ነአምን media @neamn_media Channel on Telegram

ነአምን media

@neamn_media


<< ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር!>>
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ
#ትምህርቶች
#ዝማሬዎችና
#ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ስነ-ፅሁፎች
የሚለቀቁበት ቻናል ነው።

ለሁሉም መረጃና አስተያየትና በቻናሉ ላይ ለመፃፍና ለመሳተፍ @theofloss ያናግሩን መረጃውንም ያካፍሉን።

ነአምን media (Amharic)

ነአምን media እንዴት ነው? ነአምን media ከምን ተመልክቶ ነበር? አይነትም ስለ ቶችሳም ዝማሬችና መንፈሳዊ ቀመሮች የሚለቀቁበት ችናል ነው እድሜዋን ይሳል ፡፡ ይህ ኦርቶክሳዊ ችናል በአሐዱ አምላክ እግዚአበሔር፣ ትምህርቶችና ዝማሬዎችን ለመማር ለስነ-ፅሁፍ እና ለልኡላን መንፈሳዊ ችናል ነው። የሚለቀቁበት ችናል ላይ መረጃና አስተያየት ለመፃፍና ለመሳተፍ የእራሱን ላይ @theofloss በትክክል እንደገና ያካፍላችኋል።

ነአምን media

21 Nov, 17:18


🫃👉መንታ ወንድና ሴት ቢወለዱ ክርስትና እንዴት  ይነሳሉ⁉️
👉ሴት በወር አበባ ጊዜስ⁉️
👉 ወንድ ህልመ ሌሊት ቢያጋጥመው ለስንት ቀን ይረክሳል ⁉️
👉 ሰባቱ አጽዋማት እነማን ናቸው⁉️
👉 አምስቱ አዕማደ ምስጢራት ማን ናቸው⁉️
👉 ከአስርቱ ትዕዛዛት ውጪ ያለው ትዕዛዝ ምነው⁉️

⛪️ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አንፃር መልሱን ይመልከቱ⛪️
                    👇👇👇👇

ነአምን media

21 Nov, 17:06


👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

ነአምን media

02 Nov, 20:59


‹‹እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሄልዊ
ሀገረኪናሁ ገሊላ እትዊ
ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ
ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ዖዝያን ዜናዊ
እምግብፅ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ፡፡››

ትርጉም፡-
እመቤቴ ማርያም ሆይ! ስሙ ናዝራዊ የሚባል ልጅሽን ለአዳምና ለሔዋን ክብር የባሕርይ አባቱ አብ ከግብጽ ይጠራዋል፣ማለት በግብጽ ስደት አይሞትም ኋላ በቀራንዮ ተሰቅሎ ዓለምን ያድናል ብሎ ነቢዩ ዖዝያን (ሆሴዕ) ትንቢት እንደተናገረ እስከ መቼ በባይድ አገር ትኖሪያለሽ? እነሆ ወደ አገርሽ ናዝሬት ተመለሽ፡፡

(ሰቆቃወ ድንግል)


https://t.me/neamn_media

ነአምን media

27 Oct, 15:00


ጌታ ሆይ፣

ሰማይን ከፍተኸው፣ ምን አለ ብትመጣ
ትልቅ ፍሬ ባይኖር፣ ሰናፍጭ አታጣ፣

*
"እውነት እላችኋለሁ የሰናፍጭ ቅንጣት ያህል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ከዚህ ወደዚያ ተነቅለህ ሒድ ብትሉት ይፈልሳል" [ማቴ. 17:20]
**

https://t.me/neamn_media

ነአምን media

26 Oct, 05:29


ነአምን media pinned «መ/ር ኢዮብ ይመኑ የጠፋው ልጅ አዲስ ስብከት በነአምን ሚዲያ የቲክቶክ ቻናል follow, share, subscribe አድርጉ https://vm.tiktok.com/ZMhHDh5yh/»

ነአምን media

26 Oct, 05:29


መ/ር ኢዮብ ይመኑ
የጠፋው ልጅ
አዲስ ስብከት
በነአምን ሚዲያ የቲክቶክ ቻናል
follow, share, subscribe አድርጉ
https://vm.tiktok.com/ZMhHDh5yh/

