አማራ ፋኖ በሸዋ @shewaamharafano Channel on Telegram

አማራ ፋኖ በሸዋ

@shewaamharafano


አማራ ፋኖ በሸዋ (Amharic)

አማራ ፋኖ በሸዋ የተሸዋው ፋኖ በከተላቀ ሸዋ ላይ የሚታመኑትን ምርጫዎችን ለማግኘት የቡድን ተወዳጅ ማለት ነው። እናም እስካሁን ነገር እና ጭምቱን ለመከላከል አማራ ፋኖ በሸዋ የሚገኙን ህብረተሰብ እና ሌቦርን የሚመረቱ ተወዳጅ ፋይሎችን ለመፃፉ የቡድን አካባቢነትን ማስጠየቅ ይችላሉ። ከጥያቄዎ በመለየት እናም ከጭምች በታች የቡድን ተወዳጅ ፋኖ ሏል ለማሰላስ እና በማሰረበት አጋማሽ መረጃዎን ለመመለስ ለሸዋው ለምኞቹ በሚሰጡት ቦታዎች ውስጥ በጥሩ አጋማሻዎች እና ቀጥሎ ለሀገሪቱ ከተከፈለው አጋማሽ መሰረት ለምኞቱ የሰነበቱን የሰልጣን ቦታዎችን ለማስተላለፍ ያግኙ።

አማራ ፋኖ በሸዋ

31 Dec, 18:23


ከመሪያችን አርበኛ ዘመነ ካሴ ሰሞኑናዊ ንግግሮች

<<ወንድም ወንድሙን መሸከም የሚችል ትክሻ ከሌለው ታጋይ አይደለም። አንዳችሁ የሌላኛችሁን ክፍተት ለመሙላት ስሩ። ማንም ሰው ሙሉ አይደለም፤ የሰው ልጅ ትምህርት ከአንቀልባ እስከ መቃብር ይቀጥላል።>>

<<የሃሳብ ልዮነቶች ትናንት የነበሩ፣ ዛሬም ያሉ፣ ነገም የሚኖሩና የሚጠበቁ ናቸው።>>

<<በአመራሩ መካከል ልዮነት ለመፍጠር የብልጽግና ቡድን ቢሊዮን ይመድባል፤ ብልጽግናን እቃወማለሁ የሚለው ምቀኛም ቢሊዮን ይመድባል። ትግላችንን እንጠብቅ! ወሬ እገሌ የመንደር ወሬኛ ነው በሚል ብቻ የሚበተን ሳይሆን የጠላቶቻችን የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ ነው። ግን አይሳካም!>>

<<በተለያየ አሰላለፍ ላሉ ወንድሞች ሽምግልናን እናስቀድም። ወንድሞቻችሁንም በመሰረተቢስና የማጥቂያ የግንባር ወገብ ምናምን ፍረጃን አቁሙ።>>

<<ፋኖን የአማራ ሕዝብ ብቻም ሳይሆን መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አዳኝ በተስፋ እየጠበቀው ይገኛል፤ እናም ከሌሎች አካላት ጋር አብረን እየሰራን እንገኛለን። ምናልባትም በቅርቡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የምንሰማው ብስራት ይኖራል። ከሃገራት ጋርም በጎ ነገሮች አሉ።>>

<<እኛ የአማራ ሕዝብ መሪዎች ነን፤ ማንም የመንደር መሪዎች ሆኖ አይቀጥልም። ከአንድነት ማግስት ብዙ ነገሮች ይቀየራሉ።>>

አማራ ፋኖ በሸዋ

08 Dec, 19:25


#ሰበርዜና!

#Amhara

የጎንደር ፋኖዎቻችን ወደ አንድ መጥተዋል። የአማራ ፋኖ በጎንደር እና የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ በአንድ መዋቅር ተደራጅተዋል።

አርበኛ ባዬ ቀናው፣ ሻለቃ ሐብቴ ወልዴ እና አባት አርበኞች የአማራ ሕዝብ አለኝታነታቸውን አሳይተዋል።

አንድነታችን መዳኛ መንገዳችን ነው!

ድል ለሕዝባችን!

አማራ ፋኖ በሸዋ

26 Nov, 19:02


የሌሊት ወፍ

"የሌት ወፍ እንደ ዓይጥ ጥርስ አላት፤ እንደ ወፍም ከንፍ አላት፡፡ አንድ ጊዜ የሰማይ ወፎችና የዱር አራዊቶች ተጣልተው አራት ቀን ሙሉ ጦርነት አደረጉ፡፡

የሌት ወፍ ግን በዳር ሁና ትመለከትና የዱር አራዊቶች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ ትሔድና እኔ እኮቁጥሬ ወደናንተ ነው እዩት ጥርሴን! እዩት ጡቴን እስቲ ከሰማይ ወፎች እንደኔ ጥርስና ጡት ያለው ማነው ትላቸዋለች፡፡

ደግሞ የሰማይ ወፎች ሲበረቱ ያየች እንደ ሆነ ወደነዚያ
ትሔድና እኔ እኮ ቁጥሬ ወደናንተ ነው! እዩት ክንፌን እስቲ ከዱር አራዊት ወገን እንደኔ በከንፍ እየበረረ በአየር ላይ የሚሔድ ማነው ትላቸዋለች፡፡

ወደ ጦርነቱ ግን ምንም ቢሆን አትገባም፡፡

ከጥቂት ቀን በኋላ ዕርቅ ተደረገና ጦርነቱ ቆመ፡፡ ስለዚሁም የሰማይ ወፎችና አራዊቶች ትልቅ በዓል አደረጉ፡፡

የሌት ወፍም ወደ ወፎች ድግስ ብትሔድ እኛ እንደ አውሬ ጥርስ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡ ወደ ዱር አራዊትም ብትሔድ እኛ እንደወፍ ክንፍ የለን ወደኛ ለምን መጣሽ ብለው አባረርዋት፡፡

ከዚህ በኋላ አፈረችና ወፎችም አራዊትም እንዳያይዋት ቀን ቀን እየተደበቀኝ እየዋለች፤ ማታ ማታ ምግብዋን ለመፈለግ ጀመረች። ቀን ወፎችም ቢያገኝዋት! አራዊትም ቢያገኝዋት አይተዋትም ይገድልዋታል እንጂ

የሌት ወፍ የተባለችውም ከዚያ ወዲህ ነው ይባላል፡፡" (ብላቴን ጌታ ኅሩይ)

አንዳንዶች እንዲህ ናቸው፤ያጠቃ ያሸነፈ ከመሰላቸው ጋር ቦርጫቸውን ያስተካክላሉ፤ላጠቃው መወድስ ለተጠቃው ተረት አያጡም። ጥርሳቸውንና ክንፋቸውን እያቀያየሩ እያሳዩ "እኔ ያንተ አሽከር ያንተ ቡችላ" ይላሉ።

እንደ ንሥርም እንደ አንበሳም ኮራ ብሎ መብረር ወይም መንጎማለል የሚቻለው ወይ ወፍነትን ወይ አውሬነትን መምረጥ ሲቻል ነው!

