ጥበብን በማሾ @tibebnbemasho Channel on Telegram

ጥበብን በማሾ

@tibebnbemasho


________________________________
________________________________
ሰላም ቶላዋቅ ኢተፋ ነኝ
እንኳን ወደ ቻናሌ በሠላም መጣችሁ።

በቻናሌ ላይ ያላችሁን ማንኛውንም ሃሳብ ለመስጠትና ግጥም ለመላክ @Tibebn_bemasho_bot ይጠቀሙ።
________________________________
________________________________

ጥበብን በማሾ (Amharic)

ቻናሌን መምራት ለዚህ እባኮት እና ለማግኘት የሚረሱት ሃሳቦችን መስጠትና ግጥም ለመላክ የመነባብን እንቅስቃሴዎች ለማስጠበቅ @Tibebn_bemasho_bot ከተጠቀሙ። መልኩን ለማደርግ እትም ላይ ያለውን መረጃ ያጠናከብናል። የቻናላችን ሃሳቦችን ባለፈው ግንኙነትና መሠረት በመሆን የተያያዘ አስተዋጽጧ እንቅስቃሴ ነን። በሌለው ለመረጃ አዘጋጆችን የተከተለ፣ በማቃጠል አሳዋቂና በሚባለው መረጃ ማንከኝ እና ማለት ይችላሉ። እናመሰግናለን!አመሰግናለሁ!

ጥበብን በማሾ

26 Apr, 11:06


#አይዞን

ደስታ አንቴን ሸሽቶ ከጎንህ ሲጠፋ
መንፈስ ታድሶ  እንድታገኝ ተስፋ

       ዛሬ ትተህ ነገን አልም
       ለልብህ ተስፋን ሸልም

       ትሁን ትናት ዛሬም ታልፋ
       ብርታት ሰንቅ አትከፋ።

       #ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
       በ20/06/2013

        @tibebnBeMasho
        @tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

18 Oct, 20:17


#አንቺዬ 💜

ዝናብ ወርዶ ፥ ምድር በጎርፍ ተጥለቅልቆ፣
ስጋ ለባሽ ፥ሲንቀጠቀጥ ተሸማቆ፣

በነፋሱ ፥ ሲውረገረግ ዛፍ ቅጠሉ ፣
ስትስቂ ፥ ፍጥረት ሁሉ.....
ከጥርስሽ ላይ ፥ ሙቀት ጸሀይ ተቀበሉ።

#ገጣሚ ሮቤል አለማየሁ

#ዝምተኛው_ሲርሎስ
2016 ዓ.ም በደሌ
@tibebnBeFanos

ጥበብን በማሾ

30 Jun, 08:43


#ገጣሚና_አንባቢ
ቶላዋቅ ኢተፋ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

18 Jul, 18:34


#መልከ_ሰብእ

ሳይመስል ሚመስል
መስሎም የማይመስል

ሁለት አይነት ፍጡር
አለ በዚች ምድር።

አንዱ ያልሆነውን ሁሉ
ለመምሰል የሚጥር

ሁለተኛው ደሞ የሆነውን
ራሱ የሚይዝ በሚስጥር።

በቶላዋቅ ኢተፋ
በ30/8/2012

👇👇👇#Join 🙏
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

10 Jun, 07:55


#ገጣሚ ሮቤል አለማየሁ
#አንባቢ ቶላዋቅ ኢተፋ

@tibebnBeFanos

ጥበብን በማሾ

07 Jun, 17:58


#ያኔ_እኔን_አያርገኝ

አንቺ ፥ ረሳውሽ ስል ማስታውስሽ፣
ብናፍቅሽ ናይልኝ ብል ማልመልስሽ።

አንቺ ፥ ደስታ ሳቄን ቀምተሽኝ ፣
ከንቱ ፍጡር አደረግሽኝ፣

#አዎ
ስናፍቅሽ መቼ መጣሽ!
ከሀሳቤስ መቼ ወጣሽ?

#ብቻ
ናፍቄሽ ሳትመጪ ፥ ጠብቄሽ ስትቀሪ፣
ሁኛለሁ አለሜ ፥ ተስፋ ቢስ በራሪ፣

#አየሽ
በመሄድሽ ብስራት ፥ ሲናወጥ መንፈሴ፣
ሲንቀጠቀጥልሽ ፥ አካልና ነብሴ፣

#አንቺ_ግን?
ህመሜም አልገባሽ፣
ጭራሽ በኔ አነባሽ።

#ብቻ
ጭካኔሽ አይሎ ፥ እርቀሽ ብትሄጂ፣
የኔን ገላ ረስተሽ ፥ ከሌላ ብትለምጂ፣
ያኔ እኔን አያርገኝ አፈር ያርገኝ እንጂ።

#ገጣሚ ሮቤል አለማየው
#ዝምተኛው_ሲርሎስ
2014 ዓ.ም በደሌ

ጥበብን በማሾ

30 May, 11:14


#ገጣሚና አንባቢ ቶላዋቅ ኢተፋ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

23 May, 18:13


#ዝምታ_ወርቅ_አይደል።


ዝምታ ወርቅ ነው ሲባል እሰማለሁ
ግና አንዳንደዚህ ስተት ነው እላለሁ
ይህንን ስል ደግሞ እተማመናለሁ።

ምክንያቱም ዝምታ ከልክ ካለፈ
ስውር ቂም አርግዟል በሆድ የታቀፈ።

ስለዚህ #ዝምታ
መስማማት እያለ በቃላት ድርድር
ወርቅ ነው አልልም ቢመጣ ተአምር።

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2012 ዓ.ም ገቺ

ጥበብን በማሾ

11 Mar, 18:34


#የጌታዬ_ምፃት
.
.
ቀኑ መሽቶ ጠሀይ ጠልቃ
ወጣች ደሞ ውብ ጨረቃ
:
የጨረቃ መውጣት
የጠሀይቷ መግባት
ለማብሰር ቢሆንም ምሽትና ንጋት
:
የሰሞኑ ትንግርት ሆኖብኝ ዱብዳ
ተአምር ያሳየኛል ከሰማይ ሠሌዳ።
:
ዘውትር ሁልጊዜ ከጥልቁ ሰማይ ላይ
ልጇን በእቅፍ እዛ ለሰው መስላ ጠሀይ
ትታየኝ ነበረ የነፍሳችን ሲሳይ።

#ግና ዛሬ.......
ደረሰ መሰለኝ የጌታዬ ምፃት
አየኅት ብቻዋን የጌታዬን እናት።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
በ09/06/2013

#ቻናሌን_ይቀላቀሉ
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

25 Feb, 17:32


#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
#አንባቢት ኤደን

@tibebnBeMasho
@tibenbnBeMasho

ጥበብን በማሾ

08 Feb, 04:59


#ይዲዲያ


@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

13 Jan, 18:07


#ቃል
2014 ዓ.ም #ገቺ

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
#አንባቢ ሮቤል አለማየሁ

ጥበብን በማሾ

27 Dec, 08:32


#አምኜሽ_ነበረ

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ

#አንባቢ ሮቤል አለማየው
#ዝምተኛው_ሲርሎስ
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

30 Nov, 18:15


#አምኜሽ_ነበረ

የሰናፍጭ ታህል መጠርጠር ተስኖኝ
አምኜሽ ነበረ የማትከጂኝ መስሎኝ።

አንቺ ግን ከዳሺኝ
እንዳንቺ ያለን ሰው
መቼም እንዳላምን እምነት አሳጣሺኝ።

#ታዲያ.........
ሰውን ማመን ቀብሮ ያለችው ቀበሮ
እውነቷን ነበረ ገብቶኛል ዘንድሮ።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም #ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

22 Nov, 17:18


#ጥለሽኝ_ስትሄጂ
ብርሃናማው ቀኔን አልብሰሽ ጨለማ
ግዙፍ ያልኩት ተስፋ ቀለጠ እንደ ሻማ

ዛሬን ኑሮ ነገን ማለም
ሄደ ጠፋ ከኔ አለም

ቀኔም መሸ ቀን ሳይበቃ
ሳትደበቅ ጀምበር ጠልቃ።

አዎ ስትሄጂ ስለት ተቀየረ
ነገ ሚባል ነገም ነገ ሁኖ ቀረ

ታዲያ እንዲህ ሁኖ ጊዜ ሲተካካ
ቀበርኩኝ ትናንቴን አሁኔ እንዲፈካ።

አዎ በትናት ትዝታ ዛሬን ለምን ላፍርስ
ትናት ትናት አልፏል በቃ ዛሬን ላድስ

#አዎ_እንዲህ_ሳስብ
ተስፋ ቢሱ ልቤ ተስፋን አዳመነ
ማግኘትን አምጦ ሲቃን አመከነ

ተስፋ ከሌለበት ካንቺ አለም መነነ
ከማጣቱም በላይ ማግኘቱ መዘነ።

አዎ .....
በልቤ ሠሌዳ ተስፋ ተፃፈበት
ሁሁታው ተሽሮ ሠላም ሰፈነበት።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2013 ዓ.ም ገቺ

ይቀላቀሉን👇👇👇👇
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

16 Nov, 18:39


#ይዲዲያ

በዛች ቅዱስ እለት
አንቺን ስመለከት ከመፅዋች መሃል
ቀልቤ ከነፈልሽ በውበትሽ ፀዳል።

ታዲያ
እጅግ ብደነቅም በፈጣሪ ስራ
አይቼ ስወድሽ ከቅዱሱ ስፍራ
አንድም ሐሴት አለው በሌላም መከራ።

መከራው ፍቅርሽ ነው
እንደ አውሎ ነፋስ እምያወዛውዘኝ
ካለሽበት ቀዬ ወስዶ የሚጥለኝ
እንደ እናቴ ኩርፊያ የሚያነጫንጨኝ።

ታዲያ
በውበትሽ ቅኔ መላቅጤን ሳጣ
በዐይኖሽ ስከረር ደስታ ከየት መጣ?

ብቻ
በኑረት ብራና ልቤ አንቺን ይደርሳል
ባለሽበት ትዕይንት እራሱን ይስላል።

ታዲያ
እንዲህ ሁኖ ሳለ ፍቅሬ እንዴት ተሸሸ
የማፍቀረስ ፀዳል ስለምን ጠለሸ?

ብቻ
እውነት ኑሯት ይሆን እያልኩ አስባለው
ይሄን ተከትሎም
ፍቅር ያስፈራኛል
የሚል ዐይነት ምላሽ ከገፇ አያለው።

ደሞ አንዳንደዚህ
ከፍቅር የሚያርቅ ምን እውነት ይኖራል
ከፍቅር እርቆስ እውነት የት እገኛል?

እያልኩ አስባለው
እውነት በማይመስሉ እውነቶች ታጥረ
እየተገረምኩኝ አንቺን በማፍቀረ።

ብቻ
በይ እስኪ ንገርኝ እጠይቅሻለው
ፍቅሬ ይዲዲያ መች አገኝሻለው?

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም ገቺ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

12 Nov, 18:05


#ጦቢያ

ሰማይ ላይታረስ ነፋስ ላይታፈስ
እንዳው ለነገሩ ነገር ብጠነሰስ
ትፈርሳለች በሚል ....
በፈረሰ ሃሳብ እምነትህ አይፍረስ።

#ምክኒያቱም.
እንዳው ዝም ብላ ተነስታ የምትፈርስ
አይደለች ሀገሬ በማንም ልክስክስ።

#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
2014 ዓ.ም ገቺ

@tibebnBemasho
@tibebnBemasho

ጥበብን በማሾ

03 Nov, 18:06


#ገጣሚ ቶላዋቅ ኢተፋ
#አንባቢ ዝምተኛው ሲርሎስ

@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho

ጥበብን በማሾ

16 Oct, 16:57


#እምነትና_እውነት

ገጣሚና አንባቢ ቶላዋቅ ኢተፋ

#ይቀላቀሉን👇👇👇
@tibebnBeMasho
@tibebnBeMasho