ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽 @tewahdobet Channel on Telegram

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

@tewahdobet


በዚህ Channel የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታዊ ትምህርቶች ይሰጡበታል Join እና Share ያድርጉ
አስተያየት https://t.me/yetewahdo_group

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽 (Amharic)

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫ክ is a channel dedicated to providing valuable information and resources related to home decor and design. Whether you are looking to spruce up your living space, get inspiration for a new project, or simply stay updated on the latest trends in home decor, this channel has got you covered. With a focus on showcasing beautiful designs, practical tips, and creative ideas, ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫ክ is the perfect destination for anyone passionate about creating a stylish and inviting home. Join the channel today to discover new ways to enhance your living space and make your house feel like a cozy oasis.

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

02 Jan, 10:00


#24

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

28 Dec, 05:13


#19

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

14 Dec, 18:51


#6 ቅድስት አርሴማ

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

11 Dec, 17:22


ልደታ ለማርያም 🥰

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

06 Dec, 07:23


JOIN HD WALLPAPER CHANNEL

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

06 Dec, 07:23


#27 🥰🙏

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

30 Nov, 03:23


#21 ማርያም 🥰 የፍቅር እናት

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

20 Nov, 19:46


"ከሚዎዱሽ ወንዶች የሞተ አለ?"

► ጊዜው፥ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር የጀመረበት፣ሐዋርያት በምልዓት ያልተጠሩበት፣ የዮሐንስ መጥምቅ ትምህርት የተፈጸመበት ወቅት ነው።

በዚያ ዘመን በገሊላ ናይን(Nain) ከተማ ይኽ ከዚኽ ቀረሽ የማትባል 'የደም ገምቦ' መልከ መልካም ሴት ነበረች። ውበቷ የኀጢኣትም የገንዘብም 'ትርፍ' ኾኗት ብዙ ጊዜ ቆይታለች።

ከዕለታት አንድ ቀን እንደልማዷ በመስታዎት ፊት ቆማ ከእግር ጥፍሯ እስከ ራስ ጠጕሯ ውበቷን ተመለከተች። ነገር ግን የመስታወቱ ምልሰት ላይ ከፊት ያለው ውበቷን ያይደለ ሞቷንና ኀጢኣቷን የነፍሷንም ድካም ተመለከተች።

ይኽም ራስን በጥልቀት የማየት ጉዳይ በሥጋ ዐይን አይኾንም። መጽሐፍ "ወብነ ክልኤቲ አዕይንት ውሳጣውያት ህየንተ አዕይንት ሥጋውያት" ብሎ በነገረን በነፍስ ዐይን እንጂ በመስታዎቷ ፊት ቆማ በዘመን ፀሓይ ለሚረግፈው አበባነቷ እንዲኽ አለች፦

"ዘወትር ወደ ዝሙት የምትሮጡ እግሮቼ ኾይ ሞት በሚያሥራችኹ ጊዜ እንደምን ትኾናላችኹ? ልታመልጡ ትወዳላችኹ አይቻላችኹም፣ ባንተ ብዙ ያጣኹ አንደበቴ ኾይ፦ ትመልስለት ዘንድ የማይቻልኽ የዐለም ኹሉ ገዥ የሚኾን ሞት ዝም ባሰኘኽ ጊዜ እንደምን ትኾናለኽ?'' ከድምፅ አልባው ምስሏ ጋር እንዲኽ ስታለቅስ ቆይታ ከኀጢኣት ወደ ጽድቅ የሚመልሳትን ጌታ ልትፈልግ ወጣች።

ግን ደገሞ ባዶ እጇን መኼድ አልወደደችም። ሃድኖክ ወደሚባል ነጋዴ ኼዳ ውድ ሽቱ ለመግዛት ጠየቀችው። የዘወትር ፈገግታዋን በፊቷ ላይ ያጣው ነጋዴም

ጠየቃት። እንዲኽ ስትል መለሰችለት

እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ፡፡"

"ማርያም! ምን ኾነሽ አዝነሻል? ከሚወዱሽ ወንዶች የሞተ አለን?" ብሎ "እወ ብዙኅ ኀጢኣትየ ሞተ ወእፈቅድ እቅብሮ፤ ብዙ ኀጢኣቴ ሞተ እቀብረው ዘንድ እወዳለኹ ::

👉https://t.me/Kdusan_Anst

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

06 Oct, 08:48


Happy Sunday

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

19 Sep, 08:50


#ወይቤላ_እግዚእ_እየሱስ_አነሂ_አልቦ_ዘእኮንነኪየዮሐንስ ወንጌል 8 : 3 - 11
"ጻፎችና ፈሪሳውያንም በምንዝር የተያዘችን ሴት ወደ እርሱ አመጡ በመካከልም እርሱዋን አቁመው፡— መምህር ሆይ፥ ይህች ሴት ስታመነዝር ተገኝታ ተያዘች። ሙሴም እንደነዚህ ያሉት እንዲወገሩ በሕግ አዘዘን፤ አንተስ ስለ እርስዋ ምን ትላለህ? አሉት። የሚከሱበትንም እንዲያገኙ ሊፈትኑት ይህን አሉ። ኢየሱስ ግን ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ፤ መላልሰው በጠየቁት ጊዜ ግን ቀና ብሎ፡— ከእናንተ ኃጢአት የሌለበት አስቀድሞ በድንጋይ ይውገራት፡ አላቸው። ደግሞም ጐንበስ ብሎ በጣቱ በምድር ላይ ጻፈ። እነርሱም ይህን ሲሰሙ ሕሊናቸው ወቀሳቸውና ከሽማግሌዎች ጀምረው እስከ ኋለኞች አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች። ኢየሱስም ቀና ብሎ ከሴቲቱ በቀር ማንንም ባላየ ጊዜ፡— አንቺ ሴት፥ እነዚያ ከሳሾችሽ ወዴት አሉ? የፈረደብሽ የለምን? አላት። እርስዋም፡— ጌታ ሆይ፥ አንድ ስንኳ አለች። ኢየሱስም፡— እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ፡ አላት።"

