Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹 @mudcpr Channel on Telegram

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

@mudcpr


This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹 (English)

Join @mudcpr on Telegram to stay updated on all things related to urban development and infrastructure in Ethiopia. This channel serves as the official page of the Ministry of Urban and Infrastructure, providing valuable insights, news, and updates on various projects, initiatives, and policies. Whether you are a stakeholder in the urban planning sector or simply interested in learning more about the development of cities and infrastructure in Ethiopia, this channel is the go-to source for reliable information. Stay informed, engaged, and connected with the Ministry of Urban and Infrastructure by joining this dynamic Telegram channel today!

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

12 Jan, 14:04


በይፋዊ ጉብኝታቸው ወቅት የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻችንን ለማጠናከር ውጤታማ ውይይቶች ካደረግን በኋላ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድን ሸኝቻለሁ።

This afternoon, I bid farewell to President Hassan Sheikh Mohamud following productive discussions on deepening cooperation and strengthening bilateral ties during his working visit to Ethiopia.

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

07 Jan, 05:19


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ የሰላም፣ የጤና፣ የአብሮነት እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

05 Jan, 10:43


የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን  ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በአል አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገለጻል!!

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

04 Jan, 13:09


'ገበታ ለትውልድ' በጅግጅጋ

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

03 Jan, 17:30


ያለንን የውሃ ሃብት ለልማት በመዋል የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው።ለአብነትም ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ በሶማሌ ክልል በግብርና ሲለማ የነበረውን 350 ሺህ ሄክታር መሬት በሶስት እጥፍ ማሳደግ ተችሏል።

Hojiileen qabeenyaa bishaanii keenya missoomarra oolchuudhaan Itoophiyaa badhaate dhugoomsuuf eegalaman bu'aa jajjabeessaa galmeessisaa jiru. Fakkeenyaaf, jijjirama akka biyyaatti dhufetti aanee Naannoo Sumaaleetti lafa hektaara kuma 350 qonnaan misoomaa ture dachaa sadiin guddisuun danda'ameera.

The efforts to harness our water resources for Ethiopia’s development are yielding promising results. For instance, following the national reforms, the country has tripled the 350,000 hectares of land cultivated by agriculture in the Somali region.

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

03 Jan, 09:50


ከሁለት አመታት በፊት ወደ ጎዴ መጥቼ ነበር። ከዚያ ወዲህ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አበረታች ነው። በጽኑ ሃሳብ ማተኮር ያለብን በልማት ላይ ነው። ይኽ መንገድ ለእድሎች በር የሚከፍት፣ የሕይወት ደረጃን የሚያሻሻልና ማኅበረሰብን የሚያሻግር ጎዳና ነው።

በምዕራብ ጎዴ የመስኖ ፕሮጀክት በተለየይ ደስታ ተስምቶኛል። በአንድ ወቅት ገላጣ የነበረው በረሃማ መሬት በመስኖአሁን ታርሶ በተስፋ ሰጪ አቅም የሰሊጥ፣ ስንዴ፣ በቆሎ አዝርዕት ምርት እና በተለያዩ የፍራፍሬ ምርቶች የተሞላ ስፍራ ሆኗል።

I came to Gode two years ago, and it’s encouraging to see the progress taking place since then. Our focus must remain steadfast on development — the path that unlocks opportunities, improves livelihoods, and transforms communities.

I am particularly pleased with the success of the West Gode Irrigation Project. What was once barren land is now being cultivated, with promising potential for producing sesame, wheat, corn, and a variety of horticultural crops.

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

07 Dec, 19:14


ከአምስት ወራት በፊት ከነበረኝ ጉብኝት በመቀጠል ዛሬ የአርባምንጭ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የደረሰበትን የእድገት ደረጃ ገምግመናል። ይኽ ሥራ የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም የሚያጠናክር የአካባቢውን አስደናቂ የተፈጥሮ መልክዓ ምድር እና የተትረፈረፈ ሀብት ቆጥሮ የሚጠቀም ሁሉን ያካተተ ነው። ቱሪዝምን ከማሳደግ ባሻገር ለአካባቢው ማኅበረሰብ ፕሮጀክቱ ትርጉም ባለው ደራጃ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። እነዚህን መሰል ሥራዎች በስኬት ሥራ ሲጀምሩ ለዘላቂ ልማት እና ብልፅግና መንገድ የሚጠርጉ ይሆናሉ።

Today, we reviewed the progress of the Dine for Generations Arba Minch project, five months after my last visit. This initiative aims to establish a fully-fledged facility that harnesses the region’s stunning natural scenery and abundant resources to strengthen the nation’s tourism capacity. Beyond boosting tourism, the project is set to create substantial job opportunities for the local community. With a promising return on investment, these interventions are paving the way for sustainable growth and lasting prosperity in the area.

