የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ @aaculturearttourism1 Channel on Telegram

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

@aaculturearttourism1


Addis Ababa Culture, Arts & Tourism bureau

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ (Amharic)

ሐምሌ 12, 2021 - በዓዝሪባ ቶሮ እና እናደርግላ ከ የአበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ አንዴንጊ ትምህርት ዱቄት በመሆን መነሻ ሊንክ አስተዳደር መኖሪያ ተርካሾን ሠርጉንዎች ላይ ተደረግላ ነበር። አብዛኞቹ ስለ ባቡᮠና ወኒቢና ሌባና ስቃይ ፕላቶንን ለመመዝገብ ከባህሉ ስርዓት በዋና አገኘሁባት። እናውጣ፦ አብዛኞቹ ስለ ባቡᮠና ወኒቢና ሌባና ስቃይ ፕላቶንን ተመልከቱ።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

20 Nov, 09:32


"አዲስ አበባ ፓሪስን መስላለች" - ዳያስፖራው የቱሪዝም ባለሞያ
****

ላለፉት 55 ዓመታት በካናዳ ነዋሪ የሆኑት የቱሪዝም ባለሞያ ልዑል እስጢፋኖስ መንገሻ አዲስ አበባ ፓሪስን መስላለች ሲሉ ተናገሩ፡፡

የቱሪዝም ባለሞያው ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ባለፉት 6 ወራት ብቻ የሀገሪቱ ግስጋሴ የሚደነቅ መሆኑን አንስተው፤ አዲስ አበባን በፈጣን ለውጥ ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ቱሪዝም እድገት ለዳያስፖራው ትልቅ ኃላፊነት ነው ያሉት ልዑል እስጢፋኖስ፤ ሀገራችን ለማየት በምንመጣበት ጊዜ ብዙ የውጭ ሀገራት ነዋሪዎችን ይዘን መምጣት ይጠበቅብናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዚህም በቀጣይ ጥር ወር ላይ ብዙ እንግዶችን ወደ ኢትዮጵያ ይዘው እንደሚመጡ እና እንግዶቹ ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆኑ ኢንቨስተሮችም መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

"እኛ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች ነን" ያሉት ዳያስፖራው፤ ለሀገራችን ማንም እስኪሾመን አንጠብቅም ብለዋል፡፡

"ሀገራችንን እኛ ሳናውቃት ለሌሎች ማሳወቅ አንችልም፤ በመሆኑም በውጭ ሀገራት ያላችሁ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ሀገራችሁን እወቁ" ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ አባተ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ የቱሪስት መስህብ ቢኖርም የለሙ ቦታዎች አለመኖራቸው ለቱሪዝሙ እድገት እክል መፍጠራቸውንና የሚፈለገውን ገቢ ለማምጣት አመቺ እንዳልነበሩ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ እየተሰሩ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሁሉን ያሟሉ በመሆናቸው ለጎብኚዎችም ሆነ ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል ብለዋል፡፡

የቱሪዝም መዳረሻዎቹ የስራ እድል በመፍጠር ጭምር ኢኮኖሚው እንዲቀሳቀስ ማስቻላቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

የቱሪዝም ዘርፍ እድገቱ ኢኮኖሚው እንዲነቃቃ ማገዙን የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ፤ የገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች የቱሪዝም ዘርፉ ይበልጥ እንዲነቃቃ ማስቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ 

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

19 Nov, 16:47


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ ደንብ ቁጥር 178/2016 መሰረት ክልከላ እና አስተዳደራዊ ቅጣት አወሳሰድ እንደሚከተለው ተጠቅሷል፡፡

ክልከላ!!

በዚህ መመሪያ ክፍል ሦስት ስለደንብ ልብስ አለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ከተደነገገው ውጭ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በማንኛውም የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋም፡-
1.  ከደንብ ልብሱ በላይ ሌላ ተደራቢ፣ ከተፈቀደው ውጭ ቀላቅሎ መልበስ፣ ከሸሚዝ ስር ረዥም የሚታይ ልብስ መልበስ፤
2.  የደንብ ልብሱን ሳያሟሉ መልበስ፤
3.  የሸሚዙን ቁልፍ ክፍት ማድረግ፣ ሸሚዙን ከሱሪ ወይም ከቀሚስ ወደ ውጪ ማድረግ፤
4.  የእጅ ጣት ጥፍር ማሳደግ፣ ቀለም መቀባት ወይም ጥፍር ልጥፍና ሙሌት መሰራት፤
5.  ማንኛውም ዓይነት በህክምና ያልታዘዘ መነጽር ማድረግ፤
6.  የደንብ ልብሱን ንጽህና ሳይጠብቁ ወይም ሳያስተኩሱ መልበስ፤
7.  ማንኛውም ዓይነት የከንፈር ቀለም ያለዉ ቻፒስቲክ ወይም ሊፒስቲክ መቀባት፤
8.  ባለሙያዎቹ የለበሱት ቀሚስ ከሆነ ቅዱ ከኃላ ያልሆነ የለበሰ፡፡