አንተ ያደረግህልኝን ማሰብ እንዳልተው አመስጋኝ ነፍስን ስጠኝ፤ በድካሜ ውስጥ ጉልበትን ስጠኝ፣ በቸርነት የላቅህ ጌታ ሆይ፤ በደሎቼን ሁሉ ይቅር በለኝ እንጂ ብዙ የሆኑትን ኃጢአቶቼን አታስብብኝ:: የእኔ የክፉውን ኃጢአተኛ ጸሎት አትናቀው:: ከዚህ በፊት እንደጠበቀኝ ሁሉ ለወደፊትም እንዲጠብቀኝ በጸጋህ እስከመጨረሻው አጽናኝ:: ጥበብን ያስተማረኝ ያንተ ጸጋ ነው፤ የእርሷን [የጥበብን] መንገድ የሚከተሉ ብጹዓን ናቸው፤ የክብር አክሊልን ይቀዳጃሉና:። ረዳቴና ጠባቂዬ አንተ ነህ:: ስምህ ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::
ወይኩነነ በከመ ፈቃድከ አምላክነ 🙏
👉 https://t.me/Kdusan_Anst

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

30 Aug, 05:23


ነሐሴ ፳፬
🌹 ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በአለ ዕረፍታቸው🌹

ረዳቴ ሆይ ልቤ በክፋት የታወረብኝ እኔን መራራትን አስተምረኝ አማላጄ ሆይ ኢቺን ዓመት ተዋት ብለህ ከጌታ ዘንድ አማልደኝ።
አባቴ ሆይ አለው የምልብህ አለኝታዬ ዙሪያዬን የምረግጠውን የማይብህ ብርሃኔንና ደስታዬን ከእኔ ያላራቅህ መድሃኒቴ የጭንቁን ቀን አብረኸኝ የተሻገርክ እረዳቴ የተደገፍኩህ ምርኩዜ የተማመንኩብህ ድጋፌ የከበርኩብህ ከፍታዬ የተሻገርኩብህ ጠባቂዬ
የሕይወቴን ብሩቱ ሰልፍ የማልፍብህ ለምኜ ያላፈርኩብህ እረዳቴ አሳዳጊዬ ተናግሬ የማልጨርሰው ውለታህ ያለብኝ ባለውለታዬ ሆይ ክበርልኝ
ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ተክለ አብ:ተክለ ወልድ: ተክለ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ♥️ ከመታሰብ በላይ ስለሆነው ፍቅርህ አንክሮ ይገባል ። በተቀደሰች ዕረፍትህም አንተን የሚያስዝንህን ነገር እንዳልሰራ ፈረስ በልጓም እንዲለጎም ሕሊናዬን፣ሀሳቤን፣ሰውነቴን፣ ሁለመናዬን በፍቅርህ ልጓም ለጉመው።
አባ ተክለ ሃይማኖት ሆይ ከዚህ : ዓለም ኑሮና: ፈተና : የመከራ : ቂም : በቀል : በመላእክት :አጃቢነት ፡በክብር : ለተለየችው : ለነፍስህ : መውጣት : ሰላም : እላለሁ ::

"ምዕቅብና ነፍስየ ወሥጋየ ወሀብኩከ ነዋ"
"#የነፍሴንም_የሥጋዬንም_ጥበቃ_ለአንተ_አደራ_ሰጥቻለሁና"♥️♥️

🌹 መልካም በአል 🌹l

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

22 Aug, 07:03


ነሐሴ 16/2016 #እናታችን_ኪዳነ_ምህረት

"የእናታችን ማርያም ትንሣኤና እርገት"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በክብር ለምናመሰግንበት #ለእናታችን_ማርያም_ትንሣኤና_ዕርገት መታሰቢያ አመታዊ ክብረ በዐል እንኳን አደረሰን

👉 #የእናታችን_የድንግል_ማርያም እድሜዋ 64 ሲሆን በእናት አባቷ ቤት 3 ዓመት በቤተመቅደስ 12 ዓመት ጌታን ፀንሳ በቤተ ዮሴፍ 9 ወር ከ 5 ቀን ከልጇ ከወዳጇ ጋር 33 ዓመት ከ 3 ወር ከቆየች በኋላ ዓለምን ለማዳን በእለት አርብ ጌታችን በመስቀል በተስቀለም ጊዜ የሚወዳት እናቱን ለሚወደው ደቀመዝሙር ለዮሐንስ እነኋአት እናትህ በማለት የአደራ ልጆቿ እንድንሆን ያደራ እናታችን እንድትሆን በቀራንዮ በእግረ መስቀል ስር ለኛ ለሁላችን ሰጥቶናል

👉ነሐሴ 16 ቀን አስደናቂውን የእመቤታችንን #የዕርገቷን በዓል ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት ታከብራለች የእመቤታችን ማርያምን ሱባኤ በፍጹም በረከት እንድንፈጽም ያደረገን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይግባው ጣዕመ ፍቅሯን ያላረቀችብን እመቤታችንን ምስጋና ይግባት የአባቶቻችን #ሐዋርያት በረከትና ረድኤት ለሁላችንም ይድረሰን

👉የእመቤታችን የእረፍቷ ጊዜ ሲደርስ ጥቂት ታመመች እመቤታችን የአምላክ እናት እንደመሆኗ መጠን ሕመም ባይገባትም የሰው ልጅ እንደመሆኗ መጠን ነው የታመመችው አገልጋይዋ ቅዱስ ዮሐንስ በኤፌሶን ወንጌልን እያስተማረ ሳለ #በመንፈስ_ቅዱስ ትዕዛዝ በደመና ተጭኖ ወደ እመቤታችን መጣ ሌሎችም ቅዱሳን ሐዋርያት በጸጋ አውቀው በደመና ተጭነው መጡ ሁሉን የምታጽናና እመቤት ሐዋርያትም ሲያጽናኗት #ልጅሽ_አምላካችን_ነውና ደስ ይበልሽ አሏት

