ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- እ“የሙእሚን ፆሞች የሰይጣንን ፊት ያጠቁራሉ።
ኢስቲግፋር የሰይጣንን የሕይወት ሥር ይቆርጣል፣ መልካም ስራ የአላህን ውዴታ ያጎናፅፋል ።ሰደቃ ወይም በጎ አድራጎት ፣አከርካሪ ይሰብራል።
መጋረጃዎቹ ከዓይኖችህ ላይ ከተነሱ፣ ስለ ፆምህ ምክንያት የሰይጣን ፊት እንደጠቆረ ታስተውላለህ። ሰይጣን ግን ደካማና የተዳከመ አይደለም በጾምህ ብቻ ፊቱን ታጠቁርና በምጽዋትም አከርካሪውን ትሰብራለህ።
በሰባቱ መጋረጃዎች ውስጥ በማለፍ የሰይጣንን አከርካሪ ሰብረው እንዲያጠፉት ሁሉንም ድርጊቶች በፍጹም ቅንነት ማከናወን አለቦት።
የሰይጣንን እናት አይቻለሁ።። በአንድ በአስከፊ ረሃብ ወቅት አንድ ሰባኪ በመስጊድ ውስጥ ሚንበር ላይ ቆሞ አንድ ሰው ሰዳቃን መስጠት ከፈለገ (70) ሰይጣኖች እጁ ላይ ተጣብቀው ሰደቃውን እንዳይሰጥ ሊከለክሉት ይሞክራሉ።
በማለት ተናገረ ። ይህን ጊዜ
ከሚንበሩ እግርጌ ተቀምጦ የነበረው አንድ ሙእሚን በመገረም ለጓደኞቹ እንዲህ አላቸው...
ሰይጣንን ከሰዳቃ ከመስጠት ጋር ምን አገናኘው? ቤት ውስጥ ስንዴ አለኝ። አሁን ወደ ቤት እሄዳለሁ ከዚያም ስንዴውን መስጂድ አምጥቼ ምጽዋት እሰጣላው እስኪ። ሰይጣን ይሄን እንዳላደርገው እንዴት እንደሚከለክለኝ አያለሁ!” አለ።
ከዚያም ሰውዬው ተነስቶ ወደ ቤቱ ሄደ። ቤት እንደደረሰ ሚስቱ ሃሳቡን ስታውቅ፣ “በዚህ አስከፊ ረሃብ ጊዜ ለሚስትህና ለልጆችህ ምንም ግድ የለህምን? ምናልባት የረሃቡ ሁኔታ ሊራዘም ይችላል እና ሁላችንም በስንዴ እጥረት በረሃብ ማለቃችን ነው አለች ።
ይህን ጊዜ ባልየው በከባድ ጥርጣሬ በመዋጥ እና
የረሀቡን አስከፊነት በመፍራት ባዶ እጁን ወደ መስጊድ ተመለሰ።
ጓደኞቹም “ምን ሆነሃል? ስንዴውን ሳትይዝ ባዶ እጅህን ከቤት ተመልሰህ ነው ? ወይስ! ሰባዎቹ ሰይጣኖች በእጆችህ ላይ ተጣብቀው ሶደቃውን ከለከሉህ አሉት?
ሰውየውም፣ እንዲህ ሲል መለሰ “ሰይጣንን አላየሁም፣ ነገር ግን በመልካም ስራዬ ላይ የመጣችውን እናታቸውን አይቻቸዋለሁ!” አለ።
ይህ የሚያሳየው ሰው ከሰይጣን ጋር ለመታገል እንደሚሞክር ነገር ግን ብዙ ጊዜ ሚስቱ ወይም ሌሎች ከመልካም ስራ ያዘናጉታል። ።።።
https://t.me/bedru511111