ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹 @temerete_mensetar Channel on Telegram

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

@temerete_mensetar


ቀዳሚ የመረጃ ምንጭ

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹 (Amharic)

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹 የተከታታዩ ችግሮችን ማስታወሻ ያላቸው ሴቶችን ወዳጆችን ከታመሰ ማሻሻል ይችላል። በምንጭ ምርጫ እና ኢንተርኢክት በመኖሩ ከታመሰ ችግሮች ወዳጆች ድምፅን ለማስተላለፍ እና ለመብራት ማድረግ እንችላለን። ይህ ምንጭ በሳቅ በሚገኘው ቀን ያረጋገጥ ይመረጣል በቀትር ገበታዎችን እና በወርቅ ማሻሻልን ለመስማት ከሚዘጋጅ አስተሳሳቢነታችን በተመለከተ መረጃ ተወካሉ።

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

17 Nov, 15:37


ሰላም ተማሪዎች እንዴት ናቹ ቻናላችንን በአዲስ መልኩ ስራ ስለሚጀምር በተስፋ እንድትጠብቁን ስንል በትህትና ነው😊

@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

11 Oct, 07:11


ሀናን ናጂ አህመድ

በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው የክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናት።

ተማሪ ሀናን ናጂ አህመድ በተፈጥሮ ሳይንስ 649 ውጤት በማስመዝገብ ከዘንድሮ ተፈታኞች በቀዳሚነት ተቀምጣለች፡፡

ባስመዘገበችው ውጤት በጣም ደስተኛ መሆኗን የገለጸችው ተማሪ ሀናን፤ በቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደመትተጋ ተናግራለች፡፡

ክሩዝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ የሚገኝ የግል ትምህርት ቤት ነው፡፡

@temerete_mensetar

@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

10 Oct, 08:19


" ምንም አይነት የሲስተም / ቴክኒካል ችግር የለም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ውጤት በዌብሳይት eaes.et ላይ ፣ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት በ6284 ፣ በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ " ሬጅስትሬሽን ቁጥር " በማስገባት ማየት እንደሚቻል ተገልጿል።

ነገር ግን በርካታ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ውጤት ለማየት መቸገራቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

ይህ በተመለከተ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎትን አነጋግሯል።

አገልግሎቱ ፤ በውጤት መመልከቻ አማራጮቹ ላይ ምንም አይነት ቴክኒካል / የሲስተም ችግር እንደሌለ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

" በአንድ ግዜ ተማሪዎችና ወላጆችን ጨምሮ ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰው ውጤት ለማየት እየሞከረ ስለሆነ መጨናነቅ መፈጠሩን " ከፍተኛ የአገልግሎቱ አመራር ለቲክቫህ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎች በትዕግስት በመሞከር ውጤታቸውን እንዲያዩ ኃላፊው መክረዋል፡፡

@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

09 Oct, 18:08


መልእክት ለ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች !

ውድ ውጤት ጠባቂ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች እንደሚታወሰው ትምህርት ሚኒስቴር የ12ተኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ውጤት ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ ይፋ እንደሚደረግ አሳውቋል።

በዚህም ተፈታኝ ለሆናችሁ የ12ተኛ ክፍል ተማሪዎች መልካም እድልን እየተመኘን ውጤት በሚለቀቅበት ሰአት ውጤት የሚታይበት ዌብሳይት እጅጉን ስለሚጨናነቅ ጥሩ የኢንተርኔት ኮኔክሽን ...

የግዱኑ የሚጠይቅ በመሆኑ እኛ የማን ዩናይትድ ኢትዮ ፋንስ አድሚኖች ውጤታችሁን ሚስጥራችሁን በጠበቀ መልኩ አይተን ለእናንተ ለማጋራት ዝግጁ እንደሆንን ለማሳወቅ እንወዳለን ።

እናም እናንተ የቻነላችን ቤተሰቦች ይህን መልእክት 12ተኛ ክፍል ለሆኑ ወዳጅ ፣ ዘመድ ፣ ጓደኛ በማጋራት ውጤታቸውን በቶሎ እንዲያዩ ይርዷቸው ።

ውጤት ለመመልከት በ @Wakanda_Event1
መልእክት እና Id number ይላኩልን !!

SHARE

@temerete_mensetar

@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

09 Oct, 11:02


#MoE

ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈቱ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑት አንድም እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።


@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

09 Oct, 11:01


#ሙሉ_መግለጫ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናን በተመለከተ የሰጠው ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ጥዋት 12 ሰዓት ጀምሮ ማየት ይችላሉ።

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

09 Oct, 10:59


#MoE

ሚኒስትሩን ያስደናገጣቸው ቁጥር ?