ጦርነትም ሆነ ጠብ በእርቅ አልያም በመሸናነፍ ይጠናቀቃል። ያኔ እንደ ሌት ወፍ ሌት መጓዝ ይመጣል።

የባንዳም ነገር ይህ ነው መጨረሻው ላኩላቸው ምንአልባት ቢገባቸው ያው ሆዳም አይገባውም እንጂ

አማራ ፋኖ በሸዋ

21 Nov, 21:53


~ ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል!

አማራን ለመጨ*ፍጨፍ በአገዛዙ የተላከን የኦሮሞ ልጅ ማርኮ ተንከባክቦ ወደቤተሰቦቹ የሚልከው የፋኖ ሠራዊት  ሰላሌ ድረስ መጥቶ አንድ ምስኪን ታዳጊ የሚገ*ድልበት ምድራዊ አመክንዮ የለም።

ይልቅስ እነ በቴ ኡርጌሳን የበላው አገዛዝ ፣ ሐጫሉንም የገደለው ሥርዓት፣ የከረዩ አባገዳዎችን የጨፈ*ጨፈው አገዛዝ ፣ በኦሮሚያ የሚታፈሱ ወጣቶች የፈጠረውን የሕዝብ ቁጣ ለማስታገስ የፈፀመው ርካሽ ተግባር ነው።

አለሁ የሚል "መንግስት" ካለ የሰላሌ ሕዝብ ቀንበር ተሸክሞ የጠየቀው ጥያቄ  ቢኖር "አርሰን እንድንበላ የሚያሠማራውን ታጣቂ ያስታግስልን" የሚል ነው።

ፋሽስቱ አብይ ሆይ፥ በእንደዚህ አይነት እንጭጭ ድራማ በፍፁም አትድንም!

@ከአዲሱ ደረበ

አማራ ፋኖ በሸዋ

03 Nov, 21:12


የአማራ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለውን ጭፍጨፋ

አንረሳውም !!!
ህዝቤ ሆይ እንዳትረሳው በሀዘንህ ግዜ ማን ከጎንህ እንደነበረ ማን እንደጨፈጨፈህ ስትሞት የተሳለቀብህ: ቆሞ ማን እንዳየህ እንዳትረሳው !! ይህ ቀን ያልፋል ,ባንዳ ያንተን መቼም አንረሳውም .. መቼም
አንረሳውም በብዙ ሺህ እጥፍ እሳት ተበቃይ ልጆች አሉት አማራዬ ዛሬ ብዙዎች ሀዘኑ እቤታቸው ስላልገባ ያንተ ደም ምንም መስሎ አይታየውም ግን የአማራ እናት ብቻ አልቅሳ አንብታ አትቀርም አትቀርም
አንረሳውም መቼም።

አማራ ፋኖ በሸዋ

24 Oct, 17:23


ጀግኖች

አማራ ፋኖ በሸዋ

23 Oct, 15:27


እባካችሁ - እንደ ዐዲስ እንሠራ

ከነገ ዛሬ ይቀድማልና፣ ከመቅረትም መዘግየት ይሻላልና

፩. አሳማኝ በምንላቸው ማስረጃዎቻችን እና ምክንያቶቻችን ጎራ ለይተን የቆምን፣

፪. ግራ ገብቶን መኻል ላይ የቀረን፣

፫. በቲክ ቶክ፣ በትዊተር፣ በፌስቡክ እና በዩቱብ ደግሞም በሳተላይት ቴቪ የምንጎሻሸም፣

ግን አንድ cause (መግፍኤነገር) - እርሱም የዐማራ ሕዝብ ሕልውና አደጋ ውስጥ መግባቱ የሚያዋሕደን፤ ፈጽሞ ያልተለያየን:-

እባካችሁ የሕዝባችን የመከራ ቀናት ያጥሩ ዘንድ የምንገፋፋባቸውን ትተን ወይም ቆም አድርገን ወደ አንድ እንምጣ።

ለሕዝባችን ስንል ልዩነቶቻችንን ለጊዜው እናምቃቸው። ከዚያም በዐደባባይ ሳይኾን ለብቻ በጓዳ እየመከርን እየተገሳጸጽን እየተማማርን ወደ አንድ ለማምጣት ቃል እንግባ።


የታናሻችሁ ጥሪ!

ከዲን ዓባይነህ ካሴ

አማራ ፋኖ በሸዋ

20 Oct, 18:03


የእነዚያ ዘር!

ቀዳሚ ምኞታችን ተቋማዊ ውህደት ካልሆነ ደግሞ በህብረት የሚያቆም አንድነትን ማየት ነው። የዓላማ ልዮነት ሳይኖረን፣ የአካሄድ ልዮነቶች ግን ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ነገር ደግሞ ህዝባችን እየጨፈጨፈ ባለው በጨቅላው አብይ አህመድ ላይ ከመተባበር ሊያግደን ፈፅሞ አይችልም።

ዛሬ በሸዋ የሰማነውም ይህንን በግልጽ የሚያስረዳ ነው። ሁለቱ በሸዋ የከተሙ የአማራ እዞቻችን አራዊት ሰራዊቱን አበራይተው፣ ከክተው፣ ፈጭተውታል። ገና ይቀጥላል!

ሸዋ የትግላችን መስፈንጠሪያ ስፕሪንግ ቦርድ ነው፤ በዚህም ትይዮ ደግሞ የፍጥነታችን መቆጣጠሪያ ቫልቭና rate limiting ነውና ብዙ የምንጠብቅበት እናም ትኩረት የምንሰጠው ብሌናችን ነው።

አማራ ፋኖ በሸዋ

20 Oct, 06:29


ሁለት መቶ ተራሮችን የፈጠረ የተራሮች ዘመቻ!