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

24 Nov, 18:11


ፓፓያ ለሀገር ውስጥ አቅርቦት በመዋሉ እንዲሁም ለውጭ ገበያ ባለው እምቅ አቅም የተነሳ በኢትዮዽያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ካላቸው የፍራፍሬ ዝርያዎች አንዱ ነው። የበለፀጉ የግብርና አሰራሮችን በመጠቀም አርሶአደሮች ከፍ ያለ ምርት እና የላቀ ትርፍ ሊያገኙ ይችላሉ። በፓፓያ ምርት ሥራ የተሰማሩ ሁሉ ጥረቶቻቸውን በእጥፍ በመጨመር እንዲተጉ ጥሪ አቀርባለሁ።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

13 Nov, 18:31


የሪል ስቴት ልማትና ግብይት እንዲቀላጠፍና አሰራሩ  ህግን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
-----------------------------
( ዜና ፓርላማ) ሕዳር 04፣ 2017 ዓ.ም.፤ የሪል ስቴት ልማትና ግብይት እንዲቀላጠፍ እንዲሁም ከብልሹ አሰራር ነጻና ህግን የተከተለ እንዲሆን ለማስቻል እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ የተገለጸው በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ፣ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሪልስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ነው።

ረቂቅ አዋጁ በሚወጣበት ወቅት የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው በማድረግ ከተሞች ልማታቸውን ማፍጠን በሚችሉበት ሁኔታ ለመምራትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የንብረት ዕሴት ጭማሪ መሰረት ተድርጎ የከተሞች የገቢ መሰረት ማስፋት እንደሚያስችል ተገልጿል።

በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግስት ጥቅምን እያሳጣ ስለሚገኝ፣ ወደፊት ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው ማደግ ጋር በተያያዘ የንብረት ገበያው እየሰፋ እንደሚሄድ ስለሚታወቅ ችግሩ አብሮ እንዳይሰፋ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

በመሬት ላይ ለተደረገ ማንኛውም ንብረት ባለንብረቱ የንብረቱ ተገቢ የገበያ ዋጋ መረጃ ኖሮት የካፒታል ገበያው ተሳታፊ እንዲሆን አስፈላጊ ነው ተብሏል።

በማይንቀሳቀስ ንብረት ልማቱና ግብይቱ እንዲቀላጠፍ፤ ከብልሹ አሰራር የነጻና ህግን የተከተለ እንዲሆንና የተዋዋይ ወገኖችን ፍላጎት የሚያረካ፤ ጤናማ የኢኮኖሚ ግንኙነት እንዲኖርና የመኖሪያ ቤት አቅርቦት ችግር እንዲቀረፍ የሚያግዝ ወጥነት ያለው የህግ ማዕቀፍ መኖር ስለታመነበት ረቂቅ አዋጁ መዘጋጀቱ ተገልጿል።

ከፍላጎት አንጻር የሪልስቴት ልማቱ አቅርቦት እጅግ ወደኋላ የቀረ በመሆኑ ቤት ለመግዛትና ለመከራየት የሚፈልጉ ወጎኖች በከፍተኛ ሁኔታ የሚቸገሩበት ሁኔታ መቀየር ስላለበት የሪል ስቴት ኢንቨስትመንትን ማበረታታትና የቤት አቅርቦት እንዲሻሻል ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም በመድረኩ ላይ ተብራርቷል።

በውይይት መድረኩም የቋሚ ኮሚቴው አባላት፣ የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የአርክቴክቸር ማህበራት፣ ኮንትራክተሮች፣ የዩንቨርስቲ ምሁራን እንዲሁም የተለያዩ የሙያና የንግድ ማህበራት የተገኙ ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ መነሳት የሚገባቸውን የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን እንዲሁም መሻሻልና መዳበር ይገባቸዋል ያሏቸውን ሀሳቦች ተነስተው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

