የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿ @yewqetabugida67 Channel on Telegram

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

@yewqetabugida67


_____________✿❀__________

... እንኳን ደህና መጣችሁ
"ኑ እናንብብ አብረን በእውቀት ከፍታ እናብብ!"

_____________❀✿___________
መልካም መስራት ክፉ ከማሰብ ይልቅ የበለጠ ደስ ይላል፡፡

ለማንኛውም፦
መልዕክት
ጥቆማና ቅሬታ @Ayuma

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿ (Amharic)

የእውቀት-አቡጊዳ መልካም ችግር እና ምላሽ የሚያስፈልጋቸው የበለጠ ደስ አሳልፈዋል። እንኳን ስለጠበሱት ማህበረገፊያ ቅሬታ ፍላጎት ነው። ይህ በአሁኑ ሰአት በእውቀት ከፍታ እጅግ ለመመልከት ያሳልፋል። ስለሆነ፣ በዚህ እፅዋት ተከላካይነትና የቀላልነት ያስከትልነው ምላሽ ሳብስና ችግር ከእናት ኣፕ ወይስ ከሕይወት መሰል የበለጠ ፍላጎት ነው። አዲስ ቆይታዎችንና ቅሬታዎችን ለማግኘት ይህንም ችግር እና ምላሽ ይምለከታል። ለማቅዘመን ተጨማሪ ለአሁን ግን ቆይታዎችን ለመዘጋጀት በዚህ ቦታ በመከታተል ከቀለም ውስጥ በአቡጊዳ ያለው አገልግሎት አለ።

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

09 Mar, 15:43


#የፍቅር_አቦጊዳዬ ❣️#ክፍል12 💓
እንደ አጋጣሚ ሆኖ #ሀናም አብራኝ እዚው ት/ት ቤተ ተመዝግባ አገኘዋት፡፡ የትምርት የመጀመሪያው ቀን ላይ የዜግነት ክብር ከተዘመረ በኀላ "ተማሪዎች ስማችሁ በተለጠፈበት ክፍል ግቡ፤ ስማችሁ ያልተለጠፈ ካላችሁ እንደ አዲስ እንድትመደቡ አመልክቱ፡፡" ተባለ፡፡ እኔም በቀጥታ አመልክቱ ወደተባለበት ቦታ አመራው፡፡ አንደ መላጣ አስተማሪ ወንበር ላይ ተቀምጧል፡፡ "ምን ነበር?" አለኝ በቀና መልኩ፡፡ "ስመዘገብ የተነገረኝ ክፍል ጋር ስሜ አልተለጠፈም።" አልኩ አይኔን ግንባር ያርገው ብዬ፡፡
ስመዘገብ 9A እንደተመደብኩ ተነግሮኛል፡፡ ስሜም ተለጥፏል፡፡ ነገር ግን ሳጣራ #ፀጊ 9E ነው የተመደበችው፡፡ እና ምናልባት አጭበርብሬም ቢሆን ለአንዴ እንኳን እሷን እያየው ብማር ብዬ ነበር በውሸት ስሜ አልተለጠፈም ያልኩት፡፡ መላጣውም "የት ነበር ተመድበሀል የተባልከው?" አለኝ፡፡ ወፈርና ጠንከር ባለ ድምፅ "9A ነው" ብዬ መለስኩ፡፡ "ok ሲፅፉ ዘለውት ይሆናል፤ መጨረሻ ላይ ልፃፍክና ይስተካከላል" ብሎ ስሜን ከ9E የስም ማህደር ላይ ለማስፈር እስክርቢቶ አነሳ፡፡
"ግን ቆይ እስኪ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ አብረን ቼክ እናርገው፤ maybe ሌላ ክላስ መድበውክ ይሆናል።" አለና ደስታዬ ላይ ውሃ ቸለሰበት፡፡ ከዛም የሁሉንም ክላስ የስም ዝርዝር አውጥቶ ሲፈልግ ብዙም ሳይለፋ ስሜን 9A ላይ አገኘው፡፡ እኔም "ማሽላ እያረረ ይስቃል" እንዲሉ የይስሙላ ያህል ፈገግ ብዬ አመስግኜው ወጣው፡፡
9A ገባውና ባዶ ወንበር ፈልጌ ተቀመጥኩ። ወዳው ክላሱን ከዳር እስከዳር በእይታዬ አካለልኩት፡፡ እንኳን ከእኔ ት/ት ቤት የመጣ ለመተዋወቅ ነፃነትን የሚጋብዝ አንድም ተማሪ የለም፡፡ አብዛኞቹ ግን ከምኔው ተዋወቁ በሚያስብል መልኩ አፍ ለአፍ ገጥመው ያወራሉ፡፡ ለነገሩ እኔ ነኝ እንጅ ፍቅርን ብዬ ተሰድጄ የመጣውት በብዛት 8ኛንም እዚው የተማሩ እንደሆኑ ያስታውቃሉ፡፡
👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 13 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

