የተሰበሩ ልቦች...

@yeteseberelib


የተሰበሩ ልቦች...

23 Oct, 17:47


ደስተኛ ነች ልክ ቅዝቃዜ በምሽት በቀስታ እንደሚነፍስ ንፋስ እንደሚጋባው ሁሉ ደስታዋ በዛ ልክ ሰው ጋ ይጋባል፣
.
.
ሳያት ከሩቅ ተቀምጣ ያ በረዶ መሳይ ጥርሷን ከፊቷ አጣው ፣ ያ ያስለመደችኝ ፊገግታዋ የለም፣ ውስጤ ተላወሰ ለሷ ቢቸግራት እንጂ መች በኔ ጨክና ታውቅና፣
.
.
ከመከፋት ወዲያ ልቧን ደስታ ቢርቀው ልቧ በሀዘን ቢጨልምም ፈገግታ ለራቀው ገፅታ ቁም ነገር ነበር ትንሽም ብትሆን የሳቋ ብልጭታ....

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 19:05


`` ያመናችሁት አልከዳቸሁም፤
የሚከዳችሁን ነው ያመናችሁት!።
``

             -Imam Abi Talib..😊

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 18:40


ዘፋኝ ትመስላለህ...' አለቺኝ ፈገግ እንዳለች.. ማነው ደሞ እሱ አልኳት ....ሳላውቀው ቀርቼ ሳይሆን ስታወራ፤ ስታስረዳ ስለምወድ፤ ብዙ አታወራም ፤ ጭምት ናት።

    ፈገግ እንዳለች ዐይን አልፈው ልብን ሰርስረው የሚመለከቱ በሚመስሉ ዐይኖቿ ብቻ ትኩር ብላ እያየች በተመስጦ ታደምጣለች። ስትናገር ቃላቶቿ የተለኩ...የተመረጡ ናቸው.... ና እሷ ስትናገር ማነው ማድመጥ ማይፈልግ...... ፤እኔ በበኩሌ እንደ መላእክት ዜማ ስሰማት ውዬ ባድር አልሰለች፤

    ' አንተ ደሞ... don't you remember him from Friends ' ብላ ኩርፍ አለች ፤ በፈረንጅ አፍ ማውራት ይቀናታል። ያኮረፈችው Friends የሚባለውን ሲትኮም እራሷ ጎትጉታ እንዳይ ስላረገች የተረሳኝ መስሏት ነው፤ ብዙ ጊዜ ደጋግማ አይታዋለች  ።

  ' ደሞ ምኔ ዘፋኝ ይመስላል ...?'...  well እንግዲ .. አለች፤ አሁንም  ፈገግ ብላ.. ሁሌም እንደዚህ ናት፤ የስንቱን ልብ ይሆን ይዛ ኮንታ የገባችው። የኔስ አንዱ ሳይሆን ይቀራል...?

  well  እንግዲ look at both of you.. የሁለታችሁም personality በወላጆቻቹ ውሳኔዎች በጣም influence ተደርጓል.... ። ... ዝም ብዬ አያታለው ..

   both of you humor እንደ ማምለጫ ትጠቀማላቹ፤ ያለህበት ሁኔታ ሲያስጨንቅህ ቀልድ እንደምታበዛ  አስተውያለው።

  ልቀጥል? ....አለች ።ምን ምርጫ አለኝ አልኩ በሆዴ ...አዎ  አልኳት በጭንቅላቴ ምልክት እያሳየዋት .... okay then ሌላው ደሞ ለrealationship  negative አመለካከት  ነው ያላችሁ። እሱ ደሞ ሰውን እንዳታምን አርጎሀል።

    በዚህ መሀል ነበር የልብ ጓደኛዋ አክስቴ ያየቻት.... ከስራ ስወጣ የታመመችውን አክስቴን ተሰብስበን  ለመጠየቅ ስንሄድ ነበር ይሄ ወሬ  የተነሳው።

በእጇ ምልክት ሰጠቻት .... ሌላ ቀን እንቀጥላለን..... አለቺኝ  ፊቷን ወደኔ እየመለች። ግን አልቀጠልንም ....እኔ  በሳምንቱ ወደ ሀገሬ ሄድኩ።


   ሰዎች እንደቀልድ የሚናገሩት  ንግግር ምን ያህል ልባችን ውስጥ ቦታ ሊይዝ እንደሚችል ይሄ አንዱ ማሳያ ነው እላለው ባሰብኳት ቁጥር...❤️

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 17:53


ጥያቄ ለወንዶች እንደ እናትህ አይነት ሚስት ማግባት ትፈልጋለህ?

