የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመዉጫ ፈተና (Exit Exam) ጊዜን በድጋሚ ስለማሳወቅ
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሆኑን ከዚህን በፊት መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ፈተናውን ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች (አዲስና በድጋሚ ለመፈተን ያመለከታችሁ በሙሉ) ፈተናው የሚሰጠው ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ማሳሰቢያ፡-
ተጨማሪ መረጃዎች በምዝገባ link እና በተለያዩ የግንኙነት ዘዴዎች በየጊዜው የምናዋሳውቅ በመሆኑ እንድትከታተሉ እናሳውቃለን፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር