Bole bulbula senior secondary school for students @a12004886 Channel on Telegram

Bole bulbula senior secondary school for students

@a12004886


Bole bulbula senior secondary school for students (English)

Welcome to Bole Bulbula Senior Secondary School for Students! This Telegram channel is dedicated to providing valuable information, resources, and updates to students who are currently attending or interested in joining our prestigious school. At Bole Bulbula Senior Secondary School, we pride ourselves on offering a comprehensive education that focuses on both academic excellence and personal development. Our experienced faculty members are committed to nurturing the potential of every student, helping them grow into well-rounded individuals who are prepared to excel in the future. Whether you're a current student looking for study tips and exam schedules or a prospective student interested in learning more about our school's programs and extracurricular activities, this channel is the perfect place for you. We regularly post announcements about school events, academic achievements, and important dates to keep you informed and engaged. In addition to academic support, Bole Bulbula Senior Secondary School offers a wide range of extracurricular activities to help students explore their interests and develop new skills. From sports teams to debate clubs, there is something for everyone to get involved in and enhance their overall school experience. Join our Telegram channel, @a12004886, today to stay connected with the Bole Bulbula Senior Secondary School community. Whether you're a student, parent, or alumni, you'll find valuable information and updates that will enhance your school experience. We look forward to welcoming you to our channel and helping you make the most of your time at Bole Bulbula Senior Secondary School!

Bole bulbula senior secondary school for students

26 Dec, 13:06


የ2017 ዓ.ም የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል ፈተና መረጃ ለ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች

1️⃣6ኛ ክፍል በተመለከተ

በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉አካ/ሳይንስ  እና
👉ግብረ ገብ ሲሆኑ 

✍️ የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል ፈተና የሚዘጋጀው ከ6ኛ ክፋል first semester (5ኛ ክፍልን first semester  ይጨምራል)

የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል ፈተና የሚዘጋጀው ከ8ኛ ክፍል  first semester   (ከ7ኛ ክፋልን first semester ይጨምራል)

በፈተና የሚካተቱ የት/ት አይነቶች:-
👉አማርኛ
👉እንግሊዘኛ
👉ሒሳብ
👉ሶሻል ሳይንስ
👉አጠ/ሳይንስ
👉የዜግነት ት/ት

12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና በተመለከተ

👉በ2017 ዓ.ም ለፈተና የሚሰጡ የትምህርት አይነቶችን  በሁለቱም ዘርፎች ስድስት፡ ስድስት የትምህርት አይነቶች ናቸው::   እነሱም :-

ሀ/የተፈጥሮ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ባዮሎጅ
✍️ፊዚክስ
✍️ኬሚስትሪ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት

ለ/የማህበራዊ ሣይንስ
✍️እንግሊዝኛ
✍️ሒሳብ
✍️ታሪክ
✍️ኢኮኖሚክስ
✍️ጅኦግራፊ
✍️ስኮላስቲክ አፕቲቲውድ ቴሰት


የ1ኛ መንፈቅ ዓመት ሞዴል የፈተና ዝግጅትም:-

1.  12ኛ ክፍል first semester ብቻ
2. ከ9ኛ ክፋል በአሮጌው ስርአተ ትምህርት  ያጠቃልላል::
3. ከ11ኛ ክፋል first semester ብቻ  ::
4. 10ኛ ክፋልን አያካትትም

👉በመሆኑም የፈተና ወቅት እየተቃረበ በመሆኑ ተማሪዎች በዚህ መረጃ መሰረት በአግባቡ ማጥናት ይጠበቅባቸዋል::
👉ሁሉም ሞዴል ፈተናዎች ከጥር 7--9  ይሰጣሉ ።
በዚህ መረጃ መሠረት ሁሉም  የመንግስትና የግል ት/ቤቶች ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

Bole bulbula senior secondary school for students

21 Dec, 07:20


ስማችሁ
ከታች የተዘረዘራችሁ ተማሪዎች በኦላይን ያልተመገባችሁ እና አየር ላይ ያላችሁ ስለሆነ በአስቸኳይ ሰኞ ጠዋት ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳስባለን

Bole bulbula senior secondary school for students

20 Dec, 13:56


ቀን 11/04/17
በዛሬው እለት በጣም የምንወዳት እና የምናከብራት በቅርብ ግዜ በሞት የተለየችን የመምህርት ጽጌ ይርዳው የሻማ ማብራት ፕሮግራም የት/ቤቱ ተማሪዎች መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች በተገኙበት ተከናውኗል

Bole bulbula senior secondary school for students

13 Dec, 14:17


Date 04/04/17
For all grade 12 students, tomorrow there is no tutorial class!! But on Monday there will be tutorial class at 1:30 local time