"ዘመቻ መቶ ተራሮች" ይፋ ሲደረግ የሩቅ ጠላቶችም የቅርብ የኮንዶም ትራፊዎችም ተሳልቀው ነበር። ነገር ግን ይህ ትውልድ ከምድር ፈልቆ እንደወጣ ገሞራ ተራራን ማንቀጥቀጥ ይቅርና ተራራን መናድ የሚችል፣ ሲያሻውም ተራራን በአረንጓዴ ለባሽ ምርኮኞች መሸፈን የሚችል ክንደ ነበልባል ትውልድ መሆኑን በዘመቻ መቶ ተራሮች አስመስክሯል።

አሁን ተራሮቹ 200 ደርሰዋል - ገሚሱ የዘመቻችን ስያሜ ሲሆን ገሚሱ ደግሞ የአራዊት ሰራዊቱ የአስክሬን ቁልል ነው። የአማራ ህዝብን ለማጥፋት ልጃችሁን መርቃችሁም ሆነ አልቅሳችሁ ለውትድርና የላካችሁ እናቶች፣ ልጃችሁ መንገድ ላይ ቀርቷል - አትጠብቁት። ቀሪዎቹም የተለየ እጣፈንታ የላቸውም።

በታሪክ መዛግብት ፊት በኩራት የሚያቆም ታሪክን እየጻፈ ያለው ይህ ትውልድ፣ ጥቂት ክላሽ ይዞ ተነስቶ፣ በሃገር ሃብት አሰሱንም ገሰሱንም የታጠቀውን የግለሰብ ወታደራዊ ተቋምና ሰራዊትን ብትንትኑ እያወጣው ነው። እንኳንም የእናንተ ሆን።

#የመውጫ_መልዕክት፦ አሁንም የድል ቀናችን የሚረዝመው በእኛ ድክመት እንጅ በጠላታችን ጥንካሬ አይደለም። የጎተተንን ድክመት ደግሞ በቅርብ የምናርመው ይሆናል።

አማራ ፋኖ በሸዋ

18 Oct, 07:17


የብርቱ አርበኛ ቃል

+ + + + +

"ሀገር ሽጠው በሚያገኙት የደም ገንዘብ አሮጌ ተራ ወርደው በሚሸምቱት ድሮንና ተተኳሽ አይደለም ከዋክብት ቦንብ ኾነው የዐማራ ሕዝብ ላይ ቢዘንቡ እንኳን ጠላቶቻችን ይኽን ትግል ማሸነፍ አይችሉም።

እምቢ ያለን ሕዝብ፥ ለህልውናው ላለመጥፋት የሚታገልን ሕዝብ ማሸነፍ ፈጽሞ አይቻልም። ከገፀ ምድር ላለመጥፋት መሣሪያ ያነሣን ሕዝብ ከማሸነፍ የፀሐይን ከምሥራቅ ወደ ምዕራብ ተፈጥሯዊ የጉዞ ዑደት ከሰሜን ወደ ደቡብ ማዞር ይቀላል። ከፈጣሪ በታች ትልቁ ጉልበት ያለው የአመፀ ሕዝብ መዳፍ ላይ ነው።

እንበርታ እንጽና ብቻ!! ጽናት ነገ ከነ- ጠዋት ውብ ጀንበሯ የራስ እንደምትኾን በጥልቅ ከነፍስ በማመን የዛሬን ሰው፣ ተፈጥሮና ሁኔታዎች ወለድ ውጣ ውረዶችን የማመቅና የገለባ ያክል እንኳን ለሥነ ልቦናችን ሳይከብዱን ወደ ግብ የመገስገስ ሥነ አዕምሯዊ ኹነት ነው። እንጽና!!"


#አርበኛ_ዘመነ_ካሤ

አማራ ፋኖ በሸዋ

16 Oct, 14:43


ማስጠንቀቂያ…!

"…ሰሞኑን የአርበኛ ሌ/ኮለኔል አሰግድ መኮነን ስልክን በመጠቀም ሰዎችን እየመረጡ  "Bonda" የሚባል  በኢንሳ የበለፀገ malnware ለግለሰቦች በቴሌግራም እና በሌሎች ማህበራዊ ሚድያ አገልግልቶች እየላኩ ይገኛል። በመሆኑም ይሄን link በሚነካበት ጊዜ ስልክ ላይ የሚገኙ መረጃወችን ከመመንተፍ በተጨማሪ በስልክ ላይ Remote acess software እንዲጫንበት በማድረግ የስልኩን GpS, Microphone እና camera በመጠቀም ወገን ላይ ጥቃት እየደረሰ ይገኛል።

"…በተጨማሪም በተለያየ link መልኩ በአንዳንድ ወገኖች በኩል የሎተሪ ዕጣ በሚመስል እና ሽልማት በማስመሰል የሚላኩ ሊንኮች ባለቤታቸው ይለያይ እንጅ ተመሳሳይ የስለላ እና የሳይበር ጥቃት ስልቶች በመሆናቸው ሊንኮችን ከመከፈት እንድትቆጠቡ እናሳስባለን ብለዋል የመረጃው ምንጮች።

"…በሌላ በኩል በሀገረ አሜሪካ በሚኖረው በአምሀ እና በዋን ዐማራዎች በኩል የሳታላይት ስልክ ተገዝቶ የተላከላችሁም ዛሬ የደረሰው የስልኩ ተጠቃሚ ፋኖ አይነት የድሮን አደጋ እንዳይዳርስባችሁ የሳታላይት ስልካችሁን አስወግዱ ተብላችኋል። ይሄ የፋኖ አመራሮች መልእክት ነው።

"…በምንም ዓይነት መልኩ የተለጠፈው ዓይነት ሊንክ ከጋሽ አሰግድም ሆነ ከሌላ አካል ስልካችሁ ላይ ብታዩ ወዲያው አስወግዱት። እንዳትከፍቱት ተመክራችኋል። ሴራውን ፍርስ ነው።

• ርእሰ አንቀጹን ልለጥፍ ነኝ። ጠብቁኝ።

አማራ ፋኖ በሸዋ

15 Oct, 12:54


ህፃኑ የዕናቱን አስከሬን ተደግፎ ደም እየፈሰሰው ተገኘ።
እናት ልጇን አዝላ ተገደለች !

