💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀 @https_asselfya Channel on Telegram

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

@https_asselfya


💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው።

👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው።

💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀 (Arabic)

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀nnهذه القناة هي منبر إلكتروني رائع يهتم بالمرأة الصالحة ويعتبرها كنزًا من كنوز الدنيا. تهدف القناة إلى توجيه النساء نحو كيفية تحقيق الصلاح والتفوق في حياتهن. بمحتوى ملهم ومفيد، تقدم القناة نصائح وإرشادات تساعد المرأة على تحقيق التوازن بين العبادة والحياة اليومية

من خلال المقالات والفيديوهات التي تنشرها القناة، يمكن للمشتركين الاستفادة من تجارب وآراء نساء ناجحات في مجالات مختلفة. سواء كنت امرأة تسعى لتطوير نفسها أو ترغب في الاستماع إلى قصص إلهام، فإن هذه القناة هي المكان المثالي لك

إذا كنت تبحث عن تحفيز ودفء لروحك، فعليك الانضمام إلى هذه القناة الرائعة. اكتشفي كيف يمكن للمرأة الصالحة أن تكون كنزًا يضيء حياتها وحياة الآخرين من حولها. انضمي الآن وكن جزءًا من هذه المجتمع الملهم!💎🎀

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Jan, 05:25


😋
📣የዳዕዋህ ፕሮግራም

😓የፕሮግራሙ አቅራቢ፦
1️⃣ኡስታዝ ዐብዱረዛቅ አልባጂ
ርዕስ፦ስለ ተቅዋህ
2️⃣ኡስታዝ አቡ ሒበቲላህ
ርዕስ፦ስለ ሞት
3️⃣ኡስታዝ ኑረዲን አል ዐረቢይ
ርዕስ፦ስለ ሶብር


✈️መድረክ መሪ፦ወንድም አቡ ሑዘይፋህ

0️⃣0️⃣0️⃣የሚተላለፍበት ቻናል፦
📥📥📥📥📥📥
t.me/tdarna_islam

😮ዛሬ እሮብ ከምሽቱ 3:30😓

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Jan, 04:26


ጨለማው ብቻ ሳይሆን ፣ወንጀላችን'ንም ሸፍኖልን አድረናል። የቱን፣ ስንቱን ፀጋዉን እናመስግን።

~የጠዋት ዚክር አይርሱ

اللَّهمَّ إنا نسألُكَ خيرَ هذا اليومِ فتحه ونصرَهُ ونورَهُ وبرَكتَهُ وَهداهُ، ونعوذ بِكَ من شرِّ ما فيهِ وشرِّ ما بعدَهُ.

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Jan, 18:18


ነፍሤ  ሆይ......

ለምን  ትቸኩያለሽ  ሒወትኮ የሚገባሽን ነገር በራሧ  ጊዜ  ታሥተምርሻለች

ለመማር  ብቻ  ራሥሽን  አዘጋጂ  ሁሌም የሆነ  የምትሰጥሽ  ትምህርት  ይኖራል  ግን  አትቸኩይ 'በአንዴ  ተምሬ  ሁሉን  ልወቅ  ያለ'  ያወቀዉንም  ያጣዋልና  ሰከን  በይ 

አትቸኩይ ነፍሴ  ትንሽ ረጋ በይ
ሁሉንም  በአንዴ ልወቀዉ አትበይ

ለእያንዳዱ ነገር ቀነ ቀጠሮ አለዉ
ሁሉም የሚያምርበት በጊዜዉ ሢሆን ነዉ

በየተራ  ሢሆን  አያለፋም ብዙም
ስለዚህ  ታገሺ  ግዴለም  አይከፋም
ከሶብር ቡኋላ  የሚመጣ  ዉጤት
ለልብ ደስታ አለዉ ለነፍስያም  ሐሤት


እናማ  ሰከን... ረጋ...ቀስ...በይ..
࿐✎

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Jan, 18:13


https://t.me/fewaidabdurazaq?livestream

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Jan, 12:37


እሳት እንደ ጎርፍ እየተተራመሰ ሲሄድ!!
~~
አላህን የሚፈራ ልብ፤የሚያለቅ አይን ሲጠፋ፡አላህ ታላላቅ አያዎቹን ያሳየን ያዘ።ጌታየ ሆይ በእዘነትህ እንጂ፡በደግነታችን አይደለምና ያለነው አንተ ለማንም አትተወን።

*ኢላሂ፡ሲቆጡት የሚሰማ፤ሲያሳዩት የሚደነግጥ ልብ ስጠኝ።ወደ አንተ የተመለስኩም አድርገህ ቢሆን አንጂ አትውሰደኝ።

አቡ ኡበይዳ
t.me/AbuOubeida

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Jan, 11:09


የዘምዘም ዉሀ ሲጠጣ የሚባል ዱአ!!

ዱዓ አርጋችሁ ጠጡ የዘምዘም ዉሀ ለተጠጣለት ነገር ይዉላል።
~

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Jan, 19:56


_~መልካም ጓደኛ የስኬት ቁልፍ እንደሚሆነው ሁሉ ~መጥፎ እና ሰነፍ ጓደኛ ደግሞ የውድቀት ቁልፍ_ _ነው። በቃ!!_

🌸መልካም ለሊት🌸

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Jan, 18:56


ምን ቁንጅናህ ቢያምር ብቶንም ሸበላ
አቂዳ ከሌለህ ከሆንክ ሞላላ
እኔም ቆሜ ልቅር አንተም አግባ ሌላ!!

እጠብቀዋለዉ ያ ሰለፍይ ጀግና
!

ሳህ ትክክል👌አንዲት እህታችን የገጠመቻት ግጥም
!

:

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Jan, 18:45


🔖ስለ ነፍስህ|ስለ ራስህ ማወቅ ከፈለግክ፡
      ~  ~
قال ابن الجوزي رحمه الله
إنْ أردت أنْ تنظر إلى نفسك فخُذ كفًا من تُراب فإنك منه خلقت وفيه تعود ومنه تخرج
📚 التذكرة (١٦٩/١)

✔️እፍኝ አፈርን ዘግነህ ተመልከታት፡

👉ከሷው ተፈጥረሀል፡
👉ወደ'ሷም ትመለሳለል፡
👉ከሷም ትወጣለህ!


ስለዚህ እራስህን አታካብድ፡ ቀለል አድርግ፡ ጋሽ አፈር!

        t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Jan, 11:54


እምነትህን በሀያሉ አምላክ ባደረክ ቁጥር ይበልጥ ጠንካራና የመልካም ስብዕና ባለቤት ትሆናለህ::
አሏህ ሆይ" ጠንካራ አማኝና
የውብ ሥነ-ምግባር ባለ ቤት አድርገን ያከሪም

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Jan, 04:22


🔖 ቀልብ !!

🎙ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ

||
t.me/Muhammedsirage

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Jan, 20:43


🔖 «ህይወቴ»
ስሄድም ስቀመጥ ስገባም ከቤቴ፣ ሁሌም የማልመው ከልቤ ካንጀቴ፣ ተውሂድ የሱና ብርሁ ምኞቴ

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Jan, 13:19


~አሏህን በማስታወስ ልቦች ይረካሉ።
➻ነፍስ ትደሳለች ፣
➻ቁስሎች ይድናሉ ፣ ደስታወች ያሽንፋሉ

~እያንዳንዱ  የሒወት  ትግል  ቀላል ይሆናል .......
~‏سبحان الله،
~الحمد لله،
~لا إله إلا الله،
~ الله أكبر
.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Jan, 07:46


~ ታላቂ ሙፈሲር ኢብኑ #ከሲር ረሂመሁሏህ እንድህ አሉ።

« ድግምተኛ በአንድ ወር ውስጥእማያበላሸውን በአንድ ስአት ውስጥ ነገር አዋሳጅ ሰው  ያበላሻል,።
~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Jan, 20:00


☀️አንድ ሙስሊም ወንድ ልማድ ሊያደርጋቸው ከሚገቡ ባህሪዎች መካከል:–

ሴቶች ከፊቱ እየተራመዱ ከሆነ ቀደም ቀደም ብሎ እነሱን ማለፍ፤ ይህ ኢስላማዊ አደብ ነው።

~ምን ተፈጠረ እስኪባል ተሯሯጡ አሉ ደግሞ¡

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Jan, 18:22


☀️ሴት ልጅ ከምትናገረው ይልቅ የምትተገብረው የሷ እውነተኛ ማንነቷ ነው።

👌
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Jan, 10:46


🖋የመሬት መንቀጥቀጥ የትንሳዔ መቅረብ ምልክት ነው። ቢሆንም ነገሩ ሲከሰት ወደ አላህ በተውበት (በንስሃ) መመለስ እንዳለብን ዑለማዎች ይመክራሉ። በተረፈ ለጥንቃቄ ይረዳን ዘንድ ከባለሙያዎች የሚተላለፉ መልዕክቶችን ከማድመጥ ባለፈ፤ ያገኙትን ሁሉ ከሚያወሩ የሶሻል ሚዲያ ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች ልንረበሽ አይገባም!

ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

“ሰዓቲቱ ‘ትንሳዔ’ አትቆምም እውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 1036

🙁🙁🙁🙁🙁🙁☹️🥳

በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦

✈️፦ https://bit.ly/4ayf0xJ

📞፦ https://bit.ly/486xnrS

👤፦ https://bit.ly/41zEZkk

📸፦ https://bit.ly/4arMbTx

💬፦ https://bit.ly/41tIUPv

🎥፦ https://bit.ly/3UTTSwh

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Jan, 04:50


ቤተሠብ ጋር ደዉየ የዛሬዉ የተለየ ነዉ
ከተኛንበት ቀስቅሶናል አሉ።ሀቂቃ ያስፈራል ኢላሂ በራህመትህ..

.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Jan, 04:46


~ዛሬ ሌሊት ከስከዛሬው በተለየ መልኩ ነበር መሬት የተንቀጠቀጠው። እኔ በህልሜ ነው ብየ ነበር።: ከእንቅልፌ ስነቃ ለካስ ጎረቤት ሁሉ ስለ እሱ ነው የሚያወራው።

አላህ ይድረስልን! በዚህ ሳምንት በተከታያይ በሚባል መልኩ ነው መንቀጥቀጥ የያዘችው መሬት።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Jan, 21:57


﴿فَناداها مِن تَحتِها أَلّا تَحزَني..﴾

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Jan, 21:02


_ቁርአን ሀፍዞ ነበር ግ  ሙራጀዐ ማድረጉ
   ትቶት የሀፈዘው ጠፋበት
ይህ ሰው አላሀ ዘንደ ምንም አይነት ምክንያት የለውም። ..

እንዲህ ያለ ክስተት በጣም ያሳዝናል !

እስቲ ወንድሜ ስማኝ አዎ አንተን ነው 10 ጁዝም 15 አረ ሙሉውንም ሀፍዘህ ነበር ይሆናል ታዲያ ከዚህ ሁሉ ድካም ከቁርአን ጋር ያለውን ጣፋጭ ቆይታ  አይተህ ወደ ሇላ እንድትል ያደረገህ ነገር ምንድ ነው

የቁርአን ክብር ደረጃ አንሶብህ?
ወይስ ነፍስያህ ተራ አድርገሀት ነው
ይህን ኸይር የነፈግካት?
ነው ወይስ ከቁርአን የተሻለ አጫዋችና ጓደኛ አግኝተህ ዞር አልክ?

وعصيتم من بعد مآ أراكم ما تحبون

አላህ የምትወዱትን ነገር ካሳያቹ ቡሀላ አመፃቹት

ወንድሜ አሁንም ከቁርአን ጋር ያለህ ቀረቤታ በጣም የራቀ ሆኖ አልታየህም ወደ በፊቱ
ቃልህ መመለሻ ጊዜህ አልደረሰምን?

ከቁርአን ጋር ለረጀም ሰአት ቁጭ ብለህ ምታሳልፍበት ጉሮሮህ በውሀ ጥማት እስኪደርቅ ድረስ ቁርአን ምታነብበት..

ከዚያም ልብህን በቁርአን ብርሀን ሞልተሀት ሙሉ ቁርአንን ቆመህ ተቀምተህ ተኝተህ እንደፋቲሀ በማንበብ  ደስተኛ ሆነህ  ምታሳልፍበት ጊዜ አልደረሰምን?

በል ተነስ ወንድሜ ወስንና  በአላህ ታገዝ ወደ ቁርአንህም ዙር ሂፍዙን ካልጨረስከው ጨርሰው ከጨረስከውም ሙራጃህን አምጣው ሂፍዝህንም ጠብቀው..


ውስጥህ ላይ ቁርአን ኑር እንዲሆንልህና ወደጀነት ምትጓዝበት መንገድህ ላይ ምታበራው ብርሀንህ  አድርገሀው ልትጠቀምና በፈለከው ሰአት ልትቀራው  አትፈልግም እንዴ?


አቡ ዚክራ

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Jan, 20:59


«ረመዷን ቀርቧል ግን አስታዋሹ ምነኛ ያነሰ ነው
አላህ ልቦና ይስጠን!!
اللهم بارك لنا في رجب و شعبان
و بلغنا رمضان

«ኢላሂ የረጀብና የሸዕባንን ወር ባርክልን ለረመዷንም አድርሰን!!

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Jan, 06:14


🎁ታላቅ የሙሓደራ   ፕሮግራም📱


🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️🅰️
🔤🔤🔠🔤🔤🔤🔤🅰️🔤  ግሩፕ  ላይ  የዳዕዋ  ፕሮግራም  አዘጋጅተን  እየጠበቅናችሁ  እንገኛለን።

ተጋባዥ 🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠🔠

⭐️ኡስታዝ ኸድር አህመድ
⭐️ኡስታዝ አብዱ ረዛቅ አል-ባጂ
⭐️ኡስታዝ ዶ.ሰዒድ ሙሳ
⭐️ኡስታዝ አቡ ሱፊያን
⭐️ኡስታዝ አቡ ሙአዝ
⭐️ኡስታዝ አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
⭐️ሼህ አውል አል_ከሚሴ(አቡ አማር)

🔢መድረኩን የሚመሩልን ወንድሞች
አቡ ኹዘይፋ ሰኢድ
አቡ ሂበቲላህ ሁሴን
አቡ ፈዉዛን አብዱ ሽኩር

በእለቱም ታላቅ የምስራች ይኖረናል ሁላችሁም በጉጉት እንድትጠብቁን እናሳስባለን

❄️የፊታችን ጁማዓ✈️

ሰአት ⭐️ ከምሽቱ 3⃣:0⃣0⃣ጀምሮ

  ሙሓደራው  የሚካሄድበት  ግሩፕ
መርከዝ አቡ ፈውዛን🔤✈️🔤
    👇👇👇

t.me/merkez_abu_fewzan
t.me/merkez_abu_fewzan

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Jan, 05:11


ወዳጄቼ ተወልጀ ባደግኩባት ከተማ የተከሰተ አሳዛኝ ክስተት ነው
እናት ቤቴ በሀዘን ተውጧል የቀረኝ አንዱን ልጄን አድኑልኝ ትላለች
የእርዳታ ጥሪ ልጆቼን ተነጠኩ አንዱን ገደሉብኝ አንዱን አድኑልኝ ትላለች እናታችን

ወንድማችን ኡመር ሀሰን ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም ሉማሜ ከተማ የአባቱ የቀብር ስነ ስራአት ላይ ለመገኘት በመሄድ ላይ እያለ መንገድ ላይ ባጋጠማቸው እገታ ታላቅ ወንድሙም ወዲያዉኑ የተገደለ ሲሆን እሱም እንደታገተ ይታወቃል አጋች አካላትም ልጁን ለመውሰድ የምትፈልጉ ከሆነ 2 ሚሊዮን ብር የጠየቁ ሲሆን ቤተሰቦቹም አቅም ስለሌላቸው የአቅማቹሁን እንድትረድን ስንል በፈጣሪ ስም እንማፀናለን

የአካውን ባለቤት ስም
ኢብራሂም ሀሰን (ታላቅ ወንድም)
ንግድ ባንክ
1000270990057

አቢሲንያ
131756399

ለበለጠ መረጃ 0934181613

የአቅማችሁን በማገዝ እና ይህንን መልእክት ሼር በማድረግ አግዙን።

መልእክቱ ከወንድማችን Hussen Oumer የተወሰደ ነው።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Dec, 17:53


የምንችለውን እናስተምር
~
ኢብኑል ሙባረክ - ረሒመሁላህ - "ከእድሜህ አንድ ቀን ብቻ ነው የቀረህ ብትባል ምን ትሰራ ነበር?" ተብለው ተጠየቁ።
"ሰዎችን አስተምር ነበር" አሉ።
[አልመድኸል ኢለሱነን፣ አልበይሀቂይ፡ 309]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Dec, 11:23


🔖 "በአህሉል አሰር የሴቶች መድረሳ" ለሴቶች የተሰጠ ምክር

🎙በአቡ ዒምራን

t.me/Abu_lmran_Alaseriy

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Dec, 11:19


ጫት ፦ሲጋራ የመሳሰሉት ነገር ላይ ገንዘብን ማባከን አይቻልም።

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Dec, 04:38


🌼يَا حَيُّ يَا قَيُّومُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغِيْثُ، أَصْلِحْ لي شَأْني كُلَّهُ، وَلَا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ
🔖አንተ ህያዉ የሆንክ አምላክ ሆይ! አንተ ራስክን የቻልክ አምላክ ሆይ!

~በእዝነትህ እታገዛለሁ ።
~ጉዳዮን ሁሉ የተስተካከለና መልካም አድርግልኝ።
~ለቅጽበት እንኳ እኔን ለራሴዉ ብቻ አትተወኝ።


📚ዚክርና ዱአ የመንፈስ ቀለብ !

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Dec, 04:21


« ቁርዓንን እንደማንበብና በወላጆች ላይ በጎ እንደ መዋል የበለጠ በረከትን የሚያስገኝ ነገር የለም(ሼኽ ሱለይማን አር-ሩሄይሊ)!!

«አንድ ሰው በየቀኑ ቁርዔን የሚቀራ ከሆነ፣ በቤተ| ሰቦቹ መልካም የሚውል ከሆነ ሲሳዩ ይሰፋል፤ የፈለገውን ያገኛል። እነዚህ ሁለት ተግባራት ወደ አላህ ከሚያቃርቡ ነገሮች ዋንኞቹ ናቸው።

🎉ሲሳይ እንዲሰፋለት የሚፈልግ እንዚህ ሁለቱ ነገሮች ላይ ይበርታ!!!!

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Dec, 18:21


አላማህ ላይ አተኩር ከዓላማህ ጋር በማይገናኙ ነገሮች አትዘናጋ!!

አወ በራስህ ላይ ብቻ አተኩር! ስለ አዋዋልህ, ስለ ስኬትህ እና ስለ አለማህ በደንብ አተኩር!! ከዛ ዱዓ......

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Dec, 03:17


" من أراد العزة ..
من أراد الكرامة ..
من أراد تغير حاله من السوء إلى الحسن ..
من أراد تغير حاله من الفقر إلى الغنى..
من أراد تغير حاله من الذلة إلى الرفعة ..
من أراد تغير حاله من الجهل إلى العلم .. ".
🎙️ لفضيلة الشيخ :
د.
#محمد_بن_سعيد_الرسلان •حفظه اللّٰه•

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Dec, 18:55


➡️ቁርአን በመሀፈዝ ሂደት ላይ አጋዥና
ወሳኝ የሚባሉ 9 ነጥቦች

➡️የሀፈዝነውን ቁርአን እየጠፋብን
ስንቸገር ማከሚያ የሆኑ 4 ወሳኝ
ነጥቦች ተዳሰውበታል።

🎙በወንድም ጀላሉ ሁሰይን (አቡ ዚክራ

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Dec, 17:39


ህልማችሁን፣ እቅዳችሁን ለሰዎች አትናገሩ። ከመሳካቱ በፊት የተነገረ እቅድ የመሳካት እድሉ ጠባብ ነው።

ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ
"ጉዳዮቻችሁን ታሳኩ ዘንድ በመደበቅ ታገዙ። እያንዳንዱ ባለ ፀጋ ምቀኛ አለበትና።" [አሶ፞ሒሐህ: 3/439

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Dec, 15:36


~ነገሮች ሁሉ በተወሳሰቡበት በዚህ ዘመን አንዳንድ ጊዜ ጥግ መያዝን የመሠለ ነገር ይሆን?!

ከአብዛኛው ሰው ዉሎ መራቅ፣ መገለል።
ጥግ ይዘህ ራስህን መገምገም።ስለ ጥፋትህ፣ ስለ ጉድለትህ፣ ስለ ድክመትህ ከአላህ ጋር ማውራት፣ ማንሾካሾክ።ነገሮችን ቁጭ ብለን ስናስባቸው ይደክማል ። ከአላህ ጋር ስናንሾካሹክ ቀለል ይላል።

አምላካችን ሆይ! አትተወን፣ አታርቀን፣ አትጥላን።
=

منقول

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Dec, 09:09


የቤቱ ሸር !

🎙Usetaz muhammed sirage

||
t.me/Muhammedsirage

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Dec, 02:50


التهاون في صلاة الفجر

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Dec, 02:49


لصلاة الفجر إيناس وراحة
هي من تبعث في الصدر انشراحه

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Dec, 20:01


የprofile ስማቹን الله أكبر ...سبحان الله ....لا إله إلا الله አታድርጉ !!!

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Dec, 18:09


በህይወትህ ላይ ብዙ ነገሮችን ታስባለህ ፣ ብዙ ነገሮች ላይም ትጥራለህ ፣ ብዙ ውጣ ውረዶችም ታሳልፋለህ ግን በነዚህ ሁሉ ክስተቶች እኛ ያሰብነው ፣ እኛ ያልነው ፣ እኛ ያለምነው ሳይሆን በውሳኔው ሁሉ ስህተት የሌለው  የአላህ ውሳኔ ብቻ ነው ሚፈፀመው።

      t.me/Darutewhide

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Dec, 16:32


✔️ሀያዕ (አይናፋርነት ) ትልቁ የኢስላም ቀንዘል ነዉ።

~የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ፦
ሀያእ ከኢማን ነዉ ብለዋል ።

👉ሀያዕ ጋሻ ነዉ ከወንጀል ይከላከላል
~በተለያዩ ሚዲያዎች እንደፈለጉ ሀያዕ ጋር የሚቃረን የሆነ አቀራረብ የሚቀርቡት ትልቅ መጋረጃ ስለተገሸለጠ ሀያእ ስለተገፈፈ ነዉ።

🔖ሀያዕ ሁሉም ነገሩ ኸይር ነዉ ብለዉ የአላህ መልእከተኛ ገልፀዉታል።

~ሀያዕ ከሁክም ከዋጋዉ  አንፃር የተወደሠ ሀያዕ እና የተወገዘ የሀያዕ አይነት አለ

~ሐያዕ ከምናፍረዉ አንፃር፦
~ አላህ ጋር ያለ ሐያዕ እና ሠዎችጋ ያለ ሐያእ

~አላህ ከከለከለን ቦታ እንዳያገኘን# ካዛዘን ቦታ እንዳያጣን ማፈር  ።
ብዙ ኒእማ ከዋለልን በኋላ ከብዙ ፈተና ካወጣን በኋላ ፍጡርን መከጀል ያሳፍራል ፦ፍጡርን መማፀን ያሸማቀን ይገባል። ሶላትን ከመስገድ ፆምን ከመፆም ዝሙት ላይ ከመታየት  የመሣሠሉት እንዲህ አይነት ነገሮች ትእዛዝን ቸል ማለት ወንጀል ላይ መዉደቅ አላህን አለማፈር ስለሆነ በዚህ በኩል ማሠብ ያስፈልጋል።

~በሌላ በኩል ሠዎችን ማፈር ያስፈልጋል። እኔ አላህን ያላፈርኩትን ሠዎችን ላፍር ነዉ እንደ የሚሉ ሰዎች አሉ ይህ ሞኝነት ነዉ።በወንጀል ጀብደኛ መሆን ነዉ የተጠላዉ የተወገዘ  ለጥፋት የሚዳርግ ነዉ።

~

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Dec, 12:27


ሶላት በነብያችን ላይ ማውረድ ያለው ደረጃ

ይደመጥ

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Dec, 12:19


~በሶላትህ አትቀልድ ፣ረጋ ብለህ ዉዱእ አድርግ፣ቀስ ብለህ መስጊድ ሂድ፣
ሀሳብህን ሰብስበህ ቁም፣አስተንትነህ ቅራ፣
ተረጋግተህ ሩኩዕ አድርግ፣ለሱጁድ በቂ ጊዜ ይኑርህ።
=t.me/Sle_qelbachn1

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Dec, 01:35


«ልብ ከምትደሰትባቸዉ ነገሮች ውስጥ አንዱቁርአንን በትኩረት ማዳመጥ ነዉ።»
~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

26 Dec, 18:28


🔖 ቁርአን  በቴሌግራም «voicechat» መቅራት የምትፈልጉ   ኑ !  በጣም ዝቅተኛ ክፍያ ነዉ! በተጅዊድ ለመቅራት የምትፈልጉ  ያለ መሰላቸት ቀጥ በላችሁ የምትቀሩ ብቻ።

      ↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
@Kireat1    @Kireat1  @Kireat1

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

26 Dec, 16:50


✔️ቁጥብነትፀያፊ ነገሮችን መራቅ ለሁለት ሊከፈል ይችላል።

➀)ከብልግና ጋር በተያያዘ ራስን ማራቅ መቆጠብከአስፀያፊ ነገሮች ወደዚያ ከሚያደርሱ ነገሮች መራቅ ቁጥብነት ነዉ።

➁)ቁጥብነት ፦ገንዘብጋ በተያያዘ ያለፈ ያገደመዉን ሰዎችጋ የሚመለከተዉን ሁሉ እያየ ሊከጅል፦ ሊጠይቅሊ፦ሊያስቸግርሊያሰለች አይገባም
#ከሁለቱም አንፃር ራሳችንን መፈተሸ

✔️ቁጥብነት የኢስላም አንድ ቀንዘል ነዉና
#የአላህ መልእከተኛ እንዲህ ብለዋል
የሚቆጠብ ቁጥብነትን የሚፈልግ አላህ ቁጥብነትን ያድለዋል አሉ።ቁጥብነትን ለመጓናፀፍ ለመላበስ ሰበብ የሚያደርግን አካል አላህ ያግዘዋል።

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

26 Dec, 12:42


ሸይኽ ፈውዛን - አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና - ዒልም ፈላጊ ተማሪዎችን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፦

እውቀትን ከመፈለግ አትሰልች።
አያያዝህ ትንሽ ቢሆን እንኳ እውቀትን ፈልግ።
መልካም ስራ ከመስራት ጋር ሲሆን ትንሹም በረካ አለበት።
እውቀት ፍለጋ ላይ መቀጠል ያለጥርጥር ኸይር ነው።
እውቀት ፍለጋ ዒባዳ ነው።
እውቀት ፍለጋ ግዴታ ካልሆኑ ዒባዳዎች የበለጠ ነው።"

[አልኢጃባቱል ሙሃማህ፡ 84]
=
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

26 Dec, 11:13


ስለ ቴሌግራም
ጥቅም በሰፊው ለማወቅ

t.me/abdu_tech_1/5

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

26 Dec, 04:45


🔖 የጧት ዚክር አይርሱ..!!

ዚክር፦ የቀልብ ብርሀን፣ የልብ መድሀኒት፣ የአካል ብርታት፣ የምላስ ጌጥ ነው።


▪️اللهم بِكَ أصْبَحْنَا، وَ بِكَ أمْسَيْنَا، وَ بِكَ نَحْيَا، وَ بِكَ نَمُوتُ، وَ إلَيْكَ النُّشُورُ.  

~አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነናል፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡

(ቲርሚዝይ)

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

25 Dec, 19:48


🔖በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ በሽሪአ  ከተደነገጉ ስነምግባር ቀንዘሎች ዉስጥ....!

➀).እዉነተኝነት
➁).አደራ ጠባቂነት
⓷).ቁጥብነት
➃).አይናፋርነት

➄).ጀግንነት
➅).ቸርነት ለጋሽነት
➆).ቃልን መሙላት/ መጠበቅ
⓼). መጥራት አላህ ከከለከለዉ ሁሉ ራስን ማራቅ
➈).መልካም ጉርብትና
➉).ባለ ጉዳይን (ችግረኛን)መርዳት እንደ
አቅም ልክ /መጠን
👉ከእነዚህም ዉጭ ያሉ ቁርአንና ሓዲሰ ያመላከታቸዉ የጠቆማቸዉ የተደነገጉ በመሆናቸዉ ላይ በነዚህ መዋብ ማሸብረቅ የተገባ ነዉ።
~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

25 Dec, 11:44


🔖በቁርአን ካልሠራ የቁርአን ሰዉ አይባልም!!
~
~የቁርአን ባልደረባ በቁርአን የሚያዉቅ ነዉ ። #በልቡ ባይሸመድደዉም እንኳ ቁርአን ዉስጥ ባለዉ የሚሠራ ነዉ።

#ቁርአንን የሸመደደዉ አካልማ ሸምድዶ ያልተገነዘበዉ በሱም ያልሰራ የቁርአን ፊደላቶች ቀጥ አድርጎ አስተካክሎ፦አስዉቦ ቢያነብም ቢቀራ እንኳ ከቁርአን ሰዎች አይደለም።

[ኢማም ኢብኑ ቀይም]

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

25 Dec, 11:28


📌ክፍል ①

📚رحلة في حياة أهل القرآن

ወደ ቁርኣን ሰዎች የ ህይወት ጉዞ

🎙አቡ ዐኢሻ ሙሐመድ ሰዒድ

https://telegram.me/abutoiba
https://telegram.me/abutoiba

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Dec, 19:26


1. የምንቀራውን ኪታብ ቃላት ልቅም አድርጎ መያዝ። ከኪታቡ ውስጥ የማናውቀው ቃል ላይኖር።

2. የኪታቡ መልእክት ላይ ትኩረት ማድረግ። መልእክቱን በትክክል መረዳት። ቃላት ለቀማ #ብቻ እንዳይሆን።

3. ማስረጃ ሲጠቀስ ከርእሱ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ መለየት። مَحَلَّ الشَّاهِد እና وَجْهُ الاِستِدلال

4. ከደርስ በፊት እና ከደርስ በኋላ ሙራጀዓ ማድረግ። ከጓደኛ ጋር ወይም ለብቻ ሁኖ።

ባጭሩ = የተማርነውን ኪታብ ለሌሎች ማስተላለፍ በሚያስችል አቅም መያዝ ያሰፈልጋል።
~
ከኢብኑ ሙነወር ደርሶች ላይ የተወሰደ።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Dec, 19:13


~ዋና አላማ ግብ ፦መብላትመጠጣት፦ማግባት አደለም ።ዋናዉ አላማ ግብ የአላህ ሱብሀነሁ ተአላ መልካም ባሪያ መሆን ነዉ።
🌼 وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Dec, 16:53


🔖ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀምአንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።

~እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥየፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።"

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Dec, 12:39


~አብዘሓኛዉ የአደም ልጅ ስህተቱ በምላሱ ነዉ።

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Dec, 16:38


~ አንዳንዴ!!

በቅርብ ሆነህ ዋጋ ቢስ ከምትሆን በርቀት ሆነህ መከበር ትልቅ ረፍት ነው።

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Dec, 12:52


🔖ጓደኞችህን ለይ !!
~
ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም።

~እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀልአልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ።

~ ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከ

✍️ ጥቂት ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች»ከሚለው ድንቅ የ ኡስታዝ ኢብኑ ሙነዎር ፁሁፍ የተወሰደ…።

~

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Dec, 18:57


🔖ነጃህ ፈላህ ለመወጣት ከፈለክ #በእነዚህ ስበቦችን መንገዶችን አጥበቀህ ያዝ !
~
🌼يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ =እናንተ እመኑ በተባላችሁበት  ያመናችሁ ሰዎች ሆይ

➀ٱصْبِرُوا۟=ታገሱ

➁ وَصَابِرُوا۟ = ተበራቱ ተረዳዱ.

⓷وَرَابِطُوا۟=በጦር ሜዳላይ ተሠለፉም

⓷ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
=ትድኑም ፈላህ  ትወጡ ዘንድ አላህን ፍሩ፡፡

👉የሶብር አይነቶች
    ~
➀)በአላህ ትዕዛዝ ላይ ሶብር ማድረግ
➁) አላህ ከከለከላቸው ክልከላዎች ላይ
ላለመውደቅ ሶብር ማድረግ
⓷)አላህ በወሰናቸው ውሳኔዎች ላይ ሶብር ማድረግ


       =
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Dec, 12:27


ለሞት መዘጋጀት
~
"ከሙስሊም የሚጠበቀው እድሜው በጨመረ ቁጥር ይበልጥ ወደ አላህ የቀረበ ሊሆን፣ ይበልጥ ለአላህ የሚያደርገው ዒባዳ የጨመረ ሊሆን ነው። ከአላህ ጋር መገናኛው እየቀረበ እንደሆነ ሊያስብ ይገባል። መቼስ ማንም ሰው ቢሆን ሞት መቼ እጅ እንደሚያደርገው አያውቅም። ሙሉ ጤነኛ ሆኖ አንግቶ፣ የሞት ሃሳብ አንድ ከመቶ ያክል እንኳ አእምሮው ላይ ውል ሳይልበት ከዚያ ግን ከሞት ጋር ያመሸ ስንት ሰው አለ?! እና ሙስሊም የሆነ ሰው ዝግጁ ሊሆንና የተቅዋ ስንቅ ሊሰንቅ ይገባል።"

ሸይኽ  አልኸሥላን
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Dec, 08:11


🎁 ihsan jobs
ኢህሳን
ይህ ቻናል ለሙስሊሙ ማህበረሰብ
ይጠቅም ዘንድ ታስቦ የተከፈተ የስራ ማስታወቂያ
የምንለቅበት አዲስ ቻናል ነው 💎

በቻናሉ ነፃ ማስታወቂያ እንለቃለን
ከናንተ የሚጠበቀው የትኛውም
ማስታወቂያ በውስጥ መሥመር
ለኛ ማሳወቅ ብቻ ነው ➡️

እኛም በነፃ ከሸሪዓ የማይጋጩ ስራዎች
አጣርተን በቻናሉ እንለቃለን
⭐️ @twhidfirst1
🌟 @Tolehaaaaaa
🌟 @AbuNuhibnufedlu

https://t.me/ihsan_jobs
https://t.me/ihsan_jobs

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Dec, 20:29


🔖አላህን ስናመልክ ልባችንን ወደሱ ሰተን (ከጅለን) ናፈርተን ነዉ መሆን ያለበት ካልሆነ ኢባዳ አይባልም።
🌼وَٱذْكُر رَّبَّكَ فِى نَفْسِكَ تَضَرُّعًۭا وَخِيفَةًۭ وَدُونَ ٱلْجَهْرِ مِنَ ٱلْقَوْلِ بِٱلْغُدُوِّ وَٱلْـَٔاصَالِ وَلَا تَكُن مِّنَ ٱلْغَٰفِلِينَ

~ጌታህን በምስጢር ተዋድቀህ (ልብህን ጠጋ አድርገህ) ጌታህንም ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል# በጧትም በማታም አውሳው፡፡ አላህን ከማዉሳት ከዘንጊዎቹም አትኹን፡፡

📚ሱረቱል አእራፍ(205)

=
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Dec, 17:35


አላዋቂ ሴት ማለት ይቺ ናት

【من أحمق النساء امرأة اضطرت زوجها إلى أن يسيء إليها بعدما كان يعاملها بالحسنى】

ሞኝ ወይም ቂል ሴት ማለት ባሏ በመልካም እየተኗኗራትና መልካም እየሰራላት ሳለ በንግግሯ ወይም በተግባሯ በሷ ላይ መጥፎ እንዲሆንና መጥፎ እንዲሰራባት ያስገደደችው ሴት ናት።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Dec, 12:29



💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Dec, 11:57



« هُمُ الْجُلَسَاءُ لَا يَشْقَى بِهِمْ جَلِيسُهُمْ »

💦

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Dec, 11:34


بـــــســـــم الله الرحـــــمــــن الرحــــيــــم
اما بعد
(ፍቅር) او ልብን በሌላ አካል ላይ ማንጠልጠልን በተመለከተ ስላለው ጉዳት ነው የማወራው,,
←كما قال ابن قيم رحمه الله
انه ( من تعلق قلبه بغير الله عذب به )
ኢብን ቀይም→ከአላህ ውጪ ባለ ነገር ላይ ልቡን የሚያንጠለጥል አካል በርሱው በወደደው ነገር ይሰቃያል እንዳሉት።
ፍቅር ከድን መራቃችን እና የመሳሰሉት ጉዳቶች ከመኖራቸውም ጋ
ዱንያውይ ህይወታችንንም ጭምር በአግባቡ እንዳንመራ ዝብርቅርቅ እና ድንዝዝ የሚያደርግ ህመም ነው»
ፍቅር ራስን ይቀማል፣ በምታፈቅሩት ሰው አለም ውስጥ ራሳችሁን በራሳትሁ የምታስሩበት ስጅን ነው
ከሁሉም ነገሮች ጋ ያለንን ግንኙነት ይበጠብጣል፣ የውስጥ ረፍት እና ሀሴት የሚባልን ነገር ከህይወታችን ያርቃል...
የተፈጠርንበትን አላማ አስረስቶ የስሜታችን ተከታይ እንድንሆንም ያደርጋል
የነፍስን ፍላጎት መከተል ደግሞ ከርሱ መንገድ ያስወጣል
ልክ ጌታየ፦ ከአላህ መንገድ ያስወጣካል እና ዝንባሌክን/ ሀዋክን እንዳትከተል እንዳለው
( وَلَا تَتَّبِعِ الْهَوَىٰ فَيُضِلَّكَ عَن سَبِيلِ اللَّهِ ۚ )

نعم انه طريق الضياع / وانه طريق المميت / وطريق ضلال
ሁለቱንም ሀገር ያበላሻል፣ የአላህን መንገድ ይጋርዳል
ዒልምን ከመፈለግ ያቅባክ፣ አኽላቅን ያበላሻል
ሀያዕን፣ አደብን ያራቁታል..
ብዙ ወጣቶችን ከተስተካከሉ በኋላ መንገድን አስቷቸዋል
አእላፍ ተምሳሌት ሊሆኑ የሚችሉ ጨዋ እና ቁጥብ ሴቶችንም ጭምር ሃያዕቸውን፣ ስርዓታቸውን አሳጥቷል
ስንት እና ስንት ሰዎች ከድናቸው ርቀዋሉ!
ስንቶችስ ብዙ ለፉተው የሀፈዙትን፣ የተማሩትን ረስረዋሉ!
ወረቢ ኢማንን ይገድላል፣ የልብን ብርሃን ያጨልማል፣ ኢማን ሢሞት ልብ ሢጨልም ደግሞ ሰው መንገድን ይስታል።
انه فتن العظيم  / وانه مرض خطير يا إخواني
ሹፉ (አላህ ይዘንላችሁና) ይሄ ተዓሉቅ አው ፍቅር የሚባለው ስሜት የሚወለደው አስሉ ሸርዕየን የሚፈቀድ ባይሆንም በእህትና በወንድምነትም በሉት..
በጓደኝነትም በሉት..
በተማሪ ባስተማሪነትም በሉት..
በአብሮ አደግነትም በሉት ብቻ ሁለቱም ጎን ከማይፈቀድለት አካል ጋ ህገወጥ የሆነን ቅርርብ ሢፈጥር በጊዜ ሂደት ውስጥ የሚመጣ ጦስ ነው።
ለዚህም ሢባል ያለ ሀጃ፣ ያለ ገደብ፣ ያለ አግባብ፣ ወንዶችም ከሴትጋ ሴቶችም ከወንድጋ አትቀራረቡ፣ አትቀላቀሉ።
ፈተናንም በራሳችሁ ላይ አትመኑ
اما قال النبي ﷺ : ما تركت بعدي فتنة هي أضر على الرجال من النساء،!
ከኔ በኋላ በወንዶች ላይ እንደ ሴቶች ጎጅ አው ከባድ የሆነ ፈተናን አልተውኩም ብለዋሉ።
እንዲሁም፦
فاتقوا الدنيا واتقوا النساءَ، فإن أولَ فتنةِ بني إسرائيلَ كانت في النساءِ
ሴቶችን እና ዱንያን ተጠንቀቁ የበኑ ኢስራዔል የመጀመሪያ ፈተና ሴቶች ነበሩ በማለት አስጠንቅቀዋል።
እኛ ሴቶችም፦ ለሃጃ እንኳ ስናወራ ድምጻችንን እንዳናለሰልስ፣فلا تخضعن بالقول
በማለት እንዳንቅለሰለት ታዘናል።
ሸሪዓው ባስቀመጠው መልኩም እንድንሸፋፈን፣ እንደ ጃሂልያ ሴቶች እንዳንራቆትም ተከልክለናል።  

ምክንያቱም የፊተን መዳረሻወችን እንድንዘጋ እና በታዘዝንበት መልኩ እንድንኖር ሲባል።
ولكن لمن كان له قلب..

                                     👑..sêlwã🫧

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Dec, 05:24


≺≺ኢብኑ ተይምያ የሱናው አንበሳ≻የእውቀት ማእድ የዋትሳፕ ግሩፕ

«ኮድ ➀   ⇓⇓
https://chat.whatsapp.com/Gq46QQFVlQKG4Jv77eAwOC

«ኮድ  ➁  ⇓⇓
https://chat.whatsapp.com/H1N5Ugqz9O6GwIBtCOnxZ4

«ኮድ ➂  ⇓⇓
https://chat.whatsapp.com/JZsJJcYkgSnLpFNhqinRCY

=

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Dec, 18:16


ለጀግና ፅኑ እህቶች ብቻ ነው።

👉እንዳትሰበሪ‼️

ከህይወት ጣራ ላይ ፤
ኑሮ የቀደደው ክፍተትሽ ቢበዛም፡
በአንች የታገዘው፤
ውለታን ረስቶ 'ሽ' ጉራ ቢነዛም፡
ሚሊወን ወስላታ፤
በቢሊወን ቢሸጥ አንድ አንችን አይገዛም፡

👉እንዳትሰበሪ‼️

ስብራት ክፉ ነው፤
የትላንትን ቁስል ድጋሜ ያሳያል፡
ጊዜው ያለፈ ቀን፤
ሙሉ ያሉት ሁሉ ጎደሎው ይታያል፡
አንች ግን እንቁ ነሽ፤
በቀነሱሽ ቁጥር ሙላትሽ ይለያል፡

እንዳትሰበሪ‼️

የስደቷ እህቴ፤
ትናንት ባገዘችው ብትረጋገጥም፡
በሴትነት ላይ ነው፤
የትርታችን ልክ የወንድነት ግጥም፡
ነፍሷን አደህይታ፤
ባዳነችው ቁስል ብትገሸለጥም፡
በማንም ወንበደ፤
ንፁህ ሆና እህቴ አትርመጠመጥም፡

ስሙ⁉️

አለም በአጠቃላይ፤
ለኛ ሙስሊሞች ሀይሉን ቢሰድርም፡
ክንዱን አጠንክሮ፤
እልፍ የሰገደለት ሐይል ቢሰድርም፡
ሁሉን ለመደፍጠጥ፤
አህጉር የሚያቋርጥ ጦር ቢደረድርም፡
በሴት ልጆቻችን፤
በእህቶች ክብር አንደራደርም፡

እንዳትሰበሪ

በእምነትሽ ፀንተሽ፤
በኒቃብሽ ኮርተሽ በድል ተከበሪ፡
የጠላ ሰው ሲያማሽ፤
በፍፁም በጭራሽ አትደናበሪ፡
ማንን ደስ እንድለው፤
ቀና በይ አይዞሽ እንዳትሰበሪ፡

✍️በኑረዲን አል-አረብ
http://t.me/nuredinal_arebi
http://t.me/nuredinal_arebi

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Dec, 16:49


የተዉሂድ ክፍሎች ሶስት ለመሆናቸዉ መረጃቸዉ ይህ አንገብጋቢና አሳሳቢ ነዉና ንቁ

🎙ሼኸ ፈዉዛን አላህ ይጠብቃቸዉ

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Dec, 16:41


~አድምጡ

አድስ ግሩፕ በተከፈተ ቁጥር እዛም እዚህም የምንዘል ሠዎች ማንቂያ ....

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Dec, 16:32


«ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም»

☞︎︎︎ ክፍል - 20

የሱና ብርሃን ትምህርት ቤት ግሩፕ ላይ በየ ሳምንቱ የሚቀርብ ትምህርት።

🎙በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር


ጆይን፡‐  t.me/fejir_tube

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Dec, 18:14


https://t.me/tdarna_islam?livestream=8d916da59d632fd544

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Dec, 15:51


ሰገጆች ብዙ ናቸውበአግባቡ ህጉን ጠብቀው የሚሰግዱት ትቂቶች ናቸው

👂👂እናድምጥ !

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Dec, 15:47


🔖አል-ኹሹዑ ፊ ሰላህ በሚል ርዕስ የቀረበ ማስታወሻ

  🎙በአቡ ዘይድ ከማል አሕመድ

         t.me/Subuleselam_Medresa

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Dec, 10:39


~ሀይልም ብልሀትም የለምበአላህ ቢሆን እንጅ ..

~ከአንድ ሁኔታ ወደ አንድ ሁኔታ መንቀሳቀስ አይቻልም። በአላህ ቢሆን እንጅ...!

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Dec, 10:20


"فإمّا أن تكونَ أخي بصدقٍ
فأعرفَ منك غثِّي من سَميني

وإلّا فاطْرَحني واتّخذني
عدُوًّا أتّقيكَ وتَتَّقِيني".
🎙Abu mahir al assery

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Dec, 04:03


🌼يَا حَيُّ يَا قَيُّومُ بِرَحْمَتِكَ أَسْتَغِيْثُ، أَصْلِحْ لي شَأْني كُلَّهُ، وَلَا تَكِلْنِي إِلَى نَفْسِي طَرْفَةَ عَيْنٍ
🔖አንተ ህያዉ የሆንክ አምላክ ሆይ! አንተ ራስክን የቻልክ አምላክ ሆይ!

~በእዝነትህ እታገዛለሁ ።
~ጉዳዮን ሁሉ የተስተካከለና መልካም አድርግልኝ።
~ለቅጽበት እንኳ እኔን ለራሴዉ ብቻ አትተወኝ።


📚ዚክርና ዱአ የመንፈስ ቀለብ !

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Nov, 19:22


~ንጽህና የኢማን ግማሽ ነው
~ሶላት ብርሃን ነው።
~ሰደቃ ማስረጃ ነው።
~ትእግስትም ብርሃን ነው።

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Nov, 16:05


ኮሜንቱን እያነበብሽው ነው⁉️


ከአረብ ሀገር ተመላሽ ነኝ ብር በማጣቴ ቤተሰቦቼ እህቶቼ ጠሉኝ ጣሉኝ ....ነው የምትለው ምናልባት ሀሳቧን ለመግለፅ አልችል ብላ ወይም አሳምራ ማስረዳት አልቻለችም እንጅ ከፅሁፏ ጀርባ ብዙ የበደል ጥግ ደርሶባት ይህንን ፅሁፍም ስትፅፍ እያለቀሰች ይሆናል።

ንቁ ተጠንቀቁ ራሳችሁን ቻሉ

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Nov, 16:03


~ሰማችሁ አደል ?

.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Nov, 14:35


ብዙዎች
~ ጤናን ከገንዘብ አይቆጥሩትም፤
~ እናት አባትን እንደ ፀጋ አያዩትም፤
~  እድሜን ከሀብት አይመድቡትም፤
~  ባል ለሚስት ሚስት ለባል ያማረ ልብስ መሆኑን አያስቡትም፤
~  ውሃን ከቀለብ አይደምሩትም፤
~  ከሀሣብ ነፃ መሆንን ከድሎት አይመዘግቡትም፡፡ ነገርግን እነኚህ ሁሉ የአላህ (ሱ.ወ.) ፀጋዎች ናቸው፡፡
የአላህ መልእክተኛ (صل الله عليه وسلم) እንዲህ ይላሉ ‹በቤተሰቡ መሃል በደህንነት የዋለ፣ አካላዊ  ጤናው የተጠበቀለት፣ ለራሱም ሆነ ለቤተሰቡ የሚሆን ቀለብ ያገኘ፣ ይህች ዓለም በሙሉ እንደተለቀቀችለት ነው ።

          

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Nov, 12:43


አዳምጭው መዳም
ባይጠቅምም አይጎዳም

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Nov, 04:46


⚠️⚠️⚠️⚠️⚠️📡

⭐️የመተዋወሻ እና ለህፃን አቲካ
⭐️የትብብር  ፕሮግራም

በትዳር እና ኢስላም ቻናል

ኑ! በልብ ህመም እየተሰቃየች የምትገኘው ህፃን አቲካን ሰበብ እንሁናት

በእለቱም ተጋባዥ ኡስታዞች እና ወንድሞች:
⭐️
➡️ኡስታዝ አቡ ሂበተላህ🎤
➡️ኡስታዝ ዓብዱረዛቅ ባጂ 🎤
➡️ኡስታዝ ኢብራሂም ኸይረዲን 🎤
➡️ኡስታዝ አቡ ዑበይዳህ🎤
➡️አቡ ሁዘይፋህ (ሰዒድ)🎤
➡️አቡ ማሂ (ሙሐመድ ኢድሪስ)🎤

የህፃን አቲካ ህመም ምንድነው?👇
t.me/tdarna_islam/4859?single
t.me/tdarna_islam/4863
⬆️
ቀን እና ሰዓት ነገ እሁድ 22/03/2017
ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ➡️

የሚተላለፍበት ቻናል
⭐️ t.me/tdarna_islam
      t.me/tdarna_islam ⭐️

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 20:21


ብቻዬን የሆንኩት ብቸኝነት እንዳይሰማኝ ነው።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 20:15


እዉቀት ወድቆ የማይሠበርና ሌባ የማይሠርቀዉ ትልቅ ሀብት ነዉ

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 17:30


ሁሉ ነገር በቀደር ነውእጅህን አገጭህ ላይ ማስቀመጥህ እንኳ ቢሆን! አላህ የወሰነልህን ወደህ ተቀበል።

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 16:11


ባልሽ ባልሽ እና አለቃሽ ብቻ ሳይሆን የእምነት ወንድምሽም ጭምር ነው !
ሚስትህ ሚስት ብቻ ሳትሆን የኢስላም እህትህም ጭምር  ነች !

ይህንን በአግባቡ ብናጤን  ኖሮ የሚሰማው ወሰን ያለፈ በደል በሚሰማው መጠን ባልተሰማ ነበር ! የፍቺው መጠን እንደሚታየው ሳይበዛ ነገራችንም ባማረ ነበር ።

t.me/Muhammedsirage

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 13:32


ሙሓደራ 216

አማኝ እህቴ ሆይ ያንቺ ሞዴል እና አርዓያሽ ጥቁሯ ሴት ናት

🚦በ ደሴ የተደረገ ሙሃደራ

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ(አቡ ሓቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 06:09


~የአለማወቅ መድሃኒት መጠየቅ ነዉ።

🎙በሼኽ ሙሐመድ ዘይን

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Nov, 03:59


~የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል

👉የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል

=

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Nov, 19:42


🌼إِنَّ رَبَّكَ يَعْلَمُ أَنَّكَ تَقُومُ أَدْنَىٰ مِن ثُلُثَىِ ٱلَّيْلِ وَنِصْفَهُۥ وَثُلُثَهُۥ وَطَآئِفَةٌۭ مِّنَ ٱلَّذِينَ مَعَكَ ۚ وَٱللَّهُ يُقَدِّرُ ٱلَّيْلَ وَٱلنَّهَارَ ۚ عَلِمَ أَن لَّن تُحْصُوهُ فَتَابَ عَلَيْكُمْ ۖ فَٱقْرَءُوا۟ مَا تَيَسَّرَ مِنَ ٱلْقُرْءَانِ ۚ عَلِمَ أَن سَيَكُونُ مِنكُم مَّرْضَىٰ ۙ وَءَاخَرُونَ يَضْرِبُونَ فِى ٱلْأَرْضِ يَبْتَغُونَ مِن فَضْلِ ٱللَّهِ ۙ وَءَاخَرُونَ يُقَٰتِلُونَ فِى سَبِيلِ ٱللَّهِ ۖ فَٱقْرَءُوا۟ مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ ۚ وَأَقِيمُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتُوا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَقْرِضُوا۟ ٱللَّهَ قَرْضًا حَسَنًۭا ۚ وَمَا تُقَدِّمُوا۟ لِأَنفُسِكُم مِّنْ خَيْرٍۢ تَجِدُوهُ عِندَ ٱللَّهِ هُوَ خَيْرًۭا وَأَعْظَمَ أَجْرًۭا ۚ وَٱسْتَغْفِرُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ غَفُورٌۭ رَّحِيمٌۢ

~አንተ ከሌሊቱ ሁለት እጅ ያነሰን ግማሹንም
ሲሶውንም የምትቆም መኾንህን ጌታህ በእርግጥ ያውቃል፡፡ #ከእነዚያም አብረውህ ካሉት ከፊሎች (የሚቆሙ መኾናቸውን ያውቃል)፡፡ አላህም ሌሊትንና ቀንን ይወስናል፡ (ሌሊቱን) የማታዳርሱት መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተ ላይም (ወደ ማቃለል) ተመለሰላችሁ፡፡ ስለዚህ ከቁርኣን (በስግደት) የተቻላችሁን አንብቡ፡፡ ከእናንተ ውስጥ በሽተኞች፣ ሌሎችም ከአላህ ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ የሚጓዙ፣ ሌሎችም በአላህ መንገድ (ሃይማኖት) የሚጋደሉ እንደሚኖሩ ዐወቀ፡፡ (አቃለለላቸውም)፡፡ ከእርሱም የተቻለችሁን አንብቡ፡፡ #ሶላትንም ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ ለአላህም መልካም ብደርን አበድሩ፡፡ ከመልካም ሥራም ለነፍሶቻችሁ የምታስቀድሙትን ሁሉ እርሱ የተሻለና በምንዳም ታላቅ ኾኖ አላህ ዘንድ ታገኙታላችሁ፡፡ አላህንም ምሕረትን ለምኑት፡፡ አላህ በጣም መሓሪ አዛኝ ነውና፡፡

📚ሱረቱል ሙዘሚል 20
=
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

21 Nov, 13:45


🌼أَلَّا يَسْجُدُوا۟ لِلَّهِ ٱلَّذِى يُخْرِجُ ٱلْخَبْءَ فِى ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضِ وَيَعْلَمُ مَا تُخْفُونَ وَمَا تُعْلِنُونَ
~ለዚያ በሰማያትና በምድር የተደበቀውን ለሚያወጣው፣ የምትሸሽጉትንና የምትገ ልጹትንም ሁሉ ለሚያውቀው አላህ እንዳይሰግዱ (ሰይጣን አግዷቸዋል)፡፡

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

21 Nov, 08:47


🔖አዲስ የቂርአት ማስታወቂያ

የአላህ ፍቃድ ከሆነ ዘወትር ምሽት በሳኡዲ ሰአት አቆጣጠር 9:00 ጀምሮ የሪሳለቱል ሂጃብ ኪታብ ቂርአት የምንጀምር ይሆናል።

🛑👉በኒቃብ ዙሪያ ለሚነሱ ሹብሀዎች አንድ በአንድ መልስ የሚሰጥ ከመሆኑ ጋር

ኒቃብ ያለበሱ እንዲለብሱ
√ የለበሱት ደግሞ እንዲፀኑ
የፀኑት ደግሞ እንዲጀግኑ የሚያግዝ ወሳኝ ኪታብ ነው።

«የሚጀመርበት ቀን ቅዳሜ ሕዳር 14/3/2017 ነዉ» ከምሺቱ 9:00 ስአት በሳዑድ አቆጣጠር
በኢትዮ 3:00 ስአት! ይጠብቁን !

ቀጥታ ስርጭት የሚሰጥበት ቻናል፦
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 20:46


"اللَّهمَّ إنِّي أسألُكَ الجنَّةَ، وأَعوذُ بِكَ منَ النَّارِ."
~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 20:15


🎙በሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም  «ሀፊዘሑላህ»
📄እየተቀራ ያለ የተከበረው ቁርኣን ቃል በቃል  ትርጉም በቀላሉ ለማገኘት ....!

⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼⤼
  ↹ክፍል «❶»⥥⤸                          
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10242

↹ክፍል «➋»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10266

↹ክፍል «❸»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10288

↹ክፍል➍»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10290

↹ክፍል «➎»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZain/2986

↹ክፍል «➏»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10352

↹ክፍል «➐»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10384

↹ክፍል «➑»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10426

↹ክፍል «➒»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10448

↹ክፍል «➓»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10455

↹ክፍል «➊➊»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10471

↹ክፍል «➊➋»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10512

↹ክፍል «➊❸»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10553

↹ክፍል «➊⓸»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10631

↹ክፍል «➊⓹»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10654

↹ክፍል «➊⓺»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10690

↹ክፍል «➊⓻»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10696

↹ክፍል «➊⓼»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10726

↹ክፍል «➊➒»⥥⤸
t.me/SheikhMuhammedZainAdam/10763

  🔖ይቀጥላል ኢንሻ  አላህ ...........!!

     👉የቴሌግራም ቻናል፡-↓↓
     =
t.me/Sheikhmuhammedzainadam
 
t.me/Sheikhmuhammedzainadam

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 20:15


🔖እዉቀትን መታደል የነብያቶች ወራሸ መሆን ነዉ።

ነብያቶች ወርቅ ይሁን ብር አላወረሱም ያወረሱን እዉቀትን ነዉ።

~የድን መድከም  ሠበቡ ዋናዉ ምክንያት እዉቀት ማነስ ነዉ።

~እወቀት የትም ያኮራል ያስከብራል።
~በማወቅ ከዱኒያ ከአኼራ አደጋ መዳን ይቻላልከሠሩበት ከተጠቀሙበት

~እንደ መሀይምነት የሚያሳፍር የሚያዋርድ ካባ  የለም።

እና እዉቀትን በመፈለግ ላይ ችላ አንበል እንበርታ።

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 17:14


🔖ጉዞ ወደ አላህና ወደ አኼራ

t.me/wereda07wetat?videochat
t.me/wereda07wetat?videochat

ግቡ ቀልባችሁን አርጥቧት

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 17:12


🔖የአላህ መልእክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል

📍አራት ነገሮች የደስታ ምንጭ ናቸው
①) ሷሊህ ሚስት
②) ሰፊ መኖሪያ
③) መልካም ጎረቤትና
④) ምቹ መጓጓዣ።

📚ሲልሲለቱ አሰሒሃ (282)

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 16:33


🔖ትዳር አንዱ የሪዝቅ ማግኛ ስበብ ነዉ።
~
የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል ፦

~ሶስት ሰዎች የአላህ እገዛ ሊያደርግላቸዉ የተገቡ ናቸዉ።ከጠቀሱት አንዱ

~ከሀራም ለመጠበቅ ሲል ትዳር የመሠረተ ነዉ።

📚ትርሚዚ ዘግበዉታል።
       ~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

20 Nov, 09:16


የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲሱ  ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው 
በሀገር ውስጥም ይሁን ካሀገር ውጪ ያላችሁ
የሱና ወንድም እና እህቶቻችን 
ይህ ቻናል ይጠቅማችኋል ተቀላቀሉ
👇
join request የሚለውን በመጫን✅️
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0
t.me/+SYGKSEYXv-kyNTQ0

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

19 Nov, 20:15


ኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጁ

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

18 Nov, 03:30


~የጧት ስንቅ...

🔖ቁርአን የልብ መድሀኒት የሩህ ምግብ ነው

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

18 Nov, 03:16


~ስናማርር ውለን፣
ሰናማርር መሸ፣
ለሩቁ ስንቋምጥ፣
የሰጠኸን ሸሸ!
ደሞ አዲስ ቀን ሆነ፣
ላልተሰጠን ሁሉ፣ልናማርር ነጋ፣
የሰው ልጂ አይደለን?
በቃኝ ን የማናውቅ ባለን የማንረጋ፤
ተኝቶ መነሳት አይመስለንም ፀጋ !!!

አልሃምዱሊላህ .

~የጧት ዚክር አይርሱ....

~
   t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

17 Nov, 09:05


በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ተቀርቶ የተጠናቀቀው የሪያዱ ሷሊሒን ሙሉ ደርስ ቀጣይ ባሉት ሊንኮች ማግኘት ትችላላችሁ።

⬇️ ክፍል አንድ ከደርስ 1-105
  t.me/IbnuMunewor/6449

⬇️ ክፍል ሁለት ከደርስ 106-194
    t.me/IbnuMunewor/6450

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

17 Nov, 07:45


~አትፍራ ሪዝቅህ ሰዎች የማይደርሱበት ቦታ ነው ያለው ሊቆርጦት አይችሉም

🌼وَفِي السَّمَاءِ رِزْقُكُمْ وَمَا تُوعَدُونَ
~ሲሳያችሁም የምትቀጠሩትም  በሰማይ ውስጥ ነው፡፡

ከምድር ኗሪዎች ወደላይ ከፍ በል
የአንተ ፍላጎት በእጃቸዉ አይደል
እንቢታን የማያቅ ለለመነ ባሪያዉ
ማነዉ ሚለምነኝ እኔ የምሰጠዉ
እያለ ሚጣራ ቸርዬ  ጌታ አለህ
ወደሡ ሙጭኝ በል የምድሮቹን ትተህ


.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

16 Nov, 22:39


🔖አላህ የምንስበዉን አየር የምንመገበዉን ምግብ የምንጠጣዉን #ተክለ ሰዉነታችንን ጤናችንን ሁለ ነገራችንን የሠጠን ሁኖ ሳለ ለትእዛዙ አለማደር ክህደት ነዉ።

~➀ አንድኛዉ የሠዉልጅ ባህሪ ዉለታ ቢስ ነዉ..
🌼إِنَّ ٱلْإِنسَٰنَ لِرَبِّهِۦ لَكَنُودٌۭ
የሠዉ ልጅ በእርግጥ ለጌታው ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

#ክህደቱ በምን ይገለፃል ?ትእዛዝን ባለመፈፀም አላህ የዋለለትን ኒእማ አለማመስገን

ሁለተኛ የሠዉ ልጅ ባህሪ ገንዘቡን ለማዉጣት እንደሚከብደዉ በራሱላይ መስካሪ ነዉ (ተግባሩ ይመሠክራል)።

🌼وَإِنَّهُۥ عَلَىٰ ذَٰلِكَ لَشَهِيدٌۭ
እርሱም (የሠዉ ልጅ)በዚህ ላይ በእርግጥ (በራሱ ላይ )መስካሪ ነው፡፡( አላህ) ስስታምነቱን ዉለታ ቢስነቱን ከሐድነቱን ተመልካች ነዉ።

⓷ ሶስተኛ የሠዉልጅ ባህሪ
🌼وَإِنَّهُۥ لِحُبِّ ٱلْخَيْرِ لَشَدِيدٌ
~እርሱም (የሠዉ ልጅ) ለገንዘብን ያለዉ ፍቅር በጣም ብርቱ ነው፡፡

#ለገንዘብ ያለዉ ጉጉት የበረታ ከመሆኑ የተነሳ የተጣለበትን ግዴታ እንኳ እስከማይወጣ ያደርሰዋል። ለገንዘብ ያለዉ ጉጉት የበረታ ከመሆኑ የተነሳ በሐራም ለማግበስበስ ሐራም ዉስጥ እንዲዘፈቅ ያደርገዋል ።

📚ሱረቱል አል አድያት ...

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

16 Nov, 18:31


አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ቀጥሎ ያሉት በመርከዘ ተውሒድ ለክረምት ተማሪዎች የቀረቡ የሹሩጡ ሶላት ኪታብ ደርሶች ናቸው። አንድ ወይም ሁለት የቀሩ አሉ። ሰሞኑን ቀድቼ አሟላለሁ፣ ኢንሻአላህ ። ከዚህ በፊት የተቀዱ የሹሩጡ ሶላት ደርሶችን አታሰራጯቸው። በየትኛውም ጊዜ እርምት የሚሻ ነገር ያስተዋለ አካል እንዲያካፍለኝ እጠይቃለሁ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

16 Nov, 15:43


አራት(4) ነገሮች ያለበት ሰው ከዱንያ ምንም ነገር አላጣም። ዱንያ ብትቀንስበት ምንም ነገር አይጎዳውም።

~ አማናን ጠባቂ፣
~ እውነትን ተናጋሪ፣
~ መልካም ስነምግባር ያለው ሰው እና
~ ከሀላል የሚበላና
የሚጠጣ ሰው ናቸው።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

16 Nov, 15:40


እይታን አለመስበር አደጋ አለው
~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ወደ ሴቶች እይታውን እንዳሻው የሚለቅ ሰው ፈተና ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው።

እይታ ከኢብሊስ መርዛማ ቀስቶች ውስጥ ነው ፣ አላህ ይጠብቀንና።

አንድ ሰው ቆንጆ ሴት ባለፈች ቁጥር የሚመለከት ከሆነ ያለ ጥርጥር ልቡን ያሳምማል፤ ኢማኑ ይቀንሳል፤ የኋላ ኋላ ከማይውወጣቸው ነገሮች ላይም ይወድቃል።

[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 19/237]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

16 Nov, 12:30


🌼قال رسولُ اللهِ صلَّى اللهُ عليه وسلَّم: "
تَزوَّجوا الوَدُودَ"، أي: الَّتي تُحِبُّ زَوْجَها مَحبَّةً شديدةً...

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

15 Nov, 16:32


🌼يا عائشةُ إيَّاكِ ومُحقَّراتِ الذُّنوبِ فإنَّ لها مِن اللهِ طالبًا
~የአላህ መልእክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ አሏት ለእናታችን አኢሻ ፦

~አኢሻ ሆይ! ወንጀልን አሳንሰሸ ከማየት ተጠንቀቂ።ለሷ ለወንጀሏ አላህ ዘንድ ፀሀፊዎች አላት።

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

15 Nov, 16:26


ተቅዋ የኸይር ዋስትና
~
ሙጊረህ ለዑመር ብኑል ኸጧብ እንዲህ አሏቸው:-

"አላህ አንተን ለኛ እስካቆየልን ድረስ እኛ ኸይር ላይ ነን።"

በዚህን ጊዜ ዑመር እንዲህ አሉ፦

"አላህን እስከፈራህ ድረስ አንተ ኸይር ላይ ነህ!"

📚 [አልበሷኢር ወዘኻኢር : 1/15]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

15 Nov, 16:26


የትኛውም የስራ ማስታወቂያ ሲኖር
በእነዚህ username ሹክ በሉን @twhidfirst1 @Tolehaaaaaa
ማሳሰቢያ  ምንም አይነት ክፍያ አንጠይቅም።
- ስለ ስራው ግን እናጣራለን አጣርተን ቀጥታ በቻናሉ እንለቃለን።
ሼር በማድረግ አሰራጩት
የስራ ማስታወቂያ የሚለቀቅበት ቻናል
👇👇👇👇👇👇👇👇
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

15 Nov, 03:50


.           ሱራ አል-ካህፍ

46.ገንዘብና ወንዶች ልጆች የቅርቢቱ ሕይወት ጌጦች ናቸው፤ መልካሞቹም ቀሪዎች (ስራዎች) ጌታህ ዘንድ በምንዳ በላጭ ናቸው፤ በተስፋም በላጭ ናቸው።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

15 Nov, 01:38


☀️አያሙል ቢድ ፆም ነገ ይጀመራል የቻለ ይፁም ያልቻለ ሌሎችን ያስታውስ።

⇛ አያሙል ቢድ _ጁምዓ 13
⇛ አያመል ቢድ _ ቅዳሜ  14
⇛ አያመል ቢድ _ እሁድ 15
ደስ ሲል ከዛ ሰኞ ነው
ዛሬ የጾማችሁ አምስት ቀን ተከታታይ ይሆንላችኃል ልጆችዬ ጹሙ እሺ ጾም ጋሻ ነው

🔸قال ﷺ : إذا صمت من الشهر ثلاثًا، فصم ثلاث عَشْرَةَ، وأربع عَشْرَةَ، وخمس عَشْرَةَ.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

14 Nov, 20:01


🔖ገለልታዉ ይሻላል
~
ከሰዎች ትርምስ  ከወሬ ጋጋታ
ቆጠብ ማለቱ ይሰጣል እርጋታ

ወሬዉ አድማጭ የለዉ  ሁሉ ተናጋሪ
ቃላቱ መብዛቱ የሌለዉ ተግባሪ
ከዚችም ከዛችም ቃላቱ ይዘንባል

~ታዳ
,
ጮሌ የገባዉ ሰዉ አፉን  ይሰትራል
የቃላትን መአት ዝምብሎ ያደምጣል
በግርምት  እያየ አጀብ ጉድ ይሰኛል
ብዙዉን ታዝቦ  ብዙን ይቃኘዋል

~ከዛም
,
,
እያለ ይሄዳል..እንደዉ ከዚህ ሁሉስ ገለልታዉ ይሻላል

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

13 Nov, 15:20


🔖አላህን ለመፍራት እዉቀት ትልቅ ሰበብ ነዉ።
🌻إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ
 [فاطر:28]

አላህን የሚፈሩት እዉቀት ያላቸዉ ሠዎች ናቸዉ።

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

13 Nov, 13:04


﴿ ذَرهُم يَأكُلوا وَيَتَمَتَّعوا وَيُلهِهِمُ الأَمَلُ فَسَوفَ يَعلَمونَ ﴾ 

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

13 Nov, 04:25


ይህ ቻናል በሀገር ውስጥ ያሉ ስራ አጥ
            ወንድም እህቶች
በአላህ ፍቃድ  የስራ ማግኛ ሰበብይሆን ዘንድ
ታስቦ የተከፈተና የስራ ማስታወቂያ የምንለቅበት
አዲስ ⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ነው 

🔗ተቀላቀሉ
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0
t.me/+xN5NLvItoepjYjc0

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

12 Nov, 20:15


ከመተኛት በፊት እና ከእንቅልፍ ሲነቁ የሚባሉ ዚክሮች ልዩ ሚስጥር አላቸው።ለ አሏህ ያለንን ልዩ ፍቅር ያስታውሰናል።

በሌላ አባባል "ጌታዬ ሆይ! ስተኛ መጨረሻ ማስታውስህ አንተ ነው። ስነቃም መጀመሪያ ማስታውስህ አንተኑ ነው።" እያልን ነው።

ኢብኑ ረጀብ رحمه الله

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

12 Nov, 16:36


በቀዝቃዛ ምጣድ ላይ ዳቦ አትጋግር!
~~
ወንድሜ እስቲ  ልጠይቅህ፤ ፀጥ ረጭ ባለች ውድቅት ሌሊት ላይ ሁሉም በተኛበት ሰዓት ተነስተህ ለጌታህ የሰገድክባቸውን ቀናት ታስታውሳለህ?  
በመስጂድ ውስጥ ማንም በሌለበትስ ብቻህን ሁነህ ቁርአን አኽትመህ የተደሰትክበት ቀን ትዝ ይልሃል?
የምትሰራውን ሰናይ ተግባር ከእይሉኝና ከይስሙልኝ  የደበቅክበት ቅፅበትስ ይታወስሃል?
  የህይወት ምዕራፍ  አንድ አይደለችምና ቆም ብለህ ነፍስህን ጠይቃት!  ከዚያም መልሱን ንገራት! 

     ታላቁ ታቢዒይ ረቢዕ ቢን ኹሰይም ሁል ቀን ቤቱ ውስጥ ቁርአን ይቀራ ነበር። ሰዎች ወደ ቤቱ ሲገቡ ቁርአኑን በጨርቅ ይሸፍነዋል።
ለምን መሰላችሁ? አቀራሬ ጥሩ አይደለም ብሎ ትችትን ፈርቶ  እንዳይመስላችሁ፤ መልካም ስራውን ከሰዎች መደበቁ ነው!
አይገርምም?  እየቀራ ከሚያየው ሰው ይደበቃል!
   እኛ ደግሞ ሳንቀራ የሚያወድሰንን ፍለጋ ስንኳትን፤ ስንቀራም የሚያሞካሸንን ክጀላ ስንተጋ ከርመናል።
  አስተውል!  እነርሱ የሰሩትን መልካም ስራ ሰርተው ልቦናቸው ስጋት ይገባዋል! ቅንነታቸው ተግባራቸውን ሲያረጋግጥ ኖረዋል። ሰው ሲባል ከማየትና ከመስማት በስተኋላ ወይ ማወደስ አሊያ አቃቂር አውጥቶ መተጨት እንጂ ምንም ማድረግ እንደማይችል ተገንዘበዋልና ለሰዎች የጎመን ፍሬ ያህል ደንታ የላቸውም!
  እኛጋ ስንመጣ ደግሞ በቀዝቃዛ ምጣድ ዳቦ የሚጋግር ሞልቷል፤ የጀነትን ሰርተፍኬት ከሰው ውዳሴ የሚፈልግ በዝቷል! ይህንንም አስመልክቶ፡
  «ለአላህ በኢኽላስ የሚሰራ ሰው ምንኛ አነሰ!» ይሉናል ኢብኑል ጀውዚ!
አደራህን! ስለ ሰዎች አትጨነቅ ምንም አይፈይዱህም፤ ስራህን በቅንነትና በታማኝነት ለጌታህ ብቻ አጥራ!
t.me/abdu_rheman_aman

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

11 Nov, 23:43


سورة : مريم

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

11 Nov, 20:59


=

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

11 Nov, 19:54


ያላገባሽው እህቴ ስሚኝማ

ማግባት ፈልገሽ አሏህ አላሳካልሽም አልተሳካልሽም አይደል አትሰቢ አሏህ የፃፈው ሰአት ሲደርስ ላንቺ ያለው የትም አይሄድ ።
ግን ትዳር ህወትሽ ነው  የዱንያ የሚበልጠው የዕድሜሽ ቀይታሽ ሊሆን ይችላል ስለዚህ በአንቺ ምርጫ ሳይሆን አሏህ ህይወትሽን የሚሳምረውን በዱንያም በአኼራም ስኬታማ የሚደርግሽን  ምልካሙን ባሪያውን ይስጥሽ ዘንድ ከዱአ እዳትቦዝኒ ! አንቺም መልካም ሆነሽ በመገኝት ላይ ጠክሪ!

ጌታችንም  እንዲህ ብሎናል
وَٱلطَّیِّبَـٰتُ لِلطَّیِّبِینَ وَٱلطَّیِّبُونَ لِلطَّیِّبَـٰتِ

ትልቁ ልነግርሽ የምፈልገው!
ያለሽበት ጊዜ ሀላፍትና የሌለብሽ ጊዜ  ነው።
ላጤ ሆነሽ እስከምታገቢ  ያለሽበት ጊዜ ካገባሽ ብኃላ  አታገኝውም።

አግብተሽ ልጅ እስከምትወልጅ ያለሽበትን ጊዜ ከወለድሽ ብኃላ አታገኝውም።

√ ወደ ትዳር ስገቢ ብዙ ሀላፍትና ትቀበያለሽ ሀላፍትናን መወጣት ውዴታ ብቻ ሳይሆን ግዴታሽ ነው ስለዚህ ስበቡን እያደረሽ ያለሽበትን የጊዜ ኒዕማ በኸይር ነገር ተሯሯጪበት። ዛሬ ያለሽበትን ጊዜ መጠቀም ካልቻልሽ ነገ እናትነት ደረጃ ስደርሽ እቅልፍም በምፈልጊበት ጊዜ መታኛት አትችይ።
ዛሬ ጊዜሽን በአግባቡ መጠቀም ከቻልሽ ነገም ጠክረሽ ሀላፍትናሽን ትወጫለሽ።

ይሄን ስልሽ  ትዳር እና ልጅ አጅር አያስገኝም ማለቴ እዳልሆነ ይገባሻል ጊዜሽን በደብ ተጠቀሚ ብኃላ አታገኚውም ለማለት እንጅ! ሚስት ሆነሽ ባልሽን ስታሰደስች እናት ሆነሽ ልጅ ወልደሽ በመልካም አስተዳደግ ስታሳድጊ  አጅርሽ እጥፍ ድርብ ነው አሏህ ከመልካሞቹ  ያድርገን።

ትዳር መልካም የትዳር አጋር ለስጠው ሰው መተዛዘን ደስታ ......የሞላበት ከድካምሽ እርፍ የምትይበት የማይጠገብ ሀያት  የዱንያ ጀነት ነው።ልጆች ደሞ የትዳር ማጣፈጫ የህይወት ድምቀት  የድካምሽ ፍሬዎች ናቸው።
እናም አግቡ ውለዱ ጊዜው እስከሚደርስ ባላችሁበት ነገር ላይ የዘገየው ለኸይር ነው እያላችሁ ጊዜችሁን በመልካም ነገር ተጠቀሙ።
ሁሉም ሰው  አሏህ መርጧ ያስቀመጠበት ሁሉም ነገር  ኸይር ነው አልሐምዱሊላህ።

  የዑመሩ እናት🖋

=

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

11 Nov, 04:43


~የዱኒያ ህይወት እዉነታዋ ይህ ነዉ

~
         t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

10 Nov, 13:17


የአላህ መልእክተኛ ﷺ ለሙአዝ እንዲህ ብለውታልል።

~ሙአዝ ሆይ! በአላህ ይሁንብኝ እወድሀለሁ። ሙአዝ ሆይ! አንድ ነገር አደራ ልበልህ ከእያንዳንዱ ሰአት በኋላ "اللهم أَعني على ذڪرك، وشڪرك، وحسن عبادتك""አላህ ሆይ! አንተን በማውሳት፣ በማመስገንና ኢባዳን በማሳመር ላይ አግዘኝ ማለትን እንዳትተው።"
📚صحيح الجامع للألباني ٧٩٦٩
~
   t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

10 Nov, 13:13


~በባዶ እግር መሄድ ሱና ነዉ

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

09 Nov, 17:20


~ንግግርህን ገምግም፣ ዉሎህን ፈትሽ፣ የሰደድከዉን መልዕክት መልሰህ እይ፣ ከአንደበትህ የወጣው ንግግር ምን እንደነበር አስታውስ፣ በቅድሙ ቻት ልክ ነህ ወይ፣ የፖሰትከው ነገርስ ካንተ ይጠበቃል፣ ሞባይልህ ውስጥ ምን አለ? ጥሪውስ ምን ይላል? ሴቭ ያረግካቸው ነገሮች ምንድነው ጥቅማቸው? ቪዲዮና ፎቶዎችስ ትክክል ናቸው ወይ? ከሚያሳፍር ነገር የፀዳ ነውን? እነኚህን ጥያቄዎች መልሰህ እይ፣ አሁኑኑ ራስህን ገምግም…

ሞባይልህ አሁን ባንተ እጅ ሊኖር ይችላል፡፡ በማን እጅ ሆኖ እንደሚነጋ ግን አታውቅም፡፡  

ካመሸህ አነጋለሁ ብለህ በርግጠኝነት አትጠብቅ፤ካነጋህም አመሻለሁ ብለህ እርግጠኛ አትሁን፡፡በንጋትና ምሽት፣ በምሽትና ንጋት መካከል ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

=t.me/AbuSufiyan_Albenan

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

09 Nov, 15:43


🔖አላህ ዘንድ ሰዎች የበላይ የሚሆኑበት የእውቀት ዘርፍ# ሸሪዓዊ እውቀት ነው።

ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ مِنكُمْ وَٱلَّذِينَ أُوتُوا۟ ٱلْعِلْمَ دَرَجَٰتٍۢ ۚ

አላህ ከናንተ እነዚያን ያመኑትንና እነዚያንም ዕውቀትን የተሰጡትን በደረጃዎች ከፍ ያደርጋል፡፡

(ሙጃዲላ 11)

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

09 Nov, 01:02


وخَيرا في كل أمرٍ ننتظِرُه يا الله!

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 20:03


❀•°

إليكي أخيتي.....

.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 18:29


~"አላህ ከከለከለው ነገር እይታን ዝቅ ማድረግ፣ የአላህን ዉዴታ ይወርሳል።"

=

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 17:54


🔖ኢማም ኢብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ ይላሉ፦

"وقـد ضمـن اللَّـه سبحانـه لڪلّ مـن عمـل صالحـا أن يحييـه حيـاة طيبـة وهـو صـادق الوعـد لا يخلـف وعـده".

አላህ መልካምን ለሰራ ሰው ሁሉ ያማረ ህይወት እንደሚያኖረው ዋስትና ሰጥቶታል የእሱ ቃል እውነት ነው ቃሉን አያፈርስም

📚[አዳእ ወደዋእ]

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 17:52


🔖ሀሰነል በስርይ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብሏል።

አላህን ሳይታመፅበት ያለፈ ቀን ሁሉ ኢድ ነው። አንድ ሙእሚን አላህን በመታዘዝ፣ እሱን በመዘከርና በማመስገድ ያሳለፈው ቀን በሙሉ ኢዱ ነው።
📚لطائف المعارف لابن رجب

=
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 16:46


☑️ አላህን መፍራት የሪዝቅ መሠረት ነዉ።
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
🔍
ሀሳቡና ጭንቁ ዱንያ ብቻ የሆነ ሰው፣ ጉዳዩን አላህ ይበታትንበታል፣ ድህነቱን በዓይኑ መሀል ያደርግበታል፣ ከዱንያም የተቀደረለት እንጂ አይመጣለትም።

🔍 ሀሳቡና ጭንቀቱ አኼራ የሆነ ሰው አላህ መብቃቃትን በቀልቡ ያደርግለታል። ጉዳዩን ይሰበስብለታልዱንያ የግዷ ወደሱ ትመጣለች።

አድምጧት ጣፋጭ ምክር !
=
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 14:56


በስደት ያላችሁ በተለይ ሴቶች ወላሒ በጣም ተጠንቀቁ በጣም ነገሩ ከሚባለውም በላይ እጅግ የከፋና የከረፋ ሆኗል።

.....ዝሙት⁉️

ነቄነት ተደርጎ ዝሙት እንደ ሀላል፡
መብቴ ነው ሲባል እንደምን ያስጠላል!?
ጥርስን ካልሸፈነ ምን ይሰራል ከንፈር፡
ነውራችን ከረፋ ኸረ ተው እንፈር⁉️
ማን ከማን ተሽሎ ማንን ነው ምታሙት፡
የእለት ከእለት ስራ ሰርክ ሆኗል ዝሙት‼️

.......✍️ኑር

ትላንት ከዝሙት ስለመጠንቀቅ ማሳሰቢያ የፃፍኩት ዐረብ ሃገር ላይ እየተፈፀሙ ስላሉ ጥፋቶች የሚገልፁ አስደንጋጭ ጥቆማዎችን ከተለያዩ ወንድሞች ስላየሁ ነው። ከላይ ያያያዝኩት መልእክት ወንድማችን ከኔ ፖስት ስር ያስቀመጠው እጅግ አስደንጋጭ ትዝብት ነው። እንዲህ አይነት ወጥመዶች ወንጀሉ መቋጫ እንዳይኖረው ነው የሚያደርጉት። የመፍትሄው ሁሉ ቁንጮ አላህን መፍራት ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

08 Nov, 02:44


أفضل طريقة لتثبيت القرآن....

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Nov, 13:07


🔖እውቀትን መፈለግ ያለው ቱርፋት
~ ~
የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል


👉እዉቀትን በመፈለግ ላይ የተጓዘ ሰዉ አላህ  ለሱ የጀነትን መንገድ ያገራለታል ።

~የአላህ መልክተኛ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል

~አላህ መልካም የሻለት የሆነ ሰው ድኑን ያስገነዝበዋል

👉በተቃራኒዉ ሼር የሻበትን ሠዉ ድንን አያዉቅም።ዲንን  ለማወቅ ችልተኛ ይሆናል።

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

07 Nov, 02:32


قال تعالى :
{وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً إِنَّ فِي ذَلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ}.
[سُورَةُ الرُّومِ: ٢١] .

فَجَعَلَ الْمَرْأَةَ سَكَنًا لِلرَّجُلِ، يَسْكُنُ قَلْبُهُ إِلَيْهَا، وَجَعَلَ بَيْنَهُمَا خَالِصَ الْحُبِّ، وَهُوَ الْمَوَدَّةُ الْمُقْتَرِنَةُ بِالرَّحْمَةِ.

[الداء والدواء ٢٣٧].

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Nov, 19:14


ማራኪ ቲላዋ
የቁርአን ግብዣ

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

06 Nov, 14:58


ሙሐደራ 215 

ለ ቁርዓን ሓፊዦች የተደረገች ምክር

🚦🚦 አሸዋሜዳ በሚገኘው የ ወንድማችን ሳዳት ከማል የ ቁርዓን ሒፍዝ ማእከል ላይ የተደረገ  ነሲሃ ነው  ።

🎤 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)

https://t.me/UstazKedirAhmed
https://t.me/UstazKedirAhmed

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Nov, 20:14


🌻فَإِنَّ اصِّدْقَ طُمَأنينة وإِنَّ الكزِب رِيبة
📚رواه الترمزي

~እዉነት የአእምሮ እርፈት እና መረጋጋትን ይሠጣል። ዉሸት ደግሞ የአእምሮ መረበሸ እና መጥፎ ጥርጣሬን ያስከትላል።

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Nov, 17:59


⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️⚪️ ባለቤቶች

የሱና ቻናል ተደራሽነት ይበልጥ ይሰፋ ዘንድ
የቻናል ሊንክ መላክ ትችላላችሁ  ⚡️

✍️መስፈርት 1/ :- የሱና ቻናል ሊሆን ስለማጣራ⚫️
✍️መስፈርት2/ ከ1k member በላይ 🔤 ከዛበታች
✍️መስፈርት 3/:-  ቻናሉን አይቼ አሳውቃቹኋለሁ

🚫ግሩፕ አልቀበልም

⭐️ @twhidfirst1
🌟 @twhidfirst1

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

05 Nov, 11:24


ለምንድን ነው ስደውል ያላነሳሽው?
አስተማሪ ታሪክ
~
ለሆነ ጉዳይ ለሶስት ቀናት መንገድ ወጣሁ። ሌላኛው ሃገር እንደደረስኩ ሚስቴንና አንድ ልጄን ደህንነታቸውን ለማስረገጥ ደወልኩ። ከዚህ በፊት ከነሱ ተለይቼ አላውቅም። እነሱም መራቄን አያውቁትም። ካገባሁ ሶስት አመቴ ነው። የሆነ ሆኖ ስልኬ አልተነሳም። ስልኬ ከእጄ ሳይነጠል ሶስት ቀናት አለፉ። ያለ ግነት በየ እሩብ ሰዓቱ ቢበዛ በየ ግማሽ ሰዓት እደውላለሁ። ምላሽ የለም።

በሃይለኛ ተበሳጨሁ። ወንድሜ እና እህቴ ላይ ደወልኩ። የትንሿን ቤተሰቤን ደህንነት እንዲያረጋግጡልኝ ጠየቅኳቸው። ሰላም እንደሆኑ ነገሩኝ። አላመንኳቸውም።

የሚስቴ እናት (አክስቴ) ላይ ደወልኩ። ሰላም እንደሆኑ ነገረችኝ። ስልካቸውን እንደምጠብቅ ነገርኳት። ብጠብቅ ብጠብቅ አንድም የሚደውል የለም።
ሶስቱ ቀናት ረጃጅም ሶስት ወራት ያክል ሆነው አለፉ። አንዳንዴ ቁጣዬ ከውስጥ ሲገነፍል ይሰማኛል። ሌላ ጊዜ በሁኔታው በጣም እየተገረምኩ ምክንያቱን ለማወቅ እሞክራለሁ።

ሸይጧን አስፈሪ ጉትጎታዎችን ደግሞ ደጋግሞ ያመጣብኛል። ቀናቱ አለፉ። ወደ ሃገሬ ተመለስኩ። እግሬ እንደረገጠ ወደ ቤቴ ነበር የበረርኩት። እንደደረስኩ በሩን አንኳኳለሁ። እሱም ሳይበቃኝ ደወሉን ላይ በላይ እደውላለሁ። ባለቤቴ በሩን ከፈተች። ከነ ሙሉ ውበቷ፣ ከነ ሙሉ ድምቀቷ። ባማረ በደመቀ ሁኔታ ተቀበለችኝ። ከባድ አጋጣሚ ነበር። ልጄ ከኋላዋ አለ። አይኖቹ በደስታ ይጨፍራሉ። ሊያቅፈኝ እየሮጠ መጣ። እኔ እንደደነዘዘ ሰው ሆኛለሁ። ሰበቡም ጠፋኝ። በፍጥነት በቁጣዬ ቦታ ግርምት ተተካ።

ባለቤቴን የዚህ ሁሉ ቸልትኝነት ምክንያቱ ምን እንደሆነ ጠየቅኳት። ጉዞዬን አቋርጬ በፍጥነት ልመለስ ተቃርቤ ነበር። አጉል ጥርጣሬ ከያቅጣጫው ወሮኝ ነበር።
ባለቤቴ ተረጋግታ መለሰችልኝ። "ለእናትህ ደውለሃል?" አለችኝ። ለምን እንደጠየቀችኝ ምክንያቷ ባይገባኝም እንዳልደወልኩ ነገርኳት። ንግግሯ ገዳይ ነበር ። እንዲህ አለችኝ፡ "በነዚህ ቀናት ውስጥ ስሜትህ ምን እንደሆነ አየህ አይደል? የእናትህም ስሜት ይሄው ራሱ ነው፣ ለቀናት ሳትደውልላት ስትቆይ። ናፍቆት ለብልቧት፣ ስጋት ገብቷት እሷ ካልደወለች በቀር አንተ ደውለህ ድምጿን አትሰማም። ይሄን ጉዳይ በተደጋጋሚ ላስረዳህ ሞክሬያለሁ። የምትረዳ ግን አልሆንክም። ክቡር ባለቤቴ! ከዚህ የተሻለ መልእክቴን የማደርስበት መንገድ አላገኘሁም።

እድሜዋ ትንሽ ዐቅሏ ግን ትልቅ የሆነችዋን ሚስቴን አፈርኳት። አንገቴን ደፋሁ። ትምህርቱ በሚገባ ነው የደረሰኝ። የመኪናዬን ቁልፍ እያቀበለችኝ ወደ ጀሮዬ ጠጋ ብላ "ጀነትህ እየጠበቀችህ ነው" አለችኝ።

እድሜ ልኬን የማልረሳውን ትምህርት ከጠቢቧ ሚስቴ ተምሬ ወደ መጀመሪያዋ ውዴ ወደ እናቴ ሄድኩኝ። ፀፀት በማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት ነፍሴን ስላተረፈችኝ ውለታዋን መቼም አልረሳም። ለዚች ጠቢብና አስተዋይ ሚስት ምስጋና ይገባታል። አሳምራ ኮትኩታ ላሳደገቻት እናቷ ምስጋና ይገባታል። እሷን ለመረጠችልኝ እናቴ ምስጋና ይገባታል።

እሷን ሰበብ አድርጎ በእዝነቱ ከእንቅልፌ ያነቃኝ ጌታ ምስጋና ይገባዋል።

እናቴ! እናታቶቻችሁ ! በዱንያ ያሉ ጀነቶቻችን ናቸው። ሌላው ቢቀር በየቀኑ በመደወል እንኳ ቢሆን አትርሷቸው። ይሄ ትንሹ ነገር ነው። ልቦቻቸው እኛን ይጠብቃሉ። ለኛ ዱዓእ ያደርጋሉ። በየ ሰዓቱ ስለኛ ይጨነቃሉ። እያሰቡ እየተጨነቁም ደጋግመው በመደወል እንዳይረብሹን በመስጋት ከመደወል ይታቀባሉ። ባሎቻችሁን፣ ሚስቶቻችሁን ወላጆቻቸውን እንዲያስቡ በማስታወስ አግዙ።

ከ0ረብኛ የተመለሰ
የብዙዎቻችን በተለይም የወንዶች ችግር ነውና እንድንማርበት ብታሰራጩት ባረከላሁ ፊኩም።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥቅምት 26/ 2017)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Nov, 19:55


ነፍሱ ከዒባዳ መሰላቸቷን ያስተዋለ፤ኢስቲግፋር ያብዛ። ማንኛውም ሰው ዒባዳን መፈፀም የሚሳነው በሰራው ወንጀል ምክንያት ነው።
أَسْتَغْفِرُ اللَّهَ الْعَظِيمَ الَّذِي لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ ، وَأَتُوبُ إِلَيْهِ.
~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Nov, 13:31


قهر الهوىٰ= الجنَّة.

﴿وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَى ۝ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَى﴾ .

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

04 Nov, 10:57


እውቀትን ከመፈለግ ከሚያግዱን ነገራቶች በጥቂቱ ....?

🎙በኡስታዝ አቡል አባስ ሓፊዘሁላህ

t.me/Darutewhide

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Nov, 20:00


🔖ጣፋጭ ቲላዋ
~
~አንተ የወደድከውን ሰው ፈጽሞ አታቀናም፡፡ ግን አላህ የሚሻውን ሰው ያቀናል እርሱም ቅኖቹን ዐዋቂ ነው፡፡

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Nov, 19:01


🔍በላጩ ሰደቃ
🔹 قال  النبي ﷺ :
" أفضلُ الصدَقةِ سَقْيُ الماءِ. "
[ صحيح الجامع {1113}] 📚

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Nov, 18:12


«ነብያችን ሶለሏሁዓለይሂወሰለም እንዲህ አሉ : ዱንያ የተረገመችናት በውስጧም ያለው የተረገመነው አሏህን እሚያወሳ ሲቀር አሉ ታዳ እኛ ከየትኞቹነን አሏህ በቀን ስንት ግዜ እናወሳለን ሁላችንም እራሳችንን እንጠይቅ !!

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

03 Nov, 12:22


በሰማነው መጠቀምና መስራት

ሑዘይፋ መስጂድ የቀረበ ሙሓደራ

🎙 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር

🔗 t.me/Achachir_mkroch

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

02 Nov, 18:24


أكثِر من الإستغفار ما استطعت!
‏فإن الإستغفار  :
‏-يفتح أبواب السماء
‏-سبب من اسباب زيادة الرزق
‏-يفرّج الهمّ والغمّ ويدفع البلاء

‏أستغفرالله العظيم الذي
لا إله إلاّ ‏هو الحي القيوم وأتوب إليه.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

02 Nov, 17:52


~ሁሌም ካንተ ጋር ነኝ፣ ፈፅሞ አልለይህም ለሚሏችሁ ...ሁሌም ከኛ ጋር የሚሆነው አላህ ብቻ ነው በሏቸው።

በዚህች አጭር የዱንያ ላይ ዕድሜያችን ከስንቱ ጋር ወዳጅነት ጀምረን፤ ስንትና ስንት ሰው ወደኋላ ጥለን እዚህ ደርሰናል።ሰው ይረሳል። ይረሳና ሁሉንም ነገር ይረሳል።

ቢሆንም በሂደትም ቢሆን መርሳት የማትፈልጉት ሰው በሕይወታችሁ ውስጥ ይኖራል።ሆነብላችሁ ሳይሆን እረስታችሁ እንዳታጡት አልፎ አልፎ «እባክህን አለህ ወይ» በሉት።
=t.me/AbuSufiyan_Albenan

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

02 Nov, 17:37


ከሰዎች ምንንም ነገር ላለመከጀል ከቻልክ አድርገው።አንተ ኮርተህም ሆነ ዘንተህ የምትኖረው በነገሮችህ ላይ ሁሉ በራስህ የተብቃቃህ ሆነህ ከሰው የማትከጅል ስትሆን ነው።

ጌታዬ ሆይ በነገራቶቼ ላይ ሁሉ በአንተ የተብቃቃሁ ቁጥብ ባሪያህ አድርገኝ።

አቡ ኡበይዳ
t.me/AbuOubeida

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

02 Nov, 03:44


ﺛﻼﺙُ ﻣﺸﺎﻛﻞ ﺗُﺤﻞ ﺑﺜﻼﺙِ ﻭﺳﺎﺋﻞ:

ﺍﻷﻭﻟﻰ: ﺇﺫﺍ ﺍﺑﺘُﻠﻴﺖ ﺑﺤﺐ ﺍﻟﺸﻬﻮﺍﺕ.
- ﺍﻟﺤﻞ: ﺭﺍﺟﻊ ﺣﺴﺎﺑﺎﺗﻚَ ﻣﻊ ﺍﻟﺼﻠﻮﺍﺕ.
- ﺍﻟﺪﻟﻴﻞ: ﻗﺎﻝ ﺗﻌﺎﻟﻰ: ﴿فَخَلَفَ مِن بَعْدِهِمْ خَلْفٌ أَضَاعُوا الصَّلَاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَوَاتِ فَسَوْفَ يَلْقَوْنَ غَيًّا﴾.

ﺍﻟﺜﺎﻧﻴﺔ: ﺇﺫﺍ أﺣﺴﺴﺖ ﺑﺎﻟﺸﻘﺎﺀ ﻭﻋﺪﻡ ﺍﻟﺘﻮﻓﻴق.
- ﺍﻟﺤﻞ: ﺭﺍﺟﻊ ﺣﺴﺎﺑﺎﺗﻚَ ﻣﻊ ﺃﻣﻚَ.
- الدليل: ﴿وَبَرًّا بِوَالِدَتِي وَلَمْ يَجْعَلْنِي جَبَّارًا شَقِيًّا﴾.

ﺍﻟﺜﺎﻟﺜﺔ: ﺇﺫﺍ ﺷﻌﺮﺕ بالاﻛﺘﺌﺎﺏ ﻭﺍﻟﻀﻨﻚ.
- ﺍﻟﺤﻞ: ﺭﺍﺟﻊ ﺣﺴﺎﺑﺎﺗﻚَ ﻣﻊ ﺍﻟﻘﺮﺍٓﻥ.
الدليل: ﴿وَمَنْ أَعْرَضَ عَن ذِكْرِي فَإِنَّ لَهُ مَعِيشَةً ضَنكًا﴾.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Nov, 22:02


🌷 اسمـع وتدبـر

~ይህ ቁርኣን ወደዚያች እርሷ ቀጥተኛ ወደ
ኾነችው መንገድ ይመራል፡፡ እነዚያንም በጎ የሚሠሩትን ምእመናን ለእነሱ ታላቅ ምንዳ ያላቸው መኾኑን ያበስራል፡፡

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Nov, 16:26


የደዕዋ ማስታወቂያ
~
የፊታችን እሁድ ጥቅምት 24/ 2017 ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ በሚገኘው ሑዘይፋ መስጂድ የደዕዋ ፕሮግራም ይኖራል። ቆይታችሁ ከኛ ጋር ይሁን

1- ኸዲር አሕመድ ከሚሴ
2- ዐብዱልፈታሕ ጀማል
3- ሙሐመድ ሲራጅ
4- አቡል ዐባስ
5- ሳዳት ከማል

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

01 Nov, 02:53


አንተስ ማንን ነው የምትወደው⁉️

አነስ ኢብኑ ማሊክ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል:- "ከእስልምና ፀጋ ቀጥሎ መልዕክተኛችን ﷺ "የትኛውም ግለሰብ አኼራ ላይ ከሚወደው ጋር ነው" ከሚለው ንግግራቸው የበለጠ የተደሰትንበት  የለም እኔ አላህን፣መልዕክተኛውን፣አቡበክርን እና ኡመርን እወዳለሁ የነሱን አምሳያ ስራ ባልሰራ እንኳን በውዴታዬ ከነሱ ጋር እሆናለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።"(ሙስሊም ዘግበውታል:2639)

አላህ ደጋጎችን የምንወድ ያድርገን!

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Oct, 23:11


- اللّـهُــمَّ إنِّــــي أسألُـكَ الهُـدىٰ والتُّقـىٰ والعَفَــافَ والغِــنَىٰ.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

31 Oct, 14:43


🔖ወቅት በሄደ ቁጥር ቀን በቀን በተተካ ቁጥር #ሳምንቱ በሳምንት ወሩ በወር በተተካ ቁጥር አካል እየደከመ ይመጣል። ስለዚህ ለወቅታችን ስስት ሊኖረን ይገባል ።ወቅት በሄደ ቁጥር እኛ ወደአጀላችን እየቀረብን ነዉ።

👉ወቅትን በተመለከተ ታላቁ አሊም ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ።

أن إضاعة الوقت اشد من الموت ، لأن إضاعة الوقت تقطع عن الله و الدار الآخرة ، والموت يقطع عن الدنيا وأهلها)
~ወቅትን (ግዜን ማባከን ከሞት የበረታ ነዉ። ምክንያቱም ወቅትን ማባከን  ከአላህና ከአኼራ ሀገር ትቆርጥሀለች።ሞት ግን ከዱኒያና ከባለቤቶቿ ትቆርጥሀለች።

ግዜ ሊሳሱለት የሚገባ ታላቅ ንብረት ነዉ ።
ወቅት ጀነትን መግዣ ነዉ።

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Oct, 21:00


🔖የመኝታ ሰርዓቶች!!
〰️〰️〰️〰️
➡️ከመተኛት በፊት በር እቃዎችን መዘጋጋት መከዳደንና እሳት ማጥፋት፣-

#ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል እቃዎችን ከዳድኑ ፣ኮዳዎችንም እሰሩ ፣በሮችንም ዝጉ ሰይጣን የታሰረን አይፈታም። የተዘጋን በር አይከፍትም፣ የተከደነንም አይከፍትም።መክደኛ ካጣችሁ እቃችሁ ላይ እንጨት አድርጋችሁ ቢሆን እንኳን የአላህን ስም ጥሩበት ።እሳትንም አጥፉ አይጥ ቤታችሁ ታቃጥላለች ።
📚ሙስሊም ዘግበዉታል

➡️ጀናባ ከሆነ ውዱዕ አድርጎ መተኛት፣-
አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እንድህ ብላለች ነብዩ ስለሏ አለይሂ ወሰለም ጀናባ ሆነው መተኛት ሲፈልጉ ውዱዕ ያደርጉ ነበር።


📚አህመድ ነሳኢይ ኢብኑ ማጃህ ዳርቁጥኒይ ወግበዉታል)

➡️ፍራሹን ጠረግ ማድረህ፣-
ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ለመተኛት ወደ ፍራሻችሁ ስትቀርቡ በሽርጣችሁ ውስጠኛውን ክፍል ሶስት ግዜ ጠረግ አድርጉት።

📚ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበዉታል)

➡️ቤት ውስጥ ለብቻ አለመተኛት፣-
አብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዳስተላለፉት ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም ለብቻ መተኛትና ለብቻ ጉዞ መውጣት ከልክለዋል።

📚አህመድ ዘግበዉታል)

➡️ውዱዕ ማድረግ

ነብዩ ስለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል ወደ መኝታ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርግ።

📚ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበዉታል)

➡️የመኝታ አዝካሮችንና የተወሰኑ የቁርአን አንቀጾች ማንበብ፣-

🔖ከቁርአን
ፋቲሃ ፣አየተል ኩርሲይ ፣ የበቀራ የመጨረሻ ሁለት አንቀጾች ፣ ሱረት ካፊሩን ፣ሱረት ኢኸላስ ፣ሱረት ፈለቅ፣ ሱረት ናስ፣ ከተቻለ ሌሎችም የአላህ መልእክተኛ ሲተኙ ያነቧቸው እንደነበረ የተዘገቡ አንቀጾችን ማንበብ።

አኢሻ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ
እንዳስተላለፈችው፣የአላህ መልእክተኛ ዘወትር ሌሊት ሲተኙ ፣

👈قُلْ هُوَ ٱللَّهُ أَحَدٌ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلْفَلَقِ
👈قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ ٱلنَّاسِ
እነዚህን በማንበብ እጃቸው ላይ  ሶስት ሶስት ግዜ ተፍተው ከራሳቸውና ከፊታቸው በመጀመር የደረሱትን ያህል አካላቸውን ያብሱ ነበር።

🔖ከአዝካሮች
👈 بِاسْمِكَ رَبِّ وَضَعْتُ جَنْبِي وَبِكَ أَرْفَعُهُ، إِنْ أَمْسَكْتَ نَفْسِي فَارْحَمْهَا، وَإِنْ أَرْسَلْتَهَا فَاحْفَظْهَا بِمَا تَحْفَظُ بِهِ عِبَادَكَ الصَّالِحِين
▪️ትርጉም ፣- ጌታየ በስምህ ወገቤን አሳረፍኩ በስምህም አነሳዋለው፣ነፍሴን ከያዝካት እዘንላት ፣ከለቀካትም መልካም ባሮችን በምትጠብቅበት ጠብቃት።ሌሎችንም አዝካሮች ማለት--

➡️በቀኝ ጎን መተኛት
ነብዩ ስለሏሁአለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል፣- ወደ መኝታህ ስትሄድ ለሰላት የምታደርገውን ውዱዕ አድርገህ በቀኝ ጎንህ ተኛ።

➡️በሆድ አለመተኛት
ነብዩ ስለሏ ሁአለይሂ ወሰለም በሆዱ ተኝቶ ላዩት ሶሃባ ተነስ ይህ አተኛኝ አላህ የማይወደው ነው ብለውታል።

🔖መተኛትህ ካልቀረ በሱና ላይ ሁነህ ተኛ
👉ሱና የዱንያም የአሔራ ብርሀን ነው።
ህይወት ያለ ሱና ድቅድቅ ጨለማ ነው።

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

30 Oct, 12:09


-لا شيىءَ يعدلُ لذّةَ تلاوةِ القرآن وتدّبرِ آياته!

#تلاوة_مسائية

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 18:30


ኒቋብ ሰውነነትን እንጂ አእምሮን አይሸፍነውም።

በኒቋባችን አንደራደርም።

#ክብር_ለሙተነቂቦች

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 18:28


እህቴ ሒጃቧን እንደለበሰች ትማራለች
በሒጃቧ ደምቃ ትማራለች።

አብሸሩ ጠንክሩልኝ

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 18:24


ልሂድ ወደ ሀገሬ፣ ሻንጣዬን ጠቅልዬ
ሰላትን ለመስገድ፣ እኔ ለአላህ ብዬ

ትምህርት ብሎ ነገር፣ አልፈልግም በቃኝ
ኢስላም ሃይማኖቴን፣ ከሆነ ሚያሳጣኝ

ደግሞ ተራ ነገር፣ እርክስክስ ላለው
ለእውቀት ከሆነ፣ ዲኔ በቂዬ ነው
እስልምና እምነቴ፣ ከምንም በላይ ነው

ኒቃቤን አውልቄ፣ ሰላቴንም ትቼ፣ ዲግሪ ከማመጣ
ፈርዴንም ሱናውን፣ ሁሉንም ከማጣ
ትምህርቱ ይቅርብኝ፣ በአፍንጫዬ ይውጣ

ልሂድ ወደ ሀገሬ፣ ወደ ምኖርበት
ኒቃብ አትልበሱ ሰላት አትስገዱ፣ ወዳልተባለበት

አይደለም መማሩ፣ መኖሩም ይቅርብኝ
አላህን ረስቼ፣ እኔ ህይወት የለኝ
ሂጃቤን ለብሼ፣ ሰላቴን ሰግጄ፣ በዱዓ በርትቼ
መኖር ነው ምፈልገው፣ ከአላህ ተወዳጅቼ፡፡

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 17:39


የመርካቶ የእሳት ቃጠሎ ?

🎙በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሓፊዘሁላህ

t.me/SadatKemalAbuMeryem

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 09:29


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ከዛሬ ጀምሮ እየተቀራ የሚገኘውን የሰዕዲ ተፍሲር በዚህ ቻናል መልቀቅ እንጀምራለን።

https://t.me/SheikhMuhammedZain

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 02:02


~የዱኒያ ስካር እጅጉን የከፋ ነዉ ከኸምር ስካር ...!
~ የኸምር ስካር በመነጋዉ ይለቃል። የዱኒያ ስካር አንዴ የተገባበት እንደሆነ ከባድ ነዉ።

#ከሠለፎች አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ...

እንዲህ አይነቱ ሰዉ ራሱን የነቃ ሆኖ የሚያገኘዉ በሙታን መካከል ነፍሱን ባገኘ ግዜ ነዉ።

ዱኒያ የሚጠገብም አደለም

የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፦
#የአደም ልጅ ሁለት ሸለቆ ወርቅ ቢኖረዉ ሶስተኛ በተመኘለት ነበር ብለዋል ።አፉን ወይም ሆዱን አይሞላዉም አፈር ቢሆን እንጅ ።

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

29 Oct, 01:46


በሙሉ ልብህ ወደ አላህ ዙር ሁሉ ነገር ወዳንተ ይዞርልሃል።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Oct, 16:40


احذفوا تطبيق آيةይህ አፕ ያላችሁ አጥፉት

واستبدلوه بتطبيق وحي
ወሕይ በሚለዉ አፕ ቀይሩት እየተባልን ነዉ

~

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Oct, 16:38


قال الشيخ علي الرملي حفظه الله:

(التغير الذي حصل في تطبيق "آية" تغير منهجي عقدي وقد كنت نصحت به سابقا، والآن لا أنصح به.
أنصح بتطبيق سورة أو وحي وهذا الثاني أسهل في الاستخدامات وخدماته متنوعة ومفيدة).

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Oct, 16:03


ቂርዓት ስከታተል
ለሙራጀዓ ስቀምጥ እንቅልፍ ይጫጫነኛል ምን ባደርግ ይሻላል ????

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Oct, 10:47


ማን ደስተኛ ያደርገኛል ሳይሆን እንዴት ነው ለራሴ ደስታን መፍጠር የምችለው? ብለሽ አስቢ ..... ከሰው ምንም ነገር አትጠብቂ አትደገፊበትም.... የጎደለሽን ሳይሆን የተሰጠሽን እያሰብሽ አሏህን አመስግኚ ፤ ደስተኛም ሁኚ

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

28 Oct, 03:28


የጧት ቁርስ ይዛችሁ ¡

ኑ ቡና እንጠጣ....

