ቀሰም University @qesem_university Channel on Telegram

ቀሰም University

@qesem_university


💡ቀሰም University Campus ለሚማሩ ተማሪዎች ፤ ቲቶሪያሎችን ፣ጠቃሚ የንባብ ስልቶችን ፤Soft Copy የሆኑ አጋዥ የንባብ ማቴሪያሎችን ፣ትምህርታዊ መረጃዎችን እና አነቃቂ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ለተማሪዎች ንቃት የሚተጋ ቻናል ነው!📚

📩Owner :- @Ezkiel_T
Buy ads: https://telega.io/c/Qesem_Freshman

ቀሰም University (Amharic)

ቀሰም University ሀቅና ልጆችን እና ባለንብረት እንዲሆን የሚፈልጉ ተማሪዎችን እና ቲቶሪያሎችን ያገናኘው የትምህርት ቤት ነው። በዚህ ቤት ያልተገባ ስልቶችን እና ማቴሪያሎችን በአጋዥ ሁመራቱ መልዕክቶችንን ያረጋግጡ። እንደሚማሩ የተለያዩበት የንባብ ዝግጅቶችንና መረጃዎችን ለተማሪዎች የሚተጋፍሩ ንቃት ነው። በሚያደርግበት ሁኔታ ቻናልዎን ሊከናወን የምትፈልጉ ትምህርት እንችላለን። ታዲያ፣ ቻናልን ያግዛሉ፣ ወደ የትምህርት ቤት ያደርጋሉ፣ እና ቢሶቪል እና ማቴሪያሎችን የሚገኝ የሚሰጡ። ይህ የታሪኩ መሠረትና የለሃማን የተገናኘው ንቃት የሚተጋፍ ቻናል ነው። በእርስዎ የተላወሱ ባለንብረቶች ለተማሪዎች ንቃት ተደጋጋሚ ቻናልን አግዙት። እናም፣ አሁንም በዚህ ባህሪያት ላይ እንድታመነሩና መኖሪያን ለመጠቆም ቻናልዎን ሥሩ።

ቀሰም University

21 Nov, 08:10


ቀለሜ  ተማሪዎች የአጠናን ልምዳቸው ምን ይመስላል

🎚️ 12 ወሳኝ ነጥቦች

1️⃣ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ለምን ዓላማ እንደሚያጠኑ ቀድመው ዓላማ ያስቀምጣሉ።
ይህ ማለት ምን ለማወቅ እንደሚያጠኑ ቀድመው ያቅዳሉ።

2️⃣መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከመጀመራቸው በፊት ስለሚያጠኑት ርዕሰ ጉዳይ የራሳቸውን ግምት ያስቀምጣሉ። መፅሀፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በኃላ የነበራቸውን ግምት እያጠናከሩ...የተሳሳተው
ን እያስተካከሉ ይጓዛሉ።

3️⃣ ሲያጠኑ ያገኙትን አንኳር ነጥብ አጠር አድርገው ማስታወሻቸው ላይ ያሰፍራሉ።

4️⃣አንብበው ለ መረዳት ያስቸገራቸውን ነጥብ /ሀሳብ/ ደጋግመው ያነባሉ....

5️⃣ጥናት ከ መጀመራቸው በፊት ማጥናት ስለ ፈለጉት ርእሰ ጉዳይ ጥያቄዎች ይፋጥራሉ። መፅኃፍ ገልጠው ጥናት ከጀመሩ በሃላ ለጥያቄዎቻቸው መልስ ይፈልጋሉ እንጂ ሁሉም ነገር በ ማንበብ ጊዜያቼውን አያጠፉም።

6️⃣ሲያነቡ ያገኙትን አዲስ ሀሳብ ወይም መረጃ ከ አሁን በፊት ከሚያወቁት ጋር አብሮ ሊሄድ የሚችል መሆኑን እና አለመሆኑን ይመረምራሉ::

7️⃣ በአንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት አይሞክሩም፡፡ በ አንድ ጊዜ ብዙ ነገር ለ ማጥናት መሞከር ትርፉ ድካም መሆኑን ተረድተውታል፡፡

8️⃣ ሁልጊዜም ቢሆን ለትምህርት ጉዳዮች የሚጠቀሙበት የተለየ ጊዜ አላቸው፡፡

9️⃣ ያሰቡትን ነገር ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኝነት አላቸው...አያፈገፍጉም፣ አያቅማሙም፡፡

