ወንጌል Tube @yene_geta_tube Channel on Telegram

ወንጌል Tube

@yene_geta_tube


የዚህ ቻናል አገልግሎት -
፦ ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል
:- አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ዝማሬዎች
:- የመድረክ ዝማሬዎችን ማድረስ ነው!
:-መንፈሳዊ ታርኮች

ወንጌል Tube (Amharic)

ወንጌል Tube ከእርስዎ የተቀላቀለ ቦታ ነው። ይክን እና ማብሽት ላይ ያላችሁ መምሪያዎችን ከአዳዲስ እና ቆየት እንደሚያቀርብ ይረዳል። ቅዱሱን የእግዚአብሔር ቃል በአሰፋላይ አዲስ ምላሽ በእናንተ ላይ እንዴት በመድረክ ወደሚገባበጠዎች መምሪያዎችን ለማሳስብ እንጠቀማለን። ወንጌል Tube ለመስራት የክርስትና አፍሪካ መንገዶች ምክንያት ለመጠቀም እንጠቀማለን። እግዚአብሔርን እና መድረክ ዝማሬዎችን ማድረስ እንደሚሆን ወንጌል Tube ማህበረሰብ ነው። ይህ ቦታ ለመንፈሳዊ ታርኮች ለማስቀመጥ መሆኑን ለመጥራት ወንጌል Tube ለማስተዋወቅ ስለእኛ ከእግዚአብሔር መስሪያ ጋር ነው።

ወንጌል Tube

20 Jan, 08:21


የእኛ ሻሎም ብትሄድም የእግዚአብሔር ሻሎም ግን መታለች ስል ኤል-ሻሎም ብያታለሁ! Nothing Missing Nothing Broken!
እግዚአብሔርን አመስግኑልኝ!

ወንጌል Tube

17 Jan, 18:34


”መሥዋዕት ለእግዚአብሔር”ባለፈው እሁድ

ክብር ሁሉ በሁሉ ለረዳን ለታማኙ እግዚአብሔር ይሁን!
ሁሉ በእርሱ ከእርሱ ነዉና ለእርሱ ለዘለአለም ክብር ይሁን!
ባለፈው እሁድ በአዲስ አበባ ሚሊንየም አዳራሽ ተደርጎ በነበረው የ”መሥዋዕት ለእግዚአብሔር” የዝማሬ በዓል ጌታ ከጠበቅነው በላይ በብዙ አስደንቆን አልፈናል!ብዙዎች በፀሎት ከጎናችን ነበራችሁ አመስግኑልን የጌታን እጅ አይተናልና!
ከተለያየ አቅጣጫና ክልል ከቅርብም ከሩቅም በሚመችም በማይመችም ሁኔታ ላይ ሆናችሁ ይህንን የአምልኮ ዝግጅት ለመካፈል የተገኛችሁ ወጣቶች እናቶችና አባቶች ስለእናንተ ጌታዬን አመሰግናለሁ ጌታ ያክብራችሁ!
ለዚህ ዝግጅት መሳካት በተለያየ መንገድ አብራችሁን ለቆማችሁ ሁሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን!

Special Thanks
◦ El-Hadar engineering
◦ Yougo city church
◦ Costume designer Emmy Lakew
◦ Band
◦ Back Vocalists
◦ Choir
◦ Sound
◦ Ersam art pro light (Samuel )
◦ Anayo multimedia ( Bereketab)
◦ BBG Group (ushers)
◦ Yougo city church (ushers )
. All Christian medias and Christian TikTokers
◦ Addis Ababa city administration
◦ Federal police
◦ Addis Ababa police
◦ Millennium hall management
◦ Team Apex events

ወንጌል Tube

17 Jan, 18:18


Please family like እና share በማድረግ አበረታቱኝ 🙏

ወንጌል Tube

17 Jan, 18:17


1. #የእግዚአብሔር #ፍቅር #ዩኒቨርሳል #ነው የእግዚአብሔር ፍቅር በጥቂቶች ብቻ የተገደበ አይደለም፡ ዓለምን ሁሉ ያጠቃልላል።

2. #እምነት #ማዕከላዊ #ነው
በኢየሱስ ማመን የዘላለም ሕይወት ተስፋን ለማግኘት ቁልፉ ነው።

3. #የዘላለም #ሕይወት #ስጦታ #ነው፡- መዳን የሚገለጠው ለበጎ ሥራ ​​ሽልማት ሳይሆን ለሚያምኑት ከእግዚአብሔር በተሰጠው ስጦታ ነው።

ወንጌል Tube

17 Jan, 18:15


ውድ ወዳጆች
እግዚአብሔር ቢፈቅድና ብንኖር

"ለክብሩ" TO HIS GLORY

በሚል መሪ ሃሳብ
የካቲት 30/March 9, 2025 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የመዝሙር ድግስ ይኖረናል:: ሁላችሁ በዚህ ዝግጅት ላይ በመገኘት አብረን አምላካችንን እግዚአብሔርን በዝማሬ እንድናመልክ የበረከቱ ተካፋዮች እንድንሆንበፍቅር እና በአክብሮት እጋብዛለሁ:: ለዝግጅቱ መሳካት እና መከናወን በፀሎታችሁ አብራችሁኝ እንድትሆኑ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ:: የእግዚአብሔር ፀጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን!!

ወንጌል Tube

17 Jan, 05:18


.           "መልካም ፍሬ የምያፈራ ዛፍ"

አንድ ዛፍ ካደገና ፍሬ ማፍራት ከጀመረ በኋላ ፍረው ጣፋጭና የሚፈለግ ከሆነ በላዩ ላይ አንድ ፍሬም ብኖር ያየው ሰው ሁሉ ድንጋይ ይወረውርበታል ምክንያቱም ተፈላጊ ፍሬ ስለያዘ!

#አስተውል በአንተ/ች ላይም ፍሬ ባይኖር ማንም ድንጋይ አይወረውርብህም ነበረ የደረሰብህና የሚደርስብህ ችግር በሙሉ አስፈላግ ፍሬ ስላፈራክ ያንን ፍሬ ከአንተ ለመውሰድ የተደረገ ስራ ነወ።

ያ ዛፍ ተውኝ በሎ ለራሱ መናገር እንኳን አይችልም  ፣ ምናልባትም ያ ያፈራው ፍሬ ምን ያህል ተፈላጊ ፣ ጣፍጭ፣ ለሌሎች እንደሆነም አይቅም ።
አስተውሉ ስንቶቻችን የዚህ መልካም ዛፍ አይነት ፈተና ውሰጥ ነን!! ?

በጽናት ቆመን 30፣60፣100 ፍሬ እንድናፈራ ጌታ ይርዳን🙏


                         

ወንጌል Tube

14 Jan, 05:35


.          ትልቁ

🍬ትልቁ  ጥበብ - እግዚብሔርን  መፍራት

🍬 ትልቁ ስልጣን - ራስን  መግዛት

🍬 ትልቁ  ማስተዋል -  ከሀጢአት  መራቅ

🍬 ትልቁ  ጀግንነት  - ትዕግስት

🍬 ትልቁ  ሀብት  - ፍቅር

🍬 ትልቁ  ስጦታ -  ክርስቶስ

🍬 ትልቁ  ቁም  ነገር - ይቅርታ

🍬 ትልቁ  ምላሽ - ምስጋና  ነውና  እነዚህን  በህይወትህ  ተርጉመህ  ኑርባቸው  ::

ወንጌል Tube

12 Jan, 05:42


አለም እንድህ ነት !!!

ለዘመናት ያፈሩ ሀብት በጥቅት ማይክሮ ሴከንድ ወደ አመድ ተቀየረ ። ተዝቆ የማያልቅ የመሰለው ንብረት የእሳት እራት ሆኖ ። በሁሉም ነገር እግዚአብሔር ትልቅ ነው ።

10 ሺህ ውድና ቄንጠኛ ቪላዎች አመድ ሆኑ። ዕውቅ እና ቱጃር የሆሊውድ ተዋንያን ውድ ንብረቶች እንዳልነበሩ ሆኑ። ከአንድ ታዳጊ ሀገር ዓመታዊ በጀት በላይ የሆነ 150 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ተቃጥሎ አመድ ተዛቀ። እሳቱ አሁንም እያወደመ ቀጠለ። በመቶዎች የሚቆጠሩ ግዙፍ ህንፃዎች የእሳት እራት ሆኑ። በሺህ የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ዕምቢ ብሏቸው 900 ዕስረኞች ከማረሚያ ወጥተው በእሳት ማጥፋት ስራ ቢሰማሩም ሰደድ እሳቱ ከውቅያኖስ በሚመጣ አደገኛ ንፋስ ሃይል እያገኘ በሁለት አቅጣጫ በፍጥነት እየተዛመተ ነው። በወርቅ የተንቆጠቆጡ የሚመስሉ ቤቶች ጋዩ።

የማያልቅ የሚመስለውን ውድ ሀብታቸውን ያጡት ሀብታም የሆሊውድ አክተሮች ዕምባ አውጥተው አለቀሱ። ታዋቂው ሀብታሙ የሆሊውድ አክተር ጀምስ ውድ ሀብቱ ተቃጥሎበት ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቃለመጠይቅ በዕምባ ታጥቦ ዕምባውን መቆጣጠር ሲያቅተው ቃለመጠይቁን አቋረጠ። ልቤ ተሰበረ አለ።