አገዛዙ በአማራ ህዝብ ላይ የሚያካሒደውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ተባብሶ ቀጥሏል።

ነዋሪነቷ ሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ሶጠን ቀበሌ የሆነችው የሁለት ልጆች እናት ወ/ሮ አስበራ መሀመድ ኑር በረኸት ወረዳ መጥተህ ብላ ከተማ ልጇን አዝላ በመጓዝ ላይ ሳለች በአገዛዙ ሀይል በጥይ ተደብድባ ተገድላለች።

ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ልዩ ስሙ 03 ቀበሌ በተባለ ስፍራ ራሱን መከላከያ ነኝ ብሎ በሚጠራው ቡድን በጥይት ተደብድባ ተገድላለች።

ማህበረሰቡ በስፍራው ሲደርስም ህፃን ልጇ ጭምር በጥይት ተመትቶ ደም እየፈሰሰው ከእናቱ አስከሬን ጎን ተገኝቷል።

የሁለት ልጆች እናት የሆነችው አስበራ መሀመድ ኑር የሁለት አመት ልጇ ከወደቀችበት  ስፍራ አጠገብ ቁጭ ብሎ  ሲያለቅስና ደም ሲፈስሰው በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የፋኖ አባላት አግኝተውት ለቅርብ ቤተሰቦቿ አስረክበዋል።

ድል በግፍ ለሚገደለው አማራ ህዝብ!
ድል ለፋኖ!

አማራ ፋኖ በሸዋ

08 Oct, 15:48


     ቀን መስከረም 28/1/2017

"…የመንገድ ክልከላውን አስመልክቶ ከዐማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ መመሪያ

"…ከመስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የሲቪሊያንን ሕይወት ለመታደግ ሲባል እንዲሁም የሥርዓቱን ለመጣል ከምናደርገው ዘርፈ ብዙ ትግል መካከል አንዱ በመላው የዐማራ ክልል መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ እንዲደረጉ በተሰጠው መመሪያ መሠረት ትዕዛዙን ሕዝባችን ተፈፃሚ አድርጎ ቆይቷል።

"…የተላለፈው ትእዛዝ ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን ለማከናወን ይገጥመን የነበረውን መሰናክል በማስወገድ እና ሲቪሊያንንም በመጠበቅ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበረው። በሌላ በኩል የዐማራ ሕዝብ ከፋኖ ጋር እንደቆመ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና ለሀገራችን ሕዝብ በይፋ ማረጋገጥ ተችሏል።

"…በመሆኑም የተሰጠውን የጥንቃቄ መመሪያ ያለምንም መሸራረፍ ለፈጸመው ሕዝባችን ከፍ ያለ ክብር ያለን መሆኑን እየገለፅን ከነገ መስከረም 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ:-

1ኛ፦ ከየትኛውም አቅጣጫ ወደ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ወልቃይት ሰቲት ሁመራ እና ማዕከላዊ የጎንደር ዞኖች የሚደረግ የመንገደኞች ጉዞ፥

2ኛ፦ በዐማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የሚደረግ የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ፦

3ኛ፦ እንዲሁም በሁሉም የወሎ ቀጠናዎች ብቻ የመንገድ ትራንስፖርት የተፈቀደ በመሆኑ መንገድ ክፍት የተደረገ መሆኑን እናሳውቃለን።

"…በሌሎች አካባቢ ያለውን ነባራዊ ሁኔታው ሲፈቅድ እየታዬ ተለዋጭ ትእዛዝ የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን።

• ዘመቻ መቶ ተራሮች ይቀጥላል...

ክብር ለተሰው ሰማዕታት!
ድል ለአማራ ሕዝብ!

የዐማራ ፋኖ በጎንደር
የዐማራ ፋኖ በጎጃም
የዐማራ ፋኖ ሸዋ እዝ
የዐማራ ፋኖ በወሎ

አማራ ፋኖ በሸዋ

30 Sep, 22:45


እንዴት አያችሁት የሰሞኑን የበአዲኖችን እስር ? የኦሮሙማ ቡድን ገረዱን በአዴን እየበላት እየዋጣት ይመስላል አይደል .. አይ የባንዳ መጨረሻው

አማራ ፋኖ በሸዋ

27 Sep, 18:11


https://vm.tiktok.com/ZMh6QmcJy/

አማራ ፋኖ በሸዋ

19 Sep, 17:44


ሁለት ሞት በዳባት

ፋኖዎቻችን በዳባት ከተማ ውስጥ በከተመ ጠላት ላይ በድንገት ዘነቡ፤ አንድ ቀን ቀደም ብሎ ደግሞ ደባርቅ ከተማን ቀጨም በማድረግ ከጠላት አፅድተዋት ነበር። በደባት የሆነው ግን ሌላም አስገራሚ ነገር ነበረው…

በዳባት የዘነቡት ፋኖዎቻችን በከተማዋ ውስጥ የነበሩትን የፋሽስቱን ስርዓት ኃይሎች ግንባር መብጣት ሲጀምሩ፣ በርካታ ሁለት የግራ እግር ሚሊሽያዎች ወደ አራዊት ሰራዊቱ ወታደራዊ ካምፕ ይፈረጥጡ ጀመር። ከተማው ውስጥ ከፀዳው አራዊት ሰራዊት የተረፈ ሰራዊት ካምፑ ውስጥ ነበር፤ ይህ ሰራዊትም ሽምጥ እየፈረጠጠ የመጣውን የሚሊሽያ መንጋ ወደ ካምፕ አላስገባም ብሎ አውላላ ሜዳ ላይ በተነው።

ሁለት የግራ እግሩ ሚሊሽያ በአንድ ጫፍ ክህደት፣ በሌላ ጫፍ አፈሙዝ ከበበው። አፈሙዙ የፋኖዎቻችን ነበር። አንድ ሚሊሽያ አባት ከእነ 2 ሚሊሽያ ልጆቹ ጨምሮ፣ ከ60 በላይ ሚሊሽያ ግንባር ግንባሩን ተበጣ። አራዊት ሰራዊቱ በር ቢዘጋባቸውም፣ ምድር ግን ሆዷን ከፍታ ሆዳሞቹን ተቀበለቻቸው።

የከዱን ፍጡራን ተከዱ፤ ሁለት ሞትም ሞቱ። የእነዚህ ሁለመና ሆዶች የመጨረሻዋ እስትንፋስ፣ ለህይወት ታሪክ ጻህፍት ፈተና ሆኖ አልፏል።

ቻው!

አማራ ፋኖ በሸዋ

11 Sep, 09:06


በዱር በገደል በጫካ በዝናብ በውርጭ በበረሀ በፀሀዩ ላይ ያላችሁ የአማራ ሞት ,መፈናቀል, ሰደት ,ጭቆናው መታረዱ ,መደፈሩ መንከራተቱ ይበቃ ብላችሁ ከሞቀ ቤታችሁ ወጥታችሁ ታላቅ ተጋድሎ ,መሥዋዕትነት የምትከፋሉ ፋኖዎቻችን እንኳን አደረሳችሁ!! ይህ አመት ይህን ጨቋኝ ስረአት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የምንገረስስበት: ይህን ታላቅ ህዝብ ወደ ቀድሞ ታላቅነቱ ክብሩ ከፍታው የምንመልስበት አመት ፈጣሪ ያድርግልን:: በግፍ የታረዱ ,በጅምላ የተገደሉትን ደም የምንመልስበት ያለቀሱትን አንገቱን የደፋውን አባታችንን ቀና እንዲል የእናታችንን እንባ የምናብስበት የድል አመት ይሁንልን:: .. በመጨረሻም በአገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ ይህን ቅዱስ ትግል የምትደግፉ ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ!! ..በስደት በጭንቀት ያለኸው ወገናችን አይዞን ልጆችህ እየደረስንልህ ነው..መልካም አዲስ አመት ይሁንልህ አማራው።

አማራ ፋኖ በሸዋ

11 Sep, 06:48


የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ
ከ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ
የተላለፈ የ2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት መልዕክት!
***
በቅድሚያ በራሴ እና የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ሥም፡- ለመላው የአማራ ሕዝብ፤ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎና በጎንደር ላላችሁ ለጋራ ዓላማ፤ የጋራ መስዋዕትነት እየከፈልን ላላችሁ ወንድሞቻችን፤ የሕልውና ትግሉ የዲፕሎማሲ ግንባር ተሰላፊ ለሆነው የዲያስፖራ ወገናችን እንኳን ለአዲሱ ዓመት በጀግንነት አደረሳችሁ!!

በመቀጠል፡- የአማራ ትግል ወዳጆች፣ በፋሽስቱ የብልጽግና አገዛዝ ጭቆናና ብዝበዛ ውስጥ ላለው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በፅናት አደረሰን፤ አደረሳችሁ የሚል መልዕክቴን አስተላልፋለሁ!!

በድል የደመቅንበት 2016 ዓ.ም.፡- እጅግ ፈጣን የመደራጀት፣ የማጥቃትና የጠላትን ኃይል የመበተን አቅም የፈጠርንበት፣ የሕልውና ትግሉ በማይቀበለስ ደረጃ መድረሱ የተረጋገጠበት የድል ዓመት ነበር፡፡

ነፃ ቀጠናዎችን በማስፋት፣ የሕዝባዊ አስተዳደር ልምምዶችን ያሳደግንበት፤ ወታደራዊ፣ የመረጃና አስተዳደራዊ አቅሞችን የፈጠርንበት፤ የትግል ቅርጽና ይዘት ያለው አደረጃጀት እውን ያደረግንበት፤ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለማቀፉ ማኀበረሰብ ዘንድ የአማራ ትግል አጀንዳ የጎላበት፣ በጥቅሉ አማራ ታሪኩን ያደሰበት፣ ትውልዱም የራሱን ደማቅ ታሪክ በደምና አጥንቱ የፃፈበት ታሪካዊ የድል ዓመት ነበር፡፡

ዓመቱ ፋሽስም ወገቡ የተሰበረበት፤ ፋኖነት የአማራ መዳኛ መሆኑ የተረጋገጠበት ሆኗል፡፡

በተለይም የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ተተርከው የማያልቁ ብዙ ጀብዱ፤ እልፍ ገድሎችን ፈጽሟል፡፡ በሰፊ ቀጠና እየተንቀሳቀሰ በደምና አጥንቱ የማይሞት ታሪክ ሰርቷል፡፡ እጅግ አስደናቂ ጀብዱዎች የተፈፀሙባቸው በርካታ ዘመቻዎች በጋራ ታቅደው፤ በጋራ ተተግብረዋል፡፡ በዚህም የጠላት የሰው ኃይል ተራቁቶ ቀፎው ቀርቷል፡፡ በዓለማቀፍ የጦርነት ሕጎች መሠረት ምርኮኞችን በአግባቡ በመያዝ የሞራልና የሕግ ተገዥነታችንን ለዓለም አስመስክረናል፡፡

"አማራን ትጥቅ ብቻ ሳይሆን ቀበቶውንም እናስፈታዋለን" ያሉንን ትጥቃቸውን እያስፈታን፤ ፋሽስታዊ አስተሳብ የተሸከሙበትን አዕምሯቸውን እያጠብን የአማራነትን ልክ አሳይተናቸዋል፡፡"እናፀደዋለን" ያሉንን እየመነጠርን፤ ርቃናቸውን አስቀርተን በድል መራመዳችንን ቀጥለናል!!

የትግሉ ባለቤት የሆነው የአማራ ሕዝብ ከአብራኩ ለተገኙ ፋኖ ልጆቹ፣ ስንቅና የመረጃ ምንጭ ሆኖ የተሳተፈበት በመሆኑ ዓመቱን በድል ደምቀን ለማሳለፍ አቅም ሆኖናል፡፡

በሌላ በኩል ዓመቱ የሕልውና ትግሉ አልጋ ባልጋ የሆነበት ሳይሆን የደም ዋጋ እየከፈልን የመጣንበት፤ በርካታ ወንድሞቻችንን የገበርንበት በመሆኑ አዲሱን ዓመት 2017 ዓ.ም. በጀግንነት ስንቀበል የጀግኖች ሰማዕታትን የትግል አደራ ከግብ ለማድረስ የትግል ቃል-ኪዳናችንን በማደስ ነው፡፡ አማራነት በጀግኖች ደም ደመቆና ተከብሮ ይኖራል!

በትግላችን ውስጥ ያረጋገጥነው እውነት፣ አማራነት በእሳት ተፈትኖ ራሱን እንደንሥር አድሶ ከፍ ብሎ በመብረር ላይ ነው፡፡ ዛሬ የአማራ ሕዝብ አምጦ የወለደው ፋኖ የሕዝብ ልጅ ስለመሆኑ በተግባር ታይቷል፡፡ ፋሽስምን ብቻ ሳይሆን በፋሽስም ጥላ ስር ያሉ ሌባ፣ ቀማኛ፣ አጋችና ዘራፊዎችን በመቅጣት የሕዝብ ወገንተኝነቱን አሳይቷል፡፡

ያለፈው የትግል ዓመት፣ ፋኖ በአስተሳሰብና በተግባር ከአማራ ሕዝብ የተገኘ፤ ጠንካራ ማህበረሰባዊ ግንኙነት እና የትግል ሥነ-ምግባር ያለው እውነተኛ ታጋይ መሆኑን ያሳየበት የድል ዓመት ነበር፡፡