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፦

" ከዚህ ፈተና አንድ #ሊያስደነግጠን የሚገባ ነገር ከተፈተኑት ጠቅላላ ተማሪዎች ውስጥ 50 ከመቶ የሚሆኑት እና ከዛ በላይ 26 ከመቶ ነው ያገኙት።

ከ845 ሺህ ፤ 422,500 ሺህ ተማሪ ከ26 በታች ነው ያገኘው። እንደው ዝም ብሎ አንድ ተማሪ ፈተናውን በግምት ቢሞላ እንኳን ሊያገኘው የሚችለው ውጤት ነው።

ለዚህ ነው ከታች ጀምሮ በደንብ አጥርተን መስራት አለብን የምንለው። "

ስለ 2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ቁጥሮች ምን ይላሉ ?

- በ2015 የተፈተኑ ተማሪዎች ብዛት 845,099 ፤ 50 በመቶና በላይ ያመጡ 27,267 ተማሪዎች (3.2%) ብቻ ናቸው።

ከነዚህ ውስጥ ፦
• ከተፈጥሮ ሳይንስ ያለፉ 19,017 ተማሪዎች
• ከማህበራዊ ሳይንስ ያለፉ 8,250 ተማሪዎች

- በማታ የተፈቱ 16,541 ያለፉ 12 ተማሪዎች ብቻ

- በግል የተፈተኑ 169,502 ያለፉ 498 ተማሪዎች ብቻ

- በመደበኛ የተፈተኑ 659,056 ያለፉ 26,757 ተማሪዎች ብቻ

- የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑ 3,106 ት/ቤቶች፤ 1,328 ትምህርት ቤቶች #አንድም_ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም / ምንም ተማሪ አላሳለፉም።

- በሀገሪቱ ካሉትና የ12ኛ ክፍል ፈተና ካስፈተኑት ትምህርት ቤቶች 42.8 በመቶ የሚሆኑን አንድ እንኳን ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

- 27 ሺህ 267 ተማሪዎች በቀጥታ ፍሬሽ ማን ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ 160 ሺህ ገደማ ተማሪ በሬሜዲያል ይገባሉ።


@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

09 Oct, 10:57


#Update

ትምህርት ሚኒስቴር ዘንድሮም የሬሜዲያል ፕሮግራም እንደሚኖር አስታወቀ።

በቀጥታ ያለፉ ተማሪዎች ውስን ስለሆኑ ዘንድሮም የሬሜዲያል ፕሮግራም ይኖራል ተብሏል።

ፕ/ር ብርሃኑ አምና የገባሁትን ቃሌን በማጠፌ ይቅርታ ብለዋል።

ሚኒስትሩ አምና የሬሜዲያል ፕሮግራም ለአንድ ጊዜ የተሰጠ እድል ብቻ እንደሆነ መግለቸው ይታወሳል።


@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

14 Jul, 06:12


ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና የአምስተኛ ቀን ፈተና እየተሰጠ ነው።

ዛሬ በጠዋት እና ከሰዓት መርሃ ግብር የአካውንቲንግ እና ፋይናንስ ትምህርት የመውጫ ፈተናዎች ይሰጣሉ።

ለመጀመሪያ ዲግሪ ዕጩ ምሩቃኖች በኦንላይን እየተሰጠ የሚገኘው የመውጫ ፈተና ነገ ሐምሌ 08/2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

ምስል፦ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ

@temerete_mensetar

@temerete_mensetar

ትምህርት ሚኒስተር🇪🇹

13 Jun, 15:23


#Update

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርስቲዎች እና ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰኔ 05/2015 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተፈርሞ የተላከ ደብዳቤ እንደሚያሳየው፤ የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ከሰኔ 26 እስከ 30/2015 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

የሬሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የተቀበሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ዝርዝር፣ ፈተናውን የሚወስዱበት ካምፓስ ማዕከልና የከተማ ሙሉ አድራሻ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀውን ፈተና የሚረክብ የተቋም ኃላፊ ወይም ባለቤት መረጃ እስከ ሰኔ 15/2015 ዓ.ም ድረስ ለትምህርትና ሥልጠና ባለሥልጣን እና በትምህርት ሚኒስቴር ለአካዳሚክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ መላክ እንዳለባቸው ደብዳቤው ያመለክታል፡፡

(የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከላይ ይመልከቱ፡፡)



@temerete_mensetar

@temerete_mensetar