WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION @wsuhaile Channel on Telegram

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

@wsuhaile


This is the official channel of Wolaita Sodo University Students Union Office. Join:- https://web.facebook.com/profile.php?id=61573023263455&sk

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION (English)

Are you a student at Wolaita Sodo University looking to stay informed and connected with your peers? Look no further than the official Telegram channel of the Wolaita Sodo University Students Union Office, known by the username @wsuhaile. The Wolaita Sodo University Students Union channel is the hub for all things related to student life on campus. Here, you can find updates on upcoming events, important announcements, student initiatives, and much more. Whether you're looking to get involved in extracurricular activities, connect with fellow students, or simply stay informed about what's happening at the university, this channel has got you covered. The Students Union Office is dedicated to representing the interests of the student body and promoting a sense of community among students. By joining this channel, you'll have a direct line of communication with the union, allowing you to voice your opinions, share your ideas, and contribute to the university community. Stay up to date with the latest news and developments at Wolaita Sodo University by subscribing to the Students Union channel. Don't miss out on the opportunity to be part of a vibrant and active student community. Join @wsuhaile today and make the most of your university experience!

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

14 Feb, 08:26


🎓🎓🎓🎓🎓🎓ወድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን የመውጫ ፈተና ውጤት ስለተለቀቀ እንኳን ደስ አለቹ 💐💐💐💐🌹

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

14 Feb, 07:53


Exit Exam  የወሰዳችሁ ተማሪዎች የፈተና ውጤታችሁ ወደየትምህርት ክፍላችሁ የተላከ ስለሆነ በየትምህርት ክፍላችሁ ሄዳችሁ ማየት ትችላላችሁ፡፡

የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
የካቲት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

14 Feb, 06:26


Edited Notice for the upcoming E-Learning training for Remedial students

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

14 Feb, 06:19


#UPDATE #ExitExamResult

“ ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። ከዚህኛው ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑም እስከነጨረሻውም የሚይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” - ትምህርት ሚኒስቴር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ

ከዲሲፒሊን ጋር በተገናኘ እስካሁን ድረስ ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል። የዚህኛው ራውንድ ውጤት እስከ መሰረዝ፣ የሚቀጥለውንም ድጋሚ ያለመፈተንና እንቅፋታቸው ትልልቅ የሆኑ እስከነጨረሻውም የማይፈተኑበት ጊዜ ሊኖር ይችላል ” ብለዋል።

“ እስካሁን ግን አልተወሰነም። ለጊዜው ግን የዚህኛው ውጤት ዲስኳሊፋይድ እንደሚደረግ ነው 54ዐ ተማሪዎች የተለዩት። ቁጥሩ ሊበልጥ ይችላል፤ ለጊዜው ግን ወደ 540 ተማሪዎች ተለይተዋል ” ሲሉም አክለዋል።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

13 Feb, 21:36


#Update #EXITEXAM

ነገ በዩኒቨርሲቲዎቻቹህ በኩል ታያላቹህ

የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ህብረት ፕሬዝዳንት የሆነው ሃየሎም ስዩም የመውጫ ፈተና ውጤት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሬጅስትራር መላኩንና ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል ነገ ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

13 Feb, 11:24


ወድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን የመውጫ ፈተና ውጤት ስለተለቀቀ እንኳን ደስ አለቹ እያልን...
ውጤታቹ መልካም እና ጥሩ እንዲሆን ምኞታችን ነው። ነገር ግን በውጤት ምክንያት ጊቢ ውስጥ መጨው እና አላስፈላጊ ነገሮችን ማድረግ እንድማይቻል ለማሳውቅ እንወዳለን ይህ ካልሆነ የፀጥታ አካላት እንዲገቡ እናደርጋለን።

    መልካም ውጤት❤️

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

13 Feb, 11:09


#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተለቋል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

12 Feb, 13:46


#የሀዘን #መግለጫ

የዩኒቨርሲቲችን ተማሪ ናትናኤል ፈለቀ በኢንፎርማቲክስ ትምህርት ቤት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ትምህርት ክፍል የአራተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪ ሲሆን በቀን 03/06/2017 ዓ.ም በደረሰበት ድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ በማለፉ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተማሪው ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳዶቹና ለጓደኞቹ ሁሉ መጽናናትን ይመኛል፡፡

ነብስ ይማር!!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

09 Feb, 12:05


በዩኒቨርሲቲያችን ሲሰጥ የቆየው የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና በሰላም ተጠናቀቀ።
*****
በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ በዩኒቨርሲቲዎች የ2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ጋንዳባ ካምፓስና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ   ከ26/05/2017 ዓ.ም እስከ 01/06/2017 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው ፈተና ያለምንም እንከን የተጠናቀቀ መሆኑ ተረጋግጧል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የፈተናው  በስከት መጠናቀቁን ምክንያት በማድረግ ለስከቱ አስተዋፅዖ ያበረከቱ አካላትን አመስግነው ለሁሉ ተፈታኞች መልካም ምኞትን ገልጿል።
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
ዕውቀትን በተግባር!

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

28 Jan, 16:30


ማስታወቂያ

ለጥር ወር ተመራቂ ተማሪወች በሙሉ exit exam  ለመፈተን የሚያበቁ መስፈርቶችን ስለማሳወቅ

ተመራቂ ተማሪወች  በ ዚህ ወር መጨረሻ ቀናት ማለትም 26-30 የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመፈተን፣ ተማሪወችን ለማዘጋጀት የቀረቡትን 3 ሞዴል ፈተናወች የወሰዱ እነዲሁም በየ ትምህርት ክፍሉ የተሰጡትን የማጠናከሪያ ክላሶች 80% እና በለይ በክፍል ውስጥ በመገኘት የተከታተሉ  ተማሪወች ብቻ ፈተናውን መውሰድ እንደሚችሉ እናሳውቃለን

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

26 Jan, 11:06


ዉድ የዩኒቨርስቲያችን ተማሪወች እንኳን ደስ ያላችሁ የእግርኳስ ቡድናችን ዛሬ በነበረው ጨዋታ የመቀሌ ዩኒቨርስቲ የእግር ኳስ ቡድን 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሙሉ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

