ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch) @ortodox_mezmure Channel on Telegram

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

@ortodox_mezmure


በዚህ ቻናል ላይ ማንኛውንም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ስርአትን የጠበቁ
✥ አስተምሮቶችን ✟
❖ ስብከቶችን ✟
❖ መዝሙሮችን ✟
❖ መንፈሳዊ መጽሐፍቶችን ያገኛሉ።☨☨

"መፅሐፍ ቅዱስን ወዳጅህ አድርገው አንተ የቃሉ ወዳጅ ስትሆን
እግዚአብሔር ደግሞ የልቡ ወዳጅ ያደርግሀል።"
     /አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ/

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch) (Amharic)

ከዚህ ቻናል አሁን ስትከባሉ በአሮጌንን የሚገባቸው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች የወጡትን ሶሻል ፕሮጓል እንዲሁም መዝሙሮችን መንፈሳዊ መጽሐፍቶች ላይ ተገኝተን ያምፉትን ያድምቁትን አፕሮን ነው። በዚህ አፕሮን የጽሁፎች እና መጽሐፎች እንዲያስጠብቃቸው፣ ተጨማሪ መረጃዎችን ማገዛታት በቆሞዎ የሚጠቀሙትን መጽሐፍቶች በማግኘት ማገዛት አይነበረም። በተጨማሪም ምንም ያህል መረጃ የሌለን እነዚህ መዝሙሮች ስለአንድነትና አክሊሎች ሲኖረው ለማንም የሚዘምተው የእኛ አፕሮን ነው። የሶሻል ፕሮጓል እና ብኩሉ መጽሐፍቶችን በመስራት እና በመጽሐፍ ሥላና ሚኒስትሩን በመጠቀም ለማገዛት ብኩሉ ሁኔታ በሚለው ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች ድረገጽ ብኩል እንደሚያገኝ እና ማገዛት ሰጥቼአለሁ።

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

12 Feb, 12:45


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ክቡር አባት ሆይ እግዚአብሔርን ደስ ወደ ማሰኘት ፊቴን እስክመልስ ድረስ ፈጥኖ እንዳይጠራኝ አምላክህን ማልድልኝ ለምንልኝ ። እሱ ምሕረቱ የበዛ ፍጹም ታጋሽ ነውና ። /መልክአ ገብረ መንፈስ ቅዱስ/

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

03 Feb, 07:59


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#አንተ ሰው እስኪ ንገረኝ!

#አንድን የሥጋ ቁስል ለመፈወስ ለእያንዳንዱ ሰው ከባድ ነው፤ የነፍስን ቁስል መፈወስ ግን ለኹሉም ቀላል ነው፡፡ የሥጋ ቁስል ለመፈወስ መድኃኒት ብሎም ገንዘብ ያስፈልጋል፤ ነፍስን ለመፈወስ ግን ቀላል ብሎም ወጪን የማይጠይቅ ነው፡፡ ሥጋን ከዚያ ከሚያሰቃይ ቁስሉ ለመፈወስ አድካሚ ነው፡፡ ምክንያቱም በቀዶ ጥገና ምላጭ መቀደድ አለበት፤ መራራ መድኃኒቶችም ሊጨመሩበት ይገባል፡፡ ነፍስን ለመፈወስ ግን እንዲህ ዓይነት ነገር አያስፈልግም፡፡ ፈቃደኛ መኾን ብቻ በቂ ነው፤ ፍላጎቱ ካለ ኹሉንም ነገር ለማድረግ ቀላል ነው፡፡ የእግዚአብሔር መግቦቱም እስከ አሁን ድረስ ይህ ነው፡፡ ሥጋ ቢቆስል ያን ያህል ከባድ ጉዳትን አያመጣብንም፤ ምክንያቱም ምንም ባንታመምም እንኳን ሞት መጥቶ ይህን ሥጋችን ያፈርሰዋል፤ ያበሰብሰዋልምና፡፡ ነፍሳችን ብትታመም ግን ጉዳቱ ብዙ ነው፡፡ እግዚአብሔር የነፍስን ሕመም ለመፈወስ መድኃኒቱ ቀላል፣ ምንም ወጪና ስቃይ የሌለበት ያደረገውም ስለዚሁ ነው፡፡ ታዲያ ምንም እንኳን በሕመሙ ምክንያት የሚያገኘን ጉዳት ያን ያህል ብዙ ባይኾንም የገንዘብ ወጪን የሚጠይቀው፣ ሐኪም የሚያስፈልገው፣ ብዙ ስቃይ ያለበት ሥጋችን ሲታመም እርሱን ለማከም እጅግ የምንደክም ኾነን ሳለ፥ እጅግ ብዙ ጉዳት የሚያመጣውን፣ እርሱን ለመፈወስ ወጪ የማይጠይቀውን፣ ለማስታመም ሌሎች ሰዎች የማያስቸግረውን፣ እንደ ምላጩና እንደ መራራ መድኃኒቱ ስቃይ የሌለበትን ይልቁንም ከእነዚህ አንዱስ እንኳን ሳይፈልግ በእኛ ኃይል ባሉ ምርጫና ፈቃድ ብቻ መዳን የሚችለውን፣ ይህን ማድረግ ሳንችል ስንቀርም ከባድ ፍርድና ቅጣት ስቃይም እንደሚያገኘን በእርግጥ እያወቅን የነፍሳችንን ቁስል ችላ የምንል ከኾነ ሊደረግልን የሚችል ምሕረት እንደ ምን ያለ ምሕረት ነው? እኮ የምናገኘው ይቅርታ እንደ ምን ያለ ይቅርታ ነው?

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

27 Jan, 17:45


https://youtube.com/@anketseadeheno?si=mgSKjBcVtbMPYsAu

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

27 Jan, 06:03


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#እግዚአብሔርን_መፍራት

ከፍርሃታችን የሚመጡትን ጥቅሞች ታያላችሁ? ፍርሃት ባይጠቅም ኖሮ አባቶች ለልጆቻቸው ሞግዚቶችን አይቀጥሩም፤ ሕግ አውጪዎችም በከተሞች ላይ ዳኞችን አይሾሙም ነበር። ከገሃነም የበለጠ የሚያስፈራስ ምን አለ? እናም ገሃነምን ከመፍራት የበለጠ የሚጠቅም ነገር የለም:: ገሃነምን መፍራት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይመራናልና፡፡ ይህ ፍርሃት ባለበት ምቀኝነት ቦታ የለውም፤ ይህ ፍርሃት ባለበት የገንዘብ ፍቅር ቦታ የለውም፤ ቁጣ ይጠፋል፣ ክፉ ምኞቶች ይወገዳሉ፡፡

አንድ ዘብ ሁልጊዜ ነቅቶ በሚጠብቅበት ቤት ውስጥ ሌባ፣ ዘራፊ ወይም ክፉ አድራጊ ሊመጣ እንደማይችል ኹሉ ፍርሃት አዕምሯችንን ሲይዝ፣ ልቅ ምኞቶች በቀላሉ አያጠቁንም፡፡ ይልቁንም ሸሽተው በየአቅጣጫው፣ በፍርሀት ምክንያት ይባረራሉ፡፡

ነገር ግን ፍርሃት ማባረር ብቻ አይደለም ጥቅሙ፤ ክፉ ፍላጎቶቻችንን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን በጎነት ወደ ነፍሳችን ለማምጣትም ይጠቅማል፡፡ ፍርሃት ባለበት ለጋስ መሆን አለ፤ የጸሎት ብርታት፣ ትኩስ የሚደጋገም እንባ እና ለንስሃ የነቃች ነፍስ አለች። ኃጢአትን የሚሸፍን በጎነትን የሚያብበው በማያቋርጥ የፍርሃት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ነው:: ስለዚህ በፍርሃት የማይኖር ሰው ልቡ ደንድኖ የሰይጣን ባርያ እንደሚሆን ኹሉ፣ በፍርሃት የሚኖር ሰው በማያውቀው ጎዳና እንደማይጓዝ ኹሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት በትክክለኛው የጥበብ መንገድ ይወስደናል፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ ገጽ 20 #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

25 Jan, 06:03


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

"ሌቦች ወርቅና ብር ያለውን እንጂ ድርቆሽና ገለባ እንዲሁም ሰንበሌጥ ያለውን ቤት አይበረብሩም፡፡ ዲያብሎስም የሚያጠቃው (የሚፈትነው) መንፈሳዊ ምግባራትን የሚያበዙትን ሰዎች ነው፡፡"

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

23 Jan, 04:02


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#አንኳኩቼ_አላገኘሁም_አትበል፡፡ ብቻ የለመንከው፣ ደጅ የጠናኸው አንተ የምትወደው ሳይሆን እግዚአብሔር የሚወድልህ ይሁን፡፡ ወደ እግዚአብሔር የተዘረጋ እጅ ፈጽሞ ባዶውን አይመለስም፡፡ ስለዚህ ራስህን፣ ልመናህን ምን ዓይነት እንደሆነ ፈትሽ እንጂ አንኳኩቼ አላገኘሁም አትበል፡፡ እንኳንስ ንጹሐ ባሕርይ የሆነው እግዚአብሔር ክፋት የሚስማማው ምድራዊ አባትም ለልጁ ጀሮውን አይደፍንም፡፡

#አስቀድሞ ሕያዊት ነፍስን “እፍ” ብሎ እንዲሁ የሰጠን ጌታ፣ ኋላም ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጁን ሳይራራ ከሰጠን እንደምን በዚህ ይታማል? እንደምንስ አይሰጠንም እንላለን? /ሮሜ.8፥32/፡፡ ልጁን የሰጠው እኮ ጭራሽ “ስጠን” ብለው ላልለመኑ አሕዛብም ጭምር ነው፡፡ ታድያ እንዲህ የምንለምን እኛማ እንዴት አብልጦ አይሰጠንም? የሚበልጠውን ሰጥቶን ሳለስ እንደምን ትንሹን አይሰጠንም እንላለን? ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀውን ሳናደርግ “እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማም” የሚል የሰነፎች አባባል የምንናገር አንሁን፡፡ ጀሮን የፈጠረ ይሰማል!”

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#ምንጭ ፦ ሰማዕትነት አያምልጣችሁ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ ገጽ 178

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Jan, 17:18


https://youtube.com/@anketseadeheno?si=mgSKjBcVtbMPYsAu

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Jan, 16:53


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ወይን_እኮ_የላቸውም

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።


የቃና ዘገሊላ ታሪክ ውስጥ አስደናቂ ከኾኑ ክስተቶች ውስጥ አንዱ የወይን ማለቅ ጉዳይ ነው። በእርግጥ ቃና ዘገሊላ ውስጥ የተፈጸመው የሰርግ ጉዳይ ጥልቅ መልእክቶችን የተሸከመ መኾኑ በብዙ የሚብራራ ነው። ታሪኩን በጥልቀት ለመረዳት ግን ወደ ታሪኩ ጥልቀት ውስጥ የምንገባበትን በር ማግኘት አለብን። የዮሐንስን ወንጌል ምሥጢራዊነት ወደ መረዳት ከፍታ እስካልወጣን ድረስ በወንጌሉ ውስጥ የተፈጸሙትን አስደናቂ ክስተቶች በአግባቡ መረዳት አንችልም። ማክሲመስ ተናዛዚው መጽሐፍ ቅዱስን በጥቅሉ በቤተ ክርስቲያን ይመስልና የዮሐንስን ወንጌል ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለችውን ቅድስተ ቅዱሳን ትመስላለች ይላል። ይህ የሚያመለክተው ወንጌሉ የተሸከመውን ጥልቅ ምሥጢር ነው። እንዲያውም ቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያ ሦስቱን ወንጌላት በሥጋ የዮሐንስን ወንጌል ደግሞ በመንፈስ ይመስላል። የሌሎቹ ወንጌላት እስትንፋሳቸው የዮሐንስ ወንጌል ነውና!!

ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ የዮሐንስን ወንጌል ለመረዳት ሊቁ ኦሪገን እንዳለው ወደ ጌታ ደረት ጋር ጠጋ ብሎ እንደ ዮሐንስ ከጌታ እመቤታችንን መቀበልን ይጠይቃል። ይህ ኹሉ የሚያመለክተው በወንጌሉ ላይ የተጻፉ ክስተቶችን በችኩልነትና በለብ ለብ ስሜት አልፈን እንዳንሄድና በጥልቀት እንድንመረምር ነው። ሰርግ የተፈጸመባት የገሊላዋ ቃና ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያምን በመያዟ ከሚመጣባት ጉድለት ስትድን እንመለከታለን። ከክርስቶስ ጋር ለምናደርገው ግንኙነት የእመቤታችን ልመና እጅግ አስፈላጊ ነው። እርሷ ቀድማን ጉድለታችንን ባታሰማልን ኖሮ መሽራው ክርስቶስ እንዴት ይቀበለን ነበር!!

@እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከቤተ አይሁድ ወገን ስለ ኾነች የአይሁድን ጉድለት በእጅጉ ታውቀዋለች፤ ስለዚህ የሚጠቅማቸውን ወይን ይሰጣቸው ዘንድ ትለምናለች። በመጽሐፍ እንዲህ ተብሏል “እናንተ ሰካራሞች ንቁ ለመስከርም ወይን የምትጠጡ እናንተ ሁላችሁ! ተድላና ደስታ ከአፋችሁ ጠፍተዋልና አልቅሱ፤ እዘኑም።" ኢዩ 1፥5። በመኾኑም አይሁድ የድኅነትን ደስታ በማጣት በኀዘን ውስጥ ናቸው፤ ይህ ነውና የወይን ማጣት!! ወይን እኮ የላቸውም የድኅነት ደስታ ከደጃቸው ጠፍታለችና ስጣቸው ማለቷ ነበር። በተራው ምድራዊ ወይን ሰክረው የድኅነትን ወይን በማጣት ጨለማ ውስጥ ገብተው ነበርና ጉድለታቸውን የምታውቅ ፈጣኗ እናት ለመነችላቸው።

@ወይን እኮ የላቸውም ርቱዕ እምነት የላቸውም። አኹንም በኦሪታቸው ውስጥ የምትታየውን አንተን ወደ ማወቅ አልመጡምና አይኖቻቸውን ከፍተህ ብርሃነ ወንጌልህን ግለጥላቸው። በጨለማ ውስጥ ያለን ነገር ለማየት የግድ ብርሃን እንዲያስፈልግ በእምነት ጨለማ ውስጥ ያሉትን ወይን ርቱዕ እምነትን ሰጥተህ አድናቸው ማለቷ ነው። ያለ እምነት እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም ብሎ ቅዱስ ጳውሎስ እንደ ተናገረው በሐዲስ ኪዳኗ ትክክለኛዋ እምነት በኩል ከእግዚአብሔር ጋር እስካልተገናኘን ድረስ በእርግጥም ወይን እኮ የለንም!!

#እመቤታችን ወይን እኮ የላቸውም ማለቷ ሰዎች ከፈሪሓ እግዚአብሔር በመራቃቸው ምክንያት የደረሱበትን መልከ ጥፉነት ለማመልከትና ከዚያ እንድንፈወስ ለማስደረግ ነው። መዝ 127 “ብፁዐን ኩሎሙ እለ ይፈርሕዎ ለእግዚአብሔር ወለ እለ የሐውሩ በፍናዊሁ። ፍሬ ጻማከ ተሴሰይ፣ ብፁዕ አንተ ወሠናይ ለከ፤ ብእሲትከ ከመ ወይን ሥሙር ውስተ ጽርዓ ቤትከ - እግዚአብሔርን የሚፈሩ ኹሉ የተመሰገኑ ናቸው፣ የድካምህን ዋጋ ትበላለህ፤ ምስጉን ነህ መልካምም ይኾንልሀል፤ ምስትህም በቤትህ ውስጥ እንደ ወይን የተወደደች ናት።" በማለት በብዙ አንቀጽ ጀምሮ በአንድ አንቀጽ ወደ ማውራት ይመጣል። ይህ የሚያመለክተው የክርስቶስንና የእርሱ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን ግንኙነት ነው። በቤትህ እንደ ወይን የተወደደች ናት በማለት የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ውበት ያነሣል። ስለዚህ በፈሪሓ እግዚአብሔር ውስጥ የሚኖሩ የቤተ ክርስቲያን አካሎች የምግባር ውበታቸውን ሳያጡት እንደሚኖሩ፤ ወይን እኮ የላቸውም የተባሉት በዚህ ዓለም ፍልስፍናና ፍቅር የነጎዱትን ነው። የጠፉትን ወደ በረቱ ለመሰብሰብ የተደረገ የፍቅር ጥሪ ነው!!

#ወይን እኮ የላቸውም። ፍቅረ ቢጽ ወፍቅረ እግዚአብሔር የላቸውም። የራሳቸውን ስሜት በመውደድ የሠለጠኑ ናቸውና ወይን ፍቅር የላቸውም!! ወይን ጣዕሟ እንደሚያረካ ነፍሳቸው የምትረካባቸው ቃለ እግዚአብሔር የላቸውም!! ቃልህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው ተብሏል እነርሱ ግን ይህ በአንተ ቃል የመመራት ሐሳብ የላቸውምና  በቃልህ የመመራት ኃይልን ሙላባቸው!! እንግዳ ክፉ ፈቃድ ተነሥቶባቸዋልና ይህን ድል የሚያደርጉበትን ወይን ትዕግሥትን ስጣቸው። መናፍቃን ለሚያቀርቡባቸው ጥያቄዎች መልስ ሰጥተው ሰውነታቸውን በእውነት መሠረት ላይ ይገነቡት ዘንድ ወይን ማስተዋል የላቸውምና ማስተዋሉን አድላቸው!

#ወይን ሕገ ወንጌል ናት። በሕገ ወንጌል ወይን ውስጥ ገብተው ይኖሩ ዘንድ ወይን የወንጌል ምሥጢራትን የሚረዱበት ሀብተ ትርጓሜ የላቸውም። በወንጌል ውስጥ የተዘገበው ሰላም ቀድሞ ባለበሳቸው ጥላቻ ምክንያት አልተገኘላቸውምና “ወይን እኮ የላቸውም" ። የሕይወት ወይን አንተን ራስህን በማጣት ሕማም ውስጥ ገብተው ቆስለዋልና አምላክነትህን ገልጠህ አሳያቸው። በሕይወት ውጣ ወረድ ውስጥ የሚገጥማቸውን መከራ በጽናት ይቀበሉ ዘንድ ወይን እኮ የላቸውም። በእርግጥ የእመቤታችን ድምጿ በልጇ ዘንድ ይሰማል። የእኛ ጉድለትም ስለ እርሷ ሲባል ይሟላል። ብቻ እናታችን ቅድስት ኾይ ከመዝሙር ይልቅ ዘፈን ደስ የሚያሰኘንን እኛን ወይን እኮ የላቸውም በይልን!! ጌታ ሆይ ወይን ደምህን ጠጥተን ምሬተ ኃጢአታችንን ታስወግድ ዘንድ ስለ እናትህ ብለህ ወይንህን ስጠን! አሜን።

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Jan, 04:48


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#በጥምቀት_ዙሪያ_የሚነሱ_ጥያቄዎች_እና_መልሶቻቸው
#ጌታችን_ለምን_ተጠመቀ?
1. ምሥጢርን ለመግለጥ፡-
ጌታችን በፈለገ ዮርዳኖስ ሲጠመቅ ምስጢረ ሥላሴ ግልፅ ሆኗል፡፡ አብ በደመና “የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው” በማለቱ አብ የወልድ አባት መሆኑ ታወቀ፡፡ መንፈስ ቅዱስም የባሕርይ ሕይወቱ መሆኑን ሲያስረዳ በአምሳለ ርግብ በራሱ ላይ ተቀመጠ ወልድም በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ ሲጠመቅ ታየ፡፡ ስለዚህ ምሥጢርን ለመግለጥ ስንል የአንድነት የሦስትነት ምስጢር በጐላ ሁኔታ እንዲታወቅ ተጠመቀ ማለት ነው፡፡ /ማቴ. 3፥16/

2. ትንቢቱን ለመፈፀም፡-
በመዝሙር 46/47/፥16 ላይ “አቤቱ ውሆች አዩህ፣ ውሆችም አይተውህ ፈሩ ጥልቆች ተነዋወጡ ውሆችም ጮኹ፡፡” ተብሎ በቅዱስ ዳዊት የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም ተጠመቀ፡፡

3. አርአያ ሊሆነን፡-
ተጠምቆ እንድንጠመቅ አደረገን ሥርዓትን ሠራልን ቀድሞ በአርአያውና በአምሳሉ እንደፈጠረን አሁንም አርአያ ምሳሌ ሆነን፡፡ ለዚህም ነው ምሳሌን ከእኔ ተማሩ ያለን፡፡ /ማቴ 11፥29/ ለትምህርት ለአርአያ /ዮሐ. 13፥1-17/

4. የዕዳ ደብዳቤያችንን ለመደምሰስ፡-
አዳምና ሔዋን ፍዳው በፀናባቸው መከራው በበዛባቸው ጊዜ የሚያቃልልላቸው መስሏቸው ዲያብሎሰ ስመ
ግብርናችሁን ጽፋችሁ ስጡኝ ባላቸው ጊዜ አዳም ገብሩ ለዲያቢሎስ (አዳም የዲያብሎስ የወንድ አገልጋይ) ሔዋን ዓመቱ ለዲያብሎስ (ሔዋን የዲያብሎስ ሴት አገልጋይ) ብለው ጽፈው ሰጡት፡፡ ዲያብሎስም ይህንን ደብዳቤ አንዱን በሲኦል አንዱን በዮርዳኖስ አስቀመጠው፡፡ በዮርዳኖስ ያስቀመጠውን ጌታችን ሲጠመቅ እንደሰውነቱ ረግጦ ደምስሶታል፡፡ ይህንን ጽሕፈት ለመደምሰስ ነው ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው፡፡ ለዚህም ነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተፃፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፡፡” ያለው ቆላ 2፥14

#ጌታችን_መች_ተጠመቀ?

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው በ5531 ዓመተ ዓለም ዘመነ ሉቃስ ማክሰኞ ጥር 11 ቀን ከሌሊቱ በ10ኛው ሰዓት ነበር፡፡ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 19 በተጠመቀም ጊዜ ዕድሜው 30 ዓመት ከ13 ቀን ነበር፡፡ /ሉቃ. 3፥23/

#ጌታችን_ስለምን_በ30_ዓመት_ተጠመቀ?
በብሉይ ኪዳን ሥርዓትና ልማድ ካህናት ለቤተ እግዚአብሔር ተልእኮ እና መንፈሳውያን አገልግሎቶች ከ30 ዓመት ዕድሜ በፊት አደባባይ አይወጡም ነበር፡፡ እጅግ አስፈላጊ እንኳ ቢሆን ከ20 እና 25 ዓመት አስቀድሞ ለአገልግሎት መሰየም ልማድ አልነበረም፡፡ የቤተ እግዚአብሔር አገልጋዮች በዕድሜና በዕውቀት የበሰሉ፣ በጠባይና በሥራ ልምድ የተፈተኑ ተልዕኳቸውን በብቃት ለመወጣት በተገልጋዩ ሕዝብ ዘንድ የተመሰከረላቸው መሆን ነበረባቸው፡፡ /ዘፀ. 4፥3፤1ዜና መዋ. 23፥24፤ 1ጢሞ.  3፥6-10/ ያንን ሥርዓት ለመፈጸም ጌታችን የተጠመቀውና ለትምህርተ ወንጌል የተገለጠው በ30 ዓመቱ ነበር፡፡

ዮሐንስ መጥምቅም የጌታን መምጣት ለማወጅ በዮርዳኖስ ይሁዳ ምድረ በዳዎች ወጥቶ የታየው ከ30 ዓመት ዕድሜው በኋላ ነው፡፡ ሌላው ዐቢይ ምክንያት የሰው ሁሉ መጀመሪያ አዳም የ30 ዓመት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛ ቀን ተሰጥቶት ኋላም በኃጢአት ምክንያት ያስወሰደውን ልጅነት ለማስመለስ ነው፡፡

ክርስቶስ የተጠመቀው ክብር ሽቶ ሳይሆን የአብ የባሕርይ ልጅነቱን (የባሕርይ አምላክነቱን) ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ለማስመስከር፣ ውኃውን ለመቀደስ፣ የአዳምን ልጆች የእዳ ደብዳቤ ለመደምሰስና በስህተት የጠፋውን የልጅነት ክብር ለመመለስ ነው፡፡ ጌታ ተጠምቆ ከውኃው ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ በማረፍ አብ በደመና ‹‹ይህ ልጄ ነው›› ብሎ ሲመሰክርለት ምሥጢረ ሥላሴ አንድነትና ሦስትነት በጉልህ ተረጋግጧል፡፡ /ማቴ. 3፥16/

#ጌታችን_በዮሐንስ_እጅ_ለምን_ተጠመቀ?

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ሲሆን በአገልጋዩ በቅዱስ ዮሐንስ እጅ ይጠመቅ ዘንድ በፍጹም ትሕትና ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ ይህንንም ያደረገልን አብነት ሊሆነን ነው፡፡ ምክንያቱም ጌታችን ቅዱስ ዮሐንስን ‹‹መጥተህ አጥምቀኝ ›› ብሎት ቢሆን ኖሮ ነገ ነገሥታቱና መኳንንቱ ካህናቱን መጥታችሁ አጥምቁን ባሉ ነበር ስለዚህ እንዲህ እንዳይሆን ነው፡፡ ጌታችን ‹‹ጌታ ስሆን በባርያዬ እጅ እንደተጠመቅሁ እናንተም ወደ ቤተክርስቲያን ሄዳችሁ በካህናት እጅ ተጠመቁ›› ሲል ነው፡፡

ጌታችን በዮርዳኖስ የተጠመቀው ልጅነትን የምታሰጥ ጥምቀትን ባርኮ ቀድሶ ሊሰጠን እንጂ ክብር እንዲሆነው አይደለም፡፡ ምክንያቱም፡- እርሱ እከብር አይል ክቡር እጸድቅ አይል ጻድቅ ነውና፡፡

#ቅዱስ_ዮሐንስ_ጌታችንን_በማን_ስም_አጠመቀው?