Bole bulbula senior secondary school for students

12 Dec, 17:01


🙏🙏🙏🙏🙏ቦሌ ቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማህበሰብ በሙሉ
🙏🙏🙏🙏🙏 ዛሬ በጣም
የምንወዳት መምህርት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች:: የቀብር ስነ - ስርዓቱ የተሰካ እንደሆን አመራሩ, ተማሪዎች, ወተመህ, ሱፐርቫ ይዘር, የአካባቢው ማህበረሰብ, መምህራን ና አስተዳደር ሠራተኞች ሁሉ ላደረጋችሁ ትብብር ከልብ አመሰግናለሁ:: የቀብር ስነ ስርዓት የሚፈፀመው በትውልድ ሀገሯ ስለሆነ በነገው እለት የመማር ማስተማሩ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቃለሁ:: መልካም ምሽት!!!!

Bole bulbula senior secondary school for students

11 Dec, 16:46


የ ባህልና ኪነ ጥበብ ክበብ ዉይይት

Bole bulbula senior secondary school for students

22 Nov, 07:56


የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የተፈታኝ ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚጠበቅ ሀላፊነት እና ግዴታዎች ህዳር /2017ዓ.ም
 ፈተና ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በመቅደም በት/ቤት ውስጥ መገኘት
 በአግባቡ በክፍል ቁጥራቸው ተሰልፈው ወደ ፈተና ክፍል በመግባት በቦታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
 ከእስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ ውጪ ምንም ነገር ይዘው መግባት በተለይ ሞባይል እና ኤሌክትሮኒክስ ከፈተና ያሳግዳል
 በፈተና ሰዓት መኮረጅ ወይም ማስኮረጅ ፈተና የሚያሰርዝ በመሆኑ በስርዓት የግል ፈተና ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ መስራት
 ለፈተናው የተሰጠውን ሰዓት በአግባቡ መጠቀም 30 ደቂቃ ሳይሞላ ቀድሞ አለመውጣት ከተጀመረ ግማሽ ሰአት ከሞላ ወደ ክፍል መግባት አይቻልም
 በፈተና ሰዓት ድምፅ ማሰማት፣ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አላስፈላጊ ወረቀት(ደብተር) ይዞ መገኘት፣ ረብሻ መፍጠር ከፈተና ያሳግዳል
 ተፈታኞች አስፈላጊውን መረጃ፣ ስም፣ ቁጥር የመሳሰሉትን በአግባቡ መሙላትና የፈተናውን መልስ መሟላቱን በማረጋገጥ ለፈታኝ መምህሩ በጠየቀው ሰዓት መመለስ
 ተፈታኞች ማንኛውም ጥያቄ ሲጠየቁ በስርዓት እጅ በማውጣት መሆን ይኖርበታል
 ተፈታኞች ባግባቡ መፈተናቸውን ማረጋገጫ በሆነው አቴንዳንስ ላይ በዕለቱ በተፈተኑበት ትምህርት ስር መፈረም ይኖርባቸዋል
 ተፈታኞች ፈተና ከጨረሱ በኃላ በቀጥታ ሌሎች ተማሪዎች እንዳይረብሹ ከግቢ መውጣት ይኖርባቸዋል

Bole bulbula senior secondary school for students

22 Nov, 07:53


ቀን 13/03/17
ለቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች
የ2017ዓ.ም የመጀመርያ መንፈቅ ፈተና በ18/03/17ዓ.ም የነበረው ወደ 16/03/17ዓ.ም በመምጣቱ ሁሉም ተማሪ በወጣለት ፕሮግራም መሰረት መታወቅያ በመያዝ በሰአት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

Bole bulbula senior secondary school for students

21 Nov, 11:33


ቀን 12/03/2017 ማስታወቂያ ለትምህርት ቤታችን አንዳንድ ተማሪዎች መታወቂያ ሳትይዙ ወደ ትምህርት ቤታ እየመጣችሁ ስለሆነ ከነገ ጀምሮ 13/03/17 በር ላይ የማትገቡ መሆኑን እናሳውቃለን ::

Bole bulbula senior secondary school for students

21 Nov, 03:23


ቤታቸው በእሳት ለተቃጠለባቸው ተማሪዎች እርዳታ ሲሰጥ

Bole bulbula senior secondary school for students

16 Nov, 08:02


ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሰኞ እና እሮብ ማጠናከርያ የሚሰጠው ጠዋት ከ1፡30-2፡20 በመሆኑ በተባለው ሰአት እንድትገኙ እናሳስባለን