25 Jan, 17:58


በዛሬዉ እለት የመላው የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲወች የስፖርት ፌስቲቫል በይፋ በማረና በደመቀ መልኩ ተጀምሯል በፌስቲቫሉም ላይ ተማሪወች ከስፖርታዊ ውድድሮች በዘለለ የተለያዩ አካባቢወችን በአል ቋንቋ እና ቱፊት ተምረው ይሄዳሉ ይህም የብሔር  ብሔረሰቦችን አንድነት በማጠናከር የተሻለች ኢትዮጵያዊን ለማየት ያስችላል

በነገው አለትም ዋሊይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ከ መቀለ ዩኒቨርስቲ 4 ሰአት ላይ ይገናኛሉ


ለስፖርት ቡድናችን መልካም እድልን ተመኘን  አሻም

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

22 Jan, 07:21


ውድ የወ.ሶ.ዩ የ2013 ዓ.ም ጥር ተመራቂ ተማሪዎች Exist Exam (መውጫ ፈተና) ተራዝሟል የምል ወሬ ውሸት መሆኑን አዎቃቹ እራሳቹን  ለመውጫ ፈተናቹ እንደታዘጋጁ ስንል በትህትና እንገልፃለን።

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

21 Jan, 13:21


ምዝገባው ነገ ይጠናቀቃል‼️

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናን ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የምዝገባ  ጊዜ የሚጠናቀቀው ነገ ጥር 14/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ይህንን ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። (ትምህርት ሚኒስቴር)

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

19 Jan, 06:52


#NGAT_Result

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ለመከታተል የተመዘገቡ አመልካቾች ፈተና ረቡዕ ጥር 7/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት NGAT የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

17 Jan, 05:00


ማስታወቂያ
ዉድ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ስፖርት አፍቃሪ ተማሪዎች በሙሉ፦ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ፌስቲቫል ከ10 ዓመት በኃላ በድጋሚ በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን፤ ወላይታ ሶዶ  ዩኒቨርሲቲን አስተማሪዎች እና ተማሪዎች ዘር በቀን 9/05/017 ዓ.ም ጨዋታ ስላለ ሁላቸውም ተማሪዎች ዘር 9:00 ወላይታ እስታዲየም እግር ኳስ ሜዳ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ክብር እንግዳ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማኔጀመንት, የተማሪዎች ዲን እና የተማሪዎች ህብረት ክብር እንግዳች ናቸው።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

14 Jan, 13:39


#Notice for NGAT Eaxm Takers

To all registered NGAT exam takers at Wolaita Sodo University center that your exam will be on Wednesday Tir 7,2017 E.C. (Jan 15, 2025) morning from 3:00-4:45 (local time).

All exam takers must:-

• Bring printed out NGAT exam entry ticket

• Arrive at exam hall/room before 2:30 local time

• Come with their identification card (national ID, kebele ID, passport or driving license)

• Not bring electronic devices (tablet, phone, smart calculator, smart watch, smart eyeglass, etc) to exam room

• Check the physical address of exam lab/room ahead of exam time

Your exam room/lab assignment is attachment with this notice!!

Knowledge in Action!!
Wolaita Sodo University

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

12 Jan, 16:09


Freshman First semester mid exam schedule 👇

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

10 Jan, 19:32


 MPH in General Public Health
 MPH in Epidemiology and Biostatistics
 MPH in Reproductive Health
 Masters in Human Nutrition
 Masters in Medical Microbiology
 MPH in Health Service Management
በመደበኛ መርሃ-ግብር
 Masters in Clinical Anesthesia
  Masters in Clinical Pharmacy
  Masters in Adult Health Nursing

#የማመልከቻ #መስፈርቶች
#ለሁለተኛ ዲግሪ አመልካቾች

o ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የሙያ መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት

#ለሶስተኛ ዲግሪ አመልካቾች

o ከታወቀ ከፍተኛ ከታወቀ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ የሙያ መስኮች የመጀመሪያ እና
የሁለተኛ ዲግሪ ያለው/ያላት
o የመመረቂያ ምርምር ውጤት Good እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት
o ለምዝገባ ከአምስት ገፅ ያልበለጠ የምርምር ስራ ዕቅድ ንድፈ ሃሳብ /Concept paper/ ማቅረብ የሚችል/የምትችል
o የምርምር ህትመት (Article) ያለው/ያላት ይበረታታል።

#የመመዝገቢያ #ክፍያ፡

• ለሶስተኛ ዲግሪ ብር 400 /አራት መቶ/ እንዲሁም ለሁለተኛ ዲግሪ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ በኢትዮጵያ
ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000018182789 ገቢ በማድረግ ደረሰኝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

#የምዝገባ #አማራጮች፡

• በኢሜል አድራሻ [[email protected]]
የሚማሩበትን ፕሮግራም ስም በመጥቀስ የክፍያ እና የትምህርት መረጃቸውን መላክ
ይችላሉ።

#የምዝገባ #ጊዜ፡

የ NGAT ፈተና ለሚያልፉ አመልካቾች እስከ ጥር 15/2017 ዓ.ም

• በአካል ማመልከት ለሚፈልጉ በዩኒቨረሲቲው ዋና ግቢ (በየኮሌጆች ወይም ትምህርት ቤቶች ሬጅስትራር ቢሮ) እንዲሁም
ለጤና ትምህርት መስኮች በኦቶና ካምፓስ ሬጅስትራር ቢሮ በስራ ሰዓት ማመልከት ይቻላል።
#ማሳሰቢያ

• የዶርም አገልግሎት (መደበኛ የ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች) በተመጣጣኝ ክፍያ ያገኛሉ፡፡
• በዩኒቨርሲቲው ለሚሰጠው የመግቢያ ፈተና እና ቦታ በውስጥ ማስታወቂያ የሚገለጽ ይሆናል።
• ያለፉ አመልካቾች የፈተና ውጤት በተገለፀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡
• በስፖንሰር ለሚማሩ አመልካቾች በዩኒቨርሲቲው ዌብ ሳይት በተቀመጠው ቅፅ መሰረት ስፖንሰር ሺፕ ደብዳቤ ማቅረብ
ይኖርባቸዋል፡፡