06 Mar, 17:10


#የፍቅር_አቦጊዳዬ ❣️#ክፍል11
ውጤት ሊወጣ 2ሳምንት አካባቢ ሲቀረው እቤት አዲስ የምመደብበት ት/ት ቤት እንደማልማር፤ በአንፃሩ ከሰፈራችን ወደ 2ኪሜ ርቆ በሚገኝ #አፄ_ናኦድ የሚባል ት/ት ቤት መግባት እንደምፈልግ በቁጣ ጭምር ተናገርኩ፡፡ እናቴ ት/ት ቤቱ ከተማ ስለነበር "ማን ሊያመላልስህ ነው? መኪና ይባላሀል፤ አይሆንም እዚው ምትመደብበት ት/ት ቤት ትማራለህ አለች፡፡ እኔ ግን ስለምመደብበት ት/ት ቤት እውነት የሆነውንም ያልሆነውንም ብዙ መጥፎ ነገር ተናገርኩ፡፡ በተጨማሪም የሚወስደኝና የሚያመጣኝ ትራኖስፖርት ነው፤ በዛ ላይ የማቃቸው ብዙ ተማሪዎች አሉ፤ ስለዚህ እዛ ነው ምገባው ብዬ ደመደምኩ፡፡
በስተመጨረሻ በእኔ ኩርፊያ ታግዞ በአባቴ አፅዳቂነት ከአንድ አመት በኀላ ከልቤ ላይ ንግስት ከፀጊ ጋር አንድ ት/ት ቤት እንደምማር ተወሰነ፡፡ የተሰማኝ ደስታ ልክ እሷን በእጄ ያስገባው ያህል ነበር፡፡
ክረምቱ አለቀና የሚኒስትሪ ውጤትም ወጣ 87.5 አምጥቼ አለፍኩ፡፡ ውጤትን ከተመለከቱ በኀላ እቤት አዲሱ ት/ት ቤት መግባቴን ይበልጥ ደገፉት፡፡ የምዝገባውን ቀን ካጣራው በኀላ ከእናቴ ጋር ለምዝገባ የሚያስፈልገኝን ሙሉ መረጃ ይዤ #አፄ_ናኦድ ት/ት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተገኘው፡፡ ተመዝግቤ ከግቢው እንደወጣው #ፀጊን ከማላቃቸው እና 8ኛ ክፍልን ስትማር ካፈራቻቸው ጓደኞቿ ጋር አብራ ቁማ አየዋት፡፡ ከእናቴ ጋር በአጠገባቸው አልፈን ስንሄድ ለጓደኞቿ "ይሄ ነው ኤርሚያስ ማለት" ብላ በሌለውበት ስታስተዋወቅኝ ድንገት ሰማው፡፡ "አዎ ሁለት አመታትን እሷን በማፍቀር የከሳውት፣ የጠቆርኩት፤ እንዲሁም 7ኛ ክፍል የጀመርኩትን አሁን ለመጨረስ ተከትያት የመጣውት አዎ ኤርሚያስ እኔ ነኝ" አልኩ በውስጤ፡፡ ፍቅሬ አይጠወልግም፤ እንዲ እንደቀላል ደርቆ አይከስምም ብዬ በአዲስ ት/ት ቤት ዳግም ላፈቅራት አንድ ብዬ ጀመርኩ፡፡
    👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 12 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

26 Feb, 16:36


#የፍቅር_አቦጊዳዬ ❣️#ክፍል10
8ኛ ክፍል አብራኝ በምትቀመጠው #ሀና የመረጃ አቅራቢነት እና የደብዳቤ አመላላሽነት ወደማለቅ ተቃረበ፡፡ አሁን ካየዋት ወደ 7-8 ወራት ሆነኝ፡፡ ነገር ግን ለአንድም ቀን ተረስታኝ ውላና አድራ አታቅም ነበር፡፡

ሚኒስትሪ ተፈታኝ ስለነበርኩ በተወሰነ መልኩ ወደ ትምርቴ ትኩረት አረኩ፡፡ ግን ያ የድሮውን ጎበዝ ኤርሚያስ መልሼ ላመጣው አልቻልኩም፡፡ እናም እንደምንም የቻልኩትን በራሴ፤ ያልቻልኩትን ደሞ ከጎኔ ፈተና ላይ አብሮኝ ከተቀመጠው የት/ት ቤታችን ጎበዝ ተማሪ ኤርሚያስ ሰርቼ ፈተናውን ጨረስኩ፡፡

አሁን ት/ት ተዘግቷል፡፡ ለ3 ወራት ያለምንም ስራ እቤት ልቀመጥ ነው፡፡ ይህ ማለት ደሞ ለ3 ወራት ቀንም ሌትም ስለፀጊ እያሰብኩ ልቆዝም ነው፡፡ እናም እሷም እንደኔው ተፈትና እቤት ስለሆነ ውሎዋ በሆነ መንገድ እሷን የማየቱን መንገድ ማመቻቸት እንዳለብኝ አሰብኩ፡፡

እንደተለመደው ሁሌም የሚረዳኝ #ወገን ጋር ሄድኩ፡፡ እሱም አጣርቶ የሆነ ወጣት ማዕከል ሰርከስ እንደምትሰራ ነገረኝ፡፡ አላቅማማውም እገባለው አልኩ፡፡

ከሰፈር ልጆች ጋር አብረን ሂደን ተመዘገብን፡፡ ባያችኝ ግዜ በመገረም ፈገግ አለች፡፡ ግን አውርታኝም አውርቻትም አላቅም፡፡ ሰርከስ እንደሚታወቀው አንዱ በአንዱ ላይ የመደራረብ የቡድን ስራ ነውና እኔን ከእሷ የሚያነካካ ስራ ቢኖር ብዬ ተመኘው፡፡ ሁሌም ስንሰራ እሷ ከሌሎች ልጆች ጋር ነበር የምትመደበው፡፡ እና አንዳንዴ ሳላስበው አብረዋት በሚሰሩ ወንዶች እቀናለው፡፡ በተለይ እያወሯት ከሳቀችላቸው የቀሙኝ ያህል ይሰማኝ ነበር፡፡

ክረምቱ እያለቀ ሲመጣ ስለ 9ኛ ክፍል ማሰብ ጀመርኩ፡፡ ምክንያቱም እስካሁን የተማርኩበት ት/ት ቤት የሚያስተምረው እስከ 8ኛ ብቻ ስለነበር፤ ወደ 9 ያለፈ ተማሪ ሌላ ቦታ ነው ሚመደበው፡፡ ይህን የምመደብበትን ት/ት ቤት ደሞ ገና ማለፍ እና መውደቄን ሳላቅ ጠልቼዋለው፡፡ ምክንያቱም አልፌ የተመደብኩበት ት/ት ቤት ገባው ማለት ሙሉ በሙሉ ከፀጊ ተለያየው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እንደምንም ብዬ ቤተሰቦቼን አሳምኜ #ፀጊን ተከትዬ እሷ የገባችበት ት/ት ቤት መግባት አለብኝ ብዬ ወሰንኩ፡፡
👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 11 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