በዓለም ከእግዚአብሔር በቀር ምንም እንደማያስመካ በግልጽ ለሁሉም ታየ። የሚመካ በእግዚአብሔር ይመካ የሚለው የእግዚአብሔር ቃል ያልገባቸው ይህን የሚያውቁበት ክስተት በልዕለ ሃያሏ ሀገር አሜሪካ በቱጃሮች መንደር በካሊፎርኒያ በሎስአንጀለስ ተፈጠረ። ሰው ሆይ ማንም ሁን ምንም ይኑርህ ምንህም ዋስትና ሆኖ አያስመካህም ።

ወንጌል Tube

08 Jan, 09:35


ልጆቼ ለድመትና ለዉሻ የተለየ ፍቅር አላቸዉ።
ትንሿ ልጄ አንድ ቀን ፣እኛ ወደ መንግስተ ሰማይ ስንሄድ እነሱ ወደየት ነዉ የሚሄዱት ብላ ጠየቀችኝ ።እኔም እንስሳት ከሞቱ በኋላ ሌላ ህይወት አይኖራቸዉም በቃ ሞተዉ ይቀራሉ ስላት ቆጣ ብላ እንዴት እንደዚ ትያለሽ ማም በጣም ጨካኝ ነሽ አለችኝ።
አይ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ መንግስተ ሰማይ ይገባሉ የሚል አልተፃፈም ስላት እኔ ግን ለድመቴ እፀልይላታለሁ አለችኝ ። ከዛስ ስላት ፣ወደ ኢየሱስ ስንሄድ አስፈቅድላታለሁ መንግስተሰማይ እንድትገባ አለችኝ።መጠየቅ ትችያለሽ ግን ላይፈቅድ ይችላል እሱ የሞተዉ ለሰዉ ልጆች ነዉ ስላት ፈገግ ብላ በእርግጠኝነት ጌታ እሺ ይለኛል እሱ ደግ ነዉ አለችኝ።

ምናለ ትልልቁ ሰዉ ሁሉ እንደ ልጆች ንፁህ ልብ ቢሰጠን ብየ ተመኘሁ።ምድር ገነት ትሆን ነበር።

እንዲህም አለ፡— እውነት እላችኋለሁ፥ ካልተመለሳችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከቶ አትገቡም።
ማቲዎስ18፥3
ከfb መንደር
@yene_geta_tube

ወንጌል Tube

07 Jan, 13:01


1 ዮሐንስ 5 (1 John)
4፤ ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል በሰላም አደረሰን ""
መልካም በዓል

ወንጌል Tube

07 Jan, 09:02


“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
  — ኢሳይያስ 9፥6
እንኳን አደረሰሽ /ህ

ወንጌል Tube

24 Dec, 02:04


#ከልብ_ይቅርታ_እጠይቃለሁ...

የተወደዳችሁ የጌታ ቤተሰቦች የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፣
በዘጸአት አፖስቶሊክ ሪፎርሜሽን ቤተክርስቲያን ላለፉት ሁለት ወራት “የተነገረልንን የተስፋ ቃል የምንወርስበት ወግ” (Reset) በሚል ርዕስ ተከታታይ ትምህርት እየሰጠሁ ነበር። በታህሳስ 02 ቀን 2017 ዓ.ም እንደ ወትሮው የትምህርቱን የመጨረሻ ክፍል በመደበኛ የትምህርት ቀናችን ላይ እያስተማርኩ እንደነበረ የሚታወቅ ነው።

በዕለቱ ከተነሱ ሃሳቦች መካከል ሁለንተናዊ የሆነን ዕድገት እና ለውጥ ስለማምጣት የተነሳው አንዱ ሃሳብ ነበር። ከዚህም ጋር በተያያዘ ራሳችን እና ቤተሰባችን ላይ ሁለንተናዊ ለውጥ ስለማምጣት፣ ራስን ስለመጠበቅ፣ ስለ ግለ-ንጽህና እንዲሁም ከስንፍና ወጥቶ በትጋት ስለመስራት እና እግዚአብሔር የሰጠንን የተስፋ ቃል ስለመውረስ አጽንዖት በመስጠት ተናግሬያለሁ።
በዚህ ሁኔታ ለትውልዱ ካለኝ ልብ እና ቅናት የተነሳ አባት ልጁን እንደሚገስጽ፣ ህይወትን መለወጥ እንደሚቻል በማበረታታት መንፈስ፣ በቤተሰብ ድባብ ውስጥ በቀልድ መልክ የተጠቀምኳቸው ቃላት ነበሩ።

በጊዜው በጉባዔው ለነበሩ እና ለቋሚ የዩቱውብ ቤተሰቦቻችን የተነገረው ንግግር ከትምህርቱ ዓውድ አንጻር በበጎ የተወሰደ ሲሆን፣ በሌላ መልኩ ደግሞ ከቀጥታ የዩቱብ ስርጭቱ ላይ ተቀንጭቦ በመውጣት ትክክል ላልሆነ እና ዓላማውን ለሳተ ትርጉም ሊውል እንደቻለ ብሎም ጥያቄዎችን እንደፈጠረ አይቻለሁ።

ይህም፣ እኔም ሆንኩኝ ቤተክርስቲያን፣ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው ሰዎች የወረደ አመለካከት እንዳለን ተደርጎ እውነተኛ ማንነታችንን በማይወክል መልኩ በተሳሳተ ሁኔታ ሊተረጎም እንደቻለ ሲዘዋወሩ ከነበሩ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች አስተውያለሁ። እንደ ቤተክርስቲያን ዝቅተኛ የኑሮ ሁኔታ ላይ ለሚገኙ ወገኖች ልዩ ትኩረት በማድረግ ቃሉ እንደሚያስተምረን ራሱን የቻለ የአገልግሎት ክፍል በማቋቋም ማህበረሰባችንን በተለያየ መልኩ ስናገለግል መቆየታችን የሚታወቅ ነው።

በአካባቢያችንም ከወረዳው ጋር በመተባበር ችግረኛ ቤተሰቦችን የምንረዳ፣ ልጆቻቸውንም የምናስተምር ሲሆን በየጊዜው ልዩ ልዩ የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍም እያደረግን እንደምንገኝ የሚታወቅ ነው። በግሌም ከቤተሰቤ ጋር በዚሁ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ ስሳተፍ ኖሬያለሁ።

ስለሆነም የተላለፈው ሃሳብ ድሆችን የማንኳሰስ እና ዝቅ የማድረግ ዓላማ ያለው ሳይሆን ራስን ስለመጠበቅ ብቻ የተደረገ ንግግር እንደሆነ በቅንነት እንዲወሰድ እጠይቃለሁ። ለትውልዱ እና ወድጄ ለማገለግለው ህዘብም የግራ መጋባት ምክንያት የሚሆን ንግግር ከመናገር ይልቅ በብዙ ትጋት ዝቅ ብዬ ማገልገል የሁልጊዜ አቋሜ ነው። በተፈጠረውም ነገር እጅግ ያዘንኩ እና እንደ ቤተክርሰቲያን ለቀጣይ አገልግሎታችን ብዙ ትምህርት እንደወሰድን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጥ እወዳለሁ።

በመጨረሻም፣ የተወደዳችሁ ቅዱሳን አላስፈላጊ ትርጉም ሊሰጥ ከሚችል በማህበራዊ ሚዲያ ከሚዘዋወረው የተቆረጠ ንግግር ይልቅ ሙሉውን መልዕክት ከታች በተቀመጠው ሊንክ እንድታዩ እየጠየኩ፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለተፈጠረው ማንኛውም ዓይነት ቅሬታ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

ጌታ ይባርካችሁ!
ሐዋርያ ዮሐንስ ግርማ
ታህሳስ 2017 ዓ/ም

ወንጌል Tube

15 Dec, 07:23


""ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ ""

እንዳው የእግዚአብሔር " ምርጫ " ግርም ይለኛል እንዴት ወደ ቤቴ መጣ.... ? መዳኔ ካለኝ ብርታት ወይም ድካም ጋር አይገናኝም እንዲያው በፀጋው ያለምንም ምክንያት ድኖ መቅረት በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ለዘላለም ሰላም መሸፈት እንዴት መታደል ነው ተናጋሪ ምላስስ ይሄን እውነት ያብራራዋል ወይ ?

" ምንም ብሆን ይህን አደረገልኝ "
1ኛ ጢሞ-1 -13
ክብሩ ለታረደልኝ ቸር መምህር ለኢየሱስ ይሁን
ማነው እንደኔ እንዲህ የተደረገለት !!!

ወንጌል Tube

08 Dec, 04:47


አብዛኞቻችን ቤተክርስቲያን የምንደርሰው አምልኮ ሲጀምር ነው። ምክንያቱም ከአምልኮው በፊት ያለውን ጸሎት ቀጣይ ላሉት ፕሮግራሞች የሚያዘጋጀን መሆኑን ስላልተረዳን ነው።

#በጸሎት_ስፍራ_የማናውቀው_እግዚአብሔር_በአምልኮ_ስፍራ_አይገኝልንም!