አዎ ❤️''

አይ 💔"

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 17:44


አልፈልግም የምትሉ ሴቶች አራት ሚስት ስለ አለው ነዋ🙂

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 17:18


ጥያቄ ለሴቶች እንደ አባትሽ አይነት ባል ማግባት ትፈልግያለሽ?

አዎ ❤️''

አይ 💔"

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 16:31


አንድ ሰው ለሶቅራጥስ እንዲህ አለው፡

"ያቺ ሴት ስነ ምግባር የጎደላት ሴተኛ
አዳሪ ትመስላለች"

ሶቅራጠስ፦ ታውቃታለህ?

ሰውዬው፦  አ ይ

ሶቅራጠስ፡- ይህን እንድታምን ያደረገህ ምንድን ነው?

ሰውየው፡- ልብሷ ምን እንደሚመስል አይታይህም?

ሶቅራጠስ፡- ስነምግባር የሌለው ሴተኛ አዳሪነት እውነት የሌላት ውሸት ናት ወይስ በጎነት ያልጎበኘው ሰውነት?

ሰውየው፡- ትክክል ያልሆነው የምታደርግ እውነት የሌላት ውሸት ናት

ሶቅራጠስ፡- በጥርጣሬ ላይ የተመሰረተ ፍርድ የፍትህ መጓደል ነው ወይስ እውነት?

ሰውዬው፦ በእርግጠኝነት ግፍ ነው!

ሶቅራጥስ፦ በጥርጣሬ ነው ወይስ በእርግጠኝነት በዚች ሴት ዝሙተኝነት ላይ የፈረድከው?

ሰውየው፦ በጥርጣሬ

ሶቅራጥስ፡- ለሥነ ምግባር ጉድለት የቱ ይበልጥ የቀረበ ነው፤ በጥርጣሬ ተነስቶ በሰዎች ላይ የሚፈርድ ወይስ ዝም ያለው?

ሰውዬው፡- በሰዎች ላይ በግምት እና በጥርጣሬ የሚፈርደው ነው።

ሶቅራጠስ፡- ታድያ ሴተኛ አዳሪ ማን ነው አንተ ወይስ ያቺ ሴት?

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 15:50


ኳስ የማይመለከት ወንድ አታፍቅሪ ይሰብርሻል ብያት...:(

ኳስን ትቶ በሴቶች ልብ ምጨወተውን መርጣ እያለቀሰች ነው🙂

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 15:25


Her🧕ፈጣሪውን የምገዛ ባል እፈልጋለሁ

Me🧔እኔ አለሁ

Her🧕 sport የምሰራ ባል እፈልጋለሁ

Me🧔 እኔ አለሁ

Her🧕 ሱሳም ባል አይመቸኝም

Me🧔 ሱሳም አይደለሁም

Her🧕 ስራ የምሰራ ባል ይመቸኛል

Me 🧔 እኔ አለሁ


Her🧕 ኳስ የምያይ ባል አይመቸኝም

🧔 me አንቺም ጥንቅር በይ football is my life🔥

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 14:56


አለች ሚስኪን ሴት .."መሄጃ" ስላሌላት ብቻ...:( «ሁልጊዜ ልቧ እየተወጋ»..የምትኖረዋ ምስኪን ሴት የእንስቶች መልዕክት ብቻ ሳትሆን የተባዕቶችም ህይወት ናት።

