Harari Education Bureau @hararieducationbureau Channel on Telegram

Harari Education Bureau

@hararieducationbureau


ይሄ ቴሌግራም የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የሚያስተላልፋቸው ትምህርታዊ መልዕክቶችና የተለያዩ መረጃዎች ለትምህርቱ ማህብረሰብና ለተማሪዎች በቀላሉ ተደረሽ እንዲሆን ለማስቻል ነው ፡፡

Harari Education Bureau (Amharic)

ቴሌግራም የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ በተመለሰባቸው ትምህርታዊ መልዕክቶችና መረጃዎች መብትን ለተማሪዎች እና ማህብረሰብ ስኬቃለን። ይሄ ቴሌግራም ፣ የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ፣ በተመለሰ በአማርኛ እና እንክብካቤ ያክሉ። ትምህርት እና የመምህርት እና መረጃዎችን ተደርገዋል፤ ለተማሪዎችና እና ለመህብረሰብና አመልካቾች የተማረ እንደሆነ መታየት ይችላሉ።

Harari Education Bureau

03 Oct, 16:27


ለሁሉም  2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች በሙሉ የ2015ዓ.ም የተመሪ ውጤት ሮስተር  አንድ ኮፒ እስከ 28/1/2016 ድረስ  ለት/ቢሮ ሙያ ፍቃድ ዳይሬክቶሬት እንድታሰገቡ እናሳውቃለን።

Harari Education Bureau

30 Sep, 13:35


ጽህፈት ቤቱ ለትምህርት አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

መስከረም 19/2016(ሀክትቢ)የኤረር ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ የትምህርት አመራሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ።

የኤረር ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት በወረዳው ለሚገኙ ትምህርት ቤት አመራሮች በእቅድ ዝግጅት እና ሪፖርት እንዲሁም የትምህርት ቤት አመራር ላይ ስልጠና መስጠት ጀመረ።

ጽህፈት ቤቱ ባዘጋጀው ስልጠና ላይ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ምክትል ርእሰ መምህራን እና ዩኒት ሊደሮች እየተሳተፉበት የሚገኝ ሲሆን ስልጠናው ለሁለት ቀናት የሚቀጥል መሆኑን የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
ትምህርት ጽህፈት ቤቱ ስልጠናውን እየሰጠ የሚገኘው ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን ነው።

Harari Education Bureau

29 Sep, 15:50


ዳይሬክተሩ ሽልማት ተበረከተላቸው ።

መስከረም 18/2016(ሀክትቢ)የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሁሴን በክልሉ ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሽልማት ተበረከተላቸው ።

የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ለመምህራን እና የትምህርት አመራሮች እየሰጠ በሚገኘው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ የቢሮው የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙክታር ሁሴን ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና የግዜ አጠቃቀም የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ሽልማቱ በክልሉ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርእሰ መምህራን እና ሱፐር ቫይዘሮች ያዘጋጁት መሆኑም ተመላክቷል።