ይህ ያስጨነቀው ጠላት የትግል ስልቱን በመቀያየር የሕልውና ትግሉን የድጋፍ መሰረት ለመሸርሸር፤ ሕዝባችንን ለማማረር፤ የትግል ትኩረት አቅጣጫ ለማሳት፤… የተለያዩ የቀውስ ታክቲኮች፣ የተደራጁ ወንጀሎች፣ የሐሰት ፕሮፖጋንዳዎች፣ ከፋፋይ አጀንዳዎች ቢረጩም አማራ የብረት አጥር ሆኖ መክቶታል፡፡

በዚህ ድል ኩራት የሚሰማን ሆኖ፣ አሁንም ጠላት በባከነ ሰዓት በእኩይ ሴራዎቹ የቀጠለ በመሆኑ እንደአማራ በአዲሱ ዓመት የትግሉን ፍፃሜ ለማሳመር ኳሷን በአግባቡ መቆጣጠር፣ የመጨረሻውን ሳቅ ለመሳቅ ኳሷን የድል መረቡ ላይ ለማሳረፍ በብርቱ ጥንቃቄ ማጥቃት አለብን! የትግል ሜዳው ላይ ዋጋ እየከፈልን ያለነውን የአማራ ፋኖ መስዋትነት ማክበር የሚቻለው፣ የሕልውና ትግሉን ከጠላት ሴራ በመጠበቅ፤ አማራዊ የብረት አጥሩን በማጥበቅ ነው!!

እንደአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ፣ በአዲሱ የትግል ዓመት አማራነት በፈተናዎች የሚፀና እንጂ የሚበተን ማንነት አንዳልሆነ ለወዳጅ ጠላት እናረጋግጣለን!

ትግላችን የቱንም ያህል ፈታኝና መራራ ቢሆንም በሞት ሸለቆ ሳይታለፍ ታሪክ አይቀየርምና ለአማራ ሕዝብ ዘላቂ አሸናፊነት የማይተካ ሕይወታችንን ዋጋ እየከፈልን አዲሱን ዓመት ዘላቂ ድል የሚመጣበት የድል ዘመን እንደምናደርገው አንጠራጠርም፡፡ ለዚህም ‹አማራዊ ሕብረት፤ ለአማራ ሕልውና!› በሚል ከፍታችን አስጠብቀን በድል እንበራለን፡፡

በአዲሱ ዓመት 2017 ዓ.ም የሕልውና ትግሉ ዘመኑን ወደዋጀ ሁለገብ ትግል ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ለዚህም ከሥጋና የትግል ወንድሞቻችን ጋር በአንድነት በመቆም፣ በጋራ አመራር ስትራቴጂካዊ ድል እንደምናረጋግጥ እናበስራለን፡፡

በመጨረሻም፡- የአማራ ሕዝብ ትግል በፈተና የተሞላ፤ መራራና ዋጋ የሚከፈልበት እንደሆነ በመጣንበት የትግል መንገድ እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ዋጋ የምንከፍለው ለአማራ ሕልውና መረጋገጥ፤ አማራ አንገቱን ቀና አደርጎ እንዲሄድ፤ ለዘላቂ ጥቅሞቹ መከበር ነው፡፡ ፈተናና መከራው የቱንም ያህል ቢበረታ ድሉ አይቀሬ ነው፡፡

2017 የትግል ዘመን የአማራ ሕዝብ የዘላቂ አሸናፊነትና የነጻነት ዓመት ይሆናል!

አርበኛ ሀብቴ ወልዴ
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዋና አዛዥ
ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ
ጷግሜ 5/2016 ዓ.ም.

አማራ ፋኖ በሸዋ

08 Sep, 17:48


ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለ ጦር
   በቅርቡ ወደ አማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ውስጥ የተካተተው በፋኖ ጥላሁን የሚመራው  ራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ ሻለቃወች ከአገዛዙ የብልፅግና ሰራዊት በሁለት ቦታ አንገት ለአንገት ተያይዞ ሲደመስሰው ውሏል።

የመጀመረሚያው በመርሃቤቴ ወረዳ ገረን ቀበሌ ፋኖን እደመስሳለሁ በሚል የህልም ቅዠት ጨዋታ ወደ ቦታው ያመራው ወንበዴው ሰራዊት ያሰበበት ቦታ ሳይደርስ ልዩ ስሙ ቀርጫ ቀርጫ የሚባል ቦታ ላይ በአናብስቶቹ የፋኖ አባላት በደፈጣ ውጊያ አይቀጡ ቅጣት ተቀጥቶ ብዛት ያለው የአገዛዙ ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል።

ይህ ወንበዴ ሰራዊት በደረሰበት ክፉኛ ምት ብስጭት ውስጥ የገባው የአገዛዙ ሰራዊት ወደ ከተማው ሲመለሱ ምንም የማያውቁ  በየመንገዱ ያገኛቸውን ሲቪል ሰወች እየደበደበ እና በሰብል ጥበቃና በእንስሳት ጥበቃ ላይ የነበሩ ህፃናትን ማለትም የ10 አመት ሴት ልጅ የ11እና የ12አመት ወንድ ልጆችን   በጥይት በመምታት ሶስቱም ህፃናት በህክምና ላይ እንዳሉ ለማወቆ ችለናል።

ሁለተኛው ሬሽን በመጫን ወደ መርሀቤቴ አለምከተማ ለመቀባበል ከለሚ የወረደ እና ከአለም ከተማ የወረደ የጠለት ሃይል በጀማ ድልድይ አቅራቢያ ወደ የጎፍ ለመሻገር ሲሞክር የነበረው የአገዛዙ ጥምር ጦር በክንደ ነበልባሎች የራስ አበበ አረጋይ ብርጌድ የፋኖ አባለት በበርሲና ወንዝ ላይ ሙትና ቁስለኛ ሲሆን ሌላኛው እድል ቀንቶት ከፋኖ ጥይት ያመለጠው  የጠላት ሃይል እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ መጣበት ፈርጥጧል።

   ይህ በእንዲህ እንዳለ ሽንፈቱን የተከናነበው የአገዛዙ ቡድን ጀማ በረሃ ላይ በግል ሰራ ተሰማርቶ ግሮሰሪ የሚሰራን ግለሰብ የፋኖ ሃብት ነው በማለት ለብዙ ጊዜ ሲሰራበት የነበረውን የግሮሰሪ እና ማለትም ፍሪጅ ብዛት 2፤ ጀነሬተር፤ ባዶ እና ያለበት የቢራ ካሳ፤ በዛት ያለቸው የምግብ ቤት ዕቃወችን ብረት ድስት እንጀራ እና ያልተጋገረ ሊጥ ጭልፋ ሳይቀር ጠራርጎ በመጫን ወደየመጣበት የሄደ ሲሆን ይህ ዘራፊ ሰራዊት የወንበዴነት  ተግባሩን በግልፅ ያሳየበት ዕለት ነው።           