ነአምን media

24 Oct, 18:58


ነአምን media pinned «ዲ/ን ዘላለም ታዬ ስለ ንስሐ በነአምን ሚዲያ 👇👇👇👇👇👇👇 https://www.tiktok.com/@neamnmedia/video/7429410915033910533?_r=1&u_code=eh062mfj35116g&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e8me564b32e8ad&share_item_id=7429410915033910533&source=h5_m&timestamp=1729794760&user_id=7429…»

ነአምን media

24 Oct, 18:56


ዲ/ን ዘላለም ታዬ ስለ ንስሐ
በነአምን ሚዲያ
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/@neamnmedia/video/7429410915033910533?_r=1&u_code=eh062mfj35116g&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e8me564b32e8ad&share_item_id=7429410915033910533&source=h5_m&timestamp=1729794760&user_id=7429311620574954501&sec_user_id=MS4wLjABAAAABeL0XrebtpME_7WPLOjdJZ4BjQxdU2iJ97f7B_-H-SvXsa__UfEgEgXzQW_rj62_&social_share_type=0&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7394175688993261317&share_link_id=71c74e97-1b57-458d-8cf5-e7072cba0711&share_app_id=1233&ugbiz_name=MAIN&ug_btm=b8727%2Cb2878&enable_checksum=1

ነአምን media

24 Oct, 18:33


ነአምን media pinned «ነአምን ሚዲያ በtiktok መጥቷል follow በማድረግ የሚዲያችን ቤተሰብ ይሁኑ ነአምን ሚዲያ https://www.tiktok.com/@neamnmedia/video/7429410915033910533?_r=1&u_code=eh062mfj35116g&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e8me564b32e8ad&share_item_id=7429410915033910533&source=h5_m&timestamp=…»

ነአምን media

24 Oct, 18:32


ነአምን ሚዲያ በtiktok መጥቷል follow በማድረግ የሚዲያችን ቤተሰብ ይሁኑ ነአምን ሚዲያ

https://www.tiktok.com/@neamnmedia/video/7429410915033910533?_r=1&u_code=eh062mfj35116g&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=e8me564b32e8ad&share_item_id=7429410915033910533&source=h5_m&timestamp=1729794760&user_id=7429311620574954501&sec_user_id=MS4wLjABAAAABeL0XrebtpME_7WPLOjdJZ4BjQxdU2iJ97f7B_-H-SvXsa__UfEgEgXzQW_rj62_&social_share_type=0&utm_source=copy&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7394175688993261317&share_link_id=71c74e97-1b57-458d-8cf5-e7072cba0711&share_app_id=1233&ugbiz_name=MAIN&ug_btm=b8727%2Cb2878&enable_checksum=1

ነአምን media

24 Oct, 10:45


#ሎጎ ማሰራት እንፈልጋለን (በክፍያ)
#logo design


የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የሚዲያችን ቤተሰቦች ነአምን ሚዲያ ከተመሰረተ እነሆ አንደኛ አመቱን ያገባደደ ሲሆን በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብዙ መንፈሳዊ ይዘቶች ያላቸውን ጽሁፎች ለሚዲያው ተከታታዮች ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን አሁን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ሚዲያውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለዚህም ዘመኑን የዋጀ የሚዲያ ምልክት (media logo) ሊያሠራ ስለሚፈልግ በዚህ ስራ ላይ ልምድ ያላችሁ እንዲሁም በlogo design ላይ መስራት ፍላጎት ያላችሁ በዚህ ስራ ላይ እንድትሳተፉ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
የሚዲያው ሎጎ በዚሁ በቻናሉ ላይ ተለቆ በተመልካች ድምጽ ያሸነው ይመረጣል!
በ @theofloss inbox sample ማቅረብና ተጨማሪ መረጃዎችን መጠየቅ ይቻላል!


