የማርያም አገልጋይ

@ye_mariam_agelgay


ጌታ ሆይ ወጣትነቴን ባርክልኝ የምፈልገውን ሳይሆን የሚጠቅመኝን ስጠኝ ስለ ራሴ ከኔ በላይ አንተ ታስብልኛለህና
የአባቶቻችንን አርያ በመከተል ወንጌል የምንማርበት ቻናል ነው !
መንፈሳዊ ትምህርቶች ስብከት መዝሙር ይቀርብበታል

ለአስተያየት @asrategabriel

የማርያም አገልጋይ

21 Jan, 00:27


. #ጥያቄ ስለ ከበሮ .

💁 ከበሮ ማለት ምን ማለት ነው
🥁 ከበሮ የምን ተምሳሌት ነው ⁉️
💁 የከበሮ ጨርቅ ለምን ቀይ ብቻ ሆነ
💁 ከበሮ ዉስጡ ለምን ባዶ ሆነ ⁉️

👉ሌሎችም ጥያቄዎች......የቀሩትንም ለማየት

የማርያም አገልጋይ

21 Jan, 00:16


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓

የማርያም አገልጋይ

21 Jan, 00:15


የእግዚአብሔር ጊዜ


እግዚአብሔርን የሚጠብቁ እጆች አያፍሩም እግዚአብሔር ሁሉን ነገር ባሟላልን ጊዜ እርሱን የምንረሳበት ምክንያት የእግዚአብሔርን እጅ አለመጠበቃችን ነው ባርክልኝ አለማለታችን ነው።

ተመልከቱ እግዚአብሔር እርሱን ተስፋ ያደረጉትን መቼም አይጥልም

አሁን ባሳለፍነው ሳምንት አንድ የውጪ ዜጋ አሜሪካዊ በአሜሪካ በተነሳው አውሎ ነፋስ ምክንያት ሁሉም ሰው ሀገሩን ለቅቆ በሚሄድበት ጊዜ እርሱ ግን አንድ እግር የሌለው ቢሆንም ተስፋው በእግዚአብሔር ነበረ።

ሰማይ ምድሩን ያናውጽ የነበረው አውሎ ነፋስ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ስለሆነ ምንም አልሆነም ያመንኩት አይጥለኝም ሲል ለሀገሩ ነዋሪዎች ምላሽ መልሶ ወደ አንድ ጀልባ ወጥቶ በዚያ ተጠቀመጠ ይህ አውሎ ነፋስ ብዙ ነፍሳትን ሲቀጥፍ ይህ እግዚአብሔር ተስፋዬ ነው አይጥለኝም ጋሻዬ ነው

መከታዬ ነው
ኃይሌ ነው
ጉልበቴ ነው
ሙላቴ ነው እንዳለው ሰው ሁሉ ስለ እርሱ ሲጨነቅ ምንም ማድረግ ባይችልም እርሱ ተስፋውን የጣለበት አምላክ ተስፋውን አለምልሞ ዛሬ ለምስክርነት በህዝቡ ፊት ቆሞ አምላኳን የረሳች አሜሪካ ፊት ስለ እግዚአብሔር በሙሉነት ይመሰክራል እግዚአብሔር በህይወቱ የሰራለትን በኩራት ይናገራል ።

እግዚአብሔር በህይወታችን ሲሰራ የእውነት ነው
እግዚአብሔር በህይወታችን ሲገባ በበረከት ነው አይሆንም ያልነው እያስገረመን ይፈጸማል ።

ብዙ አላልፍም ያልነው ፈተና እንደቀላል ወደኋላ ይቀራል
አሁንስ ተስፋዬ ማነው እግዚአብሔር አይደለምን ያለው ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት በህይወቱ የተደረገውን ድንቅ እውነት ተመልክቶ ነው

