#ከፍታ፤ ከባህር ጠለል ከ700 እስከ 22ዐዐ ሜትር ከፍታ ሊመረት ይችላል፡፡
#የዝናብ_መጠን: ቀይ ሸንኩርት በዕድገቱ ወቅት ከ600-650 ሚ.ሜ. ውሃን በአማካይ ይጠቀማል፡፡የምርት ስብሰባው ወቅት ደረቅ ሁኔታዎች ያስፈልጓቸዋል፡፡
#የሙቀት_መጠን፤ ለዘር ብቅለት ከ18 - 24 ዲ.ሴ. የሚስማማው ሲሆን ለዕድገቱ ደግሞ በአማካይ ከ25 - 28 ዲ.ሴ የቀንና ከ10 -15 ዲ.ሴ. የማታ ሙቀት ይስማማዋል፡፡ ከ25 - 27 ዲ.ሴ ሙቀት ዕድገቱ ያፈጥነዋል፡፡ በአንጻሩ ዝቅተኛ ሙቀት (8 – 13 ዲ.ሴ.)
እንዲያብብ ያደርገዋል፡፡ ነገር ግን ከ 30 ዲ.ሴ. ከበለጠ ፣ ካለ ወቅቱ ቀድሞ መድርስ እና አንስተኛ ኮረት ሰለሚኖረው ምርትን በእጅጉ ይቀንሰዋል።
#የአፈር_ዓይነት፤ ለቀይ ሸንኩርት አሸዋ ቀመስ ለምና ውሃ የማይቋጥር አፈር ያስፈልገዋል፡፡ በተጨማሪም ለቀይ ሸንኩርት የሚስማማ የአፈር ኮምጣጣነት መጠን ከ5.5 - 7.5 ከሆነ የዕርጥበት መጠኑን በሚገባ በመቆጣጣር ከአሸዋ ቀመስ እሰከ ኮትቻ አፈር ላይም ቀይ ሸንኩርትን ማምረት ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ
የቴሌ ግራም ቻናላችን ይጎብኙ
👇👇👇
https:// t.me/AbdiSirajFarm