Hawassa University @hucommunicationsoffice Channel on Telegram

Hawassa University

@hucommunicationsoffice


One of the top ranking first generation Universities in Ethiopia.

Hawassa University Telegram Channel Promotion (English)

Are you a student, alumni, or simply interested in one of the top ranking first generation Universities in Ethiopia? Look no further than the Hawassa University Telegram channel, with the username @hucommunicationsoffice. This channel is your go-to source for all the latest news, updates, and events happening at Hawassa University. Whether you want to stay informed about academic achievements, research breakthroughs, or upcoming seminars and workshops, this channel has got you covered. Connect with fellow students, alumni, and faculty members to stay engaged with the vibrant community that makes Hawassa University so special. Don't miss out on important announcements or opportunities - join the Hawassa University Telegram channel today! Stay connected, stay informed, and be a part of the Hawassa University family.

Hawassa University

02 Dec, 18:44


የሴቶችና ማህ/ጉ/አ/ት/ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ምህረት ገነነ የዓለም የኤድስ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ37ኛ በሀገራችን ደግሞ ለ36ኛ ጊዜ እየተከበረ እንደሚገኝ እና የተለያዩ ሁነቶችን በማሰናዳት የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግና ውይይቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚመቻችበት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በዕለቱ ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የኤች.አይ.ቪ መከላከልና መቆጣጠር ጽ/ቤት በመጡ ባለሙያ በወቅታዊው የሀገራችን የበሽታው ስርጭት ላይ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et

Hawassa University

02 Dec, 18:43


የዓለም የኤድስ ቀን እና ዓለምአቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተከበረ::
**//**
ህዳር 23 ቀን 2017 ዓም
በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈፃሚ "ሰብአዊ መብትን ያከበረ የኤች.አይ.ቪ አገልግሎት ለሁሉም" እና "የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጠናከር አካታችና ዘላቂ ልማት እናረጋግጥ" በሚሉ መሪ ቃሎች በጥምር ባከበረው በዓላት ላይ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው በዕለቱ ተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ መርሐ ግብሩን ባስጀመሩበት ንግግራቸው ከጥቂት ዓመታት በፊት ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚደረግበት በሽታ ሆኖ የተሳለ የነበር ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሰዎች ውስጥ በተፈጠረው ቸልተኝነት የተነሳ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አንስተዋል። ኃላፊው ይህንን መዘናጋት በመቅረፍ የቫይረሱን ስርጭት መግታት እንደሚገባ ገልጸው በዕለቱ በጥምረት እየተከበረ ስላለው የአካል ጉዳተኞች ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የትምህርትና ስነ-ባህሪ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ሳሙኤል አሰፋ ስለአለምአቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን ባስተላለፉት መልዕክት ከሀገራችን ህዝብ ውስጥ 2.4% የሚሆኑት የአካል ጉዳት ያለባቸው መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ትልቅ ቁጥር ይዘው የሚገኙትን የህብረተሰብ ክፍሎች በሁሉም አገልግሎቶችና ማህበራዊ ኡደቶች ላይ ተደራሽና ዋነኛ ተሳታፊ በማድረግ ዘላቂ እድገትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተናግረዋል። የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህንጻዎቹን ለአካል ጉዳተኞች ምቹ ከማድረግ አኳያ ራንች በማሰገንባት ውጤታማ ስራ መስራቱን የጠቆሙት ዲኑ በተጨማሪም በልዩ ፍላጎት የትምህርት ክፍል በርካታ ተማሪዎችን አቅፎ እያስተማረ እንደሆነ ተናግረዋል::

Hawassa University

02 Dec, 07:04


Information related to IELTS exam at Hawassa University can be obtained through the following email address: [email protected] or mobile phone: 0925629589, and by visiting the British Council’s official website.

Take IELTS at Hawassa University!
Hawassa University
Ever to Excel!

Hawassa University

02 Dec, 07:03


HU hosts its fifth round of IELTS Exam
**//**
December 2, 2024
Hawassa University, in partnership with the British Council Ethiopia, has successfully hosted the fifth round of IELTS (International English Language Testing System) exam session on November 28-30, 2024 where 29 individuals sat for the paper-based IELTS exam (both IELTS Academic and IELTS General).