#ለተጨማሪ #ማብራሪያ እና #በቀጣይ #ለሚወጡ #መረጃዎች

• የዩኒቨርሲቲውን ድህረ ገፅ በwww.wsu.edu.et ወይም የፌስ ቡክ አድራሻ (Wolaita Sodo University) በመከታተል
እንዲሁም ሬጅስራር አልሙናይ ዳይሬክቶሬት (+251-5514325) ወይም ድህረ ምረቃ

ዳይሬክቶሬት (+251-5512466) ደውሎ መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

ቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ቢሮ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

10 Jan, 19:31


#ማስታወቂያ

    *

#በ2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ኒቨርሲቲ #የ2ኛ እና #3ኛ ድግሪ ትምህርት ለመማር ለሚፈልጉ አመልካቾች #በሙሉ፡-

በዩኒቨርሲቲው በ2017 የትምህርት ዘመን ሀገራዊ የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር የመግቢያ ፈተና #(NGAT) ተፈትነው ያለፉትን አመልካቾች ለመቀበል እስከ ጥር 15  ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ምዝገባ የሚካሄድ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡

ዕውቀትን በተግባር!!

ተጨማሪ መረጃ ፌስ ቡክ ገጻችን ይመልከቱ!!

  ፌስቡክ፡ https://www.facebook.com/Wolaita-Sodo-University-246568056057804/

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ

#በወላይታ #ሶዶ ዩኒቨርሲቲ #የሚገኙ #መርሃ ግብሮች
#PhD #Degree (የሶስተኛ ዲግሪ) (በመደበኛ መርሃ-ግብር)
1. College of Agriculture
  Ph.D. in Agricultural Economics
  Ph.D. in Agronomy
  Ph.D. in Animal Production (Dairy Animal Production)
   Ph.D. in Horticulture (Breeding of Horticultural Crops)
  Ph.D. in Rural Development
  Ph.D. in Soil Science (Soil Fertility and Chemistry)
2. College of Natural and Computational Sciences
  Ph.D. in Animal Ecology and Conservation Biology
3. College of Social Sciences and Humanity
  Ph.D. in Teaching English Language (TEL)
4. College of Education and Behavioral Studies
  Ph.D. in Educational Leadership and Policy Studies
5. College of Health Sciences and Medicine
  Ph.D. in Public Health
#MSc/MA #Degree (የሁለተኛ ዲግሪ)
1. College of Agriculture
  MSc Programs (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  Animal Nutrition
  Animal Production
  Agricultural Economics
  Agronomy
  Plant Breeding
  Plant Pathology
  Soil Sciences
  Horticulture
  Watershed Management
  Gender and Development
  Rural Development and Planning
  Agricultural Knowledge Management and Communication (AKMC)
  Plant Protection
  Sustainable Forest and Nature Management
2. College of Natural and Computational Sciences
  MSc Programs (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  Applied Microbiology
  Applied Genetics
  Zoology
  Botanical Sciences
  MSc in Chemistry
  Analytic Chemistry
  Organic Chemistry
   Inorganic chemistry
  Physics with specialization
  Atmospheric Physics
  Sustainable Energy and Environmental Physics
  Condensed Matter Physics
  Football Coaching
  Sport Management
  Volley Ball Coaching
  Mathematics with specialization
   Analysis
  Algebra
  Mathematical Modeling
  Environmental Science (with specialization)
   Environmental Resource Management
  Environmental Pollution and Sanitation
  Atmosphere, Climate, and Energy
  M.Sc. in Biostatistics
3. School of Veterinary Medicine (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  MSc in Veterinary Clinical Medicine
4. College of Business and Economics: (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  MA in Development Management
  Masters of Business Administration
  MSc in Accounting and Finance
  MA in Marketing Management
   MA in Project Management
  MSc in Economics (with specialization
   Economic Policy Analysis
  International Economics
  Development Economics
5. College of Social Sciences and Humanity
#MA Programs……. (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  Teaching English as Foreign Language (TEFL)
   Applied Linguistic and Communication
  Linguistics
  Literature in English
  Wolaiyta Language and Literature
  Socio-economic Development and Planning
  Sociology
  History and Heritage Management
  MSc in Climate Change and Sustainable Development
6. College of Education and Behavioral Studies
#MA Programs……. (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  Educational Leadership and Management
  Curriculum and Instruction
  Counseling Psychology
  Social Psychology
  Adult Education and Community Development
7. School of Law (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
  LLM in Criminal Justice and Human Rights
8. College of Engineering (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
 MSc in Thermal Engineering
 MSc in Manufacturing Engineering
 MSc in Power Engineering
 MSc in Hydraulics Engineering
 MSc in Irrigation Engineering
 MSc in Communication Engineering
 MSc in Urban Planning and Development
 M.Sc. in Geotechnical Engineering
9. School of Informatics (በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር)
 MSc in Information Technology
 M.Sc. in Artificial Intelligence
 M.Sc. in Computer Science
10. College of Health Sciences and Medicine • MSc Programs በመደበኛ እና በሳምንት መጨረሻ መርሃ-ግብር

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

10 Jan, 12:55


#Notice for NGAT Takers in Wolaita Sodo University

****

This is to inform you that all registered NGAT takers at Wolaita Sodo University Centre: Your NGAT exam  will be on Wednesday, Tir 7, 2017 E.C. (#January 15, 2025 G.C.). In the morning session only, from 3:00 to 4:45 (local time).

All exam takers must:
• Arrive at the exam hall/room before 2:00 (local time).
• Bring a printed payment confirmation receipt.
• Come with the identification card (National ID, Kebele ID, passport, or driver’s license).
• Do not bring any electronic devices (e.g., tablets, phones, smart calculators, smart watches, smart eyeglasses, etc.) into the exam room.