📌ለአንድ ክርስቲያን በጣም ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች መካከል መጸለይ ነው።

የማይጸልይ ክርስቲያን ወይም የጸሎት ሕይወቱን ለማሳደግ የማይተጋ ክርስቲያን ውጤታማ እና ስኬታማ አይሆንም። ምክንያቱም ውጤታማነት እና ስኬት ከእግዚአብሔር ጋር ባለን ህብረት የሚመጣ ነው።

“ከማመስገን ጋር ነቅታችሁ በትጋት ጸልዩ።”
— ቆላስይስ 4፥2 (አዲሱ መ.ት)

ዲያቢሎስ በዋናነት ክርስቲያን ላይ አነጣጥሮ ከሚሰራባቸው መንገዶች አንዱ የጸሎት ሕይወታችንን እንዲደክም በማድረግ ነው። ክርስቲያን ደግሞ የጸሎት ሕይወቱ ከተመታ አጠቃላይ ሕይወቱ ይመታል።

ስለዚህ ነቅተን በትጋት ልንጸልይ እና ከመንፈሳዊ አለም ጋር ሁሌ የተገናኘን እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት መሆን የምንችል መሆን አለብን። ምክንያቱም ክርስቲያን ክርስቲያን መሆኑን የሚያውቀው መጸለይ ከጀመረ ብቻ ነው።

NO PRAYER NO VOICE!
NO PRAYER NO POWER!
NO PRAYER NO ENERGY!
NO PRAYER NO LIFE!

“የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቦአል፤ ስለዚህ መጸለይ እንድትችሉ ንቁ አእምሮ ይኑራችሁ፤ ራሳችሁንም የምትገዙ ሁኑ።”
— 1ኛ ጴጥሮስ 4፥7 (አዲሱ መ.ት)

መልካም ቀን!
ሬቨረንድ ተዘራ ያሬድ

ወንጌል Tube

04 Dec, 07:25


እልልል ዛሬ ደግሞ የእንዳልክ ታላቅ እህት ጌታን ተቀበለች😇🙌🙌🙌 ሙሉ ቤተሰቡ ተወረሰ ! ሼር አድርጉ

እንስራ (ማሠሮ፤ ገንቦ) ይዛ በየሠፈሩ ምትዞር እህቴን፤ እንስራ ላይ ጨርቅ ጨርቁ ላይ የሆነ ስዕል፤ ስዕሉ ላይ 3 ክፍተት ያለዉ እንጨት እዛ ላይ ሻማ ይዛ ከተማ ለከተማ የምትዞረዉን እህቴን ጌታ እንስራ አስጥሎአት መጽሐፍ ቅዱስ አስያዛት!! ለሊት ደዉላ ያንተን ኢየሱስ አገኘሁት አለችኝ።

ወንጌል Tube

26 Nov, 02:36


#ለደካማ_ምዕመናን_የተጻፈ_ደብዳቤ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ "በታዋቂ" ሰዎች የሚደረግ ካሉበት ቤተ እምነት ወደ ሌላው ቤተ እምነት የሚደረግ ዝውውር እየተለመደ መጥቷል።
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት የቆየ ወደ ፕሮቴስታንት ማሕበር ሲቀላቀል፤ ኦርቶዶክሱ በሐዘን፤ ፕሮቴስታንቱ ደግሞ በደስታ ይንሳፈፋል።(በተመሳሳዩ ኦርቶዶክሱም እንዲሁ)
የአንድን ቤተ እምነት ሐሰተኝነትን ታዋቂ ሰው በመውጣቱ የምንመዝን ከሆንን ጴጥሮስ ኢየሱስን በመካዱ የኢየሱስን እውነት መሆንን እንጠራጠር ነበር፣ ዴማስም ዓለምን ወድዶ በመጥፋቱ የሐዋርያ ጳውሎስን አስተምህሮ በተጠራጠርን ነበር። ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም። እንዲሁም ደግሞ

የአንድን ቤተ እምነት ትክክለኛነትን ታዋቂ ሰው ወደዛ በመቀላቀሉ የምንመዝን ከሆነ ለወንጌል ብዙ ዋጋ የከፈለው ቱርቱሊያን የተቀላቀለበትን "የሞንታኒስ እንቅስቃሴን" እውነት ነው ብለን በተቀላቀልን ነበር።

የአንድን ቤተ እምነት ትክክለኝነት ሆነ ሐሰተኛነት እንደ pendulum በሚዘዋወሩ(በልጅነታቸው ዥዋዥዌ ባልተጫወቱ) ሰዎች አንመዝን።
ታዋቂ ሰው ከኦርቶዶክስ ወደ ፕሮቴስታንት ስለተቀላቀለ ብቻ ኦርቶዶክስን አናውግዝ፤ እንዲሁም ደግሞ ኦርቶዶክሶችም ታዋቂ ሰው ከፕሮቴስታንት ወደ ኦርቶዶክስ ስለሄድ አታውግዙን/ልክነታችሁንም አታረጋግጡልን።

መለኪያችን ግለሰቦች ሳይሆኑ፤ የቤተ እምነቱ አስተምህሮ ነው። አስተምሮ ላይ መነጋገር የአዋቂ ነው።
ዛሬ መጣ ያሉት ነገ ሊወጣ ይችላል፤ ፕሮቴስታንቱም ዛሬ መጣ ያሉት ነገ ሊወጣ ይችላል። በመውጣት እና መግባታቸው ደማችሁ ዝቅ እና ከፍ የሚል ከሆነ በሽተኛ ናችሁ እና ታከሙ።
የወጣው ምን አጥቶ ነው የወጣው የሚለው እና ምን አግኝቶ ነው የተመለሰው የሚለው የሁለቱም ጎራዎች የቤት ሥራ ነው።

ደግሞ ወደ እኛ ከመጣ በኌላ በገንዘብ አልደገፍነውም ብር ስላጣ ነው የተመለሰው እያላችሁ ምክንያት የምትደረድሩ ሆይ፤ ለእናንተም ፈራሁ፤(ነገ ምዕመን አልደገፈኝም ብለህ ልትክድ ያለኸው አንተ ነህና) የገባን ነገር እውነት ነው ብለን ካመንን እንኳን ማጣትን እንኳን መራብን ለጌታ መሞትን መምረጥ የለብንም እንዴ? ወይስ አሁን ምናገለግል በጣም ደልቶን እያገለገልን ነው። (ሰዎቹ ከኦርቶዳክስ ሲወጡ ብር ፈልገው ነው ይባላል፤ ወደ ኦርቶዶክስ ሲመለሱ ግን እኛ ጋር ብር ስላጡ ነው ይባላሉ።) ብቻ እኛ ያለንን ጥለን የምንከተለውን አምላክ እንጂ የሌለን እንዲሰጠን የምንከተለው አምላክ የለንም።
[ልብ አድርጉልኝ ስለ ዲያቆን ሐዋዝ እየተናገርኩኝ አይደለም። ምክንያቱም እሱ ፕሮቴስታንት እንደሆነ አላውቅምና]

ብቻ እንደ እኔ አንድ ሰው ኤቲስት ከሚሆን ሙስሊም፤ ሙስሊም ከሚሆን ደግሞ ጆቫ ዊትነስ/ሐዋርያት ቢሆን፤ ጆቫ ዊትነስ/ ሐዋርያት ከሚሆን ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ/ ካቶሊክ ቢሆ፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ/ ካቶሊክ ከሚሆን ኦርቶዶክ ተሐድሶ ቢሆን፤ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ከሚሆን ፕሮቴስታንት ቢሆን የተሻለ ነው እላለሁ።

[በሳል ምዕመን አይሳደብም፤ አይነጫነጭም፤ ጸጋና ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን]

Prist kibru ገፅ የተወሰደ!

ወንጌል Tube

24 Nov, 15:23


ይሄን ድንቅ መዝሙር በመስማት ተባረኩብት
🛑 subscribed በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ

ታሪኬን በታሪክ| singer Yishak Bekele
New Song

https://youtu.be/98ABZ5sRp4I

ወንጌል Tube

21 Nov, 05:17


የነብይ እዩ ጩፋ ወላጅ እናት የሆኑት ወይዘሮ በየነች ዶጊሶ ባጋጠማቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው እለት ህዳር 12 ወደጌታ ተሰብስበዋል። ለነብይ እዩ ጩፋ እና ለመላው ቤተሰባቸው እግዚአብሔር መፅናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

ወንጌል Tube

17 Nov, 17:01


#አባታችን_ዘማሪ_ደስታ_ብራሞ_ጌታ_ይርዳህ!
ዛሬ ዘማሪ ደስታ ቢራሞ በሶዶ ጥንታዊት ከተማ አጥቢያ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ በዋና መጋቢነት ተሹሟልና እግዚ/ር ፀጋውን ያብዛልህ ፥ጌታ የረገጥክህበትን ሁሉ አሳልፎ ይስጥህ ፥በርታ በፀሎታችን እንደግፍሃለን በሉልኝ አደራ!!!!!!!""""