ጌታችን ዮሐንስን አጥምቀኝ ባለው ጊዜ "ሌላውን በአንተ ስም አጠምቃለሁ አንተን በማን ስም ላጥምቅህ? በአብ ስም እንዳላጠምቅህ አብ አባትህ ባንተ ሕልው ነው በወልድ ስም እንዳላጠምቅህ ወልድ አንተ ነህ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዳላጠምቅህ መንፈስ ቅዱስ ሕይወትህ ባንተ ሕልው ነው ታዲያ በማን ስም ላጥምቅህ?" ብሎ ቢጠይቀው ጌታም ‹‹እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ የዓለም ካህን ብርሃንን የምትገልጥ የአብ የባሕርይ ልጅ ሆይ ይቅር በለኝ›› ብለህ አጥምቀኝ አለው፡፡

#ዮሐንስ_ጌታን_ሲያጠምቀው_እጁን_ለምን_አልጫነበትም?
- ዮሐንስ በጥምቀት አከበረው /ልዕልና ሰጠው/ እንዳይባል፡፡
- መለኮትን በእጅ መንካት ስለማይቻል

#ጌታችን_ጥምቀቱን_ለምን_በዮርዳኖስ_አደረገው?
በኢየሩሳሌም አካባቢ ብዙ ወንዞች ኩሬዎችና ሐይቆች መኖራቸው የታወቀ ነው፡፡ ጌታ ጥምቀቱን በዮርዳኖስ ያደረገው ስለዚሁ አስቀድሞ የተነገረውን ትንቢት መፈጸሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ‹‹ባሕር አይታ ሸሸች ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ›› /መዝ.113፥3/ ከዚህም ጋር ከላይ ምንጩ አንድ የሆነው ዮርዳኖስ ዝቅ ብሎ በደሴት ተከፍሎ እንደገና እንደሚገናኝ በግዝረት በቁልፈት (በመገዘርና ባለመገዘር) ተለያይተው የነበሩ ሕዝብና አሕዛብ መላው የአዳም ልጆች በጌታችን ጥምቀት አንድ መሆናቸውን የሚገልጽ ትርጉም አለው፡፡ እስራኤል ዮርዳኖስን ተሻግረው ምደረ ርስት ገብተዋል፡፡ ያመኑ የተጠመቁ ምዕመናንም በጥምቀት ገነት መንግሥተ ሰማያትን ይወርሳሉ፡፡ ሌላው በዮርዳኖስ ተጥሎ የነበረውን የዕዳ ደብዳቤ ይደመስስልን ዘንድ /ቈላ. 2፥14/

#ጌታችን_ለምን_በውሃ_ተጠመቀ?
እግዚአብሔር አምላክ በዘመነ ኦሪት ሰብዐ ትካትን በንፍር ውሃ ፈርኦንና ሰራዊቱን በኤርትራ ባሕር ካጠፋ በኋላ ሰዎች ውሃ ለመዓት እንጂ ለምሕረት አልተፈጠረም ይሉ ነበርና ለምሕረት እንደተፈጠረ ለማጠየቅ በውሃ ተጠመቀ ( ዘፍ 7÷17፤ ዘጸ 14÷1-29)

አንድም ውሃ እሳትን ያጠፋል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ከገሃነመ እሳት ትድናላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም ውሃ መልክን ያሳያል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ መልክዓ ሥላሴን የአምላክን ቸርነት ርህራሔ ታያላችሁ ሲል ነው፡፡

አንድም በማር በወተት ቢጠመቅ ኖሮ እነዚህ ለባለጸጎች እንጂ ለድሆች አይገኝም ውሃ ግን በሁሉ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ጥምቀት የታዘዘ ለሁሉ ነው ሲል ነው፡፡

አንድም ማርና ወተት ቢታጠብበት ያቆሽሻል እንጂ አያነጣም ውሃ ግን እድፍን ያስለቅቃል እናንተም በማየ ገቦ ብትጠመቁ ከኃጢአት ትጠራላችሁ ሲል ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Jan, 04:48


አንድም ማርና ወተት ተክል ላይ ቢያፈሱት ያደርቃሉ እንጂ አያለመልሙም ውሃ ግን ያለመልማል እናንተም በውሃ ብትጠመቁ ልምላሜ ሥጋ ወነፍስ ታገኛላችሁ ሲል ነው፡፡ (ዮሐ 19÷35)

#ጌታችን_ለምን_በሌሊት_ተጠመቀ?
በኃጢአት ጨለማ ስለነበረ ሕዝብ የጽድቅ ብርሃን እንዲወጣለትና በጨለማ የሚመስል ኦሪት ይኖር ስለነበረ ለሕዝብ ብርሃን የሆነ ወንጌል መገለጡን ለማሳየት ነው፡፡ ኢሳ.9፥2

አንድም ጌታ ልደቱ፣ ጥምቀቱ፣ ትንሣኤው እንዲሁም ምጽአቱ በሌሊት ነው፡፡ ይኽም የሆነበት ምክንያት፡- ሌሊቱን ተከትሎ የሚመጣው ብርሃን በመሆኑ ከሞት ወደ ሕይወት ከጨለማ ወደ ብርሃን ከሲኦል ወደ ገነት የመሸጋገራችን ምሳሌ ነው፡፡

አንድም መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል የሚወርድ ነውና በጌታ ላይ የወረደው ርግብ እንጂ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ባሉ ነበር፡፡ በሌሊት ርግብ የለም ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ ይታወቅ ዘንድ፡፡

#መንፈስ_ቅዱስ_ለምን_ጌታ_ከውኃ_ከወጣ_በኋላ_ወረደ?
ሀ. ዮሐንስን ያከብሩት ነበርና መንፈስ ቅዱስ የወረደው ለዮሐንስ እንጂ ለጌታ አይደለም ይሉ ነበርና ምክንያቱን ጌታ ውኃ ውስጥ እያለ ከዮሐንስ አልተለየም ነበርና፡፡
ለ. ውኃን የሚባርክ መልአክ እንዳለ ያውቁ ነበርና ውኃውን ለመባረክ አንጂ ለጌታ አይደለም እንዳይባል፡፡
ሐ. ማረፊያ ያጣች ርግብ በባሕር ስትበር አረፈችበት ይሉ ነበርና ሐሳባቸውን በሙሉ ያጠፋ ዘንድ ከውኃ ውስጥ ከወጣ በኋላ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ወረደ፡፡

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

19 Jan, 18:16


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የታቦታቱ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ መውረድ ከክርስቶስ ወደ ባሕር መሄድ ጋር እንዴት ተገናኘ?

👉   “ ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሓንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። (ማቴ ፫÷፲፫) እንደተባለው፦

#ጌታችን ከተጸነሰባት ካደገባት ከናዝሬት ገሊላ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ እንደሄ ታቦታትም ከማደሪያቸው ከመንበራቸው ተነስተው ወደባሕረ ጥምቀቱ ይሄዳሉ።

👉    “ ሕዝቡም ዅሉ ከተጠመቁ በዃላ ጌታ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። (ሉቃ ፫÷፳፩) እንደተባለው፦

#ጌታችን ከባሕረ ጥምቀቱ እንደደረሰ ኣልተጠመቀም ሕዝቡ ሁሉ ተጠምቀው ከጨረሱ በኋላ ነው የተጠመቀው ታቦታትም ወደ ባሕረ ጥምቀቱ እንደደረሱ ሳይሆን በተዘጋጀላቸው ቦታ ካረፉና ከቆይታ በኋላ ነው  ሥርዓተ ጥመቀቱ ይፈጸማል።

👉   “ ባሕር ዓየች ሸሸችም፥ ዮርዳኖስም ወደ ዃላው ተመለሰ። ” (መዝ ፻፲፫፥፫) እንደተባለው፦

#ጌታችን ወደ ዮርዳኖስ ለመጠመቅ ሲገባ ባሕረ ዮርዳኖስ እንደሸሸች እና ለሁለትም ተከፍላ እንደ ግድግዳ እንደቆመች (እንደተከተረች) ዛሬም ምዕመናን ከመጠመቃቸው በፊት ውኃ በተዘጋጀው ገንዳ ውስጥ ይከተራል በመቀጠልም ጌታችንም እንደተጠመቀ ምዕመናንም የመታሰቢያ ጥምቀትን ይጠመቃሉ።

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ 

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

18 Jan, 02:52


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ጾመ ጋድ እና ሰንበት

፩፦ ጾመ ጋድ በሰንበት ከዋለ ይጾማልን?
፪፦ ከቅዳሜ 7 ሰዓት ከእሁድ 2 ሰዓት ኣገናኝተን ጾመ ጋድ(ገሓድ) እንጾማለንን?
፫፦ በዕለተ በዓሉ የሚቆርቡ እንዴት ይጾማሉ?
 
#መልስ፦

፩፦ ጾመ ጋድ በሰንበት ከዋለ በሰንበት ጾም ስለማይፈቀድ ከፍስክ ምግቦች (ሥጋ ዕንቁላል….) በመከልከል ሌላ ምግብ በመመገብ እንውላለን ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ጾመ ገሓድ(ጋድ) በሰንበት ላይ ሲያርፍ እንደ ሌሎች የአዋጅ አጽዋማት ውስጥ እንዳሉ ሰንበታት ሰንበትነቱን በማይሽር መልኩ ይጾማል እንጂ ከምግብ በመከልከል መጾም አይገባም ለማለት ነው።

➙     የጥር 10 ስንክሳር "ወለእመ ኮነ በዓለ ልደት ወበዓለ ጥምቀት በዕለተ ሰኑይ ኢይትከሃል ከመ ይጹሙ በዕለተ ሰንበት ዳዕሙ ይትዓቀቡ እምነ በሊዕ ጥሉላተ" - "የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾሙ ዘንድ ኣይቻልም፤ ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይቆጠቡ" የሚለውን ነው። ስለዚህ ሰንበትም ሳይሽሩ ጾመ ጋድን ጠብቀው ያከብሩታል ማለት ነው።


፪፦ ከቅዳሜ 7 ሰዓት ከእሁድ 2 ሰዓት ኣገናኝተን ጾመ ጋድ(ገሓድ) እንጾማለን ለሚለው "ሰላም ዕብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ" (የስንክሳሩ አርኬ) ከሚለው ጋር ይጋጫል ጾመ ጋድ ቅዳሜን እስከ 7 ቆተው ከበሉ በኋላ እንደገና የእሁድ 2ሰዓት ኣገናኝተው የሚጾሙት ሳይሆን «ለጾመ ዕለት ዋሕድ/ የኣንድ ዕለት ጾም» እንዳለው በልደት እና በጥምቀት ዋዜማ በኣንድ ዕለት ሊፈጽሙት የሚገባ ጾም እንጂ ሁለት ዕለትን በማገናኘት የምንጾመው አይደለም ። ለምሳሌ ሌሎች የኣዋጅ አጽዋማት ዕለታቱ ከአንድ በላይ ናቸው ጾመ ነነዌን ብንመለከት ሦስት ዕለታት ነው በእነዚህ ሦስት የጾም ዕለታት በየዕለቱ እስከ ዘጠኝ እየጾምን እየበላን ብናሳልፋቸውም አንዱን ጾመ ነነዌን ለመጾም ነው ሦስት ዕለት ይጹሙ ይላልና።

➙    በሰንበት ስለሚሆነው ጾም ሊቃውንት ከቀዳም ስዑር (ከሰሙነ ሕማማት ቅዳሜ) ሳያጠቃልል ስለቀሪው ቅዳሜ እና እሁድ በሃይማኖተ አበው ላይ በእሁድ ሰንበት ቅዳሴው እስከሚፈፀም መጾም እንደሚገባ ሲገልጽ ስለቅዳሜ ግን እጾማለሁ የሚል ቢኖር « አላ ጊዜ ዘይደሉ እስከ ስድስቱ ሰዓት ወእመ አኮ እስከ ሰብዓቱ/ እሰከ ስድስት ሰዓት እስከ ሰባት ሰዓት ድረስ » በማለት ገልጾልናል። (ይህ በቀድሞ ጊዜ የቅዳሜ ቅዳሴ አርፍደው ይጀምሩ ስለነበር ቅዳሴው እስከሚፈጸም ስድስት ሰዓት ይሆን ስለነበር ስድስት ሰባት ሰዓት ድረስ ተባለ እንጂ በቅዳሜ ጾም ይገባል ለማለት አይደለም )
በዚህ መሠረት ቅዳሜና እሁድም ቅዳሴው እስኪፈጸም ከምግብ መከልከል ይገባል እንጂ በሰንበት መጾም አይገባም።

➙    ጥምቀት ሰኞ ቢውል እንደሚታወቀው የጥምቀት ቅዳሴ የሚጀምረው እንደልደት እና ትንሳኤ ሌሊት 6 ሰዓት ሳይሆን ሊነጋጋ ሲል ወደ 10 ሰዓት ላይ የሚጀምር በመሆኑ ይህን ታሳቢ በማድረግ 18 ሰዓት አስልተው ከምግብ መከልከል ይገባል። በዚህም ሰንበትን ሻሩ አይባልም ጠዋት ተመግበዋልና ለመቊረብ ብለው ለ18 ሰዓት ከምግብ ተከለከሉ እንጂ ሰንበትን ሽረው ጾሙ ማለት አይደለም። ይቆየን

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

10 Jan, 03:25


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የጌታችን ልደት በቅዱስ አምብሮስ

#ማርያም ከተፈጥሮ ሕግ በተቃራኒው በኾነ መንገድ ልጅ ወለደች የሚለው ለምንድን ነው አልታመን ያለው? ከተፈጥር ሕግ ውጭ ባሕር ዐየች ሸሸችም ዮርዳኖስም ወደ ኋላዋ ተመለሰች ተብሎ አይደለምን? መዝ 113÷3፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ከዓለት ውኃ ፈልቋል ዘጸ 17፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ውኃው እንደ ግድግዳ ቆሟል ዘጸ 14÷6፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ብረቱ በውኃ ላይ ተንሳፍፏል፣ ከተፈጥሮ ሕግ ውጭ ሰው በባሕር ላይ ተራምዷል” እያለ ይህ ታላቅ ሊቅ የእመቤታችንን ድንግልና ላለመቀበል ምንም ዓይነት ምክንያት መፍጠር እንደማንችል ይገልጥልና።

#ስለዚህ በጌታችን የልደት ዕለት ከሰው ልጆች ልቦና የጥርጣሬ ድንጋይ ተነቅሎ ይወድቃል የተፈጥሮን ሕግ የሚቃረነው የድንግል በድንግልና መውለድ ይመሰከራል!! ዛሬ ሊብራሩ የማይችሉ ልዩ ኹነቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነው፡፡ አምላክ የሰውን ሥጋና ነፍስ ተዋሕዶ ሰው ኾኖ የተገለጸበት፤ ድንግልም የማይወሰነውን አምላክ በማኅፀኗ ከመወሰንም አልፋ በታተመ ድንግልና የወለደችበት ዕለት ነው።

#ድንግል ወለደች ተብሎ ከተፈጥሮ ሕግና ሥርዓት ውጭ በኾነ መንገድ የሚገለጽበት ልዩ ዕለት!  የተፈጥሮ ባለቤትን በንጽሕት ሙሽራ በደንግል ማርያም ማኅፀን የራሱን ቤት በተዋሕዶ ሠርቶ የወጣበት ዕለት። ዛሬ ሰማይ ወለደች እንላለን፤ ግን ይህቺ ሰማይ ግሳንግሱ ፀሐይ የሚታይባት ሰማይ ሳትኾን የማይታየው ፀሐይ የሚታይባት ሰማይ ናት።

#በዓለምም ከዓለም ውጭ ያለው ጌታ በቤተልሔም የታየበት ዕለት ነው፡፡ ይህ ሲባል አጥርተው ማየት በማይችሉ ዘንድ ውስን ብቻ የሚመስል÷ ነገር ግን በቅድስና መስታወት ለሚያዩት በአርያምም እየተመሰገነ በቤተልሔም የተወለደበት ዕለት ነው። ሰይጣን የደነገጠበትና ኃይሉ የደከመበት ዕለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በልደቱ ስፍራ መኾን አጋንንትን እንዳይቀርቡን ያደርጋል እልፍ አእላፋት መላእክት በዚያ ከበው ይጠብቁናልና። ተፈጥሮአዊውን ሕግ የገለበጠው ጌታ የተፈጥሮን ሕግ የሠራውና እንደፈቃዱም የሚያደርገው እርሱ መኾኑን ያወቅንበት ዕለት ነው። እንኳን በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ!