Additionally, please review the attachment included with this notice for information about postgraduate (MSc/MA, PhD and speciality) programs offered by our university. Details of exam room schedule will be announced soon.

Knowldge in Action!!

Wolaita Sodo University

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

07 Jan, 05:20


ለመላው ኢትዮጵያዊ እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንቱና አስተዳደር ስራተኞች እንደሆ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለ2017 ዓ /ም የጌታችንና የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርሰቶስ የልደት በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞታችንን አስተላልፈዋል።
የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተስፋጽዮን መድህን የገና በዓል ኢየሱስ ክርቶስ የተወለደበት ዓላማ ለፍቅርና ለሰላም በመሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዮችና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዓሉን በፍቅርና በሠላም ማክበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት የመከባበርና የመደጋገፍ እንድሁም የአብሮነት እሴቶችን በማጎልበት፤ የተቸገሩትን በመረዳት በኢኮኖሚ አቅመ ደካማ ተማሪዎች በመጠየቅና በፍቅር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በዓሉ የሰላም ፣የጤና ፤የብልፅዕግና ፤የዕድገት ፤የአብሮነት ፤የአንድነት፤የመቻቻልና የመከባበር እንዲሆን ተመኝቷል።

ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

03 Jan, 11:57


በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ እና የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡

ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው የሚኖራቸው ቆይታ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት  ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተነገራቸው፡፡

****         
       
በስልጠና መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተለለፉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አክበር ጩፎ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ሥራዎች ሁሉ ለማገዝ ብቁ መምህራን የተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመው ተማሪዎቹም ከራሳቸው የሚጠበቀውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ (100%) ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወጣው ጥያቄ መሰረት እንደሚሆን የገለጹት ዶ/ር አክበር የማለፊያ ውጤት ለማምጣት ተማሪዎች፣ መምህራን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥና የተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ የተሳለጠ እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡

ዶ/ር አክበር አክለውም ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ ሳይረበሹ ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት  ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተናግረው በተማሪዎቹ አመርቂ ውጤት አስመዝግበው የተሳካ ጊዜን እንዲያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

በዩኒቨርሰቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ተስፋጽዮን መድኅን ዩኒቨርሲቲ ዕውቀት የሚጋራበት እና ተማሪዎች ራሳቸውንና ሕይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት ክህሎት የሚያገኙበት  ተቋም መሆኑን ጠቅሶ አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች በመልካም ድስፕሊን ታንፀው ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ መስራት እንዳለባቸው መክሯቸዋል፡፡

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

02 Jan, 19:14


Remedial social science class schedule 👇

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

01 Jan, 10:59


የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል ላይ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲን በእግር ኳስ ለመወከል ባለፈው የተመረጣችሁ ተማሪዎች ዘር 8:30 ወላይታ እስታዲየም እግር ኳስ ሜዳ እንድትገኙ እናሳስባለን።

የተማሪዎች ህብረት የስፖርትና መዝናኛ ዘርፍ

ታህሳስ 23/04/017

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

30 Dec, 04:26


በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ።

የወ.ሶ.ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

29 Dec, 04:14


የቀድሞ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም አዲስ ለተሾሙ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ መሀመድ እድርስ የሥራ ርክክብ አደረጉ።

***

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጉቼ ጉሌ ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም የዩኒቨርሲቲው ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲረጋገጥ በሳል አመራር በመስጠት ላሳዩት ትጋት አመስግነው አምባሳደር ሆነው በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ መልካም የሥራ ዕድል እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።

ፕሬዝዳንቱ፤ ዩኒቨርስቲው በርካታ አቅም ያላቸው መምህራንና ተመራማሪዎች ያሉበት ተቋም ስለሆነ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠትና ችግር ፈቺ ምርምሮችን ለማካሄድ ምቹ አጋጣሚ በመሆኑ ወደ ፊትም የትኩረት አቅጣጫን መሠረት በማድረግ በመሥራት የዩኒቨርሲቲው ራዕይ እስዲሳካ በጋራ እንሰራለን ብለዋለ።

ዩኒቨርሲቲውን በወፍ በረር ያስቃኙት ፕሬዝዳንቱ አዲስ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢውን ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስን እንኳን ደህና መጡ ብለው ዩኒቨርሲቲው ከአዲሱ ቦርድ ሰብሳቢ፣  ከሌሎች ቦርድ አባላት፣ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች እንዲሁም ከሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የቀድሞ የዩኒቨርሲቲዉ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩ ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቆዩበት ወቅት በዩኒቨርሲቲው ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲረጋገጥ ሙሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ እና በቅንጅት እንዲሰሩ ለቦርድ አባላት የየሥራ ድርሻቸው ተከፋፍሎ ተሰጥተዋቸው  በተቀመጠው አቅጣጫ  መሠረት ሲሰራ እንደቆየ አስረድተዋል፤ በዚህም መልካም ውጤት ተመዝግቧል ሲሉ ተናግረዋል።

ክቡር አምባሳደር አክለውም ዩኒቨርሲቲው የማደግ ዕድል ያለው ነው ሱሉ ገልፀው አሁን ያሉ አመራሮች ክፍተት ሳይታይባቸው የጀመሩትን መልካም ሥራ በማስቀጠል አመርቂ ውጤት እንዲመዘገብ መረባረብ አባቸው ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች እንዲሳለጡ ለሥራ በሚሄድበት ቦታ ሁሉ ወላይታ ሶዶ  ዩኒቨርሲቲን ካደጉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የማገናኘት ሥራ እሰራለሁ ያሉት ክቡር አምባሳደር ብናልፍ ቦታቸውን ለተኩ ክቡር መሀመድ እድሪስ በዩኒቨርሲቲው መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።