13 Nov, 11:08


ዛሬ በስምንት የኮሪደር አቅጣጫዎች እና 2879 ሄክታር በሚሸፍን ስፋት ላይ እየተሰራ ያለውን የሁለተኛውን ምዕራፍ የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ሥራ ሪፖርት ገምግመናል።

ከተማዎቻችንን ለእድገት እና ለኑሮ ይበልጥ ምቹ ለማድረግ ከመጀመሪያው ምዕራፍ ልምዶችን በመቀመር ትርጉም ያለው ርምጃ ለመራመድ ተችሏል።

አሁን በሶስት መሠረታዊ ኃላፊነቶች ላይ ማተኮር ይገባናል። በመጀመሪያ ለቀጣዩ ትውልድ ፍላጎት የተስማሙ ከተሞችን መገንባት፤ ሁለተኛ በመለወጥ ላይ ባሉት ከተሞች ከፍ ብሎ ማደግ የሚችል ትውልድ መቅረጽ፤ ሶስተኛም እነዚህን የዘመኑ ከተሞች በልህቀት ለመምራት የተዘጋጀ አመራር ኮትኩቶ ማብቃት ናቸው።

Today, I reviewed reports on the second phase of the Addis Ababa Corridor development, which is working on eight corridor pathways across 2,879 hectares in the city.

Significant progress has been made so far, drawing from the experiences of the first phase to make our cities more conducive to growth and livability.

We must focus on three essential tasks: first, building cities that are fit for the next generation; second, nurturing a generation capable of thriving in transforming cities; and third, cultivating leadership equipped to guide these cities effectively.

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

13 Nov, 06:15


#COP29 እየተካሄደ ባለበት ወቅት ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ጉዳይን መፍትሔ ለማስገኘት የሚከናወኑ ተግባራት ፋይናስን ኢላማ ከማድረግ ባሻገር ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያራምዱ የጋራ ግን በነፍስወከፍ የተለዩ ኃላፊነቶችን ብሎም ታሪካዊ ተጠያቂነትን የሚያጠይቁ መሆን እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥታለች።

ግልፅነት ያለቸው የአየር ንብረት የገንዘብ ድጋፍ ብያኔዎች እድገትን እንደ አፍሪካ ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ ዝቅተኛ የልማት መጠን ያላቸው ሀገራትን በተጨባጭ ለመከታተል አስፈላጊ ናቸው።

ኢትዮጵያ የፓሪስ ስምምነትን እና የባለፈውን አመት የCOP28 ኃላፊነቶቿን በሶስት ሥራዎች እየተገበረች ትገኛለች። ቀዳሚው የአረንጓዴ አሻራ ሥራ 40 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የደን ሽፋን ከነበረበት በ6 በመቶ እንዲያድግ አድርጓል። ሌላው በ2015 የምርት እጥረትን ወደ ትርፍ ምርት የለወጠው በመስኖ የለማ ስንዴ መርሃግብር ሲሆን በታዳሽ የኃይል ምንጭ የታገዙ የእግረኛ መንገዶች ያሏቸው እና የኤሌትሪክ ተሽከርካሪዎች የቀረቡባቸው ዘላቂና አረንጓዴ ከተሞችን የፈጠሩ ለአየርንብረት ጥበቃ ምቹ የሆኑ ዘመናዊ የከተማ ልማት ፕሮጀክቶች ሌላዎቹ ሥራዎች ናቸው።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

12 Nov, 07:18


ቤኑና መንደር የ'ይቻላል' እምነት ቋሚ ምስክር ነው።

Beynouna Village stands as a testament to the belief that “Anything is possible.”

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

12 Nov, 06:35


ቋሚ ኮሚቴው በህንጻ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያየ
------------------------------
(ዜና ፓርላማ) ህዳር 2 ቀን፣ 2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የህንጻ ረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቷል።

የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር እሸቱ ተመስገን ህንፃዎች ሲሰሩ ለዲዛይኖች ጊዜ ሰጥቶ በአግባቡ በመስራት የግንባታ ጊዜን የተቀላጠፈ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የአዋጭነት ጥናትና የአካባቢና ማህበራዊ ተጽኖዎችም በአግባቡ መታየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ምክትል ሰብሳቢው ከመድረኩ ጥሩ ግብአት መገኘቱን ገልጸው፤አዋጁ ረጅም ጊዜ የሚያገለግል እንዲሆን ተጨማሪ አስተያየቶችን በጽሁፍ ማድረስ እንደሚቻል ጠቁመዋል ። ዘርፉን ለማሳደግ የሙያ ማህበራት ተጠናክረው በጋራ መስራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

