Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን @automotivetime Channel on Telegram

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

@automotivetime


አውቶሞቲቭ ታይም የሬዲዮ ፕሮግራም በፋና ኤፍኤም 98.1 እሁድ ከ7:00-8:00 ሰኞ ከ9:00-11:00 የሚተላለፍ የሬዲዮ እና እሁድ ከጠዋቱ 2:30-3:00 የሚተላለፍ የቴሌቪዢን ፕሮግራም ነው ።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን (Amharic)

አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን የሬዲዮ ፕሮግራም በፋና ኤፍኤም 98.1 በእሁድ እና ሰኞ ምክንያተን የሚተላለፍ ሰርተፊልም ነው። የሬዲዮ ፕሮግራም እና እሁድ ምሽቱ 2:30-3:00 የሚተላለፍ የቴሌቪዢን ፕሮግራም ምንጭ፣ የሚተላለፍ እና ከቶ ማመኖች ያግኙ! እንዴት ያሉበት ፎቶ እና ትምህርት? እናነቀላቀሉን በቴሌግሳም ከተላየቱ የተዘጋጀሽ መረጃዎች የምንለውን እርምጃና ምልክት ስላላየበህ እንችላለን! ከአገሪቱ ውስጥ እንደ የውስጥ መረጃ እና ትምህርቱ ይቅርብ እና ማግኘት ለማስቻ။

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

16 Jan, 12:33


አዲሱ ቶዮታ ኮስትር

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

16 Jan, 12:26


አዲሱን ቶዮታ ሀይሲ ተመልከቱ። አወይ ቴክኖሎጂ !!!!!

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

11 Jan, 14:58


ተሻሽሎ የጸደቀው ሕግ ምን ይላል!?

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

10 Jan, 17:26


የድሮን ስምሪት‼️
በአዲስ አበባ የትራፊክ ፍሰትና አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታን የሚቆጣጠር የድሮን ስምሪት ይደረጋል ሲል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ‼️
በቅርብ ቀናት በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ ፍሰትና አጠቃላይ የፀጥታ ሁኔታ እንዲሁም ታላላቅ ፕሮግራሞችን ቁጥጥር ማድረግ የሚችሉ የድሮኖች ስምሪት እንደሚደረግ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለፁ፡፡

የፀጥታ ጥምር ኃይል በአዲስ አበባና ዙሪያዋ ያለውን የፀጥታ ሁኔታን በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል። 

ግምገማውን የመሩት ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የወንጀል መከላከል ሥራችንን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ የሚችሉ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

09 Jan, 19:23


የመኪና ጋራጅ 20 ሽህ ብር ይቀጣል

በአዲስ አበባ ከተማ ምንም አይነት የፖሊስ መረጃን ሳይዝ የመኪና ጥገና አገልግሎትን የሰጠ ጋራጅ ቤት የ20 ሺህ ብር ቅጣት እንደሚተላለፍበት የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታውቋል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አማረ ታረቀኝ እንደተናገሩት ይህ የገንዘብ ቅጣት ከጥር 1 ቀን 2017 ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

አንድ ተሸከርካሪ ጉዳት ደርሶበት ሲመጣ ፈጥኖ ጥገና ከማድረግ ይልቅ አስቀድሞ ምን አደጋ አድርሶ ነው የመጣው፣ በሰውና በንብረት ላይ ያደረሰውስ አደጋ ይኖር ይሆን የሚሏቸውን መረጃ ከፖሊስ ማጣራት እና መረጃ ማግኘት እንደሚኖርበት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ስለሆነም አንድ ጋራዥ ቤት ለመኪና ጥገና ለማድረግ ከፖሊስ በፅሁፍ የተገለፀ ማስረጃ ሊኖረው ይገባል ሲሉ አቶ አማረ የገለፁ ሲሆን ይህን ሳያደርግ የመኪና ጥገናን ያከናወነ ጋራዥ ቤት 20 ሺህ ብር ይቀጣል በማለት ጨምረው ገልፀዋል።

ይህ የገንዘብ ቅጣት ውሳኔ የሚኒስትሮች ምክርቤት ባወጣው በደንብ ቁጥር 557 _2016 መሰረት ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን የመንገድ ትራንስፖርትና ትራፊክ ደህንነትን ለመቆጣጠር ያግዛል መባሉ ታውቋል

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

06 Jan, 17:36


ለተከበራችሁ ደንበኞቻችን እንኳን ለገና በአል በሰላም አደረሳችሁ!!!