👉 ምንጭ ፦  "ትምህርተ ጽድቅ"  (ዲ . ዮሐንስ ጌታቸው)

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

08 Jan, 06:46


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የጌታችን ልደት በዮሐንስ ዘክሮንስታድ

#እኛን ከምድር አፈር የፈጠረንና የሕይወትን እስትንፍስ እፍ ያለብን ወደ ዓለም መጣ፤ በአንዲት ቃል ብቻ የሚታዩትንና የማይታዩትን ፍጥረታት ካለመኖር ወደመኖር ያመጣቸው እርሱ መጣ። ... የእርሱ መምጣት እንዴት ያለ ትሕትና ነው!! ምድራዊ ሀብት ከሌላት ድንግል በአንዲት ጎጆ ተወለደ፤ በድህነት ጨርቅ ተጠቅልሎም በበረት ተኛ።” እያለ የክርስቶስን በትሕትና መምጣት ያስረዳናል።

#ይህቺ ዕለት ትሕትና በምድር ላይ የታየችበት የትሕትና ዕለት ናት። አዳም በትዕቢቱ ከቀደመ ክብሩ ቢዋረድም ክርስቶስ በትሕትና ከቀደመው ወደተሻለ ቦታ ከፍ አድርጎ አወጣው። በእርግጥ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾኖ የተገለጠበት አንዱ ምክንያት ለአርአያነት ስለኾነ÷ በትሕትና መታየቱ የሰው ልጅ ወደ መዳን ለመግባት የትሕትናንን ትምህርት ከራሱ ከባለቤቱ መማር ስላለበት ነው። በጌታችን የልደት ዕለት በትዕቢት የሚመላለሱ ልቦናዎች የጌታችንን የልደት ዕለት የረሱ ልቦናዎች ናቸው። እጅግ ዝቅ ማለት እጅግ ከፍ ያደርጋል፤ አምላክ ሰው ኾነ የሚለውን መስማት በምንም ቋንቋ ሊገለጥ የማይቻል እጅግ ጥልቅ የኾነ የትሕትና ውቅያኖስ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ነው የማይቆጠሩ ብዙ ጸጋዎችን ልናገኝ የቻልነው። እንግዲህ በዚህች ዕለት የትሕትናንን ትምህርት ቁጭ ብሎ መማርና የትሕትና መምህራችንን ማመስገን ያስፈልገናል። በዚህች ዕለት በተድላ ሥጋ ኾነው ስለ ትሕትና መምህር ስለክርስቶስ የመወለድ ምሥጢር ሳይማሩና በምሳሌ ሳይኾን በተግባር ወደ ጌታችን የልደት ዕለት ወደምትወስደን ቅድስት ቤተልሔም ለማድነቅና በምስጋና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ለመደመር አለመሄድ እንዴት ያለ አለመታደል ነው!
ቃል ሥጋ የኾነው እኛን ከምድራዊ አኗኗር ወደ ሰማያዊ አኗኗር ለማሸጋገር ነው፡፡ ኀጥአንን ጻድቃን ለማድረግ፣ ከመበስበስ አንሥቶ ወዳለመበስበስ ሊያስነሣን፣ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባርያ ከመኾን የእግዚአብሔር ልጅ ወደመኾን ሊያሻግረን፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት፣ የእግዚአብሔር ልጆች ተብለን ከእርሱ ጋር የንጉሥ ልጆች አድርጎ ሊያከብረን መጣ፡፡ አቤት ገደብ የለሽ የእግዚአብሔር ርኅራኄ! አቤት የማይገለጽ የእግዚአብሔር ጥበብ! አቤት ታላቅ መደነቅ! የሰውን አእምሮ ብቻ የሚያስደንቅ ሳይኾን የቅዱሳን መላእክትን ጭምር ነው እንጂ!። የዛሬውን ዕለት ማክበር ማለት እነዚህን ኹሉ ጸጋዎች ለማግኘት መብቃት ማለት።

#በዛሬው ዕለት ውስጥ ወደ መደነቅ ከፍ ያላለ ፍጥረት ማግኘት ፈጽሞ የማይቻል ነው። የእግዚአብሔር ጥበብ የጠላታችንን ጥበብ ያፈራረሰበት ዕለት ነው። የጌታችንን የልደት ዕለት በማያቋርጥ ምስጋና ልናክብር የሚገባን ከላይ የተዘረዘሩትን ልዩ ስጦታዎች ለመቀበል ነው። አንድ ሕፃን ልጅ በልደቱ ዕለት ስጦታ ቢሰጠው ገና እንደተወለደ ስጦታውን ስጦታ መኾኑን ተረድቶ ሊቀበል አይችልም፡፡ ዛሬ የምናከብረው የልደት ዕለት ግን ሕፃኑ ራሱ ልደቱን ለማክበር ለመጡት በቃላት የማይገለጽ ስጦታ የሰጠበት ዕለት ነው።

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

07 Jan, 11:37


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የጌታችን ልደት በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#የቅድስና ኹሉ ሰጭ ወደዚህ ዓለም የገባው በንጹሑ ልደት በኩል ነው። የቀደመው አዳም ከድንግል መሬት ተገኘ፤ ከእርሱም ያለ ሴት ዕርዳታ ሴት ተገኘች። ልክ አዳም ያለ ሴት ሴትን እንዳስገኘ፤ ድንግልም ያለ ወንድ በዚህ ዕለት ወንድን አስገኘች። ስለዚህ ሴቶች ለወንዶች ዕዳቸውን ከፈሉ፤ አዳም ብቻውን ሔዋንን እንዳስገኘ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። አዳም ያለ ሴት ሴትን ስላስገኘ ሊኩራራ አይገባም፤ ድንግልም ያለ ወንድ ወንድን አስገኝታለችና። በምሥጢሩ ተመሳሳይነት የተፈጥሮው ተመሳሳይነት ተረጋገጠ። ከአዳም ጎን አንዲት አጥንት ወሰደ ነገር ግን አዳም ጉድለት አልተገኘበትም÷ በተመሳሳይ ከድንግል ወንድ ልጅ ተወለደ ድንግልናዋ ግን አልተለወጠም” እያለ በሚያስደንቅ መንገድ የቅድስት ድንግል ማርያም ድንግልናን በአዳም ኅቱመ ጎን በኩል ያሳየናል”። ይህ የልደት ቀን የቅድስት ድንግል ማርያምን ክብር ከማሳየቱም አልፎ ሴቶችን እንዴት እንደካሰቻቸው ፍንትው አድርጎ ያመለክተናል። የጌታችን የልደት ዕለት ማለት የሴቶች ክብር የተገለጠበትና ወንድና ሴት እኩል መኾናቸው የተረጋገጠበት ዕለት ነው። “ሴቶች ሆይ የሴትነትን ክብር ያስመለሰችላችሁን ቅድስት ድንግል ማርያምን ትረሷት ይኾንን?”። ድንግል በድንግልና ወለደች ሲባል ሰምተን እንዳንደናገጥና ወደ ጥርጣሬ ባሕር ውስጥ እንዳንገባ አስቀድሞ አዳም ብቻውን ሔዋንን ሲያስገኝ ያለውን ነገር በመጽሐፍ አጻፈልን። አዳም ሔዋንን ብቻውን ከጎኑ እንዳስገኘ አምኖ የተቀበለ ሰው እንዴት ድንግል ማርያም በድንግልና ወለደች ሲባል ለማመን ይከብደው ይኾን? በጣም የሚያስገርመው ሔዋን ከአዳም ጎን ብትወጣም ለአዳም ውድቀትም ምክንያት ኾና ነበር፤ ድንግል የወለደችው ግን ዓለምን በሙሉ የሚያድን አምላክ ነው።

#እንግዲህ በዚህ ዕለት የዓለም መድኃኒት ከድንግል ማኅፀን በቀለ!! ዓለም በሙሉ የተጠማውን የሕይወት ውኃ ለመጠጣት የተዘጋጀበት ዕለት ነው። ይህን ዕለት በመንፈሳዊ ደስታ ደስ ተሰኝተን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልናከብር ይገባናል እንጂ፤ በዘፈንና በስካር በቆሸሸ ሀሳብ በዓሉን አናበላሸው ። የልደቴ ቀን እያልን በቤታችን ኬኩን እና ሌላውን ሁሉ የምንበላ ኹሉ እውነተኛውን የልደት ቀን ማወቅ ከፈለጋችሁ ይህ ነው የልደታችሁ ዕለት/ቀን። በዚህ ቀን ጌታችን ስለሁላችን ድኅነት ብሎ ስለተወለደ የእርሱ የልደት ዕለት የእኛም የልደት ዕለት ነው። አዲስ አድሮጎ ሊወልደን በአምሳላችን ፈጣሪያችን የተወለደበት ዕለት የልደት ዕለታችን ኾኖ ካልተከበረ የቱ ቀን ሊከበር ነው። ዛሬ እውነተኛ ብርሃን ጨለማችንን ያርቅልን ዘንድ የወጣበት ዕለት ነው።

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

07 Jan, 10:06


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ለብርሃነ ልደቱ ያደረሰን ጌታ ይክበር ይመስገን የበረከት በዐል ያድርግልን

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

02 Jan, 14:43


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

"ተክለ ሃይማኖት ፀሐይ ነፍሴን አደራ በሰማይ"

የፃድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋር ትሁን ። አሜን !!!

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

31 Dec, 19:45


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ለአብሳሪነት_ቅዱስ_ገብርኤል_ለምን_ተመረጠ?

ቅዱስ ሚካኤልና ፣ ቅዱስ ሩፋኤል .... አልነበሩምን? ስለምን ቅዱስ ገብርኤልን ላከባት? ቢሉ

1፦ እስመ አብሣሬ ጽንስ ውእቱ” እንዳለ፣ ጥንቱን ቅዱስ ገብርኤል አብሣሬ ጽንስ ነው:: አስቀድሞ ማኑሄንና እንትኩይን ሶምሶንን ትወልዳላችሁ ብሎ፣ ዘካርያስና ኤልሳቤጥን ዮሐንስን ትወልድላችሁ ብሎ፣ ኢያቄምንና ሐናንም ማርያምን ትወልዳላችሁ ብሎ፣ የነገራቸው ገብርኤል ነውና ጥንት በለመደው ግብር ይሁን ሲል ገብርኤልን ላከበት:: “ዓቢይ ውእቱ ክብር ዘተውህበ ለከ ኦ ገብርኤል መልአክ ዜናዌ ፍሡሐ ገጽ ሰበከ ለነ ልደተ እግዚእ ዘመጽአ ኀቤነ ወአብሠርካ ለማርያም ድንግል ዘእንበለ ርስሐት ወትቤላ ተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልዕተ ፀጋ እግዚአብሔር ምስሌኪ” እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም (የረቡዕ ውዳሴ ማርያም ) ::

2፦  ጌታ ገብርኤልን በስም ይተባበረዋል ገብርኤል ማለት አምላክ ወሰብእ፣ እግዚእ
ወገብር፣ ፈጣሪ ወልደ እጓለ እመሕያው፣ ወልደ እግዚብሔር የሚሆንበት ቀን ነውና በስመ ትርጓሜው ገብርኤልን ላከባት:: “ወራብዑሰ ይመስል ገጹ ከመ ገጸ ወልደ እግዚአብሔር”
እንዲል “ኮነ ወልደ እጓለ እመሕያው አምላክ ዘበአማን” እንዳለ፡፡
- ቅዱስ ኤፍሬም “ሚካኤል ብሂል ዕፁብ ነገር፣ ገብርኤል ብሂል ወልደ እግዚአብሔር” እንዳለ ቅዱስ ያሬድ:: (ለ 2 ኛው የበለጠ ማብራሪያ ከፈለጉ " ገብርኤል የሚለው ስም ለወልድ ተሰጥቶ መነገሩ ስለምንድን ነው " በሚል ርዕስ ከዚህ ቀደም ያቀረብነውን ጽሑፍ ይመልከቱ።