1️⃣🔠 ሲያጠኑ የሚከብዳቸውን ክፍል ቅድሚያ ሰጥተው ያነባሉ፡፡

1️⃣1️⃣ ተባብሮ በመስራት ያምናሉ፡፡ ያግዛሉ፣ ይጠይቃሉ፡፡

1️⃣2️⃣ እራሳቸው ይገመግማሉ፡፡ ደካማ ጎናቸዉ በፍጥነት ያስተካክላሉ፡፡

⚡️  @Qesemacademy

ቀሰም University

20 Nov, 13:21


#MekdelaAmbaUniversity

በ2017 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች፣ በ2015 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነገር ግን በተለያየ ምክንያት በ2016 ዓ.ም Freshman ፕሮግራም መቀጠል ያልቻላችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር ያልተማራችሁ (ዊዝድሮዋል ሞልታችሁ የወጣችሁ) ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በሁለቱም ግቢ (ቱሉ አውሊያ እና መካነ ሰላም) የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ (ቱሉ አውሊያ ካምፓስ) መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2017 ዓ.ም መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ጥደረጋል ተብሏል፡፡

@Qesem_University ✔️

ቀሰም University

19 Nov, 19:24


📣 Jimma University

በ2017 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና በግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች በዋናው ግቢ

በ2016 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን የተከታተላችሁ ተማሪዎች በቅርቡ https://portal.ju.edu.et ላይ የመለያ ቁጥራችሁን በማስገባት አጠቃላይ ውጤታችሁን ማወቅ የምትችሉ ሲሆን፤ ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ከላይ በተጠቀሰው ቀናት በተመሳሳይ የሚፈጸም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በ2017 ዓ.ም በጅማ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ግዜ በቀጣይ ይገለፃል ተብሏል።


@Qesem_University ✔️

ቀሰም University

19 Nov, 14:57


Next Jima😐

ቀሰም University

19 Nov, 13:44


በስተመጨረሻ😅

ቀሰም University

19 Nov, 13:30


#WolkiteUniversity

በ2017 ዓ.ም ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 26 እና 27/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

- ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
- አራት 3x4 መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2016 ዓ.ም አንደኛ ሴሚስቴር በውጤታችሁ መሰረት ዳግም ቅበላ የተፈቀደላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱ ቀናት እንድታመለክቱ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

@Qesem_University ✔️

ቀሰም University

19 Nov, 03:32


📥 Uv የገባችሁ Freshman ተማሪዎች የደረሳችሁ Dorm እንዴት ነው?

@Qesem_University

ቀሰም University

18 Nov, 11:17


📣 Gambella University

በ2017 ጋምቤላ ዩንቨርስቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመግብያ ጊዜ ህዳር 23 እና 24/2017 መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያስታዉቃል::


@Qesem_University ✔️

ቀሰም University

18 Nov, 09:49


አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የተመደቡለትን አዲስ ገቢ እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታተሉ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል።

በ2017 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ለተመደቡ ተማሪዎች ተቋሙ ወደፊት ጥሪ አደርጋለሁ ማለቱ አይዘነጋም።

@Qesem_University ✔️

ቀሰም University

18 Nov, 04:50


#Fake #Jimma

ጅማ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ የተመደቡለትን ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል በሚል እየተሰራጨ ያለው ደብዳቤ የተሳሳተ መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን።

ተማሪዎች መሰል መረጃዎችን ከማሰራጨታቹህ በፊት የዩንቨርሲቲያችሁን ትክክለኛ የማህበራዊ ገፆች በማየት ማረጋገጥ ይኖርባቸሃል።

@Qesem_University ✔️

ቀሰም University

17 Nov, 13:33


#Advertisement

📚እንሆ መልካም ዜና በዚህ ዓመት Freshman ለምትጀምሩ እና ለጀመራችሁ  ተማሪዎች በሙሉ 🥰

🖱MGW በዚህ ዓመት Freshman የሚገቡ የተፈጥሮና ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች አሪፍ እገዛ ያደርጋል🙏

ኑ...ተቀላቀሉን 🤗

🔹 ሲኒዬሮቻችሁ ከጭንቀት በመላቀቅ ለፍሬሽማንና  ለCoc ብቁ  የሆኑበት ሜዲካል ጌትዎይ  እናንተንም ብቁ አድርጎ  የሚያስፈትን ይሆናል 💯

💻 በእኛ ቲቶሪያል 👇

➡️የ Freshman ፈተናዎች ይሰራሉ
➡️የልምድ ልውውጥና ምክር ይተላለፋል
➡️ተማሪዎች በፈተናው ውጤታማ የሚሆኑባቸው ቲቶሪያሎች ይሰጣሉ
➡️የባለፈው ዓመት Freshman  Mid and Final Exam እንዲሁም Coc Exam ሁሉም እኛጋር ይሰጣሉ 🥰

🔘 ተማሪዎች በፈለጉት ሰዓት እኛን ሊቀላቀሉን ይችላሉ ✈️

👨‍💻ለFreshman ምዝገባ 👇
@MGWTutorial_Reg_bot

💻ስለቱቶሪያል ለመጠየቅ
📞0704282565
📞0906014772

🌐ይቀላቀሉን
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk
https://t.me/+kEB9-ojwbeQ3YmNk