              ከሸዋ የትግል ሜዳ
                      
ጳጉሜ 3/2016ዓ.ም
ክብር ለተሰውት

   ሪፖርተር ግራ አዝማች ፈለቀ ታደሰ
የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ናደው ክፍለጦር የሚዲያና ኮምንኬሽን ተጠሪ ክፍል

አማራ ፋኖ በሸዋ

08 Sep, 09:04


የደጋዳሞቱን ደፈጣ የሚያስታውስ ግዙፍ ኦፕሬሽን በጎንደር ምድር ላይ ተፈጽሟል። በሺህ የሚቆጠር የብርሐኑ ጁላ ጦር ወደ አዲሱ ዓመት ሳይሸጋገር ቀርቷል። ክብር ለጎንደር አማራ ፋኖ

አማራ ፋኖ በሸዋ

07 Sep, 17:11


ይህ ሰው ከስድቡ በላይ ቁምነገር ያወራል በእውነት ስሙት .. "ግብፅ ልትወረን ነው ይላል ወረሞ ..እና እኛ አማሮች ምን አገባን " "..ትክክል ነው

አማራ ፋኖ በሸዋ

31 Aug, 16:16


የ ሸዋ አማራ
ሸዋ የ ንጉስ ሚኒሊክ የ ፕሮፌሰር አስራት ሀገር፡፡ሸዋ የ አክሊሉ ሀብተወልድ ሀገር ድንበር እና ካርታ ስሎ ኢትዮጵያን የ ፈጠረ ምጡቁ የ ሸዋ ህዝብ የ ራሱን መሪ ማዉጣት መቻል እንዴት አቃተዉ ፡፡ ሁሉም አማራ በ የሰፈሩ የ ራሱን መሪ ይዞ ሲወጣ ሸዋ ግን እራሱን በራሱ እንዳይቆም ለምን ተፈለገ ? ሸዋ ተሸካሚ፣መራጭ እንጂ ተመራጭ እንዳይሆን ለምን ተሰራበት ይህንን ሁሉ ስትመረምሩ የ ሸዋ አማራን ደግመን አናነግስም ከ ሸዋ አማራ ትግሬ ይግዛን ብለዉ አማራን አንገቱን አስደፍተዉ እነሱም መሬታቸዉን ተቀምተዉ ሲማቅቁ የኖሩት ወደጭንቅላቴ ይመጣሉ አሁንም በዚህ ህልዉና ትግል ዉስጥ የ ሸዋ አማራ ላይ ሴራ እየጎነጎኑ ያሉ እነኚህ ሆዳም ሀይሎች ናቸዉ፡፡ ሸዋ የ አማራ መዳኛ !!!

አማራ ፋኖ በሸዋ

27 Aug, 21:37


ሼር

ከደራ በረኸኞች ለአርበኛ ሽመልስ ንጉሴ(ዳግማዊ ምንሊክ ) እና ለቀስተንህብ ብርጌድ ጓዶቹ የተላለፈ ጥሪ
                                     21''12''16 አ.ም

    ወንድማችን በቅድሚያ እንደምን አለህ ?
  ከከበረው ኑሮ ያስመነነህ የግፉአን ትግል እንዴት ይዞሃል ?
          እኛ ደህና ነን አምክ ይመስገን።
  ጠላት በወረረው ግዛት ከንደ ብርቱ ሆነን የገፋንን አረመኔ ስርዓት እንዳመጣጡ አየሸኘነው አለን ።

ፈለጋቸውን ተከትላችሁ የወጣችሁህችለው የነ በፍቃዱ በላይ የነ ባልፈው አበይ የነ ማሙሽ ያዘው የነ ሽፈራው ደም  በወኔ ላይ ወኔ በድፍረት ላይ ድፍረት አስታጥቆን ሃሞታቸውን እንደውሃ ጠጥተን ከአላማችን ውልፍት ሳንል የዚህን መከረኛ ህዝብ እንባ በብረት ለማበስ ቆርጠን ተነስተናል ። 
ትግሉንና የናንተን ናፍቆት እንኳን አታንሱት መንታ ናቸው ።

ክንዳለም ሽሜ እኛማ ------ አምስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው የቱቲ አውደ ውጊያ ላይ ሆነን ከወደ ወለቃ ተኩስ በሰማን ቁጥር ጀግናው ጦሩን ይዞ ከተተ እያልን ብናማትርም የለህም  ።
  ነጋ ጠባ የናንተን  መምጣት እየጠበቅን እንገኛለን  ።
አስችሏችሁ  ይሆን ? ወይስ የትግል ጓዶቻችሁ ወገኔ ተደፍሯል እንዝመትለት ስትለበቸው ለገሙ?

ጀግኖቼ ቢሆን ይከተሏችሁ ታልሆነ ግን እናንተ ብቻ ኑ!
   ተቃላችን ከወጣችሁ ብረቱን አምጡ ያሉ እንደሆን ወርውሩላቸውና ኑ ። በማይመስሏችሁ  ስብስብ ውስጥ በይሉኝታ ሰንሰለት ታጥራችሁ እሰከመቼ ?
እኛ ወንድሞቻችሁ ከጠላት የማረክነው ክላሽ  ያጥር መገርገሪያ ሆኗል  ኑልን ።

  ስትሏቸው ግን ★
በሉ ደህና ሁኑ እኛ ለወጣንለት ህዝብ ሄደናል ብንሰዋ ተሰዋልን የሚለን ህዝብ አለን ።
ብንኖርም በርታ የምንለው ከአለት የፀና ወታደር አለን ። 
ሳንኖር በስማችን ይዋጋሉ ስለዚህ አናስፈልጋቸዋለን በሏቸውና ኑ ቶሎ ክንዶቼ ።

  እኔ አርማዬ ወለቃ ወንዝን ተሻግሬ እቀበልሃሁ ። 

ጀግናው ስለሺ ደግሞ እንዳለህ★
[ ሽሜዋ ጓዶችህን ይዘህ ናልኝ ቀኝ እጄ ሌሎቹ የሽዋን ትግል የመሰረተችውን ደራን ረስተው ለይፋት ሆኗል የሚዋጉት ናና ጠላትን እንደቀድሟችን እንቅጣው ]  ብሎሃል ።

   አርማዬ ነኝ ወለቃ ወንዝ ስር ።  💪

አማራ ፋኖ በሸዋ

20 Aug, 12:01


በእነዋሪው ውጊያ 387 የገዢው ቡድን ወታደሮች መገደላቸው ተገለፀ!