ይቺ ሴት በየቀኑ በየደቂቃው በእያንዳንዷ ቅፅበት በምታምናቸው ሰዎች ልቧ እየቆሰለና አካሏ እየነደደ ትኖራለች።
ይቺ ሴት መኖር እየናፈቃትና ነፃነት እያማራት እያቃሰተች ትኖራለች..።

አለች ሚስኪን ሴት ለራሷ ተስፋ እየሰጠች ለህልሟ እያሰበች ውስጧን ካቆሰለው ህመም በላይ ነገዋን እየሳለች እያለመች የምትኖር☺️

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 13:17


አሁን ይሄን ፅሁፍ እያነበባችሁ ያላችሁ በሙሉ የትኛው የስሜት ማዕከል እንዳላችሁ አላውቅም። አንዳንዶቻችሁ ደስተኞች ናቸው። አንዳንዶቻችሁ ህይወት የከበዳችሁ ናቸው። አንዳንዶቻችሁ ደግሞ ክፍላችሁን ዘግታችሁ የምታለቅሱ ናችሁ።

አብዛኞቻችሁ ከማንም በላይ ሀሳብ ያላቸው ብትሆንም የሚረዳችሁን አጥታችዋል። ሁልጊዜ ለመለወጥ ትጥራላችሁ ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ዝቅ ያደርጓችዋል። መስራት እና ማደግ እየቻላችሁ ነገር ግን በሆነ ምክንያት ወድቃችሁ ራሳችሁን ታገኙታላችሁ።

የሆነ ሰአት ላይ ወንድ ሲያልቀስ አይቻለሁ....የሆነ ሰአት ላይ ውስጧን እፍን አድርጋ የያዘች አንዲት ሴት አይቻለሁ....:( በቃኝ ብለው ከህይወት የተለዩ ብዙ ነፍሶች አይቻለሁ....አንዱ ልጅ ራኩ ህይወት ደክሞኛል ብሎ ቴክስት ሲያደርግልኝ ደነገጥኩ.....ምክንያቱም አቅም ያለውና አለምን መቀየር የሚችል ወጣት ስለሆነ! ምክንያቱም ራሱንና ቤተሰቡን መለወጥ የሚችል ጠንካራ ስለሆነ!

አሁን ሁላችሁም "እኔ ጠንካራ ነኝ" እንድትሉኝ እፈልጋለሁ.....እያለቀሳችሁ ያላችሁ እንባችሁን ጠርጋችሁ "እኔ ጠንካራ ነኝ" በሉኝ.......በችግር ውስጥ ያላችሁና የደክማችሁ "እኔ ጠንካራ ነኝ" በሉኝ! አለም ምንም ያህል ከባድ ብትሆን.....ነገሮች አልሳካም ቢሉን...ድካም አካላችንን ቢመታን "እኛ ግን ጠንካሮች ነን"! በእያንዳንዷ ሰከንድ ጥንካሬያችን ይጨምራል!

እኔ ጠንካራ ነኝ

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 09:18


ፍቅር ውስጥ ደስታን ብቻ መፈለግ ራስ ወዳድነት ነው::
የሰው ልጅ ፍቅር እና ደስታ እያበዛ ስመጣ ደደብ ይሆናል..!
ሀዘኖች ያስተምራሉ ስብራቶች ያጠናክራሉ☺️

የተሰበሩ ልቦች...

22 Oct, 08:38


ሴት ከወንድ እኩል የምትሆነው ቀን ተቆጥሮላት በማክበር አደለም: :
መፈክር ያለው ቲሸርት ለብዞሶ በመሄድም አይደለም ቀን ሠይመህ እሩጫ በመሮጥም አይደለም ወይም እኩልነት ማለት ጓዳ ገብቶ ወጥ መስራት አይደለም
ሴት ከወንድ እኩል ናት ለማለት አስተሣሠብን መቀየር ነው እኩልነት ማለት እውነታውን ተጋፍጦ ሠብአዊ መብቶቿን ማስከበር ነው😌
አለም ላይ ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሴቶች ገንዘብ ለማግኘት ሴተኛ አዳሪነት ይሠራሉ !
ከአንዲት ትንሽ መንደር ጀምሮ እስከ ዋና ከተማ ድረስ በየ 15 ደቂቃ ልዩነት ውስጥ አንዲት ሴት ያለፍላጎቷ በዘመዷ ወይ በአሠሪዋ ተገዳ ትደፈራለች ! ከነዚህ ውስጥ 47%የሚሆኑት እድሚያቸው ከ14 አመት በታች ነው !