21 Feb, 15:20


#የፍቅር_አቦጊዳዬ ❣️ #ክፍል9
አሁን ነገሮች ይበልጥ ከበዱ፡፡ ለወትሮው ለቀናት ሳላያት ስውል የሚከብደኝ ልጅ አሁን ጭራሽ አመቱን ሙሉ ከአይኔ እራቀች፡፡ እንዲህ ነች ህይወት፤ በጣም የፈለከውን ነገር ከአይንህ በጣም አርቃ ትወስድብህና ከልብህ ለማራቅ፤ ተስፋ ለማስቆረጥ ትሞክራለች፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ ፍቅሬ ተስፋ ላለመቁረጥ ለእራሴ ቃል ገባው፡፡
"ሳይደግስ አይጣላም" አለ ያገሬ ሰው፤ ምንም እንኳን ፀጊ ከአይኔ እርቃ ት/ት ቤት ቀይራ ብትሄድም፤ የሰፈርና የት/ት ቤት ጓደኛዋ የሆነችው #ሀና ከእኔ ጋር አንድ ክላስ ደረሳት፡፡ አንድ ዴስክ ላይም መቀመጥ ጀመርን፡፡ ሁሉን ነገር ስለምታቅ ታዝንልኝ ነበር፡፡ በእየቀኑ ደንነቷን ከእሷ እሰማለው፡፡
መስከረም 17 የመስቀል ቀን ከሌሎቹ ቤተ-ክርስትያናት በተለየ መልኩ ሰፈሬ ያለው አንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያን የደመራ ፕሮግራሙ እንደሌሎቹ በ16 ሳይሆን በ17 ጠዋት ስለነበር እሱን ለማክበር ከሰፈር ልጆች ጋር ሄድን፡፡ የሰፈሬ ልጆች ግማሾቹ አብረውኝ አንድ ት/ት ቤት ይማሩ ስለነበር ሁሉን ነገር ያውቃሉ፡፡ አብዛኛውን ግዜ "አፍቃሪው" እያሉ ያበሽቁኝም ነበር፡፡
እና የእዛን እለት #ፀጊን ቤተ-ክርስትያን ውስጥ አይተዋት ኖሮ እኔ ሳላቅ አብሮን በነበረ አንደ የ8 አመት ህፃን ልጅ "ኤርሚያስ ሊያወራሽ ይፈልጋል" ብለህ ንገራት ብለው አስላኩ፡፡ ህፃኑ ደርሶ ሲመጣ "ና በለው" የሚል መልስ ይዞ ተመለሰ፡፡ በዚህ ግዜ ለእኔ ነገሩኝ፡፡ አገኛታለው ብዬ ስላላሰብኩ በጣም ደስ አለኝም፤ በጣምም ደነገጥኩ፡፡ እንደምንም ብዬ ሄድኩ፡፡
የአዱስ ት/ት ቤቷ እና የሰፈር ጓደኛዋና ጎረቤቷ ከሆነችው #ስንታየው ጋር ነበረች፡፡ ሁለቱንም ሰላም ብዬ አጠገቧ ተቀመጥኩ፡፡ በጣም እየፈጠንኩና እየተርበተበትኩ ስለአደመሱ ት/ት ቤቷ፣ ስለጤንነቷ አውርቻት ብዙም ሳልቆይ ተሰናብቻቸው ሄድኩ፡፡
አግኝቻት በተመለስኩበት ቅፅበት የተሰማኝ ነገር ቢኖር እንዲ በቀላሉ እንደማልተዋትና፡፡ እንደምከተላት ነው፡፡ ደሞስ ሰው እንዴት ከልቡ ያፈቀረውን ሰው አንዴ ብቻ ጠይቆ ለዛውም አሳማኝ ባልሆነ መንገድ እምቢ ስለተባለ ይተዋል??? አልተዋትም!!!
👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 10 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

15 Feb, 18:59


#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል8
#ክረምት አለቀና ዛሬ የምዝገባ ቀን ነው፡፡ ሰርተፍኬቴን ይዤ ከቤት እንደወጣው በቅድሚያ ሰፈሬ የሚገኘው አንቀፀ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያን እንዲሁም በመንገዴ የሚገኙት ገነተ እየሱስ እና ማርያም ቤተ-ክርስቲያን ገብቼ እኔን ከፀጊ ጋር አንድ ክላስ እንዲመድቡኝ ፀሎቴን አድርሼ ወደ ት/ቤት አመራው፡፡
በዛ እንደደረስኩም ክላስ እንዳዲስ ተቀላቅሎ ተመድቦ ስለነበር የማስታወቂያ ቦርዱ ላይ ስሜንና ስሟን ለመፈለግ ሄድኩ፡፡ 8A ላይ ስሟን ፈለኩኝ፤ የለም፡፡ 8B ላይ ፈለኩ፤ የለም፡፡ 8C ላይ ፈለኩ የለም፡፡ 8D ላይ ስፈልግ ስሟን አገኘውት፡፡ እዛው ክፍል የእኔን ስም ስፈልግ አጣውት፡፡ ቀኔ ተበላሸ፡፡ 8C,8B,8A ላይ የእኔን ስም አገኘውት፡፡
በዕደለ ቢስነቴ ተከፍቼ ተመዝግቤ ከግቢ ወጣው፡፡ በር ላይ ስደርስ ጓደኞቿ ከላይ ሲመጡ አየዋቸው፡፡ እሷ ግን አልነበረችም፡፡ ልቤ ፈራ፤ አጠገቤ እንደደረሱም ሰላም ከተባባልን በኀላ "ፀጊስ?" ብዬ ጠየኳቸው፡፡ ሁሉም በተከፋ ፊት እርስ በእርስ ከተያዩ በኀላ "እናዝናለን ኤርሚ ት/ቤት ቀይራለች።" ብለው አረዱኝ፡፡ ስጋዬ ከአጥንቴ የተላቀቀ መሰለኝ፡፡ ምንም ሳልል ትቻቸው ሄድኩ፡፡ ድንገት ሳላስበው እንባዬ ከአይኖቼ ዱብ ዱብ አለ፡፡ ለካ ይህን ያህል አፍቅሪያታለው አልኩኝ፡፡

👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 9 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

02 Feb, 14:08


#የፍቅር_አቦጊዳዬ ❣️#ክፍል7

#ወገን_ምን ያህል እንዳፈቀርኳት እና ችግሬን ከእኔ በተሻለ ተረድቶኝ ስለነበር እሷን የማይበትን ማንኛውንም መንገድ በማመቻቸት ከጎኔ ነበር፡፡ እናም በተጨማሪ በሳምንት 3ቀን ለሁለታችንም እኩል እርቀት ላይ ከሚገኘው #እየሱስ ቤተ-ክርስትያን መንፈሳዊ መዝሙር እንደምታጠና ነገረኝ፡፡ እኔም ቶሎ ብዬ ቀኖቹን፣ ሰዓቱንና መመዝገብ እንደምችል ጠየኩት፡፡ እሱም ደስ እያለው ሁሉንም ነገረኝ፡፡
ተመስገን አምላኬ አልኩ በልቤ፡፡ እሷን ካለማየት ወደማየት ስላበቃህኝ ተመስገን አልኩ መልሼ፡፡ ስለመዝሙር ጥናት ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ከዚህ በፊትም አጥንቼ አላቅም፡፡ ማጥናት ብፈልግ እንኳን አሁን እሷ ከምታጠናበት እየሱስ ቤተ-ክርስትያን ለእኔ ሰፈሬ ያለው ሚካኤል ቤተ_ክርስትያን ይቀርብ ነበር፡፡ ግን ምን ያረጋል በዛ ስዓት እኔ የእሷ ጥላ ሁኜ በሄደችበት ሁሉ እንድከተላት ልቤ ያስገድደኝ ነበር፡፡
የሆነ ቀን አንድ ደብተርና 1ስክርቢቶ ይዤ ትገኛለች የተባልኩበት ቦታ ቀድሜ ደረስኩ፡፡ በዙሪያዬ የእኛ እኩዮች የሆኑ ልጆች ነበሩና ስለመዝሙር ጥናቱ እና መመዝገብ እንደምችል ጠየኳቸው፡፡ እነሱም ደስ ብሏቸው በአዎንታ ተቀበሉኝ፡፡ ሰዓቱ ደረሰና አንድ ጣራና 3ግድግዳ ያለው፤ በአንዱ በኩል ክፍት የሆነ ክፍል ውስጥ ገብተን ወንዶች በአንድ መደዳ ሴቶች በሌላኛው ፊት ለፊት ተፋጠን ተቀመጥን፡፡
ወዳው አይኖቼን ስራ አስጀመርኳቸው፡፡ ወደ 20 የሚሆኑ ሴቶችን Scan አደርጌ የእኔዋን #ፀጊ አጣዋት፡፡ እድለቢስነት ተሰማኝ፡፡ "እንዴት እኔ ስመጣ ትቀራለች? ነው #ወገን ተሳስቶ ነው?" እያልኩ እራሴን በመጠየቅ ላይ ሳለው #ፀጊ ሙሉ ፀጉሯን ሸፍና፣ ነጠላዋን ለብሳ፣ የመዝሙር ደብተሯን እንደያዘች ከአንድ ጓደኛዋ ጋር አብዛኞቹን ሰላም ብላ ከእኔ ትይዩ ባለ የሴቶች መቀመጫ ትንሽ ራቅ ብላ ተቀመጠች፡፡ ከእሷ ቀድማ ጓደኛዋ አይታኝ ስለነበር በጆሮዋ ስትነግራት ተመለከትኩ፡፡ ወዳው #ፀጊ ቀና ብላ ወደእኔ ስታይ፤ እኔ እሷ ላይ እንዳፈጠጥኩ ተያየን፡፡ ወዳው አንገቴን ሰበርኩ፤ አላስችል ብሎኝ መልሼ ስመለከታት ፈገግ እያለች ከጓደኛዋ ጋር ስታወራ ተመለከትኩ፡፡

ከደቂቆች በኀላ መዝሙር አስጠኝው መጣና "ለፀሎት እንነሳ" ብሎ ሁሉችንም ተነሳን፡፡ ፀሎት አርገን እንደጀመርን "አዲስ የመጣ አለ?" ብሎ ጠየቀና እኔና ሁለት ልጆች እራሳችንን አስተዋውቀን ጥናቱ ተጀመረ፡፡

ከእዛች ቀን ጀምሮ ለሁለት ወር ያህል በሳምንት ሶስት ቀን በአይኖቼ ፍቅሬን በአንደበቴ አምላኬን ሳመሰግን ቆይቼ እመለሳለው፡፡ ነገር ግን አንድም ቀን አይቻት ከመመለስ በቀር ቀርቤ ሰላም ብያትም አውርቻትም አላቅም፤ እሷም እንደዛው፡፡

👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 8 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

31 Jan, 12:50


አጓጒ ታሪክ ነው በናታችሁ ቶሎ ቶሎ

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

31 Jan, 11:29


#የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል6

ክላስ እያለቀ መጣ፡፡ ገና ከአሁኑ በሳምንት 5ቀን አይቻት የማልጠግባት ልጅ ጭራሽ ት/ት ሲዘጋ ምን ሊውጠኝ እንደሆነ ጨነቀኝ፡፡ ብቻ የማውቀው አንድ ነገር ቢኖር ምንም እንኳን አብሪያት ሆኜ ባላወራት፣ ባልነካትም እሷን ማየቱ በራሱ ሰላም እንደሚሰጠኝ ነው፡፡