አዲሱ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው የሚታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና  ድክመቶችን በማረም በትኩረት በመሥራት የተሻለ ዩኒቨርሲቲ እንፈጥራለን ብለዋል።
ዩኒቨርሲቲው በመማር ማስተማር፣ በምርምር፣ በቴክኖጂ ሽግግር እና በማህበረሰብ አገልግሎቶች ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ እንዲሆንና ጥራት ያለውን ትምህርት በመሥጠት ብቁ  ተማሪዎቹ ፈርተው ገና ሳይመረቁ እንዱስትሪዎች የሚፈልጓቸው ብቁ እንዲሆኑ ይሰራል ያሉት ቦርድ ሰብሳቢው የዩኒቨርሲቲው አመራሮችም በቂ የአመራር ክህሎት እንዲያዳብሩ በስልጠናና በቴክኖሎጂ የመደገፍ ሥራ አጠናክረን እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ ላይ ክቡር አምባሳደር ብናልፍ አንዷለም ለአዲሱ ቦርድ ሰብሳቢ የሥራ ርክክብ አድርገው የዩኒቨርሲቲው ማናጅመንት በክብር የሸኙት ሲሆን ለአዲሱ ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ አቀባበል በተደረገው የዕለቱ ሁኔት ተጠናቅቋል።

ዕውቀትን በተግባር!

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

28 Dec, 12:06


በ2017 ዓ. ም በኢ. ፌ. ዴ. ሪ  ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡች አዲስ የአቅም ማሻሸያ (REMEDIAL) ፕሮግራም ተማሪዎች ነገ 20/04/2017  ዓ.ም መግባት ይጀምራሉ።

ማሳስቢያ
አዲስ የተመደባቹ የአቅም ማሻሻያ ተማሪዎች ወደ ጊቢ ስትመጡ አዲስ እንዳይሆንባቹ አንገታቸው ላይ ባጅ ያደረጉ የቀድሞ ተማሪዎችን/አስተባባሪዎችን የምትፈልጉትን ነገር በመጠየቅ አገልግሎቱን ማግኘት ትችላላቹ።

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

ውድ ተማሪዎቻቾን ከወዲሁ እንኳን ደህና መጣችሁ እያልን።

➭ «ዕውቀትን በተግባር!!»

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

27 Dec, 11:41


Remedial dorm placement

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

21 Nov, 15:20


ለ Electrical እና Architecture 3ኛ እና 4ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ ።Electrical እና Architecture 3ተኛ እና 4ተኛ ዓመት ተማሪዎች ከጥቅምት 22 / 02 / 17 ዓ.ም ጀምሮ በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ እንፈልጋለን በሚል ምክንያት የትምህርት ማቆም አድማ ላይ መሆናችሁ ይታወቃል ።

በዚህም መነሻ በተቋም ደረጃ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ በልበ ሰፊነት ተገቢውን ምላሽ ከበቂ ማብራሪያ ጋር የሰጠንና ትምህርት የማቆም አድማ የዩኒቨርስቲውን ስነምግባር ደንብ የሚጻረር መሆኑን አስገንዝበን ትምህርት እንድትጀምሩ በተደጋጋም ከማስጠንቀቅያ ጭምር ብናሳውቅም ትምህርት ለመጀመር ፈቃደኛ ስላልሆናችሁ ኮሌጁ የራሱን እርምጃ ለመውሰድ ተገዷል ::

ስለሆነም ማንኛውም ትምህርት ለመቀጠል የሚፈልግ ተማሪ ለአንደና ለመጨረሻ ጊዜ በAC ውሳኔ መሰረት ከዛሬ ማለትም 12 / 03 / 17 ዓ.ም ጀምሮ በት/ ክፍሎች በአካል በመቅረብ ሪፖርት እንድታደርጉና ትምህርት መቀጠል የማትፈልጉ ተማሪዎች clearance ሞልታችሁ እንድትወጡ እያሳወቅን ለተፈጻሚነቱ የሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ተገቢውን ክትትል እንድታደርጉ አሳስባለሁ።

ሌላው በግቢ ውስጥ በማኔጅመንት አካላት መግለጫ ባልተስጠበት ነገር እና ባልተነገረ ወሬ ተማሪውን እና መልካሙን የመማር ማስተማር ሂደት ለማውክ የምትሞክሩ ተማሪዎች ለመጨረሻ እርምጃ ለመውሰድ አሳስባለሁ ።

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
ወሶዩ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

20 Nov, 09:07


መረጃ!
#####

===============
በዩኒቨርሲቲያችን የ"DAAP" ስልጠና ወስዳችሁ ያጠናቀቃችሁ ተማሪዎች Certificate ተዘጋጅቶ የመጣላችሁ ስለሆነ የተማሪዎች ህብረት ሚኒሚዲያ በአካል ቀርባችሁ እንዲትወስዱ እናሳስባለን።

ተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

  

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

19 Nov, 13:01


To all freshman students (2017 batch)
WSU arranged Welcome and Orientation program on 11/03/2017 E.C. starting from morning 2:30.
📌Life skills training afternoon 8:00.

😍Welcome to your home once again!

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

19 Nov, 12:52


ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ  አዲስ ገቢ የተማሪዎች አቀባበል ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በ2017 የትምህር ዘመን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የተመደቡ መደበኛ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች አቀባበል ፍፁም ሠላማዊ በሆነ ሁኔታ እየተካሄደ ነው፡፡
የአቀባበል መርሃ ግብሩ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት፣ ከተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት፣ ከተቋሙ ፀጥታና ደህንነት  እንዲሁም ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል ።

  ወድ አዲስ ገቢ ተማሪዎቻችን የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁን አስመልክቶ ነገ ህዳር 11/2017 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ የአካዳሚክ ህግጋትና ተማሪ ድስፕሊን በተመለከተ አጠቃላይ ገለጻ እና ከሰዓት 8፡00 ጀምሮ የህይወት ክህሎት ስልጠና ስለሚኖር በተጠቀሰው ሰዓት በዩኒቨርሲቲው መመረቂያ አዳራሽ እንድትገኙ ከወዲሁ እናስታውቃለን!

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

17 Nov, 13:37


Dears,all student Please share the scholarship application link of Beijing University of Chemical Technology of 2025 scholarship opportunities for your networks.