👉እመቤታችንም በአልጋዋ ጠርዝ ተቀምጣ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ወደ ዘላለማዊው ዓለም እንደምሄድ በምን አወቃችሁ አለቻቸው ሐዋርያትም ‹#መንፈስ_ቅዱስ በደመና ጭኖ እንደ ዓይን ጥቅሻ ያመጣን አንቺ ወደ ዘላለማዊ ሕይወት ልትሄጂ ስለሆነ ነው አሏት እመቤታችንም ድምጿን ከፍ አድርጋ ጌታዬ #ፈጣሪዬ_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ ክቡር ምስጉን የሆነ ስምህን ፈጽሜ አመሠግናለሁ የእኔን አገልጋይህን መከራ ተመልክተህ ድንቅ አድርገህልኛልና ከእንግዲህ #ትውልድ ሁሉ ያከብሩኛል ያመሠግኑኛል አለች

👉 #ቅዱሳን_ሐዋርያትም ከእነሱ መለየቷን ሲያውቁ ትባርካቸው ዘንድ እያለቀሱ ጠየቁ ወላዲተ አምላክም እጇንም በላያቸው ላይ ዘርግታ ባረከቻቸው በዚያን ጊዜ የክብር ባለቤት ልጇ እልፍ አእላፍ መላእክት አጅበውት እያመሰገኑት መጥቶ አረጋጋት በሰማይ ያዘጋጀላትን ተድላ ደስታ ነገራት ጌታችንም ከገነት ያመጣውን አፒሊያኖስ የሚባል መዓዛው ለነፍስ የሚጣፍጥ የሚመስጥ አበባ በአፍንጫዋ እያሸተተች በጆሮዋ የመላእክትን ምስጋና እየሰማች ያለ ጣር ያለ ጋር በተመስጦ በደስታ ነፍሷ ከሥጋዋ ተለየ

👉ጌታችንም ንፅህት ነፍሷን የብርሃን መጎናፀፊያ አልብሶ በመላእክት ዝማሬ ጥር 21 ቀን ወደ ሰማይ አሳረጋት ነብዩ ዳዊት ‹"ነፍሴ ሆይ ወደ እረፍትሽ ግቢ እግዚአብሔር መልካም ነገርን አድርጎሻልና›" እንዳለ መዝ.114÷7 #እመቤታችንም በልጇ ደስታ ወደ ሰማይ እረፍቷ ገባች

👉በሌላ ታሪክ #እመቤታችን በእረፍቷ ጊዜ ጌታችን ሲመጣ "ልጄ ወዳጄ እኔ አንተን ወልጄ እንዴት እሞታለሁ በእውኑ ሞት ለእኔ ይገባኛልን ብላ ጠይቃው ነበር "እሱም በሲዖል የሚሰቃዩትን ነፍሳት አሳይቷት እናቴ እነዚህ በሲዖል የሚሰቃዩት ነፍሳት የሚያገኙት እረፍት ባንቺ ሞት ነው ሲላት የሞቷን መልካምነት
በሲዖል ለሚሰቃዩት ነፍሳት ነፃ መውጣት መሆኑን የተረዳችው እመቤታችን "ልጄ ሆይ ለእነዚህስ አይደለም አንዴ ሰባቴ ልሙትላቸው"ብላ በፍቃዷ እዳረፈች ሊቃውንት ይተርካሉ

👉ወዳጆቼ እመቤታችን ለእኛ ለልጆችዋ ሰባቴ ለመሞት በነፍሷ የተወራረደች እናት ሆና ሳለ በዚህም እመቤታችንን በነፍስ ፍቅር አለመውደድ ማለት ከጣዕመ ፍቅሯ መሰደድ በቁም ለሲዖል እሳት መማገድ ነው #እመቤታችን_ማርያምን አለማመስገን ማለት በነፍስ በሥጋ ከፀጋ ፍቅሯ መራቆት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ተላልፎ መሰጠት ነው ከወለላይቱ ከአዛኝቱ ጣዕመ ፍቅር መለየት ማለት ከሞቱት በላይ ከሚኖሩት በታች ሆኖ በቁም መሞት ነው

👉ከዚህ በመቀጠል አብይ ነጥቡ የወላዲተ አምላክ #ማርያም #ትንሣኤና_እርገቷ ነዉ በእለተ እረፍቷ የተፈፀመዉን የመሠወር ሚስጢር ያየ ዮሐንስ ሲሆን የመጨረሻውን ትንሣኤና ዕረፍት ለማየት የታደለዉ #ቶማስ ብቻ ነዉ

👉በወቅቱና በቦታዉ ያልነበረው ቶማስ የትንሣኤዋንና የእርገቷን ምስጢር ተገልፆለት ለሐዋርያት በነገራቸው ጊዜ መቃብሩን ከፍተዉ ቢያዪት ባዶዉን ስላገኙት #ትንሣኤዋንና_እርገቷን ለማየት በአመቱ ነሐሴ አንድ ቀን እንደገና ሌላ ፆመ ሱባኤ በመግባትና ፈጣሪያቸዉን በመለመን በነሐሴ 16ኛዉ ቀን ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር ቅዱስ ጴጥሮስን ረዳት ካህን ቅዱስ እስጢፋኖስን ቀዳሚ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁሩቧቸዋል ሐዋርያትም የዚህ ድንቅ ሚስጢር ተካፋይ ሆነዋል