3፦  ገብርኤል የሥላሴ ባለወሮታ ነውና።

መላእክት በተፈጠሩ ጊዜ  “እምአይቴ መጻእነ ወመኑ ፈጠረነ” /ከየት መጣ? ማን ፈጠረን? / ብለው ቢሸበሩ ዛሬ መልካም ጐልማሳ ባጭር ታጥቆ፣ ጋሻ ጦሩን ነጥቆ፣ አይዞህ ባለህ እርጋ፣ ጽና፣ ብሎ ሰልፍ እንዲያረጋጋ ቅዱስ ገብርኤልም ፈጣሪያችንን እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንጽና ብሎ አረጋጋቸው:: “ንቁም በበህላዌነ እስከ ንረክቦ ለአምላክነ ወአኅድዖሙ መልአከ ሰላም በቃሉ” እንዲል (አክሲማሮስ ፶፬)

-  ይህን በተናገረበት ቃሉ የጌታችንን ሥጋዌ ለመናገር የእመቤታችንን ባለ ብሥራት ለመሆን
አበቃው:: ወበእንተዝ ደለዎ ለገብርኤል ከመ
ይፁር ዜናሃ ለማርያም” እንዲል፡፡ (መቅድመ ወንጌል)

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተሰፋዬ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

28 Dec, 02:54


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ታህሳስ 19

#እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል:
ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።

#ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ቀን ነው፡፡

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

27 Dec, 06:02


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#እውነተኛ ጿሚ ራሱን ከክፉ ምግባራት የከለከለ፤ ከንቱ የሆኑ ንግግሮችን ከመናገር የተቆጠበ፣ ሐሰትን የማይናገር፣ ሐሜተኛ ያልሆነ፣ በማንም ላይ የማይፈርድ፣ ሽንገላን የማይወድና እኒህንም ከመሰሉ ነገሮች ራሱን የተጠበቀ ፣የማይቆጣ፣ የማይበሳጭ ፣ተንኮለኛ ያልሆነ፣ ቂመኛ ያልሆነና፣ እነዚህን ከመሳሰሉ ክፋቶች ሁሉ የራቀ ሰው ነው፡፡

#ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ ከስድብ፣ ከውሸት ፣ከማታለል፣ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡''

#ቅዱስ ኤፍሬም

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

19 Dec, 06:16


🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱

#እግዚአብሔር አባታችን እስከ ሽበት እንኳን ተሸክሞን አይሰለቸንምና ከቤቱ ያውም ከእቅፉ አንውጣ ። (ኢሳ 46፥4)

#አቤቱ የቤተ መቅደስህ ተክል ያደረከኝ የውጪ ተክል አታድርገኝ !!! (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ መጽሐፈ አርጋኖን ዘአርብ)

🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

18 Dec, 09:43


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ ። (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4:29)

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

17 Dec, 06:09


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ምጽዋት ሥርየተ ኃጢአትን ትሰጣለች፡፡ ሞትንም ቢኾን ታርቃለች፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም ቀጥዬ ግልጽ አደርግልሃለሁ፡፡

#“መጽውቶ ከሞት የተረፈ ማን አለ?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ ወዳጄ ሆይ! ምጽዋት ሞትን እንድታርቅ ኃይል ጉልበት እንዳላት በእውን ከተደረገ ታሪክ ተነሥቼ እነግርሃለሁና የምነግርህን ነገር አትጠራጠር፡፡

#ጣቢታ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፡፡ መልካም ሥራን የሞላባትና ምጽዋትን የምትወድ በዚህም ለራሷ መዝገብ የምታከማች ነበረች፡፡ ለመበለቶች ልብስንና የሚያስፈልጋቸውን ኹሉ ትሰጣቸው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንዱ ቀን ግን ሞተች፡፡

#አሁን ደግሞ እነዚያ እርሷ ስትረዳቸው የነበሩ መበለቶች በየትኛው ሰዓት ብድራታቸውን እንደሚከፍሉ ተመልከት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን መበለቶቹ ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ኼዱ፡፡ ጣቢታ የሰጠቻቸውን ልብስንና ሌላውን ኹሉ አሳዩት፡፡ ከእነርሱ ጋር በሕይወተ ሥጋ ሳለች ምን ምን ታደርግላቸው እንደ ነበረች ነገሩት፡፡ እንደ እናት የምትኾንላቸውን እንደ አጡ አልቅሰው ነገሩት፡፡ ስለ እነርሱ እጅግ እንዲያዝንም አደረጉት፡፡ 

#የተወደደ ጴጥሮስስ ምን አደረገ? “ኹሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮ ጸለየ፡፡ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ ‘ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ’ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች፡፡ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች፡፡ እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፡፡ ምእመናንንና መበለቶችንም ጠራ፡፡ ሕያውም ኾና በፊታቸው አቆማት”  (ሐዋ.9፥40-41)፡፡

#የሐዋርያውን ኃይል ወይም በሐዋርያው አድሮ እግዚአብሔር ምን እንዳደረገ አስተዋልህን? በወዲያኛው ዓለምስ ተወውና በዚህ ዓለምም ሳይቀር ጣቢታ ስለ መልካም ሥራዋ ምን እንደ ተቀበለች ተገነዘብን? እርሷ ለመበለቶች የሰጠችውንና መበለቶቹም ለእርሷ የሰጡትን አየህን? እርሷ ምግብና ልብስ ሰጠቻቸው፤ እነርሱ ግን ከሞት ወደ ሕይወት እንድትመጣ አደረጓት፡፡ ለመበለቶቹ ባሳየችው ቸርነት ቸሩ እግዚአብሔር ብድራቷን ከፈላት፡፡ 

#እንግዲህ የምጽዋት የመድኃኒትነቷን ኃይል ተመለከትህን? እንግዲያውስ እኛም ይህን መድኃኒት ለራሳችን እናዘጋጅ፡፡ መድኃኒቱ ይህን ያህል ጽኑ መድኃኒት ቢኾንም ቅሉ እጅግ ርካሽ እንጂ ውድ አይደለምና ለራሳችን እንግዛ፡፡ ይህን መድኃኒት ለመግዛት ብዙ ወጪ አይጠይቅምና እንግዛ፡፡ መልካም ሥራ መልካም የሚባለው በሚሰጡት ገንዘብ መጠን ሳይኾን በሚሰጡት የእደ ልብ ስፋት መጠን ነውና እንግዛ፡፡ አንድ ሰው አንዲት ኩባያ ቀዝቃዛ ውኃ ሰጥቶ እጅግ እንደ ሰጠ የሚቈጠርለትም እግዚአብሔር ከእያንዳንዳችን የሚሻው ወደንና ፈቅደን የምንሰጠው በጎ ፈቃዳችንን መኾኑን የሚያሳይ ነውና ይህን እንግዛ፡፡ መበለቶች፥ እንደ ጣቢታ ከሞተ ነፍስ ይታደጉን ዘንድ ይህን መድኃኒት ከእነርሱ እንግዛ፡፡

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ አምስቱ የንስሐ መንገዶች

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

12 Dec, 04:08


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#በዓታ ለማርያም

#ታኅሣሥ 3 ቀን የሚታሰበውና የሚከበረው በዓል ‹‹በዓታ ለማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡ ከእናቷ ከቅድስት ሐና እና ከአባቷ ቅዱስ ኢያቄም በስዕለት የተወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት የከበረ እንደመሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ታከብረዋለች፡፡   

#በዓት ቃሉ የግእዝ ሲሆን ቤት ማለት ነው፡፡ ደጋጎቹ የእግዚአብሔር ሰዎች ቅዱስ ኢያቄምና ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው ለብዙ ዘመናት ከመኖራቸው የተነሣ በኀዘን ፈጣሪያቸውን ሲማጸኑ ቃል በመግባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት በእግዚአብሔር ቤት ትኖርና ታገለገል ዘንድ በቤተ ክርስቲያን እንድትኖር ስለሰጧት በዓሉም ስያሜውን በዚያ መሠረት አግቷል፡፡  
በዚያን ጊዜም በቤተ ክርስቲያን ያገለግል የነበረው ካህኑ ዘካርያስ ስዕለታቸውን አስተውሶ ቅድስት ድንግል ማርያምን ሊቀበላት ሲቀርብ እንደ ፀሐይ የምታበራ ሕፃን ሆና አገኛት፤ በመገረምና በመጨነቅም ከወላጆቿ ጋር ምን ሊመግቧት እንደሚችሉ በመጨነቅ ላይ ሳሉ ሕዝቡ በተሰበሰበበት መካከል መልአኩ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ ጽዋዕ ይዞ ከሰማይ ወረደ፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ለእርሱ የመጣ መና መስሎት ሲቀረብ ወደ ላይ ተመለሰበት፡፡ በዚያ የተሰበሰቡት ሰዎችም እያንዳንዳቸው ቢሞክሩ በተመሳሳይ መልኩ ተመልሶ ወደ ላይ ራቀባቸው፡፡ ‹‹ምን አልባት ለእንግዶች የመጣ ሀብት እንደሆነ›› ብለው ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም እንዲቀርቡ ቢደረግም ለእነርሱም ራቀባቸው፡፡ ካህኑ ዘካርያስም ቅድስት ሐናን ‹‹እግዚአብሔር የሚያደርገውን የሚያውቅ የለምና ልጅቷን ትተሸ ወደዚህ ነይ›› አላት፤ ሆኖም ግን ቅድስት ማርያም እናቷ ትታት ስትሄድ መከተል ጀመረች፤ ምርርም ብላ አለቀሰች፡፡

#በዚህም ጊዜ መልአኩ ፋኑኤል ወደ እርሷ ቀርቦ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ጋርዶ መገባት፤ ከዚያም በክብር ዐረገ፤ ሊቀ ካህናቱና ሕዝቡም ‹‹የምግቧ ነገር ከተያዘልን በቤት እግዚአብሔር ትኑር›› ብለው ወደ ቤተ መቅደስ አስገቧት፡፡
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ሰማያዊ ኅብስትና መጠጥ እየተመገበች  በቤተ መቅደስ  ለ፲፪ ዓመታትም ኖራለች፡፡
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን፤ በረከቷ ይደርብን፤አሜን! 

#ምንጭ፡- ነገረ ማርያም

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

09 Dec, 06:42


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ተወዳጆች ሆይ! ማለፍ መለወጥ በሌለባት በመንግሥተ ሰማያት ጸጋንና ክብርን እናገኝ ዘንድ በምግባር በትሩፋት እናጊጥ፡፡ በዚህ ዓለም የሚኖረን ውበትና ጌጥ ድንገት ታይቶ የሚጠፋ ነው፡፡ የማይቻል ቢኾንም ምንም በሽታ፣ ኀዘን፣ ብስጭት፣ ይህም የመሳሰለ ኹሉ ባያገኘን እንኳን የዚህ ዓለም ውበትና ጌጥ ሃያ ዓመት ነው፡፡ በወዲያኛው ዓለም የሚሰጠው የሚገኘው ክብር ግን በዝቶ ሲሰጥ ይኖራል እንጂ መቼም ቢኾን መች አያልፍም፡፡ አይለወጥም፡፡ እርጅና የለምና ቆዳው አይጨማደድም፡፡ ደዌ ሥጋ ደዌ ነፍስ አያገኘውም፡፡ ኀዘን አያወይበውም፡፡ በዚያ የምናገኘው ክብር፣ ውበት፣ ጌጥ ከዚህ ኹሉ የተለየ ነው፡፡ በዚህ ዓለም የምናገኘው ክብርና ውበት ግን የሚጠፋው ገና ከመምጣቱ ነው፡፡ ቢመጣ እንኳን አድናቂዎቹ ብዙ አይደሉም፡፡ ትሩፋትን ጌጥ ያደረጉ ሰዎች አያደንቁትም፡፡ የሚያደንቁት አመንዝሮች ናቸው፡፡

#ስለዚህ ከዚህ ዓለም ከኾነው ክብር ልንለይ ይገባናል፡፡ መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ ልንፈልገው የሚገባን ትሩፋትን ነው፡፡

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

03 Dec, 11:25


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ኃጢአት ጸሎት የማቋረጥ ውጤት ነው። እውነተኛ ጸሎት ኃጢአትን የማቆም ምልክት ነው። ሰው ኃጢአትን ልምዱ ካላደረገ በቀር እየጸለየ የሚበድል፣ ከአምላኩ ጋር እየተነጋገረ የሚያምጽ የለም። አዳም እጸ በለስን የቆረጠው ከአምላኩ ጋር የነበረውን ንግግር (ጸሎቱን) በማቋረጡ ነው። ይኸውም አዳምን ጠርቶ "ወዴት ነህ?" ባለው በፈላጊው ድምጽ ተረጋግጧል።

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

23 Nov, 17:53


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#በውጭው ካሉት ይልቅ በአንተ ውስጥ የሚገኙት ፍትወታት ጠንካራ ጠላቶችህ ናቸው። ልክ ያልተሠራለት ምኞት ከባቢሎን እሳት ይልቅ ያቃጥላል። አልጠግብ ባይነትም ከጥፉት ውኃ ይልቅ ያሰጥማል። ያልተገራ ፍላጎት ማንነትን አስጥሎ የሰይጣን ባሪያ ያደርጋል። ራስን መግዛት የሰው ልጆች ጌጥ ነው። ዮሴፍ ግብጽን ከፈርዖን ሁለተኛ ሆኖ ከገዛበት ታላቅ ሥልጣን ይልቅ፣ በጌታው ሚስት ፊት ያሳየው ራስን መግዛት ይበልጥ ይደነቃል። ጠቢቡ "በመንፈሱ ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ (ከሚገዙ) ይበልጣል" እንዳለ።(ምሳ 16፥32)