ትምርት ተዘግቶ አይኗን ካየውት ሳምንታት ተቆጥረዋል፡፡ መርዝ እንደበላች አይጥ የማደርገውን አጥቼ መክለፍለፍ የዕለት ተዕለት ስራዬ ሆኗል፡፡ የሆነ ቀን እነወገን ሰፈር ሄጄ አገኘውት፡፡ እናም ሰፈሯን አሻግሬ እየተመለከትኩ እኔ ከእዚህ በላይ ሳላያት መቆየት አልችልም አልኩት፡፡ ልክ እንደ እናት አዘነልኝ፡፡ "ልታያት ትፈልጋለህ? ና እንሂድ" ብሎ ወደሰፈሯ ይዞኝ ሄደ፡፡

ሰፈሯ እንደደረስን ከኪሱ 1ብር አውጥቶ "ሱቅ አላቸው፤ ሱቃቸው ሂድና Banana ማስቲካ ገዝተህ ና። ምናልባት እሷ እራሷ ሱቅ ሆና ልታያት ትችላለህ" አለኝ፡፡ መጀመሪያ ላይ በጣም ስለፈራው "ኧረ ይቅር እንመለስ" አልኩት፡፡ "ምናገባኝ ልታያት ካልፈለክ እንመለስ" አለኝ፡፡  ሳስበው ፍርሀቴ ሳላያት ስውል ከሚሰማኝ መጥፎ ስሜት አይበልጥም፤ እናም 1ብሩን ተቀብየው ሱቁን በጣቱ ጠቁሞኝ ወደሱ አመራው፡፡

እንደደረስኩ በትንሿ መስኮት ፊት ለፊት ቆሜ ወደውስጥ ተመለከትኩ፤ ማንም የለም፡፡ በትንሿ መዳፌ መደገፊያውን እየደበደብኩ "እዚህ ሱቅ" እያልኩ ተጣራው፡፡ ወዳው "አቤት" የሚል ደስ የሚል ድምፅ በጆሮዬ ገባ፡፡ ከሰከንዶች በኀላ ቆንጆዋ ፍቅሬ ቱታ ለብሳ መጣች፡፡ ስታየኝ ደነገጠች፤ እኔ ደሞ የእሷን 10እጥፍ ደነገጥኩ፡፡ ልክ እንደሁሌው ከፈገግታ ጋር ሰላም ካለችኝ በኀላ "ምን ልስጥህ?" አለችኝ፡፡ በውስጤ "አንቺን" አልኩ፡፡ ምክንያቱም ይህን ሁሉ ሰፈር አቋርጬ ፊቷ የቆምኩት የምፈልገውን ዕቃ የሚሸጡ ሱቆች ጠፍተው ሳይሆን የምፈልጋትን ልጅ ስላልያዙ ነበር፡፡ ዳሩ ምን ያረጋል ፍቅር ከያዘከ አይደለም የምትፈልገውን መናገር መተንፈስም ሊጠፋብህ ይችላል፡፡ እየተርበተበትኩ "ማስቲካ፤ 1Banana ስጪኝ" አልኳት፡፡

እሷም ከታሸገ ማስቲካ ውስጥ አንድ መዛ ሰጠችኝ፡፡ እኔም በእጄ የያዝኩትን 1ብር ሰጠዋት፡፡ መልስ ልትሰጠኝ ዞር ስትል ሳላስበው እራሴን በሩጫ መም ላይ አገኘውት፡፡ በመስኮት ወጥታ "ኧረ ቆይ መልስክን ውሰድ እያለች ጮኸች።" እኔ ግን በጣም ከመደንገጤ የተነሳ Boltን በሚያስንቅ ፍጥነት ከአይኗ ጠፍቻለው፡፡ #ወገን ጋር ስደርስ ቁና ቁና እየተነፈስኩ በፈገግታ ቀና ብዬ አየውት፡፡ "አግኝተሀታል ማለት ነው" እያለ እሱም ፈገግ አለ፡፡ ማስቲካውን ስሰጠው "መልሱስ?" አለ፡፡ የተፈጠረውን በሙሉ ነገርኩት፡፡ እሱም ከት ብሎ እየሳቀ "የ20 ሣንቲም ማስቲካ በ1 ብር ገዝተህ መጣህ! ወይ ፍቅር!" ብሎ በአግራሞት ይመለከተኝ ጀመር፡፡
👇👇👇👇👇
   📩 ክፍል 7 ይቀጥላል ........
    👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

28 Jan, 11:36


#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 5

አሁን ያ ጎበዝ ተማሪ አይደለውም፤ ያ ሩጦና ተጫውቶ የማይጠግበው ታዳጊ አይደለውም። በቃ አይደለም ለ14 አመት ታዳጊ ለአዋቂም በሚከብድ ፍቅር በተባለ ጉልበተኛ ተደብድቤ ቀንም ሌትም ስለአንዲት ቆንጆ ወጣት ስብሰለሰል የምውል የማድር የፍቅር ርሀብተኛ እንጂ፡፡

ትምርት ቤት የምሄደው እንደወትሮው ተምሬና ከጓደኞቼ ጋር ተጫውቼ ለመምጣት ሳይሆን በፍቅሯ ሁሉን የነጠቀችኝን ታዳጊ እያየው ለመቆዘም ነበር፡፡ በእየቀኑ እየተደበኩ ምሳዋን በልታ እስክትጨርስ አያታለው፡፡ በእየቀኑ በተቻለኝ መጠን ሳታየኝ ከኀላዋ እየተከተልኩ ከወገን ጋር ሰፈሯ ድረስ እሸኛታለው፡፡

ከወገን ጋር ሰፈራቸው ብዙም ስለማይራራቅ በደንብ ይተዋወቃሉ፡፡ እስከቤተሰብ ድረስ፡፡ የሆነ ቀን 9 ሰዓት ከክላስ ተለቀን ከግቢ እንደወጣን ልክ እንደኔ አፈቀርንሽ የሚሉ ሁለት ልጆች በሰጠቻቸው የእምቢታ ምላሽ ተናደው እሷና አንድ ጓደኛዋን መቷቸው፡፡ እንዳጋጣሚ ልክ እሷ ስታለቅስ እኔ ከወገን ጋር ስንደርስ ተገጣጠምን፡፡ #ወገን የመቷትን ልጆች አባሮ ሁለቱንም እያባበልን ሰፈራቸው ድረስ ሄድን፡፡

