*****
(ት/ማ/ባ ጥቅምት 23/2017 ዓ.ም)፡- የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ ሰላማዊና ተቀባይነት ያለው የትራፊክ እንቅስቃሴን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሂደት በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ግምገማ እና የቀጣይ ሩብ ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ላይ በዛሬው ዕለት ተወያይቷል፡፡
በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዝግጅት ምዕራፍ በመሆኑ በሁሉም ዘርፍ ለሚከናወኑ ስራዎች አስፈላጊ የሆኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እና የሰነዶች ዝግጅት ከመጠናቀቁም በላይ ወደ ትግበራ ስለ መገባቱ የእቅድና በጀት ዳይሬከቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ተሬሳ የተቋሙን የ3 ወራት የእቅድ አፈፃጸም ሪፖርት ሲያቀርቡ ገልጸዋል፡፡
በሩብ ዓመቱ ከተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት መካከል እግረኞች እና አሽከርካሪዎችን መሠረት ያደረጉ የምህንድስና ዘርፍ ማሻሻያዎች፣ በግንዛቤ የተደገፈ የቁጥጥር ስራዎች እንዲሁም የፓርኪንግ አገልግሎት አሰጣጥ እና አስተዳደር ስራዎች እንደሚገኙበት ዳይሬክተሩ አብራርተዋል:;
አያይዘውም በስራው ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ እርምጃዎች፣ እና በቀጣይ ሊስተካከሉ የሚገቡ ነጥቦችንም አንስተዋል፡፡
እንዲሁም በሩብ ዓመቱ የዋናው መ/ቤቱንና የ11ዱምን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች እቅድ አፈፃፀምን የተመለከተ ክትትልና ድጋፍ ሲያደርግ የቆየው ኮሚቴ በበላይነት ሲመሩ የነበሩት አቶ ደረጄ ወርቁ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን የውስጥ ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርኬ የኦዲት ምርመራ ግኝቶችና የአሰራር ግድፈቶች እንዲሁም በቀጣይ ማስተካከያ ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ያመላከተ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
በቀረቡት ሶስቱ ሰነዶች፣ በስራ ወቅት በነበሩ የግበዓት እጥረቶችና ተግዳሮቶች፣ በተወሰዱ የመፍትሄ መንገዶች እንዲሁም በቀጣይ ሊተገበሩ በሚገቡ ጉዳዮች እና መፍትሄዎች ላይ የማናጅመንት አባላቱ ሃሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄዎችን አንስተው በስፋት ተወያይተዋል፡፡
በመጨረሻም የባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀም አበረታች እንደነበረ እና ለቀጣይ የስራ ጊዜያትም ስንቅ በመሆኑ ለውጤቱ አስተዋጽኦ ላደረጉ የተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል:;
በተለይም በጥንካሬ የሚወሰዱት እቅድን በጠራ መልኩ እንዲታቀድ ጥረት መደረጉ; ከባለድርሻ አካት ጋር የተደረጉ የትስስር ሰነዶችና ውይይቶች፣ ለባለሙያዎች አቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች መሰጠቱ እና የክረምት የማህበራዊ አገልግሎት ስራዎቾ ተጠቃሽ እንደሆኑ ዋና ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል፡፡
ይሁን እንጂ እንደ ተቋም ጥሩ አፈፃፀሞች እና ስኬቶች አጠናክሮ በመያዝ በዝግጅት ምእራፍ የታዪ ክፍተቶች እና ጉድለቶችንም በማስተካከል በቀጣይ ሩብ ዓመታት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል::
በግምገማዊ ውይይቱ ላይ የባለስልጣን መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች፣ ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡
በመኴንንት ምናሴ
ፎቶ በአማረ ጠገናው