እኔ ኃጢተኛ ነኝ የሰው ደም በእጄ ፈሷል ብሎ ተስፋ ሲቆርጥ እግዚአብሔር በልጅህ መቅደሴ ይሰራል ብሎ ተስፋ ሰጠው እግዚአብሔር መቼም ቢሆን በህይወታችን በሰጠነው ቦታ በሚያስደንቅ ለውጥ ይሞላናል

የልባችንን መሻት ያያል ቅዱስ ጳውሎስ ያስገርመኛል እግዚአብሔር ግን ዓላማ ነበረው በርሱ እርሱ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲወገር የወጋሪዎቹ ልብስ ያዥ ነበረ እግዚአብሔር ግን ያየው ልቡን ነው ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲወገር እያሰበ የነበረው የእግዚአብሔር ፈጣሪ ተቃዋሚ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተወገረ እግዚአብሔር ከበረ ብሎ ነበረ እያሰበ የነበረው እግዚአብሔር በአገልጋዩ የፈጸመውን በድል ሳይሆን ያየው የልቡን ለእግዚአብሔር ተገዢነት ነው ለዚህም ነው በደማስቆ በፍቅር የማረከው

እኛም በእግዚአብሔር ተስፋ ከመቁረጣችን በፊት ለእግዚአብሔር በልባችን ቦታ እንስጥ የዚያኔ ህይወት በአዲስ መልክ ይጀምራል ይፈካል

በህይወት እስካለን በጸሎት እንትጋ ከወዳጅ መሳይ ጠላት ዲያብሎስ ይጠብቀን አሜን


ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ዲያቆን አቤኔዘር ሙሉ

ጥቅምት/4/2017 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 23:58


#እሬቻ_ላይ_የሚከብረው_እግዚአብሔር_አይደለም_ዲያብሎስ_ነዉ።

🔵 እሬቻ ከክርስትና እምነት ጋር ፈጽሞ ተጻራሪና ጸረ ነፍስ ነው። የእሬቻ የዛር መንፈስ እንጂ ከመንፈስ ቅዱስ አይደለም። ለእግዚአብሔር እንጂ ለዛፍ አትንበርከክ። ለሚያልፍ ፖለቲካ የማያልፍ እግዚአብሔርን አናስቀይም።

"በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ " ኢሳይያስ 1፥29

🔵 እሬቻ ደብረ ዘይት [ቢሾፍቱ] ሆራ አርሰዲ ሓይቅ ዙርያ አርሰዲ የሚባለው መንፈስ እየተወደሰ አንዲት የአድባር ዛፍ ስር ይከበራል። ኢሬቻ የራሱ ካህናት አሉት።

🔵 ተከታዮቹም የሚገብሩት ራሱን የቻለ ግብር አለ። የአድባር ዛፏ ቅቤ ትቀባለች። ሐይቁ ውስጥ አለ ተብሎ ለሚገመተው ቆሪጥም የስለት አረቄ ይጣልለታል። ደስ እንዲለውም ከብት እየታረደለት ደም ይጠጣል። ሞራ ገላጮች "ትንቢት" ይናገራሉ። አማኞችም ተንበርክከው ተረፈ መስዋዕትን ይበላሉ።

🔵 ቪድዮውንና ፎቶውን ይመልከቱ። ቪድዮው ላይ ቁልጭ ብሎ እንደምትመለከቱት ኢሬቻ ሲደርስ አርሰዲ ለሚባለው መንፈስ የደም ግብር ይቀርብለታል። ደም ይጠጣል። የተረፈውን መስዋት ደግሞ ተከታዮቹ ይበሉታል። አርሰዲ የተባለው የኢሬቻ መንፈስ ደም ከጠጣ በኋላ - የኢሬቻ ካህን የሆኑት ወገኖች ላይ አድሮ ያስጓራቸዋል። መንፈሱ አርሰዲም "እኔ ሰው አይደለሁም። መንፈስ ነኝ። አልሞትም ወዘተ" እያለ ይፎክራል። የዛር ፈረስ በመባል የሚታወቁት ካህናቱም ለታመመ "ፈውስ" ይሰጣሉ።