#ፀጊ እንባዋ አልቆመም ነበር፡፡ ከሁለቱም አይኖቿ እንባ እንደ ውሃ ሲፈስ ሳይ አንጀቴ ተላወሰ፡፡ አቅም የለኝ የመቷትን አልመታላት፤ ብቻ ሚስቱ ስታምጥ አብሮ እንደሚያምጥ አባወራ አብሪያት አለቅስ ነበር፡፡

እነሱን ሰፈራቸው ድረስ ሸኝተን አባብለን እኔና ወገን እነወገን ሰፈር መተን የፀጊን ሰፈር አሻግረን እያየን ቁጭ አልን፡፡ #ወገን ከልቤ መከፋቴን ተመልክቶ እኔ የተደበደብኩ በሚመስል መልኩ "አይዞህ" እያለ ያባብለኝ ጀመር፡፡

ወዳው ከወደ ፀጊ ሰፈር ወደኛ የሚመጣን አንድ ወጣት እየጠቆመ ወገን ወንድሟ ነው አለኝ፡፡ በጣም ተቻኩሏል፤ አጠገባችን እንደደረሰም ወገንን ያውቀው ስለነበር  " #ኤርሚያስ ማነው?" እያለ ወደእኔ አፈጠጠ፡፡ እየተርበተበትኩ "እኔ ነኝ" አልኩ፡፡ እሱም ወዳው በሁለት እጆቹ አንገቴ ላይ ያለውን ዩኒፎርም ይዞ አንጠለጠለኝ፡፡ ወገን "ኧረ እሱ አይደለም ሌላ ነው የመታት" በማለት ሊያስለቅቀኝ መታገል ጀመረ፡፡ ወዳው የኔ ፍቅር #ፀጊ እሱ አይደለም እያለች መጣች፡፡ "እሱ አይደለም፤ እንደውም እነሱ ናቸው ይዘውን የመጡት" ብላ ወንድሟን አረጋጋችው፡፡ እሱም ይቅርታ ጠይቆኝ አሁን ባላስታውሰውም ስሙን ነግሮኝ እህቱን ይዞ ሄደ፡፡
👇👇👇👇👇
📩 ክፍል 6 ይቀጥላል ........
👉♥️ @Yewqetabugida67🌹🌷
👉 ለማንኛውም ቅሬታም ሙገሳም ሆነ አስተያየት 👉📩 @Ayuma የሚለውን ተጭነው ይጣፉና ይላኩለት ይመልሳልም

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

28 Jan, 11:28


በእክል ምክንያት ተቋርጦ የነበረው #የፍቅር_አቡጊዳዬ የሚለው አጓጊ የፍቅር ታሪክ ከዛሬ ጀምሮ በተከታታይ የሚለቀቅ መሆኑን እየገለጥን ለመዘግየታችን ትልቅ ይቅርታ እንጠይቃለን። መልካም_ንባብ
@Yewqetabugida67

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

28 Jan, 11:17


. #አስተውል
ልጄ፦ የሚበልጥህ ልኩራበት እንዳይል ያነሰህ ደግሞ ልድረስብህ ብሎ እንዳያጠፋህ የእውቀትህ እና የሃብትህን ልክ ሁሉን እንዳታወራ፤ በገዛ አፍህ በአንዱ ስትከብር በአንዱ ደግሞ ክብርህን ትንዳለህና አንድም ደግሞ ድሃው በድህነቱ እንዲያዝን ታደርጋለህና ለአንተነትህ መገለጫ ሃብትህን በፍጹም አታድርግ ልጄ ሚዛንህን አስተካክል ጥሩ ከሆነ በአንደበትህ ትከብራለህ አሊያም ትቀልበታለህ!!፡፡


🌹@Yewqetabugida67🌷

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

21 Apr, 05:19


#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል 4

ከወራቶች በኀላ #ወገን እንዳናግራት አደፋፈረኝና ላናግራት ወሰንኩ፡፡ በሰዓቱ እንደሷ የምፈራው ሰው አልነበረም፡፡ በሆነ አጋጣሚ ሳያት ከያዘችኝ የምገባበት ነበር የሚጠፋኝ፡፡ ነገር ግን የሚሰማኝን በውስጤ አምቄ ከምሰቃይ ልተንፍሰውና ይለይለት ብዬ ወሰንኩ፡፡ እንደነገ ላወራት እንደዛሬ አዳር ላይ የምላትን እና ከእሷ ሊመጡ ይችላሉ የምላቸውን ምላሾች በመገመት በድጋሚ የምላትን ከእራሴ ጋር ስለማመድ አደርኩ፡፡

አይነጋ የለም ነግቶ ት/ት ቤት ገባን፡፡ ላናግራት የወሰንኩት ምሳ ሰዓት ስለነበር እስከዛ ያለው ሰዓት በጣም እራቀኝ። ሙሉ ሰውነቴን የፍራት ካባ ሲለብሰኝ ተሰማኝ፡፡ ምሳ እንደበላን ከትምርት ቤታችን ባለ 4 ፎቅ ህንፃ እራሱን እንደሚያጠፋ ሰው 4ኛው ላይ ሁኜ አስጠራዋት፡፡ ቦታውን የመረጥኩበት ምክንያት አንድም ተማሪዎች በምሳ ሰዓት ስለማይበዙበት ነበር። ሌላው ደሞ በሰዓቱ ሴትን ቀጥሮ ስለማውራትም ሆነ ምቹ ስለሆኑ ቦታዎች እውቀቱ ስላልነበረኝ ነው፡፡