አስተዳደራዊ ቅጣት አወሳሰድ

ቢሮዉ ወይም ጽሕፈት ቤቱ የተሰጠዉን ተግባር እና ኃላፊነት ወይም በደንቡ ላይ የተቀመጠዉን የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ግዴታ መሰረት በቁጥጥር ባለሙያ የተደረሰባቸዉ የህግ ጥሰት ሲኖር፡-
1.  የቁጥጥር ባለሙያው ባከናወነው የቁጥጥር ተግባር  ያገኘውን ውጤት በዚህ መመሪያ አባሪ ላይ በተያያዘ ቅፅ ና ቼክ ሊስት መሰረት አስፈላጊዉን መረጃ በመሙላትና ተጨማሪ መረጃ በማያያዝ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ከውሳኔ ሃሳብ ጋር ለክትትልና ቁጥጥር ባለሙያ የቅርብ ኃላፊ  24 ሰዓት  ውስጥ ያቀርባል፤

2.  በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀጽ (1) በተደነገገዉ መሰረት በቀረበዉ የክትትል እና ቁጥጥር ዉጤት መሰረት በደንቡ አንቀጽ 18 መሰረት እንደ ጉዳዩ አፈፃፀም ወይም አግባብ ወይም የጥፋት ድግግሞሽን መሰረት በማድረግ ቢሮዉ ወይም ጽሕፈት ቤቱ አማካኝነት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወስዳል፣ ዉሳኔዉን ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

19 Nov, 16:25


"አዲስ እንደ አዲስ ትገለፅ በዳንስ"


ህዳር 10/2017ዓ.ም(ባኪቱ ቢሮ)

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የኪነ ጥበብ ዘርፍ "አዲስ እንደ አዲስ ትገለፅ በዳንስ" በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም  ዘመናዊ የዳንስ ውድድር ማጣሪያ በዛሬው ዕለት በሀገር ፍቅር አካሄደ።

በክፍለ ከተማ የሚገኙ ዘመናዊ የዳንስ አማተር ተወዳዳሪዎች በውድድሩ የተሳተፉ ሲሆን በመድረኩም አስተማሪና አዝናኝ የሆኑ ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።

ውድድሩም ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ሲሆን የውድድሩ ውጤትም አሀዱ የዳንስ ቡድን 1ኛ ፣ ጥያቄ የዳንስ ቡድን 2ኛ፣ ጊዎን የዳንስ ቡድን 3ኛ፣ አንድ ቅኔ የዳንስ ቡድን 4ኛ በመውጣት ውድድሩን ያጠናቀቁ ሲሆን ከአንድ እስከ አራተኛ የወጡት ተወዳዳሪዎች ወደ ቀጣይ ዙር የፍጻሜ ዳንስ ውድድር ተዘዋውረዋል።

የማጣሪያውን ዙር ላለፉ አራት የዘመናዊ የዳንስ ተወዳዳሪዎች  በቅርብ ቀን የፍጻሜ ውድድር እንደሚካሄድም ተገልጧል።

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

18 Nov, 17:24


የጥሪ ማስታወቂያ ለሁሉም የሜይንስትሪም ሚዲያ ተቋማት፣ ቲክቶከሮችና ዩትዩበሮች በሙሉ

ጉዳዩ:- በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ የሚሰሩ ሙያተኞች የደንብ ልብስ አለባበስ ደንብ ላይ መወያየትን ይመለከታል!

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ በአዋጅ የተሰጠውን ስልጣንና ኃላፊነት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማው ማህበረሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ ይገኛል።

በዚህም መሠረት ቢሮው ለተገልጋዮች ከሚሰጣቸው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ውስጥ ቱሪስቶችና የከተማው ነዋሪዎች የሚገለገሉባቸው ተቋማትን ድጋፍ፣ ክትትል እና ቁጥጥር በቋሚነት ማድረግ አንዱና ዋነኛው ነው፡፡

ስለሆነም በእነዚህ ተቋማት ማለትም በባለ ኮከብ ሆቴሎች፣ በባለኮከብ ሬስቶራንቶች፣ በተመራጭ፣ በከፍተኛ እና በአነስተኛ ደረጃ በሚገኙ ሆቴሎች በሬስቶራንቶች፣ በባሮች፣ በካፌዎች፣ በፔንሲዮኖች እና በመሳሰሉት ለእንግዶች አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት ባለሙያዎች የሚለብሱት አልባሳትና የሚጠቀሙበት ጌጣጌጥ የአገርን ባህልና እሴት ያገናዘበ እንዲሆን ቢሮው ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጀውን የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የደንብ ልብስ አለባበስና የጌጣጌጥ አጠቃቀም ደንብ ቁጥር178/2016 ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱና ይህንንም ለማከናወን ቅድመ ሁኔታዎችን ያጠናቀቅን በመሆኑ በ11/03/2017ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ቦሌ መድሃኒአለም ጎን አቢሲኒያ ህንጻ ላይ በሚገኘው ጎልደን ኬተሪንግ የተቋሙ፣ የማህበሩ እንዲሁም ሁሉም የሚዲያ ተቋም ኃላፊ በቦታው በመገኘት በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ውይይት እንድናደርግ እንጠይቃለን።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