According to Dr. Mihireteab Abraham, Coordinator of the Centre at HU, individuals are taking the advantage of geographical proximity and other factors which make it convenient for them when deciding to take the exam at Hawassa University, and the figure shows growing demand among the community to take the IELTS exam at HU. Dr. Mihireteab mentioned that the next round of IELTS exam session at Hawassa University will be conducted in February, 2025 and the registration is already being undertaken, and IELTS exam preparation is also part of the service that the Center provides through its British Council certified trainers.

Hawassa University

30 Nov, 12:45


በኢትዮጵያ ሰላም ተቋም የፕሮግራም ኃላፊ አቶ ካሳሁን አብደታ ተቋሙ በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ አካባቢዎች ላይ የሰላም እሴቶች ግንባታና ግጭት አፍታት ዙሪያ አመራሩንና አጠቃላይ ማህበረሰቡን ዝግጁ በማድረግ ረገድ የተጣለበትን ሀገራዊ ግዴታ ሲወጣ መቆየቱን አስረድተዋል። ሰላም ለአንድ አካል የሚሰጥ የአንድ ጊዜ ስራ አለመሆኑን የገለጹት አቶ ካሳሁን ሰላማዊ የዩኒቨርሲቲ ከባቢን መፍጠርም የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ውጤት ስለሆነ ከፍተኛ አመራሩን በብቃት ለማስታጠቅ ስልጠናው መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
ሁሌም ለልህቀት!

በዚህ ይከታተሉን:-
*****
Facebook: https://www.facebook.com/Hawassa.University?mibextid=ZbWKwL
Website: https://www.hu.edu.et

Hawassa University

30 Nov, 12:44


የግጭት አፈታትና ሰላም አጠባበቅ ክህሎት ላይ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ተሰጠ።
**
ህዳር 21 ቀን 2017 ዓም
ሰላማዊ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብን ለመፍጠር ላለፉት ሶስት አመታት ለተለያዩ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አካላት ስልጠናዎችን ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በግጭት ጥንቁቅነትና ዝግጁነት ላይ ያተኮረ ሁለት ቀናት ስልጠናዊ ውይይት በሮሪ ሆቴል እየሰጠ ነው::

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዚደንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ውይይቱን ባስጀመሩበት ንግግራቸው የዩኒቨርሲቲ ሰላም ሊስተጓጎል የሚችለው የመማር ማስተማር ሂደቱ በአግባቡ ሳይመራ ሲቀር፣ የተቋም ህግና ሰላም ተጠብቆ ጥያቄዎች በአግባቡ ሳይስተናገዱ ሲቀሩ፣ ተማሪው የሚጠቀማቸው አገልግሎቶች ተሟልተው አለመቅረብ እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ ውጪ ያሉ አላስፈላጊ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ አካላት ተጋላጭነት ሲኖር ዋና ዋናዎቹ በመሆናቸው በእነዚህ ዘርፎች ላይ ውጤታማ ስራ መስራት ሰላምን ለማስጠበቅ የራሱ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። ሰላምን ማረጋገጥ ለአንድ ወገን የሚሰጥ ኃላፊነት ሳይሆን ሁሉም አካላት አስፈላጊውን ክህሎት ተላብሰውና እጅ ለእጅ ተያይዘው የሚያስቀጥሉት በመሆኑ ስልጠናው በሁሉም ክፍሎች ላይ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ አክለዋል።

የሀ/ዩ/ፕሬዚደንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ አዳቶ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ሰላም ተቋም ጋር በትብብር ከተሰሩ ዋነኛ ስራዎች መካከል የሰላም አምባሳደሮችን በማሰልጠን የግቢውንና የአካባቢውን ሰላም ማስጠበቅ በሚችሉበት ቦታ ማሰማራት ዋነኛው መሆኑን አስታውሰው ስልጠናው ከጥቂት በቅርቡ በዩኒቨርሲቲው በተደረገው የከፍተኛ አመራር ለውጥ ምክንያት ም/ፕሬዚደንቶች፣ ዲኖችና ማኔጂንግ ዳይሬክተሮችን ጨምሮ በሥራ ላይ የጋራ መግባባት እንዲኖር ታስቦ በድጋሚ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

23,158

subscribers

6,857

photos

32

videos