የሞረትና ጅሩ ወረዳ ዋና መቀመጫ በሆነችው እነዋሪ ከተማ ላይ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ በቁጥር 387 የገዢው ቡድን ወታደሮች ሲገደሉ ከዘጠኝ ተሽከርካሪ በላይ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን የአማራ ፋኖ በሸዋ ዕዝ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

የአገዛዙ ጦር የፋኖ አባላትን ገደልኩ በሚል ከባሕልና ከእሴት ባፈነገጠ መልኩ የሟቾችን አስከሬን አውራ ጎዳና ላይ እየጎተተ ተንቀሳቃሽ ምስል በመቅረፅ በሚዲያ ማሰራጨቱ ይታወቃል።

ለዚህ ምላሽ የሰጠው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ አገዛዙ የደረሰበትን ከባድ የሆነ የሰውና የንብረት ኪሳራን ለማካካስ በሚል በማሕበረሰቡ ላይ የግፍ በትሩን በጭካኔ እያሳረፈ ነው ያለ ሲሆን፡ ሰራዊታችንም ዘመቻ ሰማዕታት በማወጅ ይሄንን ወራሪ ቡድን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ከባድ ትንቅንቅ እያደረገ ነው ብሏል።

ነሐሴ 11/2016 ዓ/ም ከንጋት ጀምሮ እስከ አመሻሹ በተደረገ ውጊያ 336 የኮማንዶ አባላት፣ ሁለት ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ ሦስት የፖሊስ አባላት፣ 48 ሚኒሻ፡ በድምሩ 387 የአገዛዙ ወታደሮች ሲገደሉ ከዘጠኝ ተሽከርካሪ በላይ ቁስለኛ ወደ ሆስፒታል መወሰዱን ዕዙ በላከው መግለጫው ገልጿል።

እኛ ብንወድቅ፣ ብንሰዋ እንኳን እልፍ ጠላት ይዘን ነው ሲል በመግለጫው የጠቀሰው ዕዙ፡ ስለዚህ ሕዝቡ በውጊያ በሚሰው ጀግኖች ስነ ልቦናው እንዳይጎዳና ማዘንም እንደለለበት አሳስቧል።

ሰራዊታችን ከትናንት የተሻለ ቁመና ላይ የሚገኝ ሲሆን ለቀጣይ ግዳጅ የተዘጋጀ አስተማማኝ አቅም ያለው ነው ሲል የጠቀሰው መግለጫው፡ በማሕበረሰባችን ላይ የበቀል ዱላ ያነሳውን የገዢው ቡድን ወታደርን በዘመቻ ሰማዕታት አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ ነው ብሏል።

በመጨረሻም ዕዙ በመግለጫው፡ የሰማዕታቱን ሞት የግል ፖለቲካ ፍላጎታቸው ማሟያ ለማድረግ ከፋፋይ ሃሳቦችን ሚያናፍሱ አካላትን ተመልክተናል ያለ ሲሆን፡ እነዚህ ከፋፋይ ያላቸውና በሰማዕት ጓዶቻችን ነፍስ ላይ ቁማር ለመጫዎች ሙከራ እያደረጉ ነው ላላቸው አካላት በአስቸኳይ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

አማራ ፋኖ በሸዋ

19 Aug, 21:16


ሸዋ ውስጥ በዚህ መጠን ፋኖ ሞቶ አያውቅም እነዚህ ጀግኖች በዚህ ሰው በላ ስርአት እንዲጨፈጨፉ ያደረጋችሁ ሰዎች ልትጠየቁ ይገባል ። ሸዋ በጊዜ መሪህን አርቅ መሪ ነው ለሁሉም መሰረቱ ዝርክርክ አመራር ጀግና ያስበላል ጦር ይበትናል እና እቅድ የሌለው ጦርነት ኪሳራ ነው። የሰውም መሳለቂያ ነው የሚያደርገን ቆም ብለን መክረን በቶሎ ወደ አንድነት መጥተን የጀግኖቹን ደም በፍጥነት እንመልስ። ሸዋ የጀግኖች ምድር ናት በቶሎ ቅስሙን እና ልቡን የሰበርነውን ህዝብ መካስ ይኖርብናል።

ሼር በማድረግ አድርሷቸው

አማራ ፋኖ በሸዋ

18 Aug, 21:41


በትናንትናው ዕለት እነዋሪ የተደረገው ውጊያ የጨበጣ(እጅ ለእጅ) ውጊያ ነበር ። የፋሺስቱ የብልፅግና አፈቀላጤዎች በእነሱ ላይ የደረሰውን ሽንፈት ለመደበቅ ሲሉ ለፋኖ አዛኝ መስለው ታይተዋል ። ነገር ግን ጠላት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ። ሞቱ ተብሎ ከተሰራጨው መረጃ ውስጥ አብዛኛው ሚሊሻና የአድማ ብተና ፓሊሶች ናቸው ።

እርካሽ የፓለቲካ ትርፈ ለማግኘት ሲባል አብረዋቸው ተሰልፈው የተገደሉትን ጭምር ፋኖ እንደገደሉ አሰራጭተዋል ። ከዚህ በተጨማሪ የቆሰሉ ፋኖዎችን ደማቸው እየፈሰሰ ፎቶ አንስተው ለቀዋል ። እንግዲህ ስርዓቱ ወርዶ ወርዶ በሞተ ሰው ፎቶ መነገድ ጀምሯል ።

በዚህ የተነሳ በሚሊሻና በመከላከያ መካከል አለመግባባት ተደርሷል ። ምክንያቱ ደግሞ በትላንትናው እለት በተደረገ ውጊያ ላይ ተገደለ ከተባለው ውስጥ 50% በላይ የሚሊሻ አባላት እና አድማ ብተና ፖሊሶች ናቸው ።

ለሚዲያ ፍጆታ በፋኖ የተገደሉ የሚሊሻ አባላትን አስኬረን በጥይት ሁሉንም ግንባራቸው እንዳይታወቁ ተመተዋል ። በቀብር ወቅት ህዝቡ ሚሊሻዎቹ አብረው አሉ ግን እንዳይታወቁ ሁሉም ግንባራቸው ተመትቷል ብለው ነበር ።

ይህ ጉዳይ አሁን ላይ የሚሊሻ ቤተሰብ መጠየቅ ሲጀምር የወረዳው ሚሊሻ ቀድሞም ተናግረን ነበር አሁን ላይም ቢሆን እውነቱን እንናገር እና ቤተሰብም ካሳ ያግኝ በሚለው ሀሳብ ባለመስማማት እርስ በርሳቸው ተፋጠዋል ።