🔵 እነዚህ የኢሬቻ ካህናት ኢሬቻ ሲከበር ሆራ አርሰዲ ያለችው የአድባር ዛፍ ስር እየተገናኙ ድቤ ይመታላቸዋል። ሆራ ቀውጢ ትሆናለች። ያቺ የአድባር ዛፍም ቅቤ ትቀባለች። በግምጃ ታጌጣለች። የሽቶ አይነት ይርከፈከፍላታል። ወዘተ . . . ማንም ሰው የፈለገውን ማምለክ ይችላል። መብቱ ነው። እጁን ወደሚያቃጥለው ወይም ወደ ቀዘቀዘው ውሃ የመክተት ነጻ ሕሊና አለው። መዘዙ ግን በኋላ ነው- የዛሬ ሳቅ የነገ ለቅሶ ስትሆን! ግን ኢሬቻ በሃይማኖት በተለይም በክርስትና አይን ሲታይ ምንድነው? ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ኢሬቻን ማክበር ይገባዋልን? መልሱን መፅሐፍ ቅዱስ በማያሻማ ሁኔታ እንዲህ ሲል ይነግረናል።

🔵 "በወደዳችኋት የአድባር ዛፍ ታፍራላችሁና፥ " ኢሳይያስ 1፥29፤ እርግጥ ነው ኢሬቻ የምስጋና ቀን [thanksgiving] ነው። ግን የሚመሰገነውና የሚክብረው ማነው? አርሰዲ የሚባል ደም የሚጠጣ ክርስቲያናዊ አምላክ ወይም ቅዱስ መንፈስ የለም። የኢሬቻን ካህናት የሚያስጓራው ዛር ከክፉው እንጂ ከቅዱስ መንፈስ አይደለም። የክርስቶስም መገኛ ዛፍ ስር ወይም ሐይቅ ውስጥ አይደለም። የራሱ መመለኪያ ቦታ አለው።

🔵 ሳር የሚበተንለት፣ ስለት የሚገባለት፣ ከብት ታርዶ ደም የሚረጭለት፣ የሆራው ቆሪጥ ርኩስ መንፈስ እንጂ ቅዱስ መንፈስ አይደለም።  ዛፍ ምን ስለሆነ ነው ቅቤ የሚቀባው? እንዴት ክርስቲያን ራሱ ተክሎ ላበቀላት ዛፍ ይሰግዳል? እንዴትስ እንደ አምላክ እየታየ ቅቤ ይቀባል። ለምን ህዝብ ይንበረከካል ? ለምንስ ዛፍ ግምጃ ያለብሳል? እኛ ክርስቲያኖች በአምልኮ ልንሰግድለት፣ ልንበረከክለት የሚገባን አንድ አምላክ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንጂ ዛፍ አይደለም።

🔵 እዚህ በዓል ላይ መገኘትም ሆነ መታደም በክርስትና ዓይን ፈጽሞ የነፍስ ስብራትን የሚያመጣ አምልኮ ባዕድ ነው። ጮክ ብዬ እደግመዋለሁ:- እሬቻን ያከበረ ክርስቲያን በእግዚአብሔር ፊት መጠየቁ አይቀርም። እሬቻ ላይ እግዚአብሔር አይከብርም። እርግጥ ነው:- ዛሬ ፖለቲካው ሃይማኖት ሆኗል። ብዙዎቹንም ፖለቲካ ከሃይማኖት በልጦባቸው "እሬቻ" አይነኬና አይደፈሬ ፖለቲካዊ ሃይማኖት ሆኗል። ትሰሙ እንደሆነ ለራሳችሁ ስትሉ ስሙ መቼም ቢሆን የጅብ ራስ ከመሆን ያንበሳ ጭራ እንሁን! ፖለቲከኞች ተደስተውብን እግዚአብሔር ከሚያዝንብን - መንጋው ጠልቶን እግዚአብሔር አይፈርብን። በነጻነት ስም በአምልኮ ባዕድ አተላ አንጠመድ። ወፍጮ ቤት ገብቶ ብናኝ ዱቄት ሳያገኘው የማይወጣ ሰው የለም። እንዲህ ዓይነት በዓላትም ላይ ተሳትፎ በመንፈሱ የማይወጋ አይኖርም። ወደሽ ከተደፋሽ - ቢረግጡሽ አይክፋሽ ነው ነገሩ። ዛሬ በዓል ያከበርን መስሎን ያደመቅነው የመንፈስ በዓል ነገ spiritual parasite ሆኖ እድሜ ዘመናችን ዋጋ የሚያስከፍለን እንዳንሆን!