ትክክለኛ ሰው በትክክለኛ ቦታ ይቀጥላል ...አባቴ የኔ ጀግና ሰው ጌታ ይርዳህ እወዳለሁ !!

ወንጌል Tube

15 Nov, 16:42


የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ላለፉት 52 ዓመታት በላው ኢትዮጲያ 351 አጥቢያ ቤተክርስቲያን የተከለች ሲሆን በሳውዝ አፍሪካም ከ 9 አጥቢያዎች በላይ ያሏት በመንፈሳዊ አገልግሎት እና በማህበራዊ አገልግሎት በጎ አድራጎት ስራዎችን ስትሰራ የቆየች እየሰራች ያለችም ቤተክርስቲያን ናት::
ከ 2002 ዓ.ም ጀምሮ ስንገለገልበት የነበረው በመካኒሳ አካባቢ የሚገኘው የፌይዝ ባይብል ኢንተርናሽናል ቸርች ሚራክል ቻፕል የማምለኪያ አዳራሽ በእድሳት እያለ ከ10,000,000 ( አስር ሚልዮን ) ብር በላይ ወጪ ተደርጎበት በመጠናቀቅ ላይ ሳለ ጥቅምት 26/2017 ማክሰኞ ለሊት ሙሉ በሙሉ የመደርመስ አደጋ የደረሰበት ሲሆን ከ27,000,000(ሃያ ሰባት ሚልዮን ብር) በላይ ውድመት ደርሶበታል ፡፡
በመሆኑም በዋናነት የእግዚአብሔር ቤተመደስ የሆነው የሰው ልጆች ወይም ቅዱሳን ላይ
ምንም አይነት ጉዳት ባለመድረሱ የእግዚአብሔን መልካምነት ያየንበት እና እግዚአብሔርን አመስግነናል::
ቅደሳን ለጊዜው ድንኳን በመከራየት ጌታን በማምለክ የቤተክርስቲያኒቱ መደበኛ ፕሮግራሞች ቀጥለዋል::
የመልሶ ግንባታ ስራ ቅድመ ዝግጅቶች የተጠናቀቁ ሲሆን ለግንባታውም ወደ 106 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል ::
ስለዚህም የተወደዳችሁ ቅዱሳን በመልሶ ግንባታ ላይ የበኩላችሁን አስተዋፅኦ በማድረግ በልግስና እና በደስታ ፣በገንዘብ በማገዝ የበረከቱ ተካፋይ እንድትሆኑ እንጠይቃለን ፡፡
ይህች አጥቢያ ቤተክርስቲያን ለብዙ አጥቢያዎች መተከል ለብዙ የምድራችን አገልጋዮች መነሳት ለብዙ ዘማሪያን መነሳት እና ማደግ ለምድራችን ብሎም በዓለም ባለት ላይ ሁሉ መልካም መንፈሳዊ ተፅዕኖ የፈጠረች ብዙዎች ወደ እግዚአብሔር መንግስት እንዲፈልሱ የተጠቀመባት የበረከት ቤት ነች ፡፡

ይህ አገልግሎት ይቀጥላል፡፡

ኢየሱስ ጌታ ነው!

1000486915386 Cbe Bank
013521026278100 Awash Bank
69112714 Abyssinia Bank
2600350021102 Berhan Bank
Faith Bible International Church

https://gofund.me/c0f4c92e

ወንጌል Tube

13 Nov, 16:20


#አርፈዋል...
በኢትዮጵያ የወንጌል አገልግሎት ቀዳሚ ከሆኑት የወንጌል አባቶች መካከል አንዱ እና ምሳሌ የሆኑት፤ በእግር እና በእንስሳት ኋላ ላይም በትራንስፖርት እገዛ እየተጓዙ (አንዳንዱን ከ100 ኪ/ሜ በላይ) ከ1200 በላይ አጥቢያዎችን የተከሉት ሐዋርያ ዳዊት ባዩ ዛሬ ወደሚወዱት እና ወዳገለገሉት ጌታ ሄደዋል።

"የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።" ዘኅ 23፥10

ለቤተሰባቸው ሁሉ በሚወዱት እና ባገለገሉት መንፈስ ቅዱስ መፅናናት ይሁን።

አብይ ታደለ (ኪያ)

ወንጌል Tube

13 Nov, 04:41


#23_ዝማሬዎች_በአንድ_አልበም 🙏🥰
ዘማሪ ፓስተር እንዳለ ወልደጊዮርጊስ ይዞ እየመጣ ነው ።
#ሕዳር_21 ይመረቃል ብሏችኃል !

ወንጌል Tube

12 Nov, 18:07


የቆዩ የቴሌግራም ግሩፖችን እየገዛን ነው

ማንኛውም አይነት የቴሌግራም ግሩፕ ካላቹ  በተመጣጣኝ ዋጋ እንገዛለን።
የmember ማነስ ችግር የለውም

@Ya_man06 👈 inbox Us

ወንጌል Tube

12 Nov, 13:19


የዘማሪት ሐና ተክሌ መልዕክት ነዉ፦

ቆጠርከኝ..

ከኔ መልካም ነገር ካገኛችሁ
የአምላኬን ምሕረት ብቻ ተመልከቱ!!

'ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤'
1ኛ ጢሞቴዎስ 1:12

ባዶነታችሁን በሙላት አለመቻላችሁን በመቻል ቀይሮ
ምንም የጎደላችሁ እስካይመስል ድረስ ሙሉ አድርጎ የሚያቆማችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ስሙ ይክበር!
ታናሽነቴንና አለመብቃቴን ሳይንቅ ለስሙ ክብር እንድቀኝ የወደደውን አምላኬን ሳስብ እደነቃለሁ!አገልጋይነቴ ለኔ ብዙ ትርጉም አለው!ስለበቃው ሳይሆን ትበቂያለሽ ብሎ ታማኝ አድርጎ በቆጠረኝ እስከዚህች ሰዓት በፀጋው አለሁ! በወደድኩት መንገድ ሳይሆን በወደደው መንገድ በምህረቱና በፍቅሩ ብዛት ሕይወቴን እየመራ ዛሬን ደርሻለሁ!
ከኔ መልካም ነገር ካገኛችሁ የአምላኬን ምሕረት ብቻ ተመልከቱ! እርሱ ከወደደ ማንንም ምንም ማድረግ ይችላል ለቁምነገር የማይጠበቀውን ሰው ቁምነገረኛ ያደርጋል..ብቻ እርሱ ይፈልግ ማንንም የወደደው ጋር ይመድባል ያደርሳል!
እኔ ምስክር ነኝ የማልሆነውን ነው እንዲህ አድርጎ ያቆመኝ ያለእርሱም ምንም ነኝ ምንም የሌለኝ!!ተቆጥሬ እንጂ በቅቼ አይደለም በcriteria ቢሆን አላሟላም!ተጠርቼ ነው ተቆጥሬ!ብቃቴ እግዚአብሔር ብቻ ነውና ክብር ሁሉ ለእርሱ ይሁን በጥበቡ አገልጋዩ ላደረገኝ!

ቆጠርከኝ የእውነት ታሪኬ ነው አመስግኑልኝ!

የአለምን ጥበብ ልታሳፍር ሞኝን ነገር የመረጥህ
ብርቱውንም ደግሞ ልታሳፍር ደካማውን የፈለግህ
ይገርመኛል አሰራርህ
የኔን ሕይወት እንዲህ ያደረግህ
ቆጠርከኝ ታማኝ አድርገህ
የሾምከኝ ለቤትህ አምነህ
ምን አይነት አምላክ ነህ አንተስ
ሰው ሰውን እንደሚያይ መቼ ታያለህ

Hanna 🥰🥹

ወንጌል Tube

12 Nov, 12:32


ወንጌል Tube pinned «የቆየ telegram group ያላችሁ እየገዛን ነው አውሩኝ member ብዛት ችግር የለም @Ene_negn56»

ወንጌል Tube

12 Nov, 12:30


የቆየ telegram group ያላችሁ እየገዛን ነው አውሩኝ member ብዛት ችግር የለም

@Ene_negn56

ወንጌል Tube

07 Nov, 01:24


መሥዋዕት ሙሉ አልበም ተለቋል!እግዚአብሔር ይመስገን!
https://youtube.com/@hannatekleofficial?si=sy_KvMQ29iIBPPKT

ወንጌል Tube

06 Nov, 18:39


"መስዋዕት" ቁጥር 4 አልበም ዛሬ 4:30 ላይ ይለቀቃል ይጠብቁን!
https://youtube.com/@hannatekleofficial?si=ElVfvhcNQnRZGb06

ምስጋና
አሁንም ከማንም በፊት ለዚህ እድል ያበቃኝን መከናወንን የሰጠኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ!
በመቀጠል የአልበሙን ሙሉ project በመያዝና manage በማድረግ፥ አልበሙ ውስጥ ካሉት 17 መዝሙሮች ስምንቱን በማቀናበር ፤የአብዛኛውን ዝማሬ ቅጂና እጀባ በማድረግ ከመጀመሪያ ጀምሮ ለዚህ ስራ መሳካት ብዙ የደከመውን የተባረከው ወንድሜን ሙዚቀኛ ፍቃዱ ቤጤላን ከውድ ባለቤቱ ራሔል እልፍዬስ ጋር በጣም ማመስገን እፈልጋለሁ።ስላሳያችሁኝ ፍቅርና የበዛ እንክብካቤ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ማለት እፈልጋለሁ ቤተሰቦቼ!

