Wolkite University Registrar @wku_registrar Channel on Telegram

Wolkite University Registrar

@wku_registrar


It is the official telegram channel of Wolkite University Registrar Directorate.

Wolkite University Registrar (English)

Welcome to the official Telegram channel of the Wolkite University Registrar Directorate! Are you a student or prospective student of Wolkite University looking for up-to-date information on admissions, registration, and academic policies? Look no further than our channel @wku_registrar! Here you will find all the latest news and announcements straight from the registrar's office. Who are we? The Wolkite University Registrar Directorate is responsible for overseeing all matters related to student records, registration, and enrollment. Our team is dedicated to providing students with accurate and timely information to ensure a smooth academic experience. What can you expect from our channel? By joining @wku_registrar, you will have access to important updates on registration dates, course offerings, academic calendars, and more. We also provide guidance on graduation requirements, transcript requests, and other administrative procedures. Stay connected with us to stay informed and make the most of your time at Wolkite University. Whether you are a current student navigating your academic journey or a prospective student considering Wolkite University for your higher education, our channel is here to support you every step of the way. Join us today and never miss a beat when it comes to your academic success! We look forward to having you as part of our Telegram community.

Wolkite University Registrar

11 Feb, 13:54


https://courses.wku.edu.et/

Wolkite University Registrar

07 Feb, 11:39


Summer Exit Exam Schedule (የካቲት 01)

Wolkite University Registrar

05 Feb, 19:50


በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ያለው የቅድመ ምርቃ ተማሪዎች የመዉጫ ፈተና EXIT-EXAM ከጥር 26 ጀምሮ ላለፉት ሦስት ቀናት በተሳካ ሁኔታ ተካሂዷል:: ፈተናው በቀጣይ ቀናትም የሚሰጥ ሲሆን: አርብ እለት በሚሰጠው ፈተና ላይ 2ኛ እና 3ኛ ሴሽን ፕሮግራም በትምህርት ሚኒስቴር የሰአት ማሻሻያ ተደርጓል:: የተደረገውን ለውጥ ከታች በምስሉ ላይ ማግኘት ይቻላል::

Notice for EXIT-EXAM takers at Wolkite University Tir 30, 2nd & 3rd session schedules are  updated by MoE.
(Be aware of the time changes)

Wolkite University Registrar

02 Feb, 05:08


#ይነበብ

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ይጀምራል።

ለመሆኑ በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እንዲሁም ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን
ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ: 2017 ዓ/ም

Wolkite University Registrar

21 Jan, 08:39


በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናን ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የምዝገባ ጊዜ የሚጠናቀቀው ነገ ጥር 14/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ይህንን ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Wolkite University Registrar

16 Jan, 19:10


Subject: Preliminary Exam Schedule for Huawei ICT Competition (Northern Africa 2024-2025 - Ethiopia)

Dear Huawei ICT Competition 2024-2025 Practice Competition Participants,

This is to inform you that the exam time for the Huawei ICT Competition (Northern Africa 2024-2025 - Ethiopia) Practice Competition (Network Track, Cloud Track, and Computing Track) is scheduled as follows:

🔔Date: Wednesday, January 22, 2025
The Exam.will be Active from:

   ➡️9:00 AM - 5:59 PM
   ➡️3:00-11:59Local time(Ethiopia)
➡️Each one has two trials for this stage

➡️Exam Place: Online
➡️Exam Duration:90Minute
🔔The National final exam will be in March,2025 and we will announce the exact exam date.
Please ensure you are prepared and ready to log in on time.


For any support, please contact your university’s Huawei ICT Academy Administrator, Huawei ICT Academy Instructors, or Huawei ICT Academy Ambassadors.

If you have further questions or require additional information, feel free to reach out.
Best regards,
Tamire Dawud.
ICT Ecosystem Development Manager.
Huawei Technologies Ethiopia.

Wolkite University Registrar

16 Jan, 09:00


በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናን ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህንን ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

Wolkite University Registrar

13 Jan, 14:38


05/05/2017 ዓ.ም
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል (REMEDIAL) ተማሪዎች በሙሉ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለሪሜዲያል (REMEDIAL) የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 26-27/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ትምህርት የሚጀመረው ጥር 28/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኃል፡፡
1ኛ. መሰናዶ ያጠናቀቃችሁበትን ሰርተፍኬት፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር እና አራት 3x4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ፡፡
2ኛ. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ እናሳስባለን፡፡
3ኛ. ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት

Wolkite University Registrar

10 Jan, 20:14


ማስታወቂያ
e-SHE ኮርስ ላይ ያልተመዘገባችሁ አንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ክፍል ከቀን 23/04/2017 ዓም እስከ 25/04/2017 ዓም
ለተከታታትይ ሶስት ቀናት የተቋማዊ ኢሜል አድራሻ ማስተካከልና እና የe-SHE መስመር ላይ (SSS) ኮርስ ምዘገባ
መርሃ ግብር እንደነበር ይታወቃል። ነገር ግን አንዳንድ ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያት እስካሁን ድረስ የተቋማዊ ኢሜል
ያላገኛችሁና ኢሜል አልሰራ ያላችሁ ተማሪዎች እስከ 06/05/2017 ዓም ድረስ ብቻ ኤሌክትሮኒክ ትምህርት
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በአካል በመምጣት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። ከተጠቀሰው ቀን ውጪ
የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

የኤሌክትሮኒክስ ትምህርት አስተዳደር ክፍል ዳይሬክቶሬት
                 

Wolkite University Registrar

23 Dec, 12:39


ማርኬቲንግ ማኔጅመንት አመልካቾች

Wolkite University Registrar

23 Dec, 12:38


አካውንቲንግ እና ፍይናንስ አመልካቾች

Wolkite University Registrar

23 Dec, 12:38


ማኔጅመንት አመልካቾች

Wolkite University Registrar

23 Dec, 12:37


ቀን፡ 14/04/17 ዓ.ም
ለ2016 ለግል ትምህርት አመልካቾች በሙሉ
እንደሚታወቀው በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም የት/ት ዘመን በቅድመ ምረቃ መርሃ- ግብር የግል አመልካቾችን ሲመዘግብ መቆየቱ ይታወቃል፡፡ በቂ አመላካች በተገኘባቸው ፕሮግራሞች ለማስጀመር በወልቂጤ ግቢ በቅዳሜና እሁድ መርሃ-ግብር ማኔጅመንት እና አካውንቲንግ እንዲሁም በማርኬቲነግ ያመለከታችሁ የቅበላ መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ወደ አካውንቲንግ መቀየር የምትፈልጉ የትምህርት ክፍያ እስከ 17/04/2017 ዓ.ም ድረስ እንድታጠናቅቁ እንጠይቃለን፡፡

ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት

Wolkite University Registrar

23 Dec, 06:56


ቀን፡- 14/04/2017ዓ.ም
ለግቢያችን የአንደኛ አመት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በሙሉ
ዲጂታል መታወቂያ ስለተዘጋጀ የተመዘገባችሁበትን ስሊፕ በመያዝ በቀን 14/04/2017 ከ8፡30 በኋላ ሬጅስትራር ህንጻ ላይ በመምጣት እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡
ሬጅስትራር ጽ/ቤት

Wolkite University Registrar

09 Dec, 20:16


Additional Section for Social Science

Wolkite University Registrar

09 Dec, 20:10


Additional Section placement for natural science

Wolkite University Registrar

08 Dec, 06:23


Section Placement Year One student 2017 N.B
All class are @ freshman building
Class will start tomorrow (30/03/2017 E.C) morning 2:30

Wolkite University Registrar

06 Dec, 15:01


ማስታወቂያ !

አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ:-
በ2017ዓ.ም ወደ ግቢያችን የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ያላችሁን መብት እንዲሁም ግዴታ፣ የመማር ማስተማር ሁኔታው በምን መልኩ ማስኬድ እንደሚቻል የሚያሳይ ገለፃ ( Orientation ) ነገ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ መሰጠት ስለሚጀምር ከተጠቀሰው ሰዓት ቀደም ብላችሁ በቦታው በመገኘት ገለጻውን እንድትከታተሉ ጥሪ እናስተላልፋለን ።

ቦታ : ሁለገብ ስቴዲየም

Wolkite University Registrar

05 Dec, 14:57


ህዳር 26/2017 ዓ.ም

በ2017 የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች እና በ2016 በዩኒቨርሲቲው የሪሜዲያል ፕሮግራም ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ በመግባት ላይ ናቸው፡፡
********
ውድ ተማሪዎች እንኳን በደህና መጣችሁ እያልን ቆይታችሁ ያማረና የሰመረ እንዲሆን እንመኛለን!!

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ
ለጥበብ እንተጋለን!
We Strive for Wisdom!

Wolkite University Registrar

05 Dec, 14:57


https://www.facebook.com/share/p/18WqWB8S32/

Wolkite University Registrar

04 Dec, 12:06


የ2017 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎች መልካም መንገድ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን የማደርያ ዶርም ድልድል ከታች ስላያያዝን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።
በተጨማሪም ሙሉ ስማችሁን በማስገባት በቴሌግራም ቦት
@WKUDormitoryBot
ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ።

Wolkite University Registrar

19 Nov, 13:02


ቀን፡- 10/03/2017 ዓ/ም
ማስታወቂያ!!
ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ!!
በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታችሁ ለመማር ከትምህርት ሚኒስቴር ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እንዲሁም በ2016 ዓ/ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ህዳር 26 እና 27 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን በማሟላት በአካል በመገኘት በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
1ኛ) ከስምንተኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቃችሁበት ሙሉ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁ (ሠርተፊኬትና ትራንስክሪብት) ዋናውንና ፎቶ ኮፒ
2ኛ) አራት 3x4 መጠን ያላቸውን ፎቶ ግራፎች፤
3ኛ) ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
ማሳሰቢያ፡-
• ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፤
• በ2016 ዓ/ም 1ኛ ሴሚስተር በውጤታችሁ መሠረት ዳግም ቅበላ የተፈቀደላችሁ ተማሪዎች በተጠቀሱ ቀናት እንድታመለክቱ እናሳስባለን፤
በ2017 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ የሪሚድያል ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት!!

Wolkite University Registrar

08 Nov, 11:39


ለ 2017 ዓም በድህረ ምረቃ ፕሮግራም በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን [በቅዳሜና እሁድ] የኮርስ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ ትምህርት የሚጀመረው ነገ (ጥቅምት 30/2017 ዓም) ስለሆነ ዋናው ግቢ ጠዋት 2፡30 በመገኘት ትምህርት እንድትጀምሩ እናሳስባለን፡

Wolkite University Registrar

04 Nov, 12:42


የREMEDIALፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆነ።

በ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የREMEDIAL ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ተደርጓል።

ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ተማሪዎች ምደባቸውን ፦

በWebsite: https://placement.ethernet.edu.et 

በTelegram: https://t.me/moestudentbot ላይ መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ተማሪዎች ተቋማት በሚያስተላልፉት ጥሪ  መሰረት የREMEDIAL ፕሮግራሙን እንዲከታተሉ ተብሏል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ገልጿል።

Wolkite University Registrar

01 Nov, 12:22


በ 2017 ዓ.ም ተመራቂ የሆናቹ ተማሪዎች በሙሉ ነገ ማለትም በ ቀን 23/02/2017 ዓ.ም ከ ጠዋት 4፡00 ጀምሮ ከ ግቢያችን የአስተዳደር አካላት ጋር በ መውጫ ( EXIT) ፈተና ጉዳይ ውይይት ስለሚኖር ሁላችሁም ሲኒየር ካፌ እንድትገኙ እናሳስባለን። 
ማሳሰቢያ
  ባለመገኘታቹ በሚገጥማቹ ነገር ህብረቱ ሃላፊቱንት አይወስድም።
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ሕብረት "OUR REWARD IS STUDENTS' HAPPINESS!!!"

የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም 👉
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት 
ፌስቡክ     👉 
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት
ድህረ-ገፅ   👉  የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

ለየትኛውም አስተያየት እና ጥያቄ
ቴሌግራም ቦት 👉
@WKU_SU_BOT

ለአብሮነቶ ከልብ እናመሰግናለን
🙏

Wolkite University Registrar

29 Oct, 09:33


አስቸኳይ ማስታወቂያ
እስከ 6:30 ያልሞላችሁ ስማችሁ በዝርዝሩ የተካተታችሁ ተማሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ በተያያዘው ሊንክ
https://forms.office.com/r/V27dbncPBT?origin=lprLink
በመጠቀም ወይም ዲጂታል ላይብራሪ በአካል በመገኘት ከ ቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 3፡00 እንድትሞሉ እናሳስባለን!!