18 Nov, 16:48


የሁሉም ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሞያዎች የደንብ ልብሶቻቸው የሰውነት ቅርጽን እንዲያሳዩ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ከተገኙ ከፍተኛ ቅጣት እንደሚያስከትል ተገለጸ፣

******
ህዳር 9/2017 ዓ.ም (ባኪቱ ቢሮ)

ቢሮው በአዲስ አበባ በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰሩ ባለሞያዎችን የደንብ ልብስ አለባበስና አፈጻጸም ረቂቅ ደንብ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ከዘርፉ ባላድርሻ አካላት ጋር ምክክር እያደረገ ነው፡፡

ከዚህ በፊት በባለሞያዎች የደንብ ልብስ አለባበስና የመዋቢያ ጌጣጌቶች አጠቃቀም ላይ በከተማዋ በቱሪዝም ዘርፍ ላይ ተሰማርተው አገልግሎት ለሚሰጡ አካላት ኢትዮጵያዊ አለባበስ ሥርዓትና መስተንግዶ እንዲኖር አሳዉቆ እንደነበር የቢሮው ኃላፊዋ ዶ/ር ኂሩት ካሳው ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባ ከአፍሪቃ ወደ ዓለም መዲናነት መምጣቷን ያነሱት ቢሮ ኋላፊዋ ÷በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የዘርፉን ኢኮኖሚ ማሳደግና የሀገር ገጽታን መገንባት እንደሚባ አሳስበዋል፡፡

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የባለሞያዎችን የደንብ ልብስ አለባበስና መዋቢያ በሚመለከት በአዋጅ ቁጥር 178/2016 ተፈጻሚ የሚሆን የደንብ ረቂቅ በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ በኩል ይፋ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

"ደንቡ የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሀገሪቱን ባህልና ዕሴት በማስጠበቅ፤የባህል ወረራን የሚከላከልና የዘርፉ ባለሞያዎች ከሚደርስባቸው አካላዊና ስነ ልቦናዊ ጫናን ለማስቀረት የሚያግዝ ነው" ብለዋል፡፡

የሁሉም ሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሞያዎች የደንብ ልብሶቻቸው የሰውነት ቅርጽን እንዲያሳዩ ሆነው አገልግሎት እየሰጡ ከተገኙ በመመሪያው መሰረት ቢሮው በቀጥታ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ተገልጿል፡፡

በተለይም ደግሞ ከአንገት በታችና ከጉልበት በላይ ያለውን የሰውነት ክፍል በሚያሳይ መልኩ ለብሶ አገልግሎት መስጠት እስከ ሃምሳ ሺህ ብር እንደሚያስቀጣ ደንቡ ያመላክታል፡፡

ቢሮው ተቋማቱ በደንቡ መሰረት አገልግሎት እየሰጡ ስለመሆናቸው ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ  በደንቡ አፈጻጸም ላይ ጉድለት ላልተገኘባቸው ተቋማት ተገቢውን እውቅና የሚሰጥ ሲሆን ተግባራዊ የማያደርጉ ተቋማት ላይ ደግሞ የስራ ፈቃዳቸውን እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ ይወሰዳል ተብሏል፡፡

ከተቋማቱ በአፈጻጸም ትግበራ ላይ ምን ይጠበቅባቸዋልበሚሉ ጉዳዮች ላይ ገለጻ የሰጡት የቢሮው የቱሪዝም ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍታይ ገብረእግዚአብሔር÷በባለቤትነት ረቂቅ ደንቡን የማስፈጸም፣በክትትል የተደረሰባቸውን ደግሞ የማስጠንቀቂያና የክስ ጥሪ ወረቀቶችን ተቀብሎ እርማት መውሰድ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡


ደንቡ የፈጻጸም ግልጽነት እንዲኖረው የራሱ መመሪያ የሚያስፈልገው በመሆኑ የወጣው የመመሪያ ረቂቅ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ በኩል ለሚመለከተው አካል ቀርቦ እንደሚጸድቅ ም/ቢሮ ኋላፊው አንስተዋል፡፡

በመቀጠልም ደንቡን ለሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ለሚዲያ አካላት ፣በየደረጃው ለሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሞያዎች የማስገንዘብ ስራ በተከታታይነት ለውይይት የሚቀርብ ይሆናል።

የመድረኩ ታዳሚዎችም የተዘጋጀው ረቂቅ ደንብ የሀገር ባህልና ወግን በማስጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል፡፡