ከትንሽ መንቆራጠጦች በኀላ በደም ፈንታ በደም ቧንቧዎቼ የምትዘዋወረው ቆንጆ ከህንፃው መወጣጫ ደረጃዎች በአንዱ በኩል መጣች፡፡ ልክ እንዳየዋት ውስጤ ይረበሽ ጀመር፤ ማታ የተዘጋጀውበት በሙሉ እንደ ጉም ተኖ ጠፋ፡፡ አጠገቤ እንደደረሰችም ልብን በሚያቀልጠው ፈገግታዋ ሞቅ ያለ ሰላምታ ከሰጠችኝ በኀላ እንዳላወቀ ሰው "ለምን ነበር የፈለከኝ?" አለች ትኩር ብላ እያየችኝ፡፡ አይኖቼ ከአይኖቿ ጋር ሲላተሙ ይባስ እፈራትና እረበሽ ጀመር፡፡

ትንፋሽ እንዳጠረው ሰው እያቃሰትኩ "እየውልሽ #ፀጊ አፍቅሬሻለው፤ ጓደኛ እንሁን" አልኳት አንዴ እሷን አንዴ መሬቱን እያየው፡፡

"አይ እኔ እንደዚህ አይነት ነገር ማሰብ አልፈልግም፤ አልችልም፡፡" አለች እጥር ምጥን ብሎ ለጆሮ በሚከብድ አማርኛ፡፡

"እሺ፤ ቻው" ብያት እኔ በአንዱ ደረጃ እሷ በሌላኛው ዳግም ላንገናኝ በሚመስል መልኩ እየተጣደፍን ሄድን፡፡ ቀጥታ ክላሴ ገባውና እራሴን ካረጋጋው በኀላ ለምን ልናገር ያሰብኩትን እንዳልተናገርኩና "አልችልም" ስትለኝ "ለማስረዳት በመሞከር ፈንታ ለምን "እሺ" የምትለው ቃል ከአፌ እንደወጣች እራሴን ጠየኩት፡፡ ለካ ከሚያፈቅሩት ሰው ፊት መቆም ለሞት ፍርድ ከመቆም ባልተናነሰ ልብን ሰልቦ በፍርሀት ይለውሳል፡፡

.....👉 ይቀጥላል
🌹@Yewqetabugida67

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

11 Apr, 04:14


#የፍቅር_አቦጊዳዬ #ክፍል3
ከዛን ቀን ጀምሮ በእየቀኑ ስለሷ ማሰብና መጨነቅ ስራዬ ሆነ፡፡ ት/ት ቤት፣ ሰፈር፣ ማታ አልጋዬ ላይ ተኝቼ የማስበውም የማልመውም እሷኑ ሆነ፡፡ በሰዓቱ ገና የ14 አመት ልጅ ስለነበርኩ በተጨማሪም ለእንደዚህ አይነት ስሜት አዲስ በመሆኔም ስሜቱ ምን እንደሆነ አላቅም ነበር፡፡ ነገር ግን ህንድ ፊልም ላይ እንደምናየው ነገሩ ቀስ በቀስ ፍቅር መሆኑ እየገባኝ መጣ፡፡

በእየቀኑ ምሳ ስትበላ፣ ስትጫወት፣ ወደ ቤቷ ስትሄድ በቅርብ ዕርቀት እከታተላታለው፡፡ ነገር ግን በዛ በልጅነት አንደበት ማን ቀርቦ ያውራ? ዝም ብቻ፡፡

ይህ ስሜት ቀስ በቀስ የውስጥ መንፈሴን እየጎዳኝ መጣ፡፡ ለወትሮው ተጫዋች የነበርኩ ልጅ አሁን መቆዘም ትልቁ ስራዬ ሆነ፡፡ ትምርቴንም እየደከምኩ መጣው፡፡ በፍቅሯ መነደፌን ከጓደኛዬ #ወገን በስተቀር ማንም እንዳያውቅብኝ ብጥርም የማሳያቸው ያልተለመዱ ባህሪያት ሚስጥሬን አደባባይ አወጡት፡፡ አብዛኞቹ የክላሴ ልጆች እንዲሁም የፀጊ ጓደኞች እና እራሷ ፀጊ ጭምር እሷን ማፍቀሬን ደረሱበት፡፡ ይህ ደሞ ይበልጥ ኑሮን አከበደብኝ፡፡

ማንኛውም ሰው እኔን እያየ ከተጫወተና ከሳቀ በፍቅሬ ያፌዘና ያላገጠ መስሎ ይሰማኝ ጀመር፡፡ በቃ በሰዓቱ እራሴን ሙሉ በሙሉ እሷን በማለምና በመፈለግ ውስጥ አጣውት፡፡

ከወገን ውጪ ቀርቤ የማወራውም የማማክረውም ጓደኛ አልነበረኝም፡፡ ት/ት ቤት ስሆን ከእሱ ጋር እቤት ስሆን ከግጥም ደብተሬ ጋር ሆነ ግዜዬን የማሳልፈው፡፡ በሰዓቱ የግጥም ደብተሬ የምለው አሁን ላይ ግጥም የሚለውን መጠሪያ ለመያዝ ይከብዳል፡፡ ነገር ግን በእዛን ወቅት ስለሷ የሚሰማኝን እና ለእሷ መንገር አለብኝ ብዬ የማስበውን በሙሉ ለእኔ ብቻ ትርጉም በሚሰጡ ቃላት የማሰፍርበት፣ የምተነፍስበት ጓደኛዬ ነበር፡፡......4
🌹@Yewqetabugida67

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

07 Apr, 07:55


#የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል 2
በሰዓቱ እረፍት አልቆ ተደውሎ ስለነበር እሷ ከጓደኞቿ ጋር እየሮጠች ወደ ክፍሏ ሄደች፡፡ እኔም በወደኩበት ከእይታ እስክትርቅ ድረስ በአይኔ ሸኘዋት፡፡