https://t.me/neamn_media

ነአምን media

23 Oct, 05:31


ነአምን media pinned «#ሎጎ ማሰራት እንፈልጋለን (በክፍያ) #logo design የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የሚዲያችን ቤተሰቦች ነአምን ሚዲያ ከተመሰረተ እነሆ አንደኛ አመቱን ያገባደደ ሲሆን በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብዙ መንፈሳዊ ይዘቶች ያላቸውን ጽሁፎች ለሚዲያው ተከታታዮች ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን አሁን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ሚዲያውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ አልሞ እየተንቀሳቀሰ…»

ነአምን media

23 Oct, 05:31


#ሎጎ ማሰራት እንፈልጋለን (በክፍያ)
#logo design


የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የሚዲያችን ቤተሰቦች ነአምን ሚዲያ ከተመሰረተ እነሆ አንደኛ አመቱን ያገባደደ ሲሆን በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብዙ መንፈሳዊ ይዘቶች ያላቸውን ጽሁፎች ለሚዲያው ተከታታዮች ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን አሁን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ሚዲያውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለዚህም ዘመኑን የዋጀ የሚዲያ ምልክት (media logo) ሊያሠራ ስለሚፈልግ በዚህ ስራ ላይ ልምድ ያላችሁ እንዲሁም በlogo design ላይ መስራት ፍላጎት ያላችሁ በዚህ ስራ ላይ እንድትሳተፉ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
የሚዲያው ሎጎ በዚሁ በቻናሉ ላይ ተለቆ በተመልካች ድምጽ ያሸነው ይመረጣል!
በ @theofloss inbox sample ማቅረብና ተጨማሪ መረጃዎችን መጠየቅ ይቻላል!


https://t.me/neamn_media

ነአምን media

22 Oct, 19:01


ነአምን media pinned «#ሎጎ ማሰራት እንፈልጋለን (በክፍያ) #logo design የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የሚዲያችን ቤተሰቦች ነአምን ሚዲያ ከተመሰረተ እነሆ አንደኛ አመቱን ያገባደደ ሲሆን በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብዙ መንፈሳዊ ይዘቶች ያላቸውን ጽሁፎች ለሚዲያው ተከታታዮች ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን አሁን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ሚዲያውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ አልሞ እየተንቀሳቀሰ…»

ነአምን media

22 Oct, 19:01


#ሎጎ ማሰራት እንፈልጋለን (በክፍያ)
#logo design


የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የሚዲያችን ቤተሰቦች ነአምን ሚዲያ ከተመሰረተ እነሆ አንደኛ አመቱን ያገባደደ ሲሆን በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብዙ መንፈሳዊ ይዘቶች ያላቸውን ጽሁፎች ለሚዲያው ተከታታዮች ሲያቀርብ የቆየ ሲሆን አሁን የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች በመጠቀም ሚዲያውን ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሳደግ አልሞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ለዚህም ዘመኑን የዋጀ የሚዲያ ምልክት (media logo) ሊያሠራ ስለሚፈልግ በዚህ ስራ ላይ ልምድ ያላችሁ እንዲሁም በlogo design ላይ መስራት ፍላጎት ያላችሁ በዚህ ስራ ላይ እንድትሳተፉ ሲል ጥሪውን ያቀርባል።
የሚዲያው ሎጎ በዚሁ በቻናሉ ላይ ተለቆ በተመልካች ድምጽ ያሸነው ይመረጣል!
በ @theofloss inbox sample ማቅረብና ተጨማሪ መረጃዎችን መጠየቅ ይቻላል!


https://t.me/neamn_media

ነአምን media

16 Oct, 04:43


Godaansa giiftii teenyaa maariyaam ilmaa ishee waajjiin taasiste



Nazreet(Iyyaruusaalemii) gara misir(gibxii)tti...
1. Giiftii Maariyam
2. Iyyasuus Kiristoos
3. Yooseef jaarsicha kaadhimss Maariyaam
4. Ilma Yooseef jaarsichaa"Yoosaa"
5. Saloomee fi harroota 5 ta'anii godaanan.