👉አባቶቻችን ሐዋርያት የእመቤታችንን እረፍቷን ትንሣኤዋን እርገቷን በፆምና በፀሎት አይተዉ የህሊና እረፍታቸውን የደመደሙት እመቤታችን ለትንሣኤዋ ተጨባጭ ምልክት በእርገቷ ጊዜ #ለቅዱስ_ቶማስ የሰጠችዉን ሰበን ለበረከት ከተካፈሉ በኋላ ነዉ ለኛም የቃል ኪዳን ልጆቿ በረከት ረድኤቷ ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

06 Aug, 17:24


ነሐሴ 1/2016 #ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት እናታችን ወላዲተ አምላክ #ማርያምን ከልጇ ከወዳጇ እንድታማልደን በፆምና በፀሎት ለምንለምንበት #ለፆመ_ማርያም እንኳን አደረሰን

👉 #ፆመ_ፍልሰታ እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ከሰባቱ የአዋጅ አፅዋማት መካከል አንዱ ሲሆን #ፆመ_ፍልሰታ_ለማርያም ተብሎ ተወስኖ ይፆማል

👉የፆሙ ዋና ምክንያት #ሐዋርያት የእመቤታችንን የእረፍቷን ነገር አስመልክተው የፆሙት ፆም ነው

"ታሪኩን በአጭሩ እንዲህ እንመለከታለን"

👉እመቤታችን በጥር እሁድ ቀን በ21 ቀን አረፋለች ሐዋሪያት በአጎበር አድረገው ወደ #ጌቴሴማኒ_ስጋዋን ይዘው ሲሄዱ አይሁድ ቀድሞ ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል ዛሬ ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለምን ስለዚህ አስክሬኗን በእሳት እናቃጥላለን ብለው ተነሱ

👉ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ተራምዶ አጎበሯን ጨበጠው መልአኩ ሁለት እጁን ቆረጠው እጁ ከአጎበሩ ተንጠጥሎ ቀረ ከዚህ በኋላ መላዕክት #የእመቤታችንን_አስክሬን ወስደው በገነት አኑረዋታል ይህንንም ሚስጥር ያየው ሐዋርያው አባታችን #ቅዱስ_ዮሐንስ ነዉ

👉ሐዋርያትም ከዮሐንስ ጠይቀዉ የተረዱትን ምስጢር ለማየት ነሐሴ 1 ሰኞ ቀን ፆመ ሱባኤ ጀመሩ #የእግዚአብሔርን ፀጋና ቸርነት ደጅ ሲጠኑ ሁለቱን ሱባኤ እንዳገባደዱ በ14ኛዉ ቀን እሁድ አምጥቶ ስጋዋን ሰጥቷቸዋል በጥር የእረፍት ጊዜ ተወስኖ በነበረበት ቦታ በጌቴሴማኒ ቀብረዋታል ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ በሶስተኛው እለት ተነስታ አርጋለች #እንደ_ልጇ_ትንሳኤ ያሰኘው ይህ ነው በዚህ የቀብር ስነ ስርዓት ላይም ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ #ቅዱስ_ቶማስ አልነበረም

👉 #ቅዱስ_ቶማስም ደመና ጠቅሶ ከሀገረ ስብከቱ ሲመጣ ስታርግ አገኛት ከሚጓዝበት የደመና ጉዞ ላይም ለመውደቅ ወደደ ቀድሞ የልጇን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ዛሬ ደግሞ ያንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ አይዞህ አትዘን ወንድሞችህ ሐዋርያት ትንሳኤዬን ዕረገቴን አላዩም አንተ አይተሀል ተነሳች አረገች ብለህ ንገራቸው ብላ ምልክት ይሆነው ዘንድ የያዘችውን #ሰበን ሰጥታ ሰደደችው

👉ከዚህ በኋላ #ቶማስ_የእመቤታችን ነገር እንደምን ሆነ ብሎ ሐዋርያትን ጠየቃቸው አግኝተን ቀበርናት አሉት ሞት በጥር በነሐሴ መቃበር ተው ይሄ ነገር አይመስለኝም አላቸው

👉ቅዱስ #ጴጥሮስም አንተማ ልማድህ ነው አንተ ብቻ ተጠራጥረህ አትቀርም አንተ እየተጠራጠርክ ሰውን ሁሉ ስታጠራጥር ትኖራለህ አለው

👉እርሱም የያዘውን ያውቃልና ፀጥ ብሎ ይሰማቸዋል ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ ተቆጥቶ ሂዶ መቃብሩን ቢከፈተው አጣት ደንግጦ ቆመ አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ #እመቤታችን_ተነሰታለች አርጋለች አላቸው የያዘውን ሰበን ሰጥቶአቸው ለበረከት ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከታቸው ተበታትነዋል

👉በዚህ ምክንያት በአመቱ ቶማስ ትንሳኤሽን ዕረገትሽን አይቶ እኛ ሳናይ ብለው #ቅዱሳን_ሐዋርያት ነሐሴ 1 ሌላ ሱባኤ በመግባት ፈጣሪያቸዉን ለምነዉ ነሐሴ 16 ቀን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር ቅዱስ ጴጥሮስን ረዳት ካህን ቅዱስ እስጢፋኖስን ቀዳሚ ዲያቆን አድርጎ ቀድሶ አቁርቧቸዋል እመቤታችንም ከልጇ እጅ ቆርባለች

👉ከዚህ ጊዜ ጀምሮ #የሐዋርያት_ቤተ_ክርስቲያን የእናታችን የእመቤታችንን #ማርያምን በረከት ለማግኘት ይኼን ጊዜ ትፆማለች

👉እኛም #ከእናታችን_ማርያም በሱባኤውና በፆሙ ስንጠነክር የእሷ አማላጅነት የልጇ የመድኃኔዓለም ቸርነት ከመከራ ስጋና ከመከራ ነፍስ አድኖ ለንሰሀ ጥሪ እንደሚያበቃንና ቅዱስ ስጋውን እና ክቡር ደሙን ለመቀበል እንደሚፈቅድልን አምነን ልንፆምና ልንፀልይ ይገባናል የይቅርታ የበረከት የረድኤት ፆም ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

