በመካከለኛው ዘመን የነበሩ ቀደምት የቁም ጸሐፊዎች የብራና መጻሕፍትን ለመጻፍ ጥቁርና ቀይ ቀለማትን ከእጽዋት በማዘጋጀት የዘወትር መገልገያዎቻቸው አድርገዋቸው እንደነበር መዛግብት ያስረዳሉ።
ጸሐፊዎቹ ቢጫ(የወይን ጠጅ) ቀለም ፣ አረንጓዴ ቀለም ፣ ውሃ ሰማያዊና ነጭ ቀለማትን ከየመልካቸው ጋር የሚቀርቡትን ድንጋዮችና የአፈር አይነቶችን አሰባስበው በመፍጨት በጣም ሲልም እየቀቀሉና እያነጠሩ ለማያያዣ ሙጫ ጨምረው ወደ ቀለምነት በመለወጥ ይጠቀሙ እንደነበር ይነገራል።እነዚያም ቀለማት ሰባቱ ቀለማት የሚል መጠሪያ ስም ማግኘታቸው ይታወቃል።
ጸሐፊዎቹ ቀለማቱን የሚጠቀሙባቸው ለቤተ ክርስቲያን ሥዕል በሚስሉበትና የብራና መጻሕፍትን ጽፈው ለመጻሕፍቱ ውበት ሐረግ በሚጥሉበት ጊዜ ፣ ድርሰቱን የጻፈውን ሐዋሪያ ወይም መጻሕፍቱ የተጻፈለትን ባለ ታሪክ (በገድል) በሥዕል ለማስተዋወቅ የሚያደርጉት መግለጫ እንደ ነበር በየዘመናቱ የተጻፉት መጻሕፍት በዋቢነት ይጠቀሳሉ።
ይቀጥላል!
.
@ethale