡-የኢትዮጵያ ኢንሳይደር
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity

ETH Coffee Network News

24 Oct, 06:58


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የነዳጅ ማደያዎች እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠንን ከትላንት ጀምሮ ይፋ ማድረግ ጀምሯል

አሁን ላይ በከተማዋ 123 ማደያዎች ግልጋሎት እየሰጡ ነው ተብሏል። ቢሮው ፤ " በየዕለቱ የነዋጅ ማደያዎችን እለታዊ የነዳጅ አቅርቦት መጠን ይፋ ማድረግ የተጀመረው በአገልግሎቱ ሂደት እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የተገልጋች እንግልት ለመቀነስ ነው " ብሏል።

ነዳጅ ማደያዎች የት ቦታ እንደሚገኙ እና በእለቱ የተራገፈው ነዳጅ መጠን እንዲሁም የጥቆማ ስርዓቱ ከላይ ተያይዟል።

#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

23 Oct, 07:44


ለውጪ ገበያ የሚቀርብ ሳምንታዊ የቡና አነሰተኛ የዋጋ ማንፃፀሪያ
ከጥቅምት 12  እስከ  ጥቅምት 18/2017
(October 22  - October 28/2024)

ETH Coffee Network News

22 Oct, 06:00


ኢትዮጵያ በየዓመቱ ሁለት ቢሊዮን ቶን ለም አፈር ታጣለች ተባለ

ፒፕል ኢን ኒድ(People in need) ከቼክ ሪፐብሊክ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር የአየር ንብረት ለውጥ እና ዘላቂ የመሬት አያያዝን በኢትዮጵያ ለማጠናከር የባለሙያዎችን አጋርነት ማጎልበት በሚል ባካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ ከፍተኛ የአካባቢ አየር ንብረት ለውጥ ስጋት ተጋርጦባታል ሲል አስታውቋል ። ለዚህ ምክንያቱ የደን መጨፍጨፍ ፣ የአፈር መሸርሸር እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በእጅጉ በመቀነሱ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች የምግብ ዋስትናን አደጋ ላይ ጥሏል ብሏል ።

የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎች ፣ የሙቀት መጨመር እና ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብን ጨምሮ ሌሎችም ሁኔታውን በማባባስ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ለአደጋ ተጋላጭ እንዲሆን ማድረጉ ተጠቁሟል ። እንዲሁም እየጨመረ በመጣው የህዝብ ቁጥርና ፍላጎት ፣ ልቅ ግጦሽ እንዲሁም የግብርና እና የተፋሰስ ልማት ስራወች በበቂ ሁኔታ ባለመተግበራቸው የደን ሽፋን ሊራቋት እንደቻለ ተጠቁሟል ። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያ በዓመት ሁለት ቢሊዮን ቶን ለም አፈርን እንደምታጣ ተነግሯል ። እነዚህ ተግዳሮቶች ስነ-ምህዳራዊ ብቻ ሳይሆኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ፣ የምግብ እጥረት ፣ ድህነትን እና ፍልሰትን የሚያባብሱ ናቸው ተብሏል ። ስለሆነም ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ፈጣን እርምጃ እንደሚያስፈልጋት ተመላክቷል።

#Ankuaru
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

22 Oct, 05:16


NYCE Market Closing
Date: 21/10/2024
Arabica = -3.67 US cents lb.                      
                      (-1.43%)
    252.07 Closing

#Ankuaru
@EthCoffeeCommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

21 Oct, 13:00


የቅባትና ጥራጥሬ እህሎችን በ60 ቀናት ውስጥ ለውጭ ገበያ እንዲቀርቡ የሚያስገድድ ሕግ ፀደቀ

ላኪዎች በቀጥታ የግብይት ሥርዓት የገዙትን የቅባትና ጥራጥሬ እህሎች በአንድ የምርት ዘመን ወይም የምርት ዘመን ባለቀ በ60 ቀናት ውስጥ አጠናቀው ለውጭ ገበያ እንዲያቀርቡ መመርያ ቁጥር 1026/2017 የቅባት እህሎችንና የጥራጥሬ ምርቶችን የቀጥታ ግብይት ለመወሰን የወጣው መመርያ ክፍል አንድ በተራ ቁጥር ስምንት ያስገድዳል።