30 Jul, 20:08


ሐምሌ 23/2016 #ሰማእቱ_ቅዱስ_ጊዮርጊስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ለሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉ሐምሌ 23 መናገሻ ገነተ ጽጌ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ቤተ ክርሰቲያን በመድኃኔዓለም ፈቃድ በሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት እና ረዳትነት በንጉሣችን ዳግማዊ አፄ ምኒልክ (ምን-ይልክ)ንጉሠ ነገስት ዘኢትዮጵያ መስከረም 23/1888 ዓ.ም ተመስርቶ 1894ዓ.ም ሥራው ተጠናቆ ሐምሌ 23/1894 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ተከበረ

👉 #ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ ብሩህ ሐረገ ወይን ፀሐይ ማለት ነው ሊቀ ሰማእቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ በጥር 20ቀን በ 277ዓ/ም ተወለደ ሃገሩ ፍልስጤኤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይበላል አባቱ ዞሮንቶስ አንስጣስዮስ ይባላል ከልዳ መኳንንት ተሹሞ ይኖር ነበር እናቱ ቴዎብስታ አቅሌስያ ትባላለች ማርታና እስያ ተብለዉ የሚጠሩ እህቶች ነበሩት

👉10 አመት ሲሞላው አባቱ ስለ ሞተ ሌላ ደግ ክርስትያናዊ መስፍን ከቤቱ አሳደገው በጦር ሃይልም አሰለጠነው 20 ዓመት ሲሞላዉ የ15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ #እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቤሩት ሄደ

👉በቤሩት ደራጎን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ #እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል

👉ወደ ፋርስ ሲመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገስታትን ሰብስቦ ጣኦታት ሰብስቦ ሲሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖት ቀናዒ ነውና ከቤተ መንግስቱ ገብቶ እኔ ክርስትያን ነኝ #በኢየሱስ_ክርስቶስ አምናለሁ አለው

👉እርሱንም ማንነቱ ከተረዳ በኋላ አንተ እማ የእኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የእኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ አለው #ቅዱስ_ጊዮርጊስም ሹመት ሽልማትክ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬን ኢየሱስ ክርስቶስ አልክድም አለ በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት

👉እርሱ ግን ይህን ከሀዲ እስካስፈራው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ በማለት #እግዚአብሔር ለመነና እንደ ፀሎቱ በእምነቱ ፅናት ሰው ሊሸከመዉ የማይቻለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው

👉የኢትዮጵያ ጠባቂ ሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሀገራችንን ህዝባችንን ጌታ ይጠብቅ ዘንድ በምልጃህ አስበን

👉በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸው የሚታወሱ ቅዱሣን በረከት ለሁላችንም ይድረሰን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

23 Jul, 04:21


ሐምሌ 16/2016 #ቅድስት_ኪዳነ_ምህረት

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በምስጋና ከፍ ለምናደርግበት እናታችን #ኪዳነ_ምህረትን በቃል ኪዳኗ እንድታስበን ለምንማፀንበት ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአሏ እንኳን አደረሰን

👉 #ኪዳነምህረት ስንል የምህረት ቃል ኪዳን ማለት ነው በዚህ ውስጥም ምህረት አድራጊው ጌታችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ምህረት ተቀባይም መላው የአዳም ዘር ነው

👉 #እናታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም በምድራዊ ቆይታዋ ዘውትር ወደ #ክርስቶስ_መካነ_መቃብር_ጎለጎታ እየሔደች ትፀልይ ነበር ልጇ እና ወዳጇ ጌታችን መድሐኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረገችውን ልመናና ፀሎት ተመልክቶና ሰምቶ #የምህረት_ቃል_ኪዳንን ሰጣት

👉እንኳን የእናቱን ፀሎት እና ልመና ቀርቶ ዘውትር በሀጥያት የምንዘፈቀውን እኛን ክፉዎቹን የሚሰማ አምላክ ስለ አንቺ ስለ እናቴ ክብርና ፀጋ ስል ይኸው ቃሌ ብሎ #ቃል_ኪዳን አደረገ

👉"ከመረጥሁት ጋር #ቃል_ኪዳኔን አደረግሁ" መዝ.89፥3

👉ስሟን ለሚጠሩ በእርሷ አማላጅነት ለሚታመኑ በምድር በረከትን በሰማይ የዘለዓለም መንግስትን እንደሚወርሱ የምህረት እና የቸርነት #ቃል_ኪዳን ሰጥቷታል

👉በታላቁም መፅሐፍ ቀስቲቱም በደመና ትሆናለች በእኔና በምድር ላይ በሚኖር ሥጋ ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ያለውን የዘላለም #ቃል_ኪዳን ለማሰብ አያታለሁ ኦሪት ዘፍ.9፥16

👉አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ለእናታችን #ኪዳነ_ምህረት በሠጠኻት #ቃል_ኪዳን አስበን ሀገራችንን ህዝባችንን ከክፉ መከራ ጠብቅልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

28 Jun, 04:09


ድንግል ማርያም 😍

እማ....እናቴ ...ወለላይቱ... አዛኝቷ...

ከፋኝ እኮ... ሆድ ባሰኝ ያንቺ ልጅ
ይኸው በማለዳ ...ተገኘው ካንቺ ደጅ

ሀጢያቴ ቢበዛ ..ምህረትን ፍለጋ
እንባን እያዘራው..መጣለሁ አንቺ ጋ

እናቴ አይደለሽ ?????