#ራስህን ነጻ ማውጣት ትፈልጋለህ? እንግዲያውስ ከውስጥህ ጀምር። ሁል ጊዜ ካልበላሁ የሚለው ሆድህ ስስት አስለምዶ በወንድምህ ላይ ጨካኝ እንዳያደርግህ ለሰውነትህ ጾም አስተምረው። "ነገ እሞታለሁና ልብላ ልጠጣ" የሚለውን የዐሣማ ፍልስፍናህን (Pig philosophy) ተውና አንተ በፈቃድህ እየተራብህ (እየጾምህ) ያለ ፈቃዱ የተራበው ወንድምህን በምጽዋት አጥግበው።

#ጌታ ወደ ገሊላ የተመለሰው ሄሮድስ ከሞተ በኋላ ነበር።(ማቴ 2፥20) አንተ ውስጥ ያለውን ሄሮድስ የተባለ ክፉ ምኞት እንዲሞት ካላደረግኸው በቀር የተሰደደው ክርስቶስ ወደ አንተ ሊመለስ አይችልም። ይህ ክርስቶስን ከልብህ የሚያሳድድብህን ሄሮድስ እንዴት ልትገድለው ትችላለህ? እርሱንስ ወግተህ የምትጥልበት የብረት ካስማ ምን ይሆን? ለዚህስ ከጾም እና ከጸሎት የሚበረታ ምንም ዓይነት የጦር ዕቃ አታገኝም። በል እነዚህን ይዘህ ዝመትበት።

#መልካም የነቢያት ጾም ይሁንልን!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Nov, 15:59


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ
ቅዱስ ሚካኤል ሆይ የተቸገሩትን የተጨነቁትን ዘወትር እንደምትረዳቸው ሁሉ በጠራንህ ጊዜ እኛንም ለመርዳት ክንፍህን ዘርግተህ ፈጥነህ ድረስልን ። #አሜን በእውነት

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Nov, 07:46


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ህዳር 11 በዚች ዕለት አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እናቷ የሆነች የተመሰገነች የቅድስት ሐና የእረፍቷ መታሰቢያ ነው ።

#ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅድስት ሐና ጸሎት ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ትሁን ለዘለዓለሙ አሜን !!!

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

20 Nov, 07:11


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

ለወፎች ክንፍ የተሰጣቸው በወጥመድ እንዳይያዙ ነው። ሰዎችም የማሰቡ ኃይልን የተሰጣቸው ኃጢአትን እንዲያስወግዱ ነው።

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

19 Nov, 08:52


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የምክር ቃል ከቅዱስ ኤፍሬም

#ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

#ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

08 Nov, 12:53


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ልጆቼ! በድህነቴ ላይ ቸርነትን አድርጉልኝ፡፡ በዚህስ አልችልም ካላችሁ እሺ በቁስሌ ላይ ዘይትን አፍስሱልኝ፡፡ አሁንም ይህን ማድረግ ካልቻላችሁ ወደ እኔ ጠጋ በሉና አናግሩኝ፡፡ እናንተን ማየት፣ ከእናንተ ጋር መጨዋወት ይናፍቀኛልና፡፡

#በገዛ ደሜ የገዛኋችሁ ልጆቼ! ከባድ ነገር እኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እኔ የምፈልገው ትንሽ ዳቦ፣ ጊዜአዊ ማደርያ፣ እንዲሁም የሚያጽናኑ ቃላትን ብቻ ነው፡፡ “ይህ ሁሉ ማድረጌ ምን ይጠቅመኛል?” ካላችሁ ስለ ምሰጣችሁን ርስት መንግሥተ ሰማያት ብላችሁ አድርጉት፡፡ አሁንም ልባችሁ አልተነካምን? ስለ መንግሥተ ሰማያት አታድርጉት፤ ግን ደግሞ ስለ ሰብአዊ ርኅራኄ ይህን አድርጉልኝ፡፡ የእኔን መራቆት የሚያሳዝናችሁ በቀራንዮ አደባባይ ስለ እናንተ ብዬ የተራቆትኩት ብቻ ነውን? ታድያ አሁንም ‘ኮ በደጃችሁ ላይ ተጥዬ ዕራቆቴን ነኝ፡፡ ለምን አላዘናችሁልኝም? የታሰርኩት በቀራንዮ ብቻ ነውን? አይደለም፡፡ ታድያ እንደምን አታዝኑልኝም?

#የማፈቅራችሁ ልጆቼ! በመስቀል ላይ ተሰቅዬ ሳለሁ “ተጠማሁ” እንዳልኩ ዛሬስ ስለ እናንተ ብዬ ደጋግሜ ይህን ቃል አልተናገርኩምን? ጕሮሮዬ ደርቆ ስለምን ትንሽ እንኳ አላሳዝናችሁም? ስለምንስ ይህ ሁሉ ፍቅር ስለ እናንተ መሆኑን ትዘነጉብኛላችሁ? የምለምናችሁ እናንተን ባለጸጋ ለማድረግ አይደለምን? ይህችን ትንሽ ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ በዐይን ያልታየች፣ በጀሮ ያልተሰማች፣ በሰውም አእምሮ ያልታሰበች ርስት መንግሥተ ሰማያት እንድታገኙ ብዬ አይደለምን? ስለ እናንተ ብዬ ደሀ የሆንኩት ያኔ በመዋዕለ ሥጋዌዬ ብቻ እንደሆነ አታስቡ ልጆቼ! ዛሬም ቢሆን በደጃችሁ የተጣልኩት ስለ እናንተ ጥቅም እንደሆነ ተረዱልኝ፡፡

#ከባድ ነገር ‘ኮ አልለመንኳችሁም፡፡ እስር ቤት መጥታችሁ ጠይቁኝ እንጂ አስፈቱኝ አላልኳችሁም፡፡ ታምሜ ጠይቁኝ እንጂ ፈውሱኝ አላልኳችሁም፡፡ ከጠየቃችሁኝ ብቻ በቂዬ ነው፡፡ እስኪ ልጠይቃችሁና እናንተም መልሱልኝ! በዚያ በአስፈሪው ቀን ስመጣ “ኑ እናንተ የአባቴ ብሩካን” የሚለውን ቃለ ሕይወት መስማት አትፈልጉምን? ዛሬ የሰጣችሁኝ ሁሉ የምረሳ ይመስላችኋልን? ያኔ በክብር ስመጣ ከእልፍ ወለዱ ጋር እንድሰጣችሁ አትሹምን? የማፈቅራችሁ ልጆቼ! ከደጃችሁ ተጥዬ የምለምናችሁ፣ ከበራችሁ ላይ ቆሜ ማደርያን የምጠይቃችሁ፣ እጄን ዘርግቼ እናንተን እናንተን የማየው ያኔ ትሉ ወደማይጠፋው እሳቱ ወደማያንቀላፋው እሳት እንዳትሄዱብኝ ብዬ ነው፡፡ ታድያ ይህን ለምን አትረዱልኝ ልጆቼ? ስለምን እንዳስቸገርኳችሁ ታስባላችሁ? ለእናንተ ጥቅም እንደሆነ እንዳትረዱ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው? ከእናንተ ጋር ቁጭ ብዬ ልብላ ስላችሁ ስለምን ትገፈትሩኛለችሁ? ይህን ያህል ቸርነት አድርጌላችሁ ሳለሁስ ስለምን በግልምጫ አያችሁኝ? ይህን ያህል መውደድ ወድጃችሁ ሳለሁ ስለምን በቅጡ ልታነጋገግሩኝ አልወደዳችሁም? ከአዳም ጀምሮ ዓለም እስኪያልፍ ድረስ ያለው ሕዝብ ሁሉ በአንድ አደባባይ ላይ ቆሞ፣ እልፍ አእላፍ መላእክት በዙርያዬ ረበው “ይህ/ ይህቺ ልጅ ወዳጄ ነው/ ናት፤ በመሆኑም በታላቅ ክብርና ዕልልታ አጅባችሁ ወደ ዘለዓለም ደስታዋ አግቡት/ አግቧት” የሚለውን ፍርዴ አትናፍቁምን?

#ልጆቼ! እኔን ላለማየት ስለምን ፊታችሁን ትሸፍናላችሁ? ስለምን፡ታፍራላችሁ? እኔ ሳላፍርባችሁ ስለምን እናንተ አፈራችሁ?

#ልጆቼ! ልባችሁ እንደተነካ አውቃለሁ፡፡ ነገር ግን ስሜት ብቻ አይሁን፡፡ ከንፈራችሁን ብቻ አትምጠጡብኝ፡፡ ከእናንተ የምፈልገው አንዲት ነገር ብቻ ነው፡፡ ከላይ የጠየቅኳችሁን ነገሮች ወደ ተግባር ቀይሯቸው፡፡ ለማይጠቅማችሁ ነገር አብዝታችሁ እየሮጣችሁ ለሚጠቅማችሁ ነገር አትስነፉ፡፡ “እኔኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ ይህን እንደምን እችላለሁ?” አትበሉኝ፡፡ አውቃለሁ! ነገር ግን ፈቃዳችሁን ብቻ ስጡኝ እንጂ እኔ ራሴ አደርግላችኋለሁ፡፡ “ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉም” ብዬ.ያስተማርኳችሁን ቃል ረሳችሁትን? /ዮሐ.15፡5/፡፡ እንግዲያውስ ከእናንተ የምፈልገው ፈቃዳችሁን ነው፡፡ አሁን ካላችሁበት ቦታ ተንቀሳቅሳችሁ ወጣ ስትሉ ታገኙኛላችሁ፡፡ አናግሩኝ! አፍቃሪያችሁ መድኃኔዓለም ነኝ፡፡

#መቅረዝ ዘተዋሕዶ ብሎግ የተወሰደ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

07 Nov, 08:33


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#አልቆም ያለ ደም

"በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ" ሉቃ. ፰፥፵፬

ከዐሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። ደምዋ ፈስሶ አያልቅም ወይ? ዓሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ? እንዴት ያለ ሕመም ነው?! ሰው በክፉ ሽታዋ እስኪርቃት ድረስ የማይቆም ደም። ባለ መድኃኒቶች ሊያቆሙት ያልቻሉትን የደም ጎርፍ የናዝሬቱ ባለ መድኃኒት በቀሚሱ ብቻ አቆመው። በልብሱ ጫፍ ብቻ። ሳያያት ሳይነካት እጁን ሳይጭንባት በልብሱ ጫፍ ብቻ የደምዋን ዝናብ እንዲያባራ አደረገው። የሕመምዋን ማዕበል ገሠጸው።

በልብሱ ጫፍ ብቻ የሚፈውስ ሐኪም እንዴት ያለ ነው? ቀጠሮ ሳይሠጥህ ሳያናግርህ ቀና ብሎ ሳያይህ ስትነካው ብቻ የምትድንበት ከሆነ እርሱ መድኃኒት የሚያዝ ሐኪም ሳይሆን ራሱ መድኃኒት ነው። የልብሱን ጫፍ የነካ ከዳነ ሥጋውን የበሉ ደሙን የጠጡማ ምንኛ ይድኑ ይሆን? ሊፈውሳት አስቦ አልነበረም የዓሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ከሞት ሊያስነሣ መንገድ ሲሔድ ግን እግረ መንገዱን የዓሥራ ሁለት ዓመት የቁም ሙትዋን ፈወሳት። መድኃኔዓለም እንዲህ ነው። ወደ በሽተኛው ሳይሔድ በቃሉ ብቻ ተናግሮ ይፈውሳል፤ በሽተኛው ቤት ገብቶ በአልጋው ላይ ይፈውሳል። ሊፈውስ ሲሔድም ይፈውሳል። እናም የሴቲቱ አልቆም ያለ ደም በልብሱ ጫፍ ብቻ ቀጥ አለ።

ጌታዬ ሆይ የእኔንስ ደም የምታቆመው መቼ ነው? ምን ደም ፈስሶህ ያውቃል ካልከኝ ኃጢአት የሚባል ደም ሲፈሰኝ አይታይህም? አንተስ በቃልህ "ኃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች" ብለህ የለ? እንደ ደም የቀላው የእኔ ኃጢአት ነው። ይኸው ሲፈስ ከሴቲቱ በላይ ቆየ። ላቆመው ብል አልቆም አለኝ። ያላሰርኩበት ጨርቅ፣ ያልሞከርኩት ቅባት፣ ያልሔድኩበት ባለ መድኃኒት የለም። ገንዘቤን ከሰርኩ እንጂ ኃጢአቴ ግን መቆም አልቻለም። እንዲያውም መጠኑ እየጨመረ ነው። ባሕር ሆኖ ሊያስጥመኝ የደረሰ የኃጢአት ደም ከብቦኛል።

ለእኔ የሚሆን የቀሚስ ጫፍ ታጣ ይሆን? እኔ እንደ ሴቲቱ ታላቅ እምነት የለኝም ቀሚስህ ግን አሁንም ኃይል አለው። ልትፈውሰኝ ና አልልህም ስታልፍ ግን ልዳስስህና ልዳን። ጉዞህን ሳላሰናክል ሰው ሳይሰማ በልብስህ ጫፍ ብቻ ደሜን አቁምልኝ። የእኔን ደሜን መግታት ላንተ ምንህ ነው? ደምህንስ አፍስሰህልኝ የለ? እባክህን ደሜ ሳይቆም ሌላ ዓመት አልሻገር። እኔ ኃጢአቴን "ያለፈው ዘመን ይበቃል" ማለት ቢያቅተኝም አንተ ግን ይበቃሃል በልልኝ። በእምነት ማጣት የታጠፈውን እጄን ወደ ልብስህ ጫፍ ዘርጋልኝ። እኔ ማቆም ያልቻልኩትን የበደል ደም ጸጥ አድርገህ "አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ ወጥቶአል" በል። እነጴጥሮስም ይደነቁ እኔም በሰላም ልሒድ።

(ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - የኤፌሶን ወንዝ ገጽ 168-170)

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

05 Nov, 16:35


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ጥቅምት 27 "በዓለ ስቅለት"

#ጥቅምት 27 በዚህች ዕለት የአምላካችን የመድኃኔዓለም የስቅለቱ መታሰቢያ ነው።

መድኃኒታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና በቸርነቱ ስለኹላችን ድኅነት ሲል ራሱን ወድዶ ፈቅዶ ለሞት አሳልፎ በመስጠት ፍጹም ፍቅሩን አሳይቶናል። በቅዱስ ወንጌልም እርሱም መድኃኒታችን " ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም" ብሎ ነግሮናል። እውነት ነው፣ ራስን ነፍስን ስለጠላት ነፍስ አሳልፎ ከመስጠት በላይ ምን ድንቅ ነገርና ምን ድንቅ ፍቅር አለ?