የተባረክ ወንድሜ ንፁህ ይልማ ከጅማሬዬ (ከቁጥር 1 አልበም) ጀምረህ እስካሁን ድረስ በአገልግሎቴ እንደቤተሰብ አብረኸኝ ስላለህ በጣም አመሰግናለሁ! ውለታህን እግዚአብሔር ይክፈልልኝ!
የSound ባለሞያ የሆነው ንፁህ ይልማ ይህንን አልበም ጨምሮ በ3 አልበሞቼና በየጊዜው በሚለቀቁት አብዛኞቹ መዝሙሮች ላይ በMixing and Mastering ብዙ ተሳትፎ አድርጓል።በዚህኛውም ዙር ለዚህ ስራ መሳካት ብዙ ደክሟል!እርሱን እና የተባረከችውን ውድ ባለቤቱን ምህረት ተረፈን ከስራው ባለፈ አሁንም ስላሳዩኝ ፍቅር ማመስገን እፈልጋለሁ ተባረኩ እላለሁ!
ይህንን አልበም በማቀናበር 7 የተባረኩና የተወደዱ ሙዚቀኞች የተሳተፉ ሲሆን ከላይ እንደጠቀስኩት
ሙዚቀኛ ፍቃዱ ቤጤላ 8
ሙዚቀኛ መስፍን ዴንሳ 2
ሙዚቀኛ በረከት ጃንጄ 1
ሙዚቀኛ ናሆም መሰለ 1
ሙዚቀኛ ሮቤራ መኮንን 1
ሙዚቀኛ ክብረአብ ምትኩ 1
ሙዚቀኛ አቤኔዘር ዳዊት 3 መዝሙሮችን አቀናብረዋል!ሁላችሁንም በዚህ የስራ ሂደት ውስጥ ስላሳያችሁኝ አክብሮት እጅግ በጣም አመሰግናለሁ!
በዚህ ስራ በlive instrument የተሳተፋችሁ ሙዚቀኞች
Lead guitarists:-
ምህረትአብ በራሳ
ናትናኤል ደሳለኝ
አቤኔዘር አለማየሁ
አቤኔዘር ዳዊት
Bass Guitarists:-
ዳዊት ኩመራ(Didi)
ብሩክ ዬሀንስ(candy)
በረከት አበበ
Drum-እንዳልካቸው ጌታቸው
Kirar-ዘካርያስ ታደሰ እና አቤኔዘር ዳዊት
Saxophone-ናትናኤል ገብረፃድቅ
እንዲሁም በድመፅ እጀባ አብራችሁኝ የነበራችሁትን ወዳጆቼን ዘማሪ ያዕቆብ ሚልዬን ፣ማልዳ ቢቂላ፣ምህረት ተረፈ፣ዘካሪያስ ታደሰ፣ሱራፌል ኃይለማርያም እና ሳሙኤል ዬሀንስ
እንዲሁም በዚህ ስራ ላይ በGraphics Design የተሳተፈውን አስተዋይ አሰፉንና በፀሎትና በምክር አብራችሁኝ የነበራችሁትን ሁላችሁንም አመሰግናለሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ !
ወድ ባለቤቴ ላንተ ቃል የለኝም አብሮነትህ ግልፅ ነው ኑርልኝ መዝሙሬን ቀድማችሁ በመስማት በስሜታችሁ ሞራል ስትሰጡኝ የነበራችሁ መጀመሪያዎቹ ሰሚዎች የሆናችሁት ልጆቼ እደጉልኝ ቡሩክ ሁኑልኝ እወዳችኃለሁ!
የእግዚአብሔር ሕዝብ ለሆናችሁ ለእናንተ ወዳጆቼ በየጊዜው ስለምታሳዩኝ የበዛ ፍቅር ጌታዬን እባርካለሁ ተባረኩ በጣም አመሰግናችኃለሁ!
"መሥዋእት"ምስጋናዬ ነው አብራችሁኝ ልዑሉን አመስግኑልኝ!!
እወዳችኃለሁ!
Hana tekile

ወንጌል Tube

06 Nov, 05:18


የዘማሪ በረከት ተስፋዬ መልዕክት፦

እስቲ በGCA ፌሎ ያላችሁን ትዝታ አጋሩኝ..

ዛሬ ዶክመንቶቼን ለሆነ ጉዳይ እየበረበርኩ የዘጠነኛ ክፍል መታወቂያዬን አገኘሁትና ብዙ ነገር ትዝ አለኝ። ከ9 እስከ 12 የተማርኩት አብዩት ቅርስ በቀድሞ ስሙ GCA በሚባለዉ ትምህርት ቤት ዉስጥ ነዉ። ይሄ ትምህርት ቤት እነ ተስፋዬ ጫላ እነ ሳሚ ተስፋሚካኤል እና ብዙ አንጋፋ የጌታ ልጆች የወጡበት ትምህርት ቤት ነዉ። እንደ ገባዉ የተማሪዎች ፌሎሺፕ ተቀበሉኝ። ከትምህርት ቤቱ አጠገብ ፀጋ ቃለ ህይወት የምትባል የምንሰበሰብባትና የምንፀልይባት ቤተ ክርስቲያን ነበረች። ክፉ ጓደኞች እንዳያጠምዱኝ እንዲሁም ወደ አለም ተስቤ ሰይጣን እንዳያገኘኝ ፀጋ ቃለህይወት በመሰብሰባችን ከተጠቀሙ ሰዎች አንዱ ነኝ። አስታዉሳለዉ በፈለግነዉ ሰአት እንገባለን የሙዚቃ መሳሪያ ይፈቅዱልን ነበር። እጅግ ደግ ቤተ ክርስቲያን ናት ጌታ ይባርካቸዉ። እስቲ በGCA ፌሎ ያላችሁን ትዝታ አጋሩኝ እወዳችኋለዉ

ወንጌል Tube

05 Nov, 05:05


በቪክትሪ ፋሚሊ ቤተክርስቲያን - VFC- Church ከዛሬ ጀምሮ ጥቅምት 26 ጀምሮ በተዘጋጀው ልዩ የአምልኮ እና የፀሎት አገልግሎት ላይ በመገኝት አብረውን እግዚአብሔር ያመልኩ ዘንድ ጋብዘነዎታል።

ዘወትር ማክሰኞ ከ11፤30 - 2፤00 ሰዐት ድርስ

አድራሻችን መካኒሳ ቆሬ

ይህን የጎግል ካርታ መስፈንጠሪያን በመጫን አድራሻችንን ያገኙታል::

https://maps.app.goo.gl/19u2B77Sf4299KG6A?g_st=com.google.maps.preview.copy

ወንጌል Tube

04 Nov, 20:43


#ስዊዘርላንድ በህግ ዜጎቿን አስራት (church tax) እንደምታስከፍል ያውቃሉ?


ላለፉት 200 ዓመታት በላይ ጦርነትን የማታውቅ የአውሮፓ እጅግ ሀብታሟና ሰላማዊቷ የመስቀል ሀገር ብዙ ድንቅ ነገሮች አሏት::

የእግዚአብሔር ቃል አትስረቅ፣ አታመንዝር፣ አትግደል፣ በሀሰት አትመስክር....ይላል ብለህ ገና ስትጀምር ሃይማኖትና መንግስት የተለያየ ነው ብሎ ያልገባውን የምቀበጣጥር ትውልድ ይህን ስያይ ምን ይሰማው ይሁን?

1ኛ: ሰንደቃላማዋ ምንም ያልተጨመረበት መስቀል ስሆን የህገ መንግስቷ የመጀመርያው መግቢያ ስንኝ 'In the Name of God Almighty!'(በሃያሉ እግዚአብሔር ስም) ብሎ የምጀምር ሀገር ነች::
2ኛ: በሀገርቱ የምሰሩ ዜጎችም ይሁኑ ከውጭ ሀገር የመጡ ሰራተኞች ግብር ስከፍሉ የቤተክርቲያን ግብር (Church tax) የመክፈል ግዴታ አለባቸው:: ለምን ብባል በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ለሚያገለግሉ አገልጋዮች አስፈላጊውንና በቂ ደመወዝ ለመክፈል:: አፍህን ይዘህ ዝም ከማለት ውጭ ምን ልታደርግ ትችላለህ🙈
መስቀሉን ሰንደቅአላማው አድርጎ በጦርነት የምናጥ፣ በቅኝ ግዛት የተጨቆነ፣ በድህነት የምማቅቅ፣ በአንባገነኖች የሚረገጥ ስርዓተ መንግስት ምድር ላይ ፈልጌ አጣሁኝ::

ወንጌል Tube

03 Nov, 14:09


መሥዋዕት!