ልታስምሪኝ ልትለምኚ...ቆመሻል ከፊቱ
ይመረኛል ባንቺ...ወለል ይላል ቤቱ

ስለ አንቺ ልመና ..ስለ እንባሽ ብሎ
ከፊቱ ያቅርበኝ ..ሸክሜን አንከባሎ

በጎሎጎታ ማርያም ስታነባ ልጇ ስላያት
የማይጠፋ ኪዳን ...በስሟ ገባላት

ሊምር ሊታደግ ..በእሷ የመጣሁን
ቃሉን የሰማውን ...በህይወት የኖረውን
ቃል ገባ ለእናቱ ...ሊያብስ እንባዋን

በእንተ ማርያም ..መሀርነ ክርስቶሰ
ስማን ተለመነን ...ና ስንልህ ድረስ

.
.
.
.
.
.
.
.
.✍️VVerutawit Yohanes....21/10/2016 👑
.....12:30
.....አርብ
.

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

25 Jun, 07:33


🥰የተባረከ ቀን ይሁንላቹ 🥰

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

13 Jun, 19:08


ሰኔ 7/2016 #ቅድስት_ሥላሴ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ምስጢረ_ሥላሴ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው #እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን #አንድ_ሕያው_አምላክ ነው

👉 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው #የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው

👉 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ.ቁ.1_2 ምሳ.30_ቁ.4

👉 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ.ቁ.2_7

👉 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

👉 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

👉 #ለመንፈስ_ቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።

👉 #የሦስቱ_የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም

👉 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።

👉 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ.2_7

👉#መንፈስ_ቅዱስ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው ኢዮ.ቁ.26_13

👉አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም #ቅድስት_ሥላሴ ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

11 Jun, 08:22


#ሰኔ_2/2016 #መጥምቀ_ዮሐንስ

"በእዉነት #ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል"

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በሰማእቱ ስም ለምናመሰግንበት ሰኔ ሁለት የመጥምቁ #ቅዱስ_ዮሐንስ ሥጋ የቀናተኛው ኤልያስ ደቀ መዝሙር ከሆነው #ከነቢዩ_ኤልሳዕ ሥጋ ጋር በአንድነት ተገኘ

👉ከሀዲው ንጉሥ ዑልያኖስ የጥጦስ ልጅ አስባስያኖስ ከአፈረሰው በኋላ በዘመኑ በኢየሩሳሌም የአይሁድ ምኵራባቸውን ሊሠራ በወደደ ጊዜ እርሱ በቅዱስ ወንጌል ደንጊያ በደንጊያ ላይ ተቀምጦ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም የተባለውን #የእግዚአብሔርን ቃል ሊሽር ፈልጎ መሥራት በጀመረ ጊዜ ሦስት ጊዜ ፈረሰበት

👉አይሁድም እንዲህ አሉት የደጋግ ክርስቲያኖች ዐፅሞቻቸው በዚህ ቦታ ስለሚኖሩ ከዚህ ካላወጣሃቸውና ካላቃጠልኻቸው በዚህ ቦታ ምኵራብ አይሠራም በዚያንም ጊዜ #የቅዱሳንን ዐፅሞቻቸውን አውጥተው በእሳት እንዲአቃጥሉት አዘዘ

👉በአፈለሱም ጊዜ የመጥምቁ #ቅዱስ_ዮሐንስንና የነቢዩ #ኤልሳዕን ሥጋቸውን አግኝተው በእሳት ሊአቃጥሉ ፈለጉ ምእመናንም መጥተው ለወታደሮች ብዙ ገንዘብ ሰጡ ንጉሡም ሰምቶ እንዳያጠፋቸው በዚያች አገር እንዳያስቀሩ ከአማሏቸው በኋላ #የቅዱሳንን ሥጋ ወሰዱ

👉የዑልያኖስም ዜናው እንዲህ ሆነ የጳጳሳት አለቆች ባስልዮስንና ጎርጎርዮስን በአሠራቸው ጊዜ እነርሱ #በቅዱስ_መርቆሬዎስ ሥዕል ዘንድ እያለቀሱ ጸለዩ የክብር ባለቤት የሆነ የጌታችንን የከበረ ስሙን ሰድቧልና ያን ጊዜ #እግዚአብሔር ቅዱስ መርቆሬዎስን በአካለ ነፍስ ላከው ዑልያኖስንም በጦር ወጋው ከደሙም ዘግኖ #ኢየሱስ የሰጠኸኝን ነፍስ ተቀበል እያለ ወደ አየር ረጨ ወዲያውኑም በክፉ አሟሟት ሞተ

👉የከበሩ #የዮሐንስንና_የኤልሳዕን ሥጋ ግን እሊያ ሰዎች በእስክንድርያ ከተማ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱ አባ አትናቴዎስ አደረሱ እርሱም በእርሳቸው ታላቅ ደስታ ደስ አለው ቤተ ክርስቲያንም እስኪሠራላቸው ድረስ በርሱ ዘንድ አኖራቸው

👉በአንዲት ዕለትም አባ አትናቴዎስ በአባቶቹ ቦታዎች ላይ ስለ ጸሐፊው ቴዎፍሎስም አብሮት ሳለ #እግዚአብሔር መልካም ዘመን ቢሰጠኝ ሥጋቸውን በውስጧ አኖር ዘንድ ለቅዱሳን #መጥምቁ_ዮሐንስና_ለነቢዩ_ኤልሳዕ በስማቸው በዚህ ቦታ ቤተ ክርስቲያን እሠራለሁ አለ ቴዎፍሎስም ሰማው

👉አባ ቴዎፍሎስም በተሾመ ጊዜ አባ አትናቴዎስ የተናገረውን ያንን ቃል አስቦ ቤተክርስቲያን ሠራ ከርሱ ጋራም ብዙዎች ካህናትንና የክርስቲያን ወገኖችን ይዞ የቅዱሳን የመጥምቁ #ዮሐንስና_የነቢዩ_ኤልሳዕ ሥጋቸው ወዳለበት ሔደ በታላቅ ክብርም ተሸክመው አምጥተው ወደ ቤተ ክርስቲያን አስገቡ