በውይይቱም የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ የአዋጁ ማሻሻያ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

የከተሞች ስታንዳርድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱን ገልጸው፤ የሙያ ማህበራት በጋራ ሆነው ጠንካራ አቅም መፍጠር ቢችሉ የተሻለ መሆኑን ጠቁመዋል ።

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮንስትራክሽንና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ክብርት መዲና አህመድ አዋጁን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ አዋጁ የህዝብን ደህንነት ለመጠበቅ እና ለአካል ጉዳተኞችና ለሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች የህንጻ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ዝቅተኛውን ደረጃ ለመወሰን አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል ።

በነባሩ ህግ በአፈጻጸም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፣ የአካል ጉዳተኞች ተደራሽነትን፣የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ግልጽና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ተገቢ ሆኖ መገኘቱን ተናግረዋል ።

ማንኛውም ሰው አዲስ ግንባታ ለማከናወን፣ ነባር ህንፃ ለማሻሻል ፣ለማስፋፋት ወይም ለማፍረስ እንዲሁም የአገልግሎት ለውጥ ለማድረግ በቅድሚያ ተገቢውን የግንባታ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት እና ማንኛውም ሰው የህዝብ መገልገያ የሆኑ የተጠናቀቁ ህንፃዎች አገልግሎት ላይ ከመዋላቸው በፊት የህንጻ መጠቀሚያ ፈቃድ ማግኘት እንዳለበት ገልጸዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ ባለድርሻ አካላት አዋጁን በሚመለከት አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል ።

በውይይቱ ከክልል እና ከከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የመጡ የስራ ሃላፊዎች ፣ከኢትዮጵያ አርክቴክቶች ማህበር፣ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፣ቲንክታንክ ቡድን እና ሌሎችም በዘርፉ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

05 Nov, 16:49


“In a crisis-prone world with a growing population, ensuring food security demands innovative solutions.

We must adopt sustainable practices, advance modern farming, expand access to essential agricultural inputs, and address climate change to enhance productivity.

However, ending world hunger is about more than just increasing food production; it requires us to tackle systemic issues such as poverty, inequality, and climate resilience in a holistic manner.”

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

05 Nov, 10:45


የ'World Without Hunger' ጉባኤ ተሳታፊዎችን እንኳን ወደ አፍሪካ የዲፕሎማሲ መዲና በሰለም መጣችሁ እላለሁ።

አለምአቀፍ መሪዎችን፣ ባለሞያዎችን እና የጉዳዩ ተቆርቋሪዎችን በአንድ ላይ በማምጣት እንዲወያዩ በማድረግ የጋራ ጥረቶቻችን ረሃብን በማጥፋት ለሁሉም የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ርብርብ ፍሬ እንዲያፈራ እንደሚያስችሉ ተስፋ አለኝ።

በኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ዓመታት በግብርና ሽግግር እና ምርታማነት ላይ በማተኮር የሠራነው ሥራ የታረሰ መሬታችን እጥፍ በማድረስ ከፍ ያለ እሴት ባላቸው የኢንደስትሪ አዝርዕት ምርት ላይ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች አስገኝቷል።

በሚቀጥሉት ቀናት የጉባኤው ውይይቶች የጋራ ግቦቻችንን ስኬት የሚያፋጥኑ ታላላቅ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ እተማመናለሁ።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

01 Nov, 09:24


ዛሬ ጠዋት መልዕክት ይዘው የመጡትን የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ልዩ መልዕክተኛ ዶክተር ማርቲን ኤልያ ሌሙሮን ተቀብያለሁ። በሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይም ውይይት አድርገናል።

Har'a ganama ergamaa addaa Pirezdaantii Sudaan Kibbaa Salvaa Kiir Dr. Martiin Eliyaa Lemuuroo simadhee haasofsiiseera. Mariin keenya dhimmoota garlameefi naannawaarratti kan xiyyeeffatedha.

This morning, I received Dr. Martin Elia Lemuro, Special Envoy of President Salva Kiir of South Sudan, who came to deliver a message. Our discussions focused on bilateral and regional issues.