Sababa godaansaa baay'"ee keessaa muraasa....

1. Raajiin dubbatame akka raawwatuuf. "mucaa koo gibxittan waame" Hoosee 11:1 dabalaatanii raajii Isa. 19÷2 irratti "Waaqayyo duumessa aritiidhaan gara gibxii ni dhufa" jedhameera. Waaqayyo kan jedhame Iyyasuus kiristoosidha. "Sagaleen sun waaqa ture" yoh.1÷1 akkuma jedhame. Duumessi saffistuun giifti Maariyaamiidha. Duumessi tajaajila gurguddaa lama qaba. A. Samii uwwisee miidhaksa. B. Rooba laata. Giiftii Maariyamiin duumessa dhugaa namootatti kabaja uwwistee,sanyiin namaa du'a irraa oolchiteedha. Isa.1÷9"osoo sanyii nuuf hambisuu baatee..." akka jedhame. Duumessi dhugaa Giiftii Maariyamii ishee rooba dhugaa jireenya Kiristaanummaa lalisiise Iyyasuus Kiristoos nuuf argamsiistedha.

2. Fkn raawwachuuf.
Ser. Um.37÷1-35 yoo dubbisnu Yooseef obboloota isaatiin gurguramee gibxii bu'uu arganna. Fkn Yooseef kan ta'e gooftanis firoota fi saboota isaa keessaa kan ta'e Heroodsiin ari'atame gibxii bu'e. Kana malees sagalee wangeelaa "yoo magaala kanaa isin ari'atan isa biroott baqadhaa" (Mat.10÷23) jedhu raawwidhaan(hojiidhaan) barsiisuufidha.

3. Xaa'otii gibxii barbaadeessufi. Isa.19÷1 "xaa'ootiiwwan gibxii fuuldura isaatti hoollatanii badu."

4. Godaansa qulqullootaa eebbisuuf godaane. Godaanee Addaam gara iddoo isaa isa duraatti deebisuufis godaane. (Galata Maariyaam guyyaa wiixataa)
Raajii Iyyasuus irrattis"ኢየሱስ ስዱድ ተስፋሆሙ ለስዱዳን" jechuunis "Iyyasuus Inni godaane,abdii godaantootaati." Jechuudhaan katabameera.

5. Dhiigni isaa yeroo malee akka hin dhangalaaneef godaane. Dhiigni isaa Jimaaya fannoo qofa dhangala'ee kan fayyina laatu waan ta'eefidha.

   Bara Abaaboo(Tsigee)
Guyyoota 1260 ykn waggaa sadiif ji'a jahaadha. Mul. 13÷1-6 irratti caqasameera. Akka barsiisa mana Kiristiyaanatti
Fulbaana 26-sadaasa 05 yaadanna. Guyyoota 40 jechuudha. Kunis goonka eebba kan argamsiisu ta'uu agarsiisufidha.
Fulbaana 26- onkoloolessa 20...bara godaanuu yoo jennu
Onkooolessa 21 -sadaasa 05 immoo....bara deebi'uu jenna.
Kunis yeroo abaaboon daraarte keessatti yaadatamuun isaa #abaaboon_dhugaa mataa dhuma ishee giiftii Maariyamii waan taateef. Kana qulqlluu Efreem inni Sooriyaa galata Maariyamii guyyaa sanbata Kiristiyaanaa lakkoofsa 7 irratti "አንቲ ዉእቱ ጽጌ ዘመዓዛ ሠናይ" #jechuunis abaaboon dhugaa foolii gaarii qabdu si'iidha jechuun ibseera. Kanaaf abaaboo yeroo abaabootti yaadachuun waan miidhaguufidha.



+++join & share+++
👇👇👇👇👇👇👇
@neamn_media
@neamn_media
@neamn_media

https://t.me/neamn_media
@,Arsii Asellaa

ነአምን media

16 Oct, 04:35


ቅምሻ ፪ - ከአሐቲ ድንግል

ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ስለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው ወይስ ንጽሕት ስለሆነች ነው እግዚአብሔር የመረጣት?