👉ሥጋቸውንም ይዘው በሚጓዙበት ጊዜ በጐዳናቸው አቅራቢያ ቤት ካለበት ቦታ ደረሱ በውስጡም በምጥ ተይዛ አራት ቀናት እየጮኸች ለሞት የተቃረበች ሴት ነበረች እርሷም አረማዊት ነበረች #በቅዱሳኑም_ሥጋ ዘንድ ካህናቱ የሚያመሰግኑትን ሰምታ በቤቷ መስኮት ተመለከተች ይህ ምንድን ነው ብላ ጠየቀች

👉የቅዱሳን #የመጥምቁ_ዮሐንስና የነቢዩ ኤልሳዕ ሥጋቸው ነው አሏት እርሷም ከዚህ ሥቃይ ከዳንኩ ክርስቲያን እሆናለሁ አለች ገና ቃሏ ከአፉዋ ሳይፈጸም ያን ጊዜ መልካም ሕፃን ወለደች ስሙንም #ዮሐንስ ብላ ጠራችው ከዚህም በኋላ ከቤተሰቦቿ ሁሉ ጋራ የክርስትና ጥምቀትን ተጠመቀች።

👉የቅዱሳኑንም ሥጋቸውን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አኖሩት ከእርሳቸውም ታላላቅ ድንቆችና ተአምራት ተገለጡ በቅዳሴ ቤተ ክርስቲያኑም ጊዜ ከሊቀ ጳጳሳት አባ ቴዎፍሎስ ጋራ ብዙዎች ሰዎች #ቅዱሳን_መጥምቁ_ዮሐንስንና_ነቢዩ_ኤልሳዕን ሲዞሩ አዩአቸው በቀድሞ መልካቸው ያውቋቸዋልና የመጥምቁ ዮሐንስ መልክ ሁለመናው ፀጉር ሲሆን ኤልሳዕም ቁመቱ ረጅም ራሱ በራ ነበር

👉ከዚህም በኋላ ኤጲስቆጶሱ #አባ_መቃርስ በሰማዕትነት በሞተ ጊዜ ሥጋውን #ከቅዱሳን_ዮሐንስና_ኤልሳዕ ሥጋ ጋራ አደረጉ #የነብዪ_ኤልሣና_የመጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ ምልጃና ፀሎታቸዉ ይጠብቀን የተባረከ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

30 May, 12:52


ግንቦት 22/2016 #ቅዱስ_ዑራኤል

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በመልአኩ ስም ለምናመሰግንበት ለሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ዑራኤል ወርሐዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል እንኳን አደረሰን

👉 #ዑራኤል የሚለው ስም “ዑር” እና “ኤል” ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው

👉 #ዑራኤል ማለት ትርጉሙ #የብርሃን_ጌታ የአምላክ ብርሃን ማለት ነው

👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ለነቢዩ ዕዝራ ጽዋዓ ልቡና ያጠጣዉ ጥበብና ማስተዋልን የሰጠዉ የጠፉትን ቅዱሳት መፃህፍትን በቃሉ አጥንቶ እንደገና እንዲጽፋቸዉ የረዳዉ መልአክ ነዉ (ዕዝ ሱቱኤል13፥39)

👉 #ቅዱስ_ዑራኤል ቅድስት ማርያም ልጅዋን ህፃኑን ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ ለስደት በተነሳች ጊዜ ከምድረ እስራኤል ወደግብጽ ከዚያም ወደ ቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ እየመራ ያመጣት መልአክ ነው (ድርሳነ ዑራኤል ገጽ 26 ምዕ 4)

👉አቤቱ የመላእክት ሁሉ አለቃ የሚሆን #የቅዱስ_ዑራኤል አምላክ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ሆይ በክርስቶስ ክርስቲያን የተሰኘን የጥምቀት ልጆችህን ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ጠብቀን ምህረት ቸርነትህ አይለየን "አሜን" ✝️ ⛪️ ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

05 May, 05:41


".... ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ? እነሆ ተነስቷል እንጂ በዚህ የለም፤ የሰው ልጅ በሀጢያተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በ3ኛውም ቀን ሊነሳ ግድ ነው..."ሉቃስ ፳፬:፭
❤️እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል❤️(Bezi💕)

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

21 Apr, 19:56


ሚያዚያ 13/2016 #እግዚአብሔር_አብ
#ቅዱስ_ሩፋኤል
#አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ_አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት ለመልአኩ #ቅዱስ_ሩፋኤል ለፃድቁ #አቡነ_ዘርዐ_ብሩክ ወርሐዊ መታሠቢያ በአላቸዉ እንኳን አደረሰን

👉 #ቅዱስ_ሩፋኤል ቊጥሩ ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት ሲኾን ሩፋ፤ ማለት ሐኪም፤ ኤል ማለት #እግዚአብሔር ማለት ሲኾን ሩፋኤል ማለት “እግዚአብሔር ሐኪሜ ነው” ማለት ነው፤ ሄኖክም “በሰው ቁስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” ይለዋል (መጽሐፈ ሄኖክ 6፥3)

👉ይኽ መልአክ በራማ ሰማይ ያሉ ነገደ መናብርትን የሚመራቸው ነው ነገደ መናብርት ያላቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል የሚመራቸው በራማ ሰማይ የሚኖሩ ነገደ መላእክት ናቸው

👉ቅዱስ ኤጲፋንዮስም በሥነ ፍጥረት መጽሐፉ ላይ “ወለዳግም ጾታ ዐሠርቱ ስሞሙ መናብርት ወሊቆሙ #ሩፋኤል እሉ እሙንቱ እለ ይቀልል ሩጸቶሙ እምነፋስ ወእለ ይጸውሩ ወላትወ መብረቅ ወኲናተ እሳት ዘይነድድ ወአንበሮሙ በዳግሚት ሰማይ” ይላል