Note that:

1. Each applicant should contact the supervisor based on the given links of PI lists
2. Must select a major stream based on his/ her academic background
3. Must have original certificate and transcript of the highest degree.
4. Passport
5. It's impossible to apply more than once.
6. And other required documents.

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

17 Nov, 13:29


https://mp.weixin.qq.com/s/vtEgR_r4IHars-Apu3HHeQ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

12 Nov, 15:47


ለዛሬ የነበረው የGc ኮሚቴ ፈተና በ አንድ አንድ ሁኔታወች አለመመቻቸት ለ ነገ (እሮብ ) 11:00 ተቀይሯል ከታላቅ ይቅርታ ጋር


የተማሪወች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

10 Nov, 11:40


➡️በግቢ ዉስጥ በቡድን ሆኖ ማንኛውንም ዓይነት በኃይማኖታዊም ይሆን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ይችላሉ ወይ?

አንቀጽ 7-2 የተከለከሉ ተግባራት

ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

08 Nov, 17:06


#ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም  ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ  ለተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት (FRESHMAN) ተማሪዎችሙሉ

በ2017 ዓ.ም ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አድስ የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመት (FRESHMAN) እንድሁም በ2016 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (REMEDIAL) ፕሮግራም ተከታትላችሁ ማለፊያ ዉጤት 50% እና ከዛ በላይ ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደዉ ህዳር 09 – 10/2017 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሰዉ ቀን ብቻ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳዉቃለን፡፡
ለበለጠ መረጃ፤☝🏿☝🏿☝🏿☝🏿☝🏿☝🏿☝🏿☝🏿☝🏿

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

07 Nov, 09:33


የወ.ሶ.ዩ የ2013 ዓ.ም እና የ2014 ዓ.ም ተማሪዎች ተውካዮች በሙሉ በካላንደር ምክንያት የምታደርጉት አድማ እና የተለያዩ ክስተቶችን ትታቹ እንዲመለስላቹ የምትፈልጉትን ጥያቄ ይዛቹ ወደ ተማሪዎች ህብረት ቢሮ መታቹ መጠየቅ ትችላላቹ።

  ሌላው በግቢ ውስጥ በማኔጅመንት አካላት መግለጫ ባልተስጠበት ነገር እና ባልተነገረ ወሬ ተማሪውን እና መልካሙን የመማር ማስተማር ሂደት ለማውክ የምትሞክሩ ተማሪዎች ከመሰል ተግባራቹ እንድትቆጠብ እናሳስባለን።

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
ወሶዩ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

02 Nov, 09:13


የየዲፓርትመንቱ የየክፍል ተውካዎች በየባቻቹ ያለውን ሊስት በማየት ስም ዝርዝራቸው ያለውን ልጆች እዛቹ በመምጣት Natural,social lab and GIS በመገኘት online እንድታስሞሏቸው እናሳስባለን። 

    ከ9 ሰዓት ብዋላ ሰለማይቻል ሁላቹም እስክ 9 ሰዓት እንድትጨርሱ።

ማስጠንቀቂያ
፦ስማቹ ያለ ተማሪዎች ቅጣት እንዳለ አውቃቹ
እንድትገኙ።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

02 Nov, 07:04


All dep.t section Rep 2 year-6 year share to student.

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

31 Oct, 17:39


ውድ የወ.ሶ.ዩ የ2013 ዓ.ም ጥር ተመራቂ ተማሪዎች የካላንደር መዛባት እንደተፈጠረ ተደርጎ በጊቢ ውስጥ የሚናፈሰው ወሬ ውሸት መሆኑን አዎቃቹ እራሳቹን  ለመውጫ ፈተናቹ እንደታዘጋጁ ስንል በትህትና እንገልፃለን።
   
      ማስጠንቀቂያ
እንዲ አይነት የአሉ ባልታ ወሬ እያውራቹ የጊቢውን ሰላም ለመረበሽ የምትሞክሩ ተማሪዎች ከመሰል ተግባራቹ እንድትጠበቁ በጥብቅ እናሳስባለን።

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

31 Oct, 06:51


Big News, Wolaita Sodo University!

In partnership with Dereja, we’re bringing exciting events to your campus from November 13-15!  Get ready to unlock your potential and elevate your career journey. Save the date! 

#Dereja
#WolaitaSodoUniversity
#CareerOpportunities

📣 Hey, Wolaita Sodo University! 📣

Exciting events in partnership with Dereja!

The Dereja Campaign is coming to multiple campuses at Wolaita Sodo University with exciting sessions lined up.

🗓 Dates & Times:


Wednesday, November 13 | 1:30 PM Main and Health Campus at Graduation Hall

Friday, November 15| 9:00 AM Dawro Tercha Campus at Council Hall



ARE YOU #GC2025? Don’t miss out on the opportunity to elevate your career journey! 🚀

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

31 Oct, 06:50


ለ 2017 ዓ.ም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂዎች በሙሉ
==========================

እንኳን ለ2017 የት/ም ዘመን በሰላም አደረሳችሁ እያለ  የወላይታ  ዩኒቨርሲቲ አካ/ጉ/ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከደረጃ ጋር በመተባበር በአይነቱ ለየት ያለ የስልጠና አገልግሎት ዘመቻ ማዘጋጀቱን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው!!

ስለሚሰጠው  አገልግሎቶች ገለፃ የፊታችን ህዳር 4 እና  ጠዋት እና ከሰዓት ከላይ በፖስተሩ ላይ በተጠቀሱት ካምፓስ እና አዳራሾች ይደረጋል።

በቆይታችን የተለያዩ የደረጃ ነባርና አዳዲስ አገልግሎቶች ገለጻ ይደረጋል፣ በተጋባዥ እንግዶች ንግግር ይደረጋል፣ እንዲሁም ለተማሪዎች የተለያዩ ስጦታዎች እና በሚደረጉ ውድድሮች ላይ ላሸነፉ ተማሪዎች ሽልማቶችም ይኖሩናል።

የፊታችን ህዳር 4 እና 6 አይቀርም!!