ስለሁሉ እግዚአብሔር ይመስገን! መሥዋዕት ቁጥር 4 አልበም በዚህ ሳምንት ይለቀቃል!እስከዚያው ከአልበሙ ውስጥ"በማለዳ"በተሰኘው አዲስ ዝማሬ ተባረኩ!

https://youtu.be/binGZ6i8-yI?si=kcGoXx-QIYBNh9Hz

https://youtube.com/@hannatekleofficial?si=Vu4U3C8z-QtxX1jV

ወንጌል Tube

02 Nov, 17:08


☞︎︎︎ነገ ፏ ብለሽ ወደ ቸርች...💇‍♀
☞︎︎︎ነገ ፏ ብለህ ወደ ቸርች...💇
☞︎︎︎ነገ ፏ ብዬ ወደ ቸርች...🙍
☞︎︎︎ነገ ፏ ብለን ወደ ቸርች...👨‍👩‍👦‍👦

“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሄድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።”
መዝሙር 122፥1

☞︎︎︎ወደ እግዚአብሔር ቤት በመሄዳችን
ደስ ይለናል🤩
☞︎︎︎መጽሀፍ ቅዱስ እና ማስታወሻ መያዣ እንዳይረሳ👍

ወንጌል Tube

29 Oct, 20:11


በአምላክ እግር ስር በጸሎት የሚቆዩ ሰዎች ምንኛ ብሩካንና የታደሉ ናቸው በጌታ😥🙏

እናንተዬ ይሄ ነገራችሁ አይወሰድበችሁ በኢየሱስ ስም🙏🙏

ወንጌል Tube

29 Oct, 06:03


እስኪ በሰላም ላሳደረን እግዚአብሔር እጃችንን ለምስጋና እንዘርጋ🙏

ወንጌል Tube

28 Oct, 10:58


የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ከተቀበሉት ከወንጌላዊት ሉተራን ቤተክርስቲያን በአሜሪካ (ELCA)፣ እና የስዊድን ቤተክርስቲያን (Church of Sweden) ጋር የጀመረችውን የግንኙነት ሂደት አስመልክቶ የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ማ/ም የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን በግልፅ ከተቀበሉ ከቀድሞ አጋሮቿ፣ የወንጌላዊት ሉተራዊት ቤተክርስቲያን በአሜሪካ (ELCA)፣ እና የስዊድን ቤተክርስቲያን (Church of Sweden) ጋር ማንኛውንም የመንፈሳዊ አገልግሎት እና የልማት ሥራ ግንኙነትን ማቋረጧ በ6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ካውንስል ላይ መወሰኑ ይታወሳል።

ነገር ግን በ8ኛው ጉባኤ የ“Rescue Mission" የመታደግ ተልዕኮ እንዲካሄድ የተወሰነ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከተወሰነበት ዓላማ ውጭ ውሳኔውን ሽፋን በማድረግ ከላይ ከተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ጋር የተለያዩ ግንኙነቶችን እያደረገች መሆኗ እየተስተዋለ ይገኛል ሲሉ በመግለጫቸው ገልጿል። በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ዜሮ ዜሮ ሙዚየም የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ባዘጋጀችው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ከላይ የተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች በክብር እንግድነት ተጋብዘዉ መገኘታቸዉ አንድ ማሳያ ነው ብለዋል።

ስለዚህ ይህ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያናችን ምእመናን እና መሪዎች ዘንድ ትልቅ ስጋት ፈጥሯል፡፡ በተጨማሪም በአማኞች መንፈሳዊ አገልግሎት እና አንድነት ላይ እንዲሁም በእምነታችን መስረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንደሚያሳድር እሙን ነው ሲሉ በመግለጫው ጠቅሷል።

የቢፍቱ ቦሌ መካነ ኢየሱስ ማህበረ ምዕመናን አመራሮች በጥቅምት 19 ቀን 2024 ልዩ ስብሰባ በማካሄድ እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ጥቅምት 20 ቀን 2024 ጉባኤውን በማሳወቅ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

1. ከላይ ከተጠቀሱት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ በኋላ ከእነዚህ እግዚአብሔርን ቃል የሚፃረር ተግባር ጋር የሚተባበሩትን እና እግዚአብሔር ላይ ካመፁት ሰዎች ጋር የመታደግ ተልዕኮ (Rescue Mission) በሚል የሚደረገውን ማንኛውንም ህብረት የመፍጠር እንቅስቃሴ አጥብቀን እንቃወማለን!

2. ቀደም ሲል በ6ኛ፣ 7ኛ እና 8ኛ ካውንስሎች የተላለፉ ውሳኔዎች ያለ ምንም ትርጓሜ እንዲከበሩ!

3. የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ከፍተኛ አመራሮች ከወንጌላዊት ሉተራዊት ቤተክርስቲያን በአሜሪካ (ELCA)፣ እና የስዊድን ቤተክርስቲያን (Church of Sweden) ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት ከማድረግ የማይቆጠቡ ከሆነ አመራራቸውንና የትኛውንም አገልግሎታቸዉን ፈጽሞ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

4. በአጠቃላይ ከግብረ ስዶማውያንን ጋር የትኛውንም ዓይነት ትሥሥርም ሆነ ግንኙነት ከሚያደርጉ ጋር ህብረት የማናደርግ እና የማንስራ ማሆነን አቋማችንን አፅንኦት እንገልፃለን፡፡

ወንጌል Tube

25 Oct, 18:32


በዚህ ቻናል በክርስቶስ አምኖ የዳነ 40 ሰው ብቻ ነው እንደ  🙄🙄

ወንጌል Tube

23 Oct, 17:55


ቆይ ግን🤔 እዚህ ቻናል ላይ በክርስቶስ አምኖ የዳነ ምን ያህል ሰው አለ?

🥰👈እችን react ያሳየኝ

ወንጌል Tube

23 Oct, 17:35


#ወደጌታ_ሄደ😭
ይህ የተወደደ ወንድም አገልጋይ ኤፍሬም ይባላል። በዱባይ ምድር የሚኖሩ በደንብ ያውቁታል። አገልጋዮችን የሚቀበል ፣ ለእግዚአብሔር ሰዎች ብዙ የሚሆን፣ ጌታን አብዝቶ የሚወድና በመሰጠት የሚያገለግል እንዲሁም በስራው ደግሞ ጎበዝ ነጋዴ የሆነ ወንድም ነበር። በዛሬው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ተለይቶ ወደጌታ ሄዷል። የሄደው ወደአባቱ ቢሆንም የሚወዱት ሰው በስጋ ሲለይ ያሳዝናልና ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ጓደኞቹ በሙሉ መፅናናትን እንመኛለን...

ወንጌል Tube

12 Oct, 16:35


#ዝምታ_ክብር_ያመጣል 💪 #ስራህ_ይናገር 🥰
( ✍️ አቤል ደመላሽ )
ለረጅም ጊዜያት ለሕይወቴ የጠቀመኝ አንድ ነገር ቢኖር በዝምታ ስራ በዝምታ ኑር የሚለው መርሄ ነው ። ለብዙ ሰዎች አንተነትህን ብቻ እየገለጥክ እና እኔ ይህ ነኝ እንዲህ አለኝ በዚህ ወጣሁ በዚህ ገባው የምትል ከሆነ እመነኝ ምንም ያሳካኸው ነገር የለም ማለት ነው...ለዚህ ነው አልሸጥ እንዳለ ዕቃ በሄድክበት የሚያስለፈልፍህ...ሁሌ ዝም በል በዝምታም ስራ አንተ ስላንተ አትናገር...ሁሌም ኑሮህን ብቻ ቀጥል...ዓላማህን ኑር...ሰዎች ጋር ለመታየት አትጣር...እመነኝ ያኔ ነፍስህ ደስተኛ ትሆናለች ። እኛ የምንፈልገው ድል ማድረግን ከሆነ ለምን እወቁልኝ እናበዛለን ። ለብዙ ሰዎች ግር የሚላቸው ነገር የኔ የዝምታ ሕይወት ነው ። ምንም መንገድን ብሄድ በዝምታ እጓዛለሁ...በዚያ ሲገምቱኝ በዚህ ነኝ...ምንም መንገዴ እወቁልኝ የለውም...ስለዚህ የኔ ድል በጊዜው አፍ አውጥቶ ያወራል ። ለዚህ ነው የሚያውቁህ ሰዎች እንዲገምቱህ ዕድል ስጣቸው በሕይወትህ ግን አስደንግጣቸው የሚባለው...ለዓመታት የጠቀመኝ ነገር ሰዎች እርምጃዬን እንጂ ሩጫዬን አለማወቃቸው ነው ። ዛሬም እላለሁ...በዝምታ ስራ...በዝምታ ኑር...ተራ አስተሳሰብ ካላቸው ጋር ወርደህ አትመካከር...እንደ ልጅ ከሚያስቡ የወተት ዘመን ላይ ካሉ ሰዎች ጋር አትወያይ...መልስም አትሰጣጥ...ወርደው ከሚያወርዱ ጋር አትዋል...ስትወድቅ ትተውክ ይሄዳሉና ጌታ ምን ይላል እንጂ ሰው ምን ይለኛል አትበል...በዝምታዬ ውስጥ ወዳጄን..ራስህን.ጠላቴን እና ሸንጋዬን ለይቻለሁ ግን የኔ መንገድ ለእነርሱ ሩቅ ነው... እና ስጠቀልለው የምለው ቢኖር እግዚአብሔር የሚልህን ስማ...እመነኝ ይሄንን ስታደርግ የእግዚአብሔር ሞገስ እና ድል አድራጊ ሕይወት ያንተ ይሆናል ።
#እግዚአብሔር_ይባርካችሁ 🙏🥰
#ጥበብ_እና_ማስተዋል_ይብዛልን

ወንጌል Tube

09 Oct, 10:11


ከተገለጠው ድርጊታችን በላይ የልብ አካሄዳችን የነገ ፍሬያችንን ይወስናል!የተገለጠው ድርጊታችን ለሰው ይታያል!
ልባችን ግን በእግዚአብሔር ዘንድ ታይቶ ይመዘናል!
ምንም ነገር ስናደርግ የምናደርግበት መንፈስ ከድርጊታችን በላይ በእግዚአብሔር ዘንድ ዋጋ አለው!
ያልተኖረ የታይታ ብቻ ገፅታ ምን በሰው ዘንድ ጎሽ ቢያሰኝና ቢገነባ ጊዜ ቆጥሮ ባዶነቱ ይገለጣል ከትወና ሕይወት አያልፍም!እግዚአብሔር እያዘነ የምንገነባው ገፅታ የትም አያደርሰንም!
በልባችን እንለወጥ!ብልህ እንጂ ብልጣብልጥ አንሁን!
ሳይረፍድ ብዙ ሳንከስር የእውነት እንሁን! የእውነት እንኑር! አንሸነጋገል! የእውነት ልብና ቅንነት ገፅታችን ይሁን!እርሱ ጎሽ ይበለን ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው!

በእውነት መንፈስ ተባረኩ!

#singer_hana_tekile

ወንጌል Tube

04 Oct, 19:35


#ተለቋል...
26 ትራኮች ያሉት የዘማሪት አስቴር አበበ ሃሌሉያ አልበም በ apple music ,በ Spotify ,በ i tunes እና በተለያዩ የonline ገበያዎች ተለቋል።
youtube ላይ ስለሌለ ለጊዜው በውጭ ያሉ ወገኖች በኢትዮጵያ ያለነውን እንቁልልጭ እያሉን ነው😂
ከ Apple music የአስቴርን አልበም መግዛት የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ተጠቀሙ።
https://music.apple.com/ca/album/hallelujah/1771682841

ወንጌል Tube

04 Oct, 12:09


ወንጌል Tube pinned «ከመንፈሳዊ ነገሮች ጎን ለጎን አርፍ online ስራ መስራት የምትፈልጉ በጣም አስተማማኝ ስራ ነው 👇👇 https://gracesfarm.com/login/register?inviteCode=597d35ec»

ወንጌል Tube

04 Oct, 11:49


እነሆ መልካም ልደት እያከበርን ነው።

የተወደድክ ድንቅ ወንድሜ መጋቢ ተኬ ለማይቆጠረው እድሜህ መልካም ልደት እያልኩ አሁንም ከቁጥር በላይ በሆነ ክብር ይባርክህ ።
#tekeste_getnet

ወንጌል Tube

02 Oct, 06:48


#የተመሳሳይ_ፆታ_ጋብቻን_ፈፅሞ_አንቀበልም_አንባርክም...
ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በአንዳንድ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተሰጠ መግለጫ፤

መስከረም 21-2017 ዓ/ም
በስመ አብ፤ በወልድ፤ በመንፈስ ቅዱስ ስም አንድ አምላክ፤ አሜን!
በጌታ የተወደዳችሁ በአገር ውስጥና ከአገር ውጭ የምትገኙ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ምዕመናን፤ በያላችሁበት ሁሉ የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ፡፡
የዚህ መግለጫ ዓላማ ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ከሚባርኩና ግብረ ሰዶማዊያንን ለመንፈሳዊ አገልግሎት ከሚጠሩና ከሚያሰማሩ አብያተ ክርስቲያናት ጋር የአጋርነት ስምምነት ፈርማለች ወይም ልትፈርም ነው፤ በሚል እየተሰራጨ ያለው ወሬ ትክክለኛ አለመሆኑን ለቤተ ክርስቲያኒቱ ምዕመናንና አገልጋዮች ለማስገንዘብ ነው፡፡
እንደሚታወሰው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በ19ኛው ዓብይ ጉባኤ ከሲዊድን ቤተ ክርስቲያንና በሰሜን አሜሪካ ከምትገኘው ወንጌላዊት ሉተራን ቤተ ክርስቲያን ጋር የነበራትን የአጋርነት ግንኙነት እንዲቋረጥ ወስኖ ነበር፡፡
ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ምክክር የተጀመረው በ1998 ዓ.ም. በይርጋለም ከተማ በተካሄደው 2ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል ስብሰባ ቢሆንም፤ ሥነ መለኮታዊ አቋም ተይዞ ውሳኔ መስጠት የተጀመረው በግምቢ ከተማ በተካሄደው 6ኛው ካውንስል ስብሰባ ነበር፡፡ በዚህ ካውንስል ቤተ ክርስቲያኒቱ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን መባረክንና ግብረሰዶማዊያንን ወደ ቅስና አገልግሎት መጥራትን በጽኑ በመቃወም፤ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ከሚፈጽሙና ግብረሰዶማዊያንን ወደ ቅስና ለመጥራት ውሳኔ ካደረጉት ጋር ያላትን ግንኙነት ለማቋረጥ የምትገደድ መሆኗን ይፋ አድርጋለች።
ይሁን እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከእነዚህ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ከነበራት ታሪካዊ ግንኙነት  የተነሳ፤ ይህንን ውሳኔአቸውን በማጤን እንዲመለሱና ምላሻቸውን በአንድ ዓመት  ውስጥ እንዲያሳውቁ ጥሪ ብታደርግም የአብያተ ክርስቲያናቱ ምላሽ አዎንታዊ  አልነበረም። ይኸው ጉዳይ ለ7ኛው ካውንስል ሪፖርት ተደርጎ ቀደም ሲል የተወሰነው ውሳኔ ተፈጻሚነት እንዲያገኝ አቅጣጫ ተቀመጠ፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ 8ኛው ካውንስል ከላይ ስማቸው የተጠቀሰውን ብቻ ሳይሆን፤ ተመሳሳይ አቋም የያዙትን አብያተ ክርስቲያናት ጭምር ታሳቢ ያደረገ የትድግና ሚሲዮናዊነት (Rescue Mission) አገልግሎት እንዲታቀድና ለዚህም የአፈጻጸም መመሪያ እንዲዘጋጅ ወሰነ፡፡ በየካውንስሉ ስብሰባዎች የተላለፉት ውሳኔዎች የዓብይ ጉባዔውን ይሁንታ ማግኘት ስለነበረባቸው፤ 19ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓብይ ጉባዔ በ6ኛው፣ በ7ኛው እና በ8ኛው ካውንስል ስብሰባዎች የተላለፉትን ውሳኔዎች ተቀብሎ በማጽደቅ ቤተ ክርስቲያኒቱ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ከተቀበሉትና ግብረሰዶማዊያንን ከሚያቀስሱ አብያተ ክርስቲያናት ጋር የነበራት የአጋርነት ግንኙነት እንዲቋረጥ ወሰነ፡፡
ከላይ የተጠቀሰው በ8ኛ ካውንስል የተወሰነው የትድግና ሚሲዮናዊነት አገልግሎትን አስመልክቶ ለተላለፈው ውሳኔ የአፈጻጸም መመሪያ ባለመዘጋጀቱ፤ 19ኛው የቤተ ክርስቲያኒቱ ካውንስል የ21ኛውን የቤተ ክርስቲያኒቱ ዓብይ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት በማድረግ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሥነ መለኮታዊ አቋም በምንም መልኩ ሳይሸራረፍ ከእውነት የሳቱትን ለመመለስና በእምነት ያሉትን በደቀ መዝሙርነት ሕይወት ለማነቃቃትና ለማጽናት የሚያስችል ስልት ቀይሶ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ እንዲያቀርብ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሚሲዮንና ቲኦሎጂ ቦርድ መራ፡፡ 
የቤተ ክርስቲያኒቱ ሚሲዮንና ቲኦሎጊ ቦርድም ሥራውን አጠናቅቆ ለሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሪፖርቱን አቅርቦ ማስተካከያዎች ታክለውበት እንዲዳብር ባዘዘው መሰረት፤ ይኸው ለቀጣይ ውሳኔ ሰጭ አካል የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ይህም ማለት ሂደቱ ገና ያልተጠናቀቀና የመጨረሻ ውሳኔ ያልተሰጠበት እንደመሆኑ፤ የትድግና ሚሲዮናዊነት አገልግሎትን የሚያስጀምር እርምጃ እስካሁን አልተወሰደም፤ በዚህም አቅጣጫ የተደረገ አንዳች ስምምነት የለም፡፡
ስለሆነም ለምዕመናኖቻችና በየደረጃው ለሚገኙ አገልጋዮች የሚከተለውን መልዕክት አበክረን እናስተላልፋለን፡-
1. ቤተ ክርስቲያኒቱ ማናቸውንም ዓይነት ግብረሰዶማዊ ግንኙነት አጥብቃ ትቃወማለች፤ እንደዚሁም ግብረሰዶማዊነት በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮ መሠረት ግልጽ የሆነ የድፍረት ኃጢአት እንደሆነ ስለምታምን ይህንን ኃጢአት ከሚፈጽሙ ጋር አትተባበርም፤
2. እግዚአብሔር በመጀመሪያ ጋብቻን በአንድ ተፈጥሮአዊ ወንድና በአንዲት ተፈጥሮአዊ ሴት መካከል ከመሠረተባቸው ምክንያቶች አንዱ የሆነውን የሰው ልጆች ትክክለኛ ወሲባዊ ግንኙነትንና የሥነ-ተዋልዶን ሥርዓት የሚያፋልስና በሙሽራው ክርስቶስና በሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለውን ምሳሌያዊ ግንኙነት የሚያፋልስ በመሆኑ ቤተ ክርስቲያኒቱ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን ትቃወማለች፡፡
3. ቤተ ክርስቲያኒቱ ግብረሰዶማውያንን ለቃሉና ለቅዱሳት ምስጢራት አገልግሎት መጥራትንም ሆነ ማቅሰስን አጥብቃ ትቃወማለች፤
4. ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁንም ሆነ ለወደፊት  የተመሳሳይ ፆታ  ጋብቻንና ግብረሰዶማውንን  ማቅሰስን በተመለከተ የተወሰኑትን ውሳኔዎች በሙሉ እንደተጠበቁና የማይሻሻሉ መሆናቸውን ታረጋግጣለች፤
5. ቤተ ክርስቲያኒቱ  ስማቸው ከተጠቀሰው ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ጋር ስምምነት ፈርማለች በማለት የሚናፈሰው ወሬ ፈጽሞ ከእውነት የራቀ መሆኑን መሆኑን እንገልጻለን፤
6. በዚህ ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ በማሰራጨት የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም የሚያጎድፉና አንድነቷን ለማናጋት  ከሚሰሩ ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ፣ምዕመናኖቻችን እንዲጠነቀቁ እናሳስባለን።
7. በመጨረሻም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ  ጥያቄ የሚኖራቸው ምዕመናኖቻችን ካሉ በማንኛውም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱ ማብራሪያ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን እናስታውቃለን፡፡