🔵 ሞቀ ደመቀ በሚል በይሉኝታ ወይም በአድባርይነት የአምልኮ ባዕድ ሰባኪዎች የሆናችሁም - ነገ በእግዚአብሔር ፊት ዋጋ ትከፍሉበታላችሁ። የማይረባ የዘር ፖለቲካ ሰማይ ቤት ተክትሎህ አይሄድም። ዛሬ የሰበካት ውሸት ነገ ሰማይ ቤት እሳት ሆና ትበላሃለች። ዛሬ ለዛፍ እንዲሰግድ፣ ዛፍ ቅቤ እንዲቀባ ባደረከው ሕዝብ ነፍስ ነገ ለፍርድ ትቀርባለህ።

🔵 የመጨረሻው ዘመን ስለሆነ ሚሊዮኖች ይተማሉ። ርኩሰትም በተቀደሰችው ሀገር ይበዛል። ሌላው ቀርቶ መስቀል ይዞ የክርስቶስን ቀሚስ ለብሶ "እሬቻ ክርስቲያናዊ ነው" ብለው የሚሰብኩ ተረፈ ይሁዳዎች በየሚድያው ይበዛሉ። የመጨረሻው ዘመን ላይ ነን። ትንቢቱ ይደርስ ዘንድ ግድ ነው። ግን አንተ እግዚብሔርን እንጂ ዛፍን አታምልክ። ለቅዱስ መንፈስ እንጂ ለዛር አትገብር። ለክርስቶስ እንጂ ለአርሰዲ አትሸበር። "እሬቻ ኦርቶዶክሳዊ ወይን ኦሪታዊ ነው" የሚሉ በለአሞችን አትስማ። ስለበዙና መንጋ ስለሆኑ የቁጥራቸው ብዛት ያንተን እግዚአብሔርን አያስፈራውም። አንተንም በቁጥር አነስክ ብሎ አይንቅህም። ብቻህን ብትቀር እንኳን ከእውነት ጋር ብቻህን ኑር። አሸናፊው አንተ ነህ። ግን ሁሌም እውነትን እውነት በል።

🔵 እንኳን ለእሬቻ አደረሳችሁ ወይም መልካም እሬቻ ከማለታችን በፊት ደጋግመን ቃሉን እናስበው። ለማን አምልኮ በዓል አደረሳችሁ እያልን እንደሆነ እያስተዋልን።

🔵 እግዚአብሔርንም አመልካለዉ እያላችሁ ነገር ግን [ከእሬቻ፣ ከጨንበላላ፣ ከጊፋታ፣ በመስቀል ስም በሌሎች ባህላዊ አምልኮ ስም] ሰጥታችሁ ከምታመልኩት ጣዖት አምልኮ ባስትመለሱ መጨረሻችሁ ገሃነም እሳት ነው።

“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኵሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ሁሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ሁለተኛው ሞት ነው።”
  — ራእይ 21፥8

“የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።”
  — 2ኛ ቆሮ 13፥14

#የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
🔵 መልዕክቱን ለሌሎች አድርሱልኝ።

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 23:48


መስቀል ሃይላችን ነው ፣መስቀል መፅናኛችን ነው ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው ።
አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን ድነንማል።
የተወደዳቹ የቻናላችን ቤተሰቦች
እንኳን ለታላቁ የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 23:47


# ልዩ የመሰቀል ደመራ ፕሮግራም !!
     ✝️✝️✝️
#የሶዶ_ወረዳ_ቤተክህነት_ልዩ_የደመራ_ዝግጅት
በምሥራቅ ጉራጌ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከት የሶዶ ወረዳ ቤተክህነት አስተባባሪነት በተዘጋጀው የደመራ በዓል የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ልዩ ፕሮግራም በቡኢ ከተማ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
✝️✝️✝️
እርስዎም የበዓሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ እናሳስባለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
✝️✝️✝️
የምስራቅ ጉራጌና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ሰብከት !
መስከረም 11/01/2017 ዓ.ም
             ቡኢ
          ኢትዮጵያ
         ✝️✝️✝️

#ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 23:22


👉 ያለፈው ዘመን ይበቃናል 👉
    ፩ ጴጥ ም ፬ ቁ ፫
                   4     3

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

🙏 እንኳን ለሊቀ መላዕክት ለቅዱስ ሩፋኤል በዓለ ሢመት አው ለካህኑ መልከጼዴቅ በዓል አደረሳችሁ አደረስን 🙏

👉 ጳጉሜን ፫ (3) በዓለ ሥሉስ ቅዱስ በዓሉ ለቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላዕክት ወመልከጼድቅ ወሰራጵዮን ወዘርያዕቆብ ንጉሥ ኢትዮጵያ 👉

👉 ዘነግህ ምስባክ 👉

መሐለ እግዚአብሔር ወኢይኔስሕ
አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሢመቱ ለመልከጼድቅ
እግዚአብሔር በየማንከ

✥ ትርጉም ✥

እንደ መልከጼዴቅ ሥርዓት አንተ ዘላለም ካህን ነህ ብሎ
እግዚአብሔር ማለ አይጸጸትም
እግዚአብሔር በቀኝህ
   
   መዝ ፻፱-፬
        109  4

✤ ወንጌል ✤

ሉቃ ም ፲፯ ቁ ፳-፴፩
           17   20  31

የቅዳሴ ምንባባት

ዕብ ም ፯ ቁ ፩-፭
ይሁዳ ም ፩ ቁ ፲፩-፲፯
ግብ.ሐዋ ም ፭ ቁ ፲፯-፳፮

❖ ምስባክ ❖

እግዚአብሔርሰ ገሃደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነደድ ቅድሜሁ

🙏 ትርጉም 🙏

እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል
አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል
 
    መዝ ፵፱-፪
          49   2

❖ ወንጌል ❖

ማቴ ም ፳፭ ቁ ፴፩-ፍ.ም
            25    31   ፍፃሜው

❖ ቅዳሴ ❖

ያዕቆብ ዘሥሩግ(ተንሥኡ)

" የብርሃናት ፈጣሪ ሆይ ጨለማን የደፋው ጣዖትንም የሻረው በሞቱ ሞት ያጠፋው "
     ቅዳሴ ያዕቆብ ዘሥሩግ
           ም ፩ ቁ ፹፫
                1     83

በዓሉ በዓለ ምህረት በዓለ ድኀነት ያድርግልን ቸሩ መድኃኔዓለም በቸርነቱ ይማረን እመ አምላክ እግዝእትነ ማርያም በምልጇዋ ትጠብቅን ከሊቀ መላዕክት ቅዱስ ሩፋኤል በረድኤቱ ይጠብቅን ካህኑ መልከጼዴቅ በረከቱ ይደርብን ድርሳነ ሩፋኤል ገድለ ቅዱሳን ዕጣነ አሮን መስዋዕት መልከጼዴቅ የተቀበለች የኛም ፆም ፀሎት ጥምቀት ምሕላ በቸርነቱ በብሩህ ገጽ ይቀበልልን ለበዓለ ዓውደ ዓመት በሰላም ያድርሰን