ክላስ ገብቼ ልክ እንደሌሎቹ ደብተር አውጥቼ እስክርቢቶ በእጄ ይዣለው፡፡ ነገር ግን በአእምሮዬ ከደቂቆች በፊት አይኔን ስለወጋኝ ውበት እያሰላሰልኩ ነው፡፡ "ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? ስሟ ማነው? እንዴት እስከዛሬ አላየዋትም? " በዛች ቅፅበት ፍቅርን አዝለው ወደ አእምሮዬ የመጡ ጥያቄዎች ነበሩ፡፡

እንዳያልቅ የለም ቀሪው የት/ት ክፍለ ግዜ አልቆ ምሳ ተደወለ፡፡ ምሳ አብሬው ምበላ፣ ወደቤት የሆነ መንገድ ድረስ አብሬው የምሄድ፣ አብዛኛውን ግዜዬን አብሬው ማሳልፈው #ወገን የሚባል ጓደኛ ነበረኝ፡፡

እናም ምሳ እየበላን "ስማ ቅድም አባሮሽ ስንጫወት እኔ እንዳባራት የተሰጠችኝን ልጅ ታቃታለህ እንዴ?" ብዬ ጠየኩት፡፡

"እእእእእ ፀገነትን ነው? አዎ" በማለት መለሰ፡፡

"ፀገነት ነው ስሟ! ማለት ስንተኛ ክፍል ናት? የት ነው ሰፈሯ? የነማን ጓደኛ ናት? ምሳ የት ነው ምትበላው?" በማለት ስለሷ ለማወቅ እንደጓጓው በሚያሳብቅ መልኩ የጥያቄ ናዳ አወረድኩበት፡፡

እሱም "እንደኛው ሰባተኛ ነች፡፡ ሰፈሯ ከእኔ ሰፈር ብዙም አይርቅም፤ ቅርብ ለቅርብ ነን፡፡ እና ቆንጆ ነች፡፡" አለ እየሳቀና በእጁ መታ እያደረገኝ፡፡

ወዳው እንዴት እንደሆነ በማላውቀው መልኩ ውስጤ እሷን እሷን ሲለኝ ተሰማኝ፡፡ "ምሳ የት ነው ሚበሉት?" አልኩት፡፡

እሱም በልተን እንጨርስና እወስድሀለው ብሎ የሚበሉበት ቦታ ወሰደኝ፡፡ የመማሪያ ክላስ ሲሆን ግድግዳው በጠፍጣፋ ጣውላ ተደርድሮ የተሰራ ነው፡፡ በጣውላና ጣውላው መካከል ባላው ቀዳዳ አጮልቄ እንዳይ ጠቆመኝ፡፡ አዎ #ፀጊ ከሶስት ጓደኞቿ ጋር ምሳዋን እየበላች ነበር፡፡ በሰውነት ሁሉም ይበልጧታል፡፡ በመልክ ግን አዳላህ አትበሉኝ እንጂ ትቦንሳቸዋለች፡፡ ስትስቅ ደሞ ላለመሳቅ ቀጠሮ የያዘ ሰውም ቢሆን ፈገግ ይላል፡፡ በቃ እንዴት እንደሆነ ባላቅም ገና በ14 አመቴ ፍቅር ይዞኛል፡፡ ግን ፍቅር ምንድን ነው? አላቅም!!!....... ፫ ❤️
@Yewqetabugida67

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

22 Mar, 11:32


#የፍቅር_አቦጊዳዬ
#ክፍል1

በወቅቱ እንደማንኛውም ታዳጊ ጨዋታን አብዝቼ የምወድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ፡፡ በትምርቴ ከ1-10 ባለው ደረጃ እወጣ ነበር፡፡ በብዛት 4ኛ እና 5ኛ የኔ ደረጃዎች ነበሩ፡፡ ከዛ በዘለለ ግን ሙሉ ቀን ሙሉ ለሊት ስጫወት በውልና ባድር ጨዋታ የማልሰለች ልጅ ነበርኩ፡፡

ከቀኖች ሁሉ በቅጡ በማላስታውሰው በአንዱ ቀን ከተወሰነ የት/ት ክፍለ ግዜ በኀላ ለእረፍት ተለቀን ከተወሰኑ ተማሪዎች ጋር ተመራርጠን አባሮሽ እየተጫወትን ነው፡፡

በሰዓቱ እኔ አባርሬ እንድይዝ የተሰጠኝ አንዲት ቀይ ቀጠን ያለችን ልጅ ነበር፡፡ ልጅቷን ከዚህ በፊት ልብ ብዬ አይቻት አላቅም፤ ስሟንም ሰምቼው አላቅም፡፡ ጨዋታው ተጀመረና እኔ ነብር እሷ ሚዳቆ ሆነን በረጅሙ የት/ቤታችን የሳር ሜዳ ላይ ያዝኩሽ አመለጥኩህ ሩጫ ያዝን፡፡

ልይዛት በጣም እቀርብና በድንገት የእኔ ፍጥነት ቀንሶ የእሷ በመጨመር ታመልጠኛለች፡፡ ከብዙ ልብ አፍርስ ሩጫ በኀላ ከነብር እጅ ሚያመልጥ የለምና ሚዳቆዋን ያዝኳት፡፡ ነገር ግን እሷ ልታመልጠኝ እኔም ይዣት ለማስቀረት ስንሞክር እኔ በእሷ ላይ ወደቀን ተገኘን፡፡

ዩኒፎርሟ እንደመገላለጥ ብሎ ነበርና እንደማፈር ብላ ልብን በሚያቀልጥ ሁኔታ በእነዛ ሁለት አይኖቿ ለመጀመሪያ ግዜ አይኖቼን ተመልክታ እየተሽኮረመመች ከመሬት ተነስታ ሄደች፡፡ በዛች ቅፅበት ያቺ ቀጭን ቀይ ቆንጆ የመጀመሪያ ፍቅሬ ልትሆን ሳታስፈቅድ ወደ ልቤ ዘልቃ ገባች። 👇 ክፍል ሁለት ይቀጥላል

የእውቀት-አቡጊዳ ✏️💧💦❀✿

22 Mar, 11:32


አዲስ የፍቅር ታሪክ ሊጀመር ነው።