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከደረጃ ጋር በመተባበር ።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

29 Oct, 12:57


📲 ለሁሉም ተማሪዎች! 💻

በቅርቡ 3ኛ አመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የSSS ስልጠና ዘመቻው በስኬት የተጠናቀቀ ቢሆንም ከ 4,200 ተማሪዎች መካከል 1,700 ብቻ በስልጠናው የተሳተፉት በዋናነት ተቋማዊ ኢሜይሎች ባለመገኘታቸው ነው።

ሁሉንም ኮሌጆችን ለዘመቻው ስንል ብቻ ቀላቅለን በጋራ ያስተናገድነው ቢሆንም፣ ዋናው  የስልጠናው ሃላፊነት በተማሪዎች፣ በአሰልጣኞች እና በአይሲቲ ቡድን ላይ ነው።

አሰልጣኞች በWSU አስተዳደር መመሪያና እቅድ መሠረት ያካሂዳሉ፣ የአይሲቲ ቡድን ተማሪዎችን  institutional ኢሜይል በማውጣት ይደግፋሉ።

ከተማሪ ተወካዮችና ስልጠና አስተባባሪዎች እየተመካከሩ መቆየት እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው።

የሥልጠና አስተባባሪዎች (3ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ ተማሪዎች)፡-

1. 📚CNCS-📡ፀጋዬ ጌታቸው (0910463229)
2. 💳CBE📈- ጌታሁን ሶርሳ (0926171166)💷
3.📐CoE፣🎓 SEBS፣ እና SL- Fitsum Markos (0913347629)
4.🌱 CoA🐝- መንግስቱ መና (0946325013) 🥑
5. SI🗂🇪🇹CSSH፣ እና 🐏SVM- Liulseged Ephrem (0916880357)

ተማሪዎች ከዚህ በኋላ በዋናው ግቢ ምንም ተጨማሪ የፊት ለፊት ዘመቻዎች እንደማይኖኖር አውቀው ቀጣይ የሥልጠና ክፍለ ጊዜዎች በተርጫ- ዳውሮ፣ ኦቶና እና ሁለተኛ ዓመት ዋና ግቢ ተማሪዎች ላይ ያተኩራሉ፣ ልዩ ኮርሶችን ይሸፍናሉ።

ሁሉም ተማሪዎች ለተቀላጠፈ የስልጠና አሰጣጥ ከአሰልጣኞች፣ ከዲኖች፣ ከተወካዮች እና ከአይሲቲ ቡድን ጋር መቀናጀት አለባቸው።

Digital-WSU!

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

20 Oct, 04:28


Urgent: Enroll in the SSS Program!

Obtain a WSU institutional email, complete e-Learning training, and earn an Arizona State University certification.

Assistance is available from university administration, including the presidents, registrar, deans, and experts.

Students are required to participate in this program. Non-certified students will not have access to registrar or cafeteria services due to the transition of WSU academic programs to online learning and Digital-WSU.

Student Training Schedule (for regular 3rd& 4th-year students, including 2nd-year students in the  Veterinary M, Law, & Dept of Wolaitegna):

Monday, October 21: Agriculture/Veterinary

Tuesday: Business/Economics/Behavioral

Wednesday: Engineering/Informatics/Social Sciences

Thursday: Natural Sciences/Law

All training sessions will be held at the main campus training centers: Cisco Lab, Hydraulic Lab, Electrical/Architecture Lab, Civil Association Lab, and Mechanical Lab. Labs are located near the registrar's office, LH7, and the third gate.

Please practice in other labs after the training campaign sessions.

Your prompt attendance/ participation are crucial for a successful transition to online learning & Digital-WSU.

For more information about further lab access, contact your deans.

For  assistance with email and/or subsequent course website, communicate your **assigned trainers, and IT experts

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

20 Oct, 04:27


ይህንን ለየተማሪዎችዎ ያካፍሉ? አመሰግናለሁ!

አስቸኳይ፡ በኤስኤስኤስ ፕሮግራም ይመዝገቡ!

የWSU ተቋማዊ ኢሜይል ያግኙ፣ የኢ-ትምህርት ስልጠናን ያጠናቅቁ እና የአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ የምስክር ወረቀት ያግኙ። ፕሬዝዳንቶችን፣ ሬጅስትራሮችን፣ ዲኖችን እና ባለሙያዎችን ጨምሮ ከዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እርዳታ ይገኛል።

ተማሪዎች በዚህ ፕሮግራም መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል። ወደፊት የWSU አካዳሚክ ፕሮግራሞች ወደ ኦንላይን ትምህርት እና ዲጂታል-WSU በሚደረገው ሽግግር ምክንያት የምስክር ወረቀት የሌላቸው ተማሪዎች የመዝጋቢ ወይም የካፊቴሪያ አገልግሎት አይኖራቸውም።

የተማሪ ማሰልጠኛ መርሃ ግብር (ለመደበኛ 3ኛ እና 4ኛ-አመት ተማሪዎች፣ የ2ኛ አመት ተማሪዎችን በ  ቬተሪን ኤም፣ ህግ እና የወላይትኛ መምሪያ) ጨምሮ፡ ሰኞ፣ ኦክቶበር 21፡ ግብርና/የእንስሳት ሕክምና ማክሰኞ፡ ቢዝነስ/ኢኮኖሚክስ/ባህሪ ረቡዕ: ምህንድስና / ኢንፎርማቲክስ / ማህበራዊ ሳይንሶች ሐሙስ: የተፈጥሮ ሳይንስ / ሕግ ሁሉም የሥልጠና ክፍለ ጊዜዎች የሚካሄዱት በዋናው የካምፓስ የሥልጠና ማዕከላት፡ cisco ላብ፣ ሃይድሮሊክ ላብ፣ ኤሌክትሪክ/አርክቴክቸር ላብ፣ የሲቪል ማኅበር ቤተ-ሙከራ እና መካኒካል ቤተ-ሙከራ ነው። ቤተሙከራዎች የሚገኙት በመዝጋቢው ቢሮ፣ LH7 እና በሶስተኛው በር አጠገብ ነው። ከስልጠና ዘመቻ ክፍለ ጊዜ በኋላ እባኮትን በሌሎች ቤተ ሙከራዎች ውስጥ ይለማመዱ።