                  ✧ ምስባክ ✧

#ድምፀ_ተዋህዶ

           YouTube chnnl
👇🏽🔻 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘 🔻👇🏽
        
የይቱብ ቻናላችን
             🔔
  🔺 𝒔𝒖𝒃𝒔𝒄𝒓𝒊𝒃𝒆 𝒏𝒐𝒘🔺‌‌


❤️በናታኒም ቲዩብ❤️
         👇🏽👇🏽
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4
https://youtu.be/MsXeCVCPxX4

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 22:42


🔴አዲስ አበባ
ይህንን ቤተክርስቲያን ለኮሪደር ልማት በሚል ምክንያት እንደ ሱቅ መንገድ ላይ ቤተመቅደሱን ብቻ ባዶውን ሊያስቀሩት ነው።
በማንኛውም ማሕበራዊ ሚዲያ ድምፅ ሆነን ከመፍረስ እናድነው።
➟ከኪነ-ጥበብ

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 22:35


† "በጽዮን መለከትን ንፉ:: ጾምንም ቀድሱ:: ጉባዔውንም አውጁ:: ሕዝቡንም አከማቹ:: ማሕበሩንም ቀድሱ:: ሽማግሌዎችንም ሰብስቡ:: ሕጻናቱንና ጡት የሚጠቡትን አከማቹ:: ሙሽራው ከእልፍኙ: ሙሽራይቱም ከጫጉላዋ ይውጡ::"

         †(ኢዩ. 2:15)

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †

#አቤቱ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ ጌታ ሆይ ማራቸው
ከፍ  ከፍ አድርጋቸው/2/

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!

#ድምፀ_ተዋህዶ

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 22:18


#ቅዱስ_ቂርቆስና_እናቱ_ቅድስት_ኢየሉጣ (#ሐምሌ_19)

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው። 

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው። 

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ። 

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ። 

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። 

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው። 

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና። 

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው። 

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ ➛ ስንክሳር ዘተዋሕዶ ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ)

#ድምፀ_ተዋህዶ

የማርያም አገልጋይ

20 Jan, 21:59


እንኳን ለቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ዓመታዊ የሰማዕትነት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችኁ፤ አደረሰን።

"ሰላም ለከ ጴጥሮስ ተልሚድ፤ ዘኢያቅበጽከ ተስፋ ነገረ ኑፋቄ ወካህድ፤ እንዘ ትረውጽ ጥቡዐ ለመልእክተ ክርስቶስ ወልድ፤ አመ ለሊከ ወሬዛ ቀነትከ በእድ፤ ወአመ ልህቀ አቅነተከ ባዕድ።"

"ሰላም ለጳውሎስ ሃይማኖተ ክርስቶስ ዘአግሀደ፤ እስከ አቊሰልዎ በሰይፍ ወመተርዎ ክሣደ፤ ከመ ያግብእ ሕዝበ ህየንተ ቀዳሚ ሰደደ፤ በላዕለ አብዳን ተመሰለ አብደ፤ ወለአይሁድኒ ኮኖሙ አይሁደ።"

❖ ሐምሌ ፭ ❖

✞ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ [የምስክርነታቸው መታሰቢያ]፤ ቅዱሳት አንስት:- ዴውርስ፣ ቃርያ፣ አቅባማ፣ አቅረባንያ፣ አክስትያና (የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታዮች) [መታሰቢያቸው]፤ ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (የቅዱስ ጴጥሮስ ደቀ መዝሙር) [መታሰቢያው] የሚከብርባት ዕለት ናት✞

12,405

subscribers

435

photos

178

videos