👉በራማ ሰማይ የሚገኘውን ኹለተኛውን ዐሥሩን ነገድ መናብርት ሲላቸው አለቃቸው #ቅዱስ_ሩፋኤል ነው፤ እነዚኽም ረቂቅ የኾነ የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘው ከነፋስ ይልቅ የፈጠኑ ሲኾኑ በራማ በኹለተኛው ክፍል ላይ አስፍሯቸዋል

👉#የእግዚአብሔር_አብ ቸርነት የልጁ የመድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስ ምህረት #የመንፈስ_ቅዱስ አንድነት ከኛ ከልጆቹ አይለየን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

16 Apr, 08:29


bishop mar mari emmanuel ኢትዮጵያ መተው ዘምረው ነበር 🧡🧡🙏🙏ፀሎት እናድርግላቸው

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

14 Apr, 19:21


ሚያዚያ 7/2016 #ቅድስት_ሥላሴ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ለአጋእዝተ አለም ቅድስት #ሥላሴ ወርሐዊ መታሠቢያ በአል እንኳን አደረሰን

👉 #ምስጢረ_ሥላሴ ስለ ሥላሴ ምስጢር የሚናገር ትምህርት ማለት ነው እግዚአብሔር አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፋፍለው በአንድነትና በሦስትነት የሚመሰገን #አንድ_ሕያው_አምላክ ነው

👉 #የእግዚአብሔር ሦስትነት ስንል እግዚአብሔር የማይለያይና የማይቀላቀል ፍጹም የሆነ ሦስትነት አለው ማለታችን ነው #የእግዚአብሔር ሦስትነት በስም በግብር በአካል ነው

👉 #እግዚአብሔር በስም ሦስት ስንል ሦስት የተለያዩ ስሞች አሉት ማለታችን ነው እነዚህም #አብ_ወልድ_መንፈስ_ቅዱስ የሚባሉት ሲሆኑ እርስ በርሳቸው አይወራረሱም አንዱ በሌላው ስም አይጠራም ዘፍ፣1፤2 ምሳ 30፤4

👉 #እግዚአብሔር በግብር ሦስት ነው ስንል ሦስት የተለያዩ የአካል ሥራዎች አሉት ማለት ነው እነሱም መውለድና ፤መወለድ፤ ማስረፅ "የአብ ወላዲ"፣"የወልድ ተወላዲ"፣"የመንፈስ ቅዱስ ሠራፂ" የሚሉት ሲሆኑ የአካል ግብር ይባላሉ መዝ፣ 2፤7

👉 #እግዚአብሔር በአካል ሦስት ነው ማለት ደግሞ
ለአብ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው።

👉 #ለወልድ፤ ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ።

👉 #ለመንፈስ_ቅዱስ፤ፍፁም መልክ፤ ፍፁም ገጽ፤ ፍፁም አካል አለው ማለታችን ነው።

👉 #የሦስቱ_የእግዚአብሔር ስሞች ትርጉም

👉 #አብ ማለት አባት ማለት ሲሆን የሚወልድ፤የሚያሰርጽ ወይም የሚያስገኝ ያለ እናት ወልድን የወለደ፤ መንፈስ ቅዱስን ያሰረጸ ነው።

👉 #ወልድ ልጅ ማለት ሲሆን የሚወለድ ወይም ያለ እናት ቅድመ ዓለም፤ ያለ አባት ድህረ ዓለም የተወለደ ነው መዝ፣2፤7

👉#መንፈስ_ቅዱስ ረቂቅ፤ ልዩ፤ ንፁህ; ከፍጡራን መናፍስት ሁሉ የተለየ ማለት ነው። ኢዮ፣26፤13

👉አለምን ካለ መኖር ወደ መኖር ያመጡ አጋዕዝተ አለም #ቅድስት_ሥላሴ ህይወታችንን በምህረት ቤታችንን በበረከት ይጎብኝልን ፆም ፀሎታችንን ተቀብሎ ለሀገራችን ሠላምን ለህዝባችን ፍቅር አንድነትን ይስጥልን የተባረከ #ቀዳሚት ሰንበት ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️

ተዋሕዶ ቤት 𝓽𝓮𝔀𝓪𝓱𝓭𝓸 𝓫𝓮𝓽

13 Apr, 06:43


ሚያዚያ 5/2016 #ብርሐናተ_አለም_ጴጥሮስና_ጳዉሎስ
#ፃድቁ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ

👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በፆምና በፀሎት ለምንማፀንበት በቅዱሳኑ ስም ለምናመሰግንበት #ለቅዱስ_ጴጥርስና #ለቅዱስ_ጳዉሎስ ለፃድቁ አባታችን #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ወርሐዊ መታሠቢያ በዐል እንኳን አደረሰን

👉አባታችን #አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብፅ ነው አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ #እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች

👉በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን #ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ

👉አባታችን ዓይን በገለፁ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ብለዉ ተነስተው "ስብሐት #ለአብ ስብሐት #ለወልድ ስብሐት #ለመንፈስ_ቅዱስ ከፅልመት ወደ ብርሐን ያመጣኸኝ ብለው አመስግነዋል

👉በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን መስለዋል አባታችን #ጻድቁ_አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማፀነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል

👉የፃድቁ አባታችን #ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ ረድኤት በረከታቸው አይለየን በዚህ እለት በመታሠቢያ በአላቸዉ የምናስባቸው ቅዱሣን #ብርሃናተ_አለም_ጴጥሮስ_ወ_ጳዉሎስ እንዲሁም ሌሎች ቅዱሣን ምልጃ ፀሎታቸዉ ይጠብቀን የከበረዉ ቃል ኪዳናቸዉ ሀገራችንን ህዝባችንን ይጠብቅልን የተባረከ የተቀደሰ #ቀዳሚት_ሰንበት ይሁንልን "አሜን" ✝️ 💒 ✝️