ወደ online  ትምህርት እና ዲጂታል-WSU ስኬታማ ሽግግር የእርስዎ ፈጣን ክትትል/ ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ስለ ተጨማሪ የላቦራቶሪ መዳረሻ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ዲኖችዎን ያነጋግሩ።

በኢሜይል እና/ወይም በሚቀጥለው የኮርስ ድርጣቢያ ላይ እገዛ ለማግኘት የተመደቡትን አሰልጣኞች እና የአይቲ ባለሙያዎችን ያነጋግሩ ማሳሰቢያ፡የተመደቡበትን ቀን schedule ይመልከቱ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

16 Oct, 16:17


የሀዘን መግለጫ

    በወ.ሶ.ዩ የቢዝነስ ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የቱሪዝም ትምህርት ክፍል የሁለተኛ ዓመት ተማሪ የነበረችው ተማሪ ሩት ማስረሻ በደረስባት ህልፈተ ህወይት የተስማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን።ለቤተስቦቿ፣ለወዳጅ ዘመዶቿ እናም ለጎደኞቿ በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን።

  ፈጣሪ ነፍሷን በአፀደ ገነት ያኑርልን!

👉የተማሪዎች ፕሬዝዳንት ተስፋጽዮን መድህን

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

15 Oct, 09:04


የማስታውቂያ ቅያሪ

  ውድ የወ.ሶ.ዩ የእያንዳንዱ ዲፓርትመንት የየክፍል ተወካዮች ማክሰኞ በቀን 5/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ የነበረንን ስብስባ/ውይይት ላልተውስነ ጊዜ መራዘሙን እናስታውቃለን።
       

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

14 Oct, 05:24


ማሳሰቢያ

  ውድ የወ.ሶ.ዩ የእያንዳንዱ ዲፓርትመንት የየክፍል ተወካዮች ማክሰኞ በቀን 5/2/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ላይ በመመረቂያ አዳራሽ እንድትገኙ እናሳስባለን።
       
       መቅረትም ማርፈድም አይቻልም!

👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

10 Oct, 18:15


ወደ ተርጫ ካምፓስ የምትሄዱ ተማሪዎች ነገ ጥዋት 12:00 ሰዓት ዋናው ሪጅስትራር እና ካፌ መሃል ያለው አስፓልት ላይ እንድትገኙ።

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

10 Oct, 05:58


ጥብቅ ማሳሰቢያ

  ውድ የወ.ሶ.ዩ ተማሪዎች ከ3ተኛ ዓመት በላይ ያላቹ  የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከመስከረም 23/1/2017 ዓ.ም ጀምሮ መጀመሩ ይታውቃል።ሰለዚህም በትምህርት ገበታቹ ያልተገኛቹ ተማሪዎች ተገኝታቹ እንድትከታተሉ በጥብቅ እናሳስባለን።

       መልካም የትምህርት ጊዜ!!

  👉ከተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
ወሶዩ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

07 Oct, 11:44


ዛሬ ማለትም በቀን 26/1/2017 አዲሱ የተማሪወች ህብረት  በ ግቢ ውስጥ ከሚገኙ የተለያዪ  የሀማኖት ተወካዮች ጋር  የግቢያችን  ሰላም እንዴት እንጠብቅ በሚል እርእስ  ውይይት ተካሂዷል በዉይይቱም ላይ  የግቢው ምድረ ግቢ ደህንነት ዳሬክተር  የሆኑት ሀምሳ አለቃ ሀይሌ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል

በዉይይቱም ላይ ከሀይማኖት ተወካዮች ፀሎት ወይም የተለያዩ ፕሮግራሞች ሲኖሩ ከ 2 ሰአት በላይ ስለሚያመሹ ግቢ በር ላይ ለመግባት እንደሚቸገሩ ገልፀው ይህ ሁኔታ እንዲስተካከልላቸው ጠይቀዋል

የተማሪወች ህብረት ፕሬዝዳንት ተስፋጺውን መድህን በበኩላቸው  ይህን እና መሰል ሁኔታወችን ለማስተካከል  ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል እንዲሁም የሀይማኖት ተቋማት  ትውልድን በመቅረፅ  ደረጃ ከ ትምህርት ተቋማት ያላነሰ ሚና እንደሚጫወቱ ገልፀዋል ስለሆነም የግቢያችንን ሰላም ለመጠበቅ እጅ እና ጓንት ሁነን ልንሰራ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

07 Oct, 11:32


የሐዘን መግለጫ

  በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል የ3ተኛ ዓመት ተማሪ  የነበረው ያየህ ዓለሙ  ባደረበት ህመም ምክንያት ህይወቱ በማልፉ የተማሪዎች ህብረት የተስማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለውዳጅ ዘመዱ መፀናናትን እንመኛለን።

    👉የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት
   ወ.ሶ.ዩ

WOLAITA SODO UNIVERSITY STUDENTS UNION

07 Oct, 10:48


ውድ የወላይታ ሶዶ ዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆናቹ ስፓርት አፍቃሪየን።ያው እንደሚታውቀው ከሁለት ቀን በፊት  ሁሉን ነገር በአሟላ መልኩ የዴስቲቪ አገልግሎት ለተማሪዎች ክፍት መሆኑ ይታውቃል።
ለዚህም ውድ ተማሪዎች  እንኳን ደስ አላቹ እያልኩኝ የዩንቨርስቲያችንን ሰላም በጠበቀ መልኩ ምንም አይነት ግርግር እና ረብሻ ሳይኖር ስፓርታዊ ጨዋነት በተሞላበት መልኩ ውድድሮችን ትመለከቱ ዘንድ አሳስባችዋለው።
       
     ይህ እንዲሳካ ትብብራቹን  ያልነፈጋቹ አካላት በሙሉ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው።
   
  መልካም ጊዜ!!
👉የተማሪዎች ፕሬዝዳንት 
ተስፋጽዬን መደህን
         ወ.ሶ.ዩ