ዘርፉን ከሕገወጥ ንግድ ለመታደግ እና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል አማራጭ ግብይት ለመዘርጋት በማስፈለጉ መመሪያው እንደወጣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለጥራጥሬና ቅባት እህል ላኪዎች ማኅበር ስለመመርያው በላከው የማብራሪያ ደብዳቤ ይገልጻል፡፡ የቀጥታ ግብይት ሥርዓት ያስፈለገበት ምክንያት የረዥም የግብይት ሰንሰለት ለምርት ብክነትና የጥራት መጓደል፣ ሕገወጥ ግብይትና የኮንትሮባንድ መስፋፋት፣ የምርት ክምችትን የመደበቅ ችግሮች በተሞክሮ በመስተዋሉ መሆኑን የተላከው ደብዳቤ ያስረዳል፡፡
ይህም በውጭ የንግድ አፈጻጸም ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የቅባት እህሎችና የጥራጥሬ ምርቶችን የቀጥታ ግብይት አሠራር በመዘርጋት እንደ አንድ መፍትሔ እንደተወሰደ ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡ሪፖርተር
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

21 Oct, 11:08


October 21, 2024 Dollar Transaction
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

17 Oct, 06:44


ለውጪ ገበያ የሚቀርብ ሳምንታዊ የቡና አነሰተኛ የዋጋ ማንፃፀሪያ
ከጥቅምት 5  እስከ  ጥቅምት 11/2017
(October 15  - October 21/2024)

ETH Coffee Network News

17 Oct, 05:00


NYCE Market Closing
Date: 16/10/2024
Arabica = +0.001 US cents lb.                      
                      (0.001%)
    256.93 Closing

#Ankuaru
@EthCoffeeCommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

11 Oct, 06:04


NYCE Market Closing
Date: 10/10/2024
Arabica = 0.21 US cents lb.                      
                      (0.08%)
       254.92 Closing

#Ankuaru
@EthCoffeeCommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

08 Oct, 09:36


October 8, 2024 Dollar Transaction
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

07 Oct, 09:14


October 7, 2024 Dollar Transaction
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

07 Oct, 05:37


የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን የቡና ምርቱን ወደ አዳዲሰ ገበያዎች ለማስፋት እንዳቀደ ይፋ አደረገ

በተለምዶ የኢትዮጵያ ቡና ዋና መዳረሻ ገበያ ወደሆኑት ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጀርመን ቤልጂየም፣ ጃፓን እና ሳዑዲ አረቢያ ኤክሰፖርቱን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚፈልግ የገለጸው ባለስልጣኑ የቡና ገበያውን በተለይም ወደ ደቡብ ኮሪያ እና ቻይና ለማስፋት እንዳቀደ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ ወደ ቻይና እና ደቡብ ኮሪያ እየተደረገ ያለው ትኩረት ኢትዮጵያ ከተለመዱት መዳረሻዎች ባለፈ የቡና ገበያዋን ለማስፋት ራእይ እንዳላት ያመላክታል ብለዋል። በቁጥጥር እና የማስፋፋት እርምጃዎች የቡና ምርትን ለማሳደግ፣ ጥራትን እና የክትትል አቅምን ለማረጋገጥ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሆነም ዋና ዳይሬክተሩ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

05 Oct, 07:37


የአውሮፓ ህብረት የደን ጥበቃ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆንበት ጊዜ ሊራዘም
መሆኑን የሚየወሳው መግለጫ

        እና

በመመሪያው ዙሪያ ተደጋግመው የሚነሡ
ጥያቄዎች የተመለሱበት ፋይል።

ከስር አያይዘናል።

ETH Coffee Network News

04 Oct, 09:04


NYCE Market Closing
Date: 3/10/2024
Arabica = -2.151 US cents lb.                      
                      (-0.84%%)
        254.13 Closing

@EthCoffeeCommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

04 Oct, 07:08


የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ቦርድ ለኢትዮጵያ 3.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠጋ የተራዘመ የብድር አገልግሎት አቅርቦትን እናዳጸደቀ ይታወሳል።

ይህ የ4 ዓመት የተከፋፈለ ክፍያ ከሚጥይቃችው ነግሮች ውስጥ:-
- የማክሮ ኢኮኖሚ ሚዛን መፋለስን ማስተካከል።
- በግሉ ዘርፉ የሚመራ እድገት ላይ መሠረት መጣል ።
- የመንግሥትን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ አፈጻጸምን የሚደግፍ ነው ተብሏል።

የዚህን ሙሉ የዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት ያወጣው ሙሉ ማብራሪያ እና ይዝት ከላይ አያይዘናል ከፍታችሁ ማንበብ ትችላላቹ።

#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

03 Oct, 10:31


October 3, 2024 Dollar Transaction
#Ankuaru
@ethcoffeecommunity
@EthCoffeeNetworkNews

ETH Coffee Network News

03 Oct, 06:06


NYCE Market Closing
Date: 2/10/2024
Arabica = -7.51 US cents lb.                      
                      (--2.85%%)
        256.29 Closing

@EthCoffeeCommunity
@EthCoffeeNetworkNews