አንዳንዶች ስለ ድንግል መመረጥ ሲነገር ሲሰሙ ሲመርጣት ላትመረጥ ነውን? እርሱ ጠበቃት እንጂ እርስዋ ምን አደረገች ሲሉ ይሰማሉ። እግዚአብሔር ሰለመረጣት ነው ንጽሕት የሆነችው የሚለው አደገኛ ክህደት ነው። ለምን ቢሉ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠውን ነፃ ፈቃድ የሚንድ ነውና። ዳግመኛ እርሷ እግዚአብሔር ስለመረጣት ብቻ ከሆነ ንጽሕት የሆነችው እያንዳንዱ ሰው ንጹሕ የማይሆነው እግዚአብሔር ስላልመረጠው ነው ወደሚል የቅድመ ውሳኔ ክህደት የሚያመራ ጠማማ መንገድ ነው።

እንዲህ ከሆነ ደግሞ በዓለም ላይ ለሚሠሩ የርኩሰትና የአመፅ የበደል ውድቀቶች ሁሉ ተጠያቂው እግዚአብሔር እንጂ ሰው አይደለም ብሎ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው። ምክንያቱም እግዚአብሔር የመረጠው ብቻ ንጹሕ ከሆነ ሁሉም የመንጻት ሥልጣን ካልተሰጠው በበደለኛነት ዘመናቸውን የፈፀሙ ሰዎች ተጠያቂ መሆን የለባቸውም፤ ከኃጢአት ለመንጻት ቢፈልጉ እንኳን አልተመረጡምና አይችሉም ማለት ነዋ! እንዲህ ከሆነ ሰዎች ሁሉ ሊድኑ እና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ የሚወድ እግዚአብሔር (ጢሞ. ፪፥፫) ፈቃዱ ወዴት አለ? እርሱ የመረጣቸው ብቻ የሚነጹ ከሆነ ባልመረጣቸው ላይ ለምን ይፈርድባቸዋል? ፈታሒ በጽድቅነቱስ ወዴት አለ?

ነገር ግን ርቱዕ የሆነው የሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን የቀና የጸና አስተምህሮዋ እንዲህ አይደለም። እግዚአብሔር ሰዎችን ፍጻሜያቸውን አስቀድሞ አይቶ ይመርጣል እንጂ ወስኖ መርጦ የፈጠረው ሰው የለም። በወንጌል የእግዚአብሔር መንግስት በመካከላችሁ ናት ማለቱም ሰው ለመዳን የሚያስችለው ለመምረጥ የሚያበቃው ኃይል በእጁ እንዳለ ሲያጠይቅ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው የተባለውም ለዚህ ነው። በስሙ ለሚያምኑ የተሰጣቸው ስልጣን የተባለው ለመዳንም ላለመዳንም የሰው ነፃ ፈቃድና ልጅነት እንደተሰጠ ሲያስረዳ ነው። እግዚአብሔር ወደ አቤልና ወደ መስዕዋቱ ተመለከተ የተባለውም አቤል የልቡን ቅንነት የመስዕዋቱን መበጀት ስሙርነት አይቶ ተመልክቶ አቤልን ተቀበለው እንጂ አቤል እንዲያ እንዲሆን አድርጎ ወሰኖ መርጦ አልፈጠረውም። በአንፃሩ ወደ ቃየልና መስዕዋቱ አልተመለከተም ማለት የቃየልን የልቡን ጥመት አየና የመስዕዋቱን አለመበጀት አይቶ አልተቀበለውም ነገር ግን እግዚአብሔር ለክፋት ወስኖ አልፈጠረውም። እግዚአብሔር ሲኦል የሚገቡ ሰዎች እንዳሉ አውቆ ሲኦልን አዘጋጀ እንጂ ሲኦል በሚገቡ ሰዎች ላይ አስቀድሞ እንዲገቡ አድርጎ ወስኖ አልፈጠረም።