' ሴትነት ማለት የበደል ምሣሌ
የተረጅነት ምልክት
የቁጭትና ስሜት ማብረጃ
ሴት ሲባል ጥገኛ
ሴት ማለት ገንዘብ የሚገዛት ምናምን የሚሉ አስተሣሠቦችን ቅድሚያ ማፅዳት ነው!🤧

የሴቶች መብት አቀንቃኝ /ፌሚኒስት / ነን የምትሉ ሠዎች ከወረቀት ያለፈ ስራ ብትሠሩ በሂደትም ቢሆን ለውጥ ይመጣል ባይ ነኝ !

የተሰበሩ ልቦች...

21 Oct, 19:36


ስለ ሴት ልጆች PESSIMISTIC የሆነ አስተሳሰብ
ያላቹ ወንዶች ትኖራላቹ ግን ስለ ሴት ልጅ መጥፎ
ነገሮችን እየነጠሉ ማውራት FAIR አይደለም እኔ
በበኩሌ ስለ ሴት ልጅ ባህሪ የተረዳሁት የሆነ
ነገር ልበል !
ሴት ልጅ እኮ ከባድ ፍጥረት ናት! ጭንቅላታቸው በአንዴ ብዙ ነገር መስራት ይችላል...
በጀርባዋ የ3 አመት ልጇን አዝላ እያስተኛች በፊት በኩል ደግሞ የስድስት ወር ልጇን እያጠባች ኪችን ውስጥ ምግብ ኩክ እያደረገች ላውድ ሲፐከር ላይ አድርጋ ባሏን እራት ልጠብቅህ ልትል ትደውላለች... አኛ አህዮቹ ደግሞ ኳስ እያየን እንኳን ስልክ አናነሳም ብናነሳም ኳስ እያየን ከቀልባችን ሆነን ማውራት አንችልም... ሃቅ ነው!!
" በኛም ብሶ ደግሞ ሴት እንንቃለን!!
ወንድ ልጅ በአንዴ ሶስት ስራ መስራት የሚችለው ሻወር ውስጥ ብቻ ነው!
ሻወር እየወሰደ  በዛው ጥርሱን እየቦረሸ  በዛው ሻወር ውስጥ መሽናት ነው !

መልካም ምሽት ሴቶችዬ☺️

የተሰበሩ ልቦች...

21 Oct, 19:20


ፅድቅና ኩነኔ ቢኖር ኖሮ ብቸኝነት ፅድቅ በመንጋ መሆን ደሞ ኩነኔ ሆኖ ይቆጠር ነበር ቢሆንም ባይሆንም ግን ብቸኝነት ፅድቅ ነው ::
መንጋነት ለኔ እንስሳዊነት መስተጋብር እንደሆነ ነው የሚሰማኝ
ምክንያቱም እራስን በመንጋ ከመክፈል የሚገኝ ፅድቅ አይታየኝም..!
ብቸኝነት ደስታ ነው😃
ብቸኝነት ጥንካሬ ነው💪
ብቸኝነት ምርጫ ነው🫶🏾

የተሰበሩ ልቦች...

21 Oct, 17:27


Old memories really hit hard when you know that bond is never coming back...


الذكريات القديمة تتضرر بشدة عندما تعلم أن هذا السند لن يعود أبدًا...

የተሰበሩ ልቦች...