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 09:13


እኛ ከማንም በላይ ሰላም እንፈልጋለን ፤ ጦርነትን በወሬ ሳይሆን በተግባር ስለምናውቀው እንዲሁም ብዙዎችን ስለቀጠፈብን አንፈልገውም ፡፡

በዚህ ሀገር ላይ የሚጨበጥ ለውጥ ለማምጣት ሰላም እጅጉን ወሳኝ በመሆኑ ሰላም የምንፈልገውና የምንመኘው ጉዳይ ነው፡፡

ከኃይል አማራጭ ይልቅ የሰላም አማራጭ ውጤቱ ከፍተኛና ተመራጭ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 09:07


"የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ በሚቀጥሉት ዓመታት 50 እና 100 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ አለብን "
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

✍️ባለፉት ሶስት ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች የወጪ ንግድ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል ፡፡

✍️በሩብ ዓመቱ ያገኘነውን የወጪ ንግድ ገቢ ማስቀጠል ከቻልን በዓመት ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ልናስገኝ እንችላለን፡፡

✍️የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ገቢ  በሚቀጥሉት ዓመታት 50 እና 100 ቢሊዮን ዶላር ማድረስ አለብን ፡፡

✍️ባለፉት ሶስት ወራት ስድስት ነጥብ አራት በመቶ ብልጫ ያለው የውጭ ኢንቨስትመንት መሳብ ተችሏል።

✍️ኢንቨስትመንቱን በዚህ መጠን መሳብ የተቻለው የሀገሪቱን የፋይናንሻል ስርዓት  በመሻሻሉ ነው

✍️ኢትዮጵያ ውስጥ መሬት የህዝብና የመንግስት መሆኑ፤ ርካሽና ንጹህ የተለያዩ ዓይነት ኃይል ያለ መሆኑ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት  ለመሳብ ሰፊ እድል አለ፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በትይዩ ገበያው መካከል ያለው ክፍተት ሰፊ እንዳይሆን ተሰርቷል፡፡

✍️በበጀት ዓመቱ ሰባት መቶ ሺህ ሰዎች የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው

✍️በበጀት ዓመቱ ባለፉት ሦስት ወራት ከ100 ሺህ ዜጎች በላይ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አግኝተዋል

✍️ወደ ውጭ ሀገራት ለስራ ስምሪት የሚላኩ ዘጎች ከኤስያ ሀገራት በተጨማሪ ወደ አውሮፓም መላክ ተጀምሯል ብለዋል፡፡

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 08:53


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ‼️

✍️ እንደሀገር የደሞዝ ማሻሻያና ጭማሬ ለማድረግ ወስነናል፣ ጥቅምት ወር ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል፣

✍️ ባለፉት ጥቂት ዓመታት 249 ሺህ ቤቶችን መሰራት ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች አስተላልፈናል፣

✍️ ባላፉት ስድስት ዓመታት መንግስት ምንም አይነት የንግድ ብድር አልወሰደም፣

✍️ የኢትዮጵያ የብድር ጫና ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት ከነበረበት ከ30 በመቶ ወደ 13 ነጥብ 7 በመቶ ዝቅ ብሏል፣

✍️ በሚቀጥሉት ዓመታትም ይህን አሃዝ ከ10 በመቶ በታች ዝቅ ለማድረግ ይሰራል፣

✍️ ባለፉት ስድስት ዓመታት አየር መንገድና ቴሌን ሳይጨምር 13 ቢሊዮን ዶላር እዳ ተከፍሏል፣

✍️በተለይ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በወርቅ ምርት ወጪ ንግድ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል፡፡

✍️ ባለፉት ሶስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ 500 ሚሊዮን ዶላር ገቢ ተገኝቷል፣