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

24 Dec, 00:50


Des 23 20 24 Fana FM 98,1

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

16 Dec, 18:43


des 15 2024

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

15 Dec, 04:22


https://www.tiktok.com/@auto.concept32/video/7448199504114830598?_r=1&u_code=ddm10402c6l8bb&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e7d1i2hmje699f&share_item_id=7448199504114830598&source=h5_m&timestamp=1734236537&user_id=6858366377594848262&sec_user_id=MS4wLjABAAAACq0R_MYkehEKsiEKhOqLWNum5MQmwjtWP8CJhM2SNtn6--BsTBvJ1iANgYTFMJz5&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7447969079275161349&share_link_id=c0055b8e-a56d-469d-bd62-c568356c4b4e&share_app_id=1233&ugbiz_name=MAIN&ug_btm=b8727%2Cb2878&link_reflow_popup_iteration_sharer=%7B%22click_empty_to_play%22%3A1%2C%22dynamic_cover%22%3A1%2C%22follow_to_play_duration%22%3A-1.0%2C%22profile_clickable%22%3A1%7D&enable_checksum=1

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

03 Dec, 08:16


ውድ ተከታታዮቻችን በተለይ የስዕል ችሎታ ያላችሁ www.jaguar.com በመግባት ለ2026 የጃግዋር መኪና ዲዛይን ለመሥራት ተወዳደሩ። መልካም ዕድል!!

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

25 Nov, 16:50


ኪሎሜትር ማስተካከል ትልቅ ሌብነት ነው።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

25 Nov, 16:44


25 Nov 2024

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

24 Nov, 14:06


24 Nov 2024

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

14 Nov, 08:35


በአሽከርካሪዎች የሚፈጸሙ ጥፋቶች እንዲሁም የጥፋት ዝርዝር ከእነ ቅጣቱ በሚኒስቴሮች ምክር አዲስ የፀደቀው መመሪያ ከላይ ተያይዟል።
የአሽከርካሪ ፈቃድ ታግዶበት ሲያሽከረክር የተገኘ 3000 ብር
ሳያስፈቅድ አሸዋ፣ድንጋይ፣ አፈር...መንገድ ላይ ያራገፈ 3000 ብር ይቀጣል።
በአልኮል መጠጥ ትንፋሽ መመርመሪያ ከ1.0 በላይ ሚሊግራም/ሊትር የተገኘበት አሽከርካሪ 3000 ብር ይቀጣል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

12 Nov, 14:54


Nov 11 2024

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

07 Nov, 18:30


👍

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

02 Nov, 09:41


የትራንስፖርት መጫኛና ማውረጃ ተርሚናል ለውጥ መደረጉን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል

በዚህ መሰረት

1. መገናኛ  ውስጥ ተርሚናል ሲሰጡ የነበሩ
ከመገናኛ - ቃሊቲ
ከመገናኛ - ሳሪስ
ከመገናኛ - ጋርመንት መስመሮች
በጊዜያዊነት መገናኛ ሙሉጌታ ህንጻ ዝቅ ብሎ አምቼ ፊት ለፊት መንገድ በመዛወር በሁሉም ሞዳሊቲ አገልግሎት እየተሰጠ ሲሆን

2. ቦሌ ክፍለ ከተማ ፊት ለፊት ሲሰጥ የነበረው;
ከመገናኛ - ቱሉ ዲምቱ እና ኮዬ ፈቼ  አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው መስመሮች አምቼ አጠገብ (ቀደም ሲል ከነበረበት ቦታ ትንሽ ዝቅ ብሎ)

3. ከዚህ በፊት ሙሉጌታ ህንፃ አካባቢ   ይሰጡ የነበሩ መስመሮች
ከመገናኛ - ገርጂ
ከመገናኛ-ጎሮ
ከመገናኛ - አያት እና
ከመገናኛ - ሰሚት የመጫኛና መውረጃ መስመሮች ወደ ዘርፈሽዋል አካባቢ በተዘጋጀው ጊዜያዊ ተርሚናል ውስጥ ተዛውሯል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

30 Oct, 19:22


ከመገናኛ ቦሌ (ከቦሌ መገናኛ) ለትራንስፖርት ዝግ ሆነ ።

ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ እንዲሁም ከቦሌ ወደ መገናኛ አደባባይ በሁለቱም አቅጣጫ ለተሽከርካሪ ዝግ መሆኑን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን አሳውቋል።