Bole bulbula senior secondary school for students

15 Nov, 15:16


1ኛ ክ/ግዜ 2:30_3:15
2ኛ ክ/ግዜ 3:15_4:00
ዕረፍት 4:00_4:15
3ኛ ክ/ግዜ 4:15_5:00
4ኛ ከ/ግዜ 5:00_5:45

Bole bulbula senior secondary school for students

15 Nov, 15:10


ት/ርት የሚጀምርበት ሰዐት 2:30 በመሆኑ ሁላችሁም በሰዐት እንድትገኙ አናሳስባለን

Bole bulbula senior secondary school for students

15 Nov, 14:38


ለ12ኛ ክፍል የቅዳሜ ማጠናከሪያ

Bole bulbula senior secondary school for students

14 Nov, 16:48


05/03/2017
የበጎ አድራጎት ክበብ አባል መምህራን ነገ ማለትም 06/03/17 9:00ሰአት አጠቃላይ ስብሰባ በቤተ መፅሀፍት ስላለ እንድትገኙ።

Bole bulbula senior secondary school for students

14 Nov, 16:48


05/03/17
ለበጎ አድራጎት እና የቀይ መስቀል ክበብ አባል ተማሪዎች ነገ አርብ 06/03/17 ስብሰባ ስላለ ቤተ መፅሀፍት 9:00ሰአት እንድትገኙ።

Bole bulbula senior secondary school for students

12 Nov, 12:59


ቀን 03/03/2017 ዓ፣ም ቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ትምህርት ቤት ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ለተማሪዎች በሁለቱም ቋንቋ ጥያቄና መልስ በማዘጋጀት "የሀገራዊ መግባባት ለህብረ በሄራዊ አንድነት " በሚል መሪ ቃል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ::

Bole bulbula senior secondary school for students

11 Nov, 09:11


ቀን 02/03/17
ለቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የቀን 12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች
ስም ከነ አያት መረጃ ዛሬ ለት/ቢሮ ተሞልቶ መላክ ስላለበት በት/ቤት በመገኘት ስም ከነ አያት የተመዘገበውን ስማችሁን እንድታረጋግጡ እና እንድትፈርሙ እያለን ዛሬ ያልተገኛችሁ ነገ ጠዋት የመጨረሻ መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

Bole bulbula senior secondary school for students

11 Nov, 02:34


Trainning was accelerated for members of HIV /AIDS ...

Bole bulbula senior secondary school for students

02 Nov, 03:06


ቀን 22/02/2017ዓ.ም ቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደ/ት/ቤት በአካባቢ እንክብካቤ ክበብ አማካኝነት በክረምት የተተከሉትን ችግኞች ሲኮቶኩቱና ውሃ ሲያጠጡ የሚያሳይ ፎቶ።

Bole bulbula senior secondary school for students

30 Oct, 09:56


አማዞን የቋንቋ እና የጥናት ት/ቤት
-English language(spoken and grammar)
-የአባከስ /ሶሮባን ትምህርት
-ለ6 እና ለ8ኛ ክፍል ለሚኒስትሪ አጋዥ ልዩ
የጥናት ክ/ጊዜ
- የመደበኛ 1-12ኛ ክፍል የጥናት ክ/ጊዜ
አድራሻ:ቦሌ ቡልቡላ ቢጫ ፎቅ🏤
ለመመዝገብ *0927356694
*0984673109ይደውሉ::

Bole bulbula senior secondary school for students

30 Oct, 04:24


የትምህርት ማህበረሰቡ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ::

(ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም) መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (National ID Ethiopia) አማካኝንት በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንዲያከናውኑ ለማድረግ እንዲቻል ተካሄዳል::

ዲጂታል መታወቂያ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ምዝገባው የተማሪዎችንና የትምህርት ማህበረሰቡን ማንነትን በመለየት የተማሪን መረጃ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል ብለዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በጋራ መስራት ለማህበረሰቡ አቅም ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለስራው ስኬታማነት ጉልበት እንደሚሆን ተናግረዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አዲስ አበባን ዘመናዊ ለማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ እየተሰጠ ያለውን የኢ-ስኩል ትግበራን ለማሳካት የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን ለትምህርት ሴክተሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም በትምህርት ቤቶች የሚከናወነውን የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድና አፈፃፀሙን ውጤታማ ለማድግ ሁሉም የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም በዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ስርዓት ዘመቻ ውስጥ ከ14 ዓመት በላይ ያሉ ተማሪዎችና

Bole bulbula senior secondary school for students

30 Oct, 04:24


በትምህርት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ አካላት ሁሉም የዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል::

የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ሕግና ፖሊሲ ክፍል ባልደረባ ገብርኤላ አብርሃም የዲጂታል መታወቂያን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ አቅርበው በተሳታፊዎች የተነሱ ነጥቦች ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል::

በንቅናቄ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ፣ የሶስቱም ተቋማት ማኔጅመንት አባላት ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ፣ የክፍለ ከተሞች ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል ::



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- [email protected]

Bole bulbula senior secondary school for students

26 Oct, 15:46


117 የመከላከያ ቀን በቡልቡላ ሁለተኛ ት/ቤት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሮ ውሏል።

በቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የመከላከያ ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ታስቦ ውሏል።
በዝግጅቱም ሻ/ል ፍቅሩ ተማሪዎች በሰላም እንዲማሩ የወታደር መኖር ግድ ነው፤ ሀገር እንድትቀጥልም በስነ-ምግባር የታነፀ ተማሪ ያስፈልጋል ብለዋል።

ይህ የመከላከያ ቀን በሐገር ደረጃ 117ተኛ ጊዜ በመከላከያ ሰራዊት ቢሮ እንዲሁም በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በደማቁ ተከብሮ ውሏል።

ጥቅምት2/2017 ዓ.ም

ቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሚኒ ሚድያ ክበብ አባላት🫡🫡🫡🫡🫡🫡🫡

Bole bulbula senior secondary school for students

26 Oct, 08:59


በቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የጋዜጠኝነት አጭር ገለፃ በሻ/ል ፍቅሩ ሲሰጥ

ዛሬ ላይ የምታያቸው እኔም ሆንኩ ትላልቅ ጋዜጠኞች እንዲሁም የሚድያ ሰዎች መነሻቸው ሚኒ ሚድያ ነው ጋዜጠኛ ሻ/ል ፍቅሩ
ጥቅምት 15/2017 ዓ.ም የመከላከያ መስሪያቤት የሶሻል ሚድያ ድረገፅ ባለሞያ በት/ቤታችን በመገኘት አጭር የጋዜጠኝነት መሰረታዊ ስልጠና ሰተዋል።

በቀጣይም ጊዜ በማመቻቸት አንድ ሳምን የሚፈጅ መሰረታዊ የጋዜጠኝነት ስልጠና ለሚኒ ሚድያ አባላት እንደሚሰጡ ቃል ገብተዋል።
ዘጋቢ👇👇👇👇
የቦሌ ቡልቡላ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሚኒ ሚድያ ክበብ አባላት

Bole bulbula senior secondary school for students

21 Oct, 11:43


የ2017 የቴክኒክና ሙያ የመደበኛ ስልጠና ዘመን መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆኗል

👉የተፈጥሮ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 141 ከዚያ በታች፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 137 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 142 ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 138 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 179 ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 167 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 170 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 162 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤


👉የማህበራዊ ሳይንስ የመግቢያ ውጤት !

የስልጠና ደረጃ 1 እና 2

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 139 ከዚያ በታች፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 134 እና ከዚያ በታች፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 124 እና ከዚያ በታች፤

የስልጠና ደረጀ 3 እና 4 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 140 ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 136 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 135 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 125 እና ከዚያ በላይ፤

የስልጠና ደረጀ 5 ፦

° ወንዶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 172 ከዚያ በላይ፤
° ወንዶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 164 እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢን #ሳይጨምር የመቁረጫ ነጥቡ 165 እና እና ከዚያ በላይ፤
° ሴቶች ከታዳጊ ክልሎች እና አርብቶ አደር አካባቢዎች የመቁረጫ ነጥቡ 160 እና ከዚያ በላይ፤
° ለሁሉም የአካል ጉዳተኞ የመቁረጫ ነጥቡ 154 እና ከዚያ በላይ፤

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Bole bulbula senior secondary school for students

19 Oct, 12:19


ad

Bole bulbula senior secondary school for students

19 Oct, 12:19


ቦሌ ቡልቡላ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ 09/01/2017 ከ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ወላጆች ጋር በተለያዩ አጀንዳዎች
1.በ2017 ዓ.ም. እቅድ
2.በተማሪዎች ስነምግባር መመሪያ
3.በእንግሊዘኛና በሂሳብ ት/ት ውጤት ከማሻሻል
4.12ኛ ክፍል ውጤት ትንተና እና በቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት በሰላም የተጠናቀቀ ስሆን 10/10/2017
የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ውይይት የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Bole bulbula senior secondary school for students

14 Oct, 19:19


የ2017ዓ/ም የበጎ አድራጎት ክበብ የበጎአድራጎት ሳምንት በማክበር የመጀመሪያ የገቢ ማሰባሰቢያ ሲያደርግ