✍️በቡና ምርትም በበጀት ዓመቱ 2 በሊሊዮን ዶላር ገቢ ይጠበቃል፡፡

✍️ የኢኮኖሚ ስርዓታችን እጅግ የተዘጋ ነበር፣

✍️ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን መሰረት የሚጥል ነው፣

✍️ ብልጽግና ድሃን ይወዳል፣ ነገር ግን ድህነትን ይጠላል፤ስለምንጠላውም አጥብቀን  ድህነትን እንበቀለዋለን፣

✍️ ከወርቅ፣ ከቡና፣ ከመብራት፣ ትልቅ ለውጥና እምርታ እያመጣን ነው፣

✍️ ኢትዮጵያ ታክስ ከማይሰበስቡ ሀገራት ተርታ ናት፣

✍️ በዚህም በቀጣይ አንድ ነጥብ 5 ትሪሊዮን ገቢ እንደሀገር ያስፈልጋል፣

✍️ ህግን ያልተከለ ዘረፋ ለመከላከል ተጨማሪ ስራ ይሰራል፣ እንሰራለን

✍️18 የነበሩት የባንኮች ቁጥር አሁን 33 ደርሰዋል፣

✍️ ባላፉት ሶስት ወራት በተለያየ መንገድ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ 3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ሆናል፣

✍️ ባለፈው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ሶስት ወራት ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ሃብት 400 ሚሊዮን ዶላር ነበር፣

✍️ በማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው 27 ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ይጠበቃል፣

✍️ ሀገር እየተቀየር ሲሄድ የማይቀየሩ ሰዎች አሉ፣

✍️ ባለፉት 6 ዓመታት ኮመርሺያል ብድር አልወሰድንም፤ ዕዳን እየቀነስን ወደ ምንዳ እየተጓዝን ነው፣

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 07:55


ባለፉት ሶስት ወራት የብሔራዊ ባንክ ተከቀማጭ ገንዘብ 161 በመቶ ማደጉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።

ጠቅላየ ሚኒስትሩ በማብራራሪያቸው በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ሶስት ወራት የብሔራዊ ባንክ ተከቀማጭ ገንዘብ 161 በመቶ አድጓል።

ኢትዮጵያ እንደሀገር ለክፉ ቀን ብላ የምታስቀምጠው ተቀማጭ ገንዘብ አድጓል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የግል ባንኮች ተቀማጭም 29 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን አያይዘው ጠቅሰዋል።

ባለፈው ዓመት ዓመቱን ሙሉ 20 ዓለም አቀፍ ኮንፈረሶችን አላካሄድንም፤ ዘንድሮ በሶስት ወር ብቻ 20 የሚደርሱ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን አካሂደናል ብለዋል፡፡

በቀጣይም በርካታ ዓለም ዓቀፍ ኮንፈረንሶች በኢትዮጵያ ይካሔዳሉ ሲሉ አመላክተዋል፡፡

የኮሪደር ልማት እና በኢትዮጵያ የተፈጠረው አውድ ዓለም አቀፍ ጎብኚዎችን ኮንፈረንሶችን ለመሳብ እድል መፍጠሩን አንስተዋል፡፡

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

31 Oct, 07:51


ከ130 ሚሊዮን የሚደርሱ መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት ጥናት ተጠናቋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተርር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

በማብራሪያቸው አየር መነገዱ አሁን ካለን አውሮፕላን ማረፊያ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ሁለቱ አየር መንገዶች በባቡር ይገናኛሉ ብለዋል፡፡

በአፍሪካ ትልቁ አየር መንገድ ብቻ ሳይሆን ትለቁ አየር ማረፊያም ይሆናልም ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አዲስ የሚገነባውን አየር ማረፊያ ማጠናቀቅ ከቻልን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነበረው ክብርና ዝና ይጨምራል ።

Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹

26 Oct, 07:55


ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ብሎም የማሌዢያ ሕዝብ እና መንግሥት በቆይታችን ለሰጣችሁን ደማቅ አቀባበል እና ፍቅር እናመሰግናለን።

ትብብራችንን ትኩረታቸውን በግብርና፣ ማዕድን፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ታዳሽ ኃይል ላይ ባደረጉ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ብሎም ሰፊ አድማስ ባላቸው ሌሎች ቁልፍ ሥራዎች ላይ ለማጠናከር ተስማምተናል።

የማሌዢያ የንግድ ማኅበረሰብ በፍጥነት በመስፋፋት ላይ ባለው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ያለውን የኢንቬስትመንት እድል እንዲጠቀሙ አበረታታለሁ።

Thank you Prime Minister Anwar Ibrahim and the government and people of Malaysia for the warmth and love you have shown us during our stay.

We have agreed to deepen our collaboration across several key areas, including in trade and investment, with particular focus on agriculture, mining, manufacturing, and renewable energy.

I encourage Malaysian businesses to seize vast investments opportunities in Ethiopia’s rapidly expanding economy.