ባለሥልጣኑ መገናኛ አካባቢ ያለውን የትራንስፖርት መጨናነቅ በዘላቂነት ለመፍታት የመሬት ውስጥ የእግረኛ መተላላፊያ መስመር ግንባታ ትላንት ምሽት መጀመሩን ገልፆ እግረኞች በቦሌ ክ/ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት በኩል ባለው የእግረኛ መንገድ እንዲጠቀሙ ጠቁሟል።

እንዲሁም አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲገለገሉ አሳስቧል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

29 Oct, 23:44


ስለተሽከርካሪዎ ሊያውቁት የሚገባ

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

29 Oct, 04:18


በ 5000 ዶላር ብቻ ይሸጣሉ የተባሉት በራሪዎቹ የቻይና መኪኖች።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

28 Oct, 22:07


በውሀም በምድርም መጓዝ የምትችለው ሞተር ሳይክል

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

28 Oct, 22:07


ዮክሬናዊው የአርሰናል ተጫዋች ዢንቼንኮ በ 7 ሚሊየን ዶላር ከገዛት የግል አውሮፕላኑ ጋር

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

23 Oct, 16:09


👍

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

14 Oct, 15:00


በኢትዮጵያ ለሚገኙ ችግር ያለባቸው የሱዙኪ SPRESSO ተሽከርካሪዎች ጥሪ ቀረበ

ሱዙኪ ኩባንያ የሚያመርታቸው ስፕሬሶ (SPRESSO) በሚል መጠሪያ የሚታወቁ የተወሰኑ ተሽከርካሪዎች ላይ የመሪ ዘንግ ክፍል አካባቢ ችግር መኖሩ በመታወቁ በኢትዮጵያ ይህ ችግር ያጋጠማቸው የተጠቀሱት ዓይነት ተሽከርካሪዎች ተሰብስበው ማስተካከያ እንዲደርግባቸው ጥሪ ቀረበ።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሱዙኪ ተሽከርካሪዎች ህጋዊ አከፋፋይ ድርጅት የሆነው ታምሪን ኩባንያ ዛሬ በሪፖርተር ላይ ባወጣው ይፋዊ መረጃ በተወሰኑ የ SPRESSO የምርት ባች ላይ በተደጋጋሚ ለጉዳት ሊጋለጥ የሚችል የመሪ ዘንግ ክፍል አካባቢ እክል ስለመኖሩ አምራች ኩባንያ ሱዙኪ መረጃ እንዳደረሰው አስታውቋል።

"በመሆኑም ከላይ የተገለጽው ችግር ይኖርባቸዋል ተብለው የታሰቡ የምርት ባች ላይ ያሉትን SPRESSO መኪናዎች በሙሉ ጥሪ በማድረግ ሊያጋጥም ከሚችል እክል ማስወገድ አስፈላጊ ሆኗዋል" ያለው ታምሪን ፤ በኢትዮጵያ የ SPRESSO መኪና ባላቤት የሆኑ ባለንብረቶች ይፋ የተደረገውን የምርት ዘመን ዝርዝርና የሻንሲ ቁጥር በማየት ተሽከርካሪዎቻቸው ለጥሪ እና ጥገና የሚፈለጉ መሆኑን እንዲያረጋገጡ እናሳስባለን።

ይፋ በተደረገው ዝርዝር ውስጥ የሻንሲ ቁጥራቸውን ያገኙ ባለቤቶች ተሽከርካሪዎቹን በታምሪን ኩባንያ የአገልግሎት ማዕከል በማቅረብ ችግር እንዳለበት የተለየውን ክፍል (የመሪ ዘንግ አካላት) በኦርጂናል የሱዙኪ መለዋወጫዎች
በማስቀየር ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ
እንዲተባበሩን ጥብቅ ጥሪውን አቅርቧል።

"በመሆኑም የ SPRESSO መኪና ባላቤት የሆናችሁ ባለንብረቶች ከታች ባለው ዝርዝር የሻንሲ ቁጥር በማየት ተሽከርካሪያችሁ ለጥሪ እና ጥገና የታሰበ መሆኑን እንድታረጋገጡ በጥብቅ እናሳስባለን" ብሏል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