እናቱ ድንግል ማርያምን ከእናቷ ማሕፀን መርገም እንዳይኖርባት የጠበቃት እርሱ ነው ቅድመ ዓለም የአምላክ እናት እንድትሆን የመረጣትም እርሱ ነው። ነገር ግን ፍፃሜዋን በነፍስ በስጋ በአፍኣ ንጽሕት እንድትሆን አውቆ መረጣት እንጂ እርሱ ሰለወሰነ የጠበቃት የመረጣት አይደለችም። በዘመኗ ሁሉ በቅድስናዋ ተሸልማ እንደምትኖር አውቆ ከመርገም አነጻት፥ ኖሮባት አይደለም እንዳይኖርባት ጠበቃት እንጂ!

መንፈስ ቅዱስ ጠበቃት አነፃት መባሉም ፍፃሜዋን አይቶ መርገም እንዳይኖርባት ጠበቃት ማለት ነው እንጂ በዓለም ኃጢአት እንዳትሰራ ከለከላት ማለት አይደለም። ንጹህ ሆኖ መፈጠርማ አዳምም ተፈጥሮ ነበር በተፈጥሮ የተሰጠውን ንጹህ ጠባይ በቅድስና መጠቀም አልተቻለውም እንጂ እርሷ ግን ንጽሕናን ቅድስናን ደራርባ ይዛ ተገኝታለችና በዛው ድንግልናዋ ለአምላክ እናትነት በቃች። የሕይወት ፍሬን አፈራችበት እንዲመርጣት እግዚአብሔርን የሳበ በአምላክ ዘንድ ሞገስን የያዘ ንጽሕና ይዛ ተገኝታለችና እንድትመረጥ ሆና ተገኝታለች። ንጹሃንን ለክብር መምረጥማ ለፈጣሪ ድንቅ አይደለም ከእርስዋ ይልቅ ጠላቶቹን እኛን በደሙ ፈሳሽነት ይቅር ማለቱ አይደንቅምን?.......(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል ገፅ 272-277 ላይ የተቀነጨበ)

ነአምን media

16 Oct, 04:32


ቅምሻ - ፩

አሐቲ ድንግል - አንዲት ድንግል

ድንግል ማርያም ለምን አንዲት ድንግል ትባላለች?

እመቤታችን ድንግል ማርያም በምድርም በሰማይም አቻ የማይገኝላት አንዲት ድንግል ናት። ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌልም የምትልቅ በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች በወንጌል የተፃፈች አንዲት ድንግል አለች። ይላል ቅዱስ ያሬድ።

ከዚህም ተነስቶ አንድ ሰው ተነስቶ በወንጌል ሌሎች ደናግል የሉምን? ስለምን በወንጌል የተጻፈች አንዲት ድንግል ትላለህ? ብሎ ቢጠይቀው ከኪሩቤል የምትበልጥ ከሱራፌል የምትበልጥበት የድንግልና ዘውድ ያላት አንዲት ድንግል አልኩህ እንጂ ደናግላንማ ብዙ ደናግል አሉ ብሎ ይመልስለታል።

ቀጥሎም በመላዕክት ክንፍ የምትጋረድ በክብሩ መንበር በፊት ምህረት የምትለምን በራሷ ላይ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊል የተቀዳጀች አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል አለች።

አሁንም ቅዱስ ያሬድን ስለምን አማኑኤል የመረጣት አንዲት ድንግል ትላለህ አርሱ የመረጣቸው ብዙ ደናግላን የሉምን? ብሎ የሚጠይቀው ቢኖር፥ አማኑኤል ሥጋን ይለብስ ዘንድ የመረጣት፤ ከእርስዋም ሥጋን ለብሶ አማኑኤል የተባለባት፥ በመላእክት ክንፍ የምትጋረድ፥ እግዚአብሔር በክብሩ ዙፋን በፊቱ ለመቆም የመረጣት፥ በእናትነት የሰለጠነ የባለሟልነት ዘውድን የተቀዳጀች አንዲት ድንግል አልኩ እንጂ እርሱ የመረጣቸው ደናግላንማ ስንቱ! ብሎ ይመልስለታል።