Wolkite University Registrar

29 Oct, 06:48


አስቸኳይ ማስታወቂያ
በትምህርት ሚኒስተር የተዘጋጀ የተማሪ እርካታ ጥናት ላይ ለመሳተፍ ናሙና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ዝርዝር ከላይ የተያያዘ ሲሆን ነገ (19/02/17 E.C) ጠዋት @4:30 ዲጂታል ላይብረሪ በመገኘት ኤሌክትሮኒክ መጠይቅ እንድትሞሉ እንጠይቃለን፡፡
These are list of students sampled to participate in the student satisfaction survey administered by MoE! This is an urgent request to be filled by tomorrow (19/02/17 E.C) morning @4:30 L.T!
Computers are arranged at Central Digital Library as the survey is electronic!

Wolkite University Registrar

28 Oct, 19:07


አስቸኳይ ማስታወቂያ
በትምህርት ሚኒስተር የተዘጋጀ የተማሪ እርካታ ጥናት ላይ ለመሳተፍ ናሙና የተመረጣችሁ ተማሪዎች ዝርዝር ከላይ የተያያዘ ሲሆን ነገ (19/02/17 E.C) ጠዋት @4:30 ዲጂታል ላይብረሪ በመገኘት ኤሌክትሮኒክ መጠይቅ እንድትሞሉ እንጠይቃለን፡፡
These are list of students sampled to participate in the student satisfaction survey administered by MoE! This is an urgent request to be filled by tomorrow (19/02/17 E.C) morning @4:30 L.T!
Computers are arranged at Central Digital Library as the survey is electronic!

Wolkite University Registrar

22 Oct, 12:11


12/02/2017 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ 2017 ዓ.ም የድህረ-ምረቃ አመልካቾች በሙሉ
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ 2017 ዓ.ም በዋናው ግቢ የድህረ-ምረቃ በመደበኛ እና ተከታታይ ፕሮግራም NGAT ያለፉ አመልካቾች መካከል Nutrition (Regular), Reproductive Health (Regular) እና Master of Business Administration (Regular & Extension) ፕሮግራሞች በቂ አመልካች ቁጥር ስለተገኘ የሚከፈቱ መሆኑን እያሳወቅን የትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ከጥቅምት 13-19/2017 ዓ.ም ስለሆነ በአካል በመቅረብ እንድተመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
• በሌሎች ትምህርት ክፍሎች ያመለከታቸሁ በቂ አመልካች ቁጥር ያልተገኘ ሲሆን የትምህርት ዝግጅታችሁ በሚያሳትፋችሁ በተከፈቱ ትምህርት ክፍሎች ላይ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን፡፡
• በ online የተመዘገባችሁ ለምዝገባ ስትመጡ ለማመልከት የተጠየቁትን መረጃዎች ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችሆል፡፡
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

MORE INFORMATION: VISIT TELEGRAM CHANNEL
https://t.me/wku_registrar

Wolkite University Registrar

11 Oct, 16:13


መስከረም 30/2017 ዓ.ም. የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አጭር ምልከታ
https://www.facebook.com/share/v/tSEbagsebChQTGei/

Wolkite University Registrar

08 Oct, 19:20


#MoE

በ2017 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም (Remedial Program) ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ተወስኗል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና የወሰዱና እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 31% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የሪሚዲያል ፕሮግራም መከታተል ይችላሉ ተብሏል።

★ በመንግስት ተቋማት ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ የሪሚዲያል ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎች የመቁረጫ ነጥብ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል::

Wolkite University Registrar

02 Oct, 13:50


List of 25 students placed under architecture department 2017 E.C

Wolkite University Registrar

01 Oct, 13:08


Social Science #2

Wolkite University Registrar

01 Oct, 13:08


Social Science #1

Wolkite University Registrar

01 Oct, 13:07


Natural Science #1

Wolkite University Registrar

01 Oct, 13:06


Pre Engineering #1

Wolkite University Registrar

01 Oct, 13:06


ስማችሁ ከዚህ በታች የተጠቀሱት የመጀመርያ ዓመት ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ውጤታችሁን እስከ ነገ (22/01/2017) 4፡00 ሰዓት ድረስ ሬጅስትራር ጽ/ቤት እንድታስገቡ እናሳስባለን፡፡

Wolkite University Registrar

24 Sep, 19:53


Sep 24 , 2024