ቸሩ አምላካችንን የአስቆሮቱ ይሁዳ ሊያስይዘው የሊቃነ ካህናቱን አገልጋዮች እየመራ አመጣቸው። እነርሱንም ማንን ትፈልጋላችሁ ሲላቸው የናዝሬቱ ኢየሱስን አሉት፣ እኔ ነኝ ቢላቸው የቸሩን አምላክ ድምጽ ሰምቶ አይደለም መቆም በሕይወት መጽናት የሚቻለው የለምና ወደ ኋላቸው ተስፈንጥረው ወደቁ። ደጋግሞም እንዲህ ኾነ። በኋላ ግን እኔ ነኝ ብሎ በፈቃዱ ይሁዳ ስሞ አሳልፎ ሰጣቸው።

ከያዙት በኋላ እያዳፉና እየጎተቱ በሰንሰለት አስረው ወደ ቀያፋና ሐና ግቢ ወሰዱት፣ እስከ ሦስት ሰዓትም አላሳረፉትም ሲያሰቃዩት አድረዋል፣ በራሱም ላይ ሰባ ሦስት ስቊረት ያለው ወደ ሦስት መቶ እሾኾችን የያዘ የእሾህ አክሊል ጎንጉነው ቢያደርጉበት የራስ ቅሉን ቀዶ ገብቶ እስከ ልቡ ዘልቋል። እንደምን ጭንቅ ነው? እንዲህም አድርገው ደግሞ እያፌዙ ርኲስ ምራቃቸውን ይተፉበትና በዘንግም ደጋግመው ይመቱት ነበር። እየተፈራረቁ ያለ ምንም ርኅራኄ ቸሩን አምላክ ሥጋው እየተቆረጠ እስኪወድቅ ድረስ ስድስት ሺህ ስድስት መቶ ስድሳ ስድስት ጽኑዕ ግርፋትን ገርፈውታል። የገረፉበትም ጅራፍ በላዩ ላይ ሥጋን እየጎመደ የሚጥል፣ ሕመሙ አንጀት ሰርሥሮ የሚገባ በስለት የተያያዘበት ነበር።

በኋላም አላሳረፉትም እንዲህ አድርገውትም በሊቶስጥራ አደባባይ ያንን ዕርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት። እርሱ ግን ይህን ኹሉ ግፍ ሲያደርሱበት አንድም አልተናገረም ነበር። በቀራንዮም በአምስት ጽኑዕ ቅንዋት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ አዴራ እና ሮዳስ) ቸንክረው ዕርቃኑን ሰቀሉት።

በዚህች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተሰበረ መጽናናትንም አልፈለገች ነበር፤ ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ እናቱንም እናት ትሆነው ዘንድ በእግረ መስቀሉ አደራን ተቀበለ። ቅዱሳት አንስት በፍጹም ሀዘንና በዋይታ ዋሉ። በስልጣኑም ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ። ሰባት ድንቅ የኾኑ ተአምራትንም አድርጎ አምላክ መኾኑን ገለጠ። ይህም ጽኑዕ የኾነ ለሰማይ ለምድር የከበደ ነገር ሲከሰት ፀሐይ አምላኬን ዕርቃኑ እንዴት አያለሁ ብላ ጨለመች። ጨረቃ ደም ኾነች፣ ከዋክብቱም ረገፉ፣ ንዑዳን ክቡራን ንጹሐን መላእክትም ትዕግስቱን እያደነቁ በጽኑዕ ሐዘንና መደነቅ ከቅዱስ ዕፀ መስቀሉ ፊት እንደሻሽ ተነጠፉ።

አስራ አንድ ሰዓት በሆነም ጊዜ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር ቅድስት ሥጋውን ከመስቀሉ አውርደው በክብር ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን እንደተናገረ ተነሳ።

#በዛሬዋ ቀን ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔለምን የስቅለት በዓል በደማቁ ታከብራለች፤ ይህም የለውጥ በዓል ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ስጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ቀን ነው፤ ይህ በዓል ግን በዐቢይ ጾም ስለሚውል በዐቢይ ጾም ሀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለና በዓል ማክበር ስለማይፈቀድ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን እንድናከብረው ቤተ ክርስቲያን ስርዓት ሰርታልናለች፡፡

#ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

04 Nov, 09:27


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#አንድ ምድራዊ ንጉሥ "ጠላቱን ያልወደደ ሰው በሞት ይቀጣል" ብሎ አዋጅ ቢያውጅ ሁሉም ሰው በአካለ ሥጋ ላለመሞት ሲል ሕጉን ለመጠበቅ የሚፋጠን አይደለምን? ወዮ! ምድራውያን ነገሥታት በሥጋዊ ሞት እንዳይቀጡን ብለን ፈርተን የሚያወጡትን ሕግ ለመፈፀም የምንፋጠን ሆነን ሳለ፥ ለነገሥታት ንጉሥ ለእግዚአብሔር ሕግ አለመታዘዛችን እንደ ምን ያለ ወቀሳ ያመጣብን ይሆን?

#ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

31 Oct, 10:32


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ማለዳይቱ

#ማን ናት ያቺ እንደማለዳ ብርሃን የምትጎበኝ :-
-> ማለዳን የማይናፍቀው ሰው የለም የራበው ሰው ሲነጋ የሚጠግብ ይመስለዋል፤  የታመመ ሰው ሲነጋ የሚድን ይመስለዋል፤ የታሰረ ሰው ሲነጋ የሚፈታ ይመስላዋል ..
በሞት የታሰሩ ማለዳይቱ ማርያም ስትመጣ እንፈታለን እያሉ ፤ የሕይወት እንጀራ እና መጠጥ የራባቸው የጠማቸው አባቶች ማለዳይቱ ማሪያም ስትመጣ እንጠግባለን እንረካለን እያሉ ፤ የአዳም በደል ዕዳ የተሸከሙ አባቶች የማርያምን ንጽሕና ከፍለን ነፃ እንወጣለን እያሉ ተስፋ ያደረጓት ዘመኑ በደረሰ ጊዜ የእግዚአብሔር አንድ ልጁ ፀሐይ ጽድቅ ክርስቶስ የወጣበት ሁሉ የሚናፍቃት ማለዳይቱ እመብርሃን ናት ::

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

27 Oct, 11:54


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የቅዱስ እስጢፋኖስ ደም ለሐዲስ ኪዳንዋ ቤተክርስቲያን ምርጥ ዘር ነው እርሱ ሰማዕት በሆነ ጊዜ በኢየሩሳሌም ተወስና የነበረች ቤተ ክርስቲያን በስደት በዓለም ሁሉ ተዳርሳ በዝታ ለመገኘቷ እርሱ ምርጥ ዘር ሆኗታል።

#አውግስጢኖስ «በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት፣ ቤተ ክርስቲያን የጠፋውን ጳውሎስን አገኘች፤» በማለት ተናግሯል።

#የቀዳሚ ሰማዕት ቅድስት የምትሆን በረከቱ በእኛ አድራ ጸንታ ትኑርልን።

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

22 Oct, 08:01


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም "  ። /ት ዳን 10፥21/

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

19 Oct, 12:53


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ" / አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

18 Oct, 06:29


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#በቀትሩ ጊዜ ልጅሽ በመስቀል ላይ በሚጨነቅ ጊዜና አንቺን እናቱን ወደ ሚወደው ደቀ መዝሙሩ አደራ ሲሰጥ በምድር ላይ የተንጠባጠበው ዕንባሽ ለመተዳደፌ መታጠቢያ ይኹን ። /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ/

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

15 Oct, 11:33


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ጥቅምት_5

#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ (ገብረ ሕይወት)

ጥቅምት አምስት በዚህች ቀን የታላቁ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የዕረፍታቸው መታሰቢያ። ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ። አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ የቅዱሳን የበላይ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው። የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አነደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ /ምግባቸው ምስጋና ነውና/ ልብስ ያልለበሱ /ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና/ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት፤ ሃገራችንን አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው፤ ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።

የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮጵያ ልዩ ፍቀር አላቸው። ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቋላ መከራን ተቀብለዋል። ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው።

ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት። በ8ኛው ክ.ዘ አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ.ዘ አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ። "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ።" እንዲል።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እረፍቱ መጋቢት 5 ቀን ነው ይህ ደግሞ በታላቁ ዓብይ ጾም ወቅት ነው ፍትሃ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ በዓብይ ጾም በዓል ማክበር ይከለክላል የሀዘን ወቅት ነውና ከበሮ አይመታም እልልታና ጭብጨባ የለም ፍጹም ሀዘን እንጂ የመጋቢት 27 ስቅለት ጥቅምት 27 ቀን እንደሚከበረው ሁሉ ወደ ጥቅምት 5 ቀን ተዛውሮ እንዲከበር ተደረገ፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር )

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

03 Oct, 09:51


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የተባረከች አይን የእግዚሐብሔርን ቃል በማንበብ ትጠመዳለች፤

#የተባረከች ጆሮ የንስሀ መዝሙር በመስማት እራሷን ታንጻለች፤

#የተባረከ ጉሮሮ ላይ የተቀደሰ ውሀ ይንቆረቆርበታል፤

#የተባረከች ምላስ የአምላኳን ስጋና ደምን ትቀበላለች፤

#የተባረከ አንደበት ላይ እግዚሐብሔር ይመስገን የሚል ቃል አይጠፋበትም፤

#የተባረከች አንገት የአምልኮ ደም የፈሰሰበትን ቅዱስ መስቀል ትሸከማለች፤

#የተባረከች ልብ ኢየሱስን እስከ እናቱ አንግሳ በፍቅር ትሞላለች፤

#የተባረከች እጅ የቀረበላትን ምግብ በአምልኮ ስም ትባርካለች፤

#የተባረከች እግር ጠዋትና ማታ የአምላኳን መቅደስ ትረግጣለች፤

"እኔ እግዚሐብኤር አምላካቹ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ ቅዱስም ሁኑ እኔ ቅዱስ ነኝና" ዘሌ. 11፥44

#አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

01 Oct, 10:41


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ብዙኃን ማርያም

#መስከረም ፳፩ ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡  ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን ነው

318ቱ ሊቃውንት በጉባኤው አርዮስን አውግዘው በመለየት ‹‹ነአምን በአሐዱ አምላክ፤ በአንድ አምላክ እናምናለን›› የሚለውን የሃይማኖት ጸሎት (የሃይማኖት መሠረት) እና ሌሎችንም የሃይማኖት ውሳኔዎችን ደንግገዋል፡፡ ሊቃውንቱ ጉባኤውን ያካሔዱት ኅዳር ፱ ቀን ይኹን እንጂ በአንድነት የተሰባሰቡት መስከረም ፳፩ ቀን ስለ ነበረ ይህ ዕለት ‹‹ብዙኃን ማርያም›› እየተባለ ይጠራል፡፡

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

26 Sep, 19:16


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#የድኅነት ድልድይ

#በአንድ እንጨት ምክንያት ሰው ሁሉ ወደ ሲኦል እንደወረደ  እንዲሁ በአንድ እንጨት ምክንያት የሰው ልጅ ሁሉ ወደ ሕይወት ማደሪያ ተሸጋገረ ። በእንጨት መራራ ሞትን ተጎነጨን ፣ በእንጨት ደግሞ ጣፋጭ ሕይወትን አጠጣን።”  (ቅዱስ ኤፍሬም)

#በትረ ሙሴ ባህረ ኤርትራን ከፈለ ወደ ምድረ ርስት ለመግቢያ መንገድን ተገኘ ክርስቶስም በመስቀሉ የኃጢአትን ባሕር ሲኦልን ከፈለ ወደገነት መግቢያ አደረገው፡፡

#በበትረ ሙሴ ጽምዓ እስራኤል ያበረደ ውኃን ከዓለት መነጨ ፤ በዕፀ መስቀልም ጽምዓ ነፍሳትን የሚያረካ መጠጥ ተገኘ :: ዮሐ.19

#ለብርሃነ መስቀሉ ያደረሰል አምላክ ይክበር ይመስገን የበረከት በዐል ያድርግልን

✍️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተስፋዬ 

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

24 Sep, 06:11


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#Ilma koo  guyyaa hojii kee irratti , halkan siree kee irra ;   kan si eegu Waaqayyodhati  Halkan yeroo raftu , Ganama yeroo kaatu waaqa kee  kadhachuu fi galateeffachuu hin dhiisin.