13 Oct, 11:18


በሚንስትሮች ምክር ቤት የፀደቀው የተሻሻለው የመንገድ እና የትራንስፖርት ትራፊ መቆጣበሪያ የ👇👇
1 - ተሽከርካሪ በማሽከርከር በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ማንኛውም አሽከርካሪ 1,600 ብር ይቀጣል

2 - በተሽከርካሪ ማንኛውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው አካል ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ያደረሰ ለ 6 ወር መንጃ ፈቃዱ ይታገዳል

3 - በተሽከርካሪ ማንኛውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው አካል ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ያደረሰ ለ 1 አመት መንጃ ፈቃዱ ይታገዳል

4 - በተሽከርካሪ ማንኛውንም አይነት ጥፋት በመፈፀም በሰው ሞት ያደረሰ ለ 1 አመት መንጃ ፈቃዱ ይታገዳል

5 - ግልፅ የሆነ ደምብ ወይም መመሪያ በመተላለፍ 2 እና ከዛ በላይ የሞት ጉዳት ያደረሰ 1 አመት ከ6 ወር ይታገዳል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

09 Oct, 16:52


ከአዲስ መንጃ ፈቃድ ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ ጀምሮ ይታደሱ ተብሏል‼️
ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ያሉ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እድሳት ያድርጉ ተብሏል።

ተገልጋዮች  መንጃፍቃዳቸውን  በየአራት ዓመቱ እንዲያድሱም የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታውቋል፡፡

ባለሥልጣኑ ባለፉት 6 ዓመታት የመልካም አስተዳደር እና የፍትኃዊነት ጥያቄን ሲያስነሳ የነበረው የሁለት ዓመት እና የአራት ዓመት የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱን ገልጿል።

በዚህም ከአዲስ መንጃ ፈቃድ እና ዕድሜያቸው ከ55 በላይ ከሆኑ ግለሰቦች ውጭ ሁሉም መንጃ ፈቃዶች ከነገ መስከረም 30/2017 ዓ.ም ጀምሮ በአራት ዓመት እንደሚታደሱ አስታውቋል፡፡ 

አዲስ መንጃ ፈቃድም ከሁለት ዓመት የሙከራ በኋላ፣ ባለው አሰራር መሠረት በየአራት ዓመቱ እንደሚታደስ ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ነገር ግን ዕድሜያቸው ከ55 ዓመት በላይ ለሆኑ ግለሰቦች በየሁለት ዓመት የሚታደስ ሆኖ ክፍያው የአራት ዓመቱ ክፍያ ግማሽ (50%) እንደሚሆን ተመላክቷል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

04 Oct, 08:59


ተከለከለ‼️
ከዛሬ አርብ እስከ ሰኞ ለአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ‼️
ለኢሬቻ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ሲባል ዛሬ እለተ ዓርብ መስከረም 24 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 6:00 እስከ ሰኞ መስከረም 27 ቀን 2017 እስከ ንጋቱ 12:00 በአዲስ አበባ ከተማ የሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት መከልከሉ ተገልጿል፡፡
ይህንን ክልከላም የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ ፖሊሶች አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
=============🎉🎉🎉

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

01 Oct, 03:30


https://vm.tiktok.com/ZMhruxQp3/

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

28 Sep, 07:21


በኢትዮጵያ የሱዙኪ መኪና አስመጪ ኩባንያ S-PRESSO የተባሉ ሞዴሎች በአስቸኳይ ለጥገና እንዲቀርቡ አሳሰበ‼️
የመኪናዎቹ አስመጪው ታምሪን የተባለው ድርጅት በቅርቡ በተወሰኑ የ S-PRESSO መኪናዎች ላይ በተደጋጋሚ ለጉዳት ሊጋለጥ የሚችል የመሪ ዘንግ ክፍል እንዳለ የሱዙኪ አምራች መረጃ አድርሶናል ብሏል።

በመሆኑም ከላይ የተገለጸው ችግር ይኖርባቸዋል ተብለው የታሰቡ የምርት ባች ላይ ያሉትን S-PRESSO መኪናዎች በሙሉ ጥሪ በማድረግ ሊያጋጥም ከሚችል እክል ማስወገድ አስፈላጊ ሆኗል ያለው ድርጅቱ የመኪናው ባለቤት የሆኑ ኢትዮጵያውያን ተሽከርካሪዎቻቸውን ለጥገና እንዲያቀርቡ አሳስቧል።

ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ የሻንሲ ቁጥሮችን ያጋራ ሲሆን ቁጥራቸው በዚህ ዝርዝር ውስጥ ያሉ ተሽከርካሪዎች በሙሉ ወደ ድርጅቱ የሰርቪስ ማእከል በመሄድ በኦርጂናል የሱዙኪ መለዋወጫዎች የመሪ ዘንግ አካላት ቅያሬ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

25 Sep, 14:52


መስከረም 16/2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
#Soldaily | የ2017 ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በሠላም እንዲከበር የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባቸው የሚታወቅ ሲሆን መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
በዚህም መሠረት ፦
• ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ
• ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና
• ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)
• ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ
• ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ
• ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ
• ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ
• ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ
• ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ እንዲሁም
• ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ መንገድ የሚዘጋ ሲሆን በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ መሆኑን አሽከርካሪዎች ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀምና የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያሳይዋቸው መንገድ በመጓዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።

በአሉ ያለ አንዳች የፀጥታ ስጋት እንዲጠናቀቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጎ ወደ ስራ መግባቱን ያስታወሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት በዓሉ ኃይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር እና የበዓሉ ታዳሚዎች ሠላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጿል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
#addisababapolice

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

21 Sep, 07:06


ተሽሯል‼️
የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ ዛሬ አውጥቶት የነበረውና ከመጭው እሁድ  ጀምሮ ይተገበራል የተባለው ለብዙሃን ትራንስፖርት ብቻ የሚሰጡ መስመሮች ልየታ እንዲቀር ወስኗል።
በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይቼ ይፋ እስከማደርግ  በአዲስ አበባ ለብዙሃን ትራንስፖርት ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ መስመሮች በሚል ይፋ የተደረጉት መስመሮች እንደድሮው ባለበት ይቀጥላል መባሉ ታውቋል።ትራንስፖርት ቢሮው:-
👉ከቦሌ- ፒያሳ፣
👉ከቦሌ- ሜክሲኮ፣
👉ከቦሌ- አራት ኪሎ፣
👉ከቦሌ- አውቶቢስ ተራ፣
👉ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣
👉ከጀሞ- ፒያሳ እና
👉ከጀሞ- ሜክሲኮ በደርሶ መልስ ለብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ መሰጠት እንድችሉ በሚል አሳውቆ ነበር፡፡

Automotive Time 🚗 አውቶሞቲቭ ታይም ፋና ኤፍኤም 98.1 እና ፋና ቴሌቪዢን

20 Sep, 10:51


በአዲስ አበባ ለብዙሃን ትራንስፖርት ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ መስመሮች ይፋ ሆኑ‼️
ከትምህርት ቤቶች መከፈት ጋር ተያይዞ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ከመጪው እሑድ ጀምሮ በተመረጡ መስመሮች ላይ ተግባራዊ እንደሚደረግ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል።መስመሮቹም ከቦሌ- ፒያሳ፣ ከቦሌ- ሜክሲኮ፣ ከቦሌ- አራት ኪሎ፣ ከቦሌ- አውቶቢስ ተራ፣ ከቦሌ- ሽሮሜዳ፣ ከጀሞ- ፒያሳ እና ከጀሞ- ሜክሲኮ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ  ከፒያሳ- ቦሌ፣ ከሜክሲኮ- ቦሌ፣ ከአራት ኪሎ- ቦሌ፣ ከአውቶቡስ ተራ- ቦሌ፣ ከሽሮ ሜዳ- ቦሌ፣ ከፒያሳ ጀሞ እና ከሜክሲኮ - ጀሞ  የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት ብቻ መሰጠት እንደሚጀምር ተመላክቷል፡፡ቢሮው " የአገልግሎቱ መጀመር የመንገድ መዘጋጋቱን ለመቀነስ እና ብዙ የሰው ቁጥር ያለው ተጓዥ በአንድ ጊዜ ማመላለስ ያስችላል " ብሏል።

በዚህም ተማሪና መምህራን ብሎም ሌሎች ተገልጋዮች በሰዓታቸው ወደ ሚፈልጉት ቦታ በመንቀሳቀስ አገልግሎት እንዲያገኙ ያግዛል ተብሏል፡፡" በከተማዋ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው የተነቃቃ እንዲሆን ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል " ሲልም አክሏል።

3,890

subscribers

564

photos

64

videos