ማርዳ ሚዲያ-Marda Media @mardamediastudio1 Channel on Telegram

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media

@mardamediastudio1


ማርዳ ሚዲያ-Marda Media (Amharic)

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media የግል ተከብሮ ዜና እና የቴሌግራም ገጽ መረጃዎች የሚሰጡ ቤተሰብና ሰፈር አስተዳወቀ የቴሌግራም ቻናል አገልግሎቶች ናቸው። በአሁኑ ክፍል ከዚህ በፊት ማለትም በእውን በእንትኞች በግል እና በማስታወቅ ቻናሉ ከፈሊገም ለማሳር የሚችሉ ሰፈር አገልግሎቶችን ያገኙ ነው። ሚዲያዊ ለመረበሽ ሳቅ አገልግሎቶችና ቴሌግራም አመንሷታዊ ዘዴውን ለማወቅ እንድታገኙ እንዲሆኑ ይህን ዳታ ይጠቀሙት። የማርዳ ሚዲያ ቻናሉ ችግሮች እና አዝናኝ የሚኒሽን አገልግሎቶች ናቸው።

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media

19 Oct, 12:42


https://www.facebook.com/profile.php?id=61566914597105

👆Follow

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media

21 Sep, 11:52


የ15 ዓመት ታዳጊን ለአራት በመሆን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ !

https://www.facebook.com/100081824400065/posts/pfbid033BM6hyW8mL9Y53makpcLJRtHB2hY1ELVYdKSeYE3JA3HGzvzKwY5j3RP9zkQ38Ael/

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓላሼ ቀበሌ ለአራት በመሆን የ15 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾች በቁጥር አራት ሲሆን አስፋቸው አለሙ፣ አሻግሬ አበራ፤ ማቲዎስ ደዋና እና አስማማው አሉላ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ግለሰቦቹ በአመያ ዙሪያ ወረዳ በግምት 8:00 አካባቢ ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኦፓላሼ ቀበሌ እየሄደች የምትገኝ የ15 አመት ታዳጊ አስገድደው መድፈራቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ጳግሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 7 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጥተዋል።

አራተኛ ተከሳሽ ዕድሜው ከ10 እስከ 13 ዓመት በመሆኑ ተከሳሹ መታሰር የማይችልና እንደዚህ ዓይነት ታዳጊ እስረኞችን ተቀብሎ በማረምያ ተቋም በዞኑ ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቡ ፈርሞ ወስዶት ክትትልና በቁጥጥር እንዲያደርግ በማለት ውሳኔ መሰጠቱን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media

16 Sep, 09:54


የቻይናዋ ከተማ በ75 ዓማታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ አውሎ ነፋስ ተመታች
***

በአውሎ ንፋሱም የተነሳ 25 ሚሊዮን የሚጠጉ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከቤታችሁ አትውጡ የሚል መልዕክት ተላልፎላቸዋል።

እግረኞችን ከነጃንጥላቸው የሚያወዛውዝ፣ ቁስን ከቁስ የሚያጋጨው አውሎ ንፋስ ከአውሮፓውያኑ 1949 ወዲህ ቻይና አይታው የማታውቀው ነው ተብሎለታል።

አውሎ ነፋሱ ሰኞ እለት ከጠዋቱ 1፡30 በሻንጋይ ምስራቅ ሊንጋንግ ኒው የተባለቸውን ከተማ የባህር ዳርቻ አካባቢ መምታቱን የቻይና ሜትሮሎጂ አስተዳደር አስታውቋል።

በሰዓት እስከ 151 ኪሎ ሜትር የንፋስ ፍጥነት ያለው አውሎ ንፋስ የቻይናዋን ቤቢንካ በ1949 ከታይፎን ግሎሪያ በኋላ ከተማዋን የመታው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ነው ሲል ግሎባል ታይምስ ዘግቧል።

በግዛቲቷ በረራዎች እና የባቡር አገልግሎቶች ተሰርዘዋል፣ አውራ ጎዳናዎች ተዘግተዋል 25 ሚሊዮን የሚጠጉ ይህንን አስፈሪ ንፋስ ለመሸሽ በቤታቸው መሽገዋል።

በአውሎ ንፋሱ የተነሳ 9 ሺህ ሰዎች ከቾንግሚንግ አውራጃ በያንግትዝ ወንዝ አፋፍ ላይ ከምትገኘው ደሴት ተፈናቅለዋል ሲሉ የከተማዋ ባለስልጣናት ተናግረዋል።

የአካባቢው ባለስልጣናት ከባዱን ንፋስ በመፍራት በባህር ላይ የሚከሰተውን ወጀብ በመስጋት ሁሉም መርከቦች ወደ ወደብ እንዲመለሱ አዘዋል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media

13 Sep, 11:28


ሚሳኤሎችን ለዩክሬን መላክ በጦርነት አሸናፊ አያደርጋትም ተባለ

ዩክሬን የምዕራቡ ዓለም የሚሳኤል ድጋፍ ቢያደርግላት ወደ ሩሲያ የምትተኩሰዉ ዒላማዎች ዝርዝር እንዳላት ተናግራለች። ሩሲያ በምስራቅ ፖክሮቭስክን ለመያዝ እጅግ አስፈላጊ የሆነዉን መስቀለኛ መንገድ ለማግኘት እየታገለች ትገኛለች፡፡በጦርነቱ ወቅት በሙሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጠንካራና የተሻሉ የጦር መሳሪያዎችን እንዲሰጣቸዉ ሲጠይቁ የነበረ ቢሆንም በዚህ ሁሉ ተአምር አልተፈጠረም፣ ዩክሬናውያን የሚፈልጉትን ድል አልሰጡም ፣ ሲሉ የጦር ተንታኞች ተናግረዋል፡፡

ዩክሬን የምዕራባውያን ሚሳይሎችን ወደ ሩሲያ እንድትልክ የሚፈቀድላት ከሆነ፣ ይህ እየተካሄደ ያለውን ነገር አንዳንድ ሁኔታዎችን ሊለውጥ ይችላል ግን በእርግጥ ሩሲያውያንን ለመምታት እድል ሊሰጥ ይችላል ነገር ግን ዩክሬንን በጦርነት አሸናፊ አያደርጋትም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ሩሲያ ስድስት የእንግሊዝ ዲፕሎማቶችን በስለላ በመወንጀል የሰጠችውን እውቅና ሰርዛለች፡፡ፕሬዚደንት ቭላድሚር ፑቲን ዩክሬን ሩሲያን ለማጥቃት የረዥም ርቀት ጦር መሳሪያ ከምዕራባውያን የጦር መሳሪያ ምርት እንዳትጠቀም ባስጠነቀቁበት መልዕክት ላይ የእንግሊዝ ዲፕሎማቶችን አያይዘዉ ከሰዋል፡፡ፑቲን እንዳሉት በኔቶ እገዛ ዩክሬን የሩሲያን ግዛት ከመታች ሞስኮ “ተገቢ ውሳኔዎችን ትወስዳለች” ብለዋል።

ማርዳ ሚዲያ-Marda Media

25 Aug, 11:09


የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሲቪል አቪዬሽን ሕግና አሠራር ጥሰዋል ያላቸዉ  ስድስት ተጠርጣሪዎች



ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎች እንዲደርሳቹሁ ቻናላችን ይቀላቀሉ
https://t.me/MardamediaStudio1

3,864

subscribers

239

photos

18

videos