ደግሞም ፀጉሯ እንደ ሐር ፈትል ያማረ፥ የአንደበቷ መዓዛ እንደ እንኮይ የጣፈጠ ትእምርተ መስቀል ያለው አክሊልን የተቀዳጀች የልዑል ንጽሕት አዳራሽ የሆነች አንዲት ድንግል አለች።

የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ሌሎች ደናግላን የሉምን ስለምን ለይቶ እርሷን አንዲት ድንግል አለ ቢሉ? ከእርሷ ስጋ ይነሳ ዘንድ እግዚአብሔርን በማህፀኗ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን የወሰነች እውነተኛ የእርሱ ማደሪያ ሌላ ድንግል ከማርያም በቀር ወዴት አለ ይለዋል! ብቻዋን የእግዚአብሔር መቅደስ ለመሆን የበቃች እንደሆነች ሁሉ ከቅዱሳን ሁሉ ተለይታ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ያለው እንደ እንኮይ የጣፈጠ አማላጅነት ያላት አንዲት ድንግል እርሷ ብቻ ናት! ስለዚህ እንደ ቅዱስ ያሬድ እመቤታችን ብቻዋን አንዲት ድንግል የተሰኘችበት ወላዲተ አምላክነቷ፤ ንፅሕናዋ ፤ማኅደረ መለኮትነቷ አማላጅነቷ እና ዘለዓለማዊ ድንግልናዋ ናቸው ማለት ነው።

፩.በድንጋሌ ሥጋ ዘለዓለማዊ
በተፈትሆ የማይመረመር ድንግልናዋ ነው። ይህም ሥስት የማይመረመሩ ግብራት አሉት። ድንግል እንደሆነች መፀነስ፥ ድንግል ሆና ሳለ መውለዷ፥ ከወለደች በኋላ ድንግል ሆና መኖሯ ናቸው። እነዚህ በህገ ተፈጥሮ የማይታሰቡ ረቂቅ ግብራት ናቸው። ሰው ድንግል ሆኖ ያለ ወንድ ዘር መፀነስ አይቻለውም፥ በድንግልና እያለ የፀነሰ መሆን አይችልም፥ ሰው በድንግልና መውለድ አይቻለውም፥ ከወለደ በኋላ ደግሞ ድንግል መሆን እንዴት ይችላል? ድንግል የሆነች ሌላ ሰው እናት አይደለችም፥ እናትም ከሆነች ድንግል አይደለችም። ይህ ለአንዲቱ ለድንግል ማርያም ብቻ የተቻለ ነው።

፪. ድንግል በቃሏ - በቃሏም ድንግል
የቃል ድንግልና በሦስት ወገን ነው። እኒህም ክፉ አለመናገር፥ ምስጋና አለመብላትና በጎውን መናገር ናቸው። ሰው በንግግሩ ብዙ ኃጢአቶች ይሰራል። ሐሜት፣ ማጉረምረም፥ ቁጣ፥ ብስጭት፥ መዋሸት፥ መርገም፥ መሳደብ፥ ዋዛ ፈዛዛ፥ ያለጊዜው መሳቅ መሳለቅ፥ ዘፈን፥ ተውኔት፥ ድንፋታ፥ መንፈግ ነገር ማመላለስ፥ ቃል መለዋወጥ፥ አደራ መብላት፥ በሀሰት መማል፥ ሰጥቶ መንሳት፥ ክህደት፥ ማታለል፥ ማስነወር፥ አድልዎ፥ መጠራጠር፥ ማሽሟጠጥ፥ አሽሙር፥ ኃጢአትን ማመስገንና ማስፈራራት እነዚህን የመሳሰሉ ሁሉ ናቸው።