=

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Oct, 21:31


5 ወሳኝ ምክሮች በስደት ላሉ ለእህቶች

1--የዋህነት አታብዙ

~እህቶች የዋህነታችሁ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከልኩ በላይ ሲሆን ግን ይጎዳል። ሁሉም ነገር ላይ የዋህ አትሁኑ ።ለምን? እንዴት? ማለት ያለባችሁ ነገር ላይም ለምን በሉ። ብልሆች፣ብልጦች፣አስተዋዮች ሁኑ።

2--ሁሉንም አትመኑ

~ሁሉንም በማመናችሁ ያጣችሁት ነገር የለም? የተጎዳችሁት ነገር የለም?   በእርግጠኝነት ይኖራል ።ጥርጣሬም አታብዙ ግን ሁሉንም አትመኑ።
ልቅ በሆነ እምነት ስንት ነገሮቻቸውን ያጡ አሉ መሰላችሁ። በተለያዩ ሽፋን በተለያዩ ካፓ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉም እወቁ። ተጠንቀቁ።ንቁ። እራሳችሁን፣ገንዘባችሁን ጠብቁ።

3---ስትሰጡ በልክ ስጡ።
መስጠት ያሰጣል።አላህም ይተካል። ጀነትን ያስገኛል።ደስታን ይሰጣል።መካራን  ያስወግዳል። ግን በልክ ይሁን ።

4- ለችግር ግዜ የሚሆናችሁን ገንዘብ አስቀምጡ።
~ሰው ነን መታመም ሊመጣ ይችላል።ስራ መፍታት ሊኖር ይችላል። የተለያዩ ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ለዛ ችግር እዳም እንዳትገቡና እንዳትቸገሩ ለዚህ ቀን የሚሆን ከደሞዛችሁ፣ከጉዳዮቻችሁ ሸረፍ እያደረጋችሁ አስቀምጡ።

5--ደርስ ላይ ፣ቂረአት ላይ በርቱ

~በቻላችሁት አቅም  ግዜያችሁን ለመጠቀም ሞክሩ ።በስደት ቆይታችሁ ባለቻችሁ ሽራፊ ግዜ ለመጠቀም ሞክሩ። ወደ ሀገር ቤት ከተመለሳችሁ በሗላ ሁሉ ነገሩ እንደጠበቃችሁት ላይሆን ይችላል። የመቅራቱም ሞራል እንደዛ ላይሆን ይችላልና  በርቱ።ሸምቱ።
በሶሻል ሚድያው ተጠቀሙ።
          አቡ ሀፍሷ
~››@AbuHafsaYimam
~››@AbuHafsaYimam

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

27 Oct, 14:38


👉አጠር ያለች ምክር የሀሜት
አደገኝነትና አክሳሪነት

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

26 Oct, 20:07


የመኗኗር ጥበብ
~
"ብልህና አስተዋይ ማለት ከቤተሰቡ፣ ከወዳጆቹ፣ ከጓደኞቹና ከጎረቤቶቹ ትንሽ ትልቁን አጥብቆ የማይዝ ነው።"
ኢብኑል ጀውዚይ
[ተህዝቡል ከማል፡ 19/370]
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

25 Oct, 20:02


ዋ  የኛ ነገር

በዘመድ ፣በጉቦ፣በብልጠት የማይታለፍበትና ሁሉም የስራውን ውጤት የሚሰጥበት ከባድ የመከራ ቀን ቂያማ‼️

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

25 Oct, 19:54


https://t.me/nuredinal_arebi?livestream

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

25 Oct, 17:48


በጊዜ ተንፍስ
~
አንዳንድ ወንድሞች በሆነ የዒልም ዘርፍ ከእኩዮቻቸው ሲበልጡ ወይም የበለጡ ሲመስላቸው ትእቢት ሲፈትናቸው ይታያሉ። አንዱን መናቅ፣ ያኛውን ማጣጣል፣ ሌሎችን በመገምገም ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ላይ ይጠመዳሉ።
የሸሪዐ እውቀት አላህን መፍሪያ መሳሪያ መሆኑ ሁሌም ሊዘነጋ አይገባም። ማወቅህ ትእቢት ካወረሰህ፣ በማወቅህ ለሌሎች ንቀትን ካዳበርክ ወላሂ ማወቅህ ጎድቶሃል። ጅህልና ላንተ የተሻለ ነበር። ሰው ቴኳንዶ ሰልጥኖ ቀድሞ ያልነበረውን አደብ ሲላበስ በምናይበት ጊዜ የሆነን ዒልም ሲማር እብሪትና ንቀትን የሚያዳብር ማየት አሳፋሪ ነው።
ወንድሜ ሆይ! መከበር ከፈለግክ ሰዎችን አክብር። ሌሎችን መናቅ ምናልባት ጥቂት ጊዜ ቢያስከብር ነው። ወይ ሰዎች እስከሚነቁ፣ ወይ ደግሞ ማንነትህ እስከሚገለጥ ድረስ ቢዘልቅ ነው። ከዚያስ? ከዚያማ መናቅህ መንናቅን ነው የሚያስከትልብህ። መተንፈስህ ላይቀር አፀፋ ሳያስተነፍስህ በፊት አላህን ፈርተህ ተንፍስ። በጊዜ ተንፍስ። አዎ መተንፈስ ይሻልሃል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

24 Oct, 11:45


ለሆነ ነገር ጉጉ መሆናችሁን ሰዎች ሁሉ እስኪያወቅባችሁ ድረስ ስለዚያ ነገር አብዝታችሁ አታንሱ፡፡ ገንዘብ፣ ትዳር፣ ዝና … ጥቂቶች ናቸው፡፡
ምኞታችሁን ለአላህ ብቻ ንገሩ፡፡ ሰው ፊት አንድን ነገር አብዝቶ ማውሳት ልመና ይመስላል፡፡

~

        t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

24 Oct, 11:32


📌«إنَّ الصِّدِّيْقِينَ إذَا قُرِئَ عَليْهُمْ القُرآنُ، طَربَتْ قُلُوبُهُمْ إلىْٰ الآخرة»

مالك بن دينار


#تلاوة

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

23 Oct, 17:09


السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

መርከዝ-ረያን

መርከዛችን በኦ-ላይን ከአሊፍ ጀምሮ እስከ ቁርአን ሂፍዝ ድረስ ከህፃን እስከ አዋቂዎች ከሁሉም የእድሜ ክልል የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ በአላህ ፍቃድ ቁርአንን በቀላል ዘዴ ያቀርባል። እናም ወንድም እህቶች ፈጥነው እንዲመዘገቡ እናሳውቃለን።


👉 በመርከዛችን የሚሰጡ የት/ት       
                አይነቶች፦
➡️ቃኢደቱ ኑራኒያ ለጀማሪዎች
➡️ቁርአንን በእይታ(በነዞር) ከመሰረታዊ ተጅዊድ ጋር
➡️የቁርአን ሽምደዳ (ሂፍዝ) ከተሟላ ተጅዊድ ጋር በአላህ ፍቃድ እንሰጣለን።

የቂርአት ክፍለ ጊዜ

↪️ጠዋት ከአንድ ሰዐት አስከ ሶስት ሰዐት

↪️ማታ ከሁለት ሰዐት እሰከ አራት ሰዐት


ት/ቱ የሚሰጠው  በቴሌ ግራም መሆኑን እናሳውቃለን።

🌟መመዝገብ ለምትፈልጉ👇👇
@abu_munib1

@Umu_Khaled1

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

22 Oct, 15:52


ዝምታ፦የአሊም ውበት የጃሂል መደበቂያ ነዉ።

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

22 Oct, 12:33


«እንዳታገቢ»

በሰለፍያ ስም ዋሽቶ የሚነግድ፡
ሴት የማያከብር አስተሳሰብ ውልግድ፡
ብርሀን አልባ ፅልመት በቀን የሚለግድ፡
ሰነፍና ዋልጌ ማይሰራ ማይነግድ፡

ሴትን ለማሳመን በሱና እሚያማልል፡
ነገ የማይገባው ጂል ቡለሀ ቅውልል፡
ስሙን በመቀየር ሚስቱን የሚሰልል፡
በሌለው ማንነት አቅሙን የሚቆልል፡

       «እንዳታገቢ»

ለቅሶና ጭቅጭቅ ከሚሆን ህይወትሽ፡
ይህን ሰው አባሪው ነስከሽ ከፊትሽ፡
ተይው አይጠቅምሽም ለሱ ሚስትነትሽ፡

ባህሪው የሆነበት ማግባትና መፍታት፡
ምላሱ ቀጣፊ ባህሪው የራስ ምታት፡
ህልሙ ብር የሆነ ሰከንድም ሰዓታት፡

       «አታግቢው»

ትዳርን ሲፈልግ የማይገነዘብ፡
ትኩረቱ የሆነ ጥቅምና ገንዘብ፡
ባለው ንብረት ብቻ ሴትን የሚታዘብ፡

ሰለፍይ ነኝ ብሎ ምንም ቃል ቢገባ፡
በተግባር ካለዬ ምርቱ ከገለባ፡
ፊትና እሚናፍቀው የሚወድ ወከባ፡
ምንም ፎቶው ቢያምር ቢመስል አበባ፡
በጨለማ ገደል ይዞሽ እንዳይገባ፡

    «እንዳታገቢ»

ጌታን የሚያስቆጣ ሽርክን የሚሰራ፡
ቀብር የሚለምን ተሸክሞ እንስራ፡
ጀበናና ስኒ በጫት የሚመጀን፡
ነገ በአኸይራ እሳት የሚያስፈጀን፡
በየሚዲያው ላይ ሴት የሚጀናጀን፡

    «እንዳታገቢ»

ስሜት ያሰከረው መንፈሱ ታማሚ፡
መታዘዝ የማይወድ ለአባየም ለማሚ፡
የሀቅን ንግግር በጥመት ተርጓሚ፡

አንገት የሚደፋ እምነቱ ሲደፈር፡
የእምነቱ ፍቅር የማያልፍ ከከንፈር፡
ሰውነት የሌለው የሚል አፈር አፈር፡
ልማድ የሆነበት ዳንስና መጨፈር፡

    «እንዳታገቢ»

የተውሒድ አርበኛ ካልሆነልሽ ቀንድል፡
ሰለፍይ ነኝ ብሎ ሴትን የሚበድል፡
ሁሌ እሚለፈልፍ ያልሰራውን ገድል፡

       «እንዳታገቢ»

ሶላት የማይሰግድ ተጠቅልሎ ጋቢ፡
ፊትና የሚያሯሩጥ ችግር አራጋቢ፡
ውጭ የሚጠይቅ ሳያቀርብ ገቢ፡
ይህ አይነቱ አልጫ አወ እንዳታገቢ፡

 👇👇[ተቀላቀሉ] ▣ تابعونا👇👇
https://t.me/Abuharisabdurahman

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

21 Oct, 19:21


~የጭንቅ ግዜ ዱዓእ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿دعَواتُ المكروبِ: اللَّهمَّ رحمتَكَ أرجو فلا تكِلْني إلى نفسي طرفةَ عينٍ وأصلِحْ لي شأني كلَّه لا إلهَ إلّا أنتَ﴾

“የጭንቅ ግዜ ዱዓእ፦ ‘አላህ ሆይ! እዝነትህን አሻለሁ፡፡ ለቅፅበት ያክል እንኳ ለራሴ አትተወኝ፡፡ ሁለ ነገሬን ያማረ አድርግልኝ፡፡ ከአንተ ውጭ በሀቅ የሚመለክ አምላክ የለም፡፡’”

t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

21 Oct, 16:59


አላህ ሆይ !ኢማናችንን በቀልባችን ላይ አድስልን።

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

21 Oct, 16:09


متى يكــــــــون العبد
من الذاكرين الله كثيرا
...

🎙استمع للشيخ عبد الرزاق البدر حفظه الله

.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

21 Oct, 11:12


🔖አዲስ ተከታታይ  ደርስ

📚የተከበረው ቁርኣን ትርጉም
📄ክፍል:- 001 (የሱረቱል ፋቲሓ ቃል በቃል ትርጉም)
(تفسير سورة الفاتحة )
🎙አቅራቢ:-ሸይኽ ሙሐመድዘይን ኣደም 

bdf ለመጋኘት
https://t.me/SheikhMuhammedZainAdam/9840

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

19 Oct, 22:27


#الأسماء_والصفات

تعرف على صفتين من صفات الله - عزوجل - لو آمنت بهما لتغيرت حياتك ! ||

🎙️ العلامة محمد سعيد رسلان

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

19 Oct, 16:55


🔖የሩቃ መስፈርቶች.......!
~ ~
➀.በሚታቅ ቋንቋ መሆን አለበት በአረበኛ መሆን አለበት

➁.የሚባለዉ ቋንቋ ከሸሪአ ጋር የሚጋጭ መሆን የለበትም

⓷.ሩቃዉ በሽታዉን ለማስወገድ ስበብ እንጅ ራሱን ችሎ በሽታዉን እሚያስወግድ አደለም።

~
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

19 Oct, 15:04


عن أبي هريرة رضي الله عنه ،
أن رسول الله ﷺ قال :

"مَنْ قَالَ سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ فِي يَوْمٍ مِائَةَ مَرَّةٍ حُطَّتْ خَطَايَاهُ ، وَإنْ كَانَتْ مِثْلَ زَبَدِ البَحْرِ".

📚متفق عليه.

🍃🌸

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

18 Oct, 20:48


የጥበበኞች ተሞክሮ(ምክር) ለባለ ትዳሮች
=
ከ አፈ_ታሪክ የተወሰደ ተሞክሮ
አንዲት ሴት ለጥበበኛው ሽማግሌ ባሌ ከፋብኝ ፀባዩን ልችለው አልቻልኩም ምን ትመክሩኛለሁ? በማለት ጠየቀየች

ሽማግሌውም የአንበሳ ፀጉር ከነ ሕይዎቱ እያለ ከ ግንባሩ ላይ ነጭተሽ አምጭልኝና የባልሽ ፀባይ እንድስተካከል መድ ኃኒት በፀጉሩ እሰራልሻለሁ አሏት።

ቴትዮዋም ይሄ ለኔ ቀላሌ ነው ብላ ስጋ ነገር በመያዝ ወደ ቤቷ ስር ወደሚገኘው ጫካ በመሄድ ላንበሳው ስጋ መወርወር ጀመረች።

አንበሳውም ገና በርቀት ጥላለት ስትሄድ ሴትዮዋን ማስተዋል ጀመረ ባለውለታውም አደረጋትና ለመዳት

እሷም ቀስ እያለች ወደ አንበሳው እየቀረበች ስጋ መስጠት ጀመረች እሱም ለመዳት ሁሌም ስጋ ይዛለት ስትመጣ ጅራቱን በመቁላት ደስታውን ይገልፅላት ጀመረ

እሷም የአንበሳውን መላመድ ስትረዳ ቀረብችውና ስጋውን በእጇ ሰጠችው እሱም ፀጥ አለ

ከዚያም እያሻሸች ፀጉሩን በምላጭ ቆረጠችው ወዲያውኑ በደስታ ተውጣ ወደ ሽማግሌው በመሄድ ይሄው የታዘዝኩትን ይዤ መጣሁ መድኃኒቱን ስሩልኝ አለቻቸው

የሚገርመው የሽማግሌው መልስ ነው

"ከዚያ ከከፋ አንበሳ ግንባር ላይ በሕይዎት እያለ አባብለሽ ፀጉር መቁረጥ ከቻልሽ ያንች ባል ካንበሳው ስለ ማይከፋ ባልሽን አባብለሽ መያዝ ነው መድኃኒቱ"አሏት።


👇👇[ተቀላቀሉ] ▣ تابعونا👇👇

https://t.me/Abuharisabdurahman

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

18 Oct, 14:41


‏قال الإمام #ابن_الجوزي رحمه الله :

فَالله الله يَا معشر الْمُؤمنِينَ وَالْمُؤْمِنَات أَكْثرُوا من الصَّلَاة على حبيبكم مُحَمَّد ﷺ فِي جَمِيع الْأَيَّام والأوقات والأحايين والساعات ، عَسى الله أَن يخلصكم من الْأَهْوَال والآفات وَالْعَذَاب.

[ بستان الواعظين : (281/1) ]

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

18 Oct, 05:02


በነብያችን ﷺ ላይ ሶለዋት ለማዉረድ አንሰስት❗️

ረሱል ﷺ እንዲህ አሉ

"ስስታም (ንፉግ) ማለት ከእርሱጋ ተወስቼ በኔ  ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነዉ።"
📚 صحيح الجامع
t.me/https_Asselfya

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

17 Oct, 21:44


اختم يومك بكلام الله ﷻ
ِــلاوة

.

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

17 Oct, 16:04


ሳታወሯቸው የሚረዷችሁ፤ ሳትነግሯቸው
የሚያውቋችሁ
ሰዎች አሉ። እነዚህ ሰዎች
ግን ሁላችንም ህይወት ውስጥ ሳይሆን ከፊሎቻችን
ህይወት ውስጥ ነው ያሉት። እነዚህ ሰዎች የዘመናት
ስጦታዎችና ክስተቶች ናቸው። አምሳያዎቻቸው
ብዙ አይደሉምና ጠበቅ አድርጋችሁ ያዟቸው።           

💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀

17 Oct, 14:57


,              #ሞት_!!
በዱንያ ውጣ ውረድ በሀሳብ ተውጠን
ንግዱን ተያይዘን መሸጥ መለወጡን
ገበሬም ከሆነ ማረስ መቆፈሩን
ሁሉም በየ ፈኑ ሙሉ ቀን  ሲፏንን
አንስቶን ይሄዳል ሞት ሳያማክረን


ስልክ ሥንጎረጉር ወይንም ኮምፒውተር
ከዳውሎዱ በፊት ሞት መጥቶ ሲገተር
የዛኔ ጭንቀቱ አወይ የኛ ነገር

ጎረምሳው ወንድሜ ጉርምስናው አስሮት
ነገ ዛሬ እያለ ዒባዳ ከልክሎት
በተግባር ተኝቶ ተሻግሮ በምኞት
ምንም ሳይዘጋጅ፣ ድንገት ይመጣል ሞት

ዘናጯም እህቴ ባለ ነጭ ጫማ
አግቢ ትዳር ያዢ ስትባል ሳትሰማ
ስትመርጥ፣ ስትመርጥ ስታማርጥ ከርማ
መጥቶ ይወስዳታል እንደቀረች ቁማ!

t.me/https_Asselfya

8,259

subscribers

1,125

photos

413

videos