21 Oct, 17:02


ብዙ ግዜ ከሰዎች ጋር የማልስማማበት ነገር ቢኖር የሴት ጉዳይ ነው ለእኔ ሴቶች በራስ ወዳድነት (Ego)የተሞሉ,ጥቅመኞች (Advantageous) & Opportunistic) ናቸው።
ወንድ አብዛኛው ግዜ ሞኝ ነው ለማፍቀር ብዙም Criteria አያወጣም ከወደደ ወደደ ነው ሴቶች ብዙ Criteria ያወጣሉ ትዳር ላይ ሲበዛ ያልተነቃበት አምባገነናዊ መንገድ ይከተላሉ።የወንዱ ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ በጣም ይጥራሉ, አብረቅራቂ ነገር ግን ዋጋ የሌላቸው ነገሮች ይወዳሉ ብዙ ግዜ ወንድ የሚፈልጉት Economical ችግራቸው እንዲቀርፍላቸው ነው።ውሏቸው,ሂወታቸው, ፍላጎታቸው ይነግሩታል የሱን ግን መስማት አይሸሹም ብዙ ግዜ Artificial character ያላየው Romantic የሚመስሉ አጭበርባሪ ወንዶች ይወዳሉ።ሲካዱ ደግሞ ያለቅሳሉ የተግባር እና serious የሆነ የሞራል ሰው አያወዱም ይባስ ብለው ደባሪ እንደሆነ ያስባሉ።ወንድ ዝም ሲል ወይም አይናፋር አልያም ኩሩ እንደሆነ ይደመድማሉ ዝምተኛነት የባህሪ አንዱ አካል መሆኑ ይዘነጉታል። ሁሌም ወንድ Comedian እንዲሆንላቸው እና እንደ አሻንጉሊት እንዲያስቃቸው ይፈልጋሉ።በወንዱ ልብ ያለው ከፍታ እና ዝቅታ አይመረምሩም ዝም ሲል ወይም በስራ ምክንያት ሲደብረው ፍቅር የቀነሰ ይመስላቸዋል እንዳይከዳት ትፈራለች።ሌላው በራስ መተማመናቸው (Confidence) ዝቅተኛ ስለሆነ መስተዋት ላይ ተጥደው ይውላሉ።ባገኙት ትንሽ ስልጣን ወንድ Abuse ለማድረግ ይፈልጋሉ የወንድ ልጅ ስቃይ ለነሱ አንዳንዴ እንደ Orgasm ነው ትንሽ ፊደል ሲቆጥሩ እማ ተወው ከጥራዝ ነጠቅነት አልፈው ፀረ-ወንድ or Feminism የዘመናዊነት አንዱ መገለጫ አድርገው ይወስዱታል በትልቅ የበታችነት ስሜት(Inferiority complex) የተጠናወታቸው ናቸው።ጠጠር ያለ ወሬ ሲወራ ያሳክካቸዋል Serious የሆነ ርእስ ሲነሳ ይደብራቸዋል ሁሌም የሚያስቅ ትርኪሚርኪ እንዲወራ እና ሰው እንዲቦጨቅላየው ይወዳሉ ለዛ ነው ሴቶች ፖለቲካ,ፍልስፍና ንባብ ስራ ሲወራ
የሚደብራቸው የማይስማሙበት ነገር ከተናገርክ ይጠሉካል በ logic አይሞጉቱም የdialectics አቅማቸው ሲበዛ ትንሽ ነው የዳበረ ንግግር አይናገሩም አንዳንደ ሴቶች የወንድ የቤት ተፈጥሯዊ መሪነቱ ለመንጠቅም ይሻሉ የሴት Weird የለውም ሁሌም ሀይማኖት ውስጥ እና ባህል ውስጥ መሆናቸው ራሳቸው እንደ ጨዋ ይቆጥራሉ ለዛ ነው አፈንጋጭ ሴት ማየት ተአምር የሆነው።

አስመሳይነታቸው ለማየት ሴት ለሴት ያላቸው መነከካስ ማየት በቂ ነው።
በአጠቃላይ አካላዊ ሞራላዊ እና መንፈሳዊ ጥንካሬ በሚፈልገው ነባራዊ አለም ስትወድቅ መነሳት በሚፈልገው የአለም ባህሪ የወንድ አሸናፊነት ግድ ይሆናል!

የተሰበሩ ልቦች...

21 Oct, 16:50


❤️‍🩹

2,293

subscribers

48

photos

6

videos