እመቤታችን በማንም ክፋትን ተናግራ አታውቅም አንደበቷ የለዘበ የለመለመ ነው። ቅዱስ ገብርኤል ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና የማይታሰብ ዕፁብ ድንቅ የመውለዷን ዜና ሲነግራትም እኔ ወንድ ሳላውቅ እንዴት ይሆንልኛል ብላ ነገሩን ወደ መረዳት ተሻገረች እንጂ ይህ የማይሆን ነገር ነው ብላ ወደ መጠራጠር ወይም መልአኩን ወደ መንቀፍ አልቃጣችም። የአንደበት ድንግልና ማለት የማይቻል ጭንቅ ፍጹም ከተፈጥሮ ህግ በላይ የሆነን ነገር በመስማት ጊዜም ቢሆን ያለመጠራጠር በሃይማኖት መጠየቅና ፍፃሜውን በትዕግሥት መጠበቅ ነው።

መከራ በደረሰ ጊዜ ብዙ የቃል ድንግልና ያላቸው ቅዱሳን ችግሩን የፈጠሩትን ከመንቀፍ ይልቅ በእኔ ችግር የተከሰተ ነው ብለው ራሳቸውን ይወቅሳሉ። ነገር ግን እነርሱ ቀድሞ መበደላቸውን እያስታወሱ ነው። የድንግል ማርያም ግን የሚደንቀው ምንም ነውር የሌለባት ስትሆን በቃሏ ድንግል ስለሆነች እኔ ኃጢተኛ ነኝ ትል ነበር። በብስራተ መልአክ አምላክን የፀነስኩ እናት ነኝ ስትል ገናንነቷን አትናገርም። መልካም በመናገር ንግግሯ ሁሉ ሃይማኖት ተስፋና ፍቅር ናቸው።

፫. ድንግል በኅሊናሃ - በኅሊና ድንግልና የፀናች አንዲት ድንግል፦
ሰው በተግባር ቢነጻ በንግግር አይነጻም፥ በንግግር ቢነጻ በኅሊናው መንፃት አይቻለውም። ጻድቃንም ቢሆኑ ወድቀው ተነስተው በተጋድሎ ለክብር ይበቃሉ እንጂ ከጅማሬ እስከ ፍፃሜው አለመበደል ከቶ የተቻለው የለም። እመቤታችን ድንግል ማርያም ግን በኅሊናዋ እንኳን ያልበደለች ፍጽምት አንዲት ድንግል ነች። ጽድቅን ሁሉ የተሞላች ድንግል ማርያም ንጽሕት በመሆኗ በኅሊናዋን ድንግልና፤ የቃሏን ድንግልና፤ የስጋዋን ድንግልና በአንድ ላይ "እንዘ ኢይአምር ብእሴ" "ወንድ ስለማላውቅ" በሚል የንፅህና ሸማ ጠቅልላ ተናገረች (ሉቃ.፩፥፴፬) በዚህ ድንግልናዋም አምላክን ለመፀነስ በቃች።.....(ቀጣዩን መጽሐፉን ገዝተው ያንብቡ)

(ከርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል መጽሐፍ ገፅ 241-251 የተቀነጨበ)

ነአምን media

14 Oct, 04:52


ነአምን media pinned «እስከ 1000 ዶላር ድረስ በቀን መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ? ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመግባት መሥራት ትችላላችሁ ስራው በጣም ቀላል ነው ምንም አይነት የትምህርት ደረጃን አይጠይቅም ያለው ቦታ ጥቂት ስለሆነ ቶሎ ቶሎ እየገባችሁ ስሩ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_573930345 Join the cherry game using this referral…»

ነአምን media

14 Oct, 04:52


እስከ 1000 ዶላር ድረስ በቀን መስራት እንደሚችሉ ያውቃሉ? ከዚህ በታች ባለው ሊንክ በመግባት መሥራት ትችላላችሁ ስራው በጣም ቀላል ነው ምንም አይነት የትምህርት ደረጃን አይጠይቅም ያለው ቦታ ጥቂት ስለሆነ ቶሎ ቶሎ እየገባችሁ ስሩ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/cherrygame_io_bot/game?startapp=r_573930345
Join the cherry game using this referral link and win prizes!