SAFARI ACADEMY GRADE 12 @safariacademygrade12 Channel on Telegram

SAFARI ACADEMY GRADE 12

@safariacademygrade12


"Your Kids Our Kids"

SAFARI ACADEMY GRADE 12 (English)

Welcome to Safari Academy Grade 12, the ultimate destination for high school students looking to excel academically! Our Telegram channel, @safariacademygrade12, is dedicated to providing a platform where students can access valuable resources, study materials, and guidance to help them succeed in their academic journey

Who are we? Safari Academy Grade 12 is a team of experienced educators and professionals who are passionate about helping students reach their full potential. We understand the challenges that high school students face, especially in their final year, and we are here to offer our support and expertise every step of the way

What do we offer? Our channel is a treasure trove of information tailored specifically for Grade 12 students. From exam tips and study guides to practice questions and revision notes, we cover a wide range of subjects and topics to ensure that our students are well-prepared for their exams. We believe in personalized learning, so we also provide one-on-one support and feedback to help students improve their understanding and performance

Your Kids Our Kids is not just a motto for us; it is a promise. We treat every student as if they were our own, offering them the best possible resources and guidance to help them succeed. Join us at Safari Academy Grade 12 and let us help you unlock your full potential! Whether you are aiming for top grades, college admissions, or simply want to improve your knowledge, our channel is the perfect place for you. Don't wait any longer - start your academic journey with us today!

SAFARI ACADEMY GRADE 12

12 Jan, 05:35


🌟አህያ- አገር እና ህዝብን ያገለገለ አስተዋይ እንስሳ!

ከቤት እንስሳቶች ሁሉ ከውሻ ቀጥሎ አስተዋይ ጭንቅላት ያላት እንስሳ አህያ ናት፡፡

ከእንስሳቶች ሁሉ አቅጣጫን እና መንገድን በመለየት እና ፈጥኖ በመረዳት የምትበልጠው አህያ እንደሆነች ያውቃሉን?

🔇 ከቤት እንስሳቶች ሁሉ ራስዋን በራስዋ በመምራት እና በማስተዳደር የምትበልጠው አህያ እንደሆነች ያውቃሉን?

አህያ አንድ ጊዜ ያየችውን ወይም የሄደችበትን መንገድ በጭራሽ አትረሳም፡፡

አህያ ወደ ፊት እያነጣጠረች የኋላዋን ኮቴ ጥርት አድርጋ ማየት ትችላለች፡፡

አህያ በአመድ ላይ የምትንከባለለው በተፈጥሮ የሰርከስ አይነት ስፖርት ስለምትወድ ነው፡፡

አህያ የመሬት መንቀትቀጥ አደጋ ከመድረሱ በፊት በትክክል ምልክት መስጠት እና ቅድመ ጥንቃቄ ጩኸት በማሰማት የሰው ልጆችን ታገለግላለች ወይንም ትታደጋለች፡፡

ከቤት እንስሳት ሁሉ አህያ የምትጠላው ቢኖር ውሻን ነው፡፡ ይህ የአህያ እና ውሻ ጥል የተጀመረው ግን ሁለቱም የቤት እንስሳ ከመሆናቸው በፊት በጫካ እያሉ ነው፡፡

🔇በጫካ ውስጥ ልክ እንደ ጅብ አህያን ሲያስቸግራት የነበረው ውሻ ነበር፡፡ ዱር በቃን ብለው ሁለቱን የቤት እንስሳ ከሆኑ በኋላ አህያ ቂምን ለልጅ ልጆችዋ ስታስተላልፍ ውሻ ግን ይህንን መረጃ ለትውልዱ አላስተላለፈም፡፡ ስለዚህ አሁንም ድረስ አህያ ቢቸግራት እና አማራጭ ቢጠፋ እንጂ ውሻ በሌለበት መንደር ብትኖር ደስ ይላታል፡፡