እግዚአብሔር ጸጋውንና ምህረቱን ያብዛልን።
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ
መስከረም 21 ቀን 2017 ዓ/ም

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!!!!!

ወንጌል Tube

02 Oct, 04:42


ከመንፈሳዊ ነገሮች ጎን ለጎን አርፍ online ስራ መስራት የምትፈልጉ በጣም አስተማማኝ ስራ ነው 👇👇


https://gracesfarm.com/login/register?inviteCode=597d35ec

ወንጌል Tube

01 Oct, 05:29


#ቀኑ_ደረሰ#Coming_Soon
#ዘማሪ_ይሳሐቅ_በቀለ#Yishak Bekele
#youtube_Subscribe_እያደረጋችው_ጠብቁ
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/@singeryishakb2022

ወንጌል Tube

24 Sep, 17:05


#እኔ_ከእህቴ_ጎን_ነኝ! በአገልግሎቷ ተባርኬያለው! ወዳጆች የምትችሉትን ሁሉ በማድረግ የፍቅር አብሮነታችንን እንድንገልጥ ጥሪ አቀርባለው! ይህን የአብሮነት ጥሪ አሁኑኑ ተቀላቀሉ! ሼር ማድረግም መርዳት ነውና ሼር አርጉት!

#ዘማሪት_የምስራች_በጠና_ታማለች 🥺
አስቸኳይ የእገዛና አብሮነት ጥሪ!
ለተወደደች እህታችን ዘማሪት የምስራች ስምዖን
1000203336997
Yemisrach Simon
Ethiopian commercial bank

1032492698329
Berhan bank
Mintiwab derese(enatua)

ወንጌል Tube

21 Sep, 19:32


family እኔ ምማርበት college ነው ምትማረው እንደማታሳፍሩን እርግጠኛ ነው screenshot inbox ላኩልኝ🙏

ወንጌል Tube

21 Sep, 19:29


አስቸኳይ የእርዳታ ጥሪ ለእህታችን ተማሪ ሜሮን ካፒታ ዋልጬ ለወገን ደራሽ ወገን ነውና እንርዳት መርዳት ባንችል እንኳን #share በማድረግ ደጋግ ኢትዮጵያን ዘንድ አድርሱልን

የእርዳታ ጥሪ‼️
..ይህቺ በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ተማሪ ሜሮን ካፒታ ዋልጬ ትባላለች የአርባምንጭ ከተማ ነዋሪ ስትሆን የሶስተኛ አመት የፋርማሲ ተማሪ ነበረች አሁን ላይ ግን የኩላሊት ታማሚ ሆና በአልጋ ላይ ትገኛለች። በአዲስአበባ ታዝማ የዉስጥ ደዌ የህክምና ማእከል ዉስጥ የምትገኝ ሲሆን ሁለቱም ኩላሊቶቿ መስራት ስላቆሙ በእጥበት ላይ ትገኛለች። እናም ይህ እጥበት ብቻ በቂ ባለመሆኑ ወደ ህንድ ሀገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ እንድታደርግ ተብላለች። ቤተሰቦቿም የተጠየቁትን ገንዘብ ማግኘት ባለመቻላቸው ለእርዳታ እጃቸዉን ዘርግተዋል እናንተም የተቻላችሁን እንድታደርጉ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን እህታችን ሜሮንን እናድናት።
ሰዉን ለመርዳት ሰዉ መሆን በቂ ነዉ።
CBE: 1000021582046/1000649803424
Dashen Bank: 5052031563011
Berhan Bank: 1030252633077
Abyssinia Bank: 203463642
Kapita Walche Mengesha & Alemnesh Wogayehu

ወንጌል Tube

14 Sep, 17:35


አንቀ*ውት፣አፍ*ነው፣ጭንቅላቱን መተው አስፓልት ላይ ጥለውት ሄዱ😭
(ሁላችሁም ሼር ሳታደርጉ እንዳታልፉ በእግዚአብሔር ፍቅር እጠይቃለሁ።)

ለአዲስ ዓመት ሊለቀው የነበረውን ብዙ የደከመበትን የሕፃናት የዝማሬ አልበም ሲሰራ አምሽቶ 3:00 አከባቢ ሲመለስ የተባበሩት አደባባይ አከባቢ በቪትዝ መኪና በመሆን 3 ሰዎች አንገቱን በማ*ነቅና በማ*ፈን እንዲሁም ጭንቅላቱን በመምታት ራሱን ከሳ*ተ በኋላ ለ Music Arrangement እንዲሁም ለ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን የ Macbook pro laptop እንዲሁም ስልኮቹን የሚኒስትሪ ማህተም እና ሰነዶቹን ብሎም በኪሱ የነበረውን ገንዘብ በሙሉ ከነቦርሳው በመ*ዝረፍ አስፓልት ዳር ጥለውት ሄደዋል።ጉዳትም ደርሶበታል።

ብዙዎች በዘነጉት የሕፃናት አገልግሎት ብዙ ሕፃናትን ለእግዚአብሔር መንግስት እያስነሳ የሚገኘው ወንድማችን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ብዙ ዋጋ የከፈለባቸውን ስራዎቹን አጥቷል። እርሱ ሰዎችን ፈፅሞ ማስጨነቅ ስለማይወድ በሕይወት ስለመትረፉ አመስግኑ ብሎ ዝም ቢልም ከፍተኛ ሕክምና ያስፈልገዋል።

በመሆኑም በዚህ ሰው አገልግሎት ትውልዱ በብዙ ተጠቅሟልና ታክሞ ያጣቸውን ብዙ እቃዎች አሟልቶ እንዲቀጥል በገንዘብም በፀሎትም አብረነው እንድንቆም በእግዚአብሔር ርህራሄ እጠይቃለሁ።

ታዛችሁ ከጎኑ የምትቆሙ እግዚአብሔር ይቁምላችሁ ከክፉም ይጠብቃችሁ።

TESFALEM MARKOS DOLEBO
1000108021652
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

(ሼር ማድረግም በጎነት ነው ቢያንስ ለ10 ሰው ሼር አድርጉለት!)

ወንጌል Tube

11 Sep, 20:00


እንኳን አደረሳችሁ!👋

➢2017 ዓመተ ምህረትን "ሀ" ብለን እንጀምራለን!....እግዚአብሔር በምህረቱ እዚህ ያደረሰን ክብር ለስሙ ይሁን!....አመቱን ደግሞ እስከ "ፐ" እግዚአብሔር በሰላም ያስጨርሰን!☺️

➢ሁሌም እንደምላችሁ ከ "ሀ" - "ፐ" እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ይታይብን!

   🤗መልካም በአል ይሁንላችሁ!🤗