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

24 Sep, 05:57


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ልጄ ሆይ፤ ቀን በሥራህ ላይ፤ ሌሊት በአልጋህ ላይ፤ የሚጠብቅህ እግዚአብሔር ነውና ማታ ስትተኛ፤ ጧት ስትነሣ እግዚአብሔርን አምላክህን መለመንና ማመስገን አትተው፡፡

/ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ /

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

21 Sep, 08:41


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

"የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል" /1ኛ ጴጥ. 4÷3 /

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

19 Sep, 05:53


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ዘመን ማን ነው? ዘመን ማለት እኛ ነን..ስንከፋ የሚከፋ ደግ ስንሆን ደግ የሚሆን የእኛው ነጸብራቅ ነው ዘመን። ለዚህ ነው አበው በአንጋረ ፈላስፋ "ዘመን ማለት አንተ ነህ፡፡ አንተ ሰላማዊ ስትሆን ሰላማዊ ትሆናለች፡፡ አንተ የከፋህ እንደሆነ ትከፋለች፡፡" በማለት የተናገሩት።

#እናም ዘመን እኛ እኛም ዘመን ነንና ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዳለው በዕሜያችን ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰብን ራሳችንን እንዲህ ብልን እንጠይቅ፡- “ቀናት እየሮጡ ነው፣ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፣ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፤ ታዲያ ምን በጎ ምግባር ያዝኩ? ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፤ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ (ዘመኔ) መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፤ ታዲያ ዕድሜዬ (ዘመኔ) ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውን የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንደ አቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችንን እንጠይቅ።"

#አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ። ሰቆ.ኤር 5፥21

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

12 Sep, 07:03


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

#ከመስከረም 1 ጀምሮ እስከ መስከረም 7 ድረስ ያለው ሳምንቱ (ወቅት) ዮሐንስ ይባላል፡፡

#እነዚህ ሰባቱ ዕለታት ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የተሰጡ የጸጋው (ሀብቱ ) ምሳሌዎች ናቸው። እነዚህም፦
- ጻድቅነት
- ስብከት
- ክህነት
- ብህትውና
- ድንግልና
- ሰማዕትነት
- ትንቢት ናቸው።

#የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓላት ፦

መስከረም 26፡ በዓለ ጽንሰቱ
ሰኔ 30፡ በዓለ ልደቱ
መስከረም 2፡ ራሱ የተቆረጠበት
መስከረም 15፡ ነፍሱ ከራሱ የወጣችበት
የካቲት 30፡ ራሱ የተገኘችበት
ሰኔ 2፡ ራሱ በኤልሳዕ መቃብር የተቀበረበት
መስከረም 1፡ ርእሰ ዐውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ


#የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች
1.ነቢይ
2.ሐዋርያ
3.ሰማዕት
4.ጻድቅ
5.ካሕን
6.ባሕታዊ/ገዳማዊ
7.መጥምቀ መለኮት
8.ጸያሔ ፍኖት (መንገድ ጠራጊ)
9.ድንግል
10.ተንከተም (የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ)
11.ቃለ አዋዲ (አዋጅ ነጋሪ)
12.መምሕር ወመገሥጽ
13.ዘየዐቢ እምኩሉ (ከሁሉ የሚበልጥ)

#መስከረም ሁለት ምትረተ ርዕሱ ነው :: #ከበረከቱ ያሳትፈን።

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

12 Sep, 06:55


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

🌻🌻ዕንቍጣጣሽ🌻🌻

ጥያቄ፡- “ዕንቁጣጣሽ” ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፡- ዕንቁጣጣሽ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የደስታ፣የብሩህ ተስፋና የአዲስነት ስሜት የሚያሳድር ነው፡፡ “ዕንቁጣጣሽ” የሚለው ስያሜ በቃል የተነገረ እንጂ በጽሑፍ የሠፈረ አልተገኘም፡፡ ሆኖም በቃል ትውፊት ሲነገር እንደ መጣ ➘

1—ዕንቁ ብሎ አዕናቁ ከግእዝ የተወረሰ ቃል ነው፡፡ ዕንቁ ለአንድ፤ አዕናቁ ለብዙ ይነገራል፡፡ ጣጣሽ፡- “ፃዕ ፃዕ” ከሚለው የግእዙ ቃል የተወረሰ ነው በኣማርኛ ጣጣ፣ መባዕ፣ ግብር፣ መፍቀድ፣ ገጸ በረከት /በረከተ ገጽ/ ማለት ይሆናል፡፡ መጽሓፍተ ብሉያት ወደ እግዚኣብሔር የሚቀርበውን መባዕ፣ የሚገባውን ግብር “ፃዕፃዕ” ይሉታል፡፡
በየዓመቱ ዕንቁጣጣሽ ማለታችን ‹‹ የዕንቁጣጣሽ ግብር፣ የእንቀጣጣሽ ገጸ በረከት ነው ›› ብለን የምሥራች ማሰማታችን ነው፡፡
በሃገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ ዕንቁጣጣሽ የተበረከተው ለቀዳማዊ ምንይልክ /ምኒልክ/ እናት ለንግሥት ማክዳ ነው፡፡
ንግሥት ማክዳ ቀዳማዊ ምንይልክን /ምኒልክን/ በወለደች ጊዜ ሕዝቡ ንጉሥ ተወለደ ብሎ እልል እያለ ገጸ በረከት አቅርበዋል “የአበባ ዕንቁጣጣሽ መባሉም መጀመሪያ ለንግሥቲቱ ስለ ተገበረ ነው፡፡ ለንጉሥ ቢሆን ኖሮ ‹‹ዕንቁ ፃዕፃሁ›› ይባል ነበር እንጂ ‹‹ዕንቁጣጣሽ›› ኣይባልም ነበር፡፡ በሸዋም ሕዝቡ ግብር ኣለብኝ ሲል ‹‹ጣጣ ኣለብኝ ›› ይላል፡፡

2—የዕንቁጣጣሽ ታሪክ ንግሥተ ሳባ የሰሎሞንን ዜና ጥበብ እየሰማች ስትደነቅ ትኖር ነበር፡፡ በጆሮዋ የሰማችውን በዓይኗ ዓይታ ለመረዳት ስለፈለገች በግመሎቿ ላይ ሽቱና እጅግ ብዙ ወርቅ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሚገኙ በኢየሩሳሌም የማይገኙ ልዩ ልዩ ገጸ በረከት ኣስጭና ከብዙ ሠራዊት ጋር ወደ ኢየሩሳሌም ገባች፡፡
ከንጉሡ ሰሎሞንም ጋር ተገናኝታ የያዘችውን ገጸ በረከት ከሰጠችው በኋላ ብዙ ነገሮችን ጠየቀችው ርሱም አንድ ነገር ሳይሰውር ገለጠላት ቤተመንግሥቱንና በቤተመንግሥቱ የሚገኙትን እጅግ በጣም የከበዱ እቃዎችን ሁሉ አስጎብኝቷት ሲያበቃ "ዕንቁጣጣሽ" (‹‹ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ››) ሲል እጅግ በጣም የከበረ ዕንቁ አበረከተላት /ሰጣት/ ይህም የተፈጸመው /ንግሥተ ሳባ ከንጉሥ ሰሎሞን ጋር የተገናኘችው/ በመስከረም ወር ነው ዕንቁጣጣሽ በዚህ ምክንያት ተጀምሯል፡፡

3— ዕንቁጣጣሽ ግጫ ማለት ነው፤ ግጫ ደግሞ የሳር ዓይነት ነው፡፡ በመስከረም ወር ምድር በአዝርዕትና በአትክልት በአበባና በፍሬ የምትሸፈንበት በተለያዩ አበቦች የምታሸበርቅበት በመሆኑ ዕንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወሩን መሠረት ያደረገ ነው፡፡

=> ‹‹ዕንቁ›› እና ‹‹ጣጣሽ›› የሚባሉት ሁለት ቃላት ለይቶ መመልከት ይቻላል፡፡ ዕንቁ የሚባለው የከበረና ከማድናት በላይ የሆነ የጌጥ ዕቃ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ጣጣሽ ሲባል ደግሞ ‹‹ያንቺ ግዳጅ ዕንቁ ነው›› ማለት በዕንቁ ታጌጫለሽ፣ ታሸበርቂያለሽ፣ ከወራት ሁሉ የተለየሽ ነሽ ለማለት ወርኃ መስከረምን የሚገልጥ ነው፡፡

=> በተጨማሪም ይህ ወር የአበባ የርጥበት ስጦታ የሚሰጣጡበት ወር በመሆኑ ነው፡፡ የአበባ የርጥበት ስጦታ መስጠት የተጀመረው በኖኅ ዘመን ነው፡፡ ኖኅ የጥፋት ውኃ በጎደለ ጊዜ መጉደሉን ለማረጋገጥ ርግብን ልኳት የወይራ ቅጠል አምጥታለታለች፡፡ እርሱም የመርከቡን ጣራ አንስቶ ከወጣ በኋላ ለእግዚኣብሔር መሥዋዕት በማቅረብ ልዩ ልዩ ጸአዳ ሽታ ያላቸውንም አበቦችንም አቅርቧል ይህም በወርኃ መስከረም ነው፡፡ ኋላም ንግሥተ ሳባ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ዘንድ ስትሄድ 500 /ኣምስት መቶ/ ደናግልት ተከትለዋት ነበር የእልፍኝ አሽከሮቿም እነርሱ ነበሩ በዚያም ለንግሥታቸው አበባ ሰጥተዋታል የኣበባውም /የእንቁጣጣሹም/ ስጦታ በእነርሱ ተፈጽሟል፡፡
ዛሬም ልጅ አገረዶች አበባ ቀጥፈው እንግጫ ነቅለው ሸልመው የሚያቀርቡበት ከሽማግሌዎችም ምርቃትን የሚያገኘበት ወር በመሆኑ ነው፡፡ ይቆየን

ዋቢ መጽሓፍት፡- ሊቀ ሥዩማን ኣክሊሉ ገብረ ኪሮስ፡- አዲስ ዘመን ጋዜጣ መስከረም 5 ቀን 1955 ዓ.ም

ዕንቁጣጣሽ ምንድን ነው መነን መጽሔት / አ፣ አ መስከረም 1965 ዓ.ም ቁጥር 1፣ገጽ 8

‹‹ዕንቁጣጣሽ ምንድነው?›› መነን መጽሔት / አ.አ፣ መስከረም 1965 ዓ.ም ቁጥር 1 ገጽ 8 አለቃ ነቢየ ልዑል ዮሓንስ

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

10 Sep, 16:27


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

           በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
                     አሐዱ አምላክ አሜን


" በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ " (መዝ 65፥11)

   "እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ" (ራዕ 21፥5) እንዳለ ክርስቶስ በወንጌሉ እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ዮሐንስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ በሰላም አሸጋገራችሁ እያልን ። በአሮጌው ዓመት ምን መልካም ስራ ሰራን ? ምንስ በጎ ነገር አደረግን ? ምን ያህል ወደ ቤተ ክርስቲያን ቀረብን ? ብለን እራሳችንን የምንመለከትበት እንዲሁም አዲሱን ዓመት እራሳችንን አዲስ አድርገን የተጣላን ታርቀን ፣ የበደልን ክሰን ፣ የተበደልን ይቅር ብለን ፣ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን ጸንተን ፣ በንስሐ ታጥበን ፣ የክርስቶስን ሥጋና ደሙን በልተን ጠጥተን ፣  ከክርስቶስ ጋር ታርቀን የምንኖርበት እና ዳግም ምጽአትን በመቅደሱ ሆነን የምንጠባበቅበት መልካም ዘመን ያድርግልን !!! አሜን !!!

         "እነሆ፥ ክረምት አለፈ፥ ዝናቡም አልፎ ሄደ።"
                            (መኃልየ. 2፥11)

                       አንቀጸ አድኅኖ ሰ/ት/ቤት

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno

ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች እና መዝሙሮች / Orthodoxsawi temehertoch (mezmuroch)

06 Sep, 17:04


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
                     
                        ☘️ ጠበል

#ጠበል ፦ አንዱ የፈውስ መንገድ ነው ።

#ጠበል ፦ በካህናት አባቶች አማካኝነት ጸሎት ተደርጎ የሚገኝ ቅዱስ ውኃ ነው ።

#ጠበል ፦ በጸሎት የከበረ በመሆኑ ምክንያት እግዚአብሔር  ተአምራቱን የሚገልጥበት ፣ ኃይለ እግዚአብሔር ያለበት ልዩ ውኃ ነው ።

#ጠበል ፦ ሰዎች ከእውነተኛው መንገድ እንዳይርቁና የእግዚአብሔር ምሕረት ሁሌም እንዲያስተውሉ ከሚያደርጉ ነገሮች አንዱ ነው ።

#በጠበል እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ምሕረት ይገልጥበታል

#በጠበል እግዚአብሔር ተጠራጣሪዎችን ወደ እውነት እንዲመጡ ይጠራበታል ።

             ☘️ የጠበል ጥቅም

#ከልጅነት ጥምቀት በኋላ በየጊዜው የምንጠበለው ወይም የምንጠመቀው ጠበል
         - ንጹሕ ሕሊና እንዲኖረን
         - ሰውነታችን እንዲነጻ
         - መንፈሳችን እንዲታደስ
         - ከደዌ ሥጋ ፣ ከደዌ ነፍስ ለመዳን
         - ከእርኩሳት መናፍስት እስራት ለመላቀቅ
         - እርኩሳን መናፍስትን ለማራቅ
         - ወደ እግዚአብሔር ለመቅረብ
         - በመንፈሳዊ ሕይወት ለማደግ
         - የሃይማኖትን ምሥጢር ለመረዳት
         - ለመንፈሳዊ አገልግሎት ሃይል ለማግኘት
         - ውስጣውና ውጫዊ ሰላምን ለማግኘት
         - ትምህርታችን ስራችን የተቃና እንዲሆን
         - ቤታችን ፣ ደጃችን ፣ እንስሳት ፣ የእርሻ
           ቦታችን ፣ ጎተራችን ..... የተባረከ እንዲሆን
 
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
https://t.me/ankets_adeheno