በጣም ጨዋ ከሚባሉ ፍትረታት ውስጥ ዶልፊን፣ ጋ'ንዳ፣ ፈረስ፣ እርግብ እና አህያ ዋንኞቹ ናቸው፡፡

አህያ በተፈጥሮ እርጋታን እንጂ ሩጫ አትወድም፡፡ አንዲት አህያ ድንገት መሮጥ ከጀመረች አንዳች ትልቅ ችግር በአካባቢው ውስጥ አለ ማለት ነው፡፡

    ''ልናከብራት የሚገባ የቤት እንስሳ አህያ❗️''
  
       ካነበብነው🙏

SAFARI ACADEMY GRADE 12

11 Jan, 04:26


ውድ ልጆቻችን ስለጠፈር ሳይንስ ምን ያህል ታውቃላችሁ?
እስኪ ያነበብነውን እናጋራችሁ🙏

SAFARI ACADEMY GRADE 12

06 Jan, 13:12


https://youtu.be/meSaQp4Sxbg?si=-hgM7GzW6B8Vzp9O

SAFARI ACADEMY GRADE 12

06 Jan, 03:50


Our Dear Kids and Respected Parents,

Merry Christmas! On this special occasion, we want to take a moment to thank you for being an integral part of our Safari family. Your unwavering support, trust, and commitment have been the foundation of our shared journey.

This Christmas, we reaffirm our promise to work tirelessly, day and night, to ensure the success of our Kids. Our mission is to guide them toward a bright and prosperous future. However, we cannot do this alone. We kindly ask for your continued cooperation and partnership in working together for the betterment of our Kids’ lives.

May this holiday season bring joy, love, and peace to your families. Thank you for being part of our journey and for trusting us with the growth and success of our children.

Wishing you a Merry Christmas!

Eyob Ayele
Safari Academy
President

SAFARI ACADEMY GRADE 12

06 Jan, 03:25


የምንወዳችሁ ልጆቻችን
የምናከብራችሁ የልጆቻችን ወላጆች፦

እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ቤታችሁ በሰላም፣ በፍቅርና በደስታ ይሞላ። ፈጣሪ ልጆቻችንን በእውቀትና በጥበብ ይባርክልን እያልን፤

በዚህ በዓል ለምንወዳቸው ምርጥ ልጆቻችን የህይወት ስኬት ሳንደክም ቀን ከሌት እንደምንሰራ ቃል እየገባንና ዘወትር የእናንተ ከፍተኛ ክትትል እንዳይለየን አደራችሁን እያልን ስለመረጣችሁንና የሳፋሪ ቤተሰብ ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።


መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ!

ኢዮብ አየለ
ፕሬዝደንት
ሳፋሪ አካዳሚ

SAFARI ACADEMY GRADE 12

05 Jan, 17:43


ንግግርን በተግባር 👌

የሁሉ መከታ፣ የሁሉ አለኝታ🥰

ለገና በዓል የተደረገ ድንገቴ ፈንጠዝያ (SURPRISE)

ሺ አመት ኑርልን ሚስተር ኢዮብ🙏

መልካም በዓል

🙏🙏🙏

SAFARI ACADEMY GRADE 12

05 Jan, 07:23


ውድ የልጆቻችን ወላጆች፦

በሀገራችን እየተከሰተ ያለውን ተደጋጋሚ የመሬት መንቀጥቀጥ በተመለከተ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት የመሬት መንቀጥቀጥ ሲከሰት ምን ማድረግ እንዳለብን የሰጠውን ማብራርያ እናስታዉሳችሁ።

➡️ ከቤት ውጭ ከሆኑ ፦ ከዛፎች ፣ ከሕንፃዎች ፣ ከኤሌትሪክ ምሶሶዎች እና ሌሎች ወድቀው ጉዳት ሊያደርሱ ከሚችሉ ነገሮች መራቅ እና ገላጣ ሜዳ አካባቢ መቆየት።

➡️ በቤት ውስጥ ከሆኑ ፦ በበር መቃኖች ፣ ኮርነሮች እና ኮሪደሮች ተጠግቶ ማሳለፍ። ከእሳት ምድጃዎች፣ ከተሰቀሉ ፍሬሞች እና የግድግዳ ጌጦች፣ ከመጽሐፍ መደርደሪያዎች እንዲሁም ከመስኮት አካባቢ መራቅ። የጋዝ ምድጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ማጥፋት ካልሆነም ከአካባቢው መራቅ።

➡️ በትልልቅ ሕንጻዎች ውስጥ ከሆኑ ፦ ከሕንጻዎቹ ለመውጣት አለመሞከር ፣ አሳንሰር (ሊፍት) በፍፁም አለመጠቀም። ከደረጃዎች አካባቢ መራቅ።

➡️ መኪና እያሽከረከሩ ከሆኑ ፦ የኤሌትሪክ መተላለፊያ ምሶሶዎችን፣ ዛፎችና ሽቦዎች አካባቢ አለመቆም፣ የኤሌትሪክ መስመር ምሶሶዎች እና ሽቦዎች ተሽርካሪው ላይ ከወደቁ ከመኪናው ለመውጣት አለመሞከር፣ በተቻለ ፍጥነት ገላጣ ወደሆነ አካባቢ መኪናን ማቆም።

''ፈጣሪ የምንወዳቸው ልጆቻችንን፣ ህዝባችንን እና ሀገራችንን ይጠብቅልን!''

SAFARI ACADEMY GRADE 12

07 Dec, 06:49


ራዕይ አንደኛ ደረጃ👇

SAFARI ACADEMY GRADE 12

07 Dec, 06:49


ሰሚት አንደኛ ደረጃ👇

SAFARI ACADEMY GRADE 12

16 Nov, 17:29


Our Dear Kids,
(እባካችሁ ልጆቼ የአባት ምክሬን አንብቡልኝ)

I write to you today with great pride and heartfelt belief in your potential. As your *teacher* and *academic father,* I want you to know that we care deeply about you, your growth, and your success—not just within these walls but in every stage of your life. Your journey matters to us, and we are committed to helping you unlock the greatness within you.

To achieve success and fulfill your dreams, there are two essential keys: *self-discipline* and *excellent time management*. These are not just skills—they are life-changing habits that will guide you through challenges and lead you to success.

*Self-discipline* is about committing to your goals, even when it’s hard. It’s waking up each day determined to make progress and staying focused on what truly matters. It’s about holding yourself accountable, making sacrifices, and pushing beyond limits to achieve the extraordinary.

*Time management* is your most powerful tool. Each of you has the same 24 hours in a day as the world’s greatest achievers. How you choose to spend those hours will determine your path. Learn to prioritize what matters, eliminate distractions, and dedicate time to growth and learning.

We believe in you. We care about your success and want to see you achieve your dreams. Know that every late-night study session, every disciplined choice, and every focused effort is a step closer to building the future you deserve.

You are not alone in this journey. We are here to support you, to guide you, and to cheer for you every step of the way. Your success is our joy, and your growth is our mission.

With discipline, time management, and determination, there is nothing you cannot achieve. *We love you*, we believe in you, and we are so proud of the incredible individuals you are becoming.

With warmest regards and Love,
Eyob Ayele
Safari Academy
President

SAFARI ACADEMY GRADE 12

10 Nov, 18:55


✍️የሌሊት ወፍ✍️

✍️የሌሊት ወፍ  ብቸኛዋ መብረር የምትችል አጥቢ እንስሳም ናት:: ከበራሪ እንስሳት በክንፍ አፈጣጠሯ ትለያለች:: የሌሊት ወፍ ክንፍ በላባ የተሞላ ሳይሆን ይልቁንም የሰው ልጅ አራት የእጅ ጣቶችን የመሰሉ አጥንቶች ላይ የተወጠረ ሞራ መሰል ቆዳ ያለው ነው:: ክንፎቿን እንደ እጅ ትጠቀምባቸዋለች::

✍️የሌሊት ወፎች ቅዝቃዜ በሚበረታበት የክረምት ወቅት ወደ ሞቃታማ ስፍራዎች ይሰደዳሉ:: ከ3 ሺህ 900 በመቶ ኪሎ ሜትሮች በላይም በየአመቱ ይበራሉ:: የአየር ሁኔታው ሲስተካከል በፊት ይኖሩበት ወደነበረው ስፍራ ሳይሳሳቱ ይመለሳሉ::

✍️የሌሊት ወፎች ሲያርፉ ተዘቅዝቀው ያገኙት ነገር ላይ ይለጠፋሉ:: ይህን የሚያደርጉት የእግሮቻቸው አጥንቶች ቀጫጭን በመሆናቸው ክብደታቸውን መሸከም ስለማይችሉ ነው::
ቀን በእንቅልፍ ያሳልፉና ማታ ለአደን ይወጣሉ:: ክንፎቻቸው ጉዳት ቢደርስባቸው በፍጥነት እንዲያገግሙ የሚያስችል የደም ቧንቧ ስርአት አላቸው::

✍️ጆሯቸው ከጭንቅላታቸው ከአምስት እጥፍ በላይ ይተልቃል:: ሰፊ ሲሆን በውስጡ የሚለጠጡና የሚኮማተሩ ጡንቻዎች አሉት:: ይህም የሚያወጡትን እና ተመልሶ የሚመጣውን የድምጽ ሞገድ እንዲለዩ ያስችላቸዋል:: የሌሊት ወፎች በማታ የተሻለ የማየት አቅም አላቸው:: ከጥቁር ነጭና ግራጫ ቀለም ውጭ መለየት አይችሉም::

✍️የሌሊት ወፍ የክብደቷን ግማሽ ያክል ነፍሳትን በአንድ ቀን ትመገባለች::በሰብል ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ነፍሳትንም ሰለምትመገብ ለግብርናው ዘርፍ ጉልህ ጥቅም አላት::

✍️ የለሊት ወፎች ያለማቋረጥ መብረር የሚችሉ ብቸኛ የወፍ ዝርያ ናቸው:: በጨለማ የተሻለ የማየት ብቃት አላቸው::

✍️ከ20 ዓመታት በላይ ትኖራለች::በሰአት 60 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ይጓዛሉ::

ካነበብነው🙏

SAFARI ACADEMY GRADE 12

04 Nov, 16:32


👉የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

👉በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦
➡️ በዌብሳይት :
👇👇👇👇👇 https://placement.ethernet.edu.et 
➡️ በቴሌግራም :
👇👇👇👇
https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

👉ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

👉ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

ከናንተ የሚጠበቀው ይህንን ቻናል ሸር ማድረግ ብቻ ነው!!
🫴🫴🫴🫴🫴
https://t.me/dam76

🔤🔤🔤🔤  🔤🔤🔤

SAFARI ACADEMY GRADE 12

30 Oct, 15:40


🦅 ንስር አሞራ 🦅

👌ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ..

የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...

ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...

ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።

👌አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

⓵ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?
⓶ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?


👌የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል።

👌ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።

👉1ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

👉2ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።

👉3ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

👉4ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

👉5ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ  አዲስ ላባ ያበቅላል።

👌ይህን በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡

"ንስር አሞራ የጥንካሬ ተምሳሌት ነው!"

ካነበብነው

SAFARI ACADEMY GRADE 12

27 Oct, 19:08


👆👆👆👆👆👆👆👆
ለ12ኛ ክፍል  ተማሪዎች ሞዴል ፈተና

አዘጋጅ 👉የካ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት

SAFARI ACADEMY GRADE 12

24 Oct, 13:10


#MoE

የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity

SAFARI ACADEMY GRADE 12

21 Oct, 12:53


#MoE

የትምህርት ሚኒስቴር ፤ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ እንደሚገለጽ አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ፤ " በ2016 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ምደባ በቅርቡ ይገለጸል